Telegram Web Link
የዉጭ ሀገር መረጃዎችን ፡ትንታኔዎችን እንደወጡ ለማግኘት የዩትይብ ቻናላችን ይወዳጁ👇👇👇https://youtu.be/erNVjpQTKk0?si=dA2_4ZsdYHKJ3Yw9
https://www.youtube.com/watch?v=XYbB67hq9UI
"የኤርትራ ክስ የኢትዮጵያን አየር መንገድ ስም የማጥፋት ሥራ በመሆኑ ክሱ ተቀባይነት የለውም" - አቶ መስፍን ጣሰው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ ከኤርትራ ሲቪል አቬሽን ባለሥልጣን የቀረበበትን ክስ “የአየር መንገዱን ስም የማጥፋት ሥራ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም” ሲል ውድቅ አደረገ።የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ፤ የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ባለሥልጣን በላከው ደብዳቤ ይህንን አጥፍታችኋል የሚል ምንም ዓይነት ማብራሪያ አልነበረውም ብለዋል።

ኢትዮጵያ አየር መንገድ በህይወት ያሉ “ለላብራቶሪ አገልግሎት የሚውሉ እንደ ጦጣ ያሉ እንሰሳትን ወደ አሜሪካ ያጓጉዛል” በሚል ከእንስሳት ተቆርቋሪ ተቋም ለሚነሳበት ቅሬታ፤ “ይህ ዓለም አቀፍ አሰራር ስለሆነ፤ ህጋዊ ፈቃድ የተሰጠው ከአሜሪካም ከሌላም ሀገር ህጋዊ ፈቃድ የተሰጠው ድርጅት እስከመጣ ድረስ ያንን የዓለም አቀፍ ህጉን ተከትለን እናጓጉዛለን” በማለት ምላሽ ሰጥተዋል።

አየር መንገዱ “ወታደሮችን ያጓጉዛል” በሚል ለሚነሳትበት ሌላኛው ቅሬታ፤ አቶ መስፍን ጣሰው” ወታደሮች በአውሮፕላኖች የሚሄዱበት አሰራር አለ፤ አየር መንገዱ ዓለሞ አቀፍ አሰራሮችን ጠብቆ ነው የሚሰራው” ብለዋል።አየር መንገዱ ሁለት አውሮፕላኖችን መድቦ ለየተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ብቻ ያጓጉዛል። በተለይ አንደኛው አውሮፕላን ለዚሁ ግልጋሎት ብቻ የተመደበ ነው ሲሆን ሁለተኛው ተጨማሪ ሲያስፈልግ አገልግሎት ይሰጣል ሲሉ ተናግረዋል።

Via Addis Standard

@sheger_press
የኢቢኤስ መዝናኛ ፕሮግራም አዘጋጁ ትንሳኤ ብርሃን በ1 ሚሊየን ብር የባሊ ፉድ ፕሮሰሲንግ አምባሳደር ሆነ

ባሊ ፉድ ፕሮሰሲንግ ሀላፊነቱ የተወሰነ ድርጅት (Balli Food Processing) ለሚያመርታቸው በማር ወለላ የተቀመመ QQ yammy snack እና በኦቾሎኒ ጣዕም ለሚያመርተው QQ coated peanut የኢቢኤስ የመዝናኛ እና የቁምነገር አዘጋጅ የሆነውን ትንሳኤ ብርሃንን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ በዛርው እለት ሾሟል፡፡

@ethio_mereja_news
#MoE

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚያስመርቋቸው ተማሪዎች የሚሰጡት ዲግሪ የህትመት ሥራ በመንግሥት ሊከናወን ነው፡፡

የዲግሪ ህትመት ሥራው በሀገር ውስጥ እነደሚከናወንና አሰራሩም ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሩ ይህን ያሉት የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ትናንት ባዘጋጀው የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዳግም ምዝገባ የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡

"ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዲግሪ በማሳተም ለተማሪዎቻቸው መስጠት አይችሉም" ያሉት ሚኒስትሩ፤ ዲግሪ የሚታተመው በትምህርት ሚኒስቴር በኩል እንደሚሆንና ለዚህም ተቋማቱ ክፍያ ለሚኒስቴሩ እንደሚፈፅሙ ገልፀዋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎቹን ዲግሪ የሚያትመው ተቋማቱ በሚልኩት መረጃ እና የተማሪዎቹ የሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ውጤትን መሰረት በማድረግ እንደሚሆንም ጠቁመዋል፡፡

አሰራሩ ተግባራዊ ሲደረግ በሀገሪቱ የሚታየውን የሐሰተኛ ዲግሪ ህትመት ለማስቆም እንደሚያስችል ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡

መንግሥት የ Security Printing ሥራ በሀገር ውስጥ በ2017 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ እንደሚጀምር ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

@ethio_mereja_news
Breaking‼️

የተደረገው ድርድር ያስገኘው ውጤት ይፋ ሆኗል።
የዓለም ባንክ በዛሬው እለት the Ethiopia First Sustainable and Inclusive Growth Development Policy Operation በሚል ባወጣው መግላጫ ኢትዮጵያ እያከናወነች ላለችው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ለመደገፍ በርካታ የድጋፍ ማዕቀፎችን ይፋ አድርጓል።
በዚህ መሰረት ዓለም ባንክ አሁን በቀጥታ ከሚሰጠው 7 ቢሊዮን ዶላር በተጨማሪ በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት 8.5 ቢሊዮን ዶላር በመጨመር ኢትዮጵያ በጠቅላላው 15.5 ቢሊዮን ዶላር ከዓለም ባንክ ብቻ ታገኛለች። ከዚህ በተጨማሪ
♦️ 1 ቢሊዮን ዶላር ቀጥተኛ ስጦታ (grant)
♦️ 500 ሚሊዮን ዶላር የእዳ ክፍያ እንዲራዘም፤
♦️ 320 ሚሊዮን ዶላር ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ትብብር (IFC)
♦️ 1.15 ቢሊዮን ዶላር የባለብዙ ወገን ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ
♦️ 6 ቢሊዮን ዶላር በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት ለበጀት ድጎማ
♦️ 2.1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ትብብር ለኢንቨስትመንት የምታገኘውን ሲጨምር ኢትዮጵያ አሁን ከምታገኘው 7 ቢሊዮን ዶላር በተጨማሪ በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት በጠቅላላው 16̂.6 ቢሊዮን ዶላር ታገኛለች።

@ethio_mereja_news
አራት የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ሰራተኞች፤ በታጣቂዎች ታግተው ተወሰዱ‼️

በኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ ሸዋ ዞን፣ ፈንታሌ ወረዳ በሚገኘው የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ተቀጥረው የሚሰሩ አራት ሰራተኞች፤ በ“ኦነግ ሸኔ” ታጣቂ ቡድን ታግተው መወሰዳቸውን የፋብሪካው ሰራተኞች ገለፁ።

የፋብሪካው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አብዱልቃድር የሱፍ፤ በሰራተኞች ላይ እገታ ሲፈጸም በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን ተናግረዋል።

የስኳር ፋብሪካው ሰራተኞች የታገቱት ባለፈው ቅዳሜ ሐምሌ 20፤ 2016 ጠዋት ሁለት ሰዓት ገደማ መሆኑን በዕለቱ በስራ ገበታቸው ላይ የነበሩ አንድ ሰራተኛ ተናግረዋል። ከታገቱት ሰራተኞች ሁለቱ የቀን ሰራተኞች ሲሆን ሌሎቹ በፋብሪካው የሱፐርቫይዝ እና የፎርማን የስራ ኃላፊነት ያላቸውን መሆኑንም አስረድተዋል።

“ሱፐርቫይዘሩ እና ፎርማኑ ‘ኤፍ አንድ’ ከሚባለው የሸንኮራ ማሳ አካባቢ ነው የተወሰዱት። ሁለቱ የቀን ሰራተኞች ‘ኤፍ ሃያ ስድስት’ ከሚባለው የሸንኮራ ማሳ አካባቢ ነው የወሰዷቸው። የሱፐር ቫይዘሩን መኪና አቃጥለዋል።

መኪናው ሲቃጠል የፌደራል ፖሊሶች በአካባቢው ደርሰው ነበር። ግን ምንም ማድረግ ሳይችሉ፤ ሰዎቹን ታጣቂዎቹ ይዘዋቸው ሄዱ” ሲሉ በፋብሪካው ለ26 ዓመታት ያገለገሉት ሰራተኛ አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
እስራኤል እንዴት ኢራን ዉስጥ ገብታ የሃማሱን መሪ ገደለች
ቤይሩትም በቦምብ ተደብድባለች
👇👇
https://youtu.be/1f0IflxV8TM?si=itrGyrhBKtSJGcWF
ዶላር ጨምሯል በሚል የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መዉሰዱን  የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ

የአዲስ አበባ ንግድ  ቢሮ  በ13 የንግድ ድርጅቶች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ  መዉሰዱን ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታወቋል፡፡

ቢሮዉ ባደረገዉ የክትትል ስራ  በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ 11 እንዲሁም በየካ ክ/ከ 2 በድምሩ 13  የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃመዉሰዱን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ሰውነት አየለ ለጣቢያችን ተናግረዋል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ በምርቶች ላይ ጭማሪ ባሳዩ ነጋዴዎች ላይ  አስተዳደራዊ  እርምጃ መዉሰዱን ነግረዉናል፡፡

ንግድ ቢሮዉ  በከተማዉ በሚገኙ የንግድ ድርጅቶች ላይ ቁጥጥር እያደረገ መሆኑን ና ህብረተሰቡ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ድርጅቶችን ሲመለከት 8588 የነፃ መስመር ጥቆማ እንዲያደርስ አሳስበዋል ፡፡

አቤል እስጢፋኖስ (ethio_fm)

ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Hamster‼️

ሀምስተርና ታፕ ስዋፕ የምትጫወቱ ሁሉ የግድ ይህን ቻናል መቀላቀል አለባቹ።

እጅግ ወሳኝ መረጃዎችን ያደርሳል።

በዚ Link ተቀላቀሉ👇👇👇

https://www.tg-me.com/+fzeZ2gn56UE3NTI0
https://www.tg-me.com/+fzeZ2gn56UE3NTI0
https://www.tg-me.com/+fzeZ2gn56UE3NTI0
😭😭😭

ያማል

ነብስ ይማር

እሁድ እለት ሰርጉን አለሙን ለማየት ሚስቱን ሊያገባ የነበረው ወጣት ሞቶ ተገኘ

ዮናስ ይባላል የአዲስ አበባ ልጅ ሲሆን እሁድ እለት በ21.11.2016 ሰርጉን ለመደገስ ዓለሙን ለማየት

ቤተሰቡ ና ራሱ ዮናስ ዝግጅት እያደረገ እያለ እንዲሁም የሰርጉ ታዳሚዎች የሰርግ ጥሪ ወረቀት ተቀብለው በነበሩበት ስአት ነው

ዮናስ የጠፋው ነገር ግን

ራሱን አጥፎቶ ነው የሚለው ምክንያት
ጉርሻዎች ያላሳመነ ሆኖ አግኝተነዋል

ጉርሻዎች ከአንዳንድ የቤተስብ አባል ጋር ከሰኞ እለት ጀምሮ ውይይት ያደረገን ሲሆን

ዮናስ ምንም አይነት ራሱን ሊያጠፋ የሚችልበት ሁኔታ ላይ እንዳልነበረ እንዲሁም በጣም ለሰርጉ ዝግጅ ና excited ሆኖ እንደነበረ አውቀናል::

በጣም ውስብስ ያለ ና የቤተሰብ ጣልቃ ገብነት እንዲሁም በሀብታም ቤተሰብ አሳዳጊነት ያደገ ልጅ ሲሆን እጅግ ዘመናዊ ምርመራ የሚያስፈልገው ሁኖ አግኝተነዋል

ስለዚህ የአዲስ አበባ ፖሊስ ምርመራውን ከክፍል ከተማው ፖሊስ ወስዶ እንደ አዲስ ምርመራውን አድርጎ የዚህ ልጅ ነብስ ፍትህ እንድታገኝ እንዲያደርግ በትህትና እንጠይቃለን::

እሁድ እለት ሰርጉ የነበረው
ዮናስም እለተ ሰኞ ቀብሩ ተፈፅሟል::

ነብስህ ይማረው ወንድማችን

@ethio_mereja_news
ኢቢኤስ እና አርቲስት ፍቃዱ ከበደ ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል።

ኢቢኤስ ሲኒማ ለተመልካቾቹ በየዕለቱ በሚያቀርበው ጥያቄው የአርቲስት ፍቃዱ ከበደ ፎቶን በመጠቀም "የዚህችን ተዋናይት ሙሉ ስም እና ከሰራቸው ፊልሞች  መካከል አንድ ጥቀስ ?" በማለት የጠየቀው ጥያቄ መነጋገሪያ ሆኗል።በዚህም ከአርቲስቱ ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል።

አርቲስቱም በማህበራዊ ትስስር ገፁ " አንዳንድ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ነገር ፈልገዋችሁ ታዋቂ ለመሆን ሲሞክሩ አይገርምም?። በርግጥ ጉዳዩን ጠበቃዬ ይዞታል እኔ የ3 ልጆች አባት ፆታዬ ወንድ ኢትዮጵያዊ ነኝ። ከቴሌቪዥን ጣቢያው ጋር በቅርብ በጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት የምናደርግ ይሆናል"

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
" ተማሪዎችን አወዳድሬ ነው የምቀበለው " - አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ

የራስ-ገዝ ዩኒቨርሰቲ የሆነው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ከ2017 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጀምሮ በራሱ ፖሊሲና መስፈርት ፤ ምዘናና የክፍያ ስርዓት ተማሪዎችን አወዳድሮ እንደሚቀበል አሳውቋል።

በመደበኛ፣ በማታና በርቀት በቅድመ ምረቃና በድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን መከታተል ለሚፈልጉ አመልካቾች በቅርቡ ዝርዝር ማስታወቂያ እንደሚያወጣ ገልጿል።

ምንጭ፡ ቲክቫህ ኢትዮጵያ

@ethio_mereja_news
ዶላር ጨምሯል በሚል የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ 77 የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መዉሰዱን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ

ቢሮዉ ሃምሌ 23 እና 24 ቀን 2016 ዓ.ም ባደረገዉ የክትትል ስራ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ 11 እንዲሁም በየካ ክ/ከ 2 በድምሩ 13 የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መወሰዱን ያስተወቀ ሲሆን ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ በሁሉም ክፍለ ከተማ በተደረገ የአሰሳ ስራ 77 ንግድ ሱቆች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን የአዲስ አበባ ከተማ ንግድ ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ሰውነት አየለ ተናግረዋል። (መናኸሪያ ሬዲዮ 99.1)

@ethio_mereja_news
በመቀሌ ከተማ የደህንነት ካሜራ ተገጠመ‼️
ከሰሜኑ ግጭት በኃላ ወንጀል ከተበራከተባቸው የትግራይ ክልል አከባቢዎች መካከል አንዷ የሆነችው መቀለ፣ የከተማዋን ደህንነትና ፀጥታ ወደነበረበት በመመለስ ሂደት ላይ ከፍተኛ ጥቅም ይሰጣሉ በሚል የተገጠሙትን የድህንነት ካሜራዎችና መቆጣጠርያ ክፍል ላይ በትግራይ ጊዝያዊ አስተዳደር አቶ ጌታቸው ረዳ የሚመራ ልኡክ ቅኝት ማድረጉን የክልሉ መገናኛ ብዙኃን ዘግበዋል።

የተገጠሙት የደህንነት ካሜራዎች እይታ ከ200 እስከ 1ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑና የዘመኑ የመጨረሻ የቴክኖሎጂ ውጤት መሆናቸውንም የዲጂታል ትግራይ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተሩ አቶ ቴድሮስ ሲሳይ ገልፀዋል።

የመቀለ ከተማ ምክትል ከንቲባ አቶ ኤልያስ ካሕሳይ በበኩላቸው በከተማይቱ የሚስተዋሉት የፀጥታ ችግሮችና የደህንነት ስጋቶች ለመፍታት አስተዳደራቸው እየሰራቸው ካሉት ሰራዎች መካከል የድህንነት ካሜራ ገጠማው አንዱ መሆኑን የተናገሩ ሲሆን የከተማ አስተዳደሩ ከረዥም ዓመታት በኃላ ጥገና የተደረገለትን የመቀለ ሆስፒታል ጨምሮ በ2.7 ቢልየን ብር በከተማይቱ የልማት ስራዎች እየሰራ መሆኑን ገልፀዋል።(Bisrat fm)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
‹‹ ኢትዮጵያ ደሃ የማይኖርባት ሀገር እየሆነች ነው ›› - የአዲስ አበባ ነዋሪዎች🥹

ከባለፈው ሰኞ ጀምሮ ተግባራዊ የተደረገው የውጭ ምንዛሪ ተመን ማሻሻያ ‹‹ የኑሮ ውድነቱን ሰማይ ጠቀስ እያደረገው መሆኑን ›› አሻም በተለያዩ የመዲናዋ የገበያ ስፍራዎች ተገኝታ ያነጋገረቻቸው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

አንድ ሸማች ከውጭ ምንዛሪ ተመን ማሻሻያው በኋላ ስላለው የገበያ ሁኔታ ሲያስረዱ ‹‹ የዘይት ዋጋ በእጥፍ ጨምሯል፤ በአንድ ጊዜ ነው ዋጋው የናረው፤ እንደኔ ያለ ደሃ መኖር አይችልም ›› ሲሉ ብለዋል፡፡

ሌላው ለአሻም ምልከታቸውን ያጋሩ ሸማች በበኩላቸው ‹‹ በውድ ዋጋ እንኳን ለመግዛት አቅርቦት የለም፣ አጥተናል ›› ሲሉ ተደምጠዋል፡፡ አክለውም ‹‹ ዕቃውን የት እንዳደርሱት አናውቅም፤ ዘይት ፈልጌ መጥቼ ነበር፤ ግን ሁሉም ቦታ የለም ›› ብለዋል፡፡

በገበያ ዋጋ ላይ የተመሰረተ ተመን ይወጣል ከተባለ በኋላ በአጠቃላይ የዋጋ ንረቱ አይሏል ሲሉ አቤቱታቸውን ለአሻም ያሰሙት ሸማቾች ብቻ ሳይሆኑ ነጋዴዎችም ጭምር ናቸው፡፡

ለአሻም አስተያየታቸውን የሰጡ አንድ ነጋዴ ‹‹ ከጅምላ አከፋፋዮች እጅ እቃ ማግኘት አልቻልንም፤ መርካቶ ስንሄድ እቃ የለም ነው እያሉን ያሉት ›› ሲሉ የገጠማቸውን አስገንዝበዋል፡፡

በመጨረሻም ‹‹ መንግስት ቁጥጥሩን ከላይ ካላደረገ የችርቻሮ ሽያጩ ምንም ማድረግ አይችልም ›› በማለት መፍትሔ ይሆናል ያሉትን ምክረሃሳብ ለግሰዋል፡፡

(አሻም)
@ethio_mereja_news
2024/09/30 21:29:18
Back to Top
HTML Embed Code: