Telegram Web Link
18 ሰዎችን አሳፍሮ ከአዲስአበባ ወደ ፍቼ ሲጓዝ የነበረ ተሽከርካሪ ላይ ባጋጠመ የትራፊክ አደጋ የ 5 ሰዎች ህይወት አለፈ

በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ዉጫሌ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ አምስት ሰዎች ህይወት ወዲያዉኑ ሲያልፍ በርካቶች ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት እንደደረሰባቸው ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል።

18 መንገደኞችን ከአዲስአበባ አሳፍሮ ወደ ፍቼ ሲጓዝ የነበረ ኮድ 3 28787 ኦሮ የሆነ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ እና ከጎጃም ወደ አዲስአበባ ከሰል ጭኖ ሲጓዝ የነበረ ኮድ 3B 33442 የሆነ የጭነት አይሱዙ ተሽከርካሪዎች ተጋጭተዉ ፥ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪዉ 50 ሜትር ጥልቀት ወዳለዉ ገደል ዉስጥ ገብቶ አደጋዉ መድረሱን የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ የትራፊክ ደህንነትና ቁጥጥር ክፍል ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ኩመላ ደንደና ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

ሰኔ 14 ቀን 2016 ዓ.ም የደረሰዉ አደጋዉ ተሽከርካሪዎቹ በሰሜን ሸዋ ዞን ዉጫሌ ወረዳ ቦሶጤ ጃቲ ቀበሌ ዱበር ወንዝ ጋር ሲደርሱ በመጋጨታቸው የተከሰተ መሆኑን ለማወቅ ችለናል። በአደጋዉ ስድስት ሰዎች ላይ ቀላል እንዲሁም ሌሎች ስድስት ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የተባለ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

አደጋ አድርሷል የተባለዉ የአይሱዙ አሽከርካሪ ወዲያዉኑ ከአካባቢው ተሰዉሮ የነበረ ቢሆንም ጫንጮ ከተማ ላይ በቁጥጥር ስር ዉሏል ። የአደጋዉ መንስዔ ፍጥነት መሆኑን የጠቀሱት የትራፊክ ደህንነትና ቁጥጥር ክፍል ሃላፊዉ በንብረት ላይም ከባድ ጉዳት ደርሷል ብለዋል።

በአደጋዉ ሁለት ወንድ እና ሶስት ሴቶች ህይወታቸዉን ያጡ ሲሆን ቀላልና ከባድ የአካል ጉዳት ያጋጠማቸዉ ሰዎች ደግሞ በዉጫሌ እና ፍቼ ሆስፒታሎች ላይ ህክምና እያገኙ ይገኛል ሲሉ በኦሮሚያ ክልል የሰሜን ሸዋ ዞን ፖሊስ የትራፊክ ደህንነትና ቁጥጥር ክፍል ሃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ኩመላ ደንደና ጨምረው ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Hamster‼️

ላስታውሳቹ ሀምስተር ኤርድሮፕ ሊጠናቀቅ ጥቂት ቀናት ነው የቀሩት።

List መሆኑ የተረጋገጠ ትልቅ ፕሮጀክት ነው።

በjuly ወር ይጠናቀቃሉ ተብሎ ከተገመቱት አንዱ ኤርድሮፕ ነው።

ጠንክራቹ ስሩ
perhour ራቹን አሳድጉ ቢያንስ 1M አሳልፉት።

ያልጀመራቹ ካላቹ በዚ ጀምሩ👇👇
https://www.tg-me.com/hamster_Kombat_bot/start?startapp=kentId7308161274
አማኑኤል ተለቋል

ለሁለት ወራት ያኽል በእስር የቆየው አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ ዛሬ ከእስር ተለቆ ወደቤቱ ገብቷል::

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በመላዉ ኢትዮጲያ በቀጣዩ ዓመት 2.5 ሚሊዮን ኮንዶም በነጻ እንደሚከፋፈል ተነገረ

በኢትዮጵያ የኤችአይቪ ታማሚ ከሆኑት መካካል ራሳቸውን የሚያውቁት 84 በመቶ ብቻ እንደሆነ መረጃዎች አመላክተዋል፡፡

ኤኤች ኤፍ ኢትዮጵያ በኤች ኤቪን  በመከላከል ዙሪያ በቅዱስ ጳውሎስ፣ አለርት ጨምሮ በ17 የመንግስት ተቋማትን  እንዲሁም በራሱ ኤ ኤች ኤፍ አዲስ የጤና ተቋም ካሉ  3600 የኤች አይቪ ታማሚዎች  ጨምሮ 60 ሺህ የኤች አይቪ ህሙማን  በማገዝ ላይ እንደሚገኝ  የኤኤችኤፍ ካንትሪ ዳይሬክተር   ዶክተር መንግስቱ  ገ/ሚካኤል በተለይ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡በአሁን ሰዓት የኤች አይ ቪ ቫይረስ በአዲስ መልኩ እተስፋፋ ያለ መሆኑን ጠቅሰው  ወጣቶች በተለየ ትኩረት ሊሰጡት እንደሚገባ አንስተዋል፡፡

ከዚህ ቀደም ይሰሩ የነበሩ  የኤች አይ ቪ   መከላከል ስራዎች  በጣም  እየቀነሱ መሆናቸው እና  ይሰጠው የነበረዉ ትኩረት በመቀነሱ በተለይም እድሜያቸው ከ15 እስከ 35 ዓመት ያሉት ለኤችአይቪ ኤድስ  ይበልጥ ተጋላጭ እየሆኑ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ሰዎች ራሳቸውን ከህክምና  እንዲሁም ከሰው መደበቃቸው እንዲሁም ወደ ጤና ተቋም አለመምጣት ፣  ህክምና ማቋረጥ  እና የኤችአይቪ ህክምና ምርመራ ያደርጉ ሰዎች  በስፋት ባለመኖራቸው በትክክል ያለው  የታማሚ ቁጥር ማወቅ እንዳልተቻለ  እና ይህም  ለስራው ትልቅ ተግዳሮት መሆኑን አንተዋል ፡፡ በመሆኑም ባለፈው ዓመት ብቻ በተደረገ ጥናት የኤች አይ ቪ ታማሚ ከሆኑት ውስጥ  84 በመቶ ብቻ የሚሆኑት  ራሳቸውን ያወቁ መሆናቸውን ጠቅሰዋል፡፡

Dagu
@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
YesCoin‼️

100% የተረጋገጠ ነው

ኋላ እንዳይቆጫቹ አሁንኑ ጀምሩት።

List መሆኑ የተረጋገጠ ኤርድሮፕ ነው።

በዚ Link ጀምሩት👇👇

https://www.tg-me.com/theYescoin_bot/Yescoin?startapp=D7siYr

ስለ አሰራሩ ይህንን
ቻናል ይቀላቀሉ👇👇
http://www.tg-me.com/sheger_crypto
http://www.tg-me.com/sheger_crypto
መንግሥት ያቋቋመው ብሄራዊ ኮሚቴ ትናንት በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ኹኔታ ውስጥ የነበሩ 1 ሺህ 175 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን መመለሱን የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል።

ከተመላሾቹ መካከል፣ እድሜያቸው ከ18 ዓመት በታች የኾኑ 20 ታዳጊዎች እንደሚገኙበት ሚንስቴሩ ገልጧል።

ከሚያዚያ 4 ጀምሮ እስከ ትናንት ከ49 ሺህ 500 በላይ ኢትዮጵያዊያን ተመልሰዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ በሚያደርገው ስብሰባ፣ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል የመሬት ይዞታ የሚለቀቅበት፣ ካሳ የሚከፈልበትና ተነሺዎች መልሰው የሚቋቋሙበትን ኹሁኔታ ለመወሰን በተዘጋጀው ረቂቅ አዋጅ ዙሪያ ጉዳዩ የሚመለከታቸው ቋሚ ኮሚቴዎች በሚያቀርቡለት የውሳኔ ሃሳብ ላይ ይወያያል።

ምክር ቤቱ፣ የቋሚ ኮሚቴዎቹን ሪፖርት መርምሮ ድምጽ እንደሚሰጥ አስታውቋል።

ምክር ቤቱ ሚንስትሮች ምክር ቤት ባቀረበለት የውጭ ባንኮች በአገሪቱ እንዲሠማሩ በሚፈቅደው የባንክ ሥስራ ረቂቅ አዋጅ ላይ ጭምር ተወያይቶ ለዝርዝሩ እይታ ለቋሚ ኮሚቴ እንደሚመራ ገልጧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አሜሪካ፣ በኢትዮጵያና ሱማሊያ መካከል በባሕር በር ዙሪያ የተፈጠረው "ፖለቲካዊ ውጥረት" እና "ውጥረቱ በጋራ የጸጥታ ጥቅሞች" ላይ የሚኖረው ተጽዕኖ "በእጅጉ እንዳሳሰባት" አስታውቃለች።

ትናንት በሱማሊያ ወቅታዊ ኹኔታ ዙሪያ በመከረው የተመድ ጸጥታው ምክር ቤት ላይ ንግግር ያደረጉት የአሜሪካ ልዑክ አምባሳደር ሮበርት ውድ፣ አሜሪካ የሱማሊያ ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት እንዲከበር አፍሪካ ኅብረትና ሌሎች አጋሮች የያዙትን አቋም ትደግፋለች ብለዋል።

አምባሳደሩ፣ በኹለቱ አገሮች መካከል የተፈጠረውን ውጥረት ማርገቢያው መንገድ ንግግር እንደኾነም አውስተዋል። ቀጠናዊ ውጥረቶች፣ ከአልሸባብን ጋር በሚደረገው ውጊያ፣ ከአፍሪካ ኅብረት ተልዕኮ መውጣት በኋላ ተተኪ ተልዕኮ በማሠማራቱ ሂደትና በአገር ግንባታ ጥረቶች ላይ እንቅፋት መኾን እንደሌለባቸውም አምባሳደሩ አውስተዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
#ኢህአፓ መሪና ሌሎች በሚገኙበት መዝገብ የተከሰሱ ፖለቲከኞች እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት ወሰ

የፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት፣ የኢሕአፓ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራ እና በሌሎች ዘጠኝ ሰዎች ላይ ፖሊስ የጠየቀውን ይግባኝ ውድቅ አድርጎ የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ግለሰቦቹ ከእሥር እንዲለቀቁ የሰጠውን ብይን አጸና።

የኢሕአፓ ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ዝናቡ አበራን ጨምሮ በአዋሽ አርባ ታሥረው ከነበሩ 17 ሰዎች መካከል፣ ግንቦት 30 ቀን 2016 ዓ. ም ወደ አዲስ አበባ የተዛወሩት ዘጠኝ ግለሰቦች የፌዴራል የመጀመርያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ባለፈው ሰኞ በገንዘብ ዋስትና እንዲወጡ ወስኖላቸው ነበር። በዚሁ መሠረትም፤ ለአምስቱ ተጠርጣሪዎች ሰላሳ ሺህ ብር፣ ለአራቱ ደግሞ የሃያ ሺህ ብር ዋስትና ቢከፈልም በእሥር ቆይተዋል። በተመሳሳይ ዜና "እብደት በሕብረት" የተባለው የመድረክ ተውኔት ተዋናይ አመኑኤል ሀብታሙ፣ አዘጋጁ ዳግማዊ ፈይሳ እና ሌሎችም ተጠርጣሪ የኪነጥበብ ባለሞያዎች ባለፈው ሐሙስ የዋስትና መብታቸው ቢከበርም ከቀናት ቆይታ በኋላ ትላንት መለቀቃቸውን ዶቼቬለ ዘግቧል::

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ተሽከርካሪ ሰርቃ የተሰወረችው ግለሰብ በሰዓታት ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋለች
***
ተጠርጣሪዋ የስርቆት ወንጀሉን የፈፀመችው ሰኔ 17 ቀን 2016 ዓ.ም በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 7 ልዩ ቦታው ቢጫ ፎቅ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

በክፍለ ከተማው ፖሊስ መምሪያ ከቤተል አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው በወቅቱ በግምት ከጠዋቱ 12:30 ሰዓት ገደማ የግል ተበዳይ በስፍራው የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 3-B32912 አ.አ የሆነ ተሽከርካሪያቸውን መኖሪያ ቤታቸው በር ላይ ሞተር አስነስተው እያሞቁ የነበሩ ሲሆን ወደ ስራ ለመሄድ ጃኬት ሊደርቡ ወደ ቤት በገቡበት ቅስፈት ተሽከርካሪያቸውን ከቆመበት ቦታ እንደሌለ አረጋግጠው ለፖሊስ ሪፖርት ያደርጋሉ።
የኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከተማ ፖሊስ መምሪያ አቤቱታው ከደረሰው ሰዓት ጀምሮ ተሰውሮ የነበረውን ተሽከርካሪ ለማግኘት ግማሽ ቀን በፈጀ ጠንካራ ክትትልና መረጃ የማሰባሰብ ሥራ ተጠርጣሪዋን ከነተሽከርካሪው በቁጥጥር ስር አውሏታል።

ግለሰቧ የግል ተበዳይ ወደቤት በገቡበት ቅስፈት ተሽከርካሪውን አስነስታ ብትሰወርም በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ ዘጠኝ ልዩ ቦታው ሰሚት ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በግምት ከቀኑ 9 ሰዓት ገደማ ከነተሽከርካሪው በቁጥጥር ስር ውላለች ። የተለያዩ ዘዴዎችንን በመጠቀም የሚፈፀሙ ወንጀሎችን ለመከላከል ተገቢውን ጥንቃቄ ማድረግ የሁሉም ስው ኃላፊነት መሆኑን ያሳሰበው ፖሊስ የተሽከርካሪ ባለንብረቶች ጥንቃቄ በጎደለው ሁኔታ መኪናቸውን አቁመውና የተሽከርካሪውን ቁልፍ በውስጡ ትተው በሚሄዱበት አጋጣሚ ለተመሳሳይ የስርቆት ወንጀል ሊዳረጉ ስለሚችሉ ተገቢውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ የአዲስ አበባ ፖሊስ መልዕክቱን አስተላልፏል

(ዘገባ ፦ ዋና ሳጅን ዘላለም አበበ -አ/አ ፖሊስ)

@sheger_press
በቃሊቲ ማረሚያ ቤት በሚገኙ እስረኞች መካከል ተነሳ በተባለ ግጭት ታራሚዎች መጎዳታቸው ተነገረ

በአዲስ አበባ ከተማ በሚገኘው ቃሊቲ ማረሚያ ቤት ባለፈው ቅዳሜ በእስረኞች መካከል ተነሳ በተባለ ግጭት ሳቢያ፤ ቢያንስ አምስት ታራሚዎች መጎዳታቸውን የእስረኛ ቤተሰቦች እና የአካባቢው ነዋሪዎች ነግረዉኛል ሲል ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል። የፌደራል ማረሚያ ቤት ኮሚሽን በዕለቱ ግጭት እንደነበር ቢያረጋግጥም፤ በክስተቱ “ቀላል ጉዳት የደረሰበት አንድ ታራሚ ብቻ ነው” ሲል አስተባብሏል።

ግጭቱን ተከትሎ በማረሚያ ቤቱ ሆነው የፍርድ ቤት ጉዳያቸውን ሲከታተሉ የነበሩ ጋዜጠኞች እና ሌሎች  እስረኞች ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እንዲዘዋወሩ መደረጉን የእስረኞቹ ቤተሰቦች መናገራቸውን ዘገባው አመልክቷል። በቃሊቲ ማረሚያ ቤቱ ግጭት ተቅስቅሶ የነበረው፤ ከሁለት ቀን በፊት ጠዋት ሶስት ሰዓት ገደማ እንደነበር የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

ልጃቸው በቃሊቲ ማረሚያ ቤት እንደታሰረ የጠቀሱ አንድ የአካባቢው ነዋሪ፤ ቅዳሜ ጠዋት በቤት ውስጥ እንዳሉ “የመሳሪያ ተኩስ ድምጽ” መስማታቸውን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግረዋል። በድንጋጤ ውስጥ ሆነው ሁኔታውን ለማጣራት ወደ ማረሚያ ቤት አቅጣጫ ሲሄዱ፤ በአቅራቢያው ባሉ መንገዶች “በፓትሮል የመጡ” በርካታ የፌደራል ፖሊሶች መመልከታቸውን አስረድተዋል።

በማረሚያ ቤት የታሰረ የቤተሰብ አባላቸውን ለመጠየቅ በዕለቱ በስፍራው ተገኝተው የነበሩ የዓይን እማኝም ይህንኑ አረጋግጠዋል። “የታጠቁ የፌደራል ፖሊስ አባላት  ማረሚያ ቤቱን ዙሪያውን ከበውት ነበር” የሚሉት እኚሁ የዓይን እማኝ፤  “ጋሻ ነገር የያዙ፣ ሄልሜት ያደረጉ፣ የታጠቁ፣ ዱላ የሚመስል ነገር የያዙ የአድማ በታኝ ፖሊሶች” በማረሚያ ቤቱ መግቢያ አካባቢ መመልከታቸውን ጠቁመዋል።
(Ethiopian insider)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በኢትዮጵያ የውስጥ ኦዲት ከሚሰሩ የመንግስት ተቋማት መካከል በአግባቡ ስራቸውን የሚከውኑት ጥቂቶቹ ብቻ ናቸው ተባለ፡፡

ከመንግስት ተቋማት ይልቅ የግል ድርጅቶች ለሰራተኞቻቸው የሚከፍሉት ክፍያ ከፍ ማለቱ ደግሞ ባለሞያዎች ወደ ግል ድርጅቶቹ ማዘንበል ሌላኛው የውስጥ ኦዲት በሚፈለገው ልክ ውጤታማ ስራ እንዳይከወን ምክንያት ከሆኑት መካከል አንዱ ነው ተብሏል፡፡

በዚህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ብሄራዊ ባንክ በውስጥ ኦዲት ሙያ ከበረቱት ተቋማት መካከል መሆናቸውን ሰምተናል፡፡

በኢትዮጵያ የውስጥ ኦዲት ዘርፍ ላይ ብዙ መስራት ይጠበቃል የተባለ ሲሆን ጥቂት ከሚባሉ ተቋማት ውጭ የውስጥ ኦዲት እንደሀገር እየተሰራበት አይደለም ተብሏል፡፡

በተለያየ ጊዜ ተቋማቱ ላይ የሚመጣ ትችት፣ የመልካም አስተዳደር እክል እና ሌሎችም በድርጅቱ ላይ የሚደርሱ ችግሮች በውስጥ ኦዲት ሙያ ላይ ያለቸው አስተዋፆ አናሳ በመሆኑ ነው መባሉን ሰምተናል፡፡

የውስጥ ኦዲት በአግባቡ እንዲሰራ ተቋማት የሚያግዘው የኢትዮጵያ የውስጥ ኦዲት ኢንስቲቲዩት ከአለም አቀፉ የውስጥ ኦዲተሮች ማህበር ጋር በጋራ በመሆን ስራዎችን እንደሚከውን ይናግራል፡፡

ይሄው ኢንስቲቲዩት ተቋማቱ ለሰሩት የውስጥ ኦዲት ማረጋጫ ይሰጣል የተባለ ሲሆን በሚከውነው ስራም ችግሮች እንደሚያጋጥሙት የኢንስቲቲዩቱ ፕሬዚደንት ገነት ሐጎስ ተናግረዋል፡፡

(ሸገር ኤፍ ኤም)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በአማራ ክልል በኮሌራ ወረርሽኝ የአምስት ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን፣ ከ500 በላይ ሰዎች መያዛቸውን ተቋሙ አስታወቀ!

በአማራ ክልል ከመጋቢት 27 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በተከሰተው ሁለተኛ ዙር ኮሌራ ወረርሽኝ ከ500 በላይ ሰዎች መያዛቸውን ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

በዚህም ወረርሽኙ ከተከሰተበት ከመጋቢት 27 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 13 2016 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ከ530 በላይ ሰዎች በኮሌራ መያዛቸው እና አምስት ሰዎች በበሽታው ሕይወታቸውን ማጣታቸውን የተቋሙ ባለሙያ ሲስተር ሰፊ ደርብ እንደገለጹለት ኢፕድ ዘግቧል።

በወረርሽኙ ከተጠቁ ሰዎች መካከል ከ11 በላይ የሚሆኑት በሕክምና ላይ እንደሚገኙ የጠቆመው ዘገባው ቀሪዎቹ በተሰጣቸው የሕክምና አገልግሎት ታክመው መዳናቸውን አመላክቷል።

ወረርሽኙ በደቡብ ወሎ 2 ወረዳዎች፣ በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን 3 ወረዳዎች፣ በሰሜን ጎጃም 2 ወረዳዎች፣ በደሴ ከተማ፣ በኮምቦልቻ ከተማና በባህር ዳር ከተማ እንዲሁም በቅርቡ ጎንደር ከተማ ላይ የተከሰተ መሆኑንም ተገልጿል፡፡

በክልሉ በአጠቃላይ በሽታው በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚገኙ በስድስት የሕክምና ማእከላት ሕክምናው እየተሰጠ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በክልሉ ከሐምሌ 8/2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 7/2016 ዓ.ም ተከስቶ በነበረው የመጀመሪያ ዙር ወረርሽኝ ከ4980 በላይ ሰዎች ተይዘው እንደነበር ያወሳው ዘገባው ይህም ለሁለተኛ ዙር የሚያስፈልጉ የኮሌራ ኪትና ሌሎች ግብአቶችን በቀላሉ ለማግኘት እንዳስቻለ ባለሞያዋ ሲስተር ሰፊ መግለጻቸውን አስታውቋል።

በተጨማሪም የሚያስፈልጉ የሕክምና እና ምርመራ ግብአቶችን ከኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ ከጤና ቢሮና አጋር ድርጅቶች ጋር በጋራ እየቀረበ ነው ሲሉ መናገራቸውንም አካቷል።

@sheger_press
@sheger_press
ፖለቲከኛው ጃዋር መሃመድ የመከላከያ ጄነራሎች ለድርድር ለመቀመጥ ለፋኖ ያደረጉትን ጥሪ፣ የፋኖ አመራርና የአማራ አክቲቪስቶች እንደበጎ እርምጃ እንዲመለከቱትና ለጥሪው ምላሽ ቢሰጡ ለሰላም አማራጭ ይሆናል ሲል በግል የማህበራዊ ሚዲያ የፌስቡክ ገፁ አስፍሯል።

መከላከያ ሰራዊት በሀገሪቱ የተፈጠሩ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በርካታ ጥረቶችን እያደረገ ያለ አንዱ የመንግሥት ተቋም ነው ብሏል።

መከላከያው እየተፈጠረ ያለውን ችግር በቅርበት የሚያውቅ በመሆኑ፣ ከፖለቲከኞች ቀድሞ ጥሪ ማቅረቡ መበረታታት አለበት ብሏል። ከኦነግ ሸኔ ጋርም ሰላም ለመፍጠር ለሁለት ጊዜ የተደራደረው መከላከያው ነው ብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አስጨናቂው የክረምት ወቅት መጥቷል ‼️

ፖስቱ ቫይራል መሆኑ ለእናቶች ይጠቅማቸዋል። ላይክ አርግ። ኮፒ አርጋችሁም በየፔጃችሁ ፖስቱት 🙏

ክረምቱ በዝናብ ታጅቦ መጥቷል ይህም ደግሞ ያለ መከለያ ጎዳና ላይ ጉሊት ለሚሸጡ እናቶች መከራ ሆኗል። የሚሸጧቸውን አትክልትና ፍራፍሬ ከማከፋፈያ ቦታ ከማምጣት ጀምሮ ቸርችሮ እስከመሸጥ ድረስ ያለውን ሂደት ክረምቱ ይበጠብጠዋል። አብዛኞቹ እናቶች በጋ ላይ ያገኙት የነበረውን ገቢ ግማሹንም አሁን ላይ አያገኙትም።

በእንቅርት ላይ ... እንዲሉ ገቢያቸው ሲቀንስ ወጪያቸውን ደግሞ ክረምቱ ያንረዋል። አብዛኞቹ እናቶች ልጆቻቸውን መንግስት ትምህርት ቤት ያስተምራሉ። በጋውን ልጆቻቸውን መንግስት በትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም ይመግብላቸው ነበረ። ክረምቱ ግን የልጆቻቸውን ፊት ከባዶ ሌማታቸው ጋር ያፋጥጠዋል።

አስቤዛ ስትገዙ እስቲ ጉሊት ግዙ። ዋጋ አትከራከሩ ። ቲፕም ስጡ 🙏

አቅሙ ያላችሁ ሰዎች ደግሞ ጉሊት ጋ መኪና አቁሙና አንዱን መደብ በሺዎች ግዙ። አስደስቷቸው። ተመረቁ🙏

#ጉሊት #ጉሊት_challenge

Tesfa Neda

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለተማሪ ቀለብ የሚያዝላቸው በጀት ካለው የምግብ ዋጋ ጋር የሚጣጣም ባለመሆኑ ተጨማሪ በጀት እንዲጠይቁ የሚፈቅድ አሰራር እንዲዘረጋ ተጠየቀ፡፡

ይህ ካልሆነ በመጭው የት/ት ዘመን ተማሪ ተቀብለው ለማስተናገድ እንደሚቸገሩ ሰምተናል፡፡

ለ2017 በተያዘው ረቂቅ በጀት ላይ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባላት ውይይት አድርገውበታል፡፡

ሸገር ኤፍ ኤም

@sheger_press
@sheger_press
ጥቆማ‼️

እንዳያመልጣቹ ስልካቹን ብቻ በመጠቀም ምንም ገንዘብ ማውጣት ሳይጠበቅባቹ ::

እንዴት ገንዘብ መስራት እንደምትችሉና ስለ ክሪፕቶ ስለ ኤርድሮፕና ታፕ ታፕ በማረግ ብቻ እንዴት ገንዘብ ማግኘት እንደምትችሉ።

ሁሉንም የONLINE ስራዎች በዝርዝር በዚ ቻናል ያገኛሉ።

በርግጠኝነት ትወዱታላቹ በዚ LINK አሁንኑ ተቀላቀሉ👇👇
http://www.tg-me.com/sheger_crypto
http://www.tg-me.com/sheger_crypto
በአዲስ አበባ የሚስተዋለው የነዳጅ እጥረት በቀናት ውስጥ ይፈታል ተባለ

ካለፉት ሳምንታት ጀምሮ በመዲናዋ ነዳጅ ለመቅዳት የሚጠብቁ ረጃጅም የተሽከርካሪ ሠልፎች መታየታቸውን አሁንም ቀጥለዋል።

የኢትዮጵያ የነዳጅ አቅራቢዎች ድርጅት እጥረት ማጋጠሙን ጠቅሶ፥ በበዓል ምክንያት ለሁለት ቀናት ከጂቡቲ ነዳጅ ባለመጫኑ ምክንያት ችግሩ እንደተፈጠረ መግለጹን ኢቢሲ ዘግቧል።

በዒድ አል አድሃ አረፋ በዓል ምክንያት እሑድ ሰኔ 9 እና በማግሥቱ ሰኔ 10 ቀን 2016 ዓ.ም. ነዳጅ ከጂቡቲ ሳይጫን መቅረቱን ጠቅሷል።

የነዳጅ ማጓጓዝ ሒደቱ አምሥትና ሥድስት ቀናት የሚወስድ መሆኑንና አሁን የሚስተዋለው እጥረት በመጪዎቹ ቀናት እንደሚፈታም ነው የገለጸው። (EBC)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ በዛሬ 37ኛ መደበኛ ስብሰባው ውሳኔዎችን አሳልፏል።ከውሳኔዎቹ መካከል በኢትዮጵያና በኩዌት መካከል በስራ ስምሪት ዘርፍ የተፈረመውን ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ አዋጅ አንዱ ነው፡፡

ስምምነቱ በኩዌት በቤት ሰራተኝነት ተሰማርተው የሚገኙ እና በቀጣይም ከአሰሪዎች ጋር የሥራ ውል ውስጥየሚገቡ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች መብታቸውን ለማስጠበቅ የሚያስችል ሕጋዊ ማዕቀፍ እንዲኖር፣ በአገሪቱ የሚገኙ ዜጎቻችን ክብር፣ መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ ትልቅ ጠቀሜታ ያለው እንዲሁም በሁለቱ መንግስታት መካከል የሁለትዮሽ ግንኙነትን ይበልጥ እንዲጠናከር የሚያግዝ ነው፡፡ ምክር ቤቱ በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትእንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

@ethio_mereja_news
2024/09/30 19:30:44
Back to Top
HTML Embed Code: