Telegram Web Link
ጎንደር

ለህፃን ኖላዊት ዘገዬ ቤተሰቦች የመኖሪያ ቤት ተሰጠ

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባን አቶ ቻላቸው ዳኘውና ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎች የህፃን ኖላዊትን አባት አቶ ዘገዬ ወልዴን በመስሪያ ቤታቸው አነጋግረዋል።

በዕለቱ የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኛው ከህፃኗ ቤተሰቦች ጎን መሆናቸውን ገልፀዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራር ለህፃኗ ቤተሰቦች የደረሰባቸውን ጉዳት ታሳቢ በማድረግ የመኖሪያ ቤት እንዲሰጣቸው መወሰኑን ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ገልፀዋል።

የህፃን ኖላዊት አባት አቶ ዘገዬ ውልዴ ደግሞ የከተማ አስተዳደሩ እያደረገላቸው ላለው ድጋፍና ትብብር ምስጋና አቅርበዋል። የከተማ አስተዳደሩ የህፃኗ አጋቾች በህግ እስኪቀርቡ ድረስ ድጋፉን እንዳይለያቸው ጠይቀዋል ሲል የዘገበው የጎንደር ከተማ ኮሙኒኬሽን ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የገቡበትን ውጥረት ለመፍታት ለሶስተኛ ጊዜ ውይይት ለማድረግ በቱርክ አንካራ ከ10 ቀናት በኋላ(September 17/2024/ እንደሚጀምሩ ተሰምቷል።

ይህ እንዳለ ሆኖ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ እንዲሁም የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሰሞኑን ቻይና በነበሩበት ወቅት ውጥረቱን ለማርገብ የናይጄሪያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት እና የሰሜኑ ጦርነት በሰላም እንዲቋጭ አደራዳሪ የነበሩት ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ እና የጅቡቲው ፕሬዚዳንት ሁለቱን መሪዎች ለማደራደር እና ለማገናኘት ሞክረው የነበረ ቢሆንም የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድ አሻፈረኝ ማለታቸው ታውቋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በበ18-6-58-16_New_compressed.pdf
14.9 MB
👆👆አዲሱ የደመወዝ ጭማሪ እንደጠበቅነዉ አይደለም ያሉ የተለያዩ የመንግስት ስራተኞች ጥናቱ በሚኒስትሮች ምክር-ቤት ቀርቦ ከመፅደቁ በፊት በድጋሚ መታየት እንዳለበት ተናገሩ‼️

ከመስከረም 1 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው አዲሱ የደመወዝ ማሻሻያ ጥናት: የሚኒስትሮች ምክር-ቤት ከማፅደቁ አስቀድሞ ሰራተኞችን ማወያየት እንዳለበት እና በድጋሚ መታየት እንደሚኖርበት ተጠይቋል።

ካፒታል ያነጋገራቸው ሠራተኞች እንደገለፁት የደመወዝ ማሻሻያው አሁን ያሉበትን የኑሮ ሁኔታ እንደተባለውም ከግምት ያላስገባና እንደጠበቁት እንዳልሆነ አስረድተዋል።

''ስለደመወዝ ማሻሻያው ጠ/ሚኒስትሩ  በተናገሩበት ሰዓት እጅግ በጣም ጠብቄ ነበር ነገር ግን አሁን ከዛ የተለየ ነገር ነው የሆነው'' ሲሉ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አዲስ አበባ ውስጥ በአንድ የመንግስት ትምህርት ቤት የሚያስተምሩ መምህር ለካፒታል ተናግረዋል።

የደመወዝ ማሻሻያ ይደረጋል መባሉን ተከትሎ ከመኖሪያ ቤት ኪራይ ጀምሮ ከምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ እቃዎችን ጨምሮ የዋጋው ንረቱ በእጥፍ እንደጨመረ ሠራተኞቹ ለካፒታል ያቀረቡት ቅሬታ ያመላክታል።

ይህ እንኳን ተፈፃሚ ይሁን ከተባለ የስራ ግብር እንዲቀነስ መደረግ አለበት በማለት ተናግረዋል ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የደመወዝ ጭማሪን በሚመለከት ከክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ከፌደራል መንግስት ባለስልጣናት እና ከግል ባንኮች ፕሬዝዳንቶች ጋር በተደረገ ውይይት ላይ እንደተናገሩት " በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የመንግስት ሰራተኞች የሚደረገው የደመወዝ ጭማሪ “በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ አይታወቅም” ብለዋል።

በአዲሱ እርከን ከተካተቱት የመንግስት ሰራተኞች ዉስጥ የጤና ባለሞያዎች ይገኙበታል። ካፒታል ያነጋገራቸዉ እነዚህ ባለሞያዎች እንደሚሉት " ቀድሞ የመሰለን ጭማሪዉ በአንድ ጊዜ እስከ 10 ሺህ ብር የሚያህል ገንዘብ ቢሆንም በተቃራኒው የሆነዉ ግን ያሳዝናል ።

አሁን ላይ ከ 1500 ብር በታች ነዉ የተጨመረዉ ይህ ደግሞ ተመልሶ በስራ ግብር የሚቀነስ መሆኑ የተደረገዉ ጭማሪ ሳይሆን ተስፋ ብቻ ነዉ በማለት ቅሬታዎች አቅርበዋል።

የደሞዝ ጭማሪ መኖሩን መንግስት መናገሩን ተከትሎ በማግስቱ  የሁሉም ነገር ዋጋ በሁለት እጥፍ ጨምሯል።

በዚህም ሰራተኛዉም ሆነ በዝቅተኛ ኑሮ ላይ የነበሩት ሰዎች ምንም የተሰጣቸዉ ነገር ሳይኖርና ጭማሪ እጃቸዉ ሳይገባ የኑሮ ዉድነቱ ተባብሶ ቀጥሏል ሲሉም ሁኔታዉን በምሬት ገልፀዉታል።

ከመስከረም 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ለዉሳኔ የቀረበዉ እና በገንዘብ ሚኒስትር እንዲሁም በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አማካኝነት ጥናት ተደርጎበታል የተባለው ይህ የሠራተኞች የኑሮ ውድነት ጫና መደጎሚያ ደመወዝ ማሻሻያ ረቂቅ ለሚኒስትሮች ምክርቤት በቀን 28 /12/ 2016 ዓ.መቅረቡን ነው ለማወቅ የተቻለው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ማስታወሻ ‼️

እንደሚታወቀው ዛሬ የ12ኛ ክፍል ውጤት ይፋ ይደረጋል።

ለተፈታኞቾ በሙሉ ከወዲሁ መልካም ዕድል እንመኛለን።

ከዚ ጋር በተያያዘ አስቸጋሪ ኔትወርክ ውስጥ የምትገኙ ተማሪዎች።

ውጤት ይፋ እንደተደረገ በቻልነው መጠን ውጤት ልናስመለክታቹ በዝግጅት ላይ እንገኛለን።

በዚ ቻናል ውጤት እናሳያለን አሁንኑ ተቀላቅላቹ ጠብቁን👇👇

Join us 👇👇
https://www.tg-me.com/+XUeXEA4uaCM3YmVk
https://www.tg-me.com/+XUeXEA4uaCM3YmVk
https://www.tg-me.com/+XUeXEA4uaCM3YmVk
ከውጤቱ መለቀቅ አስቀድሞ ዛሬ የትምህርት ሚንስትር የፈተናው ውጤት አሰመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ውጤት እንደተለቀቀ የምናሳውቃቹ ሲሆን ውጤት ማያ ሊንኮችንም አያይዘን ወደረ እናንተ እናደርሳለን።

በድጋሚ መልካም ዕድል

በዚ ቻናል ውጤት እናሳያለን አሁንኑ ተቀላቅላቹ ጠብቁን👇👇

Join us 👇👇
https://www.tg-me.com/+XUeXEA4uaCM3YmVk
https://www.tg-me.com/+XUeXEA4uaCM3YmVk
https://www.tg-me.com/+XUeXEA4uaCM3YmVk
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዕለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን

Dollar 119.ብር

@sheger_crypto_tech
@sheger_crypto_tech
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ውጤትን በተመለከተ ትምህርት ሚኒስቴር በአሁኑ ሰዓት ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጠ ይገኛል።

መልካም እድል ❤️

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የትምህርት ሚኒስትሩ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት

ለሊት 6 ሰዓት ላይ ይፋ ይደረጋል ብለዋል።

@sheger_press
@sheger_press
#Update

የዘንድሮው ውጤት ከአምና ካቻምናዎቹ የተሻለ ነው ሲሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ተናግረዋል።

ሚኒስትሩ አማካኝ ውጤቱ 29.7 ነው ብለዋል።

@sheger_press
@sheger_press
የወንዶች አማካይ ውጤት - 30.66

የሴቶች አማካይ ውጤት - 28

አዳሪ ትምህርት ቤቶች ዘንድሮም ከፍተኛ ውጤት አስመዝግበዋል።

@sheger_press
@sheger_press
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናውን ከወሰዱት ተማሪዎች 5.4% ብቻ ማለፋቸውን ትምህርት ሚኒስቴር ይፋ አድርጓል ።

ዘንድሮ ብሔራዊ ፈተና ከተፈተኑት ተማሪዎች 36,409 ተማሪዎች ናቸው ያለፉት።

አዲስ አበባ 10,690 ተማሪዎች በማሳለፍ ከፍተኛውን ስፍራ ይዟል።

አዲስ አበባ ካስፈተናቸው ተማሪዎች 21.4 በመቶ አሳልፏል።

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ከፍተኛ ውጤት ይፋ ሆኗል

የትግራይ ክልል 675 ከ 700  ወንድ

ከፍተኛ ውጤት በናቹራል ሳይንስ ተማሪ 575 ሴት

ከፍተኛ ውጤት በሶሻል ተማሪ 538 ሴት

@sheger_press
@sheger_press
684ሺህ 405 ተማሪዎች 36 ሺህ 409 ተማሪዎች አልፈዋል ፤

በአጠቃላይ 1363 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ አላሳለፉም ! 😔

ይህን እያዩ የወደፊቷ ኢትዮጵያ ምን እንደሚገጥማት ማሰብ እጅግ በጣም ከባድ ነው።

@sheger_press
@sheger_press
ከፍተኛ ውጤት የተመዘገበው ከትግራይ ክልል መሆኑ መግለፃችን ይታወሳል።

እውነት ለመናገር ከጦርነት ማግስት ከትምህርት ለረጅም ጊዜ ተርቆ ከፍተኛ ነጥብ ከኢትዮጵያ ማስመዝገብ በውነት በጣም የሚያስደንቅ ውጤት ነው።

@sheger_press
@sheger_press
ግብጽ በተደጋጋሚ የምታቀርባቸው ዛቻዎች እና አቤቱታዎች “መሠረተ-ቢሶች” ናቸው ስትል እንደማትቀበለው ኢትዮጵያ አስታወቀች!

ኢትዮጵያ ግብጽ በተደጋጋሚ የምታቀርባቸው ዛቻዎች እና አቤቱታዎች “መሠረተ-ቢሶች” ናቸው ስትል እንደማትቀበለው ለጸጥታው ምክር ቤት በጻፈችው ደብዳቤ አስታወቀች፤ የመንግስታቱ ድርጅትን ቻርተር በሚጻረር መልኩ እየሰነዘረችብኝ ያለችውን ተደጋጋሚ ዛቻ ምክር ቤቱ እንዲያጤንልኝ ስትል አሳስባለች።

አዲስ ስታንዳርድ የተመለከተው እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ፊርማ ያረፈበት ይህ ደብዳቤ እንደሚያሳየው “ኢትዮጵያ በፍትሐዊ የናይል ወንዝ አጠቃቀም ላይ ያላትን ቁርጠኝነት ገልፆ ግብጽ የአባይ ውሃን በብቸኝነት የመጠቀም ፍላጎቷን” ኮንኗል።

ኢትዮጵያ ለጸጥታው ምክር ቤት በላከችው በዚህ ደብዳቤ በቅርቡ የግብጹ ጠቅላይ ሚንስትር “በየትኛውም አገር የሚከናወን የልማት ፕሮጀክት: ግብጽ በናይል ወንዝ ላይ ያላትን ታሪካዊ ድርሻ በማይቀንስ ሁኔታ መካሄድ አለበት” ሲሉ መናገራቸው ጠቅሳ “ግብፅ አሁንም በቅኝ-ግዛት ህጎች እና አስተሳሰቦች በመመርኮዝ በአባይ ውሃ ላይ በብቸኝነት የመጠቀም ፍላጎቷን ያንጸባረቀ ነው” ስትል ኮንናለች።

በተጨማሪ ደብዳቤው ግብጽ “አዋጭነታቸው ያልተረጋገጡ” የልማት ፕሮጀክቶችን የወንዙን ተፋሰስ ሀገራት ሳታሳውቅ ስትገነባ መቆየቷን ኢትዮጵያ ስታሳውቅ እንደነበረ አስታውሶ: ይህም የሌሎቹን የተፋሰስ ሃገራት ጥቅም እና ፍላጎት ያገለለ መሆኑን አመላክቷል።

@sheger_press
@sheger_press
እንደሚታወቀው ለሊት ስድስት ሰዓት ዉጤት ማየት ይጀመራል።

እናም በተለያየ ምክንያት ውጤት ማየት የማትችሉ ተፈታኝ ቤተሰቦቻችን በተቻለን አቅም በማየት እናግዛለን

ውጤት ሲለቀቅ በዚ ቻናል እናሳያለን አሁንኑ ተቀላቅላቹ ጠብቁን👇👇

Join us 👇👇
https://www.tg-me.com/+XUeXEA4uaCM3YmVk
https://www.tg-me.com/+XUeXEA4uaCM3YmVk
https://www.tg-me.com/+XUeXEA4uaCM3YmVk
🚨 ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ:

"ሪሜዲያል ዘንድሮም አለ ነገርግን መጠኑን እንቀንሳለን ፤ በየአመቱ መጠኑ እየቀነሰ ነው የሚሄደው።"

@sheger_press
@sheger_press
ውጤት ማያ አማራጮች

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ተፈታኞች ውጤታቸውን ከዛሬ ጳጉሜን 4/2016 ዓ.ም ለሊት 6:00 ጀምሮ ማየት እንደሚችሉ መገለፁ ይታወቃል።

በሚከተሉት አማራጮች ውጤታችሁን ተመልከቱ፦

በፖርታል 👉 https://result.eaes.et

በአጭር የፅሑፍ መልዕክት 👉 6284

በቴሌግራም ቦት 👉 https://www.tg-me.com/EAESbot

ከውጤት መግለጫ ፖርታል እና ቴሌግራም ቦት ላይ ጊዜያዊ ሰርቲፊኬት ማውረድና ማተም እንደምትችሉ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

ተፈታኞች በውጤት እና ተያያዥ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ቅሬታ ካላቸው ወደ አገልግሎቱ ቢሮ በአካል መሔድ ሳያስፈልጋችሁ ከSMS በስተቀር በውጤት መግለጫ አማራጮቹ ላይ Compliant የሚለውን በመጫን የቅሬታቸውን ዓይነት በተዘጋጀ የቅሬታ ፎርም ላይ በትክክል በመሙላት ማቅረብ ትችላላችሁ።

አገልግሎቱ በቅሬታችሁ ላይ ምላሽ ቅሬታቸውን ባቀረቡበት ተመሳሳይ አድራሻ የሚያሳውቅ መሆኑን ገልጿል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/10/02 20:43:06
Back to Top
HTML Embed Code: