Telegram Web Link
የአሜሪካ ማዕቀብ ጦስ የፕሬዝዳንቱን ሕይወት ቀጥፏል‼️

አሜሪካ የአውሮፕላን መለዋወጫ ቁስ ላይ ማዕቀብ በመጣሏ በተደጋጋሚ የአውሮፕላን አደጋ የሚገጥማት ኢራን ፕሬዝዳንቷንና ውጪ ጉዳይ ሚኒስትሯን አሳቷታል።

ፕሬዝዳንቱ ይበሩበት የነበረው ይህ ሔሊኮፕተር ስሪቱ የአሜሪካ የሆነና በርካታ አመታትን ያስቆጠረ መሆኑ ሳያንስ ኦሪጅናል መለዋወጫ አልባ ነበር።

ኢራን ውስጥም ከዚህ የተሻለ ሔሊኮፕተር ባለመኖሩ ነው ፕሬዝዳንቱ እንዲበሩበት የተደረገው።

ፕሬዝዳንት ኢብራሒም ራይሲ የታሰፈሩበት አሮጌ ሄሊኮፍተር በወቅቱ አስቸጋሪ የነበረውን የአየር ሁኔታ ማለፍ ባለመቻሉ ምክንያት ከባልደረቦቻቸው ጋር ህይወታቸውን አጥተዋል።

ፕሬዚዳንቱ ኢራን ከአዘርባጃን ጋር በምትዋሰንበት ድንበር አካባቢ የተገነቡ ሁለት ግድቦችን አስመርቀው ወደ ታብሪዝ እያመሩ ነው አደጋው ያጋጠማቸው፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
#Tecno #Camon30Pro5G

ቪድዮዎች እና ምስሎችን በከፍተኛ ጥራት ማንሳት እንዲያስችል Sony Imx890 የካሜራ ሴንሰርን የተገጠመለት አዲሱ Tecno Camon Pro 5G ምርጫዎ ያድርጉ

#Camon30Et #Camon30pro5GEt #Camon30 #Camon30Pro5G #TecnoEt
ጥቆማ‼️

1000 ሺ ሰው ሲሞላ ወደ ስራ እንገባለን‼️
እንዳያመልጣቹ በፍጥነት ተቀላቀሉ👇
https://www.tg-me.com/sheger_crypto

እንዴት ኦንላይን ገንዘብ ማግኘት ይቻላል⁉️
crypto ምንድነው⁉️

የሚሉትን ጥያቄዎች ልንመልስላቹ ነው
አሁን አሁን ቴሌግራም አሪፍ ገንዘብ መስሪያ እየሆነ መቷል።

ታድያ አዲስ በከፈትነው በዚ ቻናል ከ ዜሮ ተነስተን እንዴት ክሪፕቶ እና ኤር ድሮፖችን መስራት እንዳለብን የምንማማርበት የቴሌግራም ቻናል ይሆናል

በዚ ሊንክ ተቀላቀሉ👇👇
https://www.tg-me.com/sheger_crypto
https://www.tg-me.com/sheger_crypto
ኢራን‼️

በሄሊኮፕተር አደጋ ፕሬዚዳንቷን ያጣችው ኢራን ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት ሾመች!!

የኢራኑ መንፈሳዊ መሪ አያቶላህ አሊ ሃሚኒ መሃመድ ሞክበርን የኢራን ተጠባባቂ ፕሬዚዳንት አድርገው ሾመዋል፡፡
ዜና ሹመት‼️

ዶ/ር አብርሃም በላይ ከመከላከያ ሚኒስትርነታቸው በመነሳት ሌላ ሹመት ተሰጣቸዉ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው እለት ሹመቶች ሰጥተዋል


ዶ/ር አብርሃም በላይ ከመከላከያ ሚኒስትርነታቸው በመነሳት የመስኖና ቆላማ አካባቢ ሚኒስቴር ሚንስትር መሆናቸዉን የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት አስታዉቋል።

በተጨማሪም ዶ/ር አብርሃም በላይን በመተካት ኢንጂነር አይሻ መሀመድ የመከላከያ ሚኒስቴር ሚንስትር መሆናቸዉን ዳጉ ጆርናል ያገኘዉ መረጃ ያመላክታል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ በዛሬው እለት ሹመት ከሰጧቸዉ ሰዎች ዉስጥ ዶ/ር መሀመድ እንድሪስ በሚኒስትር ዴኤታ ማዕረግ በዲሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ማስተባበሪያ ማዕከል ከግንቦት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ተሹመዋል ተብሏል::

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ቤቲንግ‼️

ቤቲንግ ቤቶች ከሀዋሳ ከተማ  ሙሉ ለሙሉ ለመዝጋት እንቅስቃሴ መጀመሩ መረጃዎች ተሰምተዋል።

በሀዋሳ ከተማ እና አከባቢዋ የሚገኙ ቤቲንግ (ቁማር) ቤቶች ፣ ሺሻ ቤቶች እና ጫት መቃሚያ ስፍራዎችን ለመዝጋት የጸጥታ ስራ እየተከናወነ እንደሚገኝ መረጃዎች አመላክተዋል።

ማህበረሰቡ ይበል የሚያሰኝ እና በቀጣይነት ሊሰራ የሚገባው ጉዳይ ነው በማለት የደገፈ ሲሆን ከተማው ውስጥ የሚደረጉ የሞተር ዝርፊያዎች እና የመሳሰሉት ውንብድናዎች ምንጫቸው የእነኚህ ህገ ወጥ ቤቶች መበራከትም ነው ብለዋል።

ሆኖም በር ዘግተው በጓዳ ተደብቀው የሚሰሩ ስላሉ ጥብቅ ክትትል ያስፈልጋል በማለትም አክለዋል።

የክልሉ እና የከተማው መንግስት የበርካቶችን ህይወት እያበላሸ እንዲሁም ውንብድናዎችን እያበራከቱ ያሉ እንዲህ አይነት ህገ-ወጥነቶችን ከማህበረሰቡ መረጃ በመሰብሰብ በዘላቂነት መፍትሔ መስጠት እንደሚያስፈልግ ነዋሪዎቹ ጠቁመዋል።

@sheger_press
@sheger_press
ጥቆማ‼️

እንዳያመልጣቹ ‼️

ምንም ገንዘብ ሳታወጡ ብር ልታገኙባቸው የምችሏቸው የኦንላይን ኤርድሮፖች ባዲሱ ቻናላችን መለቀቅ ተጀምሯል።

አሁንኑ በመቀላቀል
ትርፋማ ይሁኑ👇👇
https://www.tg-me.com/sheger_crypto
https://www.tg-me.com/sheger_crypto
የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ የእስር ማዘዣ ወጣባቸው፡፡

ዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ፍርድ ቤት በዚህ የንጹሃን ዜጎች ግድያ ተጠያቂ ናቸው ባላቸው መሪዎች ላይ የእስር ትዕዛዝ አስተላልፏል ሲል ሮይተርስ ዘግቧል፡፡

እንደዘገባው ከሆነ የእስራኤል ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ እና ዮዓቭ ጋላንት ከእስራኤል በኩል ከሐማስ በኩል ደግሞ ሶስት አመራሮች የእስር ማዘዣው የወጣባቸው አመራሪች ናቸው፡፡በሐማስ በኩል ደግሞ የሐማስ ሀላፊ ያህያ ሲነዋር፣ የሐማስ ጦር አዛዥ መሀመድ አል ማስሪ እንዲሁም የሐማስ ታጣቂዎች ኮማንደር እስማኤል ሀኒያህ የእስር ማዘዣ ወጥቶባቸዋል፡፡

ደቡብ አፍሪካ፣ ቱርክ እና ሌሎችም ሀገራት እስራኤል ንጹሀንን በመግደል እና ሌሎች የከፋ ጥቃት አድርሳለች በሚል በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ፍርድ ቤት እንድትጠየቅ ግፊቶች ሲያደርጉ የነበሩ ሀገራት ናቸው፡፡እስራኤልም ሆነች ሐማስ የጦር ወንጀሎችን እንዳልፈጸሙ ተናግረው በዓለም አቀፉ የጦር ወንጀል ፍርድ ቤት ያወጣውን የእስር ማዘዣ ውድቅ አድርገዋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Binance‼️

- ባይናንስ ምንድነው ⁉️
- የባይናንስ ጠቀሜታ ምንድነው ⁉️
- ባይናንስ ኢትዮጵያ ውስጥ ሆነን ⁉️
   እንዴት እንጠቀማለን
- የባይናንስ አከፋፈት በቪድዮ ምን ይመስላል

የሚሉትን ጥያቄዎች መልስ
በዝርዝር ይመልከቱ👇👇

JOIN US👇👇
https://www.tg-me.com/sheger_crypto
https://www.tg-me.com/sheger_crypto
ጥቆማ‼️

እንዳያመልጣቹ ‼️

ምንም ገንዘብ ሳታወጡ ብር ልታገኙባቸው የምችሏቸው የኦንላይን ኤርድሮፖች ባዲሱ ቻናላችን መለቀቅ ተጀምሯል።

አሁንኑ በመቀላቀል
ትርፋማ ይሁኑ👇👇
https://www.tg-me.com/sheger_crypto
https://www.tg-me.com/sheger_crypto
በመዲናዋ የድምጽ ብክለት ጉዳት እያስከተለ ነው ተባለ  

በአዲስ አበባ ከተማ የድምጽ ብክለት በማህበረሰቡ ላይ ጉዳት እያስከተለ መሆኑን የአዲስ አበባ የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አስታወቀ።

ባለስልጣኑ ከብዙ ምንጮች የሚነሱ ከቁጥጥር ውጭ የሆኑ ከፍተኛ ድምጾች በህብረተሰቡ ላይ አለመረጋጋት፣ ደስታ ማጣትና እና ሌሎች የጤና እክሎችን እያስከተሉ መሆኑን ለአራዳ ገልጿል።
 
ብክለቱ የመስማት ችግርን፣ አለመግባባትን፣ የደም ግፊት፣ የአዕምሮ ህመም፣ በእርጉዝ ሴቶች ላይ ደግሞ ፅንስ ማስወረድ ችግርና የጤና እክል እያስከተለ እደሚገኝ ጠቁሟል።

ከመገበያያ ስፍራዎች፣ ከሆቴሎች፣ ከሃይማኖት ተቋማት፣ ከስፖርት ሜዳዎች፣ ከሙዚቃ ማጫዎቻና ሌሎች ስፍራዎች የሚወጡ ድምጾች ለድምጽ ብክለት መንስኤ ናቸው ነው የተባለው።

ደካማ የሆነው የመዲናዋ የግንባታ ዲዛይንም ለድምጽ ብክለት ትልቅ አስተዋፅኦ እንዳለውም አንስቷል።

Arada_Fm

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
"ፖሊሱ ተይዞ ምርመራ እየተደረገበት ነው" የአፋር ፖሊስ

በማህበራዊ ሚዲያዎች የከባድ መኪና ሹፌር በማስቆም ሲያስፈራራ እና ሲያንገላታ  የሚታየው የፖሊስ አባል በቁጥጥር ስር ውሎ ምርምራ እየተጣራ እንደሚገኝ የአፋር ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ጄኔራል ቢልኤ አህመድ ገልጸዋል።

ይህ አሽከርካሪ ላይ በግድ መንገደኛ የመጫን ተግባር ከፖሊስ ዲሲፕሊን ውጭ የሆነ ተግባር  በመሆኑ  የአፋር ክልል ፖሊስ ጉዳዩን በማጣራት ተመጣጣኝ የሆነ ህጋዊ እርምጃ እንደሚወስድ ማረጋገጣቸውን ፋስት መረጃ ከአፋር ፖሊስ ያገኘው ሰምቷል።

ኮሚሽነር ጄነራሉ ይህ ተግባር የህዝብ ልጅ እና በህዝባዊ  ወገንተኝነቱ የሚታወቀው የአፋር ፖሊስ እንደማይወክል አሰረድተዋል።
fastmereja

@ethio_mereja_news
#Tecno #Camon30Pro5G

Tech – art leather ቴክኖሎጂ በመጠቀም እጅግ ዘመናዊ ዲዛይን የተላበሰው አዲሱ Tecno Camon 30 pro 5G ምርጫዎ ያድረጉ!

#Camon30Et #Camon30pro5GEt #Camon30 #Camon30Pro5G #TecnoEt
ደሞዝ‼️

የወላይታ ዞን የሠራተኞቹን ደሞዝ ከሚቀጥለው ዓመት ተበድሮ ለመክፈል መገደዱ ተገለፀ!!

የዞኑ የመንግሥት ሠራተኞች ባለፉት ሳምንታት ጀምሮ በአደባባይ የሦስት ወራት ደሞዛቸው እንዲከፈላቸው በሰላማዊ ሰልፍ በመጠየቅ ላይ ይገኛሉ።

ያምሆኖ እስከአሁን ለጥያቄያቸው ከዞንና ከክልል መስተዳድሮች ተግባራዊ ምላሽ እንዳላገኙ ሠራተኞቹ ተናግረው በዚህም የተነሳ አሁን ላይ ከነቤተሰቦቻቸው በችግር ላይ መውደቃቸውን ሠራተኞቹ ተናግረዋል።

የሠራተኞቹን የደሞዝ ይከፈለን ጥያቄ አስመለክቶ ከዶቼ ቬለ ጋር ቃለምልልስ ያደረጉት የዎላይታ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሳሙኤል ፎላ ዞኑ ለሠራተኞቹ ደሞዝ መክፈል ያተቸገረው በሁለት ምክንያቶች ነው ይላሉ፦ አንድም የወረዳ መዋቅሮች መሥፋት ሁለትም ሲንከባለል በመጣው የአፈር ማዳበሪያ ዕዳ የተነሳ የበጀት አለመጣጣም በመከሰቱ ነው ብለዋል።

በተለይም በዞኑ አዳዲስ የወረዳ መዋቅሮች መበራከት፣ የሠራተኞች እና ተሾሚዎች ቁጥር መጨመር ለበጀት ጉድለቱ መከሰት ምክንያት መሆኑን የጠቀሱት ዋና አስተዳዳሪው “በተለይም ባለፉት አራት ዓመታት የአገልግሎት ተደራሽነትን ለመፈጠር ተጨማሪ የወረዳ እና የከተማ አስተዳደሮች በመቋቋሙ የሠራተኛውና የተሾሚዎችን ቁጥር እንዲጨምር በማድረግ በ2009 ዓም ላይ 23 ሺህ የነበረው የዞኑ ሠራተኞች ቁጥር አሁን ላይ ከ61 ሺህ በላይ ደርሶ በዕቅድ ላይ ያልተመሠረተ የሠራተኛ ቅጥር በዞኑ ላይ የበጀት ጫና ፈጥሮ ይገኛል“ ብለዋል።

ወላይታ ሶዶ ደሞዝ እንዲከፈላቸው በሰልፍ የሚጠይቁ የመንግሥት ሠራተኞች ዎላይታ ሶዶ ደሞዝ እንዲከፈላቸው በሰልፍ የሚጠይቁ የመንግሥት ሠራተኞች የዎላይታ ዞን በሠራተኞች ቁጥር መጨመር እና በማዳበሪያ ዕዳ ምክንያት ደሞዝ ለመክፈል መቸገሩን አስተዳዳሪው ተናግረዋል።

በአሁኑ ወቅት አጣዳፊ የሆነውን የሠራተኞችን ደሞዝ ለመክፈል የዞኑ መስተዳድር ከቀጣዩ የ2017 ዓም በጀት ታሳቢ የሚደረግ ብድር በመውሰድ ችግሩን በጊዚያዊነት ለመፍታት እየጣረ እንደሚገኝ ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል።

በተቃራኒው የዎላይታ ዞን ባለፉት ዘጠኝ ወራት ብቻ ከ 3 ነጥብ 2 ቢሊየን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡ የተገለፀ ቢሆንም በአከባቢው ልማት ስራዎች ቆሞ በአብዛኛው መዋቅር ደመዝ መክፈል አለመቻሉ ለበርካቶች "ለምን" የሚል ጥያቄ ፈጥሯል።

@ethio_mereja_news
ጓደኛቸውን በመግደል ሲያሽከረክረው የነበረውን መኪና ወስደው ተሰውረዋል የተባሉ ሁለት ግለሰቦች በ24 ሰዓታት ውስጥ በቁጥጥር ስር ዋሉ!

የወንጀል ድርጊቱ የተፈፀመው ግንቦት 8 ቀን 2016 ዓ/ም በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 ሰሜን ማዘጋጃ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ነው፡፡ከአዲስ አበባ ፖሊስ የወንጀል እና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ዘርፍ  የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ገ/ሚካኤል ሰይፉ የተባለው ሟች የወንጀል ፈፃሚዎቹ የቅርብ ጓደኛ በመሆኑ በየዕለቱ እየተገናኙ አብረው የሚውሉ፣ የሚዝናኑ እና በእጅጉ የጠነከረ የጓደኝነት ግንኙነት ያላቸው የሱሉልታ ከተማ ነዋሪዎች እንደሆኑ  ተጠርጣሪዎቹ ለፖሊስ በሰጡት ቃል አረጋግጠዋል።

በዕለቱ ሟች በወንጀሉ ከተጠረጠሩት ከሁለቱ ጓደኞቹ ጋር አብሮ ሲዝናና እንዳመሸ ታውቋል።ተጠርጣሪዎቹ  ቴዎድሮስ ታከለ እና  ሲሳይ ጥላሁን ከምሽቱ 5 ስዓት ገደማ የጓደኛቸውን  አንገት በማነቅ ህይወቱ እንዲያልፍ ካደረጉ በኋላ አስክሬኑን መንገድ ላይ በመጣል  ሞባይል ስልኩንና መታወቂያውን ጨምሮ በወቅቱ ሲያሽከረክረው የነበረውን የሰሌዳ ቁጥር ኮድ 4-15624 ኢት መኪና ወስደው ተሰውረዋል ተብሏል፡፡

ፖሊስ የወንጀሉ ሪፖርት ከደረሰው በኋላ ባደረገው ያልተቋረጠ ክትትል ወንጀሉን ፈፅመዋል ተብለው የተጠረጠሩትን ግለሰቦች ለይቶ በማወቅ በ24 ሰዓታት ውስጥ በቁጥጥር ስር አውሏቸዋል፡፡ አንደኛው ተጠርጣሪ ከአየር ጤና አካባቢ የተያዘ ሲሆን ሁለተኛው ተጠርጣሪ  ደግሞ ሱሉልታ ከተማ ውስጥ ሊገኝ ችሏል፡፡

ግለሰቦቹ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ በተከናወነ ምርመራ የማስፋት ስራ የሰረቁትን ተሽከርካሪ በሸገር ከተማ ወለቴ ተብሎ ወደሚጠራው አካባቢ በመውሰድ እንዲሸጥላቸው ለአንድ ግለሰብ እንደሰጡት በማረጋገጥ መኪናው ከቆመበት በምሪት እንዲመለስ ተደርጓል፡፡ተሽከርካሪውን ለመሸጥ ተስማምቶ ከተጠርጣሪዎቹ የተቀበለውን ግለሰብ በቁጥጥር ስር አውሎ በህግ ተጠያቂ ለማድረግ የክትትል እና የምርመራ ስራው  የቀጠለ መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል።

@ethio_mereja_news
ማስታወቂያ!

የመውጫ ፈተና ድጋሚ ተፈታኞች የምዝገባ ጊዜን ስለማሳወቅ!

በ2016 ዓ.ም ሰኔ ወር ላይ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና በድጋሚ ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለምትገኙ አመልካቾች በሙሉ፤
ምዝገባ የሚከናወነው ከግንቦት 14 – 21/2016 መሆኑን አውቃችሁ የምዝገባ ክፍያ አምስት መቶ (500.00) ብር በመክፈል በ https://exam.ethernet.edu.et በኩል መመዝገብ የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን።

ማሳሰቢያ፤
1. ለመጀመሪያ ጊዜ የመጫ ፈተና የምትፈተኑ እጩ ተመራቂዎች ምዝገባ የሚካሄደው እና የአገልግሎት ክፍያ በተቋማችሁ በኩል መሆኑን እየገለጽን አስፈላጊ የመፈተኛ መረጃዎች በተቋማችሁ የሚደርሳችሁ መሆኑን እናሳውቃል።

2. የድጋሚ ተፈታኞች የአገልግሎት ክፍያ አምስት መቶ ብር (500.00 ብር) በቴሌ ብር ብቻ የሚከናወን ይሆናል።

የኢፌዲሪ ትምህርት ሚኒስቴር
#Tecno #Camon30Pro5G

Tecno Camon 30 pro 5G በአስገራሚ ቴክኖሎጂዎች እና በአገልግሎቱ ልቆ የቀረበ የዘመኑ ምርጥ ስልክ!

#Camon30Et #Camon30pro5GEt #Camon30 #Camon30Pro5G #TecnoEt
2024/09/29 23:28:59
Back to Top
HTML Embed Code: