Telegram Web Link
እነ አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ በ50 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ፍርድ ቤት ፈቀደ                                            

ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓትን በትጥቅ ትግል ለመቀየር” በመንቀሳቀስ የተጠረጠሩት አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ፣ የቴአትር አዘጋጅ ዳግማዊ ፈይሳ እና ፍላጎት አብርሃምን ጨምሮ 17 ግለሰቦች እያንዳንዳቸው በ50 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት ፈቀደ።

በዚሁ መዝገብ ተጠርጥረው የቀረቡት ሌሎች ሶስት ግለሰቦች በአንጻሩ 11 ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ተፈቅዶባቸዋል።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ይህንን ብያኔ ያስተላለፈው ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 13/2016 ዓ.ም. ረፋድ ላይ በነበረው የችሎት ውሎ ነው።

ችሎቱ ዛሬ የተሰየመው ከትናንት በስቲያ ማክሰኞ ዕለት በነበረው የፍርድ ቤት ውሎ ግራ ቀኙ ያቀረቧቸው ጥያቄዎችን መርምሮ ብይን ለመስጠት ነበር።

በማክሰኞ ዕለቱ የችሎት ውሎ መርማሪ ፖሊስ ሀያዎቹ ተጠርጣሪዎች ላይ ተጨማሪ የምርመራ ቀናት እንዲፈቀድለት ሲጠይቅ ጠበቆች በአንጻሩ የዋስትና መብት እንዲከበር ጠይቀው እንደነበር ጠበቃ አያሌው ቢታኔ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ከተቀመጠው አሰራር ውጪ የመኖሪያ ቤት ዋጋ ጭማሪ ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ።

የአከራይ ተከራይ አዋጅ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በህግ ከተቀመጠው አሰራር ውጪ የመኖሪያ ቤት ዋጋ ጭማሪ ማድረግና የነበረውን የኪራይ ውል ማቋረጥ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል፡፡

በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ፍትሃዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በማህበረሰቡ ላይ የሚፈጥረው ጫና ከግምት ውስጥ በማስገባት የቤት ኪራይ ስርአቱ በህግ የሚመራ እና ተገቢውን ቁጥጥር በማድረግ ለችግሩ አፋጣኝ ምላሽ መስጠት ተገቢ ሆኖ ሰለታመነበት የመኖሪያ ቤት ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 መጋቢት 24/2016 መውጣቱ ይታወቃል።

የከተማ አስተዳደሩም የአዋጁን ማስፈፀሚያ መመሪያ ቁጥር 7/2016 በማውጣት ተግባራዊ አድርጓል።

በመሆኑም አዋጁ ወጥቶ ተግባራዊ ከሆነበት ቀን ማለትም ከመጋቢት 24/2016 ጀምሮ መንግስት ከሚያስቀምጠው የኪራይ ውሳኔ ውጪ በአከራዮች የሚደረግ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ ፈፅሞ የተከለከለ በመሆኑ አዋጁ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከህግ ከተቀመጠው አሰራር ውጪ የመኖሪያ ቤት ዋጋ ጭማሪ ማድረግና የነበረውን የኪራይ ውል ማቋረጥ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ቢሮው ገልጿል።

ይህ እንዲፈፀምም ቢሮው ተገቢውን ቁጥጥር እና ክትትል እንደሚያደርግም ማስታወቁን ከአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የህግ ክልከላውን ተላልፈው የተገኙ አከራዮች ላይ በመመሪያ ቁጥር 7/2016 አንቀፅ 22 መሰረት አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድም ቢሮው አሳስቧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አንድ ቤት ለገዛ አንድ ቤት በነፃ

‼️ከ 300ሺ ብር ጀምሮ

📞0961478081

📍አድራሻ - በደማቋ ለቡ ማብራት-ሀይል

⚡️ሊኖሩበት ቢፈልጉ ሰላሚዊ መንደር፣ ሊያከራዩት ቢያስቡ በጥሩ ዋጋ እና መልሰው እንኳን ቢሸጡት በደንብ የሚያተርፉበት!

💸5% ቅድመ ክፍያ ብቻ
💸 50% የባንክ ብድር አገልግሎት



👉 እንደ ፍላጎቶ ሙሉ በሙሉ ያለቁ(fully-finished) ወይም እርሶ በሚፈልጉት መልኩ የሚጨርሱትን(semi-finished) ሆኖ መረከብ ይችላሉ።

🛌እስቱድዮ - 56 - 58 ካሬ
   ባለ 1 መኝታ - 77.7 - 98 ካሬ
   ባለ 2 መኝታ - 123 - 134 ካሬ
   ባለ 3 መኝታ - 146 -157 ካሬ
   ባለ 4 መኝታ - 177 - 186 ካሬ
የንግድ ሱቆች - 20- 900 ካሬ

👉ለ 50 ቤቶች ብቻ የወጣ ከ 8% - 25%  ቅናሽ አድርገናል

📞0961478081
ስምንት ህጻናትን በህገወጥ መንገድ ከሀገር ሊያስወጡ የነበሩ ሁለት ህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች በእስራት ተቀጡ

በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ስምንት ህጻናትን በህገወጥ መንገድ ከሀገር ሊያስወጡ የነበሩ ሁለት ህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች በድምሩ በ 30 አመት እስራት እንደተቀጡ ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል።

በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ደደር ወረዳ ተከሳሽ መሀመድ አህመድ የተሰኘዉ ግለሰብ ሃምሌ 14 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት አካባቢ በደደር ከተማ 08 ቀበሌ ከሚጠራዉ አካባቢ እድሜያቸዉ 15 ዓመት የሆኑ ሶስት ህጻናትን ወደ ሳዑዲ አረቢያ በመሄድ በከፍተኛ ገንዘብ ተቀጥራችሁ ቤተሰቦቻችሁን ትደግፋላችሁ በማለት ቤተሰቦቻቸውን ካሳመነ በኋላ ወደ ሀረር ከተማ ወስዷቸዋል ሲሉ የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ክፍል ሃላፊ አቶ ሱሌማን ቱጁሃን ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

በሀረር ከተማ አንድ ቀን ካሳደራቸዉ በኋላም ወደ ጅግጅጋ ከተማ ታዳጊዎቹን በመዉሰድ የኢትዮ-ሶማሊያ ድንበርን በመጠቀም አደዉ ከተማን ላይ ለሌላ ደላላ አሳልፎ እንደሰጣቸዉ በምርመራ ተረጋግጧል። ህጻናቱን የተረከበዉ ሌላኛዉ ደላላም ወደ ሶማሊላንድ ላሶኖ አሻግሯቸዋል ሲሉ ገልጸዋል።

በሶማሊላንድም ከእያንዳንዳቸው ህጻናት ቤተሰቦች 27 ሺህ ብር እንዲልኩ አስገድዷል ብለዋል። በዚህ መካከል አንደኛዉ ህጻን ከደላሎች እጅ አምልጧል። ፖሊስ ከደላሎች እጅ በወጣዉ ታዳጊ መረጃ መሰረት አደረኩት ባለዉ ክትትል ዋነኛ የወንጀሉ ጠንሳሽ የሆነዉን መሀመድ አህመድን በቁጥጥር ስር አዉሎታል።

ግለሰቡ የቀረበበትን ክስ ሊከላከል ባለመቻሉ የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሰኔ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ባዋለዉ ችሎት በግለሰቡ ላይ የ 15 አመታት እስራት ቅጣት መወሰኑን ተናግረዋል።በተመሳሳይ በዞኑ ጎሮ ጉቱ ወረዳም በህገወጥ የሰዎች ዝዉዉር የተከሰሰዉ ግለሰብ በ 15 አመት እስራት መቀጣቱ ተነግሯል።

ተከሳሽ መገርሳ አብደላ የተባለዉ ግለሰብ ታህሳስ 12 ቀን 2016 ዓ.ም በወረዳዉ ካራ ሚሌ ከተማ እድሜያቸዉ 15 አመት የሆኑ አምስት ህጻናትን በማታለል ወደ ሳዑዲ አረቢያ እልካቸዋል በሚል አታሏቸዋል ተብሏል። ግለሰቡ በተመሳሳይ ህጻናቱን ወደ ሶማሊላንድ ካሻገረ በኋላ ገንዘብ ቤተሰቦቻቸውን ጠይቋል።

ከእያንዳንዳቸው ቤተሰቦችም 1 ሺህ 200 ብር ለመቀበል ሲያስገድድ ነበር ብለዋል። ፖሊስ ግለሰቡን በቁጥጥር ስር አዉሎ በዚህ ግለሰብ ላይም ክስ መስርቶበታል።በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሰኔ 7 ቀን 2016 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት ተከሳሽ መገርሳ አብደላን ጥፋተኛ ሲል በ 15 አመታት እስራት እንዲቀጣ ወስኗል ሲሉ የከፍተኛ ፍ/ቤት ቤቱ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ክፍል ሃላፊ አቶ ሱሌማን ቱጁሃን ጨምረዉ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚንስትሮች ምክር ባቀረበለት የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅ ላይ ትላንት ተወያይቶ ለፕላን፣ ፋይናንስና በጀት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል።

ምክር ቤቱ ረቂቅ አዋጁን ለቋሚ ኮሚቴው ለመምራት በሰጠው ድምጽ፣ ሦስት የተቃውሞ ድምጾች ተመዝግበዋል። ረቂቅ አዋጁን የተቃወሙ ኢዜማን እና የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄን የወከሉ የምክር ቤቱ አባላት፣ መንግሥት የሚጥላቸው ተደራራቢ ታክሶች ድሃውን የኅብረተሰብ ክፍል የሚጎዱ እንደኾኑ ተናግረዋል። የአብን ተወካይ ደሳለኝ ጫኔ፣ ሕዝቡ የንብረት ታክስን ሊቋቋም የሚችልበት አቅም እንደሌለው ገልጠው ምክር ቤቱ ረቂቅ አዋጁን ውድቅ እንዲያደርገው ጠይቀዋል። ረቂቅ አዋጁ፣ በከተሞች በግለሰቦች መሬት፣ በመሬት ላይ በሚደረጉ ማሻሻያዎች እና ሕንጻዎች ላይ መንግሥት ታክስ እንዲሰበስብ የሚፈቅድ ነው። የንብረት ታክስን የመሰብሰብ አዋጅ ለክልሎች እንዲኾን ቀደም ሲል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ፌደሬሽን ምክር ቤት በጋራ መወሰናቸው ይታወሳል።
ከእንግዲህ መንግስት እንፈለገ ገንዘብ አይወስድም‼️

ብሄራዊ ባንክ ለመንግስት ቀጥታ ብድር እንዳይሰጥ የሚከለክል ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ

ባለፉት ዓመታት በመቶ ቢሊየን የሚቆጠር ገንዘብ ከብሄራዊ ባንክ የወሰደው መንግስት ከዚህ በኋላ እንደፈለገ የሚበደርበትን አሰራር የሚከለክል አዲስ ረቂቅ አዋጅ ለተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ።

ረቂቅ አዋጁ እንዳሰፈረው መንግስት የከፋ ችግር ካልገጠመው በቀር ከብሄራዊ ባንክ ያለገደብ የሚበደርበት አሰራር ከዚህ በኋላ በህግ የተከለከለ ይሆናል።

ይህ ድንጋጌ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተካቶ የቀረበ ሲሆን በረቂቅ አዋጁ ክፍል አምስት በብሔራዊ ባንክ እና በመንግስት መካከል የሚኖረውን ግንኙነት ባተተበት ምእራፍ ውስጥ ተካቷል።
“በአዋጁ በግልጽ ካልተፈቀደ በስተቀር ብሔራዊ ባንክ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለፌዴራል ; ለክልል ; ለማንኛውም የታችኛው የመንግስት የአስተዳደር እርከን ፣ የከተማ አስተዳደር ወይም የመንግስት ተቋም ብድር መስጠት አይችልም ” ይላል።

(ዋዜማ)
@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
YesCoin‼️

እንደሚታወቀው ይህ ኤርድሮፕ List መሆኑ የተረጋገጠና በTon Blockchain List የሚደረግ ነው።

አሪፍ Task ስላሉት ሰብስቡ ።

የጀመራቹ በርትታቹ ስሩ

ያልጀመራቹ ጊዜው ሳይረፈድ ቶሎ ጀምሩ

በዚ Link👇👇
https://www.tg-me.com/theYescoin_bot/Yescoin?startapp=PP9BDi
https://www.tg-me.com/theYescoin_bot/Yescoin?startapp=PP9BDi

ለዝርዝር መረጃው
ይሄን ቻናል ይቀላቀሉ👇👇
http://www.tg-me.com/sheger_crypto
http://www.tg-me.com/sheger_crypto
ሰኔ 16 ስራ ዝግ ይሆናል።የት?👇

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 16 ቀን 2016 ዓ.ም. በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በአፋር፣ በሶማሌ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች የሚያስፈጽመውን የ6ኛው ዙር ቀሪና እና የድጋሚ ምርጫን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በመግለጫውም ዜጎች ዕለቱን ለድምፅ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ የምርጫ አካባቢዎች የሚገኙ የፌዴራልና የክልል መንግሥታዊ ተቋማት ሰኔ 16 ቀን 2016 ዓ. ም. ሥራ ዝግ እንዲያደርጉ ቦርዱ አስታውቋል፡፡

የትራንስፓርት አገልግሎት በተለመደው መንገድ የሚቀጥል ቢሆንም፤ የምርጫ አካባቢዎች ዜጎች ድምፅ ከመስጠት ውጪ ከፍተኛ እንቅስቃሴን የሚፈልጉ ሁነቶችንና ዕቅዶችን እንዳይዙ፤ እንዲሁም እንቅስቃሴያቸውን ድምፅ ለመስጠት ብቻ እንዲያደርጉ ቦርዱ አስታውቋል።(wasu)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ተፈቅዷል‼️

የመንግሥት ሰራተኞች የደረጃ እድገት እና የእርከን ጭማሪ በአዲሱ ረቂቅ አዋጅ ተፈቅዷል፦ የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን

አዲሱ የፌዴራል መንግስት ረቂቅ የሰራተኞች አዋጅ ሰራተኞች ተመዝነው በአፈጻጸማቸው የሚለዩበት እንደሆነ የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) ገለጹ።   

አዋጁን በተዛባ መንገድ መረዳት አይገባም ያሉት ኮሚሽነሩ፤ አንድ ሰራተኛ ሁለት ጊዜ ተመዝኖ ውጤቱ ከመካከለኛ በታች ከሆነ ከስራው እንደሚሰናበትም ጠቁመዋል።
በዚህ ምዘና በቂ ውጤት ያመጡ ሰራተኞች ደግሞ የደረጃ እድገት እንዲሁም በየሁለት ዓመቱ የሚኖር የእርከን ጭማሪ እንዲያገኙ በአዋጁ ተደንግጓል ብለዋል።

የአዋጁ  ዋና ዓላማ ሰራተኛን መቀነስ ሳይሆን ማብቃት ነው ያሉት መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር)፤ በምዘናው  ደረጃ አሟልተው ብቁ የሆኑ፣ የተወሰነ ክፍተት ያለባቸው እና ሰፋ ያለ ክፍተት የታየባቸው ተለይተው ክፍተቶቹ በስልጠና እየተሟሉ ሶስቱም በመንግሥት መዋቅር ውስጥ የሚቀጥሉ ናቸው ብለዋል።

የመንግሥት ሰራተኛው በስራው ተመጣጣኝ ገቢ አለማግኘቱ በኑሮው ላይ ጫና ፈጥሮበታል፤ አዋጁ ይህን ችግር ለመፍታት የሚያስችል ነው ወይ ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ፥ አዋጁ የብቃት ምዘናውን ያለፉና መስፈርቱን የሚያሟሉ ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪ በእርከንና በደረጃ ዕድገት እያገኙ የሚሄዱበትን አስገዳጅ አሰራር መደንገጉን ተናግረዋል።

አዋጁ የፐብሊክ ሰርቪስ አገልግሎትን ለማሻሻልና ዲጅታል ሲቪል  ሰርቪስን ለመፍጠር ዓላማ ያደረገ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ፤ ሁሉም ብሄረሰብ የተማረ የሰው ኃይል አለው ተብሎ ስለሚታሰብ ብዝሃነትን መሰረት ያደረገ ፕብሊክ ሰርቪስ ለመገንባት መታሰቡን ተናግረዋል።

ሥራ ላይ ያለው የፌዴራል መንግሥት የሰራተኞች አዋጅ ፖሊሲን መሰረት አድርጎ የተቀረጸ አይደለም ያሉት ኮሚሽነሩ፤ የመንግሥት አገልግሎትን መሰረታዊ በሆነ መልኩ ለመቀየር የሚያስችልም አልነበረም ብለዋል።

አሁን የተዘጋጀው አዋጅ ነጻና ገለልተኛ ሲቪል  ሰርቪስ ለመገንባት፣ የሰራተኛውን ብቃት ለማረጋገጥ፣ ብዘሃነትና አካታችነትን በተገቢው መንገድ ለመምራት እንደሚረዳ መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

Via EBC

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት፣ ለኃይማኖታዊ ጉዞ ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ የተጓዙ አምስት ኢትዮጵያዊያን በደረሰባቸው የመኪና አደጋ እና በሕመም ሕይወታቸው ማለፉን እንደተናገረ ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።

አራቱ ኢትዮጵያዊያን የሞቱት፣ በሕመምና በጉዞ መጨናነቅ ሳቢያ እንደኾነ ምክር ቤቱ መግለጡን ዘገባው አመልክቷል።

ባኹኑ ወቅት ሳዑዲ ዓረቢያ ውስጥ በተከሰተው ሙቀት ሳቢያ፣ በትንሹ ከ1 ሺህ በላይ ሰዎች ሕይወታቸውን እንዳጡ ተዘግቧል።

ኾኖም ከኢትዮጵያዊያን ሐጃጆች በሙቀት ምክንያት የሞተ ሰው እንደሌለ ምክር ቤቱ ገልጧል ተብሏል።

@sheger_press
@sheger_press
ከግብር ነፃ የሆኑ የቅጥር ክፍያዎች‼️

የሚከተሉት ከመቀጠር የሚገኙ ገቢዎች ከግብር ነፃ ይሆናሉ


— ሠራተኛው ሲታመም አሠሪው ለሠራተኛው ህክምና አገልግሎት የከፈለለት ገንዘብ፤
— በሥራ ውል መሠረት ለሠራተኛው የሚከፈል የትራንስፖርት አበል፤
— በሥራ ቦታው ወይም በሥራ ሁኔታው አስቸጋሪነት ምክንያት ለሠራተኛው የሚከፈል አበል፤
— ሠራተኛው ከመደበኛ ሥራው ውጪ ሥራውን ለማከናወን ሲንቀሳቀስ የሚከፈለው የመጓጓዣ ወጪ እና የውሎ አበል፤
— የመጓጓዣ ወጪው በቅጥር ውሉ መሠረት የተከፈለ ከሆነ ከሥራ ቦታው ውጪ ተመልምሎ ለተቀጠረ ሠራተኛ ወደ ሥራው ሲመጣ ወይም ሥራውን አጠናቆ ሲመለስ የሚከፈለው የመጓጓዣ ወጪ፣ እንዲሁም የውጭ ሀገር ሠራተኞች ከሀገራቸው ሲመጡና ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ የሚከፈል የመጓጓዣ ወጪ፤
— የማዕድን ማውጣት፣ የማኑፋክቸሪንግ እና የግብርና የንግድ ሥራ የሚሠራ ቀጣሪ ለተቀጣሪው በነፃ የሚያቀርበው ምግብና መጠጥ፤
— የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት በውጭ አገር ለሚመድባቸው ሠራተኞች የሚከፈል አበል፤
— የመንግሥት የልማት ድርጅቶች ወይም የመንግሥት መስሪያ ቤቶች የቦርድ አባል ወይም ፀሐፊ እንዲሁም የፌደራልና የክልል መንግሥታት ወይም የከተማ አስተዳደሮች በሚያቋቁሟቸው የጥናት ቡድኖች አባል ወይም ፀሐፊ በመሆን የሚከፈል አበል፤
— ለሠራተኛው ጥቅም ተብሎ ከተቀጣሪው የወር ደመወዝ 15 % (አሥራ አምስት በመቶ) ባልበለጠ መጠን በየወሩ በቀጣሪው የሚዋጣ የጡረታ መዋጮ ወይም የፕሮቪደንት ፈንድ፤
— በመንግሥት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ  እና በግል ድርጅት ሠራተኞች የጡረታ አዋጅ ከግብር ነፃ የተደረገ የጡረታ ገቢ፤
— የኢትዮጵያ የፌደራል፣ የክልል ወይም የአካባቢ መንግሥታት ወይም የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከመደበኛ ሥራዎቻቸው ጋር በተያያዘ የሚያገኙት ገቢ፤
— በዓለም አቀፍ ስምምነት መሠረት ከግብር ነፃ የሆነ የገቢ መጠን ሲሆኑ ቀሪዎቹ በቀጣይ ይቀርባሉ።
#ገቢዎች

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በቤት ኪራይ ውድነት የተቸገሩ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ መምህራን፤ በተማሪዎች ዶርም “በጊዜያዊነት” እየኖሩ ነው ተባለ‼️

ትግራይ ክልል በሚገኘው መቐለ ዩኒቨርሲቲ የሚያስተምሩ የተወሰኑ መምህራን “ቤት ተከራይቶ መኖር እንደከበዳቸው” ለተቋሙ ማመልከታቸውን ተከትሎ፤ በተማሪዎች ማደሪያ ዶርም “በጊዜያዊነት” እንዲቆዩ ተፈቅዶላቸው እየኖሩ መሆኑን ገለጹ። የዩኒቨርስቲው መምህራን በክልሉ በነበረው ጦርነት ሳቢያ የ17 ወር ደመወዝ ያልተከፈላቸው መሆኑ፤ በአስር ሺህዎች የሚቆጠር ውዝፍ የቤት ኪራይ እንዲከማችባችው አድርጓል። 

የዩኒቨርሲቲው መምህራን “የቤት ኪራይ መክፈል አቅቶናል” የሚሉ ማመልከቻዎችን ለተቋሙ ማስገባት የጀመሩት ከ2014 ዓ.ም. ጀምሮ ቢሆንም፤ ካለፈው ሶስት ወር ወዲህ ግን በርካታ መምህራን ተመሳሳይ ጥያቄዎች ለተቋሙ ፕሬዝዳንት እና ምክትል ፕሬዝዳንት ቢሮ ማቅረባቸው ተነግሯል።

መምህራኑ ለዩኒቨርሲቲው ጥያቄ እንዲያቀርቡ የተገደዱት፤ በጦርነት ወቅት ሳይከፍሉ የቀሩትን “ውዝፍ የቤት ኪራይ” አሁን እንዲያመጡ እየተጠየቁ በመሆኑ እና በክልሉ ባለው የኑሮ ውድነት ምክንያት ነው ብለዋል።(#ኢትዮጵያኢንሳይደር)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
YesCoin‼️

ሇላ እንዳይቆጫቹ አሁንኑ ጀምሩት።

List መሆኑ የተረጋገጠ ኤርድሮፕ ነው።

በዚ Link ጀምሩት👇👇
https://www.tg-me.com/theYescoin_bot/Yescoin?startapp=PP9BDi

ለበለጠ መረጃ ይህን ቻናል
ይቀላቀሉ👇👇
http://www.tg-me.com/sheger_crypto
http://www.tg-me.com/sheger_crypto
የጨረቃ ቤቶች በአዲሱ የአከራይ ተከራይ አዋጅ የምዝገባ  ስርአት ውስጥ እንደማይካተቱ የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ እወቁልኝ ብሏል።(wasu)

@sheger_press
@sheger_press
በጎንደር ከተማ ከ12 ሰዓት በኋላ ባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ ማሽከርከር ተከለከለ

በጎንደር ከተማ የሰው እገታ ወንጀል እየተባበሰ በመምጣቱ ምክንያት ከዛሬ ሰኔ 15 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ የባለ ሶስት እግር ተሽከርካሪ (ባጃጅ) ከ12 ሰዓት በኋላ ላልተወሰነ ጊዜ መንቀሳቀስ እንደማይችል የከተማ አስተዳደሩ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል፡፡

የመምሪያው ኃላፊ ረዳት ኮሚሽነር አየልኝ ታክሎ በሰጡት መግለጫ እንዳሉት፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በከተማዋ በቡድን በሚንቀሳቀሱ ሀይሎች የሰው እገታ ወንጀል እየጨመረ መጥቷል፡፡

ይህን የማህበረሰቡ ከፍተኛ የደህንነት ስጋት ለመቀነስ መንግስት የተለያዩ እርምጃዎችን እየወሰደ መሆኑን ገልጸዋል፡፡

የተለያዩ ወንጀሎች በከተማዋ ሲፈጸሙ ተባባሪ ናቸው ተብለው የተጠረጠሩ 27 ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ያነሱት ረዳት ኮሚሽነሩ ተሽከርካሪዎቹ ታርጋ የሌላቸው መኾኑንም ጠቁመዋል።

በቁጥጥር ስር ከዋሉት ባለ ሦስት እግር ተሽከርካሪዎች መካከል አራቱ በእገታ ወንጀል ተሰማርተዋል ተብለው የተጠረጠሩ ተሽከርካሪዎች መኾናቸውን አስታውቀዋል።

በእገታ ወንጀል የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በህግ ተጠያቂ ለማድረግ በሚደረገው ጥረት የከተማው ማህበረሰብ ቀና ትብብር እንዲያደርግ ተጠይቋል።

የብሎክ አደረጃጀትን በማጠናከር ቤት ለቤት የሚፈፀመውን የስርቆት ወንጀል ለመቀነስ የተቀናጀ ጥረት ማድረግ ይገባልም መባሉን ከፋና ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@sheger_press
@sheger_press
#Tigray

" ከዚህ (ከሰላማዊ) ውጭ  ያለው መንገድ አዋጭ አይደለም " - አቶ ጌታቸው ረዳ

36ኛው ዓመት " የትግራይ የሰማእታት ቀን " ዛሬ ሰነ 15 ቀን 2016 ዓ/ም በመቐለ የሰማእታት ሀውልት ተከብሯል።

በስነ-ስርዓቱ ላይ የክልሉ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ንግግር አድርገው ነበር።

አቶ ጌታቸው ረዳ ፤ " ልጆቻችን በአጋቾች ለሞት እየተጋለጡ ፣ ተፈናቃዮች በመቆያ መጠለያዎች በፀሀይና በብርድ እየተሰቃዩ ባሉበት ወቅት የሰማእታት ቃልና አደራ በተሟላ መልኩ እያከበርን ነው በማለት ማምለጥ አይቻለንም " ሲሉ ተደምጠዋል።

" የሰማእታት ቃል አክበረናል የምንለው በንግግር ሳይሆን በተግባር መሆን ይገባዋል " ብለዋል።

" የሰማእታት ቃል ማክበር ማለት በትግራይ የሃሳብ ብዙህነት እንዲከበር መስራት  ለስልጣን ሳይሆን ለህዝብ ጥቅም መዋደቅ ነው " ያሉት አቶ ጌታቸው " አንዳንዶቻችን ይህንን በመዘንጋት ለስልጣንና ለሃብት ስንባላ መታየት አሳፋሪ ነውና ከዚሁ መውጣት ይህንን መቀየር አለብን " ሲሉ ተናግረዋል።

አቶ ጌታቸው " ተፈናቃዮችን በጀመርነው ሰላማዊ መንገድ ወደ ቄያቸው እንዲመለሱ በአንድነት መንፈስ የፕሪቶሪያ ውል በተሟላ መልኩ ተፈፃሚ እንዲሆን መስራት አለብን " ያሉ ሲሆን " ከዚህ ውጭ ያለው መንገድ አዋጭ አይደለም " ሲሉ አስረድተዋል።
በርካታ የኢትዮጵያ ወታደሮች ከባድ የጦር መሳሪያዎችንና ታንኮችን በመያዝ ከትናንት በስተያ ወደ ሱማሊያ ግዛት ዘልቀው እንደገቡ የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

ከኢትዮጵያ የተነሱት ወታደሮች ያቀኑት፣ ሒራን ወደሚባለው የሱማሊያ ግዛት እንደኾነ ዘገባዎቹ አመልክተዋል። የኢትዮጵያዊያኑ ወታደሮች ተልዕኮ ምን እንደኾነ ለጊዜው ግልጽ እንዳልኾነም የዜና ምንጮቹ ጠቅሰዋል።

የሱማሊያ ጦር ሠራዊት ባለፉት ኹለት ዓመታት ያገኛቸውን ወታደራዊ ድሎች፣ አልሸባብ ባለፉት ጥቂት ወራት ሙሉ በሙሉ እንደቀለበሳቸው የአሜሪካ ባለሥልጣናት መናገራቸውን የአሜሪካ ዜና ምንጮች ሰሞኑን ዘግበው ነበር። የሱማሊያ ባለሥልጣናት ግን፣ የአሜሪካ ባለሥልጣናትን ግምገማ የተሳሳተ በማለት እያጣጣሉት ይገኛሉ።
#ዋዜማ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የአባታቸውን መኪና ጥሩምባ ለናፈቁ ልጆች የእድር ጥሩምባ ማሰማት ትልቅ በደል ነው!

በአማራ ክልል በስሜን ጎንደር ከማክሰኝት እንፍራዝ ባለው መንገድ በተከታታይ 2ቀናት 2 ሾፌሮች በዘራፊዎች ተገለዋል አንድ ሾፌር በጥይት ቆስሎ ህክምና ላይ ይገኛል 2 አሽከርካሪዎች ታፍነው ተወስደዋል በዚሁ እለት ጠዋት የህዝብ ተሽከርካሪ ተሳፋሪዎችም ተዘርፈዋል ::
ጎንደር ከተማ ብልኮ ላይ የተወለደው የነዳጂ ቦቴ ሾፌር የሆነው ከጂቡቲ ነዳጂ ጭኖ ወደ ትውልድ ከተማ ለመድረስ ሲገሰግስ ከትውልድ ቀየው መዳረሻ ላይ በ 15/10/2016 በጥይት ህይወቱን ሊያጣ ችሏል ::

ይህ ወንድማችን ናፍቆቱን ቤተሰቡ ጋር ለመወጣት በዙር የደረሰውን ወደ ትውልድ ቀየው ጭኖ የመምጣት ልጆቹን በአካል የማግኘት ዕድሉን እያመሰገነ ለቤተሰቡ ግብአቱን ለጎረቤቱ ከሰሉን ለአብራኩ ክፋዮች ብስኩቱን ይዞ በሚጓዝበት ከጂቡቲ ጎንደር 1000 ኪሎ ሜትሩን ለመጨረስ 970 ውን ተጉዞ ከቤቱ ለመድረስ 30 ኪሎ ሜትር ሲቀረው በጥይት ህልሙ በአጭሩ አስቀርቶታል ሲል የሾፌሮች አንደበት ዘግበዋል።

ይህ የ2 ልጆች አባት የሆነው ከጂቡቲ ነዳጂ ጭኖ በመምጣት ከልጆቹ ጋር ለመገናኘት የጓጓው ልጆቹን እየደወለ እዚህ ደርሻለሁ ጎንደር ቀርቢያለው በማለት በስስት በብዙ ዝግጅት ለሚጠብቁት ልጆቹ እየተናገረ ባለበት ሂደት በጥይት ነፍሱን ነጥቆ አባታቸውን ለማቀፍ ለጓጉ በጉጉት ለሚጠብቁ ልጆች ሬሳ ማስታቀፍ የግፎች ሁሉ ግፍ ነው ሲል የሾፌሮች አንደበት ገፅ ዘገባ ተመልክተናል።
አንድ ቤት ለገዛ አንድ ቤት በነፃ

‼️ከ 300ሺ ብር ጀምሮ

📞0961478081

📍አድራሻ - በደማቋ ለቡ ማብራት-ሀይል

⚡️ሊኖሩበት ቢፈልጉ ሰላሚዊ መንደር፣ ሊያከራዩት ቢያስቡ በጥሩ ዋጋ እና መልሰው እንኳን ቢሸጡት በደንብ የሚያተርፉበት!

💸5% ቅድመ ክፍያ ብቻ
💸 50% የባንክ ብድር አገልግሎት



👉 እንደ ፍላጎቶ ሙሉ በሙሉ ያለቁ(fully-finished) ወይም እርሶ በሚፈልጉት መልኩ የሚጨርሱትን(semi-finished) ሆኖ መረከብ ይችላሉ።

🛌እስቱድዮ - 56 - 58 ካሬ
   ባለ 1 መኝታ - 77.7 - 98 ካሬ
   ባለ 2 መኝታ - 123 - 134 ካሬ
   ባለ 3 መኝታ - 146 -157 ካሬ
   ባለ 4 መኝታ - 177 - 186 ካሬ
የንግድ ሱቆች - 20- 900 ካሬ

👉ለ 50 ቤቶች ብቻ የወጣ ከ 8% - 25%  ቅናሽ አድርገናል

📞0961478081
እስራኤል በ24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ ከ100 በላይ ፍሊስጤማውያንን መግደሏ ተነገረ!!

የእስራኤል ጦር በ24 ሰዓታት ውስጥ በጋዛ ሰርጥ በተፈጸማቸው ጥቃቶች ከ100 በላይ ፍሊስጤማውያን መገደላቸውን በሃማስ የሚመራው መንግስት ባለስልጣናት አስታወቀዋል።

የእስራኤል ጦር አዳሩን በጋዛ ሰርጥ በፈጸመው ጥቃት ቢያንስ 42 ፍሊስጤማውያን መሞታቸውንም ነው በሃማስ የሚመራው መንግስት መገናኛ ብዙሃን የዘገቡት። የእስራኤል ጦር የአየር ድብደባ ከፈጸመባቸው ቦታዎች መካከል በጋዛ ሰርጥ ውስጥ ከሚገኙ ታሪካዊ የስደተኞች መጠለያ መካከል አል አሻ የሚገኙ ቤቶች ሲሆኑ፤ በዚህ ስፍራ 24 ሰዎች መሞታቸው ተነግሯል።

ሌላኛው የእስራኤል ጦር ኢላማ የነበረው በአል ቱፋህ የሚገኘው መኖሪያ ቤቶች አካባቢ ላይ ሲሆን፤ በዚህ ስፍራም 18 ሰዎች መሞታቸው ነው የተገለጸው። የእስራኤል ጦር ጥቃቱን ተከትሎ ባወጣው መግለጫው፤ የእስራኤል መከላከያ ኃይሎች በሁለት የሃማስ ኢላማዎች ላይ ጥቃት መሰንዘሩን እና በዚህም የሃማስ ወታደራዊ ኢላማዎችን ማውደሙን አስታውቋል። በሃማስ ወታደራዊ መሰረተ ልማቶችን ላይ በተፈጸመው የአየር ድብደባ ዙሪያ ዝርዝር መረጃ በቅርቡ እለቃለሁም ብሏል የእስራኤል ጦር በመግለጫው። ሃማስ በበኩሉ ባወጣው መግለጫ የእስራኤል ጦር መታደራዊ መሰረት ልማቶቹን ስለ መምታቱ ያለው ነገር የለም።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/09/30 17:32:42
Back to Top
HTML Embed Code: