Telegram Web Link
ትጥቅ አንግበው የሚታገሉ አካላት ወደ ሀገራዊ ምክክር መድረክ እንዲመጡ ጥሪ ቀረበ

ትጥቅ አንግበው የሚታገሉ አካላት ወደ ሀገራዊ ምክክሩ መድረኮች እንዲመጡ የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽን ጥሪ አቀረበ፡፡

ግጭት ሕይወትና ንብረትን ያጠፋል እንጂ ችግርን እንደማይፈታ የገለጹት የኮሚሽኑ ምክትል ዋና ኮሚሽነር ሂሩት ገ/ሥላሴ÷ ታሪካዊ አጋጣሚ በሆነው ሀገራዊ ምክክር በመሳተፍ ሐሳብን በማቅረብ መግባባት እንደሚገባ አስገንዝበዋል፡፡

በዚህም ትጥቅ አንግበው እየታገሉ ያሉ አካላት ወደ ምክክሩ እንዲመጡ ከፍተኛ ጥረት ሲደረግ መቆየቱን አስታውሰው÷ አሁንም ወደ ምክክሩ እንዲመጡ በመጠየቅ ሲመጡም ጥበቃ እንደሚደረግላቸው አረጋግጠዋል፡፡

ኮሚሽኑ የሚያመቻቻቸው መድረኮችም ማንኛውም ሰው በነጻነት የሚሳተፍባቸው መሆናቸውን አስረድተው÷ ትጥቅ አንግበው የሚታገሉ አካላት ወደ ሀገራዊ ምክክር መድረኩ እንዲመጡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡(ኤፍ ቢ ሲ)

@ethio_mereja_news
የአማራ ክልል መንግሥት ለሕዝቡ ጥሪ አቀረበ‼️
የሕወሓት ታጣቂ ቡድን የሰላም አማራጮችን ወደ ጎን በመተው የማንነት ጥያቄ ያለባቸውን የራያ አላማጣ፣ የራያ ባላ፣ ኦፍላ፣ ኮረም እና ዛታ አካባቢዎችን በወረራ ይዟል::

ይህንን ተከትሎ የአማራ ብሔራዊ ክልል መንግሥት ከሰሞኑ ባወጣው መግለጫ የአማራ ሕዝብ ዛሬም እንደትላንቱ ከሀሰት ፕሮፓጋንዳ እና ከሰርጎ ገቦች ራሱን እና አካባቢውን እንዲጠብቅ ጥሪ አስተላልፏል::

ሕዝቡ ከክልሉ መንግሥት እና በየአካባቢው ከሚገኙ አስተዳደሮች ጋር የጠበቀ ቁርኝት በመፍጠር ጠላቶቹ የከፈቱበትን ጥቃት ለመመከት በሚደረገው ጥረት የድርሻውን እንዲወጣ ነው ጥሪ ያደረገው::

የክልሉ መንግሥት ከአማራ ሕዝብ በተጨማሪ ለፌደራል መንግሥት እና ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ  ጥሪ አቅርቧል፤ ለፌደራል መንግሥት ባስተላለፈው ጥሪ የሕወሓት ታጣቂ ቡድን በወረራ ከያዛቸው ቦታዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ ለቆ እንዲወጣ እና ሕዝቡን ከጥፋት መታደግ እና የሀገሪቱን ሉዓላዊነት መታደግ እንደሚገባ ጠቁሟል::

ለዓለም አቀፉ ማሕበረሰብ ደግሞ ሕወሓት በክልሉ ሕዝብ ላይ የፈጸመውን ወረራ በጥብቅ እንዲያወግዝ እና ከክልሉ ሕዝብ ጎን እንዲቆም ጥሪ አቅርቧል::
ሚያዝያ 14 ቀን 2016 ዓ.ም
(አሚኮ )

@sheger_press
@sheger_press
አማጺው የኦሮሞ ነጻነት ሠራዊት በኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን ወረ ጃርሶ ወረዳ ከአማራ ክልል በተነሱ ተሽከርካሪዎች ላይ ባለፈው ሳምንት ዓርብ በርካታ ሰዎችን አፍኖ መውሰዱን ዋዜማ በስፍራው ካሉ ምንጮቿ ሰምታለች።

አማጺው ቡድን እገታውን የፈጸመው፣ በጎሃጽዮን እና ቱሉ ሚልኪ ከተሞች መሃል ባለች ቢቱ ወንዝ ተብላ በምትጠራ ሥፍራ እንደሆነ ምንጮች ተናግረዋል።

እገታው የተፈጸመው፣ መነሻውን ከምሥራቅ ጎጃም ዞን ሞጣ ከተማ ባደረገው በተልምዶ "ታታ" ተብሎ በሚጠራ የሕዝብ ማመላለሻ አውቶቡስ እና በሦስት ከባድ የጭነት ተሽከርካሪዎች ሲጓዙ በነበሩ መንገደኞች ላይ እንደኾነ ምንጮች ጠቁመዋል።

ይህ ዜና እስከተጠናቀረበት ሰዓት ድረስ፣ ታፍነው የተወሰዱት ሰዎች በታጣቂ ቡድኑ ቁጥጥር ስር መኾናቸውንም ዋዜማ ባደረገችው ማጣራት መረዳት ችላለች።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ኢሠማኮ፣ ዘንድሮ ሚያዝያ 23 ቀን በኢትዮጵያ ለ49ኛ ጊዜ የሚከበረው የዓለም ሠራተኞች ቀን በአዳራሽ ውስጥ ብቼ እንዲከበር መወሰኑን አስታውቋል። ኢሠማኮ፣ በበዓሉ የአከባበር ሁኔታ ላይ እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው፣ "የአገሪቱን አጠቃላይ ኹኔታ" እና "በአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ" ሥር የሚገኙ አከባቢዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት እንደኾነ ገልጧል።

ኾኖም ይህ የበዓሉ አከባበር፣ ባሕርዳር፣ ኮምቦልቻና በአዲስ አበባ ዙሪያ የሚገኙ ከተሞችን እንደማይጨምር ኢሠመኮ አመልክቷል።

የኢሠማኮ ፕሬዝዳንት፣ እስከ በዓሉ ድረስ ጠቅላይ ሚንስትሩ የሠራተኞችን ተወካዮች በሠራተኛው ጥያቄዎች ዙሪያ እንዲያነጋግሩ መወሰኑንና ጥያቄው ለጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት መቅረቡን ኢሠማኮ ጨምሮ ገልጧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አጫጭር መረጃዎች‼️ ሌላ ጦርነት የአማራ ህዝብ ተነስ:
ወሎ ህዝባዊ ሀይሉ ፖሊስ ጣቢያ ገባ; አሜሪካ እና እስራኤል ተጋጩ:

መረጃዎቹን በዝርዝር ይመልከቱ👇😢

https://youtu.be/wwRm2A2-U4Y
https://youtu.be/wwRm2A2-U4Y
በአቡዳቢና ዱባይ የሚገኙ ኢትዮጲያዉያን ከጉዞ ሰነድና ቪዛ ጋር ተያይዞ ያሉ የአገልገሎት አሰጣጥ ችግሮች እንዲፈቱ ተጠየቀ

በአቡዳቢና ዱባይ አካባቢ እየተሰጠ ባለው የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎቶች ከዚህ ቀደም የሚነሱ ቅሬታዎች እየተፈቱ መሆኑን የኮሚኒቲ አባላት፣ ተወካዮችና አመራሮች ተናግረዋል።በኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት የተመራ ልዑክ በአቡዳቢና ዱባይ ሚሲዮኖች የሚሰጡ የዜግነት አገልግሎቶችን ያሉበትን ሁኔታ ተመልክቶ ከሚሲዮን መሪዎችና ኮሙኒቲ ተወካዮች ጋር ተወያይቷል።

በውይይቱ በሚሲዮኖቹ ከፓስፖርት እድሳትና ተያያዥ አገልግሎቶች ጋር በተያያዘ ዜጎች ላቀረቡት ጥያቄ የተሰጠው ምላሽ የሚደነቅ ቢሆንም፤ ከጉዞ ሰነድና ቪዛ ጋር ተያይዞ ያሉ የአገልገሎት አሰጣጥ ችግሮች እንዲፈቱ ተጠይቋል፡፡በተጨማሪም የመረጃ ልውውጥ ክፍተት፣ ሐሰተኛ ማስረጃ፣ የጉዞ ሰነድ (ሊሴ ፓሴ)፣ የበይነ-መረብ አጭበርባሪዎች መበራከት እንዲሁም ከዜግነት አገልግሎት ጋር ያሉ ክፍተቶች መኖራቸው ተጠቁሟል፡፡

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ወ/ሮ ሰላማዊት ዳዊት÷ ተቋሙ 11 የሪፎርም አጀንዳዎችን ቀርጾ ወደ ስራ በመግባቱ ከዜጎች አገልግሎት ጋር በተያያዘ እየታዩ ያሉ ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴዎች መታየታቸውን ተናግረዋል።የሪፎርሙ ስራ ሙሉ ለሙሉ ሲጠናቀቅ በዘርፉ የተስተዋሉ ችግሮችን ለመቅረፍ እንደሚያስችልም ገልጸዋል።

ከሰነድ አልባና ከዜግነት አገልግሎት ጋር ያሉ ስራዎች ከሀገር ደህንነት ጋር በጥብቅ የተቆራኘ በመሆኑ በጥንቃቄና በህግ አግባብ ብቻ መሰራት እንዳለበት አስገንዝበዋል።ልዑኩ ባደረገው ጉብኝት የዱባይ ሚሲዮን ቴክኖሎጂን በመጠቀም ረገድ የሚከተለው አሰራር እንደተሞክሮ ሊወሰድ የሚገባ መሆኑን እንደተመለከተ ዋና ዳይሬክተሯ ተናግረዋል።
65 በመቶው የሚሆኑ እስራኤላዉያን ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ ጥሩ እንቅልፍ እንደማይተኙ አንድ ጥናት አመላከተ

የእስራኤል ዬዲዮት አህሮኖት ሚዲያ እና የሪችማን ዩኒቨርሲቲ የነፃነት እና ኃላፊነት ተቋም ባደረጉት የህዝብ አስተያየት 85 በመቶ የሚሆኑ እስራኤላውያን በመንግስታቸው ላይ እምነት የላቸውም።64 በመቶ ያህሉ እስራኤላውያን አገራቸው የህልውና ስጋት እንዳለባት የሚያምኑ ሲሆን 65 በመቶው ደግሞ ጦርነቱ ከተቀሰቀሰ በኋላ ጥሩ እንቅልፍ እንዳልተኙም ገልጿል።

ቢያንስ 73 በመቶ የሚሆኑት እስራኤላውያን ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ በጭንቀት ተውጠዋል።በሌላ በኩል የዮርዳኖስ ሃሺሚት መንግሥት በሁለት ክልላዊ ኃይሎች እስራኤል እና ኢራን መካከል ክልላዊ ውጥረቱ እየጠነከረ ከቀጠለ ከባድ ማህበራዊ፣ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ መዘዞች ሊገጥማቸው ይችላል በሚል የማሸማገል ሚናዉን እየተወጣ ይገኛል።

ዮርዳኖስ ማንኛውም ክልላዊ እርምጃ በኢራን እና በእስራኤል መካከል ያለው ጠላትነት መባባስ ወይም እስራኤል ራፋህ ከወረረች በአገር ውስጥ ተቀጣጣይ ምላሾች ሊኖሩት ይችላል ብላለች።በሴናጎህ ዩኒቨርሲቲ የዮርዳኖስ ኤክስፐርት እና ከሬሲሊየንስ ቱ ሪቮሊሽን ፀሃፊ ሼን ዮም "ማንኛውም የማይቀር የኢራን እና የእስራኤል ጦርነት ዮርዳኖስን በጠባብ ገመድ ላይ ሊያስቀምጣት እንደሚችል ለአልጀዚራ ተናግሯል። ከአደባባይ ውዝግብ መራቅ እንዳለበት ከየትኛውም ተዋጊ ጋር መቆም እንደማይቻል ገልጸዋል፡፡
ሕወሓት ብልፅግናን ለመቀላቀል በድርድር ላይ ነው ተባለ

ሕወሓት ከአራት ዓመት በፊት “ሕገ – ወጥ ነው” ያለውን ገዥውን ፓርቲ ብልፅግና ለመቀላቀል ተከታታይ ድርድሮች እያደረገ መሆኑን ዳ፤ ዋዜማ ከተለያዩ ምንጮች አሰባስቤ ሰራሁት ያለችዉ ዘገባ ያመለክታል።

ከሁለት ዓመት ደም አፋሳሽ ጦርነት በኋላ የፕሪቶሪያውን የሰላም ስምምነት የፈረመው ሕወሓት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ አህመድ በሊቀመንበርነት የሚመሩትን ብልፅግናን በመቀላቀል በሀገራዊ ጉዳዮች አብሮ ለመስራት መስማማቱን ቢገልፅም ፓርቲውን ለመቀላቀል ቅድመ ሁኔታ አስቀምጧል።

ከብልፅግና በፊት የነበረው ኢሕአዴግ እኩል የስራ አስፈፃሚና ማዕከላዊ ኮሚቴ ውክልና ያላቸው አራት ንዑስ ፓርቲዎች ጥምረት ሲሆን ብልፅግና ግን አንድ ወጥ ፓርቲ ነው። የብልፅግና የፓርቲ ውክልና በህዝብ ብዛት የሚወሰን እንጂ እንደ ኢሕአዴግ አባል ድርጅቶች እኩል ውክልና አይኖራቸውም።

አሁንስ እየተደረገባቸው ባለው ድርድር ሕወሓት የብልፅግና ፓርቲ ሕገ-ደንብ ተሻሽሎ በፓርቲ ውስጥ አባል ድርጅቶች እኩል የማዕከላዊ ኮሚቴና የስራ አስፈፃሚ ውክልና እንዲኖራቸው ይፈልጋል። ብልፅግና ግን ሕወሓት የተናጠል ህልውናውን አክስሞ ብልፅግናን እንዲቀላቀልና ውክልናውም በትግራይ ህዝብ ቁጥር ልክ የሚወሰን መሆኑን ይገልፃል።

የሕወሓት ሊቀ መንበር ደብረፅዮን ገብረሚካዔል በአዲስ አበባ ተገኝተው ይህን ድርድር የጀመሩት ሲሆን ከሁለት ሳምንት በኋላ የብልፅግና ምክትል ሊቀመንበር አደም ፋራህ ወደ መቀሌ ተጉዘው በጉዳዩ ላይ በስፋት ተነጋግረዋል።

በሕወኋት በኩል ብልፅግናን መቀላቀል “ስህተት ነው …አስፈላጊም አይደለም” ብለው የሚያምኑ አመራሮች ቢኖሩም ፣ ውህደቱ ለትግራይ ችግሮች መፍትሄ ለማምጣት ጠቀሜታ አለው፣ በተለይም የትግራይን ፀጥታና ደህንነት ለመስጠበቅ ከብልፅግና ጋር አብሮ መቆም አስፈላጊ ነው ብለው የሚያምኑም አሉ።

Via ዋዜማ
@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ከአላማጣ እና አከባቢዋ ተፈናቅለው ቆቦ እና ሰቆጣ የተጠለሉ ሰዎች ቁጥር 50 ሺ መሻገሩ ተገለጸ

በቅርቡ በራያ አላማጣ አከባቢ ተከስቶ በነበረው አለመረጋጋት ሳቢያ ከቀያቸው ተፈናቅለው በሰሜን ወሎ ዞን ቆቦ ከተማ እና በዋግ ህምራ ዞን ሰቆጣ ከተማ ተጠልለው የሚገኙ ሰዎች ቁጥር ከ50 ሺ በላይ መሆኑን  የመንግስታቱ ድርጅት የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ቢሮ (ኦቻ) ባወጣው መግለጫ አስታወቀ።

የተፈናቃዮቹ ቁጥር ያገኘሁት ከሁለቱ ዞኖች አስተዳደር ነው ያለው የቢሮው መግለጫ በአከባቢው ከሚያዚያ 5 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በተፈጠረው አለመረጋጋት እስከ ሚያዚያ 11 ቀን 2016 ዓ.ም ሪፖርት የተደረገ ተፈናቃዮች ቁጥር 29 ሺ እንደሚጠጋ አስታውሷል።

በቆቦ ከተማ ተጠልለው የሚገኙ ተፋናቃዮች ቁጥር 42 ሺ መድረሱን የጠቆመው ቢሮው በሰቆጣ የሚገኙ ተፈናቃዮች ቁጥር 8 ሺ 300 መሆኑን ገልጿል።

አብዘሃኛዎቹን ተፈናቃዮች የቆቦ ከተማ ማህበረሰብ አስጠልሏቸው እንደሚገኝ የጠቆመው ቢሮው ሌሎቹ ደግሞ ከከተማዋ በሶስት ኪሎ ሜትር ርቆ በሚገኝ ጋሪያ ሌንጫ በተባለ ቦታ ላይ የድንኳን መጠለያ ዘርግተው እየኖሩ መሆኑን ገልጿል።

ምንጭ፦ አዲስ ስታንዳርድ

@ethio_mereja_news
በትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ሕይወት አለፈ

በሰሜን ሸዋ ዞን ደብረ ሊባኖስ ወረዳ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ4 ሰዎች ሕይወት አለፈ።

አደጋው ከአዲስ አበባ ወደ ደብረ ሊባኖስ ገዳም እየተጓዘ የነበረ የቤት አውቶሞቢል ከኮሶበር ወደ አዲስ አበባ ሲጓዝ ከነበር የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ጋር ቀሲም በተባለ ልዩ ቦታ በመጋጨቱ የደረሰ ነው።

በአደጋው የአራት ሰዎች ሕይወት ወዲያውኑ ሲያልፈ በ14 ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት፤ በስምንት ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል ጉዳት ደርሶባቸዋል።

የደብረ ሊባኖስ ወረዳ ትራፊክ ደህንነት አስተባባሪ ረዳት ኢንስፔክተር ኃይለማርያም ደባሌ÷ የአደጋው መንስኤ በፍጥነት ማሽከርከር እና ቅድሚያ አለመሰጠት መሆኑን መናገራቸዉን ከወረደዉ ኮሙኒኬሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሰውዬው ተገኝተዋል

ኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ለገጣፎ አቅራቢያ 44 ማዞሪያ ጅዳ ኩራ በተባለ ፖሊስ ጣቢያ መታሰራቸው ታውቋል።

እኝህ ሰው በተደበደቡ፣በተበደሉ፣ጥቃት በደረሰባቸው እንደት ሊታሰሩ ቻሉ ለሚለው ምላሽ አልተገኘም።

በወቅቱ እሳቸውን ከፍ ዝቅ እያደረኩ ርካሽ የዘረኝነት ተግባር ሲፈፅሙባቸው የነበሩ ወጣቶች ተሰብስበው መታሰራቸውም ተሰምቷል።(wasu)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Breaking ‼️

ህወሓት ብልፅግናን ሊቀላቀቀል ነዉ መባሉን ተከትሎ ከብልፅግና ጋር የጀመርኩት ንግግር የለም ሲል አስተባበለ

የህወሓት እና የብልፅግና ድርድር ከፕሪቶሪያ ስምምነት በኋላ የተፈጠረውን አንፃራዊ ሰላም ለማስፋት እና ለማጠናከር ያለመ ነው ያለው ህወሓት ፤ ህወሓት እና ብልፅግና መሰረታዊ የዓላማ እና የአስተሳሰብ ልዩነት ያላቸው ፓርቲዎች መሆናቸውን ገልጿል።

አክሎም ልዩነቱ እንዳለ ሆኖ ሁለቱ ፓርቲዎች ሊወያዩባቸው የሚገቡ ብዙ አጀንዳዎች አሉና በነዛ ዙርያ ውይይት እያደረግን ነው ማለቱን ዳጉ ጆርናል ከፓርሪዉ መግለጫ ተመልክቷል። ከዚህ ውጭ ግን እንደሚወራው ህወሓት ብልፅግናን ለመቀላቀል ንግግር ጀምሯል የተባለው ጉዳይ ሐሰት ነው ሲልም በይፋዊ የፌስቡክ ገፁ ፓርቲዉ አጋርቷል።

በዛሬዉ እለት ህወሓት ብልጽግና ፓርቲን ሊቀላቀል መሆኑን ዳጉ ጆርናል የዋዜማ ሚዲያ ዘገባን ዋቢ በማድረግ መረጃ ማድረሱ ይታወሳል። ይህንኑ ተከትሎም ህወሓት ይፋዊ መግለጫ አዉጥቷል።

@sheger_press
@sheger_press
ሀሰተኛ የህክምና ማስረጃ በመጠቀም ወንድማችን ታሟል በማለት ሲያጭበረብሩ የነበሩ አምስት ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ

በደቡብ ኢትዮጵያ ወላይታ ሶዶ እና በ በተለያዩ ወረዳዎች በመዘዋወር ታማሚ በማስመሰል የማጨበርበር ተግባር ሲፈጽሙ የነበሩ  ግለሰቦች በህብረተሰቡ ጥቆማ መያዛቸውን ፖሊስ አስታዉቋል።

በማጨበርበር ድርጊቱ የተሰማሩት ተጠርጣሪዎች አብዛኛዎቹ ወጣቶች ሲሆኑ  ከተለያዩ አከባቢዎች በመምጣት ሀሰተኛ የህክምና ማስረጃ በማዘጋጀት  ወንድማችን በህመም እየተሰቃየብን ነው በማለት መኪና በመከራየት ሲያጭበረብሩ መገኘታቸዉ ተገልጿል።

ተጠርጣሪዎቹ  ከአስራ ዘጠኝ ሺህ ብር በላይ ከህብረተሰቡ በማጨበርበር መሰብሰባቸውን የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ኢንስፔክተር አሸናፊ ሀይሌ ለብስራት ሬዲዮ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ከሰሞኑ በቤተክርስቲያን ዉስጥ ሲተኩስ የታየዉን የፌዴራል ፖሊስ አባል ተከትሎ ኮሚሽኑ ከመተዳደሪያ ህግና አሠራር ውጭ ነዉ ሲል ኮነነ

የፖሊስ አባሉም ይህንን ተግባር እንደፈፀመ ወዲያውኑ በቁጥጥር ሥር ዉሏል
ተብሏል

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ በማህበራዊ የትስስር ገጹ ላይ ካሰራጨዉ መግለጫ ሸገር እንደተመለከተው ፖሊስ ከየትኛውም ሃይማኖት፣ ብሄር እና ፖለቲካ  ወገንተኝነት የፀዳ እና ብዛህነትን እሴቱ ያደረገ ሕዝባዊ ተቋም መሆኑን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የሃይማኖቶች ብዛህነትን የሚያከብርና የሚያስከብር በእኩልነት ለሁሉም ሙያዊ አገልግሎት የእየሰጠ ያለ ተቋም ሆኖ ሳለ ከኢትዮጵያ ፖሊስ ዩኒቨርስቲ አዲስ የፖሊስ አባላትን ለመመልመል ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ የተላከ የፖሊስ አባል ምክትል ሳጂን ታመነ ዱባለ ጥር 5 ቀን 2016 ዓ.ም ኬቾ ወዜ ቅዱስ ባለወልድ ቤተክርስቲያን  በመገኘት የደንብ ልብሱን እንደለበሰ ሃይማኖታዊ መዝሙር በመዘመር እና በሕዝብ ፊት ጥይት እየተኮሰ በማህበራዊ ሚዲያ ሰሞኑን የሚሰራጨው ቪዲዮ ከተቋሙ መተዳደሪያ ህግና አሠራር ውጭ እንደሆነ መግለጫው ወቅሷል።

አባሉም ይህንን ተግባር እንደፈፀመ ወዲያውኑ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ   በቁጥጥር ሥር አውሎት የፈፀመው ድርጊት በተቋሙ ሕገ ደንብ መሠረት በሕግ አግባብ እያጣራ እንደሚገኝ መግለጫው አመላክቷል።

ፖሊስ የሁሉም አገልጋይ ሆኖ ሳላ አባሉ እምነቱን በግል መከተል እየቻለ ነገር ግን መንግስት ፀጥታ እንዲያስከብር ያስታጠቀውን የጦር መሣሪያ ከፍተኛ ሕዝብ በተሰበሰበበት ቦታ ፍፁም የፖሊስን ዲሲፕሊን በጣሰ መልኩ የፈፀመው ተግባር በሕግ የሚያስጠይቅ ስለሆነ ተቋሙ ሕግ ፊት እንደሚያቀርበው በመግለጫው መጥቀሱን ሸገር ፕረስ ተመልክቷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በአዲስ አበባ እየተገነባ ያለ መኖሪያ ቤት የግንባታ ግብዓት ተንዶ በሌላ ቤት ውስጥ ተኝተው የነበሩ 7 ሰዎችን ለሕልፈት ዳረገ‼️

ዛሬ ሚያዝያ 16 ሌሊት 11 ሰዓት ላይ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 12፣ ጠሮ መስጂድ አካባቢ እየተገነባ ያለ የግለሰብ መኖሪያ ቤት የግንባታ ግብዓት በአቅራቢያው ባለ ሌላ መኖሪያ ቤት ላይ ተንዶ በቤቱ ውስጥ ተኝተው የነበሩ 7 ሰዎችን ለሕልፈት ዳርጓል።

የሟቾቹን አስከሬን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን የአደጋ ጊዜ ሠራተኞች አውጥተው ለፖሊስ ማስረከባቸው ተገልጿል።

@ethio_mereja_news
ኢትዮ መረጃ - NEWS
በአዲስ አበባ እየተገነባ ያለ መኖሪያ ቤት የግንባታ ግብዓት ተንዶ በሌላ ቤት ውስጥ ተኝተው የነበሩ 7 ሰዎችን ለሕልፈት ዳረገ‼️ ዛሬ ሚያዝያ 16 ሌሊት 11 ሰዓት ላይ በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ፣ ወረዳ 12፣ ጠሮ መስጂድ አካባቢ እየተገነባ ያለ የግለሰብ መኖሪያ ቤት የግንባታ ግብዓት በአቅራቢያው ባለ ሌላ መኖሪያ ቤት ላይ ተንዶ በቤቱ ውስጥ ተኝተው የነበሩ 7 ሰዎችን ለሕልፈት ዳርጓል። የሟቾቹን አስከሬን…
#Update

የግለሰብ መኖሪያ ተደርምሶ ከሞቱ 7 ሰዎች  መካከል የአራት አመት ህፃን መኖሩ ተነገረ

በአትክልት ተራ የሚሰሩት አባወራ አስቀድመው ለሊት 9 ሰአት ከቤት መውጣታቸው በህይወት ቢተርፉም በአደጋው ቤተሰቦቻቸውን አጥተዋል


በአትክልት ተራ የሚሰሩት አባወራም አስቀድመው ለሊት 9 ሰአት ከቤት መውጣታቸው በህይወት እንዲተርፉ ቢያደርጋቸውም በቤት ውስጥ ተኝተው ትተዋቸው በሄዱበት አጋጣሚ ሚስታቸውን እና ቤተሰባቸው የግንባታው እቃ ተደርምሶ እንደሞቱባቸው አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እያ ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

ዛሬ በአዲስ አበባ በአዲስ ከተማ ክፍለከተማ ወረዳ 12 ልዩ ቦታው ጠሮ መስኪድ አካባቢ ለሊት 11:00 ሰዓት ላይ እየተገነባ ያለ የግለሰብ ቤት የግንባታ እቃ ተደርምሶ የ7ሰዎች ህይወት ማለፉን ብስራት መዘገቡ ይታወሳል።

በአደጋው ከሞቱት ሰባት ሰዎች ውስጥ አራቱ ሴቶች ሲሆኑ የ28 ፤የ25 ፤የ12 አና የ11 ዓመት መሆናቸው አቶ ንጋቱ የተናገሩ ሲሆን ከሞቱት መሀከል የ30 የ12 እና የአራት አመት እድሜ ያላቸው ወንዶች ህይወታቸውን አተዋል።

@ethio_mereja_news
በልዩ ቅናሽ ኦርጅናል ስልኮች ይሸምቱ

Brand #Samsung

A15- 4 ram 128 GB - 16,500

A05 -4 ram 64 GB - 11,500

A34- 6ram 128 GB - 28,000

A54- 8ram 256GB - 38,000

S24 Ultra -12 ram - 512 GB -126,000

ይደውሉልን 👉 0913366506

Telegram @Birukepromo

ተጨማሪ እቃዎችን ለመሸመት የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ👇👇
https://www.tg-me.com/bura_collection
" ሰዎቹ ናቸው አታልለውኝ እዚያ ድረስ የወሰዱኝ " - ቀሲስ በላይ መኮንን

የቀሲስ በላይ መኮንን ጠበቃ አቶ ቱሊ ባይሳ ስለ ዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ቃላቸውን ሰጥተው ነበር።

በዚህም ወቅት ፥ ደንበኛቸው ቀሲስ በላይ መኮንን በሐሰተኛ ሰነድ ከ6 ሚሊዮን ዶላር በላይ ለማውጣት ሙከራ ተደርጎበታል የተባለው ቦታ የተገኙት " ሰዎች አታልለዋቸው " እንደሆነ ለፍ/ቤት መናገራቸውን ገልጸዋል።

ጠበቃ ቱሊ ፤ " እሳቸው በቦታው ከመገኘት ውጪ ደብዳቤውን በማዘጋጀት፣ በመቀበል በዚህ ወንጀል ውስጥ ተሳትፎ የላቸውም " ያሉ ሲሆን " ደብዳቤው ላይ የእሳቸው ስም፣ የባንክ ቁጥር የለም። የቤተ ክርስቲያን የሂሳብ ቁጥር የለም " ብለዋል።

" ከመጀመሪያውም ወንጀሉ በሌሎች ሰዎች የተሞከረ ቢሆንም እሳቸውን አይመለከትም " ሲሉ ገልጸዋል።

በችሎቱ ላይ ለመናገር ዕድል ያገኙት ቀሲስ በላይ የአፍሪካ ኅብረት ቅጥር ግቢ ውስጥ የተገኙት " ሰዎች ወስደዋቸው " እና " #ተታልለው " እንደሆነ ተናግረዋል።

" በዚያ ቦታ ላይ ከመገኘት ውጪ ምንም የፈጸሙት ድርጊት እንደሌለ " ገልጸዋል።

ቀሲስ በላይ ፦

" ሰዎቹ ናቸው አታልለውኝ እዚያ ድረስ የወሰዱኝ። እኔ ወደዚያ የሄድኩት ለመተባበር፣ ይህ ሰነድ ‘ትክክለኛ ሰነድ ነው አይደለም’ የሚለውን የባንክ ማናጀሮችን ለመጠየቅ ነው እንጂ በምንም ሁኔታ በሰነዱ ለመገልገል አስቤ አይደለም። ጉዳዩ ዞሮ እኔ ታሳሪ ሆንኩኝ እንጂ፤ ሰነዱ ‘ትክክል አይደለም’ የሚል የባንክ ማናጀሩ ሲገልጹልኝ ወዲያው ፖሊስ ያስጠራሁት እኔ ነኝ " ማለታቸውን ጠበቃው ተናግረዋል።

ቀሲስ በላይ ሰነዱን አዘጋጅተዋል የተባሉ ሰዎች " ማምለጣቸውን " እንዲሁም ስለ ሰነዶቹ " የሚያውቁት እና መመርመር ያላባቸው " እነሱ እንደሆኑም ለፍርድ ቤቱ አንስተዋል ተብሏል።

በዛሬው የፍ/ ቤት ውሎ የቀረበው የዋስትና ጥያቄ ውድቅ ተደርጎ ለመርማሪ ፖሊስ ስምንት ተጨማሪ ቀን መሰጠቱ ይታወቃል።

የመረጃው ምንጭ ቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/06/26 04:42:39
Back to Top
HTML Embed Code: