Telegram Web Link
" ተማሪዎችን አወዳድሬ ነው የምቀበለው " - አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

የራስ-ገዝ ዩኒቨርሰቲ የሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጀምሮ በራሱ ፖሊሲና መስፈርት ፤ ምዘናና የክፍያ ስርዓት ተማሪዎችን አወዳድሮ እንደሚቀበል አሳውቋል።

በመደበኛ፣ በማታና በርቀት በቅድመ ምረቃና በድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን መከታተል ለሚፈልጉ አመልካቾች በቅርቡ ዝርዝር ማስታወቂያ እንደሚያወጣ ገልጿል።

ምንጭ፡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ

@ethio_mereja_news
ዶላር ጨምሯል በሚል የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ 77 የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መዉሰዱን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ

ቢሮዉ ሃምሌ 23 እና 24 ቀን 2016 ዓ.ም ባደረገዉ የክትትል ስራ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ 11 እንዲሁም በየካ ክ/ከ 2 በድምሩ 13 የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን ያስተወቀ ሲሆን ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በሁሉም ክፍለ ከተማ በተደረገ የአሰሳ ስራ 77 ንግድ ሱቆች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ሰውነት አየለ ተናግረዋል። (መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1)

@ethio_mereja_news
በመቀሌ ከተማ የደህንነት ካሜራ ተገጠመ‼️
ከሰሜኑ ግጭት በኃላ ወንጀል ከተበራከተባቸው የትግራይ ክልል አከባቢዎች መካከል አንዷ የሆነችው መቀለ፣ የከተማዋን ደህንነትና ፀጥታ ወደነበረበት በመመለስ ሂደት ላይ ከፍተኛ ጥቅም ይሰጣሉ በሚል የተገጠሙትን የድህንነት ካሜራዎችና መቆጣጠርያ ክፍል ላይ በትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ ልኡክ ቅኝት ማድረጉን የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

የተገጠሙት የደህንነት ካሜራዎች እይታ ከ200 እስከ 1ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑና የዘመኑ የመጨረሻ የቴክኖሎጂ ውጤት መሆናቸውንም የዲጂታል ትግራይ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ቴድሮስ ሲሳይ ገልፀዋል።

የመቀለ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ኤልያስ ካሕሳይ በበኩላቸው በከተማይቱ የሚስተዋሉት የፀጥታ ችግሮችና የደህንነት ስጋቶች ለመፍታት አስተዳደራቸው እየሰራቸው ካሉት ሰራዎች መካከል የድህንነት ካሜራ ገጠማው አንዱ መሆኑን የተናገሩ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ ከረዥም ዓመታት በኃላ ጥገና የተደረገለትን የመቀለ ሆስፒታል ጨምሮ በ2.7 ቢልየን ብር በከተማይቱ የልማት ስራዎች እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።(Bisrat fm)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
‹‹ ኢትዮጵያ ደሃ የማይኖርባት ሀገር እየሆነች ነው ›› - የአዲስ አበባ ነዋሪዎች🥹

ከባለፈው ሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የውጭ ምንዛሪ ተመን ማሻሻያ ‹‹ የኑሮ ውድነቱን ሰማይ ጠቀስ እያደረገው መሆኑን ›› አሻም በተለያዩ የመዲናዋ የገበያ ስፍራዎች ተገኝታ ያነጋገረቻቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

አንድ ሸማች ከውጭ ምንዛሪ ተመን ማሻሻያው በኋላ ስላለው የገበያ ሁኔታ ሲያስረዱ ‹‹ የዘይት ዋጋ በእጥፍ ጨምሯል፤ በአንድ ጊዜ ነው ዋጋው የናረው፤ እንደኔ ያለ ደሃ መኖር አይችልም ›› ሲሉ ብለዋል፡፡

ሌላው ለአሻም ምልከታቸውን ያጋሩ ሸማች በበኩላቸው ‹‹ በውድ ዋጋ እንኳን ለመግዛት አቅርቦት የለም፣ አጥተናል ›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ አክለውም ‹‹ ዕቃውን የት እንዳደርሱት አናውቅም፤ ዘይት ፈልጌ መጥቼ ነበር፤ ግን ሁሉም ቦታ የለም ›› ብለዋል፡፡

በገበያ ዋጋ ላይ የተመሰረተ ተመን ይወጣል ከተባለ በኋላ በአጠቃላይ የዋጋ ንረቱ አይሏል ሲሉ አቤቱታቸውን ለአሻም ያሰሙት ሸማቾች ብቻ ሳይሆኑ ነጋዴዎችም ጭምር ናቸው፡፡

ለአሻም አስተያየታቸውን የሰጡ አንድ ነጋዴ ‹‹ ከጅምላ አከፋፋዮች እጅ እቃ ማግኘት አልቻልንም፤ መርካቶ ስንሄድ እቃ የለም ነው እያሉን ያሉት ›› ሲሉ የገጠማቸውን አስገንዝበዋል፡፡

በመጨረሻም ‹‹ መንግስት ቁጥጥሩን ከላይ ካላደረገ የችርቻሮ ሽያጩ ምንም ማድረግ አይችልም ›› በማለት መፍትሔ ይሆናል ያሉትን ምክረሃሳብ ለግሰዋል፡፡

(አሻም)
@ethio_mereja_news
ለዝቅተኛ ደሞዝ ተከፋይ ሰራተኞች የደመወዝ ጭማሪ ተደረገ!

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያውን በተመለከተ ማብራሪያ ሰጥተው ነበር።

በዚህ ማብራሪያቸው በሪፎርሙ በዋጋ ንረት ምክንያት ሊጎዱ ይችላሉ / ሪፎርሙ በትሩን ሊያሳርፍባቸው ይችላል ተብሎ ከተለዩት የመንግሥት ሠራተኞች ዋነኞቹ ናቸው ብለዋል።

በመሆኑም ዝቅተኛ  የሆነ ወርሃዊ ደመወዝ ለሚበሉት ሠራተኞች ከፍተኛ የደመወዝ ማሻሻያ ይደረጋል ሲሉ ገልጸዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ፦

" መንግሥት በወር 1,500 ብር የሚበላ ሠራተኛ አለው። ...የአሁኑ ደመወዝ ማሻሻያ ከ90 ቢሊዮን ብር በላይ ተጨማሪ ሃብት ጠይቆናል። ለዚህ ምን አይነት መንገድ ተከተልን ታች ያለው 1,500 ብር የሚበላው የመንግስት ሠራተኛ 300 እጥፍ ደመወዙን ጨምረናል። ይህ በኢትዮጵያ ታሪክ ታይቶ አይታወቅም።

ላይ ያለው ከ25 ሺህ በላይ ያለውን ለጊዜው ታገሰን አልነው። ደመወዝ የጨመርነው ታች ለሚጎዱት ይሄ ሪፎርም ለሚጎዳቸው ሰዎች በርከት ያለ ሃብት ጨምረን ትንሽ ሻል ሻል ያለና ለተወሰነ ጊዜ ጫናውን ለሚቋቋሙት አቆየን  ይበቃቸዋል ማለት አይደለም እነሱም ቢሆኑ ፤ በንጽጽር ግን በጣም እያለቀሰ የሚያድረውን ሠራተኛ ማገዝ አለብን ነው።"

ተሿሚዎች ብዙ ላያገኙ ይችላሉ። ታች ግን አድርገናል። "
ብለዋል

@ethio_mereja_news
ኧረ ወገን ዶላር ወደ ላይ እየተተኮሰ ነው ብራችን ዋጋ እያጣ ነው ።

ከግል ባንኮች አንዱ የሆነው አዋሽ ባንክ በዛሬ ምንዛሬ ተመኔ ዶላር በ90 ብር ከ0009 ሳንቲም ገዛለሁ ፤ 94 ብር ከ5011 እሸጣለሁ ብሏል።

ሌሎችንም ከላይ መመልከት ትችላላቹ።

@sheger_press
@sheger_press

@ethio_mereja_news
በአዲስ አበባ ህዝቡ ምሬቱን እየገለፀ ነዉ
ጠቅላዩ አታካብዱ ብለዋል ፡፡
የናይጀሪያ ህዝብ በ imf ጉዳይ አመፅ ቀስቅሶል
ዝርዝሩን በቪዲዬ
👇👇👇👇
https://youtu.be/Z5DeZT4hjWw?si=gpWwtTuTjSzmggKN
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ጥንቃቄ : ክረምቱ እየበረታ ነው።

አሽከርካሪዎች ስታሽከረክሩ እየተጠነቀቃችሁ ይሁን።

ከቤት ሳትወጡ የመኪናችሁን ደህንነት በተለይ የዝናብ መጥረጊያ፣ ጎማ ሌሎችንም ነገሮች ሁሌም ማረጋገጥ እንዳትረሱ

የምትሄዱበትን መንገድ እየተጠነቃቃችሁ።

ወላጆችም ልጆቻችሁን ጠብቁ።

በተለይ ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ ክረምት በጣም ቁጥር እጅግ በጣም የሚሰቃዩት ሠራተኞች ናቸው በተለይም በስራ የመግቢያ እና የመውጫ ሰዓት ፥ ይኸው አመታት አልፈዋል ስለ ትራንስፖርት ችግር ሲጮህ ሲጮህ ምንም የተለየ መፍትሄ አልመጣም።

ዛሬም ሠራተኞች / ዜጎች ስራ ለመግባት እና ከስራ ወጥተው ወደ ቤት ለመሄድ፣ ለሌላም ጉዳይ ረጅም ሰዓት በብርድ እና በዝናብ ሰልፍ ላይ ያሳልፋሉ። መቼ ነው መፍትሄ የሚገኘው ?

ለሁሉም ግን ስትንቀሳቀሱ ጥንቃቄ አይለያችሁ።

በክልሎችም በዚህ ክረምት ወቅት ላይ ጉሙ ለመኪና መንገድ አስቸጋሪ ነውና ሹፌሮች ተጠንቅቃችሁ አሽከርክሩ።

ሰላም ወጣችሁ ሰላም ግቡ !

ክፉ አያግኛችሁ !

ቪድዮ ፦ ዛሬ ሐምሌ 26/2016 ዓ/ም አዲስ አበባ (tikvah)


@ethio_mereja_news
በ 5000 ሜትር ማጣሪያ የመጀመሪያው ዙር ኢትዮጵያን የወከሉት ጉዳፍ ፀጋይ እና እጅጋየሁ ታዬ 5ኛ እና 6ኛ በመውጣት ፍፃሜውን ሲቀላቀሉ።

በሁለተኛው ዙር ኢትዮጵያን የወከለችው መዲና አሳም 2ኛ በመውጣት በተመሳሳይ ፍፃሜውን ተቀላቅላለች።

@ethio_mereja_news
በ 800 ሜትር ርቀት ኢትዮጵያን ከወከሉት 3 አትሌቶች

ወርቅነሽ መለሰ በምድብ 2 ሮጣ 1ኛ
አትሌት ፅጌ ድጉማም በ5ኛ ዙር 1ኛ
በመጨረስ ግማሽ ፍፃሜውን ሲቀላቀሉ

ሀብታም አለሙ 7ኛ በመጨረሷ ሌላ ማጣሪያ ትወዳደራለች።

🇪🇹❤️

@ethio_mereja_news
በኦሎምፒክ 10 ሺህ ታሪክ ፈጣኑ ሰአት በተመዘገበበት ውድድር በሪሁ አረጋዊ የብር ሜዳልያ አግኝቷል።

@sheger_press
dollar‼️

ዛሬ ፥ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ በህጋዊ መንገድ 1 የአሜሪካ ዶላር ከ 100 ብር በላይ መሸጥ ይጀምራል

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ቅዳሜ የዶላር ዋጋ አውጥቷል መግዧ 95.6931 እንዲሁም መሸጫ 101.437 መሆኑን አሳውቋል።

@ethio_mereja_news
የብሄራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምኅረቱ፣ በአዲሱ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ የሚመራው ገበያ ችግር ካጋጠው ባንኩ ጣልቃ እንደሚገባ አስታውቀዋል።

ማሞ፣ ኢትዮጵያ ከዓለማቀፉ ገንዘብ ድርጅትና ከዓለም ባንክ ጋር የብድር ስምምነቶችን መፈራረሟን ተከትሎ፣ ከሁለቱ ተቋማት 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ወደ ብሄራዊ ባንክ እንደገባ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ከውጭ ከምታስገባቸው የፍጆታ ዕቃዎች መካከል 18 በመቶዎቹ ብቻ በውጭ ምንዛሬ እንደሚመጡ የገለጡት ማሞ፣ ቀሪዎቹ ግን በትይዩ ገበያ ሲገቡ እንደቆዩ ገልጸዋል።

ባንኩ ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ ለመተግበር መዘጋጀቱንም ማሞ ተናግረዋል።

@sheger_press
@sheger_press
ባንኮች ከሚገዙበትና ከሚሸጡበት የምንዛሬ ዋጋ ውጭ በተጨማሪነት ኮሚሽን እና ሌሎች ክፍያዎችን ለብቻ ማስከፈል እንዲያቆሙ ተወሰነ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ባንኮች ይፋ ከሚያደርጉት የውጭ ምንዛሬ መግዣና መሸጫ ዋጋ ውጭ የሚያስከፍሉትን ኮሚሽን እና ሌላ ክፍያ እንዲያቆሙ መወሰኑ ተሰምቷል፡፡እንዲህ ያሉ ክፍያዎችን ካስከፈሉ እንኳን ከመግዣና መሸጫ ዋጋው ጋር አካተው አንድ ላይ ለደንበኞቻቸው ይፋ እንዲያደርጉት መወሰኑን ከብሔራዊ ባንክ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

ይህም የውጭ ምንዛሬ ግዥና ሽያጭ ላይ ግልፅነትን ለመፍጠር ያለመ ነው ተብሏል፡፡ስለ ጉዳዩ ሸገር የጠየቃቸው የምጣኔ ሐብት ባለሙያ ውሳኔው ለባንክ ደንበኞች የሚበጅ ነው ብለዋል፡፡ይህን ሲያስረዱም የአንዳንድ ምግብ ቤቶችን የዋጋ ዝርዝር እንደ ምሳሌ ያነሳሉ፡፡ሂሳብ ሲያስከፍሉ የምግብ መዘርዘሩ ላይ ከተቀመጠው ዋጋ በላይ የሚጠይቁ አሉ ለዚህም ምክንያቱን ሲጠየቁ የምግብ መዘርዝሩ ዝርዝር ላይ የሰፈረው ዋጋ ቫትን አይጨምርም ይላሉ፡፡

ይህ ለደንበኞች ግልፅነት የጎደለው ወይም መጀመሪያውኑ አጠቃላይ ዋጋውን አይተው እንዳይወስኑ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡አሁን ባንኮች የውጭ ምንዛሬ ሲሸጡና ሲገዙ የሚያስከፍሉት ኮሚሽን እና ሌላ በፐርሰንት የሚሰላ ክፍያ ካለ ይፍ በሚያደርጉት የመግዣና መሸጫ ላይ እንዲያካትቱ መወሰኑም ደንበኞች ይፋ ከተደረገው ዋጋ ሌላ ክፍያ ስለማይጠይቁ አሰራሩን ግልፅ ያደርገዋል ብለዋል ባለሞያው፡፡በሌላ በኩል ግን ይህ አሰራር ደንበኞች LC ለመክፈት ሲጠይቁ የሚኖረውን ግብይት አይመለከትም ተብሏል፡፡ውሳኔው ከዛሬ ጀምሮ ስራ ላይ መዋል መጀመሩንም ብሔራዊ ባንክ እወቁልኝ ብሏል፡፡(Sheger)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሩዋንዳ ከ4 ሺህ በላይ ቤተክርስቲያናትና መስጂዶች ዘጋች

የድምጽ ብክለት ማስከተልና የደህንነት ደንቦችን መጣስ ለመዘጋታቸው ምክንያት ሆኖ ቀርቧል።

Alain

@ethio_mereja_news
ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን የነበሩት ሀጂ ኢብሳ ወንድ ልጃቸው በሸኔ እንደተገደለባቸው ገለፁ

ለረጅም ዓመት የገንዘብ ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ቀጥሎም  የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ሀጂ ኢብሳ ብቸኛ ልጃቸውን ሸኔ እንደገደለባቸው ገለጹ።

አቶ ሀጂልጃቸው በሸኔ ስለመገደሉ በፌስቡክ ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ የገለፁ ቢሆንም መችና የት ልጃቸው እንደተገደለ አልገለፁም።

አቶ ሀጂ ኢብሳ በፌስቡክ ገጻቸው "የባለስልጣን ልጅ በመሆኑ ብቻ አንድ ወንድ ልጄን ሸኔ በጥይት ደብድባ ነጠቀችኝ ሲሉ ነው ሀዘናቸውን የገለጹት።

አቶ ሀጂ አክለውም "በመራር ሀዘኔ ከጎኔ የቆማችሁ  እናቶቼ፣አባቶቼ፣እህቶቼና ወንድሞቼ ብድራችሁ በዓለም ይመለስ።" ሲሉ አስፍረዋል።

Via አዲስማለዳ

@ethio_mereja_news
2024/09/30 17:24:02
Back to Top
HTML Embed Code: