Telegram Web Link
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዛሬ የመኖሪያ ቤት የአከራይና ተከራይ የውል ስምምነት ምዝገባ ማካሄድ ጀምሯል።

የከተማዋ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አከራዮችንና ተከራዮችን የውል ምዝገባ በኹሉም ክፍለ ከተሞች የጀመረው፣ የከተማዋ አስተዳደር ያወጣውን የመኖሪያ ቤቶች ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ ተግባራዊ ለማድረግ ነው።

አዋጁ፣ የመኖሪያ ቤት አከራዮች አስተዳደሩ በዓመት አንድ ጊዜ ከሚወስነው የኪራይ ጣሪያ በላይ ኪራይ ከመጨመርና ተከራዮችን በግዳጅ ከማስወጣት የሚከለክል ነው።

አስተዳደሩ አዋጁን ያወጣው፣ ተከራዮች በአገሪቱ የተከሰተውን የኑሮ ውድነት መቋቋም እንዲችሉ አስተዋጽኦ ያደርጋል በሚል እምነት እንደኾነ መግለጡ ይታወሳል።

@ethio_mereja_news
ባለፈው ረቡዕ ታጣቂዎች በኦሮሚያው ሆሮ ጉደሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ በፈጸሙት ጥቃት ሦስት ሰዎች እንደተገደሉ ዴይቸቨለ ዘግቧል።

በሞተር ሳይክል በመጓዝ ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ በተፈጸመው ጥቃት ከተገደሉት ሰዎች መካከል፣ አንድ መምህር እንደሚገኝበት ዘገባው አመልክቷል።

ጥቃቱን ያደረሱት፣ በዞኑ ኡሙሩ ወረዳ እና በአጎራባቹ የምሥራቅ ወለጋ ዞኑ ኪረሙ ወረዳ አዋሳኝ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች እንደኾኑ የወረዳው አስተዳደር ሃላፊዎች መናገራቸውን ዜና ምንጩ ጠቅሷል።

በኡሙሩ ወረዳ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በተለይ ባለፉት ሦስት ዓመታት በፈጽሟቸው ማንነትን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች ሳቢያ ከ40 ሺህ በላይ ሰላማዊ ሰዎች ተፈናቅለውበት የነበረ አካባቢ ነው።

@ethio_mereja_news
ከሃምሳ አመታት ጥረት በኋላ የወንዶች እርግዝና መከላከያ መድሃኒት በቅርቡ መመረት ይጀምራል ተባለ፡፡

የወንዶች እርግዝና መከላከያ መድሃኒትን ለማምረት ላለፉት 50 ዓመታ የተለያዩ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡

ይሁንና እስካሁን ድረስ አንድም የወንዶች እርግዝና መድሃኒት ማምረት ያልተቻለ ሲሆን የተደረጉ ጥረቶች አሁን ላይ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ መድረሳቸው ተገልጿል፡፡

እንደ ሲቢኤስ ዘገባ ከሆነ የወንዶች እርግዝና መከላከያ መድሃኒትን ለማምረት የተለያዩ ኩባንያዎች በሙከራ ለይ ሲሆኑ በክትባት መልኩ እና በሌሎች መልኩ የሚሰጡ መድሃኒቶችን ለማምረት ሙከራዎች እየተካሄዱ ናቸው፡፡

እየተደረጉ ካሉ የወንዶች እርግዝና መከላከያ መድሃኒቶች መካከል በጄል መልክ ክንድ ላይ የሚቀባው መድሃኒት አንዱ ነው፡፡
በአሜሪካ ብሔራዊ የወሊድ መከላከያ ኢንስቲትዩት በኩል እየተደረገ ያለው ይህ ጄል መሳይ የወንዶች እርግዝና መከላከያ መድሃኒት የመጀመሪያውን እና ሁለተኛውን ደረጃ ሙከራ ማጠናቀቁ ተገልጿል፡፡

የወንዶች የወሊድ መከላከያ እንክብል 99 በመቶ ውጤታማ ሆኗል ተብሏል።

ይህ ጄል የወንዶችን የዘር ፈሳሽ መጠን በመቀነስ እርግዝና እንዳይፈጠር የሚያደርግ ነው የተባለ ሲሆን በ222 በጎ ፈቃደኛ ወንዶች ላይ ተሞክሮ እስካሁን ውጤታማ ሆኗል ተብሏል፡፡

ሌሎች ተቋማትም የወንዶች እርግዝና መከላከያ መድሃኒቶችን ለማምረት ጥረቶች ላይ ናቸው የተባለ ሲሆን ከሆርሞን ጋር የማይገናኙ የህክምና ቁሳቁሶችን ለማምረትም ተመሳሳይ ተቋማት የመጨረሻ ደረጃዎች ላይ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

እስካሁን በዓለማችን የወንዶች እርግዝና መከላከያ መድሃኒት ለማምረት የተመዘገበ ህጋዊ ተቋም የሌለ ሲሆን በሙከራ ለይ ያሉ ተቋማት ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ መድሃኒቶችን ለማምረት ፈቃድ ለማግኘት እንደሚያመለክቱ አስታውቀዋል፡፡
Via Al ain

@ethio_mereja_news
#ኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአራት አመታት በኋላ ወደ አክሱም ከተማ ዳግም በረራ ጀምሯል። 

#ትግራይ ጦርነት ጉዳት የደረሰበት አጼ ዮሐንስ 4ኛ አውሮፕላን ማረፊያ የተደረገለት ጥገና ተጠናቆ ዛሬ ሰኔ 2 ቀን 2016 መደበኛ ስራ ጀምራል።

ዛሬ በተደረገ የመጀመሪያ በረራም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑትን አቶ መስፍን ጣሰውን፣ የፌደራል እና የክልል የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ 140 ተጓዦች የያዘው  አውሮፕላን አክሱም ሃፀይ ዮሐንስ አራተኛ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ አቀባበል ተደርጓል።

በአቀባበል ስነ ስርዓቱ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ባለስልጣናት ተገኝተዋል።

በረራውም በየቀኑ 1 ጊዜ የሚደረግ ሲሆን በቀጣይ የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት በማድረግ በቀን ወደ 3 ጊዜ ለማሳደግ እንደሚሰራም ተጠቁሟል፡፡

@ethio_mereja_news
የበርካታዎችን ሕይወት በቀጠፈው የሰሜኑ ጦርነት ወቅት በየቦታው የተቀበሩ እና የተጣሉ ተተኳሾች ፣ ፈንጂዎች አሁንም በሰው ህይወት ላይ አደጋ ማድረሳቸው ቀጥሏል።

በአፋር፣ በትግራይ እና በአማራ ክልሎች የተቀበሩ ፈንጂዎች ለሰው ህይወት መጥፋትና ለአካል መጉደል ምክንያት እንደሆኑ በተደጋጋሚ ሲገለጽ ነበር።

በትግራይ ክልል በምሰራቃዊ ዞን ሐውዜን ወረዳ ማይጎቦ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ትናንት ሰኔ 1 2016 በፈነዳ ተተኳሽ አራት ሰዎች ሕይወት መቀጠፉ ተሰምቷል።

@sheger_press
በራያ አላማጣ ከተማ ዛሬ ለሊቱን በርካታ የህወሓት ታጣቂዎች ወደ ከተማዋ መግባታቸውን የአይን እማኞች ገልፀውልኛል።

በከተማ በሚገኙ ምስራቅ ፀሀይ፣ታዳጊዋና ሹሜ በርሄ ትምህርት ቤት ከሰፈረው ታጣቂ በተጨማሪ ምድረገነት ትምህርት ቤት ዛሬ ለሊቱን በርካታ ታጣቂዎች ገብተው ሰፍረዋል ብለዋል።

ትናንት የራያ ህዝብ በከተማዋ የሚገኙ የህወሓት ታጣቂዎች ከቀናት በፊት አንድ የመብራት ሀይል ሰራተኛ የነበረ ወጣትን በመግደላቸው ምክንያት ትናንት ህዝቡ በአደባባይ ወጥቶ ቅሬታውን ማሰማቱ አይዘነጋም። ዛሬ ለሊቱን ታጣቂዎች በተኮሱት ተኩስ አራት ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል ጉዳት አድርሰዋል ብለዋል።

በከተማዋ የሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ታጣቂዎቹ ስለሰፈሩባቸው ትምህርት ከተዘጋ ወራቶች ሊቆጠሩ ነው ብለዋል(አዩዘሀበሻ)።
#ጋምቤላ‼️

በጋምቤላ ከተማ የታጣቂዎች ጥቃት ዘጠኝ ሰዎች መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ!!

በጋምቤላ ከተማ፣ ባለፈው ሳምንት ዐርብ፣ ታጣቂዎች በአንድ የመዝናኛ ክበብ ውስጥ በከፈቱት ተኩስ፣ ዘጠኝ ሰዎች መቁሰላቸውን፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

የጋምቤላ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልም፣ የጥቃቱ ሰለባ የኾኑ ሰዎችን ተቀብሎ እያከመ መኾኑንና፣ ከመካከላቸው ከባድ ጉዳት የደረሰበት አንድ ሰው፣ ለተሻለ ሕክምና ወደ አዲስ አበባ ተልኳል፡፡

የክልላዊ መንግሥቱ፣ የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ደግሞ፣ በጥቃቱ ዘጠኝ ሰዎች መቁሰላቸውን አረጋግጦ፣ ጥቃት ፈጻሚዎቹ ግን “እስከ አሁን አልተያዙም፤” ብሏል፡፡

@ethio_mereja_news
ኤርትራ በሌሊት ብቻ የሚሰራ የኢንተርኔት አገልግሎት መስጠት መጀመሯ ተሰማ

👉🏼 የሙሉ ሌሊት ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች እስከ 105 ዶላር ድረስ መክፈል ይጠበቅባቸዋል ተብሏል


ኤርትረ በትናንትናው እለት የሌሊት ኢንተርኔት አገልግሎት መስጠት መጀመሯን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል።

ኤርትራ በሌሊት ብቻ ይሰጣል ባለችዉ የኢንተርኔት አገልግሎት እጅግ ዉድ ሊሰኝ እንደሚችል የኢንተርኔት እና የኮምፒውተር ባለሙያ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። በሰከንድ 512 ኪሎ ባይት ድረስ አገልግሎት ይሰጣል የተባለዉ ኢንተርኔት በቤት ስልክ መስመር የሚመጣ ሲሆን ተጠቃሚዎች ወደ ሞባይል እና ኮምፒውተሮቻቸዉ ማገናኘት እና መጠቀም ይችላሉ ተብሏል።

ኤርትራ በትናንትናው እለት ሌሊቱን ያስጀመረችዉ የኢንተርኔት አገልግሎት ባለሙያዎች ገለጻ ዘንድ ቀርፋፋ ነዉ የተሰኘዉን ነዉ።

ሁለት አይነት የኢንተርኔት ማስተላለፊያ መስመሮች ያሉ ሲሆን ኤዲኤስኤል (ADSL) በሲርናል ኢንተርኔት የሚደርስበት ሲሆን ቀርፋፋ የኢንተርኔት አገልግሎት የሚሰጥበትም ነዉ። በአንጻሩ በፋይበር የሚተላለፈዉ ኢንተርኔት በብርሃን አጋዥነት አገልግሎት የሚሰጥበት ሲሆን እጅግ ፈጣኑም እንደሆነ ባለሙያዉ ገልጸዋል።

ታድያ ኤርትራ አስጀመረችዉ የተባለዉ የኢንተርኔት አገልግሎት ኤዲኤስኤል (ADSL) የተሰኘዉን ነዉ። ይህ አሁንም በኢትዮጵያ አገልግሎት እየሰጠ ቢሆንም ቀርፋፋዉ አገልግሎት መሆኑን ባለሙያዉ ገልጸዋል።

ከሌሊቱ 4 ሰዓት እስከ ንጋት 12 ሰዓት ድረስ ከ 512 እስከ 1 ሜጋባይት ድረስ በሰከንድ ኢንተርኔት የሚያስጠቅነዉን አገልግሎት ለማግኘት ኤርትራውያን 1575 ናቅፋህ ወይንም 105 የአሜሪካ ዶላር መክፈል አለባቸው ተብሏል።

የተለያዩ አገልግሎቶች ይሰጣሉ የተባለ ሲሆን ተጠቃሚዎች እስከ 10 ጊጋ ባይት ድረስ የሆነና ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎትን ማግኘት ካሻቸዉ ደግሞ 4200 ናቅፋህ ወይንም 280 የአሜሪካ ዶላር ከፍያ መፈጸም እንዳለባቸው ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ከተሰራጨው ማስታወቂያ ላይ መታዘብ ችሏል።

@ethio_mereja_news
መንግሥት በመጭው 2017 በጀት ዓመት 971 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር አጠቃላይ በጀት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አቅርቧል።

የቀጣዩ ዓመት በጀት ከዘንድሮው በጀት ጋር ሲነጳጸር የ21 ነጥብ 1 በመቶ ጭማሪ እንዳለው ገንዘብ ሚንስትር አሕመድ ሺዴ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተናግረዋል።

451 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር የሚኾነው በጀት ለመደበኛ በጀት 283 ነጥብ 2 ቢሊየን ለካፒታል እንዲኹም 236 ነጥብ 7 ቢሊየኑ ለክልሎች የበጀት ድጎማ እንደተያዘ ተገልጧል።

ለመደበኛ ወጪ ከተያዘው በጀት ውስጥ፣ 128 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ለመደወዝ፣ ለአበል እና
ለልዩ ልዩ ክፍያዎች እንደተመደበም አሕመድ አብራርተዋል።

@ethio_mereja_news
መንግሥት በቀጣዩ በጀት ዓመት ለአዲሶቹ ደቡብ ኢትዮጵያ፣ ማዕከላዊ ኢትዮጵያ፣ ለደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ እና ለሲዳማ ክልሎች የሚመደብላቸው የፌደራል በጀት ድጎማ በቀድሞው የደቡብ ብሄር፣ ብሄረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የፌደራል በጀት ድጎማ ቀመር መሠረት እንደሚቀጥል አስታውቋል።

የገንዘብ ሚንስትር አሕመድ ሽዴ፣ አገሪቱ አዲስ የሕዝብ ቆጠራ እስክታካሂድ ድረስ የፌደራል በጀት ድጎማ ቀመሩ በነበረበት እንደሚቀጥል የቀጣዩን ዓመት በጀት አስመልክተው ዛሬ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በሰጡት ማብራሪያ ተናግረዋል።

በተለይ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኙ በርካታ ዞኖች ዘንድሮ ገጥሞናል ባሉት የበጀት እጥረት ሳቢያ፣ ለመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ ለመክፈል ተቸግረው እንደከረሙ ሲገልጡ ነበር።

@ethio_mereja_news
የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በመጪው ሐምሌ ወር መጀመሪያ ይሰጣል

የዘንድሮ የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በመጪው ሐምሌ ወር መጀመሪያ እንደሚሰጥ ተገለጸ።

የትምህርት ሚኒስቴርና የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ፈተናውን አስመልክቶ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ምክትል ዳይሬክተር ተፈራ ፈይሳ በዚሁ ጊዜ እንደገለፁት፤ የዘንድሮው ዓመት የ12ኛ ክፍል ፈተና ከትግራይ ክልል ውጭ ባሉ አካባቢዎች ሐምሌ 3 ቀን 2016 ይጀመራል።

በዚህም መሠረት ከሐምሌ 3 እስከ 5 የሶሻል ሳይንስ ፈተና የሚሰጥ ሲሆን የተፈጥሮ ሳይንስ ፈተና ደግሞ ከሐምሌ 9 እስከ 11/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ነው የገለፁት።

በትግራይ ክልል ደግሞ በሁለት ዙር ፈተናው የሚሰጥ ሲሆን ሐምሌ 2 ተጀምሮ ሐምሌ 12 እንደሚጠናቀቅ ጠቁመዋል።

በትምህርት ሚኒስቴር የትምህርት ዲጂታላይዜሽንና የአይሲቲ መሪ ሥራ አስፈፃሚ ዘላለም አሠፋ(ዶ/ር) በበኩላቸው፤ የዘንድሮው ዓመት የ12ኛ ክፍል ፈተና በኦንላይንና በወረቀት እንደሚሠጥ ተናግረዋል።

በዘንድሮው ዓመት 701ሺህ 489 ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል ፈተናን እንደሚወስዱ ተገልጿል።

ትምህርታቸውን ዘግይተው የጀመሩና በተለያዩ ምክንያቶች በዚህ መርኃ ግብር መሰረተ ፈተና ላይ መቀመጥ ለማይችሉ ተማሪዎች ሁለተኛ ዙር ፈተና እንደሚዘጋጅም ጠቁመዋል።

@sheger_press
"ካለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ የመገናኛ ዘዴዎችን መጥለፍ፣ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን ለመመርመር የሚያስችል ረቂቅ ህግ ለፓርላማ ቀረበ‼️

በወንጀል የተገኘ ንብረትን ሕጋዊ ከማስመሰል ወይም ሽብርተኝነትን በገንዘብ ከመርዳት ወንጀል ጋር በተያያዘ ያለ ፍርድ ቤት ትዕዛዝ መገናኛዎችን እና ደብዳቤዎች ለመጥለፍ ለመርማሪዎች ፈቃድ የሚሰጥ ረቂቅ አዋጅ ለተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ።

አዲሱ ረቂቅ በሥራ ላይ ያለውን በወንጀል የተገኘ ንብረት ሕጋዊ ማስመሰል እና ሽብርተኝነትን በገንዘብ የመርዳት ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ የሚሽር ነው።

ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው ረቂቅ አዋጅ መርማሪ አካል “አስቸኳይ ሁኔታ ካጋጠመው” የሚመለከተውን የዐቃቤ ሕግ ተቋም የበላይ ኃላፊ በማስፈቀድ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ የመገናኛ እና የደብዳቤ ልውውጦችን መጥለፍ ይችላል።

መገናኛዎችን እና የደብዳቤ ልውውጦችን መጥለፍ ከወንጀሎቹ ጋር በተያያዘ ተግባራዊ ከሚደረጉ የምርመራ ዘዴዎች መካከል ናቸው።

በባንክ ሂሳቦች እና በሌሎች ተመሳሳይ ሂሳቦች ላይ ክትትል ማድረግ፣ የኮምፒውተር ሥርዓቶችን፣ መረቦችን ሰርቨሮችን መለየትም በተመሳሳይ ሌሎች የምርመራ ዘዴዎች ናቸው።

ከዚህ በተጨማሪም በሽፋን ስር የሚደረግ ምርመራም (undercover operation) በተመሳሳይ በአዋጁ የተጠቀሰ የምርመራ ዘዴ ነው::

@ethio_mereja_news
ህወሃት ይቅርታ ጠየቀ

ህወሃት ከጦርነቱ ቀደም ብሎ በ2013 ዓ.ም ከብሄራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና ውጪ ያካሄደው ህገወጥ ምርጫ ስህተት መሆኑን በማመን ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የይቅርታ ደብዳቤ መፃፉን የውስጥ ምንጮች ገልፀዋል።

ህወሀት በምርጫ ቦርድ የፓርቲነት ህጋዊ ሰውነቱ ተነስቶ እንደነበር ይታወቃል።
ባለፈው ሳምንት ህወሃት ወደ ህጋዊ ፓርቲ ሊመለስ የሚችልበት ህግ በህዝብ ተወካዮች ምክር መፅደቁን ተከትሎ በዚህ ውሳኔ ህወሃት ደስተኛ መሆኑን መግለፁ አይዘነጋም።

አሁን ላይ ህወሃት ህጋዊ ፓርቲ ሆኖ በብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ለመመዝገብ መደላድል ስለተፈጠረ ከዚህ ቀደም በ2013 ዓ.ም በትግራይ ያካሄደው ህገወጥ ምርጫ ድርጅቱ በወቅቱ ያካሄደው ምርጫ ስህተት መሆኑን በማመኑ ሰሞኑን ለብሄራዊ ምርጫ ቦርድ የይቅርታ ደብዳቤ እንዳስገባ የውስጥ ምንጮች ገልጸዋል።(ayu)

@ethio_mereja_news
በአማራ ክልል አመት በሞላው ግጭት በተለይ ትምህርት ስራ ላይ ከፍተኛ ተፅዕኖ  አሳድሯል።

ዛሬ የሰሜን ሸዋ ዞን እንዳስታወቀው በ9 ወረዳዎች የሚገኙ የ8ኛ ክፍል ተማሪዎች ለፈተና አልተቀመጡም።ማስፈተን የተቻለው በ14 ወረዳዎች ብቻ ማስፈተን እንደተቻለ ዞኑ አሳውቋል።

ከምስራቅ ጎጃም ዞን ትምህርት መምሪያ በተገኘ መረጃ መሰረት ዘንድሮ በዞኑ ከሚገኙ 996 አንደኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ 32ቱ ብቻ ክፍት ሆነው ተማሪዎቻቸው የተቀበሉት።

ት/ቤት መገኘት ከነበረባቸው 539,000 የሚሆኑ ተማሪዎች 13,000 ብቻ ናቸው እየማሩ የሚገኙት ብሏል ።

በዞኑ 593 ት/ቤቶች 38,203 ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ፈተና እንደሚወስዱ ቢታቀድም በ10 ት/ቤቶች  431 ተማሪዎች ብቻ ናቸው ፈተና የወሰዱት።

ከ407 በላይ ት/ቤቶች እንዲወድሙና ለመማር ማስተማር አገልግሎት እንዳይሰጡ ሆነዋል።

ከ290.3 ሚሊዮን በላይ የት/ቤቶች ሀብትና ንብረት ወድሟል።

ከርቀት ሆኖ ሲታይ ለሌሎች ቀላል መስሎ የታየው የአማራ ክልል ግጭት በመቶ ለሚቆጠሩ ሰዎች ሞት እና በቢሊየን ለሚቆጠር ሀብት ውድመት ምክንያት ሆኗል።አሁንም በተለያዩ አካባቢዎች እንደቀጠለ ነው።የፈጠነ የንግግር መፍትሄ ቢወሰድ መልካም ነው።(wasu mohammed)

@sheger_press
@sheger_press
2024/06/26 05:11:09
Back to Top
HTML Embed Code: