Telegram Web Link
አሜሪካ በሩስያ ላይ ያነጣጠረ ከፍተኛ ማዕቀብ ይፋ አደረገች!

የአሜሪካ ግምዣ ቤት እና እና የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር መስርያ ቤት በሩስያ ላይ ያነጣጠረ አዲስ ማዕቀብ ይፋ አደረጉ፡፡

ማዕቀቡ በሩስያ ውስጥ እና ውጭ የሚገኙ 400 ተቋማት እንዲሁም ግለሰቦች ላይ አነጣጥሯል የተባለ ሲሆን የቻይና ኩባንያዎችም በማዕቀቡ ውስጥ መካተታቸውን ሲኤንኤን አስነብቧል፡፡ከጦር መሳርያ ድጋፍ እና ምርት ጋር በተገናኝ ከሞስኮ ጋር ግንኙነት አላቸው የተባሉት አካላት ምዕራባውያን በሀገሪቱ ላይ ከዚህ ከቀደም የጣሏቸው ማዕቀቦች የታቀደላቸውን ግብ እንዳይመቱ እክል ሆነዋል ነው የተባለው፡፡
 
የቻይና ኩባንያዎች በዚህ ወቀሳ ውስጥ በቅድሚያ የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ በአዲሱ ማዕቀብ ውስጥም የሩስያን የጦርነት ኢኮኖሚ በመደገፍ እና ለጦር መሳርያ ምርት የሚያገለግሉ እንደ “ማይክሮኤሌክትሮኒክ” እና “ማሽን ቱል” ያሉ የተለያዩ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን በመሸጥ ማዕቀብ እንደሚጣልባቸው ተገልጿል፡፡ 

እነዚህ ኩባያዎች በቻይና እና በዚያው ሩስያ ፋብሪካዎችን ከፍተው በመስራት ላይ እንደሚገኙ የአሜሪካ ግምጃ ቤት ይፋ ባደረገው ሰነድ ላይ አመላክቷል፡፡ ከዚህ ባለፈም ሞስኮ ከተለያዩ ሀገራት በምታስገባቸው ጦር መሳርያዎች፣ ተተኳሶች እንዲሁም ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁሶች ግዢን በማሳለጥ የሚሳተፉ ቱጃሮች በማዕቀቡ ውስጥ ከተካተቱት መካከል ይጠቀሳሉ፡፡ 

እነኚህ የሩስያ ቱጃሮች በውጭ ሀገራት ያላቸውን የባንክ ሂሳብ እና ግንኙነት በመጠቀም ወርቅን ወደ ገንዘብ በመቀየር ሞስኮ በምዕራባውያን ከዚህ ቀደም የተጣለባት ማዕቀብ ሳይገድባት በጦር መሳርያ ግዢ ላይ እንድትሳተፍ ተባብረዋል በሚል ወቀሳ ቀርቦባቸዋል፡፡ 
የሶማሊያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሃምዛ አብዲ ባሬ ኢትዮጵያ በዚህ አመት መጀመሪያ ላይ ከሶማሌላንድ ጋር ከተፈራረመችው አወዛጋቢ የመግባቢያ ስምምነት እስካልወጣች ድረስ የኢትዮጵያ ጦር በመጪው የአፍሪካ ህብረት የድጋፍ ተልዕኮ (AUSSOM) አካል እንደማይሆን ገለፁ::

ባሬ ሞቃዲሾ ውስጥ ከሶማሌላንድ ጋር ከተፈራረመችው የመግባቢያ ስምምነት ካልወጣች ወታደሮቿ በመጪው ኦፕሬሽን አካል አይሆኑም። የሚቆዩም ከሆነ በአፍሪካ ህብረት ስልጣን ስር አይሆኑም ሲሉ ተናግረዋል።

ባሳለፍነው ሀሙስ ሞቃዲሾ ከሚገኙት የከተማው ማዘጋጃ ቤት ታዳሚዎች ለቀረቡላቸው ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡት ባሬ እንዳሉት የሶማሊያ መንግስት ከሶማሌላንድ ጋር የተደረሰውን ስምምነት ተግባራዊ እንዳይሆን የሶማሊያ መነንግስት በብቃት መምራት ችሏል።

"የመግባቢያ ስምምነቱን በተመለከተ ኢትዮጵያ አሁን አሳሳቢ ደረጃ ላይ ትገኛለች፤እኛ አልተቀበልንም ብለን ወደ ኬንያ፣ ኳታር፣ ሳዑዲ አረቢያ፣ በመጨረሻም ወደ ቱርክ ወንድሞቻችን ዞረን አሳውቀናል። በግድ ተቀበሉ የሚሉን ከሆነ እራሳችንን ለመከላከል ዝግጁ ነን” ብለዋል።

@sheger_press
@sheger_press
እጅጉን አሰቃቂ አረመኔያዊ ተግባር ‼️

ተማሪ ሊዲያ ዮሐንስ በጂንካ ዩኒቨርስቲ 3ኛ ዓመት ተማሪ የነበረች ሲሆን ክረምት እረፍት ቤተሰቦቿ ጋ  ካምባ ነበረች።

ወንድ ጓደኛዋ ፍልሞን ጫፍቄ የተባለው አርባምንጭ ከሚገኙት ከአንደኛው ኮሌጅ ተማሪ የነበረ ሲሆን የፊታችን እሁድ ነሐሴ 19/2016 ዓ.ም ተመራቂ በመሆኑ ተማሪ ሊዲያ ከቤተሰቦቿ ሸዉዳ ጂንካ ዩኒቨርስቲ እንደተፈለገች ነግራ ወንድ ጓደኛዋ ጋ አርባምንጭ መጥታ እሱ ተከራይቶ ባለበት ቤት ከሱ ጋር ሆና የምረቃውን ዝግጅት እያዘጋጀች ነበር።

ታዲያ ምን ያደርጋል? ነገሩ እሷ እንዳሰበችው አልሰመረም እንጂ። ሐሙስ ነሐሴ 16/2016 ዓ.ም ቦታው አርባምንጭ ከተማ ጉርባ ቀበሌ ሸለቆ መንደር ከወንድ ጓደኛዋ ጋር ያጋጫቸዉ ምክንያቱ በግልጽ ባይታወቅም ከምሽቱ 7:00 ሰዓት አካባቢ ተመራቂ የነበረው ወንድ ጓደኛዋ ፍልሞን ጫፍቄ

በተማሪ ሊዲያ ዮሐንስ በገዛ ፍቅረኛ ላይ ጨከነ። በተከራየበት ዝግ ቤቱ ዉስጥ በጩቤ ጉንጯ ላይ ወግቷት በመጣል በወደቀችበት አንገቷን ጩቤዉ በእጁ እስኪሰበር ድረስ አረዳት።

ለተማሪ ሊዲያ ዮሐንስ ቤተሰቦች፣ ለጓደኞቿ፣ ፈጣሪ መጽናናትን ይስጣቸው።
በግርማ ግንጫ

@ethio_mereja_news
ፒያሳ የሚገኘው የመብራት ሀይል ህንፃ የንግድ ቤት ኪራይ ጨረታ በካሬ 19ሺ ብር መቅረቡ ተሰማ

በአዲስ አበባ ፒያሳ የሚገኘው የመብራት ሀይል ህንፃ ለንግድ ቤቶች ኪራይ ጨረታ መቅረቡን ተከትሎ በካሬ 19ሺ ብር እየተጫረተ መሆኑን የወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

ይህ የብር ተመን የቀረበው 40 ካሬ ላለዉ ምድር ላይ ለሚገኘው የንግድ ቤት ሲሆን አሸናፊው ቫት እና የጋራ ወለል ኪራይን ሳይጨምር በወር 760 ሺህ ብር ይከፍላልም ተብሏል ።
<< ምላሽ ባለማግኘታችን ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዳግም ደብዳቤ ጽፈናል >> - የኢሰማኮ ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ‼️

ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል፣ የገቢ ግብር ቅነሳ፣ መንግስት አደርገዋለሁ ያለው የደመወዝ ማሻሻያና ተዛማጅ ጉዳዮችን በተመለከተ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ ማስገባታቸውን የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን ገለፀ ።
<< ረሃብ ጊዜ አይሰጥም >> የሚሉት ፕሬዝዳንቱ << መንግስት የደመወዝተኛ ሰራተኛውን የህልውና ጥያቄ እንዲመለስ >> አበክረው ጠይቀዋል።

ባለፈው 2015 ዓመት ነሐሴ መገባደጃ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ(ዶ/ር) ጋር በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ቢወያዩም፣ አቅጣጫ ቢቀመጥም እስካሁን ተግባራዊ ሊሆን አልቻለም።

ይህን ተከትሎ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋዊ ደብዳቤ ዳግም ለመፃፍ መገደዳቸውን የኢሰመኮ ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ ለአሻም ቲቪ ተናግረዋል።

@ethio_mereja_news
በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ የተከሰከሰው የቦይንግ 737 ማክስ 85 አውሮፕላን ከአደጋው በፊት የኤሌክትሪክ ችግሮች እንዳሉበት የሚያሳየውን መረጃ መደበቁን የቀድሞ የቦይንግ ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ።

ፋውንዴሽን ፎር አቪየሽን ሴፍቲ የተባለ ቡድን የሚመሩት የቦይንግ የቀድሞ ሥራ አስኪያጅ ለ157 ሰዎች እልቂት የሆነው እና ከስድስት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ የተከሰከሰው 737 ማክስ 9 አውሮፕላን የኤሌክትሪክ ችግሮች እንዳሉበት በኩባንያው ይታወቅ ነበር ብለዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በዝቅተኛ ከፍታ ላይ ከቁጥጥር ውጭ ሊሆን እንደሚችል እና በርካታ እክሎች እንደነበሩበት ይፋ አድርገዋል።

ፋውንዴሽኑ በአሁኑ ወቅት እየበረሩ ያሉ ከ1000 በላይ የቦይንግ አውሮፕላኖች በሚመረቱበት ወቅት በነበሩ ችግሮች ምክንያት የኤሌክትሪክ ብልሽት ስጋት እንደተጋረጠባቸው ገልጿል።

ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ ጉዞውን በጀመረ በስድስት ደቂቃዎች ውስጥ የተከሰከሰው አውሮፕላን የኤሌክትሪክ ብልሽቶች ነበሩበት ብለዋል።

አውሮፕላኑ በተከሰከሰበት ወቅት አዲስ ሞዴል 737 ማክስ 9 ነበር።

ከዚያ ቀደም ብሎ ተመሳሳይ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን በኢንዶኔዥያው አየር መንገድ አደጋ ተከስክሶ የ189 ሰዎች ሕይወት ተቀጥፏል።(መረጃው የቢቢሲ ነው።)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሰሜን ጎንደር : በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ
የ10 ሰዎች ሕይዎት አልፏል!

ነሐሴ 18/2016 ዓ.ም በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ አብና ቀበሌ ልዩ ስሙ ኖላ በተባለ ቦታ ነሐሴ 18/2016 ዓ.ም በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ በሰው ሕይዎት ላይ ጉዳት ደርሷል።

በአደጋው የ10 ሰዎች ሕይዎት አልፏል ያሉት የጠለምት ወረዳ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተስፋየ ወርቅነህ ናቸው።

ኀላፊው ከአሚኮ ጋር በስልክ በነበራቸው ቆይታ የአራት ሰዎች አስከሬን በፍለጋ ተገኝቷል ብለዋል። የቀሪ ስድስት ሰዎች አስከሬን ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ሊገኝ አልቻለም ነው ያሉት።

በጉዳቱ በስምንት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል ያሉት ኀላፊው በደጃች ሜዳ ጤና ጣቢያ የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ነው ብለዋል።

በመሬት መንሸራተት አደጋው ከ35 በላይ የቤት እንሰሳት ሞተዋል። ከ30 ሄክታር በላይ በሰብል የተሸፈነ መሬት ጉዳት ደርሷል ተብሏል።

እንደ አቶ ተስፋየ መረጃ በደረሰው አደጋ 480 አባውራዎች እና 2 ሺህ 400 የቤተሰብ አባላት ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለዋል። በቀበሌው ማዕከል ወደሚገኙ ማኅበራዊ ተቋማት በጊዜያዊ እንዲጠለሉ መደረጉንም ኀላፊው ጠቁመዋል።

ኀላፊው አያይዘውም በቀጣይም የመሬት መንሸራተት አደጋ ሊከሰትባቸው ይችላሉ በተባሉ የኖላ፣ ላጌ፣ ውፋ፣ ኩዳድ እና ጅብ ዋሻ አካባቢዎች የሚኖሩ ወገኖች ጥንቃቄ እንዲያደርጉም አሳስበዋል።

አሁን ካለው ከባድ የዝናብ ስርጭት አንጻር ማኅበረሰቡ ከጎርፍ እና መሰል አደጋዎች ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት ያሳሰቡት ኀላፊው ለተፈናቃዮች አፋጣኝ የሰብዓዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ነው ያሉት።
@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የTelegram መስራች የሆነው Pavel Durov ታስሯል ‼️

በሰላም እንዲፈታ ፀሎታችን ነው።(ሸገር ክሪፕቶ)

@ethio_mereja_news
ከሸዋ አካባቢ የሚወጡ ፈጣን እና ታማኝ መረጃዎችን እንዲሁም የጦር ግንባር ዜናዎች የምታገኙበት ምርጥ ቻናል

ልጠቁማችሁ👇👇👇
   https://www.tg-me.com/SNN_merja
   https://www.tg-me.com/SNN_merja
ሰበር ዜና

በሊባኖስ የሚገኘዉ ይስራኤል ዋነኛ ባላንጣዉ ሄዝቦላ እስራልን በእሳት አጠባት፡፡

የኢራኑ ሄዝቦላህ እስራኤል ላይ የበቀል ጥቃቱን ዛሬ ለሊቱን መጀመሩን ሁሉም ይወቅልኝ ብሏል። የሄዝቦላህ አለቃ ሃሰን ነስረላህ አሁን የበቀል ሰይፋችን መውረድ ይጀምራል ብለው በቴሌቭዥን መስኮት ብቅ ባሉ በግማሽ ሰዓት ልዩነት ከሊባኖስ ወደ እስራኤል የሮኬት፣ ሚሳኤል እና ድሮን በረዶ ዘንቧል።

ባለፈዉ ወር መጀመሪያ ላይ በቤይሩት አቅራቢያ እስራኤል የሄዝቦላህ የጦር ኮማንደርን ለገደለችበት አፀፋ ነዉ በሚል በዛሬዉ ንጋት ላይ 320 የሚጠጉ ሮኬቶችንና ድሮኖችን አዝንቦ 11 የእስራኤል ወታደራዊ ጣቢያዎችን መምታቱን ዘ ጋርዲያን ዘግቧል፡፡

የሂዝቦላህ ዶፍ መዝነቡን ያየው የእስራኤል አየር ሃይልም በአንድ ግዜ 6 የሚጠጉ አሜሪካ ሰራሾቹን ኤፍ-15 ተዋጊ ጀቶችን ክተት ብሎ ወደ ሊባኖስ ጥሰው በመግባት ሊባኖስን እንደ ደረሰ ሰብል በሚሳኤልና ቦምብ ሲያጭዳት ታይቷል። በዚህ የእስራኤል ጥቃትም 40 የሚጠጉ የሄዝላህ ወታደራዊ ስፍራዎችን ማዉደሙን አስታዉቋል፡፡

የእስራኤል ከፍተኛ ወታደራዊ ቃል አቀባይ ሪር አድሚራል ዳንኤል ሃጋሪ በደቡባዊ ሊባኖስ ውስጥ “በደርዘን የሚቆጠሩ” የጦር አውሮፕላኖች የሄዝቦላህ መሸሸጊያ የሆኑ ኢላማዎችን እየመቱ ነዉ ሲሉ ገልፀዋል።
@ethio_mereja_news
በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ማንኛውም አይነት የስልጣን ሹምሽር አልቀበልም ብሏል!!

በእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት " በማንኛው የሃላፊነት እርከን በራስ ፍላጎት የሚደረግ የስራ ምደባና ሹምሽር ተቀባይነት የለውም " ብሏል።

የእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ህወሓት ለሁሉም የዞንና የወረዳ የድርጅቱ ፅህፈት ጠቅሶ ባሰራጨው ደብዳቤ ፥ " ከሰርዓታዊና ተቋማዊ አሰራር ውጪ የሚካሄዱ የስራ ምደባዎች ኢህጋዊ ብቻ ሳይሆኑ ተጠያቂነትን ያስከትላሉ " ሲል አስጠንቅቋል።

የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ነሃሴ 17/2016 ዓ.ም በህወሓት የፓሊት ቢሮ አባልዋ ወ/ሮ ሊያ ካሳ ምትክ ፀጋይ ገብረተኽለ ገ/ክርስቶስ የደቡባዊ ምስራቅ ዞን አስተዳዳሪ በማድረግ ተሾመዋል።

ነሃሴ 18/2016 ዓ.ም የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ደግሞ በሰሜናዊ ምዕራብ ዋና አስተዳዳሪና በቅርቡ ህወሓት ባካሄደው ጉባኤ የፓሊት ቢሮ አባል ሆነው በተመረጡት ተክላይ ገ/መድህን ምትክ የክልሉ የስፓርት ኮሚሽን ኮምሽነር የነበሩት ተኽላይ ፍቓዱ ተሹመዋል።

@ethio_mereja_news
አሳዛኝ መረጃ‼️

በኢትዮጵያ ፊልም ኢንዱስትሪ በርካታ ፊልሞችን በመስራት የሚታወቀው ተዋናይ ጌታቸው እጅጉ ( ባቡጅ )ትናንት ምሽት ከዚህ አለም በሞት ተልይቷል።

ባቡጂ የሞተው በችግር ምክንያት
እንደሆነ እየተነገረ ነው ።

ለመላው ቤተሠቦቹና ⁠ለአድናቂዎቹ መፅናናቱት ይሰጥልን።

ተዋናይ ጌታቸው እጅጉ ( ባቡጅ )
ነፍስህ በሰላም ትረፍ!!!

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አትሌት ታምራት ቶላ በትውልድ አካባቢው አቀበባል ተደረገለት

በፓሪስ ኦሊምፒክ የወንዶች ማራቶን አሸናፊው አትሌት ታምራት ቶላ በዛሬው ዕለት በትውልድ አካባቢው አሌልቱ ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት።

አትሌቱ በከተማው ሲደርስ የአካባቢው ማህበረሰብ፣ የወረዳው አመራሮችና የአትሌቱ ቤተሰቦች የጀግና አቀባበል አድርገውለታል።

አትሌት ታምራት ቶላ በፓሪስ ኦሊምፒክ በማራቶን ክብረወሰን በማሻሻል ጭምር አሸንፎ ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ ማስገኘቱ ይታወቃል።

በዚህም አትሌቱ የእነ አበበ ቢቂላን፣ ማሞ ወልዴን እና ገዛኽኝ አበራን ታሪክ በመድገም ስሙን ከታላላቆቹ የኦሎምፒክ አሸናፊ አትሌቶች ጎን እንዲመዘገብ ማድረጉ ይታወሳል ሲል ፋና ዘግቧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ቲክቶከሩ ጆን ጨምሮ በሽብር ተከሰሱ‼️

የፌደራል ፖሊስ የአቪዬሸን አሰራርን ጥሰዋል ባላቸው 6 ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብር ወንጀል ምርመራ ጀመረ

የፌደራል ፖሊስ ሰሞኑን ከአዲስ አበባ መቀሌ ለጉዞ በተዘጋጀ አውሮፕላን ውስጥ የአቪዬሸን አሰራርን በጣሰ መንገድ ግርግርና ወከባ በፈጠሩ 6 ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብር ወንጀል ምርመራ መጀመሩን አስታወቀ።
ተጠርጣሪዎቹ ዮሀንስ ዳንኤል በርሄ፣ አማኑኤል መውጫ አብርሃ፣ ናትናኤል ወንድወሰን ሹሜ፣ ኤልያስ ድሪባ፣ ይዲድያ ነጻነት አበበ እና እሌኒ ክንፈ ናቸው።
የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የምርመራ መዝገብ እንደሚያሳየው፥ እነዚህ ተጠርጣሪዎች ተፈጥሮ በፈጠረው የአየር መዛባት ምክንያት አውሮፕላኑ መብረር አይችልም እየተባለ፣ አስገድዶ ለማስኬድ የፈጠሩት አምባጓሮ በወንጀል ሕጉ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል ብሏል።

የፖሊስ የምርመራ ቡድን ተጠርጣሪዎች ላይ በወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ ከተጀመረው ምርመራ ባሻገር፣ ከጸረሰላም ሃይሎች ተልእኮ ተቀብለው የተንቀሳቀሱ በመሆናቸው በሽብር ወንጀልም መጠርጠራቸውን ነው የሚያመላክተው።

በወቅቱ የአየር መንገዱ ከደህንነት ኃይሎች ጋር በመሆን በትዕግስት ቢማጸናቸውም፣ ድብቅ አጀንዳቸውን እያራመዱ በመሆናቸው አሻፈረን ማለታቸውንም በምርመራ መዝገቡ አካቷል።

ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ተግባር መጠቀም ሲገባቸው፣ የሀገር ኩራት እና የራሳቸውን ንብረት የሆነውን አየር መንገድ አንቋሽሸው አሳዛኝ ተግባር ስለመሆኑም የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ገልጿል።

በመሆኑም እነዚህ በቁጥጥር ስር የሚገኙ 6 ተጠርጣሪዎችን ቢሮው በተላለፉት የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ የበረራ አሰራር ጥሰት ብሎም በሽብር ወንጀሎች የምርመራ መዝገብ ነገ ነሀሴ 20/2016 ፍርድ ቤት እንደሚያቀርባቸው ለማወቅ ተችሏል።

@ethio_mereja_news
2024/09/29 21:27:50
Back to Top
HTML Embed Code: