Telegram Web Link
ሱማሊያ፣ የኢትዮጵያ ወታደሮች በቀጣዩ ዓመት ታኅሳስ መጨረሻ ከአገሪቱ እንዲወጡ ያሳለፈችውን ውሳኔ አጥፋለች ተብሎ የተሠራጨውን መረጃ የአገሪቱ ውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ አስተባብሏል።

ሚንስቴሩ፣ ሱማሊያ የአፍሪካ ኅብረት የሰላምና ጸጥታ ምክር ቤት የወቅቱ ሊቀመንበር የኾነችው ታንዛኒያ በጉዳዩ ዙሪያ የተፈጠረውን ችግር ለማርገብ ከኢትዮጵያ ጋር እንድታሸማግላት ጠይቃለች መባሉንም "ሐሰት ነው" ብላለች።

ሚንስቴሩ ማስተባበያውን ያወጣው፣ የአገሪቱ አንዳንድ ዜና ምንጮች እና ማኅበራዊ መገናኛ ዘዴዎች ውጭ ጉዳይ ሚንስቴሩ ለታንዛኒያ አቻው የጻፈው ደብዳቤ አግኝተናል በማለት መረጃውን ማሠራጨታቸውን ተከትሎ ነው። 

የሱማሊያ መንግሥት፣ የኢትዮጵያ ወታደሮች እስከ ቀጣዩ ታኅሳስ መጨረሻ ከአገሪቱ እንዲወጡ እና የአፍሪካ ኅብረትን ጦር ይተካል ተብሎ በሚጠበቀው ኅብረብሄራዊ ተልዕኮ ሥር እንዳይካተቱ መወሰኑን ባለሥልጣናቱ ሰሞኑን መናገራቸው ይታወሳል።

@ethio_mereja_news
በአማራ ክልል ጎንደር ከተማ ወደ ሌሎች አጎራባች ከተሞች የሚደረጉ የትራንስፖርት እንቅስቃሴዎች ከዕሁድ'ለት ጀምሮ መቆማቸውን ዋዜማ ሰምታለች።

ከዕሁድ ጀምሮ ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ዛሬ እኩለ ቀን ድረስ ከጎንደር ወደ ባሕርዳር እንዲኹም ከባሕርዳር ወደ ደብረታቦር የሚወስዱ መንገዶች ለተሽከርካሪ እንቅስቃሴ ዝግ እንደኾኑ የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል።

መንገዶቹ የተዘጉት፣ የፋኖ ታጣቂዎች ባስቀመጡት የትራንስፖርት እንቅስቃሴ ክልከላ ምክንያት መኾኑን የገለጹት ነዋሪዎቹ፣ ላለፉት አራት ቀናት ከባሕርዳር ወደ ኹሉም የጎንደር አካባቢዎች የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ አለመኖሩን ገልጸዋል።

ከ10 ቀናት በፊት በሦስቱ የጎጃም ዞኖች ተመሳሳይ የተሽከርካሪዎች እንቅስቃሴ ገደብ እንደነበር ዋዜማ መዘገቧ ይታወሳል።

አንድ ጊዜ ለአራት ወራት የተራዘመውና ባጠቃላይ ለ10 ወራት የቆየው አስቸኳይ ጊዜ አዋጅ የጊዜ ገደቡ ለኹለተኛ ጊዜ ሳይራዘም ትናንት አብቅቷል።

ኾኖም መንግሥት አስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ስለማብቃቱ በይፋ ያለው ነገር የለም።

@ethio_mereja_news
የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል ዕለት ይሰጣል ተብሎ የነበረው የሬሚዲያል (የማካካሻ) ትምህርት የማጠቃለያ ፈተና ቀን ተለወጠ፡፡

የሬሚዲያል (የማካካሻ) ትምህርት የማጠቃለያ ፈተናን ከሰኔ 3-10/ 2016 ዓ.ም ድረስ ለመስጠት መዘጋጀቱን፤ ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቆ እንደነበረ አይዘነጋም፡፡

ሆኖም ሰኔ 9/ 2016 ዓ.ም የኢድ አል-አድሃ (አረፋ) በዓል ስለሆነ በዕለቱ ይሰጣል ተብሎ የነበረውን ፈተና ሰኔ 11/2016 ዓ.ም እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር ተናግሯል፡፡

@ethio_mereja_news
በዜጎች የመንቀሳቀስ ነጻነት ላይ የሚፈጸሙ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ሊቆሙ ይገባል ተባለ

የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ በኦሮሚያ እና በአማራ ክልሎች እንዲሁም በተወሰኑ የኢትዮጵያ አካባቢዎች የህዝብ የትራንስፖርት እና የጭነት አገልግሎት የሚሰጡ ተሽከርካሪዎች መቸገራቸውን ገልጿል።

በእነዚህ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ የመንግስት የፀጥታ ኃይል ልብስ በለበሱ አካላት በመታጀብ ደረሰኝ እየቆረጡ አንዳንድ አካባቢዎች ላይ ደግሞ ያለ ደረሰኝ የጦር መሳሪያ ይዞ በመቆም የይለፍ (የኮቴ) እያስከፈሉ ነው ብሏል።

ኢሰመጉ ባወጣው መግለጫ በመንግስት የትራንስፖርት ተቆጣጣሪ ሰራተኞች ተገቢ ያልሆኑ ድርጊቶች ይፈጸማሉም ነው ያለው።

አሁንም ድረስ በሾፌሮች እና በተሳፋሪዎች በአንዳንድ ቦታዎች እገታ እየተፈጸመ እንደሆነ በመገለጫ ገልጿል።

@ethio_mereja_news
የፌደራሉ የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በአማራ ክልል የሚካሄደው ግጭት እና አለመረጋጋት ከሕዝብ የሚቀበለውን ቅሬታ ከ80 በመቶ በላይ እንደቀነሰበት መግለጡን ሸገር ዘግቧል።

በባሕርዳር የሚገኘው የተቋሙ ቅርንጫፍ፣ በክልሉ የሚታየው አለመረጋጋት ከቦታ ቦታ ተንቀሳቅሶ ለመስራት እንቅፋት ስለኾነብኝ በውስን የክልሉ አካባቢዎች ላይ ብቻ ለመስራት መገደዱንና 50 በመቶ የሚኾነውን የክልሉን አካባቢ መሸፈን እንዳልቻለ መግለጡን ዘገባው አመልክቷል።

ባለፈው ዓመት ከ1 ሺህ 300 በላይ አቤቱታዎችን የተቀበለው ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ፣ በዘንድሮው ዓመት ግን ከ200 አቤቱታዎች በላይ እንዳልተቀበለ መናገሩን ዘገባው ጠቅሷል፡፡

ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤቱ፣ በክልሉ የሚካሄደው ግጭት በባሕርዳር ዙሪያ፣ ጎንደር ከተማ እና በሌሎች የተወሰኑ የክልሉ አካባቢዎች ብቻ እንድንቀሳቀስ አስገድዶኛል ብሏል ተብሏል።

የፌደራሉ የሕዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም፣ በኦሮሚያ ክልል ያለው አለመረጋጋት ከአዲስ አበባ ከ200 ኪሎ ሜትር ርቀት በላይ በሚገኙ የክልሉ አካባቢዎች ተንቀሳቅሶ እንዳይሠራ እንቅፋት እንደፈጠሩበት መናገሩንም ዜና ምንጩ አመልክቷል።

@ethio_mereja_news
የአገራዊ የምክክር ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ትናንት ያቀረበችበትን ቅሬታ ተከትሎ ከቤተክርስቲያኗ ቅዱስ ሲኖዱስ ጋር ለመወያየት ዝግጁ መኾኑን አስታውቋል።

ኮሚሽኑ፣ የአካታችነት መርሁ ከኹሉም የኃይማኖት ተቋማት ጋር "በእኩልነት የሚተገበር" መኾኑን  ገልጧል።

ቅዱስ ሲኖዶሱ፣ አገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ቤተክርስቲያኗ በምክክር ተሳታፊዎች እና አጀንዳ ልየታ ሂደቱ እንድትሳተፍ ጥሪ ሳያደርግ መቅረቱ ቅሬታ እንደፈጠረበት ትናንት ባወጣው መግለጫ ገልጦ ነበር።

ኮሚሽኑ ግን፣ ከጅምሩ በምክክር ሂደቱ አብሮ ለመስራት የመግባቢያ ሠነድ የተፈራረመው ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጋር እንደኾነ ጠቅሷል፡፡

ጉባዔው፣ በተሳታፊዎች ልየታ እና በአዲስ አበባ አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት "ከፍተኛ አስተዋጽኦ" ማድረጉንም ኮሚሽኑ ጠቅሷል።

@ethio_mereja_news
የአክሱም አየር ማረፊያ ዛሬ አገልግሎት መስጠት ጀመረ‼️ 

በጦርነቱ ወቅት የህወሓት ሃይሎች ከጥቅም ውጪ አድርገውት የቆየው የአክሱም አየር ማረፊያ ፤ ከሶስት አመት ቦኃላ በፌደራል መንግስት ተጠግኖ በዛሬው ዕለት ሰኔ 1 /2016 ዓ.ም አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

@ethio_mereja_news
#Notcoin

❤️Telegram wallet verify ማድረግ ያልቻላችሁ ወይም tonkeeper ላይ notcoin ያላችሁ መሸጥ የምትፈልጉ

😄 በዚህ አናግሩን 👉 @Birukepromo

❤️ልብ ይበሉ

በእነዚህ user name መጥታችሁ ስትገበያዩ ገንዘባችሁ 100% ይሰጣችኋል (ሀላፊነቱን @sheger_press ይወስዳል)

ክፍያው እንደ ስምምነታችሁ ይፈፀማል

በእነዚህ ሰዎች ለመገበያየት ስትሄዱ ያላችሁ ስክሪንሽት አድርጋችሁ ማሳየት ግድ ነው

ton space ቤታ ከሆነ ኮይናችሁ ደግሞ 0.2 ክፍያ ስለሚጠይቅ ቶን ኮይን ከሌላችሁ ቅድሚያ ከፍላችሁ መውሰድ

notcoinu ልካችሁ ስትጨርሱ አድሚኑ በተስማማቹበት ዋጋ ብራችሁ መልሶ ያስገባል!!


🚫ለማጭበርበር የምትመጡ ካላችሁ ወዲያው Block ሰለምናረጋችሁ አትልፉ እንዳመጡ!!

ሲቀጥል የማትሸጡ አትምጡ ጊዜያችን አታቃጥሉ

ለተለያዩ ONLINE ስራዎች ለመስራት ይህን ቻናል ይቀላቀሉ👇👇
https://www.tg-me.com/sheger_crypto
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዛሬ የመኖሪያ ቤት የአከራይና ተከራይ የውል ስምምነት ምዝገባ ማካሄድ ጀምሯል።

የከተማዋ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አከራዮችንና ተከራዮችን የውል ምዝገባ በኹሉም ክፍለ ከተሞች የጀመረው፣ የከተማዋ አስተዳደር ያወጣውን የመኖሪያ ቤቶች ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ ተግባራዊ ለማድረግ ነው።

አዋጁ፣ የመኖሪያ ቤት አከራዮች አስተዳደሩ በዓመት አንድ ጊዜ ከሚወስነው የኪራይ ጣሪያ በላይ ኪራይ ከመጨመርና ተከራዮችን በግዳጅ ከማስወጣት የሚከለክል ነው።

አስተዳደሩ አዋጁን ያወጣው፣ ተከራዮች በአገሪቱ የተከሰተውን የኑሮ ውድነት መቋቋም እንዲችሉ አስተዋጽኦ ያደርጋል በሚል እምነት እንደኾነ መግለጡ ይታወሳል።

@ethio_mereja_news
ባለፈው ረቡዕ ታጣቂዎች በኦሮሚያው ሆሮ ጉደሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ በፈጸሙት ጥቃት ሦስት ሰዎች እንደተገደሉ ዴይቸቨለ ዘግቧል።

በሞተር ሳይክል በመጓዝ ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ በተፈጸመው ጥቃት ከተገደሉት ሰዎች መካከል፣ አንድ መምህር እንደሚገኝበት ዘገባው አመልክቷል።

ጥቃቱን ያደረሱት፣ በዞኑ ኡሙሩ ወረዳ እና በአጎራባቹ የምሥራቅ ወለጋ ዞኑ ኪረሙ ወረዳ አዋሳኝ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች እንደኾኑ የወረዳው አስተዳደር ሃላፊዎች መናገራቸውን ዜና ምንጩ ጠቅሷል።

በኡሙሩ ወረዳ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በተለይ ባለፉት ሦስት ዓመታት በፈጽሟቸው ማንነትን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች ሳቢያ ከ40 ሺህ በላይ ሰላማዊ ሰዎች ተፈናቅለውበት የነበረ አካባቢ ነው።

@ethio_mereja_news
ከሃምሳ አመታት ጥረት በኋላ የወንዶች እርግዝና መከላከያ መድሃኒት በቅርቡ መመረት ይጀምራል ተባለ፡፡

የወንዶች እርግዝና መከላከያ መድሃኒትን ለማምረት ላለፉት 50 ዓመታ የተለያዩ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡

ይሁንና እስካሁን ድረስ አንድም የወንዶች እርግዝና መድሃኒት ማምረት ያልተቻለ ሲሆን የተደረጉ ጥረቶች አሁን ላይ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ መድረሳቸው ተገልጿል፡፡

እንደ ሲቢኤስ ዘገባ ከሆነ የወንዶች እርግዝና መከላከያ መድሃኒትን ለማምረት የተለያዩ ኩባንያዎች በሙከራ ለይ ሲሆኑ በክትባት መልኩ እና በሌሎች መልኩ የሚሰጡ መድሃኒቶችን ለማምረት ሙከራዎች እየተካሄዱ ናቸው፡፡

እየተደረጉ ካሉ የወንዶች እርግዝና መከላከያ መድሃኒቶች መካከል በጄል መልክ ክንድ ላይ የሚቀባው መድሃኒት አንዱ ነው፡፡
በአሜሪካ ብሔራዊ የወሊድ መከላከያ ኢንስቲትዩት በኩል እየተደረገ ያለው ይህ ጄል መሳይ የወንዶች እርግዝና መከላከያ መድሃኒት የመጀመሪያውን እና ሁለተኛውን ደረጃ ሙከራ ማጠናቀቁ ተገልጿል፡፡

የወንዶች የወሊድ መከላከያ እንክብል 99 በመቶ ውጤታማ ሆኗል ተብሏል።

ይህ ጄል የወንዶችን የዘር ፈሳሽ መጠን በመቀነስ እርግዝና እንዳይፈጠር የሚያደርግ ነው የተባለ ሲሆን በ222 በጎ ፈቃደኛ ወንዶች ላይ ተሞክሮ እስካሁን ውጤታማ ሆኗል ተብሏል፡፡

ሌሎች ተቋማትም የወንዶች እርግዝና መከላከያ መድሃኒቶችን ለማምረት ጥረቶች ላይ ናቸው የተባለ ሲሆን ከሆርሞን ጋር የማይገናኙ የህክምና ቁሳቁሶችን ለማምረትም ተመሳሳይ ተቋማት የመጨረሻ ደረጃዎች ላይ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

እስካሁን በዓለማችን የወንዶች እርግዝና መከላከያ መድሃኒት ለማምረት የተመዘገበ ህጋዊ ተቋም የሌለ ሲሆን በሙከራ ለይ ያሉ ተቋማት ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ መድሃኒቶችን ለማምረት ፈቃድ ለማግኘት እንደሚያመለክቱ አስታውቀዋል፡፡
Via Al ain

@ethio_mereja_news
#ኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአራት አመታት በኋላ ወደ አክሱም ከተማ ዳግም በረራ ጀምሯል። 

#ትግራይ ጦርነት ጉዳት የደረሰበት አጼ ዮሐንስ 4ኛ አውሮፕላን ማረፊያ የተደረገለት ጥገና ተጠናቆ ዛሬ ሰኔ 2 ቀን 2016 መደበኛ ስራ ጀምራል።

ዛሬ በተደረገ የመጀመሪያ በረራም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑትን አቶ መስፍን ጣሰውን፣ የፌደራል እና የክልል የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ 140 ተጓዦች የያዘው  አውሮፕላን አክሱም ሃፀይ ዮሐንስ አራተኛ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ አቀባበል ተደርጓል።

በአቀባበል ስነ ስርዓቱ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ባለስልጣናት ተገኝተዋል።

በረራውም በየቀኑ 1 ጊዜ የሚደረግ ሲሆን በቀጣይ የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት በማድረግ በቀን ወደ 3 ጊዜ ለማሳደግ እንደሚሰራም ተጠቁሟል፡፡

@ethio_mereja_news
የበርካታዎችን ሕይወት በቀጠፈው የሰሜኑ ጦርነት ወቅት በየቦታው የተቀበሩ እና የተጣሉ ተተኳሾች ፣ ፈንጂዎች አሁንም በሰው ህይወት ላይ አደጋ ማድረሳቸው ቀጥሏል።

በአፋር፣ በትግራይ እና በአማራ ክልሎች የተቀበሩ ፈንጂዎች ለሰው ህይወት መጥፋትና ለአካል መጉደል ምክንያት እንደሆኑ በተደጋጋሚ ሲገለጽ ነበር።

በትግራይ ክልል በምሰራቃዊ ዞን ሐውዜን ወረዳ ማይጎቦ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ትናንት ሰኔ 1 2016 በፈነዳ ተተኳሽ አራት ሰዎች ሕይወት መቀጠፉ ተሰምቷል።

@sheger_press
2024/09/29 23:15:36
Back to Top
HTML Embed Code: