Telegram Web Link
የተሰጣችሁን ቀድሞ የመውጣት ተልኮ ካልተገበራችሁ ትቀጣላችሁ ተብለናል ሲል አትሌት ዮሚፍ ቀጀልቻ ተናገረ

በፓሪስ ኦሊምፒክ 10 ሺ ሜትር የወንዶች ፍጻሜ የተሳተፈው ዮሚፍ ቀጀልቻ በተሰጠን ታክቲክ ምክንያት ሀገራችን የወርቅ ክብሯን ተነጥቃለች ብሏል።

አትሌቱ በውድድሩ ጥሩ የቡድን ስራ ነበረን ግን ቀድመን መውጣታችን እኛንም ሀገራችንንም ዋጋ አስከፍሏል ፣ ቢሆንም የብር ሜዳሊያ አሳክተናል ሲል ተናግሯል።

ቀድማችሁ ወጥታችሁ ሩጡ ይህን ካላደረካችሁ ግን ትቀጣላችሁ የሚል ማስጠንቀቂያ ለኛም ለአሰልጣኞችም ተሰጥቶን ነበር ያደረግነውም እሱን ነው ብሏል።

በዚህ ምክንያት አቅማችንን ቀድመን ጨርሰን አጨራረስ ላይ ተበልጠናል ፣ ከ5 ሺ በኋላ ብንወጣ ኖሮ ሁላችንም የትኛውንም አትሌት በታትኖ የመውጣት ጥሩ ብቃት ላይ ነበርን ብሏል።

በቀነኒሳ በቀለ ተይዞ የነበረውን የኦሊምፒክ ሪከርድ የሰበረውና የወርቅ ሜዳሊያውን ያሸነፈው ዩጋንዳዊው ጆሹዋ ቸፕታጋይ የኛን የቡድን ስራና ታክቲክ በመረዳት ለድሉ ተጠቅሞበታል ብሏል ዮሚፍ።

አትሌቱ በርቀቱ የወርቅ ሜዳሊያ ባለማምጣታችን የሀገሬን ህዝብ ይቅርታ እጠይቃለሁ ሲል ከኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ጋር ባደረገው ቆይታ ተናግሯል።

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ እና አመራሮች በተወዳዳሪ አትሌቶች ፣ በቀድሞ አንጋፋ እና ስመጥር አትሌቶች እንዲሁም በስፖርቱ አዋቂዎች የሚነሳበት ነቀፌታ ቀጥሏል።

Via ሁሴን ግዛው

@ethio_mereja_news
የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ #በሕግ መጠየቅ አለበት!

“የፓሪስ ኦሎምፒክ የኢትዮጵያን አንገት ያስደፋ ነው፤ የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ #በሕግ መጠየቅ አለበት”

- ሻለቃ አትሌት ሐይሌ ገ/ሥላሴ

@sheger_press
@sheger_press
Fake News‼️

ትናንት በማህበራዊ ሚዲያዎች ሲዘዋወር የነበረው የደመወዝ ጭማሪ መረጃ " ሐሰተኛ መረጃ ነው " ሲል የኢ.ፌ.ዴ.ሪ. መንግስት ኮሚዩኒኬሽን አገልግሎት ማምሻውን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጠው ቃል አረጋግጧል። (Tikvah)

ሀሰት መሆኑ ትናንት መዘገባችን የሚታወስ ነው።

@sheger_press
@sheger_press
ኢትዮ መረጃ - NEWS
የደመወዝ ማሻሻይ ይፋ ተደርጓል ? እስካሁን የመንግሥት ሠራተኞች የደመወዝ ማሻሻያ / ጭማሪ ዝርዝር መረጃ ይፋ አልተደረገም። በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ በቴሌግራም ፣ በፌስቡክ እየተዘዋወረ ያለው " የፌዴራል መንግሥት ሲቪል ሰርቫንት ደመወዝ ማሻሻያ " የሚለው መረጃ ምንም ምንጩ የማይታወቅ ነው። የተሰራጨው የደመወዝ ማሻሻያ ሰንጠረዥ ፤ የፅሁፍ ስህተቶች ጎልተው የሚታዩበት፣ የአጻጻፉ ግድፈት…
ለትዝብት‼️

ደሞዝን በሚመለከት ትናንት መዘገባችን የሚታወስ ነው።

አንዳንዶቻቹ አንድ መስመር በማንበብ ብቻ እንዴት ሀሰተኛ መረጃ ትለቃላቹ ከሚሉ መረጃዎች በተጨማሪ ስትሳደቡ ለመመልከት ችለናል።

በድጋሚ ተመልከቱት መረጃው የሚለው ግን ሀሰተኛ መረጃ መሆኑ ነው የሚጠቅሰው።

ሳታረጋግጡ ክፉ አታውሩ አንድ መስመር በማንበብ ብቻ መረጃ አታንብቡ።

@sheger_press
የዋጋ ንረቱ ሰራተኛውን አልፎት ሄዷል! ለዚህም የደመወዝ ማሻሽያው መዘግየት የለበትም " - ኢሠማኮ

@sheger_press
ሹመት‼️

ጠቅላይ ሚንስትሩ የተለያዩ ሹመቶችን ሰጡ።

1. ለወ/ሪት ሀና ተልህኩ ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በኢትዮጵያ ካፒታል ገበያ ዋና ዳይሬክተር

2. አቶ ተስፋዬ ይገዙ  በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ

3. ዶ/ር ብሩክ ታዬ በኢንቨስትመንት ሆልዲንግ ዋና ስራ አስፈፃሚ

4. ለአቶ አብዱርሃማን ኢድ ጣሂር በገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ

5. ኮማንደር ፍቅሩ አለማየሁ የአዲስ አበባ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር

6. ለአቶ አብዱልሃኪም ሙሉ በንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ

7. አቶ አብዱርሃማን አብደላ በመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ

8. ለአቶ ፍቃዱ ተሰማ በሚኒስትር ማዕረግ በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል

9. ወ/ሮ መስከረም ደበበ በገቢዎች ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ

10. ዶ/ር ቢቂላ ሁሪሳ በሚኒስትር ማዕረግ በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል በመሆን ተሹመዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ከ2 ሺህ በላይ አስመጪና ሻጮች የሚሳተፉበት ኢግዚቢሽን ሊካሄድ ነው ተባለ

ባሮክ ኤቨንት ኦርጋናይዘር የ2017 ዓ.ም የአዲስ ዓመት በዓልን ምክንያት በማድረግ አስመጪዎች እና አምራቾች ከሸማች የሕብረተሰብ ክፍል ጋር የሚገበያይበትን ባዛር እና ኤክስፖን አስመልክቶ በዛሬው ዕለት በሚሊነየም አዳራሽ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰቷል።

የአዲስ ዓመት ባዛር እና ኤክስፖ ከነሃሴ 20 እስከ ጳግሜ 5 ቀን 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ እንደሚያካሂድ ተገልፆል ፡፡

በዝግጅቱ ላይ ከ2 ሺህ በላይ አስመጪና ሻጮች እንደሚሳተፉ የተጠቆመ ሲሆን፤ በቀን ከ7 ሺህ እስከ 10 ሺህ ሸማቾች ይገኛሉ ተብሎ ይታሰባል ተብሏል፡፡

በተጨማሪ በየቀኑ በሀገራችን የሚገኙ ከ35 በላይ ባህላዊ እና ዘመናዊ የሙዚቃ ባለሙያዎች የሙዚቃ ስራዎቻቸውን እንደሚያቀርቡም ተመላክቷል።

የዝግጅቱ የመግቢያዉ ዋጋ ከ100-150 ብር እንደሆነ ተነግሯል ።

አቤል እስጢፋኖስ (ኢትዬ ኤፍ ኤም)
“ የኦሎምፒክ ኮሚቴው ኢትዮጵያ በፓሪስ አሸበረቀች መባሉ ስላቅ ነው “ ሻለቃ ኃይሌ ገብረ ስላሴ‼️

ኢትዮጵያ በፓሪስ ኦሎምፒክ “ ያጌጠችበት ነው “ መባሉን ሻለቃ ኃይሌ ገ/ስላሴ “ ስላቅ “ ነው ሲል ገልፆታል።

“ ተሽቆጥቁጠናል መባሉ ይሄ ስላቅ ነው ፣ ስለ ውድድሩ የሚወራ ከሆነ እስከ አሁን ሜዳሊያ አልተገኘም አንገት የሚያስደፋ ውጤት ነው “
ኃይሌ ገብረ ስላሴ

ኃይሌ በዚህ ውስጥ ግን አትሌት በሪሁ አረጋዊ ፣ ፅጌ ድጉማ እና በተለይም ምስጋናው ዋቁማ ያሳዩትን ጥረት ሊደነቅ እንደሚገባ ገልፆል።

ኃይሌ ለተፈጠረው ነገር ከሀላፊነት መነሳት በቂ አለመሆኑን ሲናገር “ መጠየቅ አለባቸው “
ሲልም አሳስቧል።

የጉዳዩን አሳሳቢነት በቆይታው ያነሳው ኃይሌ በቀጣይ “ ወደ ክስ መሄዱ አይቀርም ፣ የህግ ተጠያቂነት መኖር አለበት “ ሲል ተደምጧል።

ወደ ስፍራው ያቀኑ ሰዎች በቁጥር በርካታ  መሆናቸውን የጠቆመው ኃይሌ “ የምፈራው ከዚህ በኋላ ያለውን ነው ፣ ምን ያህል ሰው ተመልሶ ይመጣል ? “ ሲል በጥያቄ ምላሽ ሰጥቷል።
ከመነሀሪያ 99.1 የራድዮ ጣቢያ የተወሰደ

@ethio_mereja_news
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Join the Kifiya AI Mastery Training Program!

Apply by August 16, 2024👉 apply.10academy.org

Learn more about the training program at https://10academy.org/kifiya/learn-more
Forwarded from Sheger Press️️
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Join the Kifiya AI Mastery Training Program!

Apply by August 16, 2024👉 apply.10academy.org

Learn more about the training program at https://10academy.org/kifiya/learn-more
አቶ ጌታቸው ረዳ ህወሓት በሚያካሂደው ቀጣይ ጉባኤ እንደማይሳተፉ አስታወቁ፣

#የትግራይ ክልል ግዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት እና የህወሓት ምክትል ሊቀመንበር አቶ ጌታቸው ረዳ ፓርቲያቸው በሚያካሂደው ጉባኤ እንደማይሳተፉ ትላንት ነሃሴ 2 ቀን 2016 ዓ.ም ለፓርቲው ሊቀመንበር በጻፉት ደብዳቤ አስታወቁ።

የፓርቲው ማዕከላዊ ኮሚቴ ውሳኔ ያላስተላለፈበት እና የማያውቀው የምዝገባ እንቅስቃሴ እየተደረገ ነው ሲሉ በመግለጽ በጉባኤው የዲሞክራሲያዊ አካሄድ እና ህጋዊነት ዙሪያ የጋራ መግባባት ላይ ባልተደረሰበት ሁኔታ አልሳተፍም ማለታቸውን በትግራይ ቴሌቪዥን ይፋ በተደረገው ደብዳቤያቸው ተመላክቷል።

አቶ #ጌታቸው ረዳ ለፓርቲው ሊቀመንበር #ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል በጻፉት ደብዳቤ ሊያካሄድ የታሰበው ጉባኤ ፓርቲውን እና የክልሉን ህዝብ አደጋ ላይ የሚከት ነው ሲሉም አስታውቀዋል።

ፓርቲው ህጋዊ እውቅና እንዲያገኝ ለብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የተጻፈው ደብዳቤም ይሁን በህወሓት ስም የሚደረጉ የጉባኤ እንቅስቃሴዎች ፓርቲውን የማይወክሉ እና የአንድ ቡድን ህገወጥ እንቅስቃሴ በመሆናቸው እንደማልቀበለው ላሳውቅ እወዳለሁ ብለዋል።

ምንጭ ፣ አዲስ ስታንዳርድ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ግንደወይን የ14 ሰዎች ህይወት አለፈ

ከግንደወይን ከተማ ወደ ባህርዳር ሲጓዝ የነበረ የህዝብ ማመላለሻ መኪና መንገድ ስቶ ወንዝ ዉስጥ በመግባቱ የ14 ሰዎች ህይወት አለፈ።

ከሟቾቹ መካከል የሁለቱ አስከሬን የተገኘ ሲሆን መኪናዉን ጨምሮ የሌሎች ሰዎች አስከሬን እስካሁኑ ሰዓት ድረስ አልተገኘም።

ከምስራቅ ጎጃም ዞን ግንደወይን ከተማ ነሀሴ 2/2016 ዓ,ም መነሻዉን አድርጎ ወደ ባህርዳር  ሲጓዝ የነበረ  ኮድ 3. 21757 አማ አነስተኛ የህዝብ ተሽከርካሪ መኪና በሁለት እጁ እነሴ ወረዳ አብያ የሚባል ወንዝ ላይ ከረፋዱ 4.00 ሰዓት አካባቢ መንገድ ስቶ በመግባቱ ሾፌሩን ጨምሮ የ14 ግለሰቦች ህይወት ሲያልፍ በሁለት ሰዎች ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል።

አደጋ ከደረሰበት ወንዝ ዉስጥ የሁለቱን  ሰዎች አስከሬን ማግኘት የተቻለ ሲሆን የ12ቱን ሰዎች አስከሬንና መኪናዉን እስካሁን ማግኘት አለመቻሉን የጎንቻ ሲሶ እነሴ ወረዳ የመንግስት ኮሙኒኬሽን አድርሷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ህውሀት‼️

ህወሃት እንደ አዲስ ፓርቲ አልመዘገብም፣የቀድሞ ህጋዊ ሰውነቴ ይመለስልኝ በሚል ለምርጫ ቦርድ ያቀረበው ጥያቄ ምርጫ ቦርድ በልዩ ሁኔታ ተቀብሎታል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ተጨማሪ‼️

ህወሓት በአዲሱ አዋጅ እውቅና ተሰጠው‼️

የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል፥ “በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፀደቀው በአመፅ ተግባር ተሰማርተው ለነበሩ ፖለቲካዊ ፓርቲዎች አስመልክቶ የወጣው ኣዋጅ ተቀብለን በእዋጁ የተቀመጡትን መስፈረቶች አሟልተን ድርጅታችን ህወሓት እንደ አዲስ ለመመዝገብ የተስማማን መሆኑን እያሳወቅን የድርጅታችን እውቅና በሚቀጥሉት14 ቀናት ውስጥ እንዲሰጠን በትህትና እየጠየቅን” ብሎ በጠየቀው ጥያቄ መሰረት ህወሓት በአዲሱ አዋጅ መሰረት ከዛሬ ነሃሴ 3 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እውቅና ተሰጥቶታል።

@sheger_press
@sheger_press
Forwarded from Sheger Press️️
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Join the Kifiya AI Mastery Training Program!

Apply by August 16, 2024👉 apply.10academy.org

Learn more about the training program at https://10academy.org/kifiya/learn-more
በእጅዎ ያለው ጥሬ ገንዘብ ዋጋ እያጣብኝ ነው ብለው ተጨንቀዎል?
የብር ዋጋ መቀነስ ወይም የዶላር ጭማሪ ሳያሳስብዎ የሚፈልጉትን ቤት ከ ዲኤምሲ ሪልስቴት ያግኙ

ዲኤምሲ ወቅቱን ባገናዘበ በከፍተኛ ዋጋ ቅናሽ ጥራታቸውን የጠበቁ ቤቶችን በተለያዩ ካሬ አማራጮች አቅርቦሎታል

በእጆ የያዙት ብር ዋጋ ከማጣቱ በፊት በቋሚ ንብረት ይቀይሩት።
  -በ10% ቅድመ ክፍያ
  -50/50 የብድር አማራጭ
  -ከ8-25% ቅናሽ
  -ከስቱዲዮ እስከ ባለ 4 መኝታ ቤቶች እና ከተጨማሪ የሰራተኛ ክፍልና መታጠቢያ ጋር
❇️ለበለጠ መረጃ 0977190118 ይደውሉ.
Telegram 👉 @MakeArtt
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሾፍቱ አቅራቢያ ለማስገንባት ላቀደው ለግዙፉ ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለዲዛይን ሥራ እና የማማከር አገልግሎት "ዳር" ከተሰኘ ዓለማቀፍ ኩባንያ ጋር ዛሬ ውል ተፈራርሟል።

ኩባንያው ባንድ ዓመት ውስጥ የአውሮፕላን ማረፊያውን የዲዛይን ሥራ እንደሚያጠናቅቅ በስምምነቱ ላይ ተገልጧል።

በአምስት ዓመት ውስጥ እንዲጠናቀቅ ከስምምነት የተደረሰበት አውሮፕላን ማረፊያ፣ በ35 ስኩየር ኪሎ ሜትር ላይ የሚያርፍ ሲኾን፣ ግንባታው ሲጠናቀቅ ባንድ ጊዜ አራት አውሮፕላኖችን ማስተናገድ እንደሚችል ተነግሮለታል።

አውሮፕላን ማረፊያው በመጀመሪያው የግንባታ ምዕራፍ 60 ሚሊዮን እንዲኹም በሁለተኛው ምዕራፍ 100 ሚሊዮን ደንበኞችን ማስተናገድ ይችላል ተብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/09/30 15:29:42
Back to Top
HTML Embed Code: