Telegram Web Link
ሦስት ጊዜ የሞት ፍርድ የተፈረደበት ነው! ~ ፖሊስ

በሽብርና በሲቪል አቪየሽን ሕግ ጥሰት ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል ኤሊያስ ድሪባ በዳኔ የተባለው ተጠርጣሪ ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተማ በተለያዩ ከባድ ወንጀሎች ተከሶ ዳዊት ድሪባ በዳኔ በሚል ስም ሦስት ጊዜ የሞት ፍርድ የተፈረደበት ደጋጋሚ ወንጀለኛ መሆኑን ፖሊስ አስታወቀ

በሽብርና በሲቪል አቪየሽን ሕግ ጥሰት ወንጀል ተጠርጥረው በቁጥጥር ሥር ከዋሉት መካከል ኤሊያስ ድሪባ በዳኔ የተባለው ተጠርጣሪ ከዚህ ቀደም በአዲስ አበባ ከተማ ከ1989 ዓ ም ጀምሮ እሰከ 1999 ዓ ም በተለያዩ ከባድ ወንጀሎች ተከሶ ዳዊት ድሪባ በዳኔ በሚል ስም ሦስት ጊዜ የሞት ፍርድ የተፈረደበት ደጋጋሚ ወንጀለኛ መሆኑን ፖሊስ አስታወቀ።

የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት ታህሳስ 25 ቀን 1999 ዓ.ም በዋለው ችሎት በዘረፋ፣ በቅሚያ፣ በሌብነት፣ በቤት ሰብሮ ስርቆት እና በደንብ መተላለፍ በዕድሜ ልክ ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑን ከፖሊስ የምርመራ ማህደር ማረጋገጥ ተችሏል።

ተጠርጣሪው ኤሊያስ ድሪባ በዳኔ ፣ ጀማል ኑሩ እና ዳዊት ድሪባ በዳኔ የሚሉ ስሞችን በመጠቀም 11 ጦር መሣሪያ መዝረፍ ወንጀል፣ 6 ቅምያ ወንጀል፣ 3 ሌብነት ወንጀሎች፣ 3 ሰው መግደል ወንጀል፣ 2 ስርቆትና ቤት ሰብሮ ስርቆት ወንጀሎች፣ አንድ ሐሰተኛ ሰነድ መገልገል ወንጀል፣ ከእስር ማምለጥ ወንጀል እና አንድ ደንብ መተላለፍ የወንጀል ሪከርድ በአጠቃላይ 28 የወንጀል ሪካርዶች ያሉበት እንደሆነና ከዚህ ውስጥ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 2ኛ ወንጀል ችሎት መጋቢት 24 ቀን በዋለው ችሎት ስድስት መዝገቦችን ሦስት ጊዜ አጣምሮ ሦስት ጊዜ በሞት እንዲቀጣ ውሳኔ የተላለፈበት መሆኑን ከፖሊስ የምርመራ ማህደር መገንዘብ ተችሏል።


ኢ.ፌ.ፖ.ሚ
አቶ ታዮ በዋስ እንዲለቀቁ ያቀረቡት አቤቱታ ውሳኔ አላገኘም!

በተለያዩ ወንጀሎች ጥርጣሬ ተከስሰዉ የታሰሩት የቀድሞ የኢትዮጵያ የሰላም ሚኒስትር ዴኤታ ታዬ ደንደዓ በዋስ እንዲለቀቁ ያቀረቡት አቤቱታ ዛሬም ዉሳኔ አላገኘም።ባለፈዉ ሐምሌ 30፣ 2016 አዲስ አበባ ያስቻለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 1ኛ የሕገ መንግስትና ሕገ-መንግስት ስርዓት ላይ የሚፈጸሙ ወንጀል ጉዳዮች ችሎት አቶ ታዬ ላይ ከተመሠረተባቸዉ ሶስት ክሶች ከሁለቱ በነጻ አሰናብቷቸዉ ነበር።

ይሁንና ፍቃድ ሳይኖራቸው የጦር መሳሪያ ይዘው ተገኝተዋል በሚል የቀረበባቸውን 3ኛ ክስ ግን እንዲከላከሉ ፍርድ ቤቱ በይኖ ነበር፡፡ የአቶ ታዬ ባለቤት ወይዘሮ ስንታየሁ ዓለማየሁ ለአዲስ አበባው ዘጋቢያችን ስዩም ጌቱ እንደነገሩት አቶ ታዬ ሥስተኛዉን ክስ በዋስ ተለቅቀዉ እንዲከራከሩ ያቀረቡትን ጥያቄ ፍርድ ቤት ዉድቅ አድርጎባቸዋል።

በዚሕም ምክንያት ተከሳሹ ለጠቅላይ ፍርድ ቤት ሁለተኛ ወንጀል ችሎት ይግባኝ ጠይቀዉ ፍርድ ቤቱ ለዛሬ ቀጠሮ ሰጥቷቸዉ ነበር።ወይዘሮ ስንታየሁ እንዳሉት ፍርድ ቤቱ አቤቱታን ዛሬ ማየት አልቻለም። አቶ ታዬ ደንደዓ የተመሰረተባቸዉን ክስ ያለጠበቃ በራሳቸዉ እየተከራከሩ ነዉ።

የአዲስ አበባዉ ወኪላችን ስዩም ጌቱ እንደዘገበዉ አቶ ታዬ የጥብቅና መብት ለመከልከላቸው መንግስትን ተጠያቂ አድርገው፣የብሔራዊ መረጃ ደህንነት ያሉትን ተቋም መክሰሳቸው አይዘነጋም፡፡አቶ ታዬ የገዢዉ የብልፅግና ፓርቲ ከፍተኛ ባለሥልጣን፣ የኦሮሚያ ምክር ቤት አባልና ሚንስትር ደ ኤታ ነበሩ።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የ3 አመት ልጅ የደፈረው የእድሜ ልክ እስራት ተቀጣ

በጋሞ ዞን ዲታ ወረዳ የግብረስጋ ድፍረት በደል የፈጸመው ተከሳሽ በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት ተወስኗል።

ተከሳሽ አቶ ቱካ ቱጋሞ ዕድሜ 45 ስሆን በ1996ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ህግ አንቀጽ 627(5) ስር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ የዲታ ወረዳ አቃቤ ህግ ክስ ተመስርቶበታል፡፡

የአቃቤ ህግ የክስ መዝገብ እንደሚያስረዳው ተከሳሽ የግብረስጋ ግንኙነት በመፈጸሙ ነሀሴ 5/ 2016ዓ.ም ዕሁድ ከቀኑ 9:00 የሚሆንበት ጊዜ በዲታ ወረዳ ዛዳ ከተማ ቀበሌ ልዩ መጠሪያው ሚሽዳ ቀጠና ተብሎ የሚጠራበት አከባቢ የ3አመት ልጅ የሆነችውን የግል ተበዳይ

ህፃን ብርቱ ገነነ ዕድሜ ሦስት ዓመት የሆነችው ልጅ ከሌሎች ልጆች ጋር ከብቶችን በሚያግዱበት ቦታ ተከሳሽ አንቀላፍታለች በማለት አቅፎ ወደ ተበዳይ ወላጅ አባቷ ቤት ድረስ በማምጣት አስገድዶ በመድፈር የከባድ አካል እና ሥነ ልቦና ጉዳት ያደረሰባት በመሆኑ የፈፀመው በህፃን ልጆች ላይ የሚፈፀም የግብረስጋ ድፍረት ወንጀል ክስ አቅርቧል።

ዐቃቤ ህግ የተከሳሽን ጥፋተኝነት ያስረዱልኛል ያላቸውን ዝርዝር የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎች ለፍርድ ቤቱ በማቅረብ የተከሳሽን ጥፋተኝነት ያሰረዳ ሲሆን ተከሳሽም ወንጀሉን ስላለመፈጸሙ ማስረጃ አቅርቦ ያላሰተባበለ በመሆኑ ፍርድ ቤቱም የዐቃቤ ህግን የሰውና የሰነድ ማስረጃ መሰረት በማድረግ ተከሳሽን ጥፋተኛ በማለት ነሀሴ 22/2016 ዓ.ም በዕድሜ ልክ ጽኑ እስራት እዲቀጣ ተወስኖበታል ፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጥቆማ‼️

ቴሌግራምን በመጠቀም ብቻ በርካቶች በርካታ ብር በማግኘት ላይ ናቸው።

እናንተም ይህን ቻናል በመቀላቀል ሙሉ ትምህርት ማግኘት ትችላላቹ።

Join us👇👇👇👍
https://www.tg-me.com/+fzeZ2gn56UE3NTI0
https://www.tg-me.com/+fzeZ2gn56UE3NTI0
ታዋቂዋ አቀንቃኝና የግጥም ፀሃፊ
Cardi B በ X ገጿ ላይ ለህፃን ሔቨን ድምፅ ሆናለች።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Telegram :

የቴሌግራም መስራች እና ዋናው ስራ አስኪያጅ ፓቨል ዱሮቭ ፍርድ ቤት ቀርቧል።
ፍርድ ቤት በ5 ሚሊዮን ዩሮ ወይም 5.56 ሚሊዮን ዶላር ዋስ ተለቆ ጉዳዩን እንዲከታተል ወስኖለታል።

ከፈረንሳይ እንዳይወጣ ግን ታግዷል።
እገዳው ተጨማሪ ምርመራ ስለሚደረግ ነው የተጣለው።

@ethio_mereja_news
ታገቱ‼️

ዛሬ ጠዋት በኦሮሚያ ክልል ከገብረ ጉራቻ እና ቱሉ ሚልኪ መሀከል አንድ የህዝብ አውቶብስ ሙሉ ተሳፋሪ ከሾፌር ረዳት ጋር በዘራፊ ወንበዴዎች በታጠቁ ሀይሎች ታፍነው መወሰዳቸው ተሰምቷል።

@sheger_press
@sheger_press
ምንም አይነት የደሞዝ ጭማሪ ሳይደረግ የሸቀጦች እና የምግብ አይነቶች ዋጋ ላይ በአንድ ወር ውስጥ ብቻ እስከ 50 ፐርሰንት ጭማሪ በተፈጠረበት ሁኔታ እንደገና ሌላ ታክስ በውሀ፣ ኤሌክትሪክ፣ ትራንስፖርት ወዘተ ላይ ማዥጎድጎድ ምንድን ነው?

ሰዉን ባትፈሩ ፈጣሪን...!

EliasMeseret

@sheger_press
@sheger_press
ምን አይነት ዘመን ላይ ነው ያለነው ግን⁉️

ያሳዝናል ይህ ድርጊት ዛሬ ጠዋት ገርባ የተከናወነ ነው

ደቡብ ወሎ ቃሉ ወረዳ ገርባ ከተማ ቀጨማ ተብሎ በሚጠራ አካባቢ አሁነ ላይ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የዋለች አንድ እናት ነሐሴ 17/2016 የወለደችውን ህፃን ልጅ ሽንት ቤት ጥላ ዛሬ ነሐሴ 23/2016 ተገኝቷል።

የአካባቢው ፖሊሶችና የገርባ ጤና ጣቢያ ባለሙያዎች ከማህበረሰቡ ጋር  የህፃኑን አስክሬን ከሽንት ቤት ወጥቶ በክብር እንዳሳረፈ ገልፀዋል።

ሴቶች ወልዳችሁ የማታሳድጉትን አትፀንሱ:ተከላከሉ።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Blum‼️

በዚ ሰአት ከBlum የተሻለ ኤርድሮፕ የለም

እኔ በግሌ ከኖትኮይንም ከዶግስም የተሻለ ይሆናል ብዬ የማስበው Blum ብቻ ነው

በተለያየ በብዙ አካውንት ስሩት ፤ በእርግጠኝነት ብዙ ነው የምታተርፉበት 😊

Blum ላልጀመራቹ  በዚ ጀምሩ👇👇👇

https://www.tg-me.com/blum/app?startapp=ref_JhjvJ1zEys

https://www.tg-me.com/blum/app?startapp=ref_JhjvJ1zEys‌‌

ስለ አጨዋወቱ ለማወቅ ይህንን ቻናል ይቀላቀሉ👇👇
https://www.tg-me.com/+fzeZ2gn56UE3NTI0
https://www.tg-me.com/+fzeZ2gn56UE3NTI0
የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ጊዜያዊ አስተዳደሩ የተሿሚዎችን ምደባና የአስተዳደሩን ሌሎች ተግባራት በሚያደናቅፉ አካላት ላይ ሕጋዊ ርምጃ እንደሚወስዱ አስጠንቅቀዋል።

ጌታቸው ይህን ማስጠንቀቂያ ያስተላለፉት፣ የሕወሓት አመራሮች የጊዜያዊ አስተዳደሩን አዳዲስ ሹመቶች እንደማይቀበሉ መግለጣቸውን ተከትሎ ነው።

ጌታቸው ትናንት ባወጡት መግለጫ፣ የሕወሓት ሊቀመንበር ደብረጺዮን ገብረሚካዔል የሚመሩት ቡድን በክልሉ ሥርዓት አልበኝነትን ለማስፈን ጥረት እያደረገ ይገኛል በማለት ከሰዋል።

ጊዜያዊ አስተዳደሩ ሕዝቡን ባግባቡ የማገልገል ሃላፊነቱን ለመውጣት በተለያዩ የክልሉ መዋቅሮች ሹም ሽሮችን ማድረግ እንደሚቀጥልም ጌታቸው ጠቁመዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ቱሉ ሚልኪ እና ገርበ ጉራቻ ከተማ መካከል በተለምዶ "ታታ" ተብሎ በሚጠራ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ የተሳፈሩ ተሳፋሪዎችን በሙሉ ዛሬ ረፋዱ ላይ ማንነታቸው ባልታወቁ ታጣቂዎች ታፍነው እንደተወሰዱ ዋዜማ ከአካባቢው ነዋሪዎች ሰምታለች።

ታጣቂዎቹ፣ የአንድ አምቡላንስ ሹፌር እና አንድ የጤና ባለሙያ ጭምር አፍነው መወሰዳቸውን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል፡፡

የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡሱ መነሻውን ከአማራ ክልል አድርጎ ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ እንደነበር ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል፡፡

የመከላከያ ሠራዊት አባላት ድርጊቱ ከተፈጸመ በኀላ ከአካባቢው መድረሳቸውንና ኾኖም ታጋቾችን ማስለቀቅ እንዳልቻሉም ለመረዳት ተችሏል።

ነዋሪዎቹ፣ አካባቢው ካሁን ቀደምም ተመሳሳይ የአፈና ድርጊቶች ሲፈጸሙበት እንደቆየ ገልጸዋል።

@sheger_press
@sheger_press
Update‼️

ትናንት ጠዋት አካባቢ ከጎጃም ወደ አዲስ አበባ በባስ ሲጓዙ የነበሩ ተሳፋሪዎች በኦሮሚያ ክልል ከገብረ ጉራቻ እና ቱሉ ሚልኪ መሀከል አንድ የህዝብ አውቶብስ ሙሉ ተሳፋሪ ሾፌርና ረዳቱን ጨምሮ በታጣቂዎች መታገታቸውን መዘገባችን ይታወሳል።

የታጋቾቹ ቁጥር አጠቃላይ 60 የሚሆኑ ሲሆን ቤተሰቦቻቸው በጭንቀት እያለቀስን ለመቀመጥ ተገደናል ብለዋል።

አጋቾቹ የት እንዳደረሷቸው እስካሁን ምንም የምናውቀው ነገር የለም ብለዋል። ታጣቂዎቹ እገታውን ተረጋግተው እና ወደ ሰማይ ጥይት እየተኮሱ ጭምር እንደፈፀሙት ምንጮች ተናግረዋል።

ከታገቱት ሰዎች አብዛኞቹ ህፃን የያዙ ሴቶች እና አዛውንቶች ናቸው። (ayu)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በማረቆ 7 ሰዎች ተገደሉ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ማረቆ ልዩ ወረዳ ማንነትን መሠረት ያደረገ ነው በተባለ ጥቃት አራት የአንድ ቤተሰብ አባላትን ጨምሮ ሰባት ሰዎች ተገደሉ ፡፡

ግድያው የተፈጸመው በልዩ ወረዳው ዲዳ ሀሊቦ በተባለ ቀበሌ ውስጥ መሆኑን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል፡፡

የሟቾቹ የቅርብ ቤተሰብ አባል መሆናቸውን ለዶቼ ቬለ የተናገሩትና አቶ ሁሴን ለመንጎ የተባሉ የዲዳ ሀሊቦ ቀበሌ ነዋሪ ታጣቂዎቹ ጥቃቱን ባለፈው ማክሰኞ የፈጸሙት ሟቾቹ ሌሊት በተኙበት የተኩስ እሩምታ በመክፈት መሆኑን ገልጸዋል፡፡

በጥይት ከተመቱት አሥራ አንድ ሰዎች መካከል የሰባቱ ህይወት ወዲያ ማለፉን የጠቀሱት የዓይን አማኙ “ ከሟቾቹ መካከል አራቱ የአንድ ቤተሰብ አባላት ሲሆኑ ሁለቱ ህጻናት ናቸው ፡፡ ቀብራቸውም ትናንት ሐሙስ ተከናውኗል “ ብለዋል ፡፡

ጥቃቱ ማንነትን መሠረት ያደረገ ፣ ዘግናኝና ታቅዶ በህጻናትና ሴቶች ላይ የተፈጸመው መሆኑን የጠቀሱት የሟች ቤተሰብ አሁን ላይ በጥቃቱ የቆሰሉት አራት ሰዎችን ደግሞ በወራቤ ሆስፒታል አስገብተናል ” ብለዋል ፡፡

ዘገባ ሸዋንግዛዉ ወጋየሁ ከሃዋሳ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ግብጽ ጦር መሳሪያዎችን፣ ወታደራዊ ቁሳቁሶችንና ወታደሮቿን ወደ ሱማሊያ መላክ መቀጠሏን የተባበሩት ዓረብ ኢምሬቶች ጋዜጣ ዘ ናሽናል ዘግቧል።

ከማክሰኞ እስከ ትናንት ምሽት ድረስ ወታደሮችንና ጦር መሳሪያዎችን የጫኑ ስምንት የግብጽ ወታደራዊ አውሮፕላኖች ሞቃዲሾ ማረፋቸውን ከምንጮቹ እንደሰማ ዘገባው አመልክቷል።

ግብጽ ጸረ-ታንክ ሚሳይሎችን፣ ተወንጫፊ ሮኬቶችን፣ ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎችን፣ ራዳሮችንና ድሮኖችን ወደ ሱማሊያ የመላክ እቅድ እንዳላት መስማቱቱንም ዘገባው ጠቅሷል።

ግብጽ ወታደሮቿን ከሞቃዲሾ ውጭ በፌደራል ግዛቶች በቋሚነት የማሠማራት እቅድ ይኑራት አይኑራት ለጊዜው ግልጽ ባይኾንም፣ የሱማሊያን ወታደሮች የማሰልጠን ዓላማ እንዳላት ግን ብሉምበርግ ምንጮችን ጠቅሶ ሰሞኑን ዘግቦ ነበር።

@sheger_press
@sheger_press
2024/09/29 17:25:56
Back to Top
HTML Embed Code: