Telegram Web Link
ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ አለም በሞት ከተለዩ 12 አመት ሆኗቸዋል

ከ 12 አመታት በፊት ነሃሴ 14 ቀን የቀድሞዉ ጠ/ሚኒስትር እና የህወሓት ሊቀመንበር የነበሩት መለስ ዜናዊ አስረስ ከዚህ አለም በሞት የተለዩበት እለት ነዉ።

ጠ/ሚኒስትር መለስ ላይ ኢትዮጵያዊያን ሁለት አይነት አመለካከት ያላቸዉ ሲሆን ግማሾች ባለራዕይ ፣ ቆራጥ እና ጀግና መሪ ሲሏቸዉ ግማሾች ኢትዮጵያን የብሔር ፖለቲካ ዉስጥ የከተቱ ፣ ከፋፋይ እና ሴረኛ መሪ ይሏቸዋል።

በጠ/ሚኒስትር መለስ አገዛዝ ዘመን ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ያሳየችበት ፣ የአባይ ግድብ ግንባታ የተጀመረበት እንዲሁም በርካታ ዩኒቨርስቲዎች የተከፈቱበት እና ከቀደመዉ አገዛዝ ለዉጥ የታየበት ነዉ ሲሉ በርካቶች ግን ኢትዮጵያዊ ዛሬ ላይ ጭምር ላለችበት የብሔር ግጭት መሰረት የጣሉ ሰዉ ናቸዉ ይሏቸዋል።

ጠ/ሚኒስትር መለስ በ 2004 ዓ.ም ነበር ከዚህ አለም በሞት የተለዩት። ጠ/ሚኒስትሩ ለ 2 ወራት በህክምና ሲረዱ ቆይተዉ በቤልጂየም ህይወታቸው ማለፉን በወቅቱ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መዘገቡ አይዘነጋም። ጠ/ሚኒሰትሩ በሌሊት ህልፈታቸዉ የተሰማ ሶሆን በኋላ ነሃሴ 14 ቀን 2004 ዓ.ም ነበር በ 57 አመታቸዉ ከዚህ አለም በሞት የተለዩት።

ዉድ የኢትዮ መረጃ ቤተሰቦች ስለ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ምን ያስባሉ?

ጠንካራ እና ባለራዕይ መሪ ናቸዉ? ለምትሉ

ኢትዮጵያ ለገባችበት ቀዉስ ተጠያቂዉ ሰዉ ናቸዉ ለምትሉ 💯

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
" ከተያዘው እቅድ ውጭ እኛ የማናቀውን ስብሰባ ማካሄድ አይቻልም " - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር

በትግራይ ክልል ፣ በመንግስት መስሪያ ቤቶች ጊዚያዊ አስተዳደሩ የማያውቀው ማንኛውም ሰብሰባ ማካሄድ የሚከልክል የስራ መመሪያ ይፋ ተደረገ።

ከትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፅህፈት ቤት በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ፊርማ ለሁሉም
የዞን አስተዳደሮች
ለወረዳ አስተዳደሮች
የክፍለ ከተማ አስተዳደሮችና
የወረዳ ምክር ቤቶች 
የተላከው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው ጊዚያዊ አስተዳደሩ ከፈቀደው ውጪ ሌላ ስብሰባ ማካሄድ አይቻልም ይላል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አስገራሚዉን የሳዉዲ መሪ እና ኢየሱስ ክርስቶስ መሳጭ ታሪክ
ይከታተሉ👇👇👇

https://www.youtube.com/watch?v=OITegUo0qVI
የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር (ኢመደአ) 3ኛውን የሳይበር ደህንነት የሰመር ካምፕ ፕሮግራም በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አስጀመረ።

በሰመር ካምፕ ፕሮግራሙ ከመላው የኢትዮጵያ ክፍል የተውጣጡ በቁጥር ሦስት መቶ (300) ታዳጊ ወጣቶች ተሳታፊ እንደሆኑ በማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ ተገልጿል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ክብርት ወ/ሮ ትዕግስት ሃሚድ እንደገለጹት ኢመደአ ተቋማዊና ሀገራዊ ተልዕኮውን በብቃት ለማሳካትና ቀጣይነት ያለው ሀገራዊ የኢንፎርሜሽን ደህንነትን ለማረጋገጥ የታዳጊዎችን ታለንት ወጥ በሆነ መንገድ መመልመል፣ ማልማት እና መጠቀም ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነ በመገንዘብ ከተቋሙ ምስረታ ጀምሮ ሲሰራ መቆየቱን ተናግረዋል።

የዲጂታል እድገት ይዞት የመጣውን ዕድል ለሀገር ልማትና ዕድገት ለማዋል በሳይበር ደህንነት ዘርፍ ልዩ ተሰጥዖ ያላቸውን ታዳጊ ወጣቶችን መለየትና ማብቃት ወሳኝ መሆኑን ያነሱት ዋና ዳይሬክተሯ፤ በዚህ ረገድ ኢመደአ ከ2014 ዓ.ም ጀምሮ የሳይበር ታለንት የሰመር ካምፕ ፕሮግራም በየአመቱ በማዘጋጀት ሥልጠናዎችን እየሰጠ መሆኑን አስታውሰዋል።

በዚህም በ2016 ዓ.ም ለሦስተኛ ጊዜ የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ ፕሮግራም ማዘጋጀቱን ገልጸው፤ በተለይም የዘንድሮው የሰመር ካምፕ ፕሮግራም ካለፉት ሁለት አመታት ከተዘጋጁት ፕሮግራሞች በቁጥርም ሆነ በተደራሽነት ከፍ ያለ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የ3ኛ ዙር የሰመረ ካምፕ ተሳታፊዎች በሰመር ካምፕ መርሃ ግብሩ ከሚሰጣቸው ስልጠና ባሻገር በሀገር አቀፍ ደረጃ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ በይፋ የተጀመረዉን “የ5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደርስ ኢኒሼቲቭ” ስልጠናዎችን በመውሰድ ፋና ወጊ መሆናቸውን የገለጹት ዋና ዳይሬክተሯ፤ ይህንንም መነሻ በማድረግ ሌሎች የኢትዮጵያ ታዳጊ ወጣቶች የኢኒሼቲቩ አካል እንዲሆኑና ስልጠናዎችን እንዲወስዱ አምባሳደር በመሆን ሊሰሩ እንደሚገባ መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

በሰመር ካምፕ ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት የአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ደረጀ እንግዳ በበኩላቸው የዩኒቨርሲቲው ዋና ተልዕኮ የሆነውን የሳይንስና ቴክኖሎጂ ስርፀት ሥራ በአግባቡ በማከናወን ረገድ ከኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በጋራ መስራት ወሳኝ ጉዳይ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡

በተመሳሳይ በሰመር ካምፕ ማስጀመሪያ መርሃ ግብሩ ላይ የተገኙት ላይ የተገኙት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከስተመር ኤክስፔሪያንስ ም/ፕሬዚዳንት አቶ ኃየለእየሱስ በቀለ ባስተላለፉት መልዕክት በተለያዩ ዘርፎች ማህበራዊ ኃላፊነቱን በመወጣት የሚታወቀው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ለሃገር ትልቅ አስተዋፅኦ የሚያበረክቱ የፈጠራ ሥራዎችንም በፋይናንስ ይደግፋል ብለዋል፡፡

በዚህም ኢመደአ የጀመረውን የሳይበር ታለንት ልማት ፕሮግራም በቀጣይነት በመደገፍና በጋራ በመስራት ለዘርፉ እድገት የበኩላችንን ሚና እንወጣለን ብለዋል፡፡

የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር በ2014 ዓ.ም ባካሄደው የመጀመሪያ ዙር የሳይበር ታለንት ሰመር ካምፕ ፕሮግራም 60 ታዳጊ ወጣቶችን፤ በ2015 ባካሄደው ሁለተኛ ዙር ደግሞ 120 ታዳጊ ወጣቶች አሰልጥኖ አስመርቋል፡፡

ዘንድሮም በ2016 ዓ.ም በሀገር አቀፍ ደረጃ በተከናወነ የሳይበር ታለንት ቻሌንጅ ፕሮግራም ከተመዘገቡ ከ6 ሺ በላይ ባለ ልዩ ተሰጥኦዎች መካከል የተለያዩ ፈተናዎችን በማለፍ በቁጥር ሦስት መቶ (300) የሚሆኑ ባለ ልዩ ተሰጥዎ ታዳጊ ወጣቶች የሰመር ካምፕ ፕሮግራሙ ተሳታፊ ሆነዋል
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለሔቨን እናት የመኖሪያ ቤት እና ሥራ አመቻቸ!!

የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አቤቤ የ7 ዓመት ልጇን ሔቨን በግፍ ተነጥቃ ባለፈው አንድ ዓመት ተገቢ ፍትህ ሳታገኝ ለቆየችው ሲስተር አበቅየለሽ የከተማ አስተዳደሩ አንድ የመንግስት የመኖሪያ ቤት እንዲሁም በሙያዋ እዚሁ አዲስ አበባ ውስጥ እንድትሰራ መመቻቸቱን ገልጸዋል።

የፍትህ ሂደቱን ለመከታተል ፣ ያለችበት ሁኔታ የተሻለ እንዲሆንላት እና ተጋላጭነቷን ለመቀነስ እንዲመች የከተማ አስተዳደሩ ድጋፉ ማድረጉንም ነው የገለጹት።

"የህፃን ሄቨን ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ በመሆኑ ድርጊቱ ተገቢውን ፍትህ ማግኘቱ የሌሎች ህፃናት ተጋላጭነትን ለመቀነስ አስተዋፅዖ ያለው ነው" ሲሉ ከንቲባዋ ተናግረዋል።

አክለውም፥ የዚህ አይነት ጭካኔ የተሞላበት ድርጊት እንዳይፈፀም የማህበረሰቡ የአመለካከት ለውጥ እንዲመጣ እና ችግሩ የጋራ ጉዳይ በመሆኑ ሁላችንም ኃላፊነታችንን ልንወጣ ይገባልም ብለዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ከኢትዮጵያ ኢንሳይደር
ለቀረበላቸው ጥያቄ የሰጡት ምላሽ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን ለመምራት ህወሓት "የራሱን ሰዎች መመደብ ይችላል" ሲሉ ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ተናገሩ። አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመሩት ቡድን "አሁን ህወሓትን መወከል አይችልም” ብለዋል።

ዶ/ር ደብረጽዮን ሊቀመንበር ሆነው የተመረጡበት እና ከትላንት በስቲያ ሰኞ የተጠናቀቀው የህወሓት 14ኛ ጠቅላላ ጉባኤ በምርጫ ቦርድ እውቅና አልተሰጠውም። የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ 14 የህወሓት ማዕከላዊ ኮሚቴ አባላትም አልተሳተፉም።

ዶ/ር ደብረጽዮን ሊቀመንበር ሆነው ከተመረጡ ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ ጋዜጣዊ መግለጫ በሰጡበት ወቅት ከ"ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙበት ትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር “ህወሓትን ወክሎ ነው የገባው። አሁን ህወሓትን መወከል አይችልም” ሲሉ ተናግረዋል።

በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር "የህወሓት ሰዎች መመደብ አለባቸው" ያሉት ዶ/ር ደብረጽዮን በጉዳዩ ላይ ጊዜያዊ አስተዳደሩን "ካቋቋሙ ወገኖች ጋር ውይይት ያስፈልጋል” ብለዋል። በጊዜያዊ አስተዳደሩ ውስጥ ከህወሓት በተጨማሪ የትግ ራይ ሠራዊት፣ ምሁራን እና ተቃዋሚው ባይቶና ድርሻ አላቸው።

በጉዳዩ ላይ ከፌድራል መንግስት ጋር ውይይት ማድረግ እንደሚያስፈልግ የጠቆሙት ዶ/ር ደብረጽዮን" እኛ ትግራይ ውስጥ ብቻ የምንጨርሰው አይደለም" ሲሉ ለ"ኢትዮጵያ ኢንሳይደር" አስረድተዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሰበር መረጃ‼️

የእነ ደብረፅዮን ቡድን ጊዚያዊ አስተዳድሩን ለመተካት እንቅስቃሴ ጀመረ‼️

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደርን ለመምራት ህወሓት " የራሱን ሰዎች መመደብ ይችላል " ሲሉ የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል ለሚዲያዎች ተናገሩ።

አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመሩት ቡድን " አሁን ህወሓትን መወከል አይችልም ” ብለዋል።

ሊቀመንበሩ ፤ አቶ ጌታቸው ረዳ የሚገኙበት ትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር " ህወሓትን ወክሎ ነው የገባው። አሁን ህወሓትን መወከል አይችልም " ሲሉ ተናግረዋል።

በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር " የህወሓት ሰዎች መመደብ አለባቸው " ብለው በጉዳዩ ላይ ጊዜያዊ አስተዳደሩን " ከፌዴራል መንግሥቱ ጋር ውይይት ያስፈልጋል " ብለዋል።

በጊዜያዊ አስተዳደሩ ውስጥ ከህወሓት በተጨማሪ የትግ ፐራይ ሰራዊት፣ ምሁራን እና ተቃዋሚው ባይቶና ድርሻ አላቸው።

በጉዳዩ ዙሪያ ከፌድራሉ መንግስት ጋር ውይይት ማድረግ እንደሚያስፈልግ ጠቁመው ፥ " እኛ ትግራይ ውስጥ ብቻ የምንጨርሰው አይደለም" ሲሉ ተናግረዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ህፃን ሄቨንን ደፍረሀል ተብሎ የተፈረደበት ጌትነት ሚስት ፍትህ ለባሌ ፍትህ ይሰጠኝ በማለት ላይ ትገኛለች።

* የምርመራ ውጤቱ ተደፍራለች
ብሎ ጌትነትን 25 ዓመት ፈርዶበታል

ሰሞኑንም ይግባኝ ጠይቋል.....

የጌትነት ሚስት አሁን ደሞ :-

* ሄቨንን ባሌ አልደፍራትም
እያለች ይገኛል::

ህክምና ማስረጃው

* ታ ን ቃ
* ተ ደ ፍ ራ ነው የሞተችው ይላል ?

አንቺ ምን ትያለች ?

የጌትነት ሚስት : - ሄቨን ወድቃ ነው የሞተችው

ኢንተርቪውን እንዴት እያችሁት (sheger press)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ብርታኒያ በአማራና ኦሮሚያ ክልሎች የቀጠሉት ግጭቶች በሲቪሎች ላይ ያስከተሉት ከባድ ተጽዕኖ እንደሚያሳስባት ገለፀች‼️

ብሪታንያ ይህን ስጋቷን የገለጠችው፣ የዓለማቀፍ ልማት ሚንስትሯ አኔሊሴ ዶድስ ሰሞኑን በአዲስ አበባ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት አገራቸው ለኢትዮጵያ ሰላምና ጸጥታ በምትሰጠው ድጋፍ ዙሪያ ከውጭ ጉዳይ ሚንስትር ታዬ አጽቀሥላሴ ጋር በተወያዩበት ወቅት ነው።

ሚንስትሯ፣ ሁሉም የግጭቶች ተሳታፊ ወገኖች ግጭቶችን እንዲያበርዱና በሰላማዊና አካታች ንግግር ግጭቶችን እንዲፈቱ ጠይቀዋል።

ሚንስትሯ፣ በሱማሊያ፣ ሱዳንና ደቡብ ሱዳን ሰላምና ጸጥታ ጉዳዮች ዙሪያ ከአፍሪካ ኅብረት ባለሥልጣናት ጋር ተወያይተዋል።
#ዋዜማ

@sheger_press
@sheger_press
የጆን ዳንኤል Live ጉዳይ,‼️

" "እቀርፅሀለው"... "ላይቭ እያስተላለፍኩት ነው"

ስለ አቪዬሽን አሰራር በቅርበት ስለምከታተል አንዳንድ ነገሮች ይገቡኛል ብዬ አስባለሁ፣ እናም በአንድ የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ውስጥ ስለተከሰተ ድርጊት የሚሰራጨውን ቪድዮ አይቼ ይህን ማለት ወደድኩ።

በወቅቱ ተሳፋሪዎች ላይ ዛቻ፣ ድብደባ፣ ማዋከብ እና ማስፈራራት ከነበረ ስህተት ነው።

ከዛ ውጪ ግን የካቢን ክሪው ለመብረር አደጋ አለው ብሎ ካመነ በረራውን የማቆየት እና የመሰረዝ ሀላፊነት አለበት። ተጓዦች ብዙ ሰዓት አውሮፕላን ውስጥም ሆነ ተርሚናል ውስጥ ቆይተው ተጉላልተው ይሆናል፣ ግን በተለይ ከትናንት ጀምሮ እንደሰማነው አይነት ጭጋግ ከተከሰተ አየር መንገዱ ቅድሚያ የሚሰጠው ለደህንነት ነው።

"እቀርፅሀለው"... "ላይቭ እያስተላለፍኩት ነው" በማለት ለማስፈራራት መሞከሩ ዋጋ የለውም፣ እንደውም ያልተለመደ የበረራ ደህንነት ሴክዩሪቲዎች ትዕግስት ገርሞኛል።

በአንድ ወቅር ከፍራንክፈርት ወደ ለንደን በነበረኝ በረራ ላይ አብራሪዎችን መነሻ ሰዓት አዘገያችሁ ብሎ ግርግር የፈጠረ አንድ ተጓዥ እንዴት አንጠልጥለው እንዳስወጡት አስታውሳለሁ።

አየር መንገዱም ሆነ ኤርፖርት ውስጥ የሚፈፀሙ ህገወጥ ድርጊቶችን ደጋግሜ አንስቻለሁ፣ አንዳንዶቹ ላይም ማስተካከያ ተደርጓል። ግን እንዲህ አይነት አምቧጓሮም ተገቢነት የለውም።

ለተሳፋሪ ደህንነት ሲባል በረራ አይደረግም ከተባለ በቃ፣ እዛ ጋር አበቃ። የትም አለም ላይ ያለ አሰራር ነው።"

via Elias Mesert

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
🌎 🛑 🗣 "በስናይፐር ይጠበጠባል"‼️


#Ethiopia | አትሌት ገዛኸኝ አበራ ደራርቱ ቱሉ"የአትሌቲክስ አመራሩን በሀይል የሚሞክር በስናይፐር ይጠበጠባል" ማለቷን ተከትሎ ዝምታውን ሰበረ‼️

👉"ከደራርቱ የስናይፐር ንግግር በኋላ የእኔም የቤተሠቤም ህይወት ስጋት ውስጥ ወድቋል"

👉"የምወዳት እህቴ እንደዚህ ጨክና [በስናይፐር ይጠበጠባል] ያለችው በጤናዋ ነው? ... ህመም ገጥሟት? የሚለውም በጣም እየረበሸኝ ነው"

👉"[በስናይፐር ይጠበጠባል] ብላ ሞት ብትፈርድብኝም ዛሬም ለደሩ ትልቅ ክብር አለኝ"
👇

"...ዕውነት ለመናገር ለቀናቶች ራሴን አላውቅም፤ በጣም በተረበሸና በተዘበራረቀ ስሜት ውስጥም ነበርኩ፤ ወደ ጆሮዬ ደጋግሞ የሚመጣው ድምፅ በጣም የምወዳት እህቴ የደሩ [በስናይፐር ይጠበጠባል]የሚለው አስፈሪ ሞትን የሚሠብክ ድምፅ ነው፤

ቪዲዮውን በተለይ ደራርቱ ስለእኔ ከስናይፐር ጋር አያይዛ የተናገረችው ዕውነት ቢሆንም ለእሷ ካለኝ ክብር የተነሳ የሆነውን አምኜ ላለመቀበል አእምሮዬን ለመዋሸት ብሞክርም አልተሳካልኝም፤ምነው ቀልድ በሆነና ውሸት ነው በተባለ ብዬ እስከመመኘት ሁሉ ደርሻለሁ፤ እኔ ብቻ ሳልሆን ባለቤቴ እልፏ(አትሌት እልፍነሽ ዓለሙ)፣ልጆቼም፣ዘመድ ጓደኞቼም አምነው መቀበል አልቻሉም፤ ክፉኛም ተረብሸዋል፣ ተጨንቀዋል።

ከመረበሽ ስጋት ውስጥ ከመውደቃቸው የተነሳም ለማመን ተቸግረው [በእርግጥ ይሄ ቃል የወጣው የእኛ ከሆነችው ደራርቱ ቱሉ ነው?] ብለው የሠሙበትን ጆሮ ተጠራጥረው በጥያቄ እያስጨነቁኝ ነው፤ ወጥቼ እስከገባ በልጆቼና በቤተሠቦቼ ላይ የተፈጠረውን የስነ-ልቦና ጉዳትን መግለፅ ይከብደኛል፤ በቃ በአጭሩ የደሩ [በስናይፐር ይጠበጠባል] የቪዲዮ ንግግር የእኔንም የቤተሠቦቼንም ሠላም አናግቶቷል፤ እኔም ሠላሜን አጥቼ በደመነፍስ ነው የምንቀሳቀሠው ማለት እችላለሁ።

ከሁሉም በጣም የገረመኝ ቪዲዮው ከተለቀቀ በርካታ ቀናት ቢነጉዱም እህቴ ደራርቱ በሆነ ነገር ተገፋፍቼ ነው በጣም ይቅርታ ወይም አምኜበት ነው የተናገርኩት ብላ አለመተንፈሷ ነገሩን የበለጠ አክብዶብኛል። "

👉ይህንን ከላይ ያለውን ቃል በጣም በተሠበረና ቁጭት በተሞላበት ስሜት ለመጀመሪያ ጊዜ በተለይ ለሀትሪክ ስፖርቱ ጋዜጠኛ ይስሀቅ በላይ የተነፈሠው የቀድሞ አትሌትና የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት የሆነው ገዛኸኝ አበራ ነው።

አትሌት ደራርቱ ቱሉ እሷን በማይገልፅና በማይመጥናት ቦታ ውስጥ ሆና ተናገረችው የተባለው ቪዲዮ በአክቲቪስቱና ደፋሩ ጋዜጠኛ ስዩም ተሾመ "ነፃ ሀሳብ" የዩቲዩብ ቻናል ከተለቀቀ በኋላ ብዙዎች የሰሙበትን ጆሮ እስከመጠራጠር ከመድረሳቸው ሌላ ለከፋ ሀዘንም ተደርገዋል።

በተለይ ለጀግናዋና ብርቅዬዋ አትሌት ከፍ ያለ ክብርም፣ ፍቅርም የነበራቸው ሠዎች በደራርቱ ንግግር ልባቸው ሲሰበር የሞት ፍርድ የተፈረደበት የሚመስለውን ሌላኛውን ጀግና አትሌት ገዛኸኝ አበራን ደግሞ በማፅናናትና አጋርነታቸውን አሳዩ።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በአማራ ክልል በፋኖ እና በመከላከያ መካከል እየተደረገ ያለዉ ዉጊያ እንደቀጠለ ነዉ፡፡ ዘገባዎችን በሚዛናዊነት የምታቀርበዉን የShewa News Network የፌስቡክ ገፅ ይቀላቁሉ
👇👇
በየሰአቱ የግንባር መረጃዎችን የምታወጣዉን የ Shewa News Network የፌስቡክ ገፅ ይከታተሉ ፡፡👇👇
https://www.facebook.com/profile.php?id=61564988365778&mibextid=ZbWKwL
ህጻን ሄቨን አወትን አስመልክቶ ሲሰጥ የነበረ ጋዜጣዊ መግለጫ፤ በፖሊሶች እንዲቋረጥ ተደረገ

የአስገድዶ መድፈር ወንጀል ከተፈጸመባት በኋላ የተገደለችውን ህጻን ሄቨን አወትን በተመለከተ፤ በዛሬው ዕለት ሲሰጥ የነበረ ጋዜጣዊ መግለጫ በፖሊሶች እንዲቋረጥ መደረጉን የአይን እማኞች እና የመርሃ ግብሩ አስተባባሪ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገለጹ። ጋዜጣዊ መግለጫው እንዲቋረጥ የተደረገው፤ “ፍቃድ ያልተጠየቀበት ፕሮግራም ነው” በሚል ምክንያት ነው ተብሏል።

በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው ኢሊሌ ሆቴል የተዘጋጀውን ጋዜጣዊ መግለጫ እና የሻማ ማብራት መርሃ ግብር ያዘጋጁት፤ የኢትዮጵያ ሴቶች ማህበራት ቅንጅት (ኢሴማቅ) እና ዘመቻ በጾታዊ ጥቃት ኢትዮጵያ አባል ድርጅቶች በጋራ በመሆን ነው። መርሃ ግብሩ የተዘጋጀላት ህጻን ሄቨን የአስገድዶ መድፈር እና ግድያ የተፈጸመባት፤ በባህር ዳር ከተማ፤ ቀበሌ 14 ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሐምሌ 25፤ 2015 ዓ.ም ነበር።

ወንጀሉ “ከአሰቃቂነቱ እና የህጻንዋን ህይወት እንዲያልፍ ከማድረጉ ባለፈ፤ በህጻናትና በሴቶች አካላዊ እና ስነልቦናዊ ደህነንት ላይ ከፍተኛ ስጋት የሚያደርስ በመሆኑ ትኩረት የሚሻ” መሆኑን ኢሴማቅ ገልጿል። የማህበራት ቅንጅቱ ለመገናኛ ብዙኃን በላከው ደብዳቤ ላይ፤ ዛሬ አርብ ነሐሴ 17፤ 2016 የተዘጋጀው መርሃ ግብር “በተፈጸመው አሰቃቂ ድርጊት” የተሰማቸውን ሀዘን ለመግለጽ እንዲሁም ለሟች ህጻን ቤተሰቦች ድጋፋቸውን ለማሳየት እንደሆነ አመልክቷል።

ከዚህ በተጨማሪ በወንጀል ፈጻሚው ላይ “ፍትህ እንዲሰፍን” በማሰብ፤ “የድርሻቸውን ለመወጣት” የዛሬውን መርሃ ግብር ማዘጋጀታቸውንም ጠቁመዋል። ይህን አላማ በመያዝ የተጀመረው የዛሬው መርሃ ግብር አካል የሆነው ጋዜጣዊ መግለጫ ከተጀመረ ከ30 ደቂቃ በኋላ “ሲቪል በለበሱ ሰዎች እና ፖሊሶች” እንዲቋረጥ መደረጉን ሁለት የአይን እማኞች ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጸዋል።

@ethio_mereja_news
በኦሮሚያ ክልል በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ባንዳንድ ወረዳዎች የመንግሥት ኃይሎች ከኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት ጋር በሚያደርጉት ውጊያ ሳቢያ ሲቪሎች አኹንም እየተገደሉ እንደኾነ ዶይቸቨለ ነዋሪዎችን ጠቅሶ ዘግቧል።

ቀርሳ ማሊማ፣ ሰደን ሶዶ፣ ቶሌ እና አመያ በተባሉ ወረዳዎች ነሐሴ ከገባ ወዲህ ብቻ 17 ያህል ሲቪሎች መገደላቸውን መስማቱን ዘገባው አመልክቷል።

በተለይ ታጣቂዎች የአርሶ አደሮችን ቤቶች የማቃጠል፣ ከብቶችን የመዝረፍ፣ የእገታ እና አፈና ድርጊቶችን ይፈጽማሉ ተብሏል።

በግጭቱ ሳቢያ ባብዛኞቹ ወረዳዎች የትራንስፖርት አገልግሎቶች እንደተቋረጡ ነዋሪዎች ተናግረዋል ተብሏል።

@ethio_mereja_news
ሴት መስሎ ሲንቀሳቀስ በ11 ወራት ውስጥ ለ3ተኛ ጊዜ ተያዘ‼️

በመስከረም ወር 2016ዓ.ም በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ ሴት መስሎ፣እንደ ሴት ተኳኩሎ፣ ጡት ማስያዣ አድርጎ፣ የፈረስ ጸጉር ቀጥሎ፣ ያታለለው ወጣት  በሌላ ስፍራ ለሶስተኛ ጊዜ መያዙን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

ከ11 ወራት በፊት ሴት በመምስል በዲማ ወረዳ ተቀጥሮ 2 ቀን ስራ እየሰራ እንዳለ በሰራተኞቹ ጥቆማ ተይዞ እንዲታሰር ቢደረግም ዳግም በተግባሩ ቀጥሎበት እንደነበር ዘገባው አስታውሷል።

በትክክለኛ መጠሪያ ስያሜው ቢንያም ከበደ በወቅቱ እንዲለቀቅ ቢደረግም ከእዚያ ድርጊት ስድስት ወራት በኋላ በመጋቢት ወር 2016ዓ.ም በሸካ ዞን አንድራቻ ወረዳ ጌጫ ከተማ  ሴት ነኝ ብሎ ህብረተሰቡን ሲያታልል ነበር ለ2ኛ ጊዜ ተይዞ እንዲታሰር የተደረገው።

በሁለቱ አከባቢዎች (በጋምቤላ ከተማ እና  በሸካ ዞን አንድራቻ ወረዳ ጌጫ ከተማ) በቁጥጥር ስር እንዲውል ተደርጎ የነበረው ወጣቱ ቢንያም በአሁኑ ወቅት ደግሞ በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ለሶስተኛ ጊዜ እንደ ሴት  በመሆን ቀሚስ ለብሶ፣ ጡት ማስያዢያ አድር እና  ዊግ በጭንቅላቱ አስሮ ሲንቀሳቀስ በቁጥጥር ስር መዋሉን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ገልጿል።

ግለሰቡ አንድ ዓመት ባልሞላ ጊዜ ውስጥ ቦታ እየቀያየር ድርጊቱን ሲፈፅም በካፋ ዞን ቦንጋ ከተማ ላይ መያዙ ሶስተኛው እንዲሆን አድርጎታል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/09/29 23:21:58
Back to Top
HTML Embed Code: