Telegram Web Link
አማራ ክልል በመንግስት የፀጥታ ኃይሎችና በፋኖ ኃይሎች መካከል አመት በሞላው ግጭት ሳቢያ:-
ከ12 እስከ 13 ቢሊዮን ብር የሚገመት ንብረት ወድሟል።
ንጹሃን ተገድለዋል።
ከ3 ነጥብ 6 ሚሊዮን በላይ ህጻናት ከትምህርት ገበታ ዉጭ ሆነዋል።
የኢኮኖሚ እንቅስቃሴ ክፉኛ ተጎድቷል።
የግልና የመንግስት ተቋማት ከቦታ ቦታ መንቀሳቀስ ባለምቻላቸው ምክንያት የአገልግሎት አሰጣጥ ከፉኛ ተዛብቷል።
ነፍሰጡር እናቶች በአግባቡ የአምቡላንስና የወላድ አገልግሎት አያገኙም።
እናቶችና ህጻናት ከጦርነት ተሳትፎ ዉጭ የሆኑ የክልሉ ዜጎች ለከፋ የስነ ልቦና ጫና ተዳርገዋል።
እገታ ተስፋፍቷል።
ዜጎች ያለከልካይ በጠራራ ጸሃይ ይዘረፋሉ፤ ይገደላሉ።
ታላላቅ ፕሮጀከቶች ተስተጓጉለዋል።
ሕዝቡ ለሁለት ወገን ግብርና ቀረጥ ይከፍላል እና ሌሎች መሰል ጉዳዮች ግጭቱ ካመጣቸው መዘዞች በጥቂቱ ናቸው ሲል የእርቅና ድርድር አመቻች ካውንስል ዛሬ በሰጠው መግለጫ አስረድቷል።

(wasu mehammed)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በሀይል ሊመጣ የሚችል ድል እንደሌለ በትግራይ፣ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች በተካሄዱ እና አሁንም እየተካሄዱ ባሉ ግጭቶች አይተናል፣ በዚህ መልኩ የሚመጣ ድል ቢኖርም ዘላቂነቱ አጠራጣሪ ነው።

ስለዚህ ይህ ካውንስል አሁን ላይ ያወጣውን መግለጫ ሁሉም አካላት በበጎ በማየት እና ጦርነቱን በሰላም ለመቋጨት ቁርጠኝነት በማሳየት ህዝቡን እንዲያሳርፉት ሁላችንም ድምፅ መሆን ይገባናል።

መሳርያ ይዞ የሚዋጉት አካላት ላይ እየደረሰ ያለውን ጉዳት ሳይጨምር ባለፉት ጥቂት ቀናት ብቻ ታጣቂዎች የሚፈፅሙትን የደፈጣ ጥቃት ተከትሎ በወታደሮች በተፈፀሙ ጥቃቶች የሞቱ ዜጎች ቁጥር ከመቶ በላይ ሆኗል።

#Peace

EliasMeseret
@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ዩኒቨርሲቲዎች የቀጣይ ዓመት የምግብ በጀት ካልተስተካከለላቸው ተማሪዎችን መቀበል እንደማይችሉ አስታወቁ

ማረሚያ ቤቶችም ታራሚዎችን መመገብ እንደከበዳቸው ተነግሯል

በተለያዩ የአገሪቱ ከተሞች በመንግሥት ተገንብተው ተማሪዎችን በራሳቸው ወጪ እያስተናገዱ ያሉ ዩኒቨርሲቲዎች፣ እንዲሁም የፌደራል ማረሚያ ቤቶች በቀጣይ ዓመት የሚመደበው የምግብ በጀት ካልተስተካከለ ምግብ ማቅረብ አዳጋች እንደሚሆንባቸው አስታወቁ፡፡ዩኒቨርሰቲዎች ተማሪ ለመቀበል የማይችሉበት ደረጃ እንደሚደርሱ ተናግረዋል፡፡

መንግሥት በየዓመቱ መጨረሻ ለመጪው በጀት ዓመት ለተቋማት የሚደለድለውን ዓመታዊ በጀት ተከትሎ፣ በርካታ ዩኒቨርሲቲዎች ጥያቄ ሲያቀርቡበት የኖረውና ለአንድ ተማሪ የሚመደብ የአንድ ቀን ወጪ 22 ብር እስካሁን መልስ ማግኘት አልቻለም፡፡ በተመሳሳይ በማረሚያ ቤቶች ለታራሚዎች የሚቀርበው ገንዘብ በቂና ጥራት ያለው ምግብ ለማቅረብ መቸገራቸውን ገልጸዋል፡፡
(Reporter)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ዝናቡ ስለሚያይል ጥንቃቄ ይደረግ

- የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት

በዘንድሮው ክረምት ከመደበኛ በላይ ዝናብ ሊያጋጥም ስለሚችል አደጋ እንዳይከሰት ጥንቃቄ ማድረግ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት አሳሰበ።

በኢንስቲትዩቱ የሚቲዎሮሎጂ ትንበያና ቅድሚያ ማስጠንቀቂያ ምርምር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አሳምነው ተሾመ (ዶ/ር) ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት እንዳስታወቁት፤ ከባድ የክረምት ዝናብ በሚፈጥረው “ላሊና” ምክንያት በቀጣይ ጊዜያት ከመደበኛ በላይ የሆነ የዝናብ መጠንና ሥርጭት ሊፈጠር ይችላል።

ከባድ የዝናብ ስርጭቱ ሊያስከትል የሚችለውን ጎርፍና መሰል ጉዳት ለመከላከል ተቋማት የቅድመ ዝግጅት ተግባራትን አጠናክረው መሥራት ይጠበቅባቸዋል ሲሉ አስረድተዋል።(EPA)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የመቀሌ ከተማ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት ባለፉት 11 ወራት ውስጥ በከተማው 12 ሴቶች ተገድለው በድምሩ ከ4 ሺህ በላይ ወንጀሎች ተፈጽመዋል አለ።

ከሰሞኑን የዘጠኝ ወር ሪፖርት ተብሎ በተለያዩ ሚዲያዎች ሲሰራጭ የነበረው መረጃ የ11 ወራት ሪፖርት መሆኑን የከተማው ፖሊስ ጽህፈት ቤት አስታውቋል።

በ2016 ባለፉት 11 ወራት 4 ሺህ 340 ወንጀሎች የተመዘገቡ ሲሆን ወንጀሎቹ 7 ዓይነት ናቸው።
12 ሴቶች ሲገደሉ፣
80 የአስገድዶ መደፈር፣
1 ሺህ 953 የስርቆት፣
583 የድብደባ፣
178 የግድያ ሙከራ እንዲሁም
10 የጠለፋ ወንጀሎች መሆናቸውን የመቀሌ ከተማ ፖሊስ ገልጿል።

ወንጀሎችን ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከ170 በላይ የማህበረሰብ አቀፍ የፖሊስ ሃይሎችን የማጠናከር ስራ እየተሰራ መሆኑ የተገለጸ ሲሆን የህብረተሰቡ ተሳትፎ በእጅጉ ያስፈልጋል ተብሏል።

በቅርቡ በክልሉ ዋና ከተማ እና ሌሎችም አካባቢዎች በሴቶች ላይ የሚደርሰውን ግድያ እና አፈና ለማውገዝ ሰላማዊ ሰልፎች እንደተካሄዱ መዘገባችን አይዘነጋም።(wasu)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
"የኢትዮጵያ ከሱማሌላንድ ጋር የገባችውን ስምምነት ካቋረጠች የሆብዮ ወደብ እንድትጠቀም እፈቅዳለሁ" የሞቃዲሾ አስተዳደር

በኢትዮጵያ እና በሶማሊያ መካከል የተፈጠረውን አለመግባባት ለመፍታት በቱርክ አስታራቂነት ሁለቱን ሀገራት በአንካራ የድርድር ጠረጴዛ ላይ መቀመጣቸው ተሰምቷል።

በኢትዮጵያ እና በሞቃዲሾ አስተዳደር መካከል በሚካሄደው ውይይት የጋራ ስምምነት ላይ ለመድረስ ሲሆን የውይይቱ አጀንዳ የኢትዮጵያና የሶማሌላንድ ስምምነት እና በቀጠናው ያለውን ዲፕሎማሲያዊ ቀውስ ያካትታል ተብሏል።

ዛሬ በአንካራ እየተካሄደ ይገኛል በተባለው ዉይይት የሶማሊያ ባለስልጣናት ኢትዮጵያ ከሶማሌ ላንድ ጋር የገባችውን ስምምነት ካቋረጠች ኢትዮጵያ በ ጋልሙዱግ ግዛት የሚገኘውን የሆብዮ ወደብ እንድትጠቀም አቅደዋል ነዉ የተባለዉ።

በሁለቱም ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች አማካኝነት በጠረጴዛ የተቀመጡት ሀገራቱ ኢትዮጵያ ከሞቃዲሾ አስተዳደር ጋር ስምምነት ላይ ከደረሰች እና ወደ የሆብዮ ወደብ ካቀናች በቀጣናው ያላትን ተፅዕኖ የበለጠ እንደምታሳድግ ይጠበቃል።
Capital

@ethio_mereja_news
በአማራ ክልል “ድጋሚ ግብር ካልከፈላችሁ ማዳበሪያ አታገኙም” የተባሉ አርሶ አደሮች የዘር ጊዜ ሊያልፍባቸው ነው😭

ግጭት ባለባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ለሁለት ወገን ግብር እንዲከፍሉ የተገደዱ አርሶ አደሮች “ግብር ካልከፈላችሁ ማዳበሪያ አታገኙም” መባላቸውን ለዋዜማ ተናግረዋል።

በአማራ ክልል ግጭት ባለባቸው አካባቢዎች አርሶ አደሮች የግብርና ማዳበሪያ ለማግኘት ግብር መክፈል እንደግዴታ በመቀመጡና ግብር እንክፈል ሲሉ የሚሰበስብ አካል በመጥፋቱ የአዝመራው ወቅት ሊያልፋቸው መሆኑንም ያስረዳሉ።

አርሶ አደሮቹ በተለይ የፋኖ ታጣቂዎች በሚንቀሳቀሱባቸው አካባቢዎች ታጣቂዎቹ አስቀድመው ግብር እየሰበሰቡ መቆየታቸውን ገልፀው፣ ድጋሚ ለመንግስት ግብር ከፍለው ማዳበሪያ ለማግኘት የጠየቁ አርሶ አደሮች ግብር የሚሰበስብ አካል አለማግኘታቸውን ነግረውናል።

“አርሶ አደሩ ማዳበሪያ እንዲቀርብለት በድጋሚ ግብር ለመክፈል ቢስማማም…..ማን ሰብስቦ ማን ያድረስው? ” ሲሉ ዋዜማ ያነጋገረቻቸው አርሶ አደሮች በዘር ወቅት ችግር ላይ መውደቃቸውን ገልጠዋል፡፡
በአንዳንድ ታጣቂዎች በተቆጣጠሯቸው አካባቢዎች አርሶ አደሩ ቀድሞ የማዳበሪያ መግዣ ገንዘብ ሰብስቦ ከላከ በኋላ አቅርቦት በትንሹ ተጀምሮ ነበር።

በመንግሥት በኩል ማዳበሪያ ሳይቀርብላቸው የዘር ወቅት የደረሰባቸው አርሶ አደሮች አቅርቦት ካላቸው አጎራባች አካባቢዎች ከነጋዴ በውድ ዋጋ እየገዙ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ በመንግስት በኩል 4ሺህ ሁለት መቶ ብር የሚሸጠውን ማዳበሪያ ከግለሰብ ነጋዴዎች በስምንት ሺህ ስምንት መቶ ብር ለመግዛት እንደተገደዱ አርሶ አደሮቹ ይናገራሉ።
በዘንድሮው አመት የአማራ ክልል ስምንት ሚሊየን ኩንታል ማዳበሪያ ቢገዛም ወደ ክልሉ የደረሰው አራት ሚሊየን ስምንት መቶ ሺህ ኩንታል ብቻ ነው። ከዚህም ወስጥ የተወሰነው በግለሰብ ነጋዴ እጅ መግባቱ ለአርሶ አደሩ ችግሩን አወሳስቦበታል።

ዋዜማ የአርሶ አደሮቹን ጥያቄ ይዛ የክልሉን ግብርና ቢሮ ጠይቃለች፡፡
የቀረቡት ችግሮች ክልሉ ካለበት ሁኔታ አንጻር በተለያዩ ክፍተቶች የተፈጠሩ መሆናቸውን የክልሉ ግብርና ቢሮ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አምሳሉ ጎባው ለዋዜማ ገልጸዋል፡፡ የፋኖ ታጣቂዎች ወጣ ገባ በሚሉባቸውና በተቆጣጠሯቸው አካባቢዎች አርሶ አደሩ ገጥሞኛል ላለው ግብርን እንደ መያዣ አድርጎ ማዳበሪያ አለማቅረብ “እንደዚያ ሊገጥም ይችላል” ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

ለዚሁ ችግር “አመራር ሁሉ አንድ አይደለም” በማለት የየአካባቢውን አመራር ተጠያቂ ያደረጉት ቃል አቀባዩ፣ አርሶ አደሩ ግብር ካልከፈልክ ማዳበሪያ አታገኝም መባሉ ስተት ነው ብለዋል፡፡

ቢሮው “ግብረናንን ተንተርሶ ግብር፣ የስፖርት፣ የቀይ መስቀል” የሚባሉ ክፍያዎችን ማዳበሪያን እንደ መያዣ አድርጎ መሰብሰብ አይቻልም የሚል መመሪያ መስጠቱን ገልጠዋል፡፡ ችግሩ የተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚገኙ አርሶ አደሮች ችግሩን ለግብርና ቢሮ ሪፖርት ማድረግ እንደሚችሉም ጠቁመዋል፡፡
ከአቅርቦት እጥረት ጋር በተያያዘ የቀረበውን ቅሬታ “እንኳንም ክልሉ በቀውስ ውስጥ ሆኖ በማንኛውም ሁኔታ ይከሰታል” በማለት አርሶ አደሮች ያነሱት እጥረት አምነዋል፡፡

ቃል አቀባዩ ማዳበሪያ በነጋዴ እጅ ስለመግባቱ በሰጡት ምላሽ “በወሬ ደረጃ ይባላል” በማለት ለቀረበው ቅሬታ የጸጥታ አካሉን ተጠያቂ አድርገዋል፡፡ ስለ ሁኔታው ሲስረዱም “ግብርና እጃችን ላይ ያለው እስኪብርቶና ወረቀት ነው፣ ሕግ የምናስከበርበት አቅም የለንም” ብለዋል፡፡ ግብርና ቢሮ ዋና ሚናው አቀርቦት መሆኑን የጠቆሙት ቃል አቀባዩ ቢሮው ያቀረበው ማዳበሪያ “አቅርቦቱን ሕገ ወጥ ሲወስደው ፖሊስ የት አለ?” ሲሉም ጠይቀዋል፡፡ [ዋዜማ]

@ethio_mereja_news
ቱርክ፣ ኢትዮጵያንና ሱማሊያን በባሕር በር ውዝግባቸው ዙሪያ ዛሬ አንካራ ውስጥ እንዳደራደረች ከባለሥልጣናት ምንጮች መስማቱን ጠቅሶ ሮይተርስ ዘግቧል።

ኾኖም ኹለት ለድርድሩ ቅርብ የኾኑ ምንጮች የድርድሩ ግብ ምን እንደኾነ ግልጽ እንዳልኾነና ከድርድሩ ኹነኛ ውጤት የመገኘቱ እድሉ ዝቅተኛ መኾኑን መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል።

የኢትዮጵያ፣ ሱማሊያና ቱርክ ባለሥልጣናት በቱርክ-መራሹ ድርድር ዙሪያ አስተያየት ከመስጠት እንደተቆጠቡ ዜና ምንጩ ገልጧል። የሶማሊላንድ ራስ ገዝ መንግሥት ቃል አቀባይ ግን፣ ሶማሊላንድ በቱርክ አደራዳሪነት በሚካሄደው ድርድር ውስጥ ተሳታፊ እንዳልኾነች ተናግረዋል ተብሏል።

የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር፣ ከሱማሊያ ጋር በቱርክ አመቻቺነት ዛሬ ይደረጋል ስለተባለው ንግግር ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ ያለው ነገር የለም። 

@ethio_mereja_news
ግጭት ባለባቸው የአማራ ክልል አካባቢዎች ለኹለት ወገን ግብር እንዲከፍሉ የተገደዱ አርሶ አደሮች “ግብር ካልከፈላችሁ ማዳበሪያ አታገኙም” እንደተባሉ ለዋዜማ ተናግረዋል።

ኾኖም ድጋሚ ለመንግሥት ግብር ከፍለው ማዳበሪያ ለማግኘት የጠየቁ አርሶ አደሮች፣ ግብሩን የሚሰበስብ አካል እንዳላገኙ ገልጸዋል።

አንዳንድ አርሶ አደሮች መንግሥት 4 ሺህ 200 ብር የሚሸጠውን ማዳበሪያ ከአጎራባች አካባቢዎች በ8 ሺህ 800 ብር  ከነጋዴ በውድ ዋጋ እየገዙ መኾኑን ጠቁመዋል።

የክልሉ ግብርና ቢሮ ስለ አርሶ አደሮቹ ቅሬታ ተጠይቆ፣ እንደዚያ ዓይነት ኹኔታ ሊያጋጥም እንደሚችል ጠቅሶ፣ ግብር ካልከፈላችሁ ማዳበሪያ አታገኙም ማለት ግን ስህተት እንደኾነና በጉዳዩ ላይ መመሪያ አስተላልፎ እንደነበር ለዋዜማ ገልጧል።

ማዳበሪያ በነጋዴዎች እጅ መግባቱን በተመለከተ፣ ለችግሩ ተጠያቂው የክልሉ ጸጥታ ኃይል እንደኾነ ቢሮው ተናግሯል።
(Wazema)

@ethio_mereja_news
የተሽከርካሪ ሰሌዳ እና የአሽከርካሪ መንጃ ፍቃድ ሊቀየር መሆኑ ተሰምቷል።

✔️አዲሱ ታርጋ የክልል ስምና ኮድ አይኖረውም።

✔️በቀለምና በስቲከር ብቻ ይለያል ተብሏል።

✔️መንጃ ፍቃድ ABC በማለት ደረጃ ይኖረዋል።

✔️ የህዝብ፣አውቶ፣ደረቅ የሚሉ የድሮ ደረጃዎች በአዲሱ ይተካሉ ተብሏል።(wasu)

@ethio_mereja_news
TapSwap‼️

ታፕስዋፖች በቅርቡ ትልቅ ዜና ጠብቁ ብለዋል ያም ዜና አዲሱን ሌላኛውን ዋጋ ይፋ የሚያደርጉበት ኤክስቼንጅ መሆኑን ነው የገለፁት ።

አሁን ላይ በቴሌግራም ከተጀመሩ ኤርድሮፖች Hamster ፣ TapSwap ፣ Yes coin እና pixel Verse በቶን ብሎክቼይን ዋጋቸው ይፋ እንደሚደረግ የገለፁ ሲሆን ከቶን ብሎክቼይን ውጪ በሌላ ብሎክቼይን ወይም ኤክስቼንጅ ዋጋቸው ይፋ እንደሚደረግ ግን አንዳቸውም አልገለፁም ነበር

ያልጀመራቹ አሁንም ጊዜ አላቹ ባጭር ጊዜ ውስጥ ከ10 M በላይ መስራት ትችላላቹ።

በዚ ሊንክ ጀምሩ👇👇
https://www.tg-me.com/tapswap_mirror_2_bot?start=r_769729488
https://www.tg-me.com/tapswap_mirror_2_bot?start=r_769729488


ዝርዝር መረጃ ከፈለጋቹ ይህንን ቻናል ተቀላቀሉ👇👇
http://www.tg-me.com/sheger_crypto
http://www.tg-me.com/sheger_crypto
ኢትዮጵያ ስለ አንካራው ውይይት ማብራሪያ ሰጥታለች

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በአንካራው ውይይት ጉዳይ የፕሬስ መግለጫ አውጥቷል።

በመግለጫው በቱርኪዬ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሀካን ፊዳን ጋባዥነት የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ እና የሶማሊያ የውጭ ጉዳይና ዓለምአቀፍ ትብብር ሚኒስትር አህመድ ሞአሊም ፊቂ ትላንት ሰኔ 24 ቀን 2016 ዓ.ም በአንካራ ተገናኝተው መወያየታቸውን አረጋግጧል።

" በቱርኪዬ መንግስት አመቻቺነት የተካሄደው የሁለቱ ሚኒስትሮች ውይይት በሁለቱ አገራት መካከል ላሉ አለመግባባቶች መፍትሄ ሊያመጡ በሚችሉ ጉዳዮች ላይ ግልፅና ወዳጅነት የተሞላበት የሀሳብ ልውውጥ የተደረገበት ነበር " ብሏል።

ሁለቱ ሚኒስትሮች ያሉ አለመግባባቶችን በሰላማዊ መንገድ እልባት ለመስጠት ቁርጠኝነታቸውን መግለጻቸውን አመልክቷል።

የቱርኪዬ መንግስት ውይይቱን ለማመቻቸት ስለተጫወተው ገንቢ ሚናም ምስጋና እንደቀረበ ገልጿል።

ሁለቱ ሚኒስትሮች መልካም ጉርብትናን እና ቀጠናዊ መረጋጋትን ከግምት በማስገባት መፍትሄዎችን ለማመላከት ያለሙ ምክክሮችን ለመቀጠልም እንደተስማሙ አረጋግጧል።

ሁለቱም ሚኒስትሮች የቱርኪዬ ፕሬዚዳንት ሬሲፕ ጣይብ ኤርዶጋን ምከከሩን አገራቸው ለማስተናገድ የወሰዱትን ተነሳሽነት በማድነቅ ሁለተኛ ዙር ውይይታቸውን ነሐሴ 27 ቀን 2016 ዓ.ም በአንካራ ለመቀጠል እንደተስማሙ የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አሳውቋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በድሬዳዋ በአሸዋ የገበያ ማዕከል በተነሳ የእሳት አደጋ ንብረት ወደመ

በድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር አሸዋ ገበያ ሰልባጅ ተራ ሰፈር በተነሳ የእሳት አደጋ ከፍተኛ የሆነ ንብረት ወድሟል።

ከአካባቢው ምንጮች ባገኘነው መረጃ መሰረት የእሳት አደጋው በሰው ሕይወት ላይ ጉዳት አላደረሰም።

ከስፍራው ተቀርጸው በማኅበራዊ ሚዲያ ላይ እየተዘዋወሩ ከሚገኙ ተንቀሳቃሽ ምስሎች እንደተመለከትነው አደጋው በንብረት ላይ ከፍተኛ ውድመት አስከትሏል።

አሁን ላይ አደጋውን ሙሉ ለሙሉ መቆጣጠር ተችሏል።

(ሔለን ታደሰ -አዲስ ዋልታ)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
"የግል ትምህርት ቤት ማን አስተምሩ አላችሁ?"

በግል ትምህርት ቤቶች የሚማሩ የማትሪክ ተፈታኞች በግል ላፕቶፕ ስለምትፈተኑ ላፕቶፕ አዘጋጁ ተብለዋል።

ታድያ ቤተሰቦችን"ላፕቶፕ ቀርቶ ወርሀዊ ክፍያ አቅቶናል" ሲሉ ትምህርት ሚኒስቴር እየሰጣቸው ያለው መልስ "በመንግስት ትምህርት ቤት ለሚማሩት ላፕቶፕ ለማዳረስ እየሰራን ነው፣ የእናንተ ግን አይመለከተንም። የግል ትምህርት ቤት ማን አስተምሩ አላችሁ?" እንደሆነ ከቤተሰቦች በተደጋጋሚ የሚደርሱኝ ጥቆማዎች ያሳያሉ።

በዚህም ምክንያት ላፕቶፕ ለመግዛት ንብረት የሸጠ እንዳለ እንዲሁ ሰምቻለሁ።

ብዙ ኢትዮጵያዊ የግል ትምህርት ቤት ልጆቹን የሚያስተምረው ተርፎት ሳይሆን እሱ ካገኘው የተሻለ ትምህርት ካገኘ በሚል ተቸግሮ ነው።

በዚህ መልኩ የተፈተነ ተቆጥሮ "ይህን ያህል ተማሪ በኦንላይን አስፈተንን" የሚል ሪፖርት ማቅረቡ ፈይዳ ይኖረው ይሆን?
(EliasMeseret)

@sheger_press
ሂውማን ራይትስ ዎች፣ በኤርትራ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ልዩ ራፖርተር ሞሃመድ አብድልሰላም ባቢከር የቆይታ ጊዜ እንዲራዘም ጠይቋል።

የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ምክር ቤቱ በጉዳዩ ላይ ውሳኔ የሚሰጠው በቀጣዩ ሳምንት ነው። ሩሲያ፣ ኢራን እና የተወሰኑ የምክር ቤቱ አባል አገራት የልዩ ራፖርተሩ የቆይታ ጊዜ እንዳይራዘም እንደሚፈልጉ ድርጅቱ ገልጧል።

የልዩ ራፖርተሩ መቀጠል አኹንም እጅግ አስፈላጊ መኾኑን የጠቀሰው ድርጅቱ፣ የምክር ቤቱ አባል አገራት የኤርትራን የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ሲቪል ማኅበረሰቦች ጥሪ እንዲሰሙና ከጎናቸው እንዲቆሙ ጠይቋል።

ልዩ ራፖርተሩ በቅርቡ ለምክር ቤቱ ባቀረቡት ሪፖርት፣ የኤርትራ መንግሥት አስከፊ የሰብዓዊ መብት አያያዙን ለማሻሻል የወሰደው ርምጃ እንደሌለ ገልጠው ነበር።

@sheger_press
@sheger_press
የአማራ ክልል ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባዔ አማረ ሰጤ፣ የፌደሬሽን ምክር ቤት በአማራ እና ትግራይ ክልሎች የይገባኛል ጥያቄ በሚነሳባቸው አካባቢዎች ላለፉት አራት ዓመታት ለምን የፌደራል ድጎማ ሳይመድብላቸው እንደቀረ ማብራሪያ እንዲሰጥ መጠየቃቸውን ሸገር ሬዲዮ ዘግቧል።

የክልሉ ምክትል አፈ ጉባዔ፣ የማንነትና የአስተዳደር ወሰን በሚነሳባቸው የተወሰኑ አካባቢዎች የመብራት፣ የባንክ፣ የሞባይል ኔትዎርክና ሌሎች አገልግሎቶች እንደተቋረጡ መግለጣቸውን ዘገባው አመልክቷል።

የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባዔ አገኘው ተሻገር ለጥያቄው በሰጡት ምላሽ፣ የወልቃይት ጠገዴ እና ሌሎች የማንነት ጥያቄዎች የሚነሳባቸውን አካባቢዎች የበጀት ጥያቄ በፌደራል በጀት ቀመር መኾኑ ቀርቶ ገንዘብ ሚንስቴር በበጀት አስተዳደር እንዲያስተናግደው ምክር ቤቱ ለሚንስቴሩ ደብዳቤ እንደጻፈና ጉዳዩን ተከታትሎ ማስፈጸም የክልል መንግሥት ኃላፊነት እንደኾነ መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

@ethio_mereja_news
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትናንት ከኢምግሬሽን ጋር የተያያዙ ኹለት ረቂቅ አዋጆችን አጽድቋል።

ምክር ቤቱ፣ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎትን እንደገና ለማቋቋም የተዘጋጀውን ረቂቅ አዋጅ በአራት ድምጸ ተዓቅቦ ማጽደቁን ገልጧል።

ረቂቅ አዋጁ የተዘጋጀው፣ ጠንካራ የቅድመ ጉዞ መረጃዎችን በማዘጋጀትና ከአገራት ጋር ውጤታማ የመረጃ ልውውጥ በማድረግ ወንጀለኞችን ለመያዝ የሚያስችል ሥርዓት ለመዘርጋት ነው ተብሏል።

ምክር ቤቱ፣ ኢትዮጵያዊያን ከአገር እንዳይወጡ የማገድ ሥልጣን ለኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የበላይ ኃላፊ የሰጠውን ሌላኛውን ረቂቅ አዋጅም አጽድቆታል።

@ethio_mereja_news
በአማራ ክልል ሥር የተቋቋሙት የጠለምት እና ማይጸብሪ አስተዳደሮች ሙሉ በሙሉ እንደፈረሱና ቢሮዎቻቸው እንደታሸጉ ቢቢሲ አማርኛ የአካባቢውን ምንጮች ጠቅሶ ዘግቧል።

በጦርነቱ ከአካባቢዎቹ የተፈናቀሉ ነዋሪዎች ወደ ቀያቸው በመመለስ ላይ እንደኾኑም ዘገባው ገልጧል።

ሰሞኑን የፈረሱት ጊዜያዊ አስተዳደሮች፣ የምሥራቅ ጠለምት ወረዳ፣ የምዕራብ ጠለምት ወረዳ እንዲኹም የማይጸብሪ ከተማ ተብለው በሰሜን ጎንደር ዞን ሥር የተዋቀሩ አስተዳደሮች ናቸው።

መዋቅሮቹ የፈረሱት፣ ከአማራ ክልል መንግሥትና ከፌደራሉ መንግሥት ተወካዮች ጋር ውይይት ከተደረገ በኋላ መኾኑንና የፖሊስና ሚሊሻ አባላትም ከቅዳሜ ጀምሮ እንዲወጡ እንደተደረገ መስማቱን ዘገባው አመልክቷል።

@ethio_mereja_news
"ጥላቻ፣ ጦርነት፣ ጠብ፣ ክርክር፣ ሞኝ መሆኑን፡ እያወቅን እዚያ ላይ እንንከባለላለን። የሰው ልጅ ህልውናውን ለመጠበቅ ሰላምን መምረጥና መከተል ይኖርበታል። የሰላምን እጦት ያመጣነው ራሳችን ነን። ማንም አምጥቶ አልጫነብንም።ሰላም ከሌለ መንፈሳዊም ሆነ ዓለማዊ ተቋማት ምንም መሰራት እንደማይችሉ አውቀን ለሰላም በአንድነት መቆምና ሰላምን መከተል ይኖርብናል።

ለዚህም ሁላችንም ከቀደመው እየተማርን መጪውን ሰላማዊ ለማድረግ መጣር ይኖርብናል።

የሔድንበት መንገድ ጎድቶናል።ስለሆነም ወደ ሰላም፡ እንመለስ ብለን መወሰን አለብን።ለዚህም ሁላችንም ወደ አእምሮችን ተመልሰን ሰላምን እንከተላት።"

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ
ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ
ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወክጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት

"የሃይማኖት ተቋሞቻችን ለዘላቂ ሰላማችን"በሚል ርእስ በሸራተን አዲስ ዛሬ በተካሔደው መድረክ ላይ ካስተላለፉት መልዕክት የተወሰደ።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሹመት‼️

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ፥ አቶ ካሳሁን ጎፌን የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሚኒስትር አድርገው ሾሙ።

ወ/ሮ ሽዊት ሻንካን ደግሞ የባህልና ስፖርት ሚኒስቴር ሚኒስትር አድርገው ሾመዋቸዋል።

የባህልና ስፖርት ሚኒስትር የነበሩት አቶ ቀጀላ መርዳሳ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የወጣቶች እና ስፖርት አማካሪ ሚኒስትር ሆነው ከዛሬ ሰኔ 26 /2016 ዓ/ም ጀምሮ እንደ ተሾሙ ታውቋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/09/29 11:14:49
Back to Top
HTML Embed Code: