Telegram Web Link
ከጎንደር ከተማ አሥተዳደር የፀጥታ ምክር ቤት   የተሰጠ  መግለጫ‼️

እስካሁን በዘረፋ እና እገታ ወንጀል የተጠረጠሩ 92 ሰዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

ከቅርብ ጊዚያት  ወዲህ  በከተማችንና አካባቢው የተለያዩ   ወንጀሎች  መከሰታቸውና  የብዙ ወገኖቻችን ሰላምና ደህንነት የሚያውክ  ድርጊት እየተፈፀመ  ከመሆኑ ጋር ተያይዞ  ወገኖቻችንን  ያሳዘነና  ልብ  የሰበረ  መሆኑ ይታዎቃል። በተለየም ደግሞ ራሳቸውን  መከላከል  በማይችሉ  በሴቶች፣ በህፃናት እና  በአረጋውያን   ላይ ያነጣጠረ አፈና፣  እገታ  እና  ግድያ ሲፈጸም ቆይቷል።

የከተማችን ሕዝብ በተለያዩ ጊዚያት  የችግሩን መንስኤ በውል በመለየት  በጥፋተኞች ላይ የሕግ የበላይነትን  እንድናስከብር የገለጸልንን ሐሳብ መነሻ በማድረግና ተጨማሪ ሥራዎችን በመሥራት በእገታ፣  በግድያና በዘረፋ  ወንጀል የተጠረጠሩ  49 ግለሰቦችን    በቁጥጥር ሥር አውለናል ።

ነሐሴ 27/16 ዓ.ም በከተማችን በተፈጠረው ችግር ምክንያት  ስለተጎዱ ወገኖቻችን ጉዳዩን አጣርተን የምንወስደውን ሕጋዊ እርምጃ ውጤቱን ለሕዝባችን የምናሳውቅ ይሆናል ።

ሌሎች ቀሪ ተጠርጣሪዎችን ለመቆጣጠር ሥራ  እየሠራን ባለንበት ወቅት የከተችንን ሰላም እና ደህንነት  የማይሹ ኃይሎች  የግል ጥቅማቸውን ለማጋበስ ሲሉ ከጎንደር እሴት ባፈነገጠ ሁኔታ ነሐሴ 22/2016 ዓ.ም የእናትና ልጅ ግድያ ተፈፅሟል። ነሐሴ 27/2016 ዓ.ም ከእናቷ ጡት ነጥቀው የሁለት ዓመት  ህፃን በማገት  300 ሺህ ብር ከተቀበሉ  በኋላ   ገድለው ከወላጆቿ ግቢ ጥለዋታል።

የእናቷን ጡት  ሳትጠግብ በጠዋቱ  ሕይወቷን በተነጠቀችው ህፃን  ልጃችን፣ ነሐሴ 22/2016 ዓ.ም በዚሁ  አረመኔና ጨካኝ ቡድን  ሕይወታቸውን  ባጡ የእናትና  ልጅ  ሕልፈተ ሕይወትና ነሐሴ 27/2016 ዓ.ም   በተፈጠረው ችግር ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖቻችን የፀጥታ ምክር ቤቱ የተሰማውን ሀዘን እየገለጸ ለተጎዱ ቤተሰቦች ለወዳጅ ዘመዶቻቸውና  ለመላው የከተማችን ሕዝብ  መፅናናትን እንመኛለን።

የጋራ ፀጥታ ምክር ቤቱ  የተከሰተውን ግጭት  ለማስቆም ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በመቀናጀት በወንጀሉ የተሳተፉ አካላትን ለሕግ የማቅረብ እና የሕግ የበላይነትን ለማረጋገጥ  ከፍተኛ ጥረት እያደረገ ነው።

ወንጀለኞችን ለመቆጣጠር፣ የሕግ የበላይነትን  ለማረጋገጥ እና የከተማችንን ሰላም ለመጠበቅ ከተፈቀደላቸው የፀጥታ አካላት ውጭ ድምፅ አልባ  መሣሪያ እና ሕገ ወጥ የጦር መሣሪያ ይዞ  መንቀሳቀስ፣  በተደራጀም ይሁን በተናጠል በከተማችን ወንጀል   መፈፀም ፍፁም ሕገ ወጥና  የተወገዘ ተግባር ነው ። 

የተከበራችሁ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና ወጣቶች የሰው ሃብት እና ንብረት ዘርፈው ለመክበር  የቋመጡ  ኃይሎች ከተማውን ለመዝረፍ  የተሰለፋ መሆኑን ተገንዝባችሁ ከመንግሥት ጎን በመቆም የምትወዷትን ከተማችሁን ከአጋችና ከዘራፊ   ቡድን እንድትጠብቁ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን"ብሏል።

@sheger_press
@sheger_press
ጥቆማ‼️

ቴሌግራምን በመጠቀም ብቻ በርካቶች በርካታ ብር በማግኘት ላይ ናቸው።

እናንተም ይህን ቻናል በመቀላቀል ሙሉ ትምህርት ማግኘት ትችላላቹ።

Join us👇👇👇👍
https://www.tg-me.com/+fzeZ2gn56UE3NTI0
https://www.tg-me.com/+fzeZ2gn56UE3NTI0
ትናንት በጎንደር ከተማ የሕፃን ኖላዊት ግድያን ለመቃወምና ሀዘናቸዉን ለመግለጽ በወጡ ሰልፈኞች ላይ የጸጥታ ኃይሎች በወሰዱት እርምጃ  ቢያንስ አምስት ሰዎች መገደላቸውን እና ሶስት ሰዎች ቆስለው ሆስፒታል መግባታቸውን ከጎንደር ከተማ ነዋሪዎች የደረሰኝ መረጃ ያመላክታል ።

@sheger_press
@sheger_press
ፋኖ እና መንግሥትን ለድርድር የሚያመቻቸው ምክር ቤት ከአሜሪካ አምሳደር ጋር ዛሬ ይነጋገራል ‼️

ገጥመውኛል ካላቸው ውስብስብ ፈተናዎች መካከል በመንግሥት እና በፋኖ ታጣቂዎች መካከል ያለው ስር የሰደደ አለመተማመን አንዱ ነው።

ሌላኛው ምክር ቤቱ ገጥመውኛል አካላቸው ችግሮች መካከል የፋኖ ታጣቂዎች አንድ ወጥ አደረጃጀት አለመኖር ነው። የፋኖ ታጣቂዎች አደረጃጀት የወሎ፣ የሸዋ፣ የጎንደር እና የጎጃም በሚል በተናጠል አደረጃጀትና መሪ የሚንቀሳቀሱ መሆናቸውን ምክር ቤቱ በግምገማ ሰነዱ ላይ ጠቅሷል።

እንዲሁም በክልሉ እና በአጎራባች ክልሎች የቀጠለው አለመረጋጋት እና ሁከት ለሰላም ምክር ቤቱ እክል እንደሆነበት ይገልፃል። ክልሉ እንደ በትግራይ እና ኦሮሚያ ክልሎች በኩል የብሔር ግጭት አውድ መቀጠሉ ለሰላም ምክር ቤቱ ጥረት እንቅፋት መፍጠሩን ያስረዳል።

ካውንስሉ ከዲፕሎማቲክ ማኅበረሰቡ ጋር ወደ ውይይት ከማምራቱ በፊት በመንግሥት በኩል ከክልል እስከ ፌደራል ከከፍተኛ ባለሥልጣናት ጋር መክሯል። በክልል  ደረጃ ከአማራ ክልል ፕሬዚዳንት አቶ አረጋ ከበደ ጋር እንዲሁም በፌደራል ደረጃ ከሰላም ሚኒስትሩ አቶ ብናልፍ አንዱአለም ጋር ከሰሞኑ መወያየቱን የዋዜማ ምንጮች አስታውሰዋል።

@sheger_press
@sheger_press
Update‼️

በአዲስ አበባ አፄ ቴዎድሮስ አደባባይ ለዕድሳት ተብሎ የተነሳው የሴባስቶፓል መድፍ ሀውልት ወደ ቦታው ተመልሷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ከሸዋ አማራ የሚወጡ የአዉደ ግንባር መረጃዎችን በፍጥነት በታማኝነት የሚያደርስ ቻናል ላስተዋዉቃችሁ👇👇👇👇

https://www.tg-me.com/SNN_merja
https://www.tg-me.com/SNN_merja
ማይክ ሀመር በአፍሪካ ቀንደ ወቅታዊ ሁኔታ ለመምከር ወደ #ኢትዮጵያ እና #ኬንያ እንደሚመጡ ተጠቆመ፣ በብራሰልስ ከአውሮፓ ህብረት ጋርም እየመከሩ መሆኑ ተገልጿል
#
#የአሜሪካ መንግስት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት ማይክ ሀመር በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ለመምከር ወደ ኢትዮጵያ እና ኬንያ እንደሚመጡ ተገለጸ።

የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ባወጣው መግለጫ እንዳስታወቀው ማይክ ሀመር በብራሰልስ፣ አዲስ አበባ እና ኬንያ ለአስር ቀናት ይቆያሉ።

ትላንት ነሃሴ 28 ቀን 2016 ዓ.ም ሀመር #ብራስልስ የገቡ ሲሆን ዋነኛ አጀንዳቸውም በአፍሪካ ቀንድ ወቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ ከአውሮፓ ህብረት እና የአሜሪካ አጋር ከሆኑ ተቋማት ጋር መምከር ነው ተብሏል።

ሀመር #በናይሮቢ በሚኖራቸው ቆይታ ከኬንያ ባለስልጣናት ጋር በቀጠናው የጸጥታ ሁኔታ እንደሚመክሩ የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ በመግለጫው አትቷል።

ሀመር በአዲስ አበባ ቆይታቸው ከአፍሪካ ህብረት እና ኢጋድ ባለስልጣናት ጋር በሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ እንደሚመክሩ መስሪያቤቱ በመግለጫው አመላክቷል።

ኢትዮጵያን በተመለከተ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤቱ በመግለጫው እንዳስታወቀው ሀመር በፕሪቶርያው የሰላም ስምምነት ዙሪያ ከሁለቱ ተፈራራሚ አካላት ጋር ይመክራሉ ብሏል።

በኢትዮጵያ ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን ለማስቻል አሜሪካ የፌደራል መንግስቱን እና የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደርን ለማገዝ አሁንም ቁርጠኛ ናት ያለው መስሪያቤቱ በመግለጫው #በአማራ እና #በኦሮምያ ክልል ግጭቶች ዙሪያ ከኢትዮጵያ ባለስልጣናት ጋር እንደሚመክሩ ጠቁሟል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በጎንደር ከተማ የቀጠለው እገታ‼️

በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ በአዘዞ ማርያምበር ቀበሌ ትናንት ከምሽቱ 1:30 ገደማ 4 ሰዎች ታግተው ተወሰደዋል‼️

ሁለቱ በመጠጥ ሽያጭ የሚተዳደሩ ሴቶች ሲሆኑ ሁለቱ ደግሞ ወንዶች ናቸው።

አንደኛው ከዚህ በፊት ፖሊስ የነበረና ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የሚሰራ ሰው ሲሆን ሌላኛው ደግሞ ባለቤቱ ገቢዎች የምትሰራ ግለሰብ መሆናቸውን ምንጮች ገልጸዋል።

@sheger_press
@sheger_press
የኢትዮጵያ አየር ሀይል የምስራቁን የአየር ክልል በንቃት እየጠበቀ እንደሚገኝ አስታወቀ‼️

- የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር ደግሞ የምስራቅ ዕዝ በተሟላ ወታደራዊ ዝግጁነት ላይ ይገኛል ብሏል‼️

ከሰሞኑ ግብፅ እና ሶማልያ በቀጠናው እያረጉት ያለውን ወታደራዊ እንቅስቃሴ ተከትሎ የኢትዮጵያ አየር ሀይል የምስራቁን የአየር ክልል በንቃት እየጠበቀ እንደሚገኝ አስታውቋል።

በኢትዮጵያ አየር ሃይል የ3ኛው አየር ምድብ የተሰጠውን ሃገራዊ ግዳጅና ተልዕኮ ለመወጣት በላቀ የዝግጁነት ደረጃ ላይ እንደሚገኝ የአየር ምድቡ አዛዥ ኮሎኔል ደረጀ ቡሽሬ ገልፀዋል፡፡

አዛዡ የ3ኛው አየር ምድብ የሃገራችንን ብሎም የምስራቁን የአየር ክልል በንቃት እየጠበቀ የሚገኝ የሃገር መከታና መመኪያ የሆነ ምድብ ነው ያሉ ሲሆን "ወደፊትም ኢትዮጵያን ከውስጥም ይሁን ከውጭ ፀረ ሰላም ኃይሎች ለመጠበቅ በላቀ የዝግጁት ደረጃ ላይ ይገኛል" ብለዋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የኢፌዴሪ መከላከያ ሚኒስቴር የምስራቅ ዕዝ በተሟላ ወታደራዊ ዝግጁነት ላይ ይገኛል ብሏል።

"በተለያዩ ዘመናት ሀገራችንን ለመውረርና የሽብር ጥቃት ለመፈፀም የሚሞክሩ ሀይሎችን በመከላከል በመስዋዕትነት የተረከቡትን አደራ ለማስቀጠል እስከ ህይወት መስዋዕትነት ለመክፈል በተሟላ የዝግጁነት ደረጃ ላይ ይገኛሉ" ሲል መከላከያ አሳውቋል።

@sheger_press
@sheger_press
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ለመቀጠር እስከ 1 ሚሊዮን ብር ጉቦ መጠየቁን ፥ የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት "የሐሰት እና የስም ማጥፋት" ሲል አጣጣለ

የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት የሕዝብ ግንኙነት መምሪያ ኃላፊ መጋቢ ሐዲስ ዘለዓለም ምሕረቴ በዛሬው ዕለት በሀገረ ስብከቱ ጽ/ቤት መግለጫ ሰጥተዋል።

በመግለጫውም "ነሐሴ 8 ቀን 2016 ዓ.ም በዋዜማ ራዲዮ የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን ላይ የተገለፀው መረጃ ማለትም የአዲስ አበባ ሀገረ ስብከት በተለያዩ አብያተክርስቲያናት ላይ ለመቀጠር የእጅ መንሻ ወይም ጉቦ እየጠየቀ ነው በማለት ያሰራጨው እና በውስጥ ደላሎች የቅጥር አገልግሎት እንደሚሰጥ እንዲሁም  ከሦስት መቶ ሺ ብር ጀምሮ እንደሚጠየቅ እና በአጠቃላይ የመልካም አገልግሎት ችግር እንዳለበት አድርጎ ያቀረበው መረጃ የሐሰት ስም ማጥፋት ነው " ማለታቸዉን  ከተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል ያገኘዉ መረጃ ያመላክታል።

አክለውም "ዋዜማ ራዲዮ ከላይ የተጠቀሰውን የሐሰት መረጃ በማስተላለፉ ለተቋሙ ያለውን ግልፅ ጥላቻ ነው ያሳየው ይህንን መረጃ ከሚመለከታቸው አካላት ማለትም ከአዲስ አበባ ሀገረስብከት ሊቀ ጳጳስ ወይም  የሀገረስብከቱ ዋና ሥራ አስኪያጅን ስለ ጉዳዩ ሳይጠይቅ ከላይ የተጠቀሱትን ብልሹ አሠራሮች ሊቀ ጳጳሱ እንደሚያውቁ አድርጎ መዘገቡ እራሱ ሆን ተብሎ ሀገረ ስብከቱን እና በጠቅላላው የኢትዮጵያ ቤተክርስቲያንን ለመኮነን የተደረገ ነው።"በማለት በመግለጫው አስታውቀዋል።

በተጨማሪም ዋዜማ ራዲዮ ነሐሴ 8 ቀን 2016 ዓ.ም የሠራውን ዘገባ እርማት እንዲሰጥበት እንጠይቃለን ያሉ ሲሆን እርማት የማይሰጥበት ከሆነ ግን በሕግ መሰረት አስተዳደራዊ ፍትሕን ከመገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን እንዲሁም ፍትሕን ከፍርድ ቤት እንደምንጠይቅ እንገልፃለን ብለዋል።

በመጨረሻም "በተሰጠው የሐሰት እና የተዛባ መረጃ ምክንያት የተሳሳተ ግንዛቤ የያዛችሁ መላው የሀገረ ስብከታችን አገልጋዮች እና ምእመናን እንዲሁም የቤተክርስቲያናችን የበላይ አመራር አካላት ሀገረስብከቱ እንደማንኛውም ተቋም ያሉበትን የአሠራር ክፍተቶችን ለማሟላት በርካታ የአሠራር ማሻሻያዎችን እያደረገ እንዲሁም ተጨማሪ ማሻሻያዎችን ለማድረግ ከፍተኛ ጥረት ላይ ስለሚገኝ ይህንን እውነታ እንድትረዱን በታላቅ አክብሮት ለመግለፅ እንወዳለን" በማለት በመግለጫቸው አሳውቀዋል።

ተዋሕዶ ሚዲያ ማዕከል

ዳጉ ጆርናል

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሳሮን በቱርክ በድጋሚ ታስራለች!
በአካባቢው ያላችሁ እና ማገዝ የምትችሉ አግዟት ፣ ሌሎቻችሁ በፀሎታችሁ አስቧት 👏

@merkato_media
ጎንደር‼️

በጎንደር ከተማ የሚገኙ ከቀበሌ እስከ ክፍለ ከተማ ያሉ ከፍተኛ አመራሮች እና የመንግሥት የፀጥታ አካላት በከተማዋ ግጭት በማባባስ ሰዎችን በማሳገት ገንዘብ በመቀበል እና በህገወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውር ውስጥ  እጃችሁ አለበት ተብለው ከየቤታቸው እና መስሪያቤታቸው ዛሬ ጠዋት ታስረዋል። በተመረጡ ቦታዎችም የቤት ለቤት ፍተሻ ተካሂዷል።

@sheger_press
@sheger_press
ጃዋር መሀመድ እንዲህ ይላል 👇

ግብጽ በአባይ ወንዝ ላይ በፍትሃዊነት የመጠቀም መብታችንን ለምግታት እንደምትዝተው ሁሉ፣ ቀጥተኛ ወታደራዊ እርምጃን መውሰድ አትችልምም፤ አትፈልግም።

ይልቁንም ውሃዉን ለማልማት አቅም የሚነሱን እና ትኩርታችንን የሚበታትኑ ሶስት መሰረታዊ ስልቶችን ተጠቀማለች፡፡

እነዚህም፣ በውስጣዊ ግጭቶች መወጠር፣ ከጎረቤት ሀገራት ጋር ማጋጨትና አለም አቀፍ የፋይናንስ ተቋማት ለአባይ ልማት የሚውል ገንዘብ እንዳይሰጡን ማግባባት።

አሁን ላይ በራሳችን ተነሳሽነት በውስጣዊ ጦርነት እየታመስን እንዲሁም ከጎረቤት ሀገራት ጋርም አምባጓሮ ውስጥ ስለገባን ለግብጽ ሰርግና ምላሽ ሆኖላታል ማለት ይቻላል። ሰሞኑን የምታደርገው ዛቻም ከዚሁ የኢትዮጲያ ተጋላጭነት የመነጨ ነው።

መፍትሄውም ዛቻውን ለማስተንፈስ ውስጣዊ ግጭቶችን በሰላም መፍታት እና ከጎረቤቶቻችን ጋር የተፈጠረውን እሰጣገባም ማርገብ ወሳኝ ይሆናል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ባለፉት አመታት በተደጋጋሚ ስጽፍና፣ ስናገር እና ምክረ-ሀሳብ ስለግስ ቆይቻለሁ።

@sheger_press
@sheger_press
በጎንደር ከተማ በታጣቂዎች ለተፈፀመው አስነዋሪ ድርጊት የማያዳግም እርምጃ ይወሰዳል፡- የአማራ ክልል የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ
***

በጎንደር ከተማ በታጣቂዎች ለተፈፀመው አስነዋሪ ድርጊት የማያዳግም እርምጃ እንደሚወሰድ የአማራ ክልል የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ አስታውቋል።

በጎንደር ከተማ የተፈፀመው አስነዋሪ እና አሳዛኝ ድርጊት ሆን ተብሎ እና ታቅዶ የተፈጸመ የጠላት አጀንዳ መሆኑን በአማራ ክልል በምክትል ርዕሰ መሥተዳድር ማዕረግ የሰላም እና ፀጥታ ቢሮ ኃላፊ ደሳለኝ ጣሰው ተናግረዋል፡፡

ኃላፊው ከቀናት በፊት በጎንደር ከተማ በአንዲት ህፃን ልጅ የተከሰተውን አሳዛኝ ታሪክ አስታውሰው፤ ገንዘብ ለመቀበል ባለው ሂደት ሕይወቷ ማለፉ ማህበረሰቡን ብሎም የክልሉን መንግስት ያሳዘነ ተግባር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ከፖለቲካ ጋር ግንኙነት የሌላቸው ሆኖም ግን የኢኮኖሚ አቅም አላቸው ተብለው የሚታሰቡ ነዋሪዎችን ዒላማ በማድረግ፣ ከህፃን እስከ አረጋዊ ባሉ ነዋሪዎች ላይ የሚፈፀሙ የዕገታ ድርጊቶች የማህረሰቡን አብሮ የመኖር መስጋብር እያሳሱት መሆኑን አንስተዋል፡፡

የአማራ ክልል እሴት ባልሆነ መልኩ የኢኮኖሚ ጥቅም ለማግኘት እንደዚህ አይነት እኩይ ተግባር እየተፈጸመ ነው ብለዋል፡፡

በክልሉ የሚፈፀሙ ዘረፋ፣ እገታ እና ግድያ በታጣቂ ኃይሉ እንደሚፈፀሙ ማስረጃ እና መረጃዎች እንዳሉ የገለፁት ኃላፊው፤ የክልሉ ሰላም እና ፀጥታ ቢሮ አስፈላጊውን እርምጃ ለመውሰድ የኦፕሬሽን ዕቅድ እያዘጋጀ መሆኑን አስታውቀዋል፡፡

ህዝቡም አካባቢውን በንቃት እንዲጠብቅ የቢሮ ኃላፊው ጥሪ አቅርበዋል፡፡

@ethio_mereja_news
ጥቆማ‼️

ቴሌግራምን በመጠቀም ብቻ በርካቶች በርካታ ብር በማግኘት ላይ ናቸው።

እናንተም ይህን ቻናል በመቀላቀል ሙሉ ትምህርት ማግኘት ትችላላቹ።

Join us👇👇👇👍
https://www.tg-me.com/+fzeZ2gn56UE3NTI0
https://www.tg-me.com/+fzeZ2gn56UE3NTI0
2024/09/29 13:33:42
Back to Top
HTML Embed Code: