Telegram Web Link
ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች በራሳቸውን ገንዘብ ለመገበያየት ተስማምተዋል ተባለ!

ኢትዮጵያና የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ለግብይት የራሳቸውን ገንዘብ ለመጠቀም ስምምነት ተፈራርመዋል፡፡ስምምነቱን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ እና የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ብሔራዊ ባንክ ገዢ ካሊድ ሞሃመድ ባላማ መፈረማቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡

በዚህም በሁለቱ ሀገራት ለሚደረግ ግብይት የራሳቸውን ገንዘብ ማለትም ድርሃምና ብር ለመጠቀም ከስምምነት የደረሱ ሲሆን ሁለቱ አካላት ለተግባራዊነቱ ምቹ መደላድል ለመፍጠር ጥረት እንደሚያደርጉ ተገልጿል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ማሞ ምህረቱ የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች የኢትዮጵያ አንዷ የንግድ አጋርና የውጪ ኢንቨስትመንት ምንጭ መሆኗን ገልጸው ስምምነቱ የሁለቱን ሀገራት ግንኙነት ይበልጥ እንዲጠናከር ያደርገዋል ብለዋል።

በጋራ ጥቅም ላይ የተመሰረት ቀጣይነት ያለው ልማትና ብልጽግናን የሚያረጋግጥ ስለመሆኑም ተናግረዋል፡፡የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች ብሔራዊ ባንክ ገዥ ካሊድ ሞሃመድ ባላማ በበኩላቸው ስምምነቱ ሁለቱ ሀገራት የኢኮኖሚ ግንኙነታቸውን እያጠናከሩ መምጣታቸውን እንደሚያሳይ አመላክተዋል።

@ethio_mereja_news
ጥቆማ‼️

እንደሚታወቀው ቴሌግራም ብዙዎችን ባለገቢ እያደረገ ይገኛል።

ታድያ አሁን ላይ ታፕ ታፕ ስለሚደረጉት Hamster TapSwap BLUM እና ሌሎችም መረጃዎች ።

በዝርዝር ለማግኘት
ይህን ቻናል ይቀላቀሉ👇👇
https://www.tg-me.com/+XUeXEA4uaCM3YmVk
https://www.tg-me.com/+XUeXEA4uaCM3YmVk
...አንዳንድ ሪፖርቶች ጦር መሳሪያው የሶማሊያ መንግሥት ከኢትዮጵያ የገዛው ስለመሆኑ እየገለጹ ነው።....

የሱማሊያ የጎሳ ሚሊሻዎች ከባድ የጦር መሳሪያዎችን ጭኖ በመጓዝ ላይ በነበረና ከኢትዮጵያ የተነሳ ነው በተባለ አንድ ከባድ ካሚዮን ላይ ትናንት በፈጸሙት የደፈጣ ጥቃት በርካታ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን ዘርፈዋል።

ጋልሙዱግ ፌደራል ግዛት ውስጥ አቡድዋቅ ከተባለች አነስተኛ ከተማ አቅራቢያ የመሳሪያ ዝርፊያው በተፈጸመበት ወቅት በጎሳ ታጣቂዎቹና በካሚዮኑ አጃቢ ጸጥታ ኃይሎች መካከል በተካሄደ የተኩስ ልውውጥ፣ በትንሹ አምስት ሰዎች እንደተገደሉ ተሰምቷል።

ካሚዮኑ መትረየሶችን፣ ጸረ-አውሮፕላን መሳሪያዎችንና ቦምቦችን ጭኖ ነበር ተብሏል። የማዕከላዊ ሱማሊያ የጎሳ ታጣቂዎች ለዓመታት አልሸባብን በመውጋት የታወቁ ናቸው።

የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት፣ በሱማሊያ ላይ ለ30 ዓመታት ጥሎት የቆየውን የጦር መሳሪያ ማዕቀብ ባለፈው ታኅሳስ ሙሉ በሙሉ ማንሳቱ ይታወሳል።

አንዳንድ ሪፖርቶች ጦር መሳሪያው የሶማሊያ መንግሥት ከኢትዮጵያ መንግሥት የገዛው ስለመሆኑ እየገለጹ ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ፣ ታከለ ኡማን የኢትዮ-ጅቡቲ ባቡር አክሲዮን ማኅበር ዋና ሥራ አስፈጻሚ አድርገው ሹመዋል።

ታከለ የተሾሙት፣ ከኹለት ዓመታት በላይ አክሲዮን ማኅበሩን በዋና ሥራ አስፈጻሚነት የመሩት አብዲ ዘነበ በቅርቡ ከሃላፊነታቸው መነሳታቸውን ተከትሎ ነው።

አብዲ ከሃላፊነት ከተነሱ ወዲህ፣ የአክሲዮን ማኅበሩ የቴክኒክ ሃላፊ ዳንኤል ኃ/ሚካዔል በተጠባባቂነት ተሰይመው ነበር።

@sheger_press
@sheger_press
ህውሀት‼️

#ህወሓት በ50 አመታት ታሪኬ አጋጥሞኝ የማያውቅ ፈተና ውስጥ ነኝ አለ፣ በቀጣይ ሳምንታት የፓርቲ ጉባኤየን ለማካሄድ ወስኛለሁ ብሏል

በሰሞኑ የፓርቲው ስብሰባ ወቅት ስብሰባ ረግጠው የወጡ ከፍተኛ አመራሮች ጭምር አሉ ተብሏል

የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት #ትግራይ (ህወሓት) ለ11 ቀናት ሳካሂደው የነበረው የፓርቲው ከፍተኛ አመራር ስብሰባ እና ግምገማ አጠናቅቂያለሁ ሲል ዛሬ ሐምሌ 9 ቀን 2016 ዓ.ም ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

ሳካሂደው የሰነበትኩት በፓርቲው አመራራ ላይ ያተኮረ የ11 ቀናት ስብሰባ እና ግምገማ “ፓርቲውን ከመበታተን ሊታደግ የሚችል ጉባኤ እንዲካሄድ ምቹ ሁኔታዎችን የፈጠረ ነው” ብሏል።

በያዝነው ሐምሌ ወር 2016 ዓ.ም ባሉት ቀጣይ ጥቂት ሳምንታት የፓርቲ ጉባኤ ይካሄዳል ሲል የገለጸው የህወሓት መግለጫ “ብሔራዊ ህልውናችንን ማረጋገጥ ቀዳሚ ተልኳችን ነው” ሲል አስታውቋል።

አሁን “በፓርቲው የማዕከላዊ ኮሚቴ ውስጥ ያጋጠመው ችግር ድርጅቱ ከተመሰረተ ጀምሮ ባሉት 50 አመታት አጋጥሞኝ አያውቅም” ያለው ህወሓት ዋነኛ የለየኋቸው ችግሮቼ “ቡድንተኝነት፣ ፀረ ዲሞክራሲያዊነት፣ ጎጠኝነት እና ሙስና ወደ ላቀ ደረጃ አድጎ ፓርቲውን አላፈናፍን ከማለት ባለፈ የመፈራረስ አደጋ ደቅነውብኝ ነበር” ብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው”የሚዲያ አዋርድ”የየዘርፉ ምርጥ አስሮች (10) ይፋ ሆኑ
በታጩበት ዘርፍ ከፍተኛ የዳኞች እና የህዝብ ድምፅ ያገኙ የሚዲያ ባለሞያዎች(ጋዜጠኞች) ሁለተኛ ዙርን ተቀላቅለዋል።
በዚህኛዉም ዙር እጩዎች በዳኞች እና በህዝብ ድምፅ የሚመዘኑ ሲሆን በመጀመሪያ ዙር ያገኙት ነጥብ በዚህ ዙር አያገለግልም ፣ ሁሉም እጩዎች ነጥባቸዉ ከዜሮ የሚጀምር ይሆናል
በመጀመሪያ ዙር ላይ ተካተዉ ከነበሩ ዘርፎች መካከል በጥቂቶቹ ላይ በቀጥታ ሚዲያዉን በበላይነት ከሚከታተሉት ተቋማት ጋር በመነጋገር የተወሰኑ ማስተካከያዎችን አድርገናል።
የምርጥ 10 እጩዎች የህዝብ ድምፅ መስጠት ሂደቱ እስከ ሀምሌ 16/2016 ዓ.ም የሚቆይ
በራዲዮ ወንዶች ዜና አንባቢ ተወዳጁን ሄኖክ ወ/ገብርኤልን በመምረጥ ይሳተፉ

ለሁሉም ተወዳዳሪዎች መልካም እድል እንመኛለን
https://ethio-mediaaward.com/
" ኮድ 2 ተሽከርካሪዎች በፈረቃ እንዲንቀሳቀሱ ይደረጋል፤ ከ2 እስከ 3 ወር ባለው ጊዜ ወደ ተግባር ይገባል " - የአ/ አ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን

መቼስ እንደ ሀገር ነዳጅ ማቅረብ እያዳገተን እንደሆነ እየሰማን ነው። ተጨማሪ መንገዶችን የመስራት አቅማችን ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሟጠጠ እንደሆነ በግልጽ እያየን ነው። የትራፊክ ማኔጅመንት መስርያ ቤቱ ተቋቋመ እንጂ የትራፊክ ስርዓቱን ለማሳለጥ የሚያስችል አስተማማኝ እውቀትም ሆነ አቅም መፍጠር እንዳልተቻለም እያየን ነው ።

በዚህ ላይ የግል ተሽከርካሪ ፍላጎት ጫፉ አልተነካም። ከ 7 እስከ 8 ሚሊየን ሕዝብ በሚኖርባት አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ 350 ሺ የግል ተሽከርካሪ ማለት ኢሚንት ነው። ፍላጎቱ ገና በሚሊየኖች ያድጋል። እንደ መርህ ለዚህ ፍላጎትና እድገት የሚመጥን ዘለቄታ ያለው መፍትሔ ከማመንጨት ይልቅ እቀባ፣ እገዳ ክልከላና ፈረቃ መፍትሔ ሆኖ ቀርቧል።

መስርያ ቤት ተቋቁሞ፣ አማራጭ ተፈትሾና እውቀት ተቀምሮ መንገድ በሌለበትና የሕዝብ ትራንስፖርት አስማት በሆነበት ከተማ መፍትሔው በግል ተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ላይ ማዕቀብ መጣልና ሌላ ጭንቅንቅ መፍጠር ከሆነ ትርጉም ያለው መፍትሔ ማመንጨት እስኪቻል ትምህርት ቤት፣ የስራ ቀን፣ ከቦታ ቦታ መዘዋወር፣ ተንቀሳቅሶ መስራት፣ በዓል ማክበር፣ ፍጆታን መሸመት፣ ርቆ መጓጓዝና መዝናናት በጥቅሉ ኑሮአችን በፈረቃ ቢደረግ መልካም ነበር።

@sheger_press
@sheger_press
በአማራ ክልል በቀጠለው ግጭት ሰሜን ወሎ ውስጥ ሲቪሎች መገደላቸው ተገለፀ።

በሰሜን ወሎ ዞን ጉባላፍቶ ወረዳ ውድመን በተባለ ስፍራ፣ በመንግስት ሀይልች እና በፋኖ ሀይሎዎች መካከል ባለፈው ሳምንት ዐርብ መካሔዱ በተገለጸው የተኩስ ልውውጥ፣ ስድስት ያልታጠቁ ሰዎች መገደላቸውን፣ የሟች ቤተሰብ እና የአካባቢው ነዋሪ ለአሜሪካ ድምፅ ተናግረዋል፡፡

ከሟቾቹ ውስጥ አምስቱ የቅርብ ዝምድና እንዳላቸው አስተያየት ሰጭዎቹ ጠቅሰው፣ ከእነርሱም ሦስቱ አባት እና ልጅ መኾናቸውን አመልክተዋል፡፡

የጉባላፍቶ ወረዳ አስተዳደር፣ የደረሰውን ጉዳት አምኖ መጠኑን ግን በዝርዝር ከመግለጽ ተቆጥቧል፡፡ የወረዳው አስተዳዳሪ ሻለቃ ያሬድ አባተ፣ “ከመንግሥት በተቃራኒ የቆሙ” ሲሉ የጠሯቸው አካላት፣ በሕዝቡ መሀል ሳሉ የተኩስ ልውውጥ ስለሚደረግ ባልታጠቁ ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱን አስረድተዋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
#Notcoin

❤️Telegram wallet verify ማድረግ ያልቻላችሁ ወይም tonkeeper ላይ notcoin ያላችሁ መሸጥ የምትፈልጉ


😄 በዚህ አናግሩን 👉 @Birukepromo

❤️ልብ ይበሉ

በእነዚህ user name መጥታችሁ ስትገበያዩ ገንዘባችሁ 100% ይሰጣችኋል (ሀላፊነቱን @sheger_press ይወስዳል)

ክፍያው እንደ ስምምነታችሁ ይፈፀማል

በእነዚህ ሰዎች ለመገበያየት ስትሄዱ ያላችሁ ስክሪንሽት አድርጋችሁ ማሳየት ግድ ነው

ton space ቤታ ከሆነ ኮይናችሁ ደግሞ 0.2 ክፍያ ስለሚጠይቅ ቶን ኮይን ከሌላችሁ ቅድሚያ ከፍላችሁ መውሰድ

notcoinu ልካችሁ ስትጨርሱ አድሚኑ በተስማማቹበት ዋጋ ብራችሁ መልሶ ያስገባል!!


🚫ለማጭበርበር የምትመጡ ካላችሁ ወዲያው Block ሰለምናረጋችሁ አትልፉ እንዳመጡ!!

ሲቀጥል የማትሸጡ አትምጡ ጊዜያችን አታቃጥሉ

ለተለያዩ ONLINE ስራዎች ለመስራት ይህን ቻናል ይቀላቀሉ👇👇
https://www.tg-me.com/sheger_crypto
4 ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ 9 ሰዎች አንድ የኬንያ የወርቅ ማውጫ ተደርምሶባቸው ሞቱ

ኬንያና ኢትዮጵያ ድንበር ላይ የሚገኝ አንድ የወርቅ ማውጫ ተደርምሶ ስራ ላይ ከነበሩት ሰዎች ኢትዮጵያውያንን ጨምሮ ቢያንስ አምስቱ ሞቱ። ሌሎች ቁጥራቸው ያልተገለፀ ሰዎችም ቆሰሉ። ይኽው ሂሎ የተባለው የወርቅ ማውጫ በአካባቢው ነዋሪዎች መካከል በቦታው የይገባኛል ጥያቄ በተነሳ ግጭት ሰበብ የሰዎች ሕይወት ከጠፋ በኋላ ስፍራው ባለፈው መጋቢት ወር ቢዘጋም ማዕድን ቆፋሪዎች ወርቅ ፍለጋውን ቀጥለው ነበር።
ባለፈው ሰኞ ምሽት አንድ ሺህ የሚሆኑ ሰዎች አካባቢውን በኃይል በመውረር በተከለከለው ስፍራ ቁፋሮ ማካሄዳቸውን አንድ የአካባቢው ከፍተኛ ባለሥልጣን ተናግረዋል። ቁጥራቸው ከፀጥታ ኃይሎች የሚበልጠው እነዚሁ ሰዎች የሚቆፍሩበት ስፍራ ተደርምሶ ቢያንስ አምስት ሰዎች በአፈሩ ውስጥ ተቀብረዋል። አንድ የአካባቢው አዛውንት ከስፍራው 9 አስከኖች ሲወጡ ማየታቸን ተናግረዋል። ከ9ኙ አምስቱ ኬንያውያን አራቱ ደግሞ ኢትዮጵያውያን መሆናቸውን ተናግረዋል። ባለፈው ግንቦት ወርም አምስት የወርቅ ማውጫ በተመሳሳይ ሁኔታ ሕይወታቸው አልፏል።(DW)

@ethio_mereja_news
📹የሚሸጥ የዩቱብ ቻናል
https://www.youtube.com/@Megenagnadaily
    STRICK FREE
    COPYRIGHT FREE
    MONITIZED የሆነ 💰 በውስጡ አለው


🛑 channel እንፈልጋለን ላላቹኝ

🔔• 1,289 SUBSCRIBE

•➤አሁኑኑ ያናግሩን 👇

📩 •➤ 𝐈𝐧𝐛𝐨𝐱 𝐌𝐞
@biruke29
@Ethio_journalist
ኢራን በትራምፕ የግድያ ሙከራ እጄ የለበትም አለች

ቴህራን በሪፐብሊካን ፓርቲ ላይ ጥቃት ለመሰንዘር እያሴረች ነው የሚለው የሲኤንኤን ውንጀላ ፖለቲካዊ ዓላማዎች እና እቅዶች ያሉት ነዉ ብላለች

ኢራን በ ፕሬዝዳንታዊ ዶናልድ ትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራ እያሴረች ነዉ የሚለዉን ዘገባ ዉድቅ ስታደርግ ነገር ግን ለቴህራን ከፍተኛ ጄኔራሎች ለአንዱ ግድያ የበቀል እርምጃ መዉሰዷ እንደማይቀር አስታዉቃለች፡፡

የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ናስር ካናኒ ዉንጀላዉን በመቃወም ቴህራን "በቅርቡ በትራምፕ ላይ በተፈጸመው የትጥቅ ጥቃት ውስጥ ማንኛውንም አይነት ተሳትፎ እንደሌላት ተናግረዋል፡፡

ሪፖርቱን በመቃወም እንዲህ ያሉ ክሶች ተንኮል-አዘል የፖለቲካ ዓላማዎች እንዳሉት ይቆጥረዋል"ብለዋል ሲል አር ቲ ዘግቧል ፡፡

በአቤል እስጢፋኖስ
ሐምሌ 10 ቀን 2016 ዓ.ም

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የትግራይ ክልል ግዜያዊ አስተዳደር በትናንትናዉ ዕለት በመጀመሪያ ዙር ቁጥራቸው ከ14 ሺሕ የሚበልጡ ተፈናቃዮችን ወደ አላማጣ ከተማ መመለሱንና እና በቀጣዮቹ ሦስት ቀናት ተጨማሪ አምስት ሺሕ ገደማ ሰዎችን ከተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች ወደ አካባቢው “እንደሚመልስ” በጊዜያዊ አስተዳደሩ የአላማጣ ከተማ ከንቲባ ተደርገው የተመደቡት ዝናቡ ደስታ ለዋዜማ ተናግረዋል።

@ethio_mereja_news
ተይዘዋል
'ሎተሪ ደርሰዎታል' በሚል ከግል ተበዳይ 99 ሺ ብር በማታለል የዘረፉ ተጠርጣሪዎች ተያዙ

ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ  ዋና መስሪያ ቤት ነው የምንደውለው እድለኛ ነዎት እንኳን ደስ አለዎት ሎተሪ ደርሰዎታል በማለት የግል ተበዳይን 99 ሺህ ብር በማታለል የዘረፉ ተጠርጣሪዎች ተይዘው ምርመራ እየተጣራባቸው መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገልጿል።

የግል ተበዳይ የአጭበርባሪዎቹን የእንኳን ደስ አሎት ዜና ከሰሙ በኋላ 'የምንነግርዎትን ቁጥሮች ይንኩ' በሚል የተነገራቸውን የማጭበርበር ተግባር ይፈጽማሉ። ተበዳይ መጭበርበራቸው የገባቸው ግን ከባንክ ሂሳባቸው ላይ ገንዘብ መቀነሱን የሚገልጽ መልዕክት በስልካቸው ሲደርሳቸው ነው።

ይህንኑ ለፖሊስ ያመለክታሉ፤ ፖሊስ ለግለ ተበዳይ የተደወለበትን ስልክ መነሻ በማድረግ ማስረጃ በማሰባሰብ ባደረገው ክትትል ሰኔ 26 ቀን2016 ዓ.ም በለሚ ኩራ ክ/ከተማ  ወረዳ  8 አካባቢ የመጀመሪያውን ወይም ለግል ተበዳይ የደወለውን ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ማዋሉን በልደታ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የጎማ ቁጠባ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ አስታውቋል።

ተጨማሪ ምርመራ በማስፍት ለወንጀሉ ተባባሪ የሆነ አንድ ግለሰብ የተያዘ ሲሆን ከፍርድ ቤት የመበርበሪያ ትዛዝ በማውጣት በተደረገ ብርበራ ከመኖሪያ ቤቱ ውስጥ 89 የሚሆኑ የተለያየ መስሪያ ቤት ማህተሞች ያለበት  ልዩ ልዩ ሀሰተኛ ሰነድ፣ 19 የተለያዩ የባንክ ደብተሮች፣ 7 ኤቲኤም ካርዶች፣ 5 የተለያዩ ግለሰቦች መታወቂያ፣ 6 ፖስፖርት እና 13 ሲም ካርድ ማቀፊያ በብርበራ ሊገኝ ችሏል ብሏል፡፡

ማህበረሰቡ ተገቢ የሆነ ጥንቃቄ ሊያደርግ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልእክቱን አስተላልፏል፡፡
በምዕራብ ጎንደር ቋራ የ"ፋኖ ታጣቂዎች" ፈጸሙት በተባለ ጥቃት በርካቶች መገደላቸውን እና 10 ሺህ የሚሆኑ መፈናቀላቸው ተነገረ!

“የፋኖ ታጣቂዎች” በአማራ ክልል ምዕራብ ጎንደር ዞን ቋራ ወረዳ በሚገኝ “የአገው ተወላጆች” መኖሪያ ቀበሌ ላይ ፈጸሙት በተባለ ጥቃት ከ10 ሺህ በላይ ነዋሪዎች መፈናቀላቸውን የአካባቢው ባለሥልጣናት፣ ሰባት ተፈናቃዮች ተናገሩ።

ለነዋሪዎቹ መፈናቀል ምክንያት በሆነው ጥቃት “ህጻናትን” ጨምሮ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ በርካታ ነዋሪዎች መገደላቸው እንዲሁም በርካታ ቤቶች መቃጠላቸውን የዐይን እማኞች ገልጸዋል።በአማራ ክልል ከመንግሥት ጋር ውጊያ ላይ የሚገኙት “የፋኖ ታጣቂዎች” በይካዎ ቀበሌ ላይ ጥቃት የፈጸሙት ባለፈው ሳምንት ማክሰኞ ሐምሌ 3/2016 ዓ.ም. እንደሆነ የቀበሌው ሊቀ መንበር አቶ አለማየሁ ታሌ እና ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ጥቃት የደረሰበት ይህ ቀበሌ በአብዛኛው “የአገው ተወላጆች” የሚኖሩበት እንደሆነ ቢቢሲ ያነጋገራቸው ሁለት አካባቢው ኃላፊዎች እና ነዋሪዎች አስረድተዋል።የቀበሌው ነዋሪዎች እንደሚያስረዱት የማክሰኞ ዕለቱ ጥቃት ከመፈጸሙ አስቀድሞ “የፋኖ ታጣቂዎች እና የቀበሌው ሚሊሻዎች” ለአራት ቀናት ውጊያ ላይ ቆይተዋል ብለዋል።

https://www.bbc.com/amharic/articles/cd16xl3zwqgo

(BBC amharic)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የታጋች ተማሪዎች ደኅንነት እንዳሳሰባቸው በቤዛ ክፍያ የተለቀቁ ተማሪዎች ገለፁ

ከሁለት ሳምንት በፊት፣ በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን በገርበ ጉራቻ ከተማ አቅራቢያ እስከ አሁን በታጣቂዎች ታግተው የሚገኙ የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ደኅንነት እንደሚያሳስባቸው፣ በቅርቡ “የቤዛ ገንዘብ ከፍለን ተለቀናል” ያሉ ተማሪዎች ገልጸዋል፡፡

ለደኅንነታቸው በመስጋት ስማችን እንዳይጠቀስ ያሉ ለአሜሪካ ድምፅ አስተያየታቸውን የሰጡት ተማሪዎች፣ “ሸኔ” ብለው በጠሩት ታጣቂ ቡድን ታግተው መቆየታቸውንና ከ50 ሺሕ እስከ 300ሺሕ ብር የቤዛ ገንዘብ ከፍለው መለቀቃቸውን ተናግረዋል፡፡

በታጣቂ ቡድኑ ቁጥጥር ሥር በነበሩባቸው ቀናት፣ “ብዙ ድብደባ እና እንግልት ይደርስብን ነበር፤” ያሉት ተማሪዎቹ፣ አሁንም በታጣቂዎቹ እጅ እንደሚገኙ የጠቆሟቸው 67 ታጋቾች፣ “በከፍተኛ ሥቃይ ውስጥ መኾናቸው በእጅጉ አሳስቦናል፤” ሲሉም አመልክተዋል፡፡

via VOA

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሾኔ

" የደመወዝ ጥያቄ እንዳንጠይቅ በፖሊስ መደብደባችንን እና መታሰራችን የኢትዮጵያ ህዝብ ይወቅልን !! " - የሾኔ ሆስፒታል ጤና ባለሙያዎች እና ሰራተኞች

" ከግንቦት ወር ጀምሮ ደመወዝ አልተከፈለንም " ያሉ የሾኔ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎችና ሰራተኞች ያሉበትን ችግር እና ቅሬታቸውን ለመግለጽ ወደዞን መምሪያ በመሄድ ላይ ሳሉ በፖሊስ ተደብድበው መመለሳቸውን ለቲክቫህ ተናግረዋል።

" ሰራተኞቹ ደመወዝ እና ጥቅማጥቅም ካየን ይሄው ሶስተኛ ወራችን ቢሆንም የሆስፒታሉ አመራሮችም ሆኑ ዞኑ ለጥያቄያችን ምላሽ መስጠት እንኳን አልፈለጉም " ብለዋል።

" ይህንም ተከትሎ ለሆስፒታሉ አመራር ከዚህ በላይ መታገስም ሆነ ችግሩን መቋቋም እንደማንችል በደብዳቤ አሳዉቀን ሁኔታውን በተጨማሪ ለሀድያ ዞን አስተዳደር ለማሳወቅ ስናቀና የዞኑ  ፖሊስ ደብድቦ መልሶናል " ሲሉ ተናግረዋል።

" በህዝብ ትራንስፖርት ተሳፍረን ስንሄድ የዞኑ ፖሊስ ዱራሜ ላይ አስቁሞ በሀይል በማስወረድና በመደብደብ  ወደመጣንበት እንድንመለስ አደረገን " የሚሉት ሰራተኞቹ ወደ ሾኔ ሲመለሱ መሪዎች ናቸው የተባሉ ጥቂት ሰዎች ለሰአታት ታስረው መፈታታቸው ገልጸዋል።

"ከችግራችን በላይ እየደረሰብን ያለውን ግፍ የኢትዮጵያ ህዝብ ይስማልን"ያሉት የሆስፒታሉ ሰራተኞች"በዚህ አመት ከተከለከልነው ደሞዝ ባለፈም በ2015 ዓ/ም ያልተከፈለ  ውዝፍ ገንዘብ ነበረን " ብለዋል።

ዘጋቢው ቲክቫህ ኢትዮጵያ የሰራተኞችን የደረሰባቸውን ነገር እና ቅሬታቸውን ይዞ የሾኔ የመጀመሪያ ሆስፒታል ሜዲካል ዳይሬክተእ አቶ አህመድ መሀመድን አነጋግሯል።

እሳቸውም ሰራተኞቹ በደብዳቤ ስራ ማቆማቸውን ገልጸው ወደስራ መመለስ የሚፈልግ ደብዳቤ በማስገባት ስራ መጀመር እንደሚችልና የአንድ ወር ደመወዝም እንደሚከፈለው ገልጸዋል።

@ethio_mereja_news
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ6ተኛ ክፍል ውጤት ይፋ አደረገ‼️

ቢሮው የ2016 የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና የማለፊያ ነጥብ 50 ከመቶ እንዲሆን ተወስኗል ብሏል፡፡

ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ደግሞ 45 ከመቶ እንዲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት ወስኗል፡፡

በ2016 የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ 85ሺ 46 በመንግስትና በግል ትምህርት ቤቶች በቀን እና በማታ ትምህርታቸውን ከተከታተሉ ተማሪዎች መካከል 94 ነጥብ 3 የሚሆኑ ተማሪዎች 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ አምጥተዋል፡፡

ቀሪ 5 ነጥብ 7 ከመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ማለፊያ ነጥብ አላመጡም ሲል ትምህርት ቢሮው ካወጣው መረጃ ለመረዳት ተችሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/09/29 23:31:59
Back to Top
HTML Embed Code: