Telegram Web Link
ለጥንቃቄዎ
ጥሩ እንቅልፍ የማይተኙባቸው ምክንያቶችን
ያስወግዱ!!

1. በውስጥዎ ጭንቀት ካለ።
2. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን መጠቀም።
3. ከመኝታ በፊት ሲጋራ ማጨስ።
4. በቂ እንቅስቃሴ(ስፖርት) አለማድረግ።
5. በመኝታ ሰዓት አካባቢ ከመጠን በላይ የአልኮል መጠጦች መጠጣት።
6. የመኝታ ሠዓት ሲቃረብ ቡና መጠጣት።
7. ከፍተኛ የስብ መጠን ያለው እራት መመገብ።
8. የመኝታ ክፍልዎ የብርሃን እና የአየር ሁኔታ።
9. የሆርሞኖች መቀያየር (መለዋወጥ)።
10. በመኝታ ክፍል ውስጥ የቤት እንሰሳቶች ካሉ።

በሰላም እደሩ

@Merkato_media
16 ጅብ‼️

ዓለም ገና (ዳለቲ )ኣከባቢ ዛሬ ረፋድ ላይ ጅብ ኣንዲት የ4 አመት ህፃን በመውሰድ ይበላታል በዚህው የተበሳጨ የአከባቢው ሰው ርብርብ በማድረግ 16 ጅቦች ገድለዋል፡።

@sheger_press
@sheger_press
አርቲስት ኩራባቸው ደነቀ አርፏል።
ነፍስ ይማር 😢
" ቁርስ ስጡኝ አለ ። ሰርተው ሲያቀርቡለት ግን ሕይወቱ አልፏል "
***
ይህ የአርቲስት ኩራባቸው ደነቀ የዛሬ ሕይወት ነው ። ትናንት ከወዳጆቹ ጋር ሰላማዊ ግንኙነቱን ፈጽሞ ነው የገባው ። ዛሬ ጧትም ሰላማዊ ነበር ። ጧት አልጋ ላይ ሆኖ ቁርስ እንዲያዘጋጁለት ተናገረ ። ቁርስ አዘጋጅተው መኝታ ቤቱ ገብተው ሲቀሰቅሱት ግን በሕይወት የለም ። በቃ ! ይህ ነው የኩራ መጨረሻ ። ይኸው ነው የማናችንም ሕይወት ። ቁርስ ተሰርቶ እስኪቀርብ እንኳ ፋታ የማይሰጥበት ዓለም ።

የሦስት ልጆች አባት የነበረው ኩራባቸው ደነቀ ነገ ከ5:00 - 6:00 በቀጨኔ መድኃኒዓለም ስርዓተ ቀብሩ ይፈጸማል ።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መንግሥት አዲስ የብር ኖቶችን ይፋ ሊያደርግ ነው በሚል በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ የሚዘዋወረው መረጃ ሐሰተኛ ነው!

መንግሥት አዲስ የ500 እና የ1000 ሺህ ብር ኖቶች ሊያትም ነው በሚል የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈትቤትን ሎጎ በመጠቀም በማኅበራዊ ሚዲያ የተሠራጨው መረጃ ሐሰተኛ መሆኑን ኢቢሲ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡

@ethio_mereja_news
ፍርድ ቤቱ ፖሊስ በእነ ዮሐንስ ዳንኤል ላይ በጠየቀው የጊዜ ቀጠሮው ላይ ብይን ለመስጠት ለነገ ቀጠሮ ያዘ !

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተረኛ ችሎት የፌዴራል ፖሊስ በእነ ዮሐንስ ዳንኤል ላይ በጠየቀው የ14 ቀን የጊዜ ቀጠሮ ላይ የግራቀኙን ሰፊ ክርክር ካዳመጠ በኋላ ብይን ለመስጠት ለነገ ነሐሴ 21ቀን 2016 ዓ.ም ቀጠሮ ይዟል።

ተጠርጣሪዎቹ በጠበቆቻቸው በኩል የዋስትና መብት እንዲፈቀድላቸው ጠይቀዋል።

የፌዴሬል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቡድን ተጠርጣሪዎቹ ላይ የአቪዬሽን አሰራር ሕግ ከመጣስ ባለፈ በሽብር ወንጀልም ምርመራ ስለጀመርኩ የዋስትና ጥያቄያቸው ውድቅ ይደረግ በማለት ተከራክሯል።

ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት ተጠርጣሪዎች ዮሐንስ ዳንኤል በርሄ፣ አማኑኤል መውጫ አብርሃ፣ ናትናኤል ወንድወሰን ሹሜ፣ ኤልያስ ድሪባ በዳኔ፣ ይዲድያ ነጻነት አበበ እና እሌኒ ክንፈ ተክለአብ ናቸው።

የፌዴራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የምርመራ መዝገብ እንደሚያሳየው እነዚህ ተጠርጣሪዎች ተፈጥሮ በፈጠረው የአየር መዛባት ምክንያት አውሮፕላኑ መብረር አይችልም እየተባለ፣ አስገድዶ ለማስኬድ የፈጠሩት አምባጓሮ በወንጀል ሕጉ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል ብሏል።

የፖሊስ የምርመራ ቡድን ተጠርጣሪዎች ላይ በወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ ከተጀመረው ምርመራ ባሻገር፣ ከጸረሰላም ኃይሎች ተልዕኮ ተቀብለው የተንቀሳቀሱ በመሆናቸው፤ በሽብር ወንጀልም መጠርጠራቸውን ነው የሚያመላክተው።በወቅቱ አየር መንገዱ ከደህንነት ኃይሎች ጋር በመሆን በትዕግስት ቢማጸናቸውም፤ ድብቅ አጀንዳቸውን እያራመዱ በመሆናቸው አሻፈረን ማለታቸውንም በምርመራ መዝገቡ አካቷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
6ኛ እና 8ኛ ክፍል የማለፊያ ነጥብ ይፋ ሆኗል

በ2016 ዓ.ም በተሰጠው ክልል አቀፍ 6ኛ እና 8ኛ ክፍል ከተመዘገበው ውጤት አንጻር ዝቅተኛ የማለፊያ መቁረጫ ነጥብ አማካኝ ውጤት
👉ለ6ኛ ክፍል
   ✍️ለወንድ 46
    ✍️ለሴት 45
ለአይነ ስውራን ተማሪዎች
✍️ ለወንድ 45
✍️ ለሴት 44 ሆኗል።
👉ለ8ኛ ክፍል
✍️ለወንድ 46
✍️ለሴት 45
👉ለአይነ ስውራን ተማሪዎች
✍️ ለወንድ 45
✍️ለሴት 44 እንዲሆን የተወሰነ መሆኑን የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

@sheger_press
@sheger_press
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የኦሞ ወንዝ ባስከተለው መጥለቅለቅ ሳቢያ ጎርፍ ወደ ዳሰነች ወረዳ ዋና መቀመጫ ኦሞራቴ ከተማ በመቃረብ ላይ እንደኾነ ተነግሯል።

ወንዙ ያስከተለው መጥለቅለቅ ከአቅም በላይ እንደኾነ የገለጸው የዞኑ አስተዳደር፣ ጉዳይ የሚመለከታቸው አካላት ለችግሩ ዘላቂ መፍትሄ እንዲፈልጉ ጠይቋል።  

የወንዙ ውሃ መንደሮችን ከጎርፍ ለመከላከል የተሠሩ የአፈር ግድቦችን በመጣስ፣ አዳንዳንድ ቀበሌዎችን ማጥለቅለቅ እንደጀመረ የዞኑ አስተዳደር ገልጧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
📹የሚሸጥ የዩቱብ ቻናል
https://www.youtube.com/@ayatdaily602
  🔹 STRICK FREE
  🔹COPYRIGHT FREE
  🔹 MONITIZED የሆነ 💰50 በውስጡ አለው
  🔹Passport Done
  🔹Pin verified

🛑 channel እንፈልጋለን ላላቹኝ

🔔• 9,514 SUBSCRIBE

•➤አሁኑኑ ያናግሩን 👇

📩 •➤ 𝐈𝐧𝐛𝐨𝐱 𝐌𝐞
@ETHIO_JOURNAL
ደብረብርሃን ባጃጆች ከጠዋቱ 12:00 ሰአት እስከ ምሽቱ 12:00 ሰአት ብቻ እንዲሰሩ ተወሰነ።

የደብረ ብርሃን ከተማ  የጸጥታ ምክር ቤት  ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ባጃጅ ተሽከርካሪን በመጠቀም በማህበረሰቡ ላይ ስርቆትን ጨምሮ የተለያዩ ወንጀሎችን ለመከላከል ለባጃጅ አሽከርካሪዎች የተለያዩ ክልከላዎችን አስቀምጠ።

በዚህ ወንጀል የተሠማሩ አካላት የባጃጅ ተሽከርካሪዎቹን ማሟላት ያለባቸውን ህጋዊ ሰውነት ተሽከርካሪዎቹ ሳያሟሉ እንደሚያሽከረክሩም የጸጥታው ምክር ቤት እንደደረሰባቸው አንስቷል።

ለህዝብ ሰላም ሲባል የጸጥታ ምክር ቤቱ ህግና ስርአት ለማስከበር ያመች ዘንድ ማንኛውም የባጃጅ አሽከርካሪ በተሽከርካሪው ላይ ስቲከር መለጠፍ ፣ መጋረጃ መጠቀም እንደማይቻል በክልከላው ገልጿል።

ያለስምሪት ፣ የጎን ቁጥርና ታርጋ  ሳይጠቀሙም ማሽከርከር በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን፣

ከዛሬ 4:00 ጀምሮ የባጃጅ ተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ከጠዋቱ 12:00 ሰአት እስከ ምሽቱ 12:00 ሰአት ብቻ ማሽከርከር  እንደሚቻል፣

ከዚህ ሰአት ውጭ ወይም ከላይ መደረግ ያለባቸውን ያላሟላ ባጃጅ ሲንቀሳቀስ ቢገኝ የማያዳግም ህጋዊ እርምጃ በባጃጅ አሽከርካሪውና ባለንብረቱ ላይ እንደሚወሰድ ከከተማ አስተዳደሩ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ያገኘሁት መረጃ ያመላክታል።
Cats በ Pre market 🔥🔥

ያልጀመራቹ ጀምሩ ቀጣዮ DOGS 👇👇

http://www.tg-me.com/catsgang_bot/join?startapp=xkQP3ezHQcUYeSPyt_-Hv
ለፖሊስ የ14 ቀን የግዜ ቀጠሮ ተፈቀደ

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት የፌዴራል ፖሊስ በእነ ዮሀንስ ዳንኤል ላይ የጠየቀውን የ14 ቀን የግዜ ቀጠሮ ፈቅዷል።

ተጠርጣሪዎቹ የዋስትና መብት እንዲፈቀድላቸው በጠበቆቻቸው አማካኝነት የጠየቁ ቢሆንም ፍርድ ቤቱ የፖሊስን የምርመራ ውጤት ለመጠባበቅ ለጳጉሜ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ይዟል።

ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡት ተጠርጣሪዎች ዮሀንስ ዳንኤል በርሄ፣ አማኑኤል መውጫ አብርሃ፣ ናትናኤል ወንድወሰን ሹሜ፣ ኤልያስ ድሪባ በዳኔ፣ ይዲድያ ነጻነት አበበ እና እሌኒ ክንፈ ተክለአብ ናቸው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/09/29 19:29:43
Back to Top
HTML Embed Code: