Telegram Web Link
ደብረጺዮን ገ/ሚካዔል የሚመሩት የሕወሓት ቡድን የፕሪቶሪያውን የግጭት ማቆም ስምምነት ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ከፌደራሉ መንግሥት ጋር ለመስራት ተቸግሬያለሁ ሲል ትናንት ማምሻውን በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ አስታውቋል።

ባሁኑ ወቅት ያለው ዋናው ልዩነት፣ በፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነት አፈጻጸም ዙሪያ የሚያጠነጥን እንደኾነ ሕወሓት ገልጧል።

በፌደራል መንግሥቱ ዘንድ የሚታየው አካሄድ፣ ትግራይን የመከፋፈል ወይም ወደተመቸው አቅጣጫ የመውሰድ ሁኔታ ነው በማለት ሕወሓት ከሷል።

ሕወሓት፣ በትግራይ እና አማራ ክልል ድንበሮች ላይ የሕዝብ ስብጥር የመቀየር ሙከራዎች እየተደረጉ ነው በማለትም በመግለጫው ላይ ወቀሳ አቅርቧል።

@sheger_press
@sheger_press
በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን መተማ ወረዳ በመንግሥት ኃይሎች እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ውጊያ እንደገና መቀስቀሱን ከዋሪዎች መስማቱን ጠቅሶ ዶቼቬለ ዘግቧል።

ትናንት ከቀኑ 11 ሰዓት  ጀምሮ በመተማ ከተማ በተለያዩ አቅጣጫዎች በሁለቱ ወገኖች መካከል የተኩስ ልውውጥ እንደነበር ነዋሪዎች መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል።

በመተማ ከተማ  ዙሪያ ውጊያ የተጀመረው ሰኞ'ለት ሲኾን፣ የፋኖ ታጣቂዎችም ከተማዋን ለሁለት ቀናት ከተቆጣጠሩ በኋላ ያለተኩስ ልውውጥ ለቀው መውጣታቸው ይታወሳል።

የፋኖ ታጣቂዎች ከማክሰኞ ጀምሮ ሽንፋ የተባለችውን ሌላ የወረዳ ከተማ ይዘው እንደሚገኙ ዘገባው ጨምሮ ጠቅሷል።

@sheger_press
@sheger_press
የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ሽንኩርት ከታንዛንያ ማስገባቱን አስታወቀ‼️

የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮሽች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ለኢትዮ ኤፍ ኤም እንደተናገሩት መጪው ዘመን መለወጫ በዓል ገበያው ላይ የአቅርቦት እጥረት እንዳይፈጠር ከክሎች ባለፈም ከታንዛኒያ ሽንኩርት ማስገባታቸውን ተናግረዋል፡፡
በተለይ የእሁድ ገበያ ላይ ከሸማች ህብረት ስራ ማህበራት ጋር በተያያዘ እንቅስቃሴዎች እየተደረጉ መሆኑን እና ታንዛኒያን ጨምሮ ከተለያዩ ሀገራት ሽንኩርት ወደ ከተማዋ ማስገባት መቻላቸውን አንስተዋል።
በቅርቡ ለተፈጠረው የሽንኩርት መወደድ ምክያትም በሽንኩርት ማሳዎች ውስጥ ውሃ ተኝቶበት እንደሆነ ተናግረው ከኦሮሚያ ከሶማሌ እንዲሁም ከሌሎች ክልሎችም ጭምር ምርት መግባቱን ተናግረዋል፡፡
ቢሮው ሽንኩርትን ከውጪ ወደ ሀገር ውስጥ ለማስገባት እና ለሸማቾች ህብረት ስራ ማህበራት በጋራ ስራዎችን መሰራቱንም ገልጧል፡፡

ዳይሬክተሩ አላስፈላጊ የገበያ ጭማሪ የሚያደርጉ ነጋዴዎችን የመከታተል ስራዎች መሰራታቸውን እና በተለይ ደግሞ ንግድ ፍቃድ ኖሯቸው እየሰሩ ባሉ አካላት ላይ ከፈቃድ ማስጠንቀቂያ እስከ ፅሁፍ ማስጠንቀቂያ ድረስ እየተሰጠ መሆኑን ጨምረው ገልፀዋል፡፡

በዚህም ለበዓሉ የሽንኩርት፣ የእንቁላል፣ የዘይት፣ የዱቄት፣ የቁም እንሰሳት ፣ የቅቤ፣ የጤፍ ምርቶች ላይ ከኦሮሚያ ክልል እንዲሁም ከአዲስ አበባ የንግድ ስራዎች ድርጅትና ከህብረት ስራ ኮምሽን ጋር በመቀናጀት ተመጣጣን በሆነ ዋጋ እየቀረቡ መሆናቸው ገልጸዋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አሜሪካ የኦነግ ከፍተኛ አመራሮች ከዕስር መፈታትን እንደምትደግፍ ገለጸች

አሜሪካ የኢትዮጵያ መንግስት የ #ኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ከፍተኛ አመራሮችን ከዕስር መፍታቱን እንደምትደግፍ አስታወቀች።

የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአፍርካ ጉዳዮች ቢሮ በኩል በወጣው መግለቻ አሜሪካ፤ “" ግጭት ለማስቆም እና ለሁሉም ኢትዮጵያውያን ዘላቂ ሰላም ለማምጣት የሚደረጉ ድርድሮችን ለመደገፍ ዝግጁ" መሆኗን አረጋግጣለች።

ትላንት አመሻሹን የኦነግ ከፍተኛ አመራሮች የሆኑት አብዲ ረጋሳ፣ ለሚ ቤኛ፣ ዳዊት አብደታ፣ ሚካኤል በረን፣ ኬነሳ አያና፣ ገዳ ኦልጂራ እና ገዳ ገቢሳ ከእስር ተፈተዋል። የፓርቲው አመራሮች ከ2012 እና 2013 ዓ/ም ጀምሮ በኦሮሚያ ፖሊስ ተይዘው በዕስር ላይ ቆይተዋል።

አመራሮቹ በፌደራል ፍርድ ቤት በተደጋጋሚ እንዲፈቱ ትዕዛዝ ቢሰጥም ተፈጻሚ ሳይሆን ለአራት አመታት በዕስር ላይ መቆየታቸው ይታወቃል። አዲስ ስታንዳርድ በሐምሌ ወር ርዕሰ አንቀጽ የአመራሮቹ ከህግ አግባብ ውጭ ታስሮ መቆየትን በማውገዝ እስሩ በ #ኢትዮጵያ የፍትህ ስርዓት ላይ አደጋ ነው ሲል ገልጾታል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት ሰኞ ይፋ ይደረጋል።

ትምህርት ሚኒስቴር የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ውጤት ሰኞ ጳጉሜን 4 ቀን 2016 ዓ/ም እንደሚገለጽ አሳውቋል።

የዘንድሮው ብሔራዊ ፈተና በቅይጥ ማለትም በወረቀት እና በኦንላይን መሰጠቱ ይታወሳል።

Via Tikvah

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አዲሱ የደሞዝ ማሻሻያ ትግበራ መስከረም 1 ሊጀምር ነው

- ለደሞዝ ጭማሪው ከ91.4 ቢልዮን ብር በላይ ተመድቧል

(መሠረት ሚድያ)- የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርሙን መምጣት ተከትሎ በመንግስት ቃል ከተገቡት ጉዳዮች አንዱ የሆነው የደሞዝ ጭማሪ ከመስከረም 1/2017 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን መሠረት ሚድያ የተመለከተው እና ትክክለኛነቱ በኢትዮጵያ ቼክ የተረጋገጠ አንድ የፋይናንስ ሚኒስቴር ደብዳቤ ጠቁሟል።

ባለፉት ሰአታት ውስጥ በርካታ የማህበራዊ ሚድያ ተጠቃሚዎች ይህ የፋይናንስ ሚኒስቴር ደብዳቤ ነው የተባለ ምስል እንዲሁም አዲሱን የደሞዝ ስኬል ያሳያል ተብሎ የተገለፀ ስሌት በስፋት ሲያጋሩ ቆይተዋል።

ደብዳቤው በሚኒስትሩ አቶ አህመድ ሺዴ የተፈረመ እንደሆነ የሚያሳይ ሲሆን ለጠ/ሚር ቢሮ ተልኮ ሲቪል ሰርቪስ ደግሞ ኮፒ እንደተደረገ ይገልፃል።

ኢትዮጵያ ቼክ የደብዳቤውን እና የደሞዝ ስኬሉን ትክክለኛነት ያረጋገጠ ሲሆን ለታሰበው የደሞዝ ጭማሪ ከ91.4 ቢልዮን ብር በላይ እንደተመደበ እና ጭማሬው ከመስከረም 1 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን ይገልፃል።

ይህ በፋይናንስ ሚኒስቴር እና በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን በኩል ተጠንቶ የቀረበው የደሞዝ ጭማሪ በሚኒስትሮች ምክር ቤት እንዲፀድቅ መቅረቡም ተመላክቷል።

በአዲሱ ስሌት መሠረት ነባር ደሞዛቸው በጣም ዝቅተኛ የነበረው እና 1,100 ብር ያገኙ የነበሩ መጠኑ በ332 ፐርሰንት ጨምሮ 3,660 ብር እንደሚሆን ያሳያል።

በሌላ በኩል ደሞዛቸው ከፍተኛ የነበረው እና 20,468 ብር ያገኙ የነበሩ መጠኑ በ5 ፐርሰንት ጨምሮ 2,1491 ብር እንደሚሆን ይጠቁማል።

Via ኢትዮጵያ ቼክ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የድምጽ ብክለት ሴቶችን የበለጠ ለመካንነት እንደሚዳርግ ተመራማሪዎች ተናገሩ

900 ሺህ ሰዎች በተሳተፉበት በዚህ ጥናት ላይ ሴቶች የበለጠ ለመካንነት ተጋልጠው ተገኝተዋል
የድምጽ ብክለት ሴቶችን የበለጠ ለመካንነት እንደሚዳርግ ተመራማሪዎች ተናገሩ፡፡
የአየር ንብረት ለውጥ የሰው ልጆችን ህይወት በእጅጉ እየፈተኑ ካሉ ክስተቶች መካከል አንዱ ሲሆን ጉዳቱ ደግሞ በቀላሉ የማይቀለበስ እና ዘላቂ ነው፡፡
የብሪታንያው ሜዲካል ጆርናል ይፋ እንዳደረገው ጥናት ከሆነ የድምጽ ብክለት ባለበት አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች ለመካንነት የተጋለጡ ናቸው ብሏል፡፡
በዴንማርክ 900 ሺህ ገደማ ሰዎች በተሳተፉበት በዚህ ጥናት ላይ የድምጽ ብክለትን ጨምሮ የተበከለ አየር ባለበት አካባቢ የሚኖሩ ሰዎች ለመካንነት ችግር ተጋልጠው ተገኝተዋል፡፡
እድሜያቸው ከ30 እስከ 45 ዓመት የሚሆናቸው ሴቶች ላይ የድምጽ ብክለት የበለጠ ለመካንነት ይዳርጋቸዋል ተብሏል፡፡
ወንዶችን ለመካንነት የሚዳርጉ ምክንያቶችን ያውቃሉ?
የአየር ንብረት ለውጥ የወንዶችን የወንድ ዘር መጠን እንዲቀንስ በማድረግ ለመካንነት ይዳርጋል መባሉ ከዚህ በፊት ይፋ የተደረገ ቢሆንም ሁካታ እና ወከባ ባለባቸወ አካባቢዎች መኖር ለመካንነት ያጋልጣል ሲባል የአሁኑ ለመጀመሪያ ጊዜ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
የድምጽ ብክለት ከሴቶች በተጨማሪም ወንዶችንም ለመካንነት ይዳርጋል የተባለ ሲሆን በተለይም እድሜያቸው ከ37-45 ዓመት ያሉት የበለጠ ተጋላጭ ናቸው ተብሏል፡፡
በጥናቱ ከተሳተፉት መካከልም 16 ሺህ ወንዶች እንዲሁም 22 ሺህ 600 ያህሉ ሴቶች ለመካንነት ተጋልጠው ተገኝተዋል ሲል ዩሮ ኒውስ ዘግቧል፡፡
የተሽከርካሪዎች ድምጽ፣አቧራ እና የፋብሪካዎች ድምጽ ለመካንነት ከሚያጋልጡ የድምጽ ብክለቶች መካከል ዋነኞቹ ናቸውም ተብሏል፡፡
የተጠቀሱት ብክለቶች በወንዶች ላይ የወንዴ ዘር ፍሬ መጠን እንዲቀንስ በማድረግ መካንነትን ያስከትላል የተባለ ሲሆን በሴቶቹ ላይ እንዴት መካንነትን እንደሚያደርስ በጥናቱ ላይ አልተጠቀሰም፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ኢትዬ fm እንኮን ለ 7ተኛ አመት አደረሳችሁ #ኢትዬ_መረጃ #አቤላ
አቶ ጌታቸው ረዳ ባጋጠማቸው ህመም ምክኒያት በአክሱም ሊካሄድ የታሰበው ውይይት ተሰረዘ‼️

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ባጋጠማቸው የጤና እክል ምክንያት ዛሬ በአክሱም ሊካሄድ የታቀደው ህዝባዊ ውይይት መሰረዙን ከጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤት ዛሬ የወጣው መረጃ ይጠቁማል።

የጊዚያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት ፅህፈት ቤቱ ፕሬዜዳንቱ ባጋጠማቸው የጤና እክል ምክንያት ከአክሱም ከተማና አከባቢዋ ነዋሪዎች ጋር ሊካሄድ እቅድ የተያዘለት ህዝባዊ ውይይት ሳይካሄድ በመቅረቱ ይቅርታ ጠይቋል።

ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ያጋጠማቸው የጤና እክል ቀላል ይሁን ከባድ በመግለጫው የተባለ ነገር የለም።

ከሰሞኑን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ እና ምክትላቸው ጄነራል ፃድቃን ገ/ትንሳኤ ያሉበት የአመራሮች ቡድን በየከተማው ህዝባዊ ምክክር እያደረገ እንደነበር አዲስ ማለዳ መዘገቧ አይዘነጋም።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጥቆማ‼️

ቴሌግራምን በመጠቀም ብቻ በርካቶች በርካታ ብር በማግኘት ላይ ናቸው።

እናንተም ይህን ቻናል በመቀላቀል ሙሉ ትምህርት ማግኘት ትችላላቹ።

Join us👇👇👇👍
https://www.tg-me.com/+fzeZ2gn56UE3NTI0
https://www.tg-me.com/+fzeZ2gn56UE3NTI0
የሶማሊያው ፕሬዚደንት ከአብይ አህመድ ጋር አልገናኝም አሉ‼️
ሐሰን ሼይክ ሞሐመድ በቻይና ቤይጂንግ በነበራቸው ቆይታ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ጋር ለመገናኘት ፈቃደኛ እንዳልሆኑ ገልጸዋል።
ጋሮዌ ኦን ላይን ከምንጮቸ አገኘሁት ብሎ እንደዘገበው ይህ የፕሬዚደንቱ ዐቢይን የማነጋገር ፍላጎት ማጣት የአፍሪካ ቀንድ ፖለቲካ መወሳሰቡን ሌላ ማሳያ ነው።
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከወራት በፊት በኢትዮጵያ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በነበራቸው ቆይታ የሶማሊያው መሪ አገር ለአገር እየዞሩ ከሚከሷቸው ወደ አዲስ አበባ ቢመጡ እና ቢነጋገሩ ይቻል እንደነበረ መግለጻቸው ይታወሳል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጎንደር

ለህፃን ኖላዊት ዘገዬ ቤተሰቦች የመኖሪያ ቤት ተሰጠ

የጎንደር ከተማ አስተዳደር ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባን አቶ ቻላቸው ዳኘውና ሌሎች የከተማ አስተዳደሩ የስራ ኃላፊዎች የህፃን ኖላዊትን አባት አቶ ዘገዬ ወልዴን በመስሪያ ቤታቸው አነጋግረዋል።

በዕለቱ የከተማ አስተዳደሩ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ አቶ ቻላቸው ዳኛው ከህፃኗ ቤተሰቦች ጎን መሆናቸውን ገልፀዋል።

የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራር ለህፃኗ ቤተሰቦች የደረሰባቸውን ጉዳት ታሳቢ በማድረግ የመኖሪያ ቤት እንዲሰጣቸው መወሰኑን ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ገልፀዋል።

የህፃን ኖላዊት አባት አቶ ዘገዬ ውልዴ ደግሞ የከተማ አስተዳደሩ እያደረገላቸው ላለው ድጋፍና ትብብር ምስጋና አቅርበዋል። የከተማ አስተዳደሩ የህፃኗ አጋቾች በህግ እስኪቀርቡ ድረስ ድጋፉን እንዳይለያቸው ጠይቀዋል ሲል የዘገበው የጎንደር ከተማ ኮሙኒኬሽን ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ የገቡበትን ውጥረት ለመፍታት ለሶስተኛ ጊዜ ውይይት ለማድረግ በቱርክ አንካራ ከ10 ቀናት በኋላ(September 17/2024/ እንደሚጀምሩ ተሰምቷል።

ይህ እንዳለ ሆኖ ጠቅላይ ሚኒስቴር አብይ አህመድ እንዲሁም የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሰሞኑን ቻይና በነበሩበት ወቅት ውጥረቱን ለማርገብ የናይጄሪያ የቀድሞ ፕሬዚዳንት እና የሰሜኑ ጦርነት በሰላም እንዲቋጭ አደራዳሪ የነበሩት ኦሊሴንጎ ኦባሳንጆ እና የጅቡቲው ፕሬዚዳንት ሁለቱን መሪዎች ለማደራደር እና ለማገናኘት ሞክረው የነበረ ቢሆንም የሶማሊያው ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሀመድ አሻፈረኝ ማለታቸው ታውቋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በበ18-6-58-16_New_compressed.pdf
14.9 MB
👆👆አዲሱ የደመወዝ ጭማሪ እንደጠበቅነዉ አይደለም ያሉ የተለያዩ የመንግስት ስራተኞች ጥናቱ በሚኒስትሮች ምክር-ቤት ቀርቦ ከመፅደቁ በፊት በድጋሚ መታየት እንዳለበት ተናገሩ‼️

ከመስከረም 1 ጀምሮ ተግባራዊ ይሆናል ተብሎ የሚጠበቀው አዲሱ የደመወዝ ማሻሻያ ጥናት: የሚኒስትሮች ምክር-ቤት ከማፅደቁ አስቀድሞ ሰራተኞችን ማወያየት እንዳለበት እና በድጋሚ መታየት እንደሚኖርበት ተጠይቋል።

ካፒታል ያነጋገራቸው ሠራተኞች እንደገለፁት የደመወዝ ማሻሻያው አሁን ያሉበትን የኑሮ ሁኔታ እንደተባለውም ከግምት ያላስገባና እንደጠበቁት እንዳልሆነ አስረድተዋል።

''ስለደመወዝ ማሻሻያው ጠ/ሚኒስትሩ  በተናገሩበት ሰዓት እጅግ በጣም ጠብቄ ነበር ነገር ግን አሁን ከዛ የተለየ ነገር ነው የሆነው'' ሲሉ ስማቸው እንዲጠቀስ ያልፈለጉ አዲስ አበባ ውስጥ በአንድ የመንግስት ትምህርት ቤት የሚያስተምሩ መምህር ለካፒታል ተናግረዋል።

የደመወዝ ማሻሻያ ይደረጋል መባሉን ተከትሎ ከመኖሪያ ቤት ኪራይ ጀምሮ ከምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ እቃዎችን ጨምሮ የዋጋው ንረቱ በእጥፍ እንደጨመረ ሠራተኞቹ ለካፒታል ያቀረቡት ቅሬታ ያመላክታል።

ይህ እንኳን ተፈፃሚ ይሁን ከተባለ የስራ ግብር እንዲቀነስ መደረግ አለበት በማለት ተናግረዋል ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የደመወዝ ጭማሪን በሚመለከት ከክልል ርዕሳነ መስተዳድሮች፣ ከፌደራል መንግስት ባለስልጣናት እና ከግል ባንኮች ፕሬዝዳንቶች ጋር በተደረገ ውይይት ላይ እንደተናገሩት " በተለይ ዝቅተኛ ገቢ ላላቸው የመንግስት ሰራተኞች የሚደረገው የደመወዝ ጭማሪ “በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ አይታወቅም” ብለዋል።

በአዲሱ እርከን ከተካተቱት የመንግስት ሰራተኞች ዉስጥ የጤና ባለሞያዎች ይገኙበታል። ካፒታል ያነጋገራቸዉ እነዚህ ባለሞያዎች እንደሚሉት " ቀድሞ የመሰለን ጭማሪዉ በአንድ ጊዜ እስከ 10 ሺህ ብር የሚያህል ገንዘብ ቢሆንም በተቃራኒው የሆነዉ ግን ያሳዝናል ።

አሁን ላይ ከ 1500 ብር በታች ነዉ የተጨመረዉ ይህ ደግሞ ተመልሶ በስራ ግብር የሚቀነስ መሆኑ የተደረገዉ ጭማሪ ሳይሆን ተስፋ ብቻ ነዉ በማለት ቅሬታዎች አቅርበዋል።

የደሞዝ ጭማሪ መኖሩን መንግስት መናገሩን ተከትሎ በማግስቱ  የሁሉም ነገር ዋጋ በሁለት እጥፍ ጨምሯል።

በዚህም ሰራተኛዉም ሆነ በዝቅተኛ ኑሮ ላይ የነበሩት ሰዎች ምንም የተሰጣቸዉ ነገር ሳይኖርና ጭማሪ እጃቸዉ ሳይገባ የኑሮ ዉድነቱ ተባብሶ ቀጥሏል ሲሉም ሁኔታዉን በምሬት ገልፀዉታል።

ከመስከረም 1 ቀን 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ተግባራዊ እንዲደረግ ለዉሳኔ የቀረበዉ እና በገንዘብ ሚኒስትር እንዲሁም በሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አማካኝነት ጥናት ተደርጎበታል የተባለው ይህ የሠራተኞች የኑሮ ውድነት ጫና መደጎሚያ ደመወዝ ማሻሻያ ረቂቅ ለሚኒስትሮች ምክርቤት በቀን 28 /12/ 2016 ዓ.መቅረቡን ነው ለማወቅ የተቻለው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ማስታወሻ ‼️

እንደሚታወቀው ዛሬ የ12ኛ ክፍል ውጤት ይፋ ይደረጋል።

ለተፈታኞቾ በሙሉ ከወዲሁ መልካም ዕድል እንመኛለን።

ከዚ ጋር በተያያዘ አስቸጋሪ ኔትወርክ ውስጥ የምትገኙ ተማሪዎች።

ውጤት ይፋ እንደተደረገ በቻልነው መጠን ውጤት ልናስመለክታቹ በዝግጅት ላይ እንገኛለን።

በዚ ቻናል ውጤት እናሳያለን አሁንኑ ተቀላቅላቹ ጠብቁን👇👇

Join us 👇👇
https://www.tg-me.com/+XUeXEA4uaCM3YmVk
https://www.tg-me.com/+XUeXEA4uaCM3YmVk
https://www.tg-me.com/+XUeXEA4uaCM3YmVk
ከውጤቱ መለቀቅ አስቀድሞ ዛሬ የትምህርት ሚንስትር የፈተናው ውጤት አሰመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል።

ውጤት እንደተለቀቀ የምናሳውቃቹ ሲሆን ውጤት ማያ ሊንኮችንም አያይዘን ወደረ እናንተ እናደርሳለን።

በድጋሚ መልካም ዕድል

በዚ ቻናል ውጤት እናሳያለን አሁንኑ ተቀላቅላቹ ጠብቁን👇👇

Join us 👇👇
https://www.tg-me.com/+XUeXEA4uaCM3YmVk
https://www.tg-me.com/+XUeXEA4uaCM3YmVk
https://www.tg-me.com/+XUeXEA4uaCM3YmVk
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የዕለቱ የውጭ ምንዛሬ ተመን

Dollar 119.ብር

@sheger_crypto_tech
@sheger_crypto_tech
2024/09/29 11:18:48
Back to Top
HTML Embed Code: