Telegram Web Link
ህወሃት የእነ ጌታቸው ረዳ ቡድን በህወሓት ስም እንዳይቀሳቀስ አግጃለሁ ብሏል‼️

በህወሃት ሊቀመንበር ደብረፅዮን ቡድን ዛሬ ባወጣም መግለጫ በ14ኛ ያልተሳተፉ የህወሓት ማእከላይ ኮሚቴ አባላት ማለትም የነ ጌታቸው ረዳ  ቡድን፥  ከዛሬ ጀምሮ በየትኛውም መድረክ በህወሓት ስም እንዳይቀሳቀሱ ማገዱን ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
“የትግራይ ፀጥታ ሃይሎች ስልጣን ለሚፈልጉ ኣካላት መሳርያ ሊሆኑ ኣይገባም”-ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ


ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ በወቅታቸው ጉዳይ ላይ ዛሬ ለሚዲያዎች መግለጫ ሰጥቷል።

ዋና ዋና ነጥቦች:-

👉 ጉባኤው ውጤት እንደሌለው ስለምናቅ ወዳልተፈለገ መሳሳሰብ ላለመግባት ጉባኤው እንዳያካሂዱ አልከለከልንም።

👉 ምንነቱ ያልታወቀ ሃይል ደጀን ይሆነናል ብለው ተማምነው እያደረጉት ያለ ጉባኤ ነው ነገር ግን ወዳልተፈለገ ችግር የሚያደገባ ነው።

👉 የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ለመንጠቅ እንቅስቃሴዎች ሊያደርጉ ይችላሉ ብለን እንጠብቃለን።

👉 የትግራይ ፀጥታ ሃይሎች ስልጣን ለሚፈልጉ ኣካላት መሳርያ ሊሆኑ ኣይገባም።

@sheger_press
@sheger_press
ባህር ዳር

ፌቨን የ7 ዓመት ህፃን ነች።እናቷ ነርስ ስለሆነች የተከራዩበት ቤት ትታት ትሄዳለች።ነገር ግን ቤት ያክራያቸውና አሁን በማረሚያ ቤት የሚገኘው ጌታቸው የተባለ የ3 ልጆች አባት ህፃኗን በአሰቃቂ ሁኔታ አስገድዶ ደፍሮ ገድሏት ተገኘች።

የ7 ዓመት ህፃኗ ልጅን ግቢ ውስጥ ወደ ሽንት ቤት ስትሄድ ጠብቆ አፏ ውስጥ አሽዋ በመጨመር ለመግለፅ በሚከብድ ሁኔታ አሰቃይቶ እንደገደላት እናት አስረድታለች።

25 ዓመት ተፈርዶበት ማረሚያ ቤት ቢሆንም በይግባኝ ለማስወጣት እየሠሩ ነው።እኔን አስፈችው በማለት ዛቻና ማስፈራሪያው ከአቅሜ በላይ ሆኗል።ህዝብ ይፍረደኝ እያለች ነው።

@sheger_press
@sheger_press
ደስ የማይል ቀን ነው

ዛሬ በሶሻል ሚዲያው በስፋት እየተዘዋወረ የሚገኘውን የ 7 አመቷ ታዳጊ የፌቨንን መረጃ አመሻሽ ላይ አይቼ ነበር ፤ እናም በእውነት ልብ ሰባሪ ነው ብዙዎችንም በጣም ያሳዘነ አስነዋሪ ተግባር ነው በዚህች ታዳጊ ላይ የደረሰው

አይደለም ለ 7 አመት ልጅ ማንም ላይ ቢከሰት ልብን የሚሰብር አይነት መረጃን ነው ያየነው ::

ኢትዮ መረጃ እንደ ቻናል በሰባት አመቷ ታዳጊ ፌቨን ላይ የደረሰውን ግፍ እና በደል ይቃወማልም ያወግዛልም

ነገር ግን መቃወም እና ማውገዙ ፍትህን ማስገኘት መቻል አለበት ፤ ሁላችንም ፌቨን ላይ የተደረገውን ነገር መቃወም አለብን ። በውጪው አለም ታዳጊ ህፃናትን ፆታዊ ጥቃት አድርሶ መግደል ይቅርና የወንድ ልጅ መብት ከውሻ ራሱ ያነሰ ነው የሴቶች መብት ደግሞ በአንደኛ ደረጃ ላይ ይቀመጣል ።

እኛ ሀገር ደግሞ እንደዚ አይነት ችግሮች ሲከሰቱ ለቀናት ይወራል ከዛ ፍትህ ሰፈነ የሚለው ተረስቶ ታሪክ ሆኖ ይቀራል

ፍትህ ፍትህ

@sheger_press
@sheger_press
#ፍትህ_ለሔቨን

ይህቺ ብላቴና ምን በወጣት ይሄን ሁሉ በደል በሷ ላይ...?

ፍትህ ፍትህ ፍትህ

@sheger_press
የአማራ ክልል የ2016 ዓ.ም የ6ኛ  እና 8ኛ ክፍል  ክልል አቀፍ ፈተና ውጤት ይፋ ሆኗል‼️

ውጤት ለማየት

👉 ለ8ኛ ክፍል ተፈታኞች
https://amhara.ministry.et/#/result

👉 ለ6ኛ ክፍል ተፈታኞች
https://amhara6.ministry.et/#/result
የተማሪውን መለያ ቁጥር (Registration Number) በማስገባት ዉጤት ይመልከቱ (Check your result) የሚለውን ቁልፍ በመጫን ማየት ይችላሉ፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
"ትልቅ የማፊያ ስራ ተሰርቷል!"

ዶ/ር አሸብር ምን እያሉን ነው?

በጋዜጠኛ ዐቢይ ወንድይፍራው ለመሠረት ሚድያ

ዶ/ር አሸብር ወ/ጊዮርጊስን ሳውቃቸው በሚዲያ ፊት የሚናገሩትን ጠንቅቀው ያውቃሉ። ስሜታዊ አይደሉም። የሚጠቀሟቸው ቃላትም የአጋጣሚ አይደሉም። ባለፉት ሁለት ቀናት በተለያዩ ሁለት መድረኮች (ከፓሪስ መልስ በሰጡበት ጋዜጣዊ መግለጫ እና ትናንትና ኢቲቪ ባዘጋጀው ውይይት ላይ) እንደዋዛ ጣል ያደረጉት “ክስ”ቀልቤን ስቦታል።

ዶክተሩ በጋዜጣዊ መግለጫቸው ላይ በተለይ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ሲፋን ሀሰን እንድታሸንፍ ሆን ተብሎ ደባ መሰራቱን ገልጠው “ትልቅ የማፊያ ስራ ተሰርቷል" ብለዋል። ይህ ተንኮል የሚሰራውም በሀገር ውስጥ አትሌቶቹን ከሚያዘጋጁ አሰልጣኞች ጋር በመሻረክ እንደሆነ ጠቅሰው ጋዜጠኞች ከሜዳ ላይ ዘገባ ባለፈ እንዲህ ያሉ ከሜዳ ውጪ ያሉ ችግሮች ላይ የምርመራ ጋዜጠኝነት ስራ እንዲሰሩ መክረዋል።

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ፕሬዚዳንቱ ጉዳዩ በሀገር ውስጥ ሚዲያው የጠበቁትን ያህል ትኩረት አለማግኘቱን ተመልክተው በማግስቱ (ትናንት) ጠንከር ባሉ ቃላት ሀሳቡን ደግመውታል። በኢቢሲው ፕሮግራም ኦሊምፒክ/አለም አቀፍ ሻምፒዮናዎች ላይ Match Fixing (የውድድርን ውጤት አስቀድሞ መወሰን) ይፈፀማል፣ ጉዳዩም 'ከገንዘብ ጋር ይያያዛል' ብለዋል።

[ሰውየው በዚህ ክስ (አጀንዳ) ምን ኢላማ አድርገዋል?]
***

1/ ሀይሌ ገ/ስላሴ

ዶክተሩ በዚህ ክሳቸው አንድም ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ዋነኛ ዒላማቸው የሆነውን ሀይሌ ገብረስላሴ ማጥቃት እንደፈለጉ ግልጥ ነው። ከኢቲቪው ማብራሪያቸው አስቀድመው ሀይሌን ተጠያቂ ያደረጉበት የብሔራዊ ቡድን መፍረስ አሰልጣኞችን እሳቸው አለም አቀፍ ማፊያ ላሉት ቡድን መጠቀሚያ አድርጓል በማለት በተዘዋዋሪ ጣታቸውን ወደ ቀድሞው የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት ጠቅመዋል።

2/ ገዛኸኝ አበራ

ከኦሊምፒክ ኮሚቴና ሰዎች ጋር የከረረ አተካሮ ውስጥ የገባው የቀድሞው አትሌት ገዛኸኝ አበራ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ፕሬዚዳንት ይሁን እንጂ በፓሪሱ ኦሊምፒክ ዝግጅት ወቅት የብሔራዊ ቴክኒክ ኮሚቴው ሰብሳቢ ነበር። ይህ ኮሚቴ ለአትሌቶች ብቻ ሳይሆን ለብሔራዊ ቡድን የአሰልጣኞችን ዝርዝር የሚወስን በመሆኑ ሰብሳቢው ገዛኸኝን በክስ መዝገባቸው ለማካተት ያስችላቸዋል።

3/ የሀገር ውስጥ ጋዜጠኞች

ትውልደ ኢትዮጵያዊቷ ሲፋን ሀሰን ባስመዘገበቻቸው ስኬቶችና ቀደም ባለው ጊዜ ትሰጣቸው በነበሩ አስተያየቶች ምክንያት ስሟ በቀላሉ ትኩረት ያገኛል። ስለዚህም ውጤቶቿ በተቀናጀ ተንኮል የተመዘገቡ ናቸው የሚል አጀንዳ በቀላሉ የሀገር ውስጥ ሚዲያውን ቀልብ ስቦ በእርሳቸው እና በተቋማቸው ላይ ያነጣጠረውን ትኩረት ሊበትንላቸው እንደሚችል ያሰሉ ይመስላል። ለዚህም ጉልበት እንዲጨምርላቸው በሚመስል መልኩ አይኖቻችሁን ክፈቱና መርምሩ እንጂ በማለት ሚዲያውን ለመኮርኮር ሲሞክሩ በተደጋጋሚ ተስተውለዋል።

[የፌዴሬሽኑ ምላሽ - ዝምታ?]

የዶ/ር አሸብር ክስ እውነት ላይ የተመሰረተ ይሁንም አይሁን ጉዳዩ ከሌሎችም ጋር ያነካካቸዋል። ሌላው ቀርቶ ከእርሳቸው ጋር በአጋርነት የቆመ የሚመስለውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን (ፕሬዚዳንቷ ደራርቱ ቱሉ) ወይም የብሔራዊ ቡድን አሰልጣኞችም እንዳልሰሙ ማለፍ አይችሉም /የለባቸውም። ዶክተር አሸብር አትሌቶቻችን የሚሰለጥኑት ሌሎች የተመረጡ አትሌቶች እንዲያሸንፉ ታስቦ በተዘጋጀ ቀመር ነው ሲሉ ደራርቱ ከጎናቸው ነበረች። ሌሎች አሰልጣኞችም በፕሮግራሙ ላይ ታድመዋል። ቢያንስ ተቀርፆ በዩቱብ በሚታየው ቪዲዮ ላይ አንዳቸውም ይህንን ሲያስተባብሉ አላየንም።

[የዶክተሩ ንግግር ጣጣ አያመጣባቸውም?]

የዓለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ (IOC) በየሀገራቱ ያሉ ብሔራዊ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ተቋማትን የኦሎምፒክ ንቅናቄ አምባሳደሮቼ ይላቸዋል። እነዚህን ተቋማት የሚመሩ ሃላፊዎችም የኦሊምፒክ ዕሴቶችን ማስተዋወቅ ይጠበቅባቸዋል። ተግባሮቻቸው እና መግለጫዎቻቸውም መከባበርን እና ወዳጅነትን ጨምሮ የኦሊምፒዝምን ዕሴቶች እንዲያሳድጉ ይጠበቃል።

ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ ንግግር ከዚህ ጋር አይሄድም:: በአምባሳደርነት የሚወክሉት IOC በሚያዘጋጀው ዓለም አቀፋዊ ድግስ የፍትሃዊነትና ተአማኒነት ጥያቄ አንስተዋል:: ንግግራቸውን ስሟ የተጠቀሰው አትሌት ሲፋን ወይም የኔዘርላንድስ ስፖርት ሀላፊዎችም ታዝበውት በቀላሉ አያልፉትም ይሆናል::

በእርግጥ ይህ ክሳቸው የተነገረው ዓለም አቀፍ ተደራሽነት ባላቸው የሚዲያ ሰዎች ተወካዮች በተገኙበት እና በውጪ ሀገር ቋንቋዎች አለመሆኑ ለጊዜ ረድቷቸው ይሆናል:: እንደዚያ ባይሆን ኖሮ ምናልባት ለሀገር ውስጥ ባላንጣዎቻቸው የለኮሱት ክብሪት ሙቀት ከቁጥጥር ወጥቶ መልሶ ራሳቸውን ሊፈጃቸው ጥቂት ሰዓታት በቂ ነበሩ።


ምንጭ:- መረጃን ከመሠረት ሚዲያ

@sheger_press
ፍትህ‼️ ሁላቹም ተሳተፉ

ስለዚች ምስኪን ህፃን የወረት ተወርቶ  ዝም መባል የለበትም  ለህፃን ሔቨን ፍተህ ያስፈልጋል።

Petition 100ሺ አልፏል
እናንተም ተሳተፉ።

ወደ ሊንኩ ከገባቹ በኋላ 👉 https://chng.it/RNMNMvD4

የናንተን ስም
የአባታቹን ስም
ሶስተኛ ላይ ኢሜል

እነዚን አስገብታቹ Petition ተቀላቀሉ !!
እስቲ ሁላችንም ይሄንን Petition እንሳተፍ

ለምታውቁት ሰው ሁሉም ሊንኩን ሼር አድርጉ !

ሊንክ 👉 https://chng.it/RNMNMvD4

@sheger_press
@sheger_press
ያሳፍራል ያልተጠበቀ ምላሽ ‼️

እናንተ ምንም በሉ ምንም እኛ ግን አንተወውም።

በሕፃን ሔቨን ጉዳይ የተጀመረው የሚዲያ ዘመቻ እንዲቆም የአማራ ክልል ዳኞች ማህበር ጠየቀ፡፡

ከሰሞኑ የአማራ ክልል መዲና በሆነችው ባህር ዳር ከተማ የሰባት ዓመት እድሜ ያላት ህጻን ሔቨን የአስገድዶ መደፈር ወንጀል ከተፈጸመባት በኋላ ህይወቷ እንዳለፈ የህጻኗ እናት ለተለያዩ ሚዲያዎች ተናግራለች፡፡

በርካቶችን ያስቆጣው ይህ ድርጊት ወንጀሉን ፈጽሟል የተባለው ግለሰብ በቁጥጥር ስር ውሎ በተፋጠነ ምርመራ ፍርድ ቤት ከቀረበ በኋላ የ25 ዓመት እስር እንደተላለፈበትም ተገልጿል፡፡

ይህን ተከትሎ ጥፋተኛ የተባለው ግለሰብ ላይ የተላለፈበት ውሳኔ በቂ ካለመሆኑ በላይ ግለሰቡ ፍርዱ እንዲቀነስለት ይግባኝ ማለቱም ተነስቷል፡፡

ከአንድ ዓመት በፊት ሐምሌ 25 ቀን 2015 ዓ.ም እንደተፈጸመ የተገለጸው ይህ ወንጀል ጉዳዩ በሀገር ውስጥ እና በውጭ ሀገራት ከፍተኛ ትኩረት የሳበ ሲሆን ተቋማት ሳይቀር በጉዳዩ ዙሪያ መግለጫዎችን በማውጣት ላይ ናቸው፡፡

የአማራ ክልል ዳኞች ማህበር በጉዳዩ ዙሪያ ባወጣው በሕፃን ሔቨን ላይ በተፈጸመው ዘግናኝ ወንጀል ማዘኑን ገልጾ ድርጊቱም ከሃይማኖትና ከባሕል ያፈነገጠ በመሆኑ በጥብቅ አወግዛለሁ ብሏል።

ይሁንና በኢትዮጵያ ወንጀል እና ወንጀለኛ የሚዳኝበት ሕግና ስርዓት እያለ እና ጉዳዩም በዳኝነት አካሉ በይግባኝ እየታየ ባለበት ሁኔታ የዳኝነት ነጻነት እና የሕግ የበላይነት መርህን የሚጥስ የሚዲያ ዘመቻ መደረጉ ስህተት መሆኑን አስታውቋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ወንጀለኛው ጌትነት ከማረሚያ ቤት አምልጦ ነበር:-የባህር ዳር ከተማ አስተዳደር‼️
የባሕር ዳር ከተማ አስተዳደር  በታዳጊዋ ሄቨን አሰቃቂ ህልፈተ ህይወት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን አሁንም በድጋሜ ይገልጿል::

ከተማ አስተዳደሩ *ሀምሌ 25 / 2015 ዓ.ም* በባሕር ዳር ከተማ ዳግማዊ ሚኒሊክ ክፍለ ከተማ በ7 አመቷ ታዳጊ ህጻን ሄቨን ላይ በተፈጸመው አሰቃቂ ድርጊትና ህልፈተ ህይወት በእጅጉ ማዘኑን ገልፆ የነበረ መሆኑ ይታወሳል።

በህጻናት ላይ የሚፈጸምን ማንኛውም ጥቃት መከላከል በዋነኛነት የመንግስት ሃላፊነት ሲሆን በሌላ በኩል የሁሉም አካል ተመሳሳይ ድርሻ ያለው መሆኑን የገለፀው ከተማ አስተዳደሩ እንደዚህ አይነት አስነዋሪና አሳፋሪ ድርጊት በከተማችን በመፈፀሙ በእጅጉ ዛሬም በድጋሜ አዝነናል ።

የባሕር ዳር ከተማ ህዝብ ሰው ወዳድ፣ ሁሉን አክባሪ፣ ባህሉን፣ ወጉንና ታሪኩን ጠባቂ አስተዋይ ጨዋ ህዝብ ነው ። በዚህ እሴትና ባህል በተገነባ ማህበረሰብ ውስጥ የተፈፀመው ድርጊት በፍፁም ነውረኛና የከተማውን ህዝብ የማይገልፅ ሁሉም ሰው ሊያወግዘው የሚገባ ዘግናኝ ተግባር ነው ።

ሁሉም እንደሚያስታዉስዉ ወንጀሉ እንደተፈፀመ  የከተማ አስተዳደሩ የሚመለታቸው ተቋማት በዋነኝነትም  ከፖሊስ ፣ ከጤና ተቋም ፣ ከፍትህ እንዲሁም ከተበዳይ ወገኖች ጋር በመቀናጀት ጉዳዩ በህግ እንዲያዝ በማድረግ ልዩ ትኩረትና ክትትል በማድረግ ድርጊቱን የፈጸመው ግለሰብ ተይዞ በ20/06/2016 ዓ.ም በከፍተኛ ፍርድ ቤት የ25 አመት ጽኑ እስራት ተፈርዶበት ባህርዳር ማረሚያ ቤት እንዲገባ ተደርጓል። 

በዚህ አጋጣሚ ከተማ አስተዳደሩ የፍርድ ቤቱን የዳኝነት ነፃነት የሚያከብር ቢሆንም ከተፈፀመው ዘግናኝ ድርጊትና የማህበረሰቡን ሞራልና ክብር ዝቅ ያደረገ ወጀል በፈፀመው ወንጀለኛ ላይ የተሰጠው ፍርድ አስተማሪነት የሚያንሰው መሆኑን አስተዳደሩ በፅኑ ያምናል ።

ከተማ አስተዳደሩ ጉዳዩን በጥብቅ ለመከታተል ባለው ፅኑ አቋም ክልሉን ባጋጠመው ቀውስ ወንጀለኛው ከማረሚያ ቤት አምልጦ የወጣ መሆኑን እንዳወቀ  በልዩ ሁኔታ የፀጥታ ሀይሉ ክትትል እንዲያደርግ አመራር ተሰጦ ወንጀለኛው ተይዞ ድጋሜ ወደ ማረሚያ ቤት እንዲገባ ተደርጓል።

ይህ እንደተጠበቀ ሆኖ በአሁኑ ወቅት ወንጀለኛው ይግባኝ የጠየቀ እንደሆነ እና ጉዳዩ ለጥቅምት 20/2017 ዓ.ም ፍ/ቤቱ ቀጠሮ የሰጠ መሆኑን የከተማ አስተዳደሩ ያውቃል። የፍርድ ቤቱን ነጻነት በጠበቀ መልኩ ከህግ አኳያ የይግባኙን ሁኔታ በተመለከተ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመሆን በትኩረት የምንከታተለው እና ፍትህ እንዲረጋገጥ በፅናት የምንታገል እንደሆነ ለማረጋገጥ እንወዳለን።

ከተማ አስተዳደሩ በልጃችን ህፃን ሄቨን  ለደረሰው ግፍ ፍትህ ሲጠይቅ ፣ ለጉዳዩ ለሰጠው ትኩረት እና እያደረገ ላለው ትግል ለመላው የህብረተሰብ  ክፍል   ምስጋና እያቀረብን በቀጣይም ለፍትህ መረጋገጥ ለምናደርገው ትግል ህ/ሰቡ ከጎናችን እንዳይለይ ጥሪያችን እያቀረብን በቀጣይም የህፃናት ጉዳይ የሁላችንም ጉዳይ ስለሆነ በትብብር መስራት ይጠበቅብናል።

@sheger_press
@sheger_press
ጥቆማ‼️

ክሪፕቶና ኤርድሮፕን በተመለከተ የተለያዩ መረጃዎችን በስፋት የምንዳስስበትን ሁለተኛው ቻናላችንን join ብታደርጉ ትጠቀማላችሁ።


- Crypto trading
- Airdrop list
- Daily combo
- Updates and listing date

አሁንኑ ይቀላቀሉ👇👇
https://www.tg-me.com/+fzeZ2gn56UE3NTI0
https://www.tg-me.com/+fzeZ2gn56UE3NTI0
🇪🇹ለሀገር ውክልና የተመረጠው አትሌት በተፈፀመበት ድብደባ የአይን ብርሃኑን አጣ!!

👉በድብደባ አንድ አይኑን ያጣው አትሌት አደጋው እንዴት ደረሰበት?

የ17 አመቱ አትሌት ሰው መሆን ታሪኩ፤ ፔሩ ለሚካሄደው የዓለም ከ20 አመት በታች ለሀገር ውክልና ተመርጦ ፌደረሽኑ ባዘጋጀላቸው ሆቴል በዝግጅት ላይነበር ። በዚህ ሁኔታ እያለ ባለፈው እሁድ የከሰዓት በኋላ ፕሮግራም ለመስራት ወደ ጫካ ወጣ ብሎ ልምምዱን ጨርሶ ያቀዘቅዛል ። በዚህ ሁኔታ አንድ ሰው ወደ አትሌቱ ይቀርብና ፓሊስ ነኝ በማለት ፤
' እዚህ አካባቢ ቁማር የሚጫወቱ ታውቃለህ ' በማለት ይጠይቃል ። አላውቅም ብሎ እንደመለሰ ወዲያው በፍጥነት አንገቱን ሲይዘው አትሌቱም እራሱን ለመከላከል ጥረት ያፈርጋል ።

ሌሎች ሁለት ሰዎች በድነገት በመምጣ በሁለት በድንጋይ ጭንቅላቱን በመምታ አልወድቅ ሲል በሽጉጥ አይኑን ተኩሰው ከመቱት በኋላ በኪሱ ያለውን ሞባይል በመውስድ እንደተሰወሩ ጓደኛቹ ለኢትዮ ራነርስ ገልፀዋል። ጉዳቱም ከፍተኛ ነው።

አትሌቱ በዳግማዊ ሚኒልክ ሆስፒታል ህክምና እየተከታተለ ሲሆን የፌደረሽን ሰዎች እየመጡም እየጠየቁት እንደሆነ ለህክምና የሚወጣውን የወጭ ደረሰኝ ያዙ ማንኛውንም ወጪ እንሸፍናለን በማለት በቃል እንደነገሯቸውም ጓደኞቹ ለኢትይ ራነርስ ገልፀዋል።

ልጁ ለሀገር ውክልና ተመርጦ ባለበት ሁኔታ ነውና አደጋው የደረሰበት ሙሉ ሀላፊነት ፌደረሽኑ ይወስዳል ብለን እንገምታለን።

ምን አልባት በፓሪስ በመጣው ውጤት የተበሳጩ ሌቦች ሊሆኑ ስለሚችሉ የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴም ህክምናው ላይ እጁን ያስገባል የሚል ግምት አለን።

Via Ethio runners

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ከሕወሓት ጠቅላላ ጉባዔ ራሳቸውን ያገለሉ የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴና የቁጥጥር ኮሚሽን አባላትና ሌሎች አካላት ትናንት መቀሌ ውስጥ "ሕወሓትን ለማዳን" ያለመ ምክክር አድርገዋል።

ምክክሩ፣ ግጭት ሊቀሰቅሱ የሚችሉ የውስጥና የውጭ ሴራዎችን በጽኑ እንደሚያወግዝ ገልጦ፣ በመደናገር በፓርቲው ጉባዔ በመሳተፍ ላይ የሚገኙ የፓርቲው አባላት ከሕዝቡ ጎን እንዲቆሙ ጠይቋል።

የማዕከላዊ ኮሚቴና የቁጥጥር ኮሚሽን አባላቱ ምክክሩን ያደረጉት፣ ምርጫ ቦርድ ዕውቅና የነፈገው ጉባዔ በፓርቲው ስም ማናቸውንም እንቅስቃሴ እንዳያደርጉ ባገዳቸው ማግስት ነው።

@sheger_press
2024/11/06 02:00:50
Back to Top
HTML Embed Code: