Telegram Web Link
ከሕወሓት ጠቅላላ ጉባዔ ራሳቸውን ያገለሉ የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴና የቁጥጥር ኮሚሽን አባላትና ሌሎች አካላት ትናንት መቀሌ ውስጥ "ሕወሓትን ለማዳን" ያለመ ምክክር አድርገዋል።

ምክክሩ፣ ግጭት ሊቀሰቅሱ የሚችሉ የውስጥና የውጭ ሴራዎችን በጽኑ እንደሚያወግዝ ገልጦ፣ በመደናገር በፓርቲው ጉባዔ በመሳተፍ ላይ የሚገኙ የፓርቲው አባላት ከሕዝቡ ጎን እንዲቆሙ ጠይቋል።

የማዕከላዊ ኮሚቴና የቁጥጥር ኮሚሽን አባላቱ ምክክሩን ያደረጉት፣ ምርጫ ቦርድ ዕውቅና የነፈገው ጉባዔ በፓርቲው ስም ማናቸውንም እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ ባገዳቸው ማግስት ነው።

@sheger_press
ገንዘብ ሚንስቴር ያለ ውጭ ምንዛሬ ክፍያ ዕቃዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ ፈቅዷል‼️

የነዳጅ አውቶሞቢሎች እና ከፀጥታና ከደህንነት ዕቃዎች ውጪ ወደ አገር እንዳይገቡ በሕግ ክልከላ ከተደረገባቸው ዕቃዎች ያለ ውጭ ምንዛሬ ክፍያ (በፍራንኮ ቫሉታ) ወደ አገር እንዲገቡ መፈቀዱን የገንዘብ ሚኒስቴር አሳውቋል።

ውሳኔው የተላለፈው መንግሥት በቅርቡ ተግባራዊ ያደረገው የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያው፤  የገቢ ንግዱን በይበልጥ እንዲያሳልጥ መሆኑን የገንዘብ ሚኒስቴር ለጉምሩክ ኮሚሽን በጻፈው ደብዳቤ አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ከተከለከሉት ሁለቱ በስተቀር ያለ ውጭ ምንዛሬ ክፍያ (በፍራንኮ ቫሉታ) ዕቃዎች ወደ ሀገር ውስጥ እንዲገቡ  በመንግስት የወሰነ መሆኑን በመጥቀስ ተግባራዊ እንዲደረግ አሳስቧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሁሉም ነገር አሳዛኝ ነዉ

በአማራ ክልል በመንግስት እና በፋኖ ሀይሎች መካከል እየተደረገ ያለዉ ዉጊያ ሰሞኑን ተባብሶ ቀጥሎል ፡፡

የአማራ ክልል የመረጃ ምንጮች እንደሚሉት ከሆነ በሰሞኑ ከፍተኛ ዉጊያ ከሁለቱም የአንድ ሀገር ወጣቶች ከፍተኛ ሰበአዊ እልቂት እንዳስተናገዱ ነዉ ፡፡

በጎጃም በጎንደር እና ሰሜን ሸዋ ባገረሸዉ ዉጊያ በአንድ በኩል ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ የመንግስት ሀይሎች ሲገደሉ እንዲሁም ለታጣቂዎቹ እጃቸዉን ሲሰጡ መከላከያ ወሰደ በተባለ አፀፋዊ ርምጃ በተመሳሳይ የፋኖ ሀይሎችም ተመሳሳይ እጣ ፈንታ ደርሶቸዋል፡፡

አንድ ስማቸዉ እንዳይጠቀስ ያሉ በጎጃም የሚኖሩ ገበሬ ስለ ሰሞኑ ሁነት ሲገልፁ' 'በኛ አካባቢ ለ ስድስት ሰአት የፈጀ ደም አፋሳሺ የጨበጣ ዉጊያ ድረስ የተደረገ ጦርነት ተካሂዶ ተኩሱ በረደ ብለን ከቤታችን ስንወጣ ማሳችን ሙሉ ለሙሉ በሬሳ ተጥለቅልቆ ነዉ የጠበቀን የመንግስትም ይሁን የፋኖ ወታደሮች ወድቆል ሲሉ ገልፀዋል'

ሰላም ለሀገራችን ሰላም ለኢትዬጲያ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ህወሓት ምርጫ አካሂዷል

ዶ/ር ደብረጽዮን ገብረሚካኤል የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሊቀመንበር ሆነው በድጋሚ ተመረጡ።

-አቶ አማኑኤል አሰፋ አቶ ጌታቸው ረዳን በመተካት የፓርቲው ምክትል ሊቀመንበር ሆነው ተመርጠዋል።

ህወሓት ሁለቱን የፓርቲውን ከፍተኛ አመራሮች ምርጫ ያደረገው ላለፉት ስድስት ቀናት በመቐለ ከተማ ሲያደርገው የነበረውን አወዛጋቢ ጠቅላላ ጉባኤ በዛሬው ዕለት ሲያጠናቅቅ ነው። በዛሬው የጉባኤ ውሎ፤ ዘጠኝ አባላት ያሉበት የህወሓት ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ምርጫም ተከናውኗል።

ፓርቲው ከስድስት ዓመት በፊት ባከናወነው ጉባኤ ከመረጣቸው የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባላት ውስጥ በአሁኑ ምርጫ የተካተቱት ዶ/ር ደብረጽዮን፣ ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚያብሔር እና ዶ/ር አብርሃም ተከስተ ብቻ ናቸው። ከጠቅላላ ጉባኤው ራሳቸውን ያገለሉት አቶ ጌታቸው ረዳ እና አቶ ጌታቸው አሰፋን ጨምሮ 6 የፖሊት ቢሮ አባላት በአዲስ ተመራጮች ተተክተዋል።

(ኢትዮጵያ ኢንሳይደር)

@ethio_mereja_news
‘’ዛላንበሳ ጨምሮ በኤርትራ ሰራዊት በተያዙ የኢሮብ አካባቢዎች ነዋሪዎች ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰባቸው ነው’’ ሲል የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የመቀሌ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ‼️
በዛላንበሳን ጨምሮ በኤርትራ ሰራዊት እጅ በሆኑ የኢሮብ አካባቢዎች አገልግሎት መስጠት እንዳልቻለ ጽሕፈት ቤቱ አስረድቷል፡፡

‘’የፌደራል መንግስት እና በሃወሃት መካከል ተደርጎ በነበረው ጦርነት ምክንያት በኤርትራ ሰራዊት እጅ የገቡ አካባቢዎች ባለመለቀቃቸው የአካባቢው ተወላጆች ላይ ችግር እየደረሳባቸው’’ እንዳለ የጽሕፈት ቤቱ ሃላፊ ፀሃዬ እንባዬ ተናገረዋል፡፡

በኢሮብ የነበረው የባንክ፣ የስልክ  እና መሰል አገልግሎት በጦርነቱ ወቅት ከተቋረጠ ወዲህ ዳግም አልተመለሰም ተብሏል፡፡

በዚህም ምክንያት ‘’በኤርትራ ሰራዊት እጅ ባሉ እና ከኢሮብ አካባቢ ወደ አዲግራት እንዲሁም ጎረቤት ከተሞች 100 ኪ.ሜ ለማይሞላ መንገድ 600 ብር እየከፈሉ’’ እንደሆነ ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

በተያዙ አካባቢዎች ያሉ ትምህርት ቤቶች እና የጤና ተቋማት እስካሁን ከአገልግሎት ውጭ ናቸው፡፡
ሸገር

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
እንዲህም ሆኗል‼️
የጭካኔ ጥግ😭😭 ነው‼️

እናት 4ህፃናት ልጆቿን እንጀራ ለማጉረስ ሁሌም ለሊት 12:00ሰዓት ከቤት ወጥታ ካገኘች የቀን ስራዋን ሰራርታ ማታ 12:00ሰዓት ትመለሳለች!!

ግንበኛው አባት ደግሞ አረፋፍዶ ጠዋት 2:00ሰዓት ከቤት ይወጣና ስራውን ሰርቶ እንደጨረሰ እሱም ወደ ልጆቹ ይመለሳል!!

በአንደኛው ክፉ ቀን እናት እንደተለመደው በለሊት መውጣቷን ተከትሎ አባት የ14ዓመቷ የ6ተኛ ክፍል ተማሪ የመጀመሪያ ሴት ልጁን

"አባዬ እባክህ ተወኝ"

እያለችው አስችሎት በተኛችበት በጭካኔ ደፈራት!

ህፃኗ ልጅ መናገር እየፈራች ስቃይዋን እንደምንም ችላ ብትኖር በድጋሚ የእናት መውጫ ሰዓት ጠብቆ አንገላቶ ደፈራት!!

በጣም ፈሪ፣ምንም አይነት የወንድ ጓደኛ የሌላት ሴት ከወራት በኋላ በአካባቢና ጎረቤት ውትወታ ሰትመረመር ምንም የማታውቀው የ14ዓመት ህፃን

የ3ወር እርጉዝ ነሽ" ተባለች!አማራጭ ስላልነበራት ሁሉንም ለፖሊስ ተናገረች!!

አረመኔው አባት እስር ቤት ገብቶ ፍርድ ቤት ቆሞ 18ዓመት ቢፈረድበትም

ህፃኗ ከአባቷ ያረገዘችውን ጨቅላ ወልዳ ጡት ማጥባት ስላልቻለች የአንድ አመት ልጅ ያላት እናቷ እያገዘቻት በደሳሳ ጎጆአቸው ውስጥ በስቃይ እየኖሩ ይገኛል!

አባትም በእስር ቤት እየተቀለበ
ሙያ እየተማረ በህይወት እየኖረ ይገኛል!!

Via Henok Fikadu

* ፍትህ ለሄቨንና
* ለእህቶቻችን🙏

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በኮንሶ ዞን “የታጠቁ ኃይሎች” ባደረሱት ጥቃት፤ የፖሊስ አባላትን ጨምሮ 11 ሰዎች ተገደሉ‼️

ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል፣ በኮንሶ ዞን፣ ሰገን ከተማ ባለፈው ቅዳሜ እና ከትላንት በስቲያ እሁድ በደረሰ ጥቃት፤ ስድስት ነዋሪዎች እና አምስት የፖሊስ አባላት ተገድለዋል።
ጥቃቱን ያደረሱት “የታጠቁ ጽንፈኛ ኃይሎች ናቸው” ሲሉ ዋና አስተዳዳሪው ወንጅለዋል።

በደራሼ ወረዳ ከምትገኝ ሀይቤና ከተባለች ቀበሌ እንደመጡ የተነገረላቸው የታጠቁ ኃይሎቹ፤ ወደ ሰገን ከተማ “በድንገት” የገቡት ቅዳሜ ነሐሴ 11፤ 2016 አመሻሽ ላይ መሆኑን አቶ ኡርማሌ ገልጸዋል።

ታጣቂዎቹ ወደ ከተማይቱ ከገቡ በኋላ “ከባድ ተኩስ” መክፈታቸውን የገለጹት የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ፤ በመጀመሪያ ኢላማ ያደረጉት “የወረዳው የአስተዳደር እና የጸጥታ ተቋማት ላይ” እንደነበር አስረድተዋል።

“ቀጥታ ተኩሱን የከፈቱት ወደ አስተዳደር እና ወደ ፖሊስ ጽህፈት ቤት፤ ፖሊስ ጣቢያው ላይ ነው። ከቅዳሜ ለሊት 6 ሰዓት እስከ 10 ሰዓት ሲታኮሱ ቆዩ። ከዚያ በኋላ በመሃል ረገብ አለ። ማለዳ ላይ 12 ሰዓት አካባቢ [በድጋሚ] ጀመሩ” ሲሉ አቶ አርማሉ በዕለቱ የነበረውን ሁኔታ አብራርተዋል።

ታጣቂዎቹን “በደንብ የተደራጁ” ሲሉ የገለጿቸው የሰገን ዙሪያ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ፤ በተኩስ ልውውጡ አምስት የፖሊስ አባላትን መግደላቸውን ተናግረዋል።
ከዚህ በተጨማሪ በርካታ ቤቶችንም ጭምር አቃጥለዋል።

(ayu)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በኤፍራታና ግድም ወረዳ በሁለት ቀበሌዎች በመሬት መንሸራት ምክንያት በ 156 የግለሰብ ቤቶች ላይ ጉዳት አደረሰ‼️

በሰ/ሸዋ ዞን ኤፍራታና ግድም ወረዳ በበርግቢ ቀበሌ እና በመንተኬ ሸረፋ ቀበሌ የመሬት መንሸራተት ተከስቷል።

በመሬት መንሸራተቱ ምክንያት በዕለቱ በሰው ህይወት ላይ ያደረሰው ጉዳት ባይኖርም በአንድ መቶ ሃምሳ ስድስት የግለሰብ የመኖርያ ቤትን ጨምሮ፣ ማሳ ላይ እና ቋሚ ተክሎች ላይ ጉዳት አድርሷል።

በዚህም መሠረት በርግቢ ቀበሌ በነሃሴ 07/2016 ዓ.ም ባስከተለው ከባድ ዝናብ የ24 ግለሰቦች ቤት የመፈራረስ እና ከነበረበት ቦታ ዝቅ የማለት(የመስጠም) አደጋ የደረሰባቸውና ቤቶቹ ከጥቅም ውጭ የሆኑ ሲሆን በዚሁ ቀበሌ በነሃሴ 12/2016 ዓ.ም በ12 አርሶ አደሮች ማሳ ላይ የመሬት መንሸራተቱ ተከስቷል።

ከዚህ በተጨማሪም በነሃሴ 12/2016 ዓ.ም በመንተኬ ሸረፋ በሶስት ጎጦች ላይ በ132 ግለሰቦች የመኖሪያ ቤት ላይ እና የቋሚ ተክሎች ላይ ጉዳት ያደረሰ ሲሆን ለጊዜው የመሬት መንሸራተት የተከሰተባቸው ቤቶች እና ተክሎች ለጊዜው ሙሉ በሙሉ የጠፉ ባይሆንም የክረምቱ የዝናብ መጠን በዚሁ የሚቀጥል ከሆነ ከጥቅም ውጭ መሆናቸው አይቀርም ሲሉ የዘገበው የወረዳው ኮሙኒኬሽን ቢሮ ነው

@ethio_mereja_news
በጉራጌ ዞን  ሁለት ህፃናት በጅብ ተበልተዉ ህይወታቸዉ አለፈ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በጉራጌ ዞን እንደጋኝ ወረዳ እድሜያቸዉ የ8 እና  የ9 ዓመት የሆኑ ሁለት  ታዳጊ ህፃናት በጅብ ተበልተዉ ህይወታቸዉ ማለፉን የዞኑ ፖሊስ ገልጿል።

በጉራጌ ዞን እንደጋኝ ወረዳ በወሌቾ ቀበሌ አንዦኔ ተብሎ በሚጠራ መንደር ድርሻዬ ኑረዲን የተባለ የ8 ዓመት ታዳጊ ነሐሴ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 7:00 ሠዓት ገደማ በጅብ መበላቱን  ፖሊስ አስታዉቋል።

በተጨማሪም ነሐሴ 13 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 8:30 ሠዓት  በወረዳው ሸውራ ቀበሌ ልዩ ስሙ ጎምሻ ተብሎ በሚጠራ መንደር መድሐኒት ፀጋዬ የተባለች የ9ዓመት ታዳጊ በጅብ ተበልታለች።

ታዳጊዋ ከሌሎች ጓደኞቿ ወንዝ ውሀ ልትቀዳ በሄደችበት በቀን አድፍጦ ይጠባበቅ በነበረ የተራበ ጅብ ተበልታ ህይወቷ ሊያልፍ መቻሉን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የሚዲያ ክፍል ኃላፊ ምክትል ኮማንደር ታጁ ነጋሽ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

ተመሳሳይ በሆነ መልኩ ሊደርስ በሚችል የጅብ ጥቃት የህፃናት ህይወት እንዳያልፍ ህብረተሰቡ ለህፃናት  ተገቢዉ ጥንቃቄና ጥበቃ ማድረግ  አለበት ሲሉ ኮማንደሩ አሳስበዋል።

በሳምራዊት ስዩም

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ተረጋገጠ‼️

ሴናተር ቦብ ሜነንዴዝ አሜሪካ በኢትዮጵያ ላይ ጫና እንድታደርግ ከግብጽ ጉቦ መቀበላቸው ተረጋገጠ‼️

የሀገሪቱ ፍትህ ተቋማት ባደረጉት ምርመራ ቦብ ሜነንዴዝ ከግብጽ እና ኳታር ኩባንያዎች ጋር ጥቅም ትስስር በመፍጠር ያልተገባ ገንዘብ እንደተከፈላቸው ማረጋገጣቸው ተዘግቧል።

ትራምፕ የአሜሪካ ፕሬዚዳንት በነበሩት ወቅት ኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን መሪዎች በታላቁ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሶስትዮሽ ውይይት በማድረግ ላይ በነበሩት ወቅት እኚህ ሴናተር ኢትዮጵያ binding agreement እንድትፈሮም ጫና ሲያደርጉ እንደነበር እና በወቅቱ ኢትዮጵያም አልፈርምም በማለቷ ድርድሩ ያለ ስምምነት መጠናቀቁ ይታወሳል።

በዚህም ባለፉት 40 ዓመታት በአሜሪካ ፖለቲካ ውስጥ ተጽዕኖ ፈጣሪ የነበሩት ሜነንዴዝ ጉቦ በመቀበል ፍትህ እንዲዛባ በማድረግና በሌሎች ወንጀሎች ጥፋተኛ ሆነዋል።
ይህን ተከትሎም የሀገሪቱ ፍርድ ቤት በጉምቱው ፖለቲከኛው ላይ የእስር እና ሌሎች ቅጣት ውሳኔዎችን ለማስተላለፍ ለመጪው ጥቅምት ወር ቀጠሮ ይዟል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
cats‼️

DOGS አልቋል አሁን ተራው የ CATS ነው 👀

CATS እንደ DOG ሁሉ በቴሌግራም የቆያችሁበትን አመት አስልቶ ነዎ POINT ሚሰጣቹ ቶሎ ጀምሩት ግዜው ሳይረፍድ ።

የ CATS LINK 👇👇👇

http://www.tg-me.com/catsgang_bot/join?startapp=xkQP3ezHQcUYeSPyt_-Hv

http://www.tg-me.com/catsgang_bot/join?startapp=xkQP3ezHQcUYeSPyt_-Hv
ወይ ጉድ‼️

ቦሌ ቡልቡላ ዶክተሮች ስፈር አንዲት የ 5 አመት ህፃን ሰፈር ውስጥ ለመጫወት ከቤት ትወጣለች ለረጅም ሰአት ድምጿ ሲጠፋ አክስቷ እሷን ለመፈለግ ከቤት ትወጣለች ፈልጋ ስታጣት አንድ በእድሜ ገፋ ያለ የሰፈር tele tawor ሚጠብቅ ጥብቃ አለ እና እሱጋ ሄዳ ስታንኳኳ አልከፍትም ይላታል ከውስጥ የልጅቷን ድምፅ ስትሰማ ሰፈሩን በጩኸት ቅልጥ ታረገዋለች የሰፈሩ ሰው ተሰብስቦ በሩን ሰብረው ውስጥ ሲገቡ ህፃኗ ልጅ አልጋ ላይ ተኝታለች ሰውዬው ደሞ ሱሪውን አውልቆ ቆሞ ነበር በአከባቢው የነበሩ ፖሊሶች ሰውዬውን በባጃጅ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ይዘውት ሄደዋል፣ልጅቷን ደግሞ ሆስፒታል ቼክ ለማስደረግ ይዘዋት ሄደዋል።

@ethio_mereja_news
ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ከዚህ አለም በሞት ከተለዩ 12 አመት ሆኗቸዋል

ከ 12 አመታት በፊት ነሃሴ 14 ቀን የቀድሞዉ ጠ/ሚኒስትር እና የህወሓት ሊቀመንበር የነበሩት መለስ ዜናዊ አስረስ ከዚህ አለም በሞት የተለዩበት እለት ነዉ።

ጠ/ሚኒስትር መለስ ላይ ኢትዮጵያዊያን ሁለት አይነት አመለካከት ያላቸዉ ሲሆን ግማሾች ባለራዕይ ፣ ቆራጥ እና ጀግና መሪ ሲሏቸዉ ግማሾች ኢትዮጵያን የብሔር ፖለቲካ ዉስጥ የከተቱ ፣ ከፋፋይ እና ሴረኛ መሪ ይሏቸዋል።

በጠ/ሚኒስትር መለስ አገዛዝ ዘመን ኢትዮጵያ የኢኮኖሚ እድገት ያሳየችበት ፣ የአባይ ግድብ ግንባታ የተጀመረበት እንዲሁም በርካታ ዩኒቨርስቲዎች የተከፈቱበት እና ከቀደመዉ አገዛዝ ለዉጥ የታየበት ነዉ ሲሉ በርካቶች ግን ኢትዮጵያዊ ዛሬ ላይ ጭምር ላለችበት የብሔር ግጭት መሰረት የጣሉ ሰዉ ናቸዉ ይሏቸዋል።

ጠ/ሚኒስትር መለስ በ 2004 ዓ.ም ነበር ከዚህ አለም በሞት የተለዩት። ጠ/ሚኒስትሩ ለ 2 ወራት በህክምና ሲረዱ ቆይተዉ በቤልጂየም ህይወታቸው ማለፉን በወቅቱ የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን መዘገቡ አይዘነጋም። ጠ/ሚኒሰትሩ በሌሊት ህልፈታቸዉ የተሰማ ሶሆን በኋላ ነሃሴ 14 ቀን 2004 ዓ.ም ነበር በ 57 አመታቸዉ ከዚህ አለም በሞት የተለዩት።

ዉድ የኢትዮ መረጃ ቤተሰቦች ስለ ጠ/ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ምን ያስባሉ?

ጠንካራ እና ባለራዕይ መሪ ናቸዉ? ለምትሉ

ኢትዮጵያ ለገባችበት ቀዉስ ተጠያቂዉ ሰዉ ናቸዉ ለምትሉ 💯

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
" ከተያዘው እቅድ ውጭ እኛ የማናቀውን ስብሰባ ማካሄድ አይቻልም " - የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር

በትግራይ ክልል ፣ በመንግስት መስሪያ ቤቶች ጊዚያዊ አስተዳደሩ የማያውቀው ማንኛውም ሰብሰባ ማካሄድ የሚከልክል የስራ መመሪያ ይፋ ተደረገ።

ከትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ፅህፈት ቤት በፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ፊርማ ለሁሉም
የዞን አስተዳደሮች
ለወረዳ አስተዳደሮች
የክፍለ ከተማ አስተዳደሮችና
የወረዳ ምክር ቤቶች 
የተላከው ደብዳቤ እንደሚያመለክተው ጊዚያዊ አስተዳደሩ ከፈቀደው ውጪ ሌላ ስብሰባ ማካሄድ አይቻልም ይላል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/09/30 23:34:56
Back to Top
HTML Embed Code: