Telegram Web Link
ይሄ ግፍ ነው

ደሴ እና ኮምቦልቻ ከ20 ያላነሱ የነዳጅ ማደያዎች ይገኛሉ።

ባለማደያዎቹ ቤንዚን ቀን ያወርዳሉ ሌሊት ከከተማ አስተዳደሮቹ የፀጥታና የንግድ ተቋማት ተቆጣጣሪዎች ጋር ተመሳጥረው በበርሚል ሽጠውት ያድራሉ።

ሠርቶ አደር የባጃጅና ታክሲ አገልግሎት ሰጭዎች በበርሚል ከገዙት በየሰፈሩ ለመቅዳት ተገደዋል።

ደሴ ከተማ አንድ ሰሞን ሂደቱ በከንቲባ ጽ/ቤት መመራት ጀምሮ ከተስተካከለ በኋላ ሆድ አደሮች አሸንፈው ደሃ ሰርቶ እንዳኖር እንደፈለጉ እየተጫዎቱበት ይገኛል።

ዛሬን እንዲኖር ህግ ላልተከበረለት ሰርቶ አደር ዜጋ ኮሪደር ምን ይሰራለታል? ግርም የሚለው ሁለቱም ከተሞች ለለውጥ እንተጋለን የሚሉ ከንቲባዎች አላሏቸው:አመራሩም ቢሆን ሲሮጥ ይታያል።

በማደያ 93 ብር የሆነ ቤንዚን በጀሪካን ከባዕድ ነገር ጋር 200 ብር ሲሸጥ ህግ ካላስከበራችሁ የምትሯሯጡት ለህዝብ ሳይሆን ለግል ጥቅማችሁ እንደሆነ ለመረዳት ቀላል ይሆናል ማለት ነው።

ይሄ በአይሱዙ ተጭኖ ሲንቀሳቀስ የተያዘው ቤንዚን ኮምቦልቻ ሲሆን ሲቀዳ ዝም ብለውት ከቀዳ በኋላ የጠየቁትን ገንዘብ ባለመክፈሉ የተያዘ ነው።ቢከፍል አይያዝም ነበር ተግባባን?ምን እንድናስብ ጠብቃችሁ ነበር።

ልብ በሉ ሁሉም ማደያዎች አስፓልት ላይ ይገኛሉ።አይደለም ለወንጀል አነፍናፊው ፖሊስ ለመንገደኛ ግልፅ ናቸው።

ይሄ ጉዳይ እዚህ በስም ያልጠቀስኳቸውንም ከተሞች ይመለከታል።ሐዋሳ ችግሩ የከፋ ነበር :አመራራ ተጠያቂ ሲደረግ:የተወሰኑት ሲታሰሩ ድርጊቱ ቆመ።አሁን አንፃራዊ መሻሻል አለ።

ባለቤቷን የተማመነች በግ ላቷን ውጭ አሳደረች ነው ነገሩ።ባለማደያዎች አመራሩን ሳይዙ በዚህ ልክ በህዝብ ላይ ያልተገባ ችግር አይፈጥሩም።(wasu)

@Sheger_press
@Sheger_press
#ሞተው ከሆነ እቀብራቸዋለሁ፣ ካሉም እነግራቸዋለሁ

እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ጌታችንን ታቅፋ ወደ ምድረ ግብጽ ስትሰደድ ሄሮድስ የእየሩሳሌምን 144 ሺህ ሕፃናት ፈጅቶ ጌታን እንዳላገኘው ሲያውቅ ፈልገው እንዲያመጡለት አራት ጭፍሮቹን ሰደደ፡፡ የዮሴፍ ልጅ ዮሳ በሕመም ምክንያት ከጊጋር ቀርቶ ነበርና ወሬውን ሲሰማ ምንም ህመምተኛ ቢሆን ተነስቶ መንገድ ጀመረ፡፡

ቀድመውት የሄዱትን ሽማግሌው ቅዱስ ዮሴፍ፣ ሰሎሜ፣ እመቤታችንና በሕጻናት ስርዓት የተወለድውን ጌትነት የባሕርዩ የሆነ ልጇን አግኝቶ ሊነግራቸው ይገሰግስ ጀመር፡፡ በቅድስት ቤተክርስቲያን ላይ አደጋ መደቀኑን ስንሰማ ቀድመን ለመገኘት እንጥራለን፣ ወይስ ምክንያቶች እንደረድራለን? ሕመማችን ከቤተክርስቲያን ችግር ይበልጥብናል ወይስ የቤተክርስቲያን ነገር ሆኖብን እንደ ዮሴፍ ልጅ እንደ ዮሳ ሁሉን ችለን ወደ ፊት እንገሰግሳለን?

ዮሳ ወደ ፊት ሲገሰግስ ሰይጣን ከመንገድ ሰው መስሎ ጠበቀውና “ወዴት ትሄዳለህ?” አለው፡፡ እርሱም ሄሮድስ አራት ጭፍሮቹን ሰድዶ ዘመዶቼን እያሳደዳቸው ነው አሉና ሔጄ ልነገራቸው ሲል መለሰት፡፡ ሰይጣንም እነርሱ እኮ ካለፉ ቆዩ አትደርስባቸውም፤ እስካሁን ገድለዋቸው ይሆናል ምን ያለፋሀል አለው፡፡ ዮሳ ግን “የለም ሞተው ከሆነ እቀብራቸዋለሁ፣ ካሉም እነግራቸዋለሁ” ብሎ መንገድ ሲጀምር የአንበሳ ኃይል ተሰጥቶት በፍጥነት ገስግሶ ያለውን ሁሉ ነገራቸው፡፡

እመቤታችን በሰማችው ነገር አዘነችና ልጇን ታቅፋ አለቀሰች፡፡ እርሱም እናቴ አትዘኚ ደሜ ከዕለተ አርብ ቀድሞ አይፈስም ብሎ አጽናንቷታል፡፡

ልክ እንደ ዮሳ በየትኛውም ሁኔታ ቢሆን ለቅድስት ቤተክርስቲያን ጉዳይ የምንሮጥ፣ ጌጠኛ ቤቷ እንዲለማ የምንጥር እንሁን፡፡ አሁን ላይ የአብያተ ክርስቲያናትን የእገዛ ጥሪ ሰምቶ መገስገስና የበረከት ስራ መስራት ከሁላችንም ይጠበቃል፡፡

ድጋፍ ለማድረግ :-ሙትአንሣ  ማር  ቅዱስ ሚካኤል አንድነት  ገዳም

                ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
                 1000442598391

                        ወይም

                   አቢሲኒያ ባንክ
                   141029444


ለተጨማሪ መረጃ:- 
   የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957     
                         ወይም 0938644444
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክሩ በቀጣይ በአማራ ክልል ይካሄዳል ተባለ

የኢትዮጵያ ሀገራዊ የምክክር ኮምሽን በቀጣይ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ በአማራ ክልል የተሳታፊና አጀንዳ ልየታ እንደሚያደረግ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነር ዶ/ር ዮናስ አዳዬ ለጣቢያችን ተናግረዋል።

የሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን፤ በአማራ ክልል እየተካሄደ ባለው ግጭት ምክንያት የዘገየውን የምክክር ተሳታፊዎች ልየታ በቀጣይ እንደሚያደርግ ጠቁመዋል።

ኮሚሽነሩ አዝማሚያው ለምክክር መድረክ የማይጋብዝ ከሆነም ከሌሎች ክልሎች ባገኘነው ልምድ መሰረት እንደተደረገው ተሳታፊዎችን ወደ ሌሎች ቦታዎች ወስደን የምንወያይ ይሆናል ሲሉ ተናግረዋል።
#የድንጋይ ወጋግራና የድንጋይ ምሰሶ

ተራራ የከፍታ፣ የታላቅነት፣ ቀና የማለት ምሳሌ ነው፡፡ የጽኑዕ ልብ፣ የትልቅ ራዕይ የጠንካራ ሀሳብ ማሳያ፡፡ ከመናገሻችን አዲስ አበባ በ622 ኪሎ ሜትሮች ርቀት ላይ የሚገኝ አንድ ድንቅ ሀገራዊ ሀብት የያዘ ጥንታዊ መዳረሻ ላይ ከትመናል፡፡ ጣሪያው፣ ግድግዳው፣ ወለሉ፣ ወራጅና ማገሩ፣ ምሰሶና ወጋግራው ዓለት፣ ከዓለትም የተዋበ ዓለት የሆነበትን ድንቅ የጥበብ ስራ በመንፈስ ቅዱስ ተቃኝቶ የሰራ ካሕን ወንጉስ ቅዱስ ላሊበላ፡፡ የሕንጻ አሰራር ከመሰረቱ ተጀምሮ ወደላይ የሚቆለል ሲሆን ቅዱስ ላሊበላ ግን ከጣራው ተነስቶ ወደ ታች በመፈልፈል ልዩ ጥበብ አሳይቷል። ይህም አይነት አሰራር ከሕንጻ ስራ ይልቅ ቅርጻ ቅርጽ ከመቅረጽ ጋር ይነጻጸራል።

11ዱን ውቅር አቢያተ ክርስቲያናት በ22 ዓመታት ውስጥ ሲያንጽ ከየትኛውም ሰራተኛ ክፍያ አላስቀረም፡፡ ንጉስ ነኝና ብሎ ማንንም አላስገደደም፡፡ በቤተ ማርያም ጀምሮ ድንቆቹን አብያተ ክርስቲያናት ሰርቶ ሲያጢናቅቅ ኢየሩሳሌምን ለመሳለም በእግራቸው በረሀውን አቋርጠው የሚሔዱ ኢትዮጵያውያን ኢየሩሳሌምን እዚሁ ሀገራቸው ላይ እንዲያገኙ በማድረጉ አምላኩን አመሰገነ፡፡ ለዚያም ነው በኢየሩሳሌም የሚገኙትን ማየ ዮርዳኖስና የአዳም መቃብር ሳይቀር በሕንጻዎቹ ውስጥ ያካተተው፡፡ ድንቅ ስራውን አይተው ካደነቁ የውጪ ሀገራት ዜጎች አንዱ ፍራንሲስኮ አልቫሬዝ የተባለው ፖርቹጋላዊ የካቶሊክ ቄስ ይገኝበታል፡፡

አልቫሬዝ በላሊበላ ያየውን ሁሉ ከጻፈ በኋላ ሲያጠቃልል እንዲህ ይላል፣ “እዚህ መጥቼ ያየሁትን ሁሉ ብጽፍ ማንም አያምነኝም፤ እናም ያየሁትን ሁሉ አልጻፍኩላችሁም፡፡ ምናልባትም ይህን የጻፍኩትን ራሱ አታምኑኝ ይሆናል፤ ነገር ግን በልዑል እግዚአብሔር ስም እምላለሁ የጻፍኩላችሁ እውነት ነው፡፡ በግራኝ መሀመድ ወረራ ጊዜም አካባቢው ላይ የደረሰው ይህ ጦረኛ ሰው ፍልፍልና ውቅር አብያተ ክርሳቲናት ሲመለከት እጅግ መደመሙን የታሪክ መዛግብት ያስነብባሉ፡፡ ግራኝ መሐመድ ያየውን ከአእምሮ በላይ የሆነ ስራ በማድነቅ በፍጹም ሳይነካው እንደሔደ አብረውት የነበሩት የጦር አበጋዞቹና ጀሌዎቹ ጽፈዋል፡፡  

በዩኔስኮ የዓለም ህዝብ ቅርስ ተብሎ የተመዘገበውን ይህንን ድንቅ የእግዚአብሔር ቸርነት የቅዱስ ላሊበላ ክብር መገለጫ መሳለም ኢየሩሳሌምን መሳለም ነው፡፡ የትኛውም ኢትዮጵያዊ በሕይወቱ ቢያንስ አንድ ጊዜ ውቅር አብያተ ክርስቲናቱን መጎብኘትም አለበት፡፡ በተለይ ከጌታ ልደት ጋር በሚከበረው የቅዱሱ ንጉስ የልደት ቀ29 ታሕሳስ 29 ላልይበላ መገኘት፣ የድንጋይ ወጋግራውንና የድንጋይ ምሰሶውን ለማየት ልዩ አጋጣሚ ነው፡፡

የቅዱሱ ንጉስ የመጀመሪያ ስራ በሆነችው ቤተ ማርያም ዙሪያ በሚገኘው ማሜ ጋራ አባቶች ሊቃውንት “ቤዛ ኩሉ ዓለም ዮም ተወልደ” የሚለውን ዝማሬ ልብን በሚመስጥ፣ ዜማ ሲያቀርቡ በዚያ መሆን መልካም ነው፡፡ የቅዳሴውን ልዩ ዜማና ምስጢር፣ የሌሊቱን ማሕሌት መታደም፣ በመላዕክት ዝማሬ ካሕናት ሲያሸበሽቡ መመልከት፣ ልደትን በኢየሩሳሌም የማክበር ያህል ድንቅ በረከት አለው፡፡ መንፈሳዊውን ነገር ብቻ እያሰቡ በዓሉን እንዲያሳልፉ ልዩ መንፈሳዊ ጉዞ ተዘጋጅቷል፡፡   

ለአረጋውያን፣  ለነፍሰጡሮች፣ ለህፃናትና ለአካል ጉዳተኞች በጤና ባለሙያዎች ልዩ እንክባቤ እንሰጣለን። ምቹ ማረፊያም አዘጋጅተናል፤ ያሉን ቦታዎች ውስን ናቸውና ፈጥነው በመመዝገብ ቦታ ይያዙ።

የጉዞ መነሻ ቀን:- 24/04/17 ዓ.ም

የጉዞ መመለሻ ቀን:- 02/05/17 ዓ.ም

የጉዞ ዋጋ ምግብን ፣ ማረፊያንና መስተንግዶን ጨምሮ :-6,500

ለበለጠ መረጃ:-0938944444

አዘጋጅ:- ማህበረ ቁስቋም
በባህርዳር ከተማ ልዩ መለያ (ባር ኮድ) ያላደረጉ ባጃጆች አገልግሎት እንዳይሰጡ ተከለከለ

በአማራ ክልል ርዕሰ ከተማ ባህር ዳር አገልገሎት የሚሰጡ ባጃጆች ከዛሬ ጀምሮ “ልዩ መለያ (ባር ኮድ) እንዲኖራቸው” የሚያዝ አስገዳጅ መመሪያ ተግባራዊ መደረጉ ተገለጸ።

በባህር ዳር ከተማ ከታኅሣሥ 7 ቀን ጀምሮ በማህበር ሳይደራጁ እና መለያ (ባር ኮድ) ያላደረጉ ባጃጆች አገልግሎት አይሰጡም” ሲሉ የከተማዋ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ጎሹ እንዳላማው ማስታወቃቸውን አሚኮ ዘግቧል።

“በባህር ዳር ከፍተኛ ቁጥር ያለውን ባጃጅ ሕጋዊ ኾኖ ሕዝብን እንዲያገለግል በመለያ ቁጥር (ባር ኮድ) መቆጣጠር አስፈላጊ ሆኗል፣ ባጃጆችን ተጠቅሞ ሕገ ወጥ ተግባር እንዳይከናወንም መለያው ተግባር ላይ ውሏል” ሲሉ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባው መገለጻቸውን መረጃው አካቷል።
በምስራቅ ቦረና ዞን የሰላም ጥሪውን የተቀበሉ ታጣቂዎች ወደ ካምፕ እየገቡ ነው

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ቦረና ዞን የቀረበውን የሰላም ጥሪ የተቀበሉ የኦነግ ታጣቂዎች ወደ ካምፕ እየገቡ ነው።

በአካባቢው ሲንቀሳቀሱ የነበሩ የኦነግ ታጣቂዎች ለቀረበው የሰላም ጥሪ ምላሽ በመስጠት ወደ ካምፕ በመግባት ላይ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

ታጣቂዎቹ በነጌሌ ቦረና ከተማ አቀባበል እንደተደረገላቸውም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል።

በኦሮሚያ ክልል መንግስትና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት መካከል የሰላም ስምምነት መፈረሙ የሚታወስ ሲሆን ይህን ተከትሎም በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ይንቀሳቀሱ የነበሩ ታጣቂዎች ወደ ካምፕ እየገቡ እንደሚገኙ ተጠቁሟል፡፡

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
ተቃዋሚዎቹ የትግራይ ነጻነት ፓርቲ፣ ባይቶና እና ዓረና ፓርቲ፣ ሕወሓት አዳዲስ ተዋጊዎችን በመመልመልና ነባሮችን በመቀስቀስ ለዳግም ጦርነት እየተዘጋጀ ነው በማለት ትናንት በሰጡት መግለጫ ከሰዋል። ፓርቲዎቹ፣ ሕወሓት በክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች በሕዝብ ተመራጭ ሹሞች ላይ ማስፈራሪያ እየፈጸመ ይገኛል በማለትም ወንጅለዋል።

የትግራይ የፖለቲካና የጸጥታ ኃይል አመራሮች በሰሜን ምዕራብና ማዕከላዊ ዞኖች በመርዛማ ኬሚካሎች በመታገዝ ከፍተኛ የወርቅ ማዕድን ዝርፊያ እያካሄዱና የአካባቢ ብክለት እያደረሱ እንደኾነም ፓርቲዎቹ ገልጸዋል።

ፓርቲዎቹ፣ የክልሉን ችግር ለመቅረፍ ኹሉን አካታች የሽግግር አስተዳደር እንዲቋቋም በድጋሚ ጠይቀዋል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
በቅናት በመነሳሳት ባለቤታቸውን እና የባለቤታቸው እህት የገደሉት የ73 ዓመት አዛውንት በእድሜ ልክ እስራት ተቀጡ 

የ73 ዓመት አዛውንት የሆኑት አቶ አህመድ  አደም እና ፋጡማ አህመድ ነዋሪነታቸው በምስራቅ ሀረርጌ ዞን በደኖ ወረዳ ሞጆ ቀበሌ ውስጥ ሲሆን ጥንዶቹ ትዳር  መስርተው ለ35 ዓመታት አብረው በመኖር  አምስት ልጆችን ማፍራት ችለዋል። 

ሁለቱ ጥንዶች  አብረው መኖር በጀመሩባቸው ዓመታት ከዘመዶቻቸው ጋር ተስማምተው  ተከባብረው  ይኖሩ ነበር። ይሁን እና እድሜያቸውን ሙሉ ከኖሩበት ትዳራቸው ላይ የሚያቃርናቸው ነገር ይፈጠራል። የ73  ዓመቱ አደም በባለቤታቸው ላይ መቅናት የጀመሩበት እና በዚህም ያልተገባ ጥርጣሬ እያደረባቸው  በመሆኑ  በተደጋጋሚ  መጋጨት መጀመራቸው  የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሳሊም ሱሌማን በተለይም ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

በዚህ ጥርጣሬያቸው የወይዘሮ ፋጡማ ዘመዶች በመጥላት እቤታቸው እንዳይመጡ መከላከል ጀምሯል። የባለቤታቸው ታናሽ እህት የሆነችው ሂንድያ አህመድ  ባለቤቴን ይዛ የምትዞረው እሷ ናት በሚል ጥርጣሬ   ቅራኔ ውስጥ መግባታቸው ተጠቁሟል። ሚያዝያ  9 ቀን 2016 ዓ.ም  ወይዘሮ ፋጡማ  እና ሂንድያ አብረው ቆይተው ወደየቤታቸው ሲገቡ አቶ አህመድ ንዴት ውስጥ በመግባታቸው ወዲያውኑ ጸብ ይጀምራሉ  ። ከዛም በያዙት ስለታም ብረት  በመምታት ከጣሏቸው በኋላ እጃቸውን ከቤት ምሰሶ ጋር በማሰር  እርዳታ  እንዳያገኙ መብራት በማጣፋት  ከውጪ  በር ዘግተው የተጎጂ ታናሽ እህት ጋር በመሄድ እህትሽ ታማለች ጤና ጣቢያ እንውሰዳት በማለት አታለው  ወደራሳቸው ቤት ያመጧታል።

በተመሳሳይ እህቷን በስለታም ብረት መተው በመጣል ሁለቱንም አስረው በተደጋጋሚ በመምታት ህይወታቸው እንዲያልፍ አድርገዋል።ተከሳሹ ድርጊቱን ከፈጸሙ በኋላ ከአካባቢው ለመሰወር የሞከሩ ሲሆን  ነዋሪዎች በመጠራጠር ለአካባቢው የጸጥታ አካላት  በማመልከት ፖሊስ በሩን ከፍቶ ሲገባ ታላቅ እና ታናሽ ሁለቱም ህይወታቸው አልፎ በማግኘቱ ወዲያውኑ ጉዳዩን ማጣራት መጀመሩ ተገልጿል ።ፖሊስም አስከሬኑን በማስመርመር እና ጉዳዩን በማጣራት ላይ እያሉ የ73 ዓመቱ  ግለሰብ እጃቸውን ለፖሊስ  በመስጠት ቃላቸው ይሰጣሉ ።ፖሊስ መዝገቡን ሚያዚያ 30 ቀን 2016 ዓ.ም ለዓቃቢ ህግ  ይልካል  ። ከፖሊስ የቀረበለትን የክስ መዝገብ የተመለከተው ዓቃቢህግ በሁለት ሰዎች ከባድ የግድያ ወንጀል በመፈጸም በሚል ክስ ይመሰርታል።

የምርመራ መዝገቡን የተመለከተው  የምስራቅ  ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት  ህዳር 26  ቀን 2017 ዓ.ም  በዋለው ችሎት የ73 ዓመት ግለሰብ የወንጀል ሪከርድ የሌለባቸው በመሆኑ እና አድሚያቸው እንደ ክስ ማቅለያ በማድረግ በመጨረሻም  ዓቃቢ ህግ ከጠየቀው  የሞት ቅጣት አንድ ደረጃ ዝቅ በማድረግ በእድሜ ልክ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ የተላለፈባቸው መሆኑን አቶ ሳሊም ሱሌማን ጨምረው ለብስራት  ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን  ተናግረዋል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
በቃሊቲ ማረሚያ ቤት ይኖሩ የነበሩ የህግ ታራሚዎች ገላን አካባቢ ወደ ተገነባው አዲስ ማረሚያ ቤት ሊዘዋወሩ ነው፡፡

በዚህ ምክንያት ከዛሬ ታህሳስ 8 ቀን 2017 ዓ.ም እስከ ታህሳስ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ደረስ የታራሚ ቤተሰብ ጥየቃም ሆነ የቢሮ አገልግሎት እንደማይኑር የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን አሳውቋል፡፡

የፌዴራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን ሁሉም እንዲያወቀው ሲል በማህበራዊ ትስስር ገጹ ባሰራጨው መረጃ በአዲስ አበባ የህግ ታራሚዎች ቀደም ብለው ይኖሩበት ከነበረው አሮጌው የቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል አዲስ ወደ ተገነባው ገላን አካባቢ ወደ ሚገኘው እና በተለምዶ አባ ሳሙኤል ተብሎ በሚጠራው የቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል ከታህሳስ 8 እስከ 13 ቀን 2017 ዓ.ም የማዘዋወር ስራ ይሰራል ብሏል፡፡

በመሆኑም በአዲስ አበባ ቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል ይሰጥ የነበረውን የታራሚ ቤተሰብ ጥየቃም ሆነ የቢሮ ስራ አገልግሎት ከታህሳስ 8 እስከ 13 ቀን 2017 ዓ.ም ድረስ ተቋርጦ እንደሚቁይ አሳውቋል፡፡

ከዛሬ ታህሳስ 8 ቀን 2017 .ም ጀምሮ የሚቋረጠው አገልግሎት ከታህሳስ 14 ቀን 2017 ዓ.ም ወደ መደበኛ ስራው የሚመለስ በመሆኑ አገልግሎቱ በአዲሱ የቃሊቲ ማረሚያ ማዕከል ገላን አካባቢ በተለምዶ አባ ሳሙኤል ተብሎ በሚጠራው ማዕከል ማግኘት የሚቻል መሆኑን ገልጻል፡፡

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
🙏🙏🙏❤️❤️❤️

እነሆ የገና ስጦታ

ከተወዳጁ ዘማሪ ዲያቆን አቤል መክብብ
እዲስ የዝማሬ አልበም

‘’በኃጢአተኛው ድንኳን ቅዱሱ ቆመሃል
ልጄ የት ነው ብለህ እኔን ፈልገኻል’’ በሚለው ዝማሬው የሁላችንንም ሕይወት የዳሰሰው…

አጋጣሚ አይደለም: ምልክቴ ነሽ ድንግል ለሕይወቴ፣ ማርያም ማርያም ልበል:
ይለይብኛል ሚካኤል፣ ምስጠረኛዬ ነሽ …..

ቀኑ ቀርቧልና በትዕግስት ጠብቁ‼️
“የውጭ ባንኮች ወደ ሃገር ውስጥ እንዲገቡ መፍቀድ  የግል ባንኮች ይጥፉ ብሎ የመወሰን ያክል አይደለም ወይ” የምክር ቤቱ አባል ደሳለኝ ጫኔ (ዶ/ር)

#የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የባንክ ስራ ረቂቅ አዋጅን አስመልክቶ  እያደረገ ያለው ውይይት አሁንም እንደቀጠለ ነው፡፡

“የንግድ ባንክን አዳ ወደ ህዘቡ ሲዞር ይህንን ታስቦ ነው” ያሉት የመንክር ቤቱ አባል ለግል ባንኮች ግን አቅማቸውን እንዲያደረጁ እንኳን ድጋፍ አልተደረገላቸውም  ተብሏል፡፡

ዶ /ር ደሳለኝ የውጭ ባንኮችን ወደ ሃገር ውስጥ ማስገባት ”የግሉ ባንከ  ይጥፉ ብሎ እንደማሰብ አይቆጠርም ወይ”  ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

የውጭ ባንኮች ወደ ሃገር ውስጥ መፈቀዱ አገልግሎቱን ከማሻሻል እና ካፒታል ከማምጣት ጥቅም ቢኖረውም የዝግጅት ማነስ ግን አንዱ ችግር ነው ብለዋል፡፡

በተለየም ሃገር ውስጥ የግል ባንኮች አጭር እድሜ ያስቆጠሩ ናቸው የሚሉት የምክር ቤቱ አባል ለአብነትም ብለው አማራ ባንከ፤ ስንቄ ባንክ እንዲሁም አሃዱን ባንክ አንስተዋል፡፡

በእንዚህ ባንኮች ውስጥ ደግሞ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ አክሲዎኖች በስራቸው እንዳሉ አንስተው  ጉዳዩ አሳሳቢ ነው ብለዋል፡፡

የምክር ቤቱ አባል ከዚህ ባለፈም በምን መልኩስ እንቆጣጠራቸዋልን ሲሉም ጠይቀዋል፡፡

ዶ/ር ደሳለኝ አያይዘውም የውጭ ባንኮች ምን አልባት ቢገቡ ሊያበድሩ የሚችሉት ከፍተኛ አቅም ላላቸው በመሆኑ ይህ ደግሞ አነስተና ገቢ ያላቸው እና ብድር የሚፈልጉትን እንደሚጎዳም ተናግረዋል፡፡›

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
በሰዓት 130 ዶላር የሚከፈልበት የጀርባ ማከክ ስራ

ሴት ጀርባ አካኪዎችን የያዘው የዓለም የመጀሪያው የጀርባ ማከክ ቴራፒ ስቱዲዮም አገልግሎት እየሰጠ ነው።

በሰዓት 130 የአሜሪካ ዶላር ወይም 16 ሺህ ብር በመክፈል ጀርባ ማሳከክ ይቻላል ይላል ከሰሞኑ ከወደ አሜሪካ የተሰማ ዜና።

በሰዎች ዘንድ ስራ ይሆናል ተብለው የማይታሰቡ ተግራት በተለያዩ ጊዜያት ወደ ስራ ተቀይረው ለሰዎች መተዳደሪያ ገቢ ሲያስገኙ ይሰማል።

ከእነዚህም ውስጥ ለመታቀፍ ወፍራም ሰዎችን በሰዓት ከመከራየት ጀምሮ ተከፍሏቸው አልጋ እስከሚያሞቁ ሰዎች ድረስ ገቢ የሚያስገኙ ያተለመዱ ስራዎች መካከል ተጠቃሽ ናቸው።

ከሰሞኑ ከወደ አሜሪካ የተሰማው ወሬ ደግሞ ባለሙያ ሴቶች የሰዎች ጀርባ በማከክ በሰዓት 130 ዶላር ወይም 16 ሺህ ብር እያገኙ ነው ይለናል።

በዓለማችን የመጀመሪያው ፕሮፌሽናል ጀርባ የማከክ አገልግሎት በ55 ዓመቷ ቶኒ ጆርጅ የተመሰረተ ሲሆን፤ ሙሉ በሙሉ ሴት አካኪዎችን የያዘው የዓለም የመጀሪያው የጀርባ ማከክ ቴራፒ ስቱዲዮም አገልግሎእ እየሰጠ ነው ተብሏል።

ቶኒ ጆርጅ ስራውን እንዴት እንደጀመረች ስትናገርም “ጀርዬን ሲታከክልኝ በጣም ነው የሚያሰደስተኝ፤ ይህ ነገር ሌሎች ሰዎች እንደሚያሰደስት በመረዳት ወደ ስራ ለመቀየር ወሰንኩ” ትላለች።

የሰዎችን ጀርባ ለማከክ እስከ 3 ኢንች የሚረዝም አርቴፊሻል ጥፈር እንደምትጠቀም የተናገረቸው ጆርጅ፤ የሰዎችን ጀርባ ስታክ በሰዓት እስከ 130 ዶላር እንደምታስከፍል ተናግራለች።

ፕሮፌሽናል ጀርባ አካኪ ሴቶች፤ የደንኛቸውን ጀርባ በጥፍራቸው ጫፍ በቀስታ ከላይ እከ ታች የሚያኩ ሲሆን፤ ይህም ደንበኞቻቸው የጭንቀት ስሜት እንዲለቃቸው በማድረግ ዘና እንዲሉ ይረዳቸዋል ተብሏል።

ቶኒ ጆርጅ ስለ አዲሱ ስራዋ ስትናገርም “በሰዎች ዘንድ ያለው ተቀባይነት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል” ብላለች።

ቶኒ ከጀርባ አከካ ባለሙያዎቿ ጋር በመሆን ከደንበኞች በሚቀርብላት ጥሪ መሰረት አገልግሎት ለመስጠት እንደ ኒው ዮርክ፣ ሎስ አንጀለስ እና ፊላዴልፊያ ያሉ ትላልቅ የአሜሪካ ከተሞች እንደመትሄድም ተናግራለች።

አል አይን ነው የዘገበው።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
2024/12/27 08:26:18
Back to Top
HTML Embed Code: