Telegram Web Link
ኢትዮ መረጃ - NEWS
Photo
" እውቀቱ ሳይኖራቸው ቤተክርስቲያንን ወክሎ ሃይማኖታዊ አስተምህሮ ማስተላለፍ አይገባም " - ብፁዕ አቡነ አብርሃም

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፥ የዲጀታል ሚዲያ እና ማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምን በተመለከተ የራሷን ሕግና መመሪያ እንደምታዘጋጅ አሳወቀች።

ይህ የተሰማው " ኦርቶዶክሳውያን ብዙኃን መገናኛ ለኦርቶዶክሳዊት ቤተ ክርስቲያን " በሚል በቤተክርስቲያኗ የሕዝብ ግንኙነት መመሪያ በተዘጋጀ ሥልጠና ላይ ነው።

ብፁዕ አቡነ አብርሃም የጠቅላይ ቤተክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ፣ የባህር ዳርና የሰሜን ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ፥ የብዙኃን መገናኛ ተቋማት እና ማኅበራዊ ሚዲያዎች ሐሰተኛ ወሬ ባለመቀበል እና ባለማስተላለፍ ኃላፊነታቸውን ሊወጡ ይገባል ብለዋል።

" ቤተክርስቲያንን ሳያውቁ ተገቢው ሙያና እውቀት ሳይኖራቸው የሃይማኖት አስተምህሮ ለማስተላለፍ እና በየማኅበራዊ ሚዲያው እና ዲጂታል ሚዲያው ለመንቀሳቀስ የሚሞክሩ አሉ " ሲሉ የጠቆሙት ብፁዕነታቸው " እውቀቱ ሳይኖራቸው ቤተክርስቲያንን ወክሎ ሃይማኖታዊ አስተምህሮ ማስተላለፍ አይገባም " ሲሉ አሳስበዋል።

" ማኅበራዊ ሚዲያውና ዲጀታል ሚዲያው  ከቤተክርስቲያን ይልቅ ለግለሰቦች እና ለቡድን ፍላጎቶች የመቆም ዝንባሌ በሰፊው ይታያል " ያሉ ሲሆን " ቅድሚያ ለቤተክርስቲያን መስጠት ይገባል ፤ ገንዘብ መስብሰብን ዓላማ ያደረገ የዲጂታል ሚዲያ እና ማኅበራዊ ሚዲያ ሥራ በመንፈሳዊ ቅኝት ያልተቃኘ በመሆኑ እርምት የሚሻ ነው " ሲሉ ገልጸዋል።

ብፁዕነታቸው በዲጂታል ሚዲያ እና ማኅበራዊ ሚዲያ የሚያገለግሉ እና የሚገለግሉ የቤተክርስቲኒቱ ልጆች ለቤተክርስቲያን ከማይጠቅሙ አጀንዳዎች ራሳቸውን እንዲያርቁ መክረዋል።

በዲጂታል ሚዲያና ማኅበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም በሕሙማን እና በቤተክርስቲያን ስም የሚከናወኑ ልመናዎች ለተባለው ዓላማ ስለመዋላቸው ማረጋገጥ ከእያንዳንዱ እርዳታ ሰጪ ይጠበቃል ሲሉ አስገንዝበዋል።

ሥርዓተ ቤተክርስቲያንን በጣስ መልኩ ምስጢራተ ቤተክርስቲያን እና ሥርዓተ አምልኮ በዲጂታል ሚዲያ የሚያስተላልፉ አገልጋዮች እና ሌሎች የማኅበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች ከድርጊታቸው መቆጠብ እንዳለባቸው አስጠንቅቀዋል።

" በቀጣይ የዲጀታል ሚዲያና ማኅበራዊ ሚዲያ አጠቃቀምን በተመለከተ የቤተክርስቲያኗ የራሷን ሕግና መመሪያ እንዲዘጋጅ ይደረጋል " ሲሉ አሳውቀዋል።(tikvah)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
እስራኤል በኢራን ላይ ለምትፈፅመው ማንኛውንም የአጸፋ ጥቃት ዩናይትድ ስቴትስ እንደማትቀላቀል ተናገረች

ዋይት ሀውስ እስራኤል በኢራን ላይ በምትሰነዘረው የአጸፋ ጥቃት አሜሪካ እንደማትሳተፍ  ማስጠንቀቋን ከፍተኛ የአስተዳደር ባለስልጣናት ገልፀዋል። ከ300 በላይ ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና ሚሳኤሎች በእስራኤል ላይ በአንድ ጀንበር ኢራን መተኮሷ የሚታወስ ሲሆን በሶሪያ የቴህራን ቆንስላ ፅህፈት ቤት እስራኤል ለፈፀመችው ጥቃት የአፀፋ ምላሽ ነው ስትል ኢራን አስታውቃለች። ሁሉም ማለት በሚቻል ደረጃ የጦር መሳሪያዎች ኢላማቸው ላይ ከመድረሳቸው በፊት በእስራኤል፣ በአሜሪካ እና በተባባሪ ሃይሎች ተመትተዋል።

ጆ ባይደን እስራኤል ምላሹን “በጥንቃቄ” እንድታጤነው አሳስበዋል። እሁድ እለት ለጋዜጠኞች መግለጫ የሰጡት አንድ የአሜሪከ ከፍተኛ የአስተዳደር ባለስልጣን ባይደን ለእስራኤሉ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንጃሚን ኔታንያሁ “በጣም በጥንቃቄ እና ስልታዊ በሆነ መንገድ እንዲያስቡ” መክረዋል። ኢራን በእስራኤል ላይ የፈፀመችው የመጀመሪያ ቀጥተኛ ጥቃት ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታውቅ እርምጃ ስለመሆኑ ተመላክቷል።በኢራን የአጸፋ ዘመቻ ከተተኮሱት ሚሳኤሎች፣ ድሮኖች እና ክሩዝ ሚሳኤሎች 99 በመቶ ያህሉ ከሽፈዋል።ይህም እንደ የአሜሪካ ባለስልጣናት ገለፃ የእስራኤል ጦር ከኢራን  የበላይ መሆኗን ማሳያ ነው ብለዋል።

ሆኖም ግን ባለስልጣናቱ ይህንን ይበሉ እንጂ ጥቃቱ በተፈፀመበት ወቅት የአሜሪካ አውሮፕላኖች እና የባህር ኃይል መርከቦች በደርዘን የሚቆጠሩ የኢራን ኢላማዎችብ አክሽፍዋል። ከ80 በላይ ሰው አልባ አውሮፕላኖች እና ቢያንስ ስድስት ባለስቲክ ሚሳኤሎች በአሜሪካ የባህር እና አየር ኃይል ተመተው ኢራቅ ላይ ወድቀዋል።የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት የኢራን አጸፋዊ ጥቃት በተመለከተ ለእስራኤል 14 ቢሊዮን ዶላር ርዳታ እንዲያጸድቁ የኮንግረሱ መሪዎችን አሳስበዋል።

የሪፐብሊካን ምክር ቤት አፈ-ጉባዔ ማይክ ጆንሰን ለፎክስ ኒውስ እንደተናገሩት ፓርቲያቸው “ከእስራኤል ጋር የመቆምን አስፈላጊነት” ተረድቷል እናም በዚህ ሳምንት የወጪ ጥቅሉን ለማስኬድ እንደሚሞክር ተናግረዋል ። የባይደን አስተዳደር ከየካቲት ወር ጀምሮ ለእስራኤል ፣ ዩክሬን እና ታይዋን የ 95 ቢሊዮን ዶላር የአሜሪካን ብሄራዊ ደህንነት ማሟያ ወጪ ፓኬጅ እንዲያፀድቅ በሪፐብሊካን ቁጥጥር ስር የሚገኘውን ምክር ቤት ግፊት እያደረገ ይገኛል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ባቲ‼️

ዛሬ የባቲ ከተማ ትልቁ የሠኞ ገበያ በአተት በሽታ ምክንያት በገዥና ሻጭ ሳትደምቅ ትውላለች‼️

በአማራ ክልል በባቲ ከተማ እና ባቲ ወረዳ ላይ በተለያዩ የገጠር ቀበሌዎች አካባቢ በተከሰተው #የአተት አጣዳፊ በሽታ ምክንያት ባቲ ከተማ አስ/ር ላይ  በየሣምንቱ የሚውለው ትልቁ ዛሬ ሰኞ ገበያ ሚያዚያ 7/2016ዓ/ም በገዥና ሻጭ ለህዝቦቿ ደህንነት ስትል ሳትደምቅ ጭርታ በዝቶባት የምትውል መሆኗ ተረጋግጦአል ።

በመሆኑም ዛሬ ሚያዚያ 7ቀን 2016 ዓ/ም ባቲ ከተማ ላይ ምንም አይነት ገበያ የማይውል መሆኑን ማህበረሰቡ ተረድቶ የሚገጥሙንን ችግሮች በጋራ በመከላከል ሀላፊነታችን እንወጣ ሲል የባቲ ከተማ አስተዳዲ የጤና ግብረ ሀይል  ያሣስባል።

የከተማ አስተዳደሩ የጤና ግብረ-ሀይል ከባቲ ሰኞ ገበያ ተጨማሪም የተለያዩ ክልከላዎችን የከለከለ ሲሆን ከነዚህም ውስጥ፦

👉1ኛ.በየመንገዱ ላይ ተጠባብሰው የሚሸጡ ምግቦች

👉2ኛ.ሀብሀብና የተለያዩ ፍራፍሬዎችን በመንገድ ላይ ዘርግቶ መሸጥ

👉3ኛ.ቀርሣ ውሃ እና ከአውሳ በር በታች የሚገኙ ውሃዎችን ከመጠቀም መቆጠብ።

👉4ኛ.የህፃናት ኬጂ ትምህርት ቤቶች ዛሬ ዝግ ሆኖ የሚውል በመሆኑ ወላጆች የኬጂ ተማሪዎችን ወደ ትምህርት ቤት ባለመላክ ንፅህናቸውን ጠብቆ በቤታቸው እንድቀመጡና በንፅህና እድመገቡ ማድረግ

👉5ኛ.ማህበረሰቡ የራስንና የአካባቢውን ንፅህና ጠብቆ ያልቀዘቀዙና ያልተበላሹ ምግቦችን በመመገብ የአተት በሽታን መከላከል የሚገባ መሆኑን ገልፆ አጣዳፊ ተቅማጥና ትውኪያ ከገጠመዎት ፈጥነው ወደ ጤና ተቋማት መምጣት እንዳይዘነጉ ሲል አሳስቧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
"ብሔራዊ ባንክ ሐሙስ ሚያዝያ 3 ቀን 2016 ዓ.ም. ይፋ ባደረገው የፋይናንስ ስታቢሊቲ ሪፖርት (Financial Stability Report) የባንክ ብድሮች በጥቂት ተበዳሪዎች እጅ ተከማችተው እንደሚገኙ ጠቅሷል‼️

👉ባንኮች ከሰጡት አጠቃላይ ብድር 23.5 በመቶውን ያበደሩት ለአስር ግለሰቦች ነው ተብሏል።😳

በአገሪቱ ያሉት ሁሉም ባንኮች እስካለፈው ዓመት ሰኔ መጨረሻ ድረስ በሥራ ላይ ካዋሉት አጠቃላይ 1.9 ትሪሊዮን ብር ብድር ውስጥ 23.5 በመቶውን ያበደሩት ለአሥር ተበዳሪዎች እንደሆነ በሪፖርቱ ተካቷል።

ከፍተኞቹ አሥር ተበዳሪዎች ከአጠቃላይ የባንክ ብድር መጠን ውስጥ በ2014 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ ከነበረው 18.7 በመቶ ነው በ2015 ዓ.ም. መገባደጃ ላይ ወደ 23.5 ያደገ ነው ተብሏል።"(ሪፖርተር)

@ethio_mereja_news
ከደቡብ ሱዳን ተሻግረዉ ወደ ጋምቤላ ክልል የመጡ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ የሙርሌ ታጣቂዎችን ወደመጡበት መመለስ ቢቻልም አሁንም በአንዳንድ አካባቢዎች ይገኛሉ ተባለ

ከደቡብ ሱዳን የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰዉ በመግባት በተከታታይ ጥቃት ሲፈጽሙ የነበሩት የሙርሌ ታጣቂዎች ከሰሞኑ በጋምቤላ ክልል ዲማ ወረዳ ጥቃት ፈጽመዉ እንደነበር ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል።

ታጣቂዎቹ መጋቢት 13 ቀን 2016 ዓ.ም ጥቃቱን ፈጽመዋል የተባለ ሲሆን አሁንም በወረዳዉ ሁለት ቀበሌያት ላይ እንቅስቃሴ እንደሚያደርጉ ስማቸዉን የማንጠቅሳቸዉ የወረዳዉ አንድ ባለስልጣን ለጣቢያችን ተናግረዋል።

ታጣቂዎቹ በአኩላ እና አቻኛ ቀበሌዎች እንቅስቃሴ እያደረጉ ይገኛሉ የተባለ ሲሆን በተለይም አኩላ በተሰኘዉ ቀበሌ በጸጥታ ሀይሎች ቅኝት እና ክትትል እየተረገ ነዉ ብለዉናል። አንዳንዶቹም በዚህ ክትትል ከመሸጉበት በቁጥጥር ስር መዋላቸዉ ተነግሯል። ከፍተኛ ቁጥር ያላቸዉ ታጣቂዎች የኢትዮጵያን ድንበር ጥሰዉ መግባታቸው ከተሰማ በኋላ እንዲመለሱ ቢደረግም አሁንም በሁለቱ ቀበሌያት እንቅስቃሴ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል።

ከደቡብ ሱዳን የሚሻገሩ ታጣቂዎች በተደጋጋሚ ወደ ኢትዮጵያ ድንበር ዘልቀዉ በመግባት በተለይም የዲማ ወረዳን ከደቡብ ሱዳን ጋር በሚያዋስኑ አካባቢዎች ጥቃቶችን ፣ እገታ እና የእንስሳት ዘረፋ ሲፈጽሙ እንደነበር ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን መዘገቡ ይታወሳል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በራያ አላማጣ ወረዳ ከቅዳሜ ጀምሮ ለቀናት የዘለቀ የተኩስ ልውውጥ መደረጉ ተገለጸ

የአማራ እና ትግራይ ክልሎች ከሚወዛገቡባቸው የራያ አካባቢዎች አንዱ በሆነው ራያ አላማጣ ወረዳ “የህወሓት ኃይሎች በከፈቱት ጥቃት” ከቅዳሜ እስከ ዛሬ የቆየ የተኩስ ልውውጥ መደረጉን የአካባቢው ባለሥልጣናት እና ነዋሪዎች ሲናገሩ፣ የደቡባዊ ትግራይ ዞን በበኩሉ ግጭት የተፈጠረው ታጣቂዎች በትግራይ ሚሊሻዎች ላይ ተኩስ በመክፈታቸው መሆኑን ገልጿል።

ከየካቲት ወር ጀምሮ በተደጋጋሚ የተኩስ ልውውጥ እየተደረገባቸው ካሉት የራያ ወረዳዎች አንዱ በሆነ ራያ አላማጣ የተከስ ልውውጡ በድጋሚ ያገረሸው ባለፈው ቅዳሜ ሚያዝያ 5/2016 ዓ.ም. ከቀኑ አምስት ሰዓት ገደማ ጀምሮ መሆነን የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ ደርበው እና የአላማጣ ከተማ ከንቲባ አቶ ኃይሉ አበራ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

ባለሥልጣናቱ “የህወሓት ኃይሎች” በማለት የሚጠሯቸው ታጣቂዎች፤ ተኩስ የከፈቱት በወረዳው አዲስ ብርሃን (በቀድሞ ስሙ ላዕላይ ድዩ) በተባለ ቀበሌ በኩል መሆኑን ገልጸዋል። ቅዳሜ፤ የነበረው ተኩስ እሁድም ቀጥሎ እንደዋለ እና ዛሬ [ሰኞ] ጠዋትም የተኩስ ልውውጥ ሲደረግ እንደነበር የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ እና አንድ ነዋሪ ተናግረዋል።

በትግራይ ክልል የደቡባዊ ትግራይ ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሆኑት አቶ ሀፍቱ ኪሮስ፤ ቅዳሜ እና እሁድ የፕሪቶሪያ ስምምነት እንዲተገበር የሚጠይቁ የራያ አካባቢ ተፈናቃዮች “ረጅም ርቀት በእግራቸው በመጓዝ” ሰልፍ ማድረጋቸውን አስታውሰዋል። ከመሆኒ እና ከማይጨው ከተሞች በመነሳት የተደረጉት ሰልፎች “የመከላከያ ሠራዊት ኬላ እስከሚገኝባቸው አካባቢዎች” የተደረጉ መሆናቸውን ጠቅሰዋል።

አቶ ሀፍቱ፤ “ድምጻችንን እያሰማን ባለንበት ወቅት ታጣቂዎች፤ ታኦ ከሚባል አካባቢ ተሰባስበው የእኛ ሚሊሻዎች ወዳሉበት አካባቢ [መጥተው] ለተኩስ የተጋበዙበት ሁኔታ ተፈጠረ” ሲሉ በሁለቱ አካላት መካከል ለተደረገው የተኩስ ልውውጥ ምክንያት የሆነውን ክስተት ጠቅሰዋል።

ይህንን ተከትሎ “ግጭቶች” መፈጠራቸውን የሚናገሩት የደቡባዊ ትግራይ ዞን ዋና አስተዳዳሪ፤ “ከእኛ ሚሊሻዎች ጋር ግጭት ተፈጠረ፤ [ከእኛ በኩል የነበሩት] ሚሊሻ እና ፖሊስ ናቸው። ሌላ ምንም ሌላ ዓላማ የነበረው አይደለም” ብለዋል።

የዚህን ተቃራኒ የሚናገሩት የራያ አላማጣ ባለሥልጣናት በበኩላቸው፤ ተኩስ የተከፈተው “አርሚ 24” ከተባለ የህወሓት የሠራዊት ክፍል ውስጥ “ሦስት ክፍለ ጦሮች” በአካባቢው ላይ ተሰማርተው እንደሆነ ገልጸዋል። የአላማጣ ከንቲባ አቶ ኃይሉ በበኩላቸው አካባቢው ላይ የተሰማሩት “አክሱም፣ አልጋነሽ እና ዮሐንስ ክፍለ ጦሮች” መሆናቸውን ተናግረዋል።

የወረዳው ዋና አስተዳዳሪው አቶ ሞላ በበኩላቸው፤ “ሦስት ክፍለ ጦር ይዞ እኛ ላይ ኦፕሬሽን እያደረገ ያለው አርሚ 24 ነው። [አርሚ] 44 እና 24 ነበሩ፤ በታች በኩል ያለው አርሚ 44 በባላ [ወረዳ] በኩል ምንም አልተጠጋም። አርሚ 24 ግን አክሱም ክፍለጦር ከእኛ ሚሊሻ ጋር እየተጋጨ ነው” ብለዋል።

ተኩስ የከፈተው ከባድ መሳሪያዎችን በመጠቀም መሆኑንም ባለሥልጣናቱ ገልፀዋል።

የአላማጣ ከንቲባ አቶ ኃይሉ፤ ታጣቂዎች “ብሬል፣ ዲሽቃ እና ስናይፐር” መጠቀማቸውን የተናገሩ ሲሆን፣ የወረዳው ዋና አስተዳዳሪው አቶ ሞላም “ዲሽቃ” በተባለው የቡድን መሳሪያ ተኩስ መከፈቱን ተናግረዋል። አንድ ነዋሪ በበኩላቸው ዛሬ አራት ሰዓት ገደማ ላይ “የዲሽቃ እና መትረየስ” ተኩስ ድምፅ መስማታቸውን አስረድተዋል።

የደቡባዊ ትግራይ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀፍቱ ግን ይህንን አስተባብለዋል። “ይህ ነገር በሰላማዊ [መንገድ] ይፈታ እያልን ባለንበት ሰዓት፤ ሌላ ኃይል ልንጠቀም የሚያስችለን ምንም ምክንያት የለም” ብለዋል። እንደ ዲሽቃ ያሉት የቡድን መሳሪያዎች ጥቅም ላይ የዋሉት በተቃራኒ ወገን በሚገኙት የአካባቢው ታጣቂዎች መሆኑንም ተናግረዋል።

የራያ አላማጣ ባለሥልጣናት እና ነዋሪዎች፤ ከትግራይ ክልል መጥተዋል የሚሏቸው ታጣቂዎች፤ አዲስ ብርሃን የተባለውን ቀበሌ መቆጣጠራቸውን የተናገሩ ሲሆን፣ በዛሬው ዕለት ደግሞ “ጋርጃሌ” የተባለ አካባቢ መያዙን ጠቅሰዋል።

የራያ አላማጣ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሞላ፤ “መከላከያው ትንኮሳ እንዲፈጠር አልፈለገም፤ ‘እባካችሁ’ እያለ እንደ ልመና ነው የያዘው። እየተጠየቁ ያለው እንደ ግዴታ አይደለም። እነሱ ግን ኃይላቸውን እያጠናከሩ እያስገቡ ነው ያለው። እኛም በተለይ በትናንትናው ዕለት ጋርጃሌ ከተማ ሊይዙብን ስለሆነ የምንችለውን ኃይሉን በሙሉ አሟጠን ብዙ ሞከርን፤ አልተቻለም” ብለዋል።

“አሁን አላማጣ [ከተማ] ሊገቡ ሦስት ኪሎ ሜትር ነው የቀራቸው” ያሉት ዋና አስተዳዳሪው፤ የአካባቢው ሚሊሻ ያለው “ኃይል ባለመመጣጠኑ ምክንያት አፈግፍጎ ተኩስ መቆሙን” ገልፀዋል።

ከቅዳሜ ዕለት ጀምሮ በነበረው የተኩስ ልውውጥ የአንድ ሰው ሕይወቱ ሲያልፍ፤ ቁጥራቸው በውል ያልታወቀ ሰዎች መቁሰላቸውን ባለሥልጣናቱ እና ነዋሪዎች ተናግረዋል። ሕይወቱ ያለፈው ግለሰብ “ሚሊሻ” እንደሆነ አንድ የአካባቢው ነዋሪ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የደቡባዊ ትግራይ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሀፍቱ፤ ቅዳሜ ዕለት “ተከፍቶብናል” ባሉት ተኩስ የተጎዳ ሰው ስለመኖሩ ለቀረበላቸው ጥያቄ “በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙም አስተያየት ባልሰጥ ደስ ይለኛል” የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

የሰሜን ኢትዮጵያው ጦርነት መቀስቀሱን ተከትሎ በአማራ ክልል ስር የገቡት አወዛጋቢ አካባቢዎች ጉዳይ መፍትሔ የሚያገኘው በሕዝበ ውሳኔ እንደሆነ የፌደራል መንግሥት መግለፁ ይታወሳል። ጉዳዩን ለመፍታትም ከፌደራል መንግሥት እንዲሁም ሁለቱ ክልሎች ከፍተኛ አመራሮች ያሉበት ዐቢይ ኮሚቴ ሥራ ላይ መሆኑን የፌደራል መንግሥት አስታውቆ ነበር።

ከሁለት ሳምንት በፊት ጋዜጣዊ መግለጫ የሰጡት የመንግሥት ኮሚዩኒኬሽን ሚኒስትር ዶ/ር ለገሰ ቱሉ፤ “በአማራ አዋሳኝ አካባቢዎች” ላይ “በትግራይ በኩል” የሚታየው “አዝማሚያ”፤ የፕሪቶሪያውን ስምምነት የሚጥስ” እንደሆነ ተናግረው ነበር።

ዶ/ር ለገሰ፤ “ወሰንን በኃይል እናስከብራለን” የሚል አካሄድ “የትግራይ ሕዝብን ለሌላኛው ዙር ስቃይ እና እንግልት የሚዳርግ ነው” ሲሉም በዚህ መግለጫቸው አሳስበው ነበር።

VIA: ቢቢሲ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጳጳሱ በጩቤ ተወጉ🥹

ታዋቂው  የኤሲሪያን  (አሶራውያን) ኦርቶዶክስ ቄስ ብጹዕ አቡነ ማር ማርያም ኢማኑኤል (ቢሾፕ ማር ማሪ) ሲድኒ ውስጥ በዘውትራዊውና የተመለደው ቀጥታ የሚሰራጭ  የስብከት መርሃ ግብራቸው ላይ ሳሉ ማንም ባልገመተው ሁኔታ አንድ ሰው በፍጥነት ተጠግቶ በጩቤ ፊትና አንገታቸው ላይ ወግቷቸዋል።

የጉባኤው አባላት ጳጳሱን ለመርዳት ሲጮሁ እና ሲጣደፉ ይሰማሉ። አንድ ሰው በቁጥጥር ስር መዋሉን የኒው ሳውዝ ዌልስ ፖሊስ አስታወቀ።

በጥቃቱ አራት ሰዎች ቆስለዋል ሲል ኒው ሳውዝ ዌልስ አምቡላንስ ተናግሯል።

ዜናውን በርካታ አለምአቀፍ የመገናኛ አውታሮች ዘግበውታል።

@sheger_press
@sheger_press
ከአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አብን የተሰጠ መግለጫ
***
ከትናንት ታሪካዊ ስህተቱ የማይማረው ህወሐት ለአራተኛ ዙር በህዝባችን ላይ ወረራ ፈፅሟል። የፌዴራልና የአማራ ክልል ክልሉ መንግስታትም በህዝብ ላይ የተቃጣውን የጥፋት ወረራ በአስቸኳይ እንዲያስቆሙ አበክረን እንጠይቃለን!

የኢትዮጵያ ህዝብ ዘላለማዊ ጠላት የሆነው ወያኔ ህወሐት በህዝብ ትግል ተገፍትሮ ወደ ትግራይ ከተሰበሰበ በኋላ በተደጋጋሚ ወረራ በመፈፀም በህዝባችን ላይ ለጆሮ የሚከብድ ዘግናኝ ግፍ ፈፅሟል። ምንም እንኳን ህወሐት በተደጋጋሚ ጊዜ በቆሰቆሰው ጦርነት የአማራ እና የአፋር ህዝብ በቀጥታ የገፈቱ ቀማሽ ይሁኑ እንጅ ዋና ዓላማው ኢትዮጵያ ሐገራችንን መበታተን እና የፈራረሰች ሐገር መፍጠር መሆኑን በአፈ ቀላጤው በኩል በተደጋጋሚ ተናግሯል።

ይህ የእናት ጡት ነካሽ ቡድን የሐገራችን ደጀን የሆነውን የሰሜን እዝ የመከለከያ ሰራዊት በማጥቃቱ ከመላው የኢትዮጵያ ህዝብ ያጋጠመውን ቁጣ መቋቋም ተስኖት ለሶስተኛ ጊዜ እየተመላለሰ ያደረገው የሐገር ማፍረስ ሙከራ ባይሳካለትም እንኳን አድፍጦ ለጦርነት ከመዘጋጀት ግን ቦዝኖ አያውቅም።

ህወሐት ከጦርነት ውጭ መኖር የማይችል፣ በጦርነት አድጎ በጦርነት ያረጀ ቡድን በመሆኑ በመላው የኢትዮጵያ ክልሎች የሚገኙ አማፂያንን ከማስታጠቅ አልፎ ከታሪካዊ ጠላቶቻችን ጋር በመወገን ሐገራችንን የጦር ቀጠና ለማድረግ ያላሰለሰ ጥረት ሲያደርግ ነበር የከረመው። በቀጥታ ከሚደግፋቸው የጥፋት ኃይሎች በተጨማሪ የራሱን ኃይል በማደራጀት የሰርጎ ገብ ኃይል እየላከ ህዝባችንን ሲረብሽ መክረሙ ሳያንሰው በአሁኑ ሰዓት በራያ በኩል ቀጥተኛ የሆነ ጥቃት በህዝባችን ላይ ለአራተኛ ጊዜ ወረራ ከፍቶ ይገኛል።

ኋላ ቀርነት እና ግትርናት ዋና መገለጫው የሆነው የጥፋት ቡድን የሚሊዮኖችን ህይዎት በቀጠፈውና ከተደጋጋሚ ስህተቱ ባለመማር ዛሬም ለሌላ ዙር እልቂት ተዘጋጅቶ በህዝባችን ላይ ጦርነት ከፍቷል።

በህዝቦች እኩልነት እና በብሔረሰቦች መብት ፈፅሞ የማያምነው ህወሐት እኔ የማልገዛት ኢትዮጵያ ተረጋግታ መኖር የለባትም የሚል ያልተገራ ክፉ አመሉን በተደጋጋሚ አሳይቷል። በዚህም እንደ ሌሎች ኢትዮጵያዊያን እኩልነትን ፈፅሞ እንደማይሻ አረጋግጧል።

ለህዝባችን የሚከተሉትን መልዕክቶች እናስተላልፋለን

1. ምንም እንኳን አሸባሪው እና ተስፋፊው ወያኔ የሁሉም ኢትዮጵያውያን ጠላት ቢሆንም ፣ በተለይ የአማራ ህዝብ የቡድኑ ወረራ ቀጥተኛ ሰለባ እና ገፈት ቀማሽ በመሆኑ ጦርነቱን የመመከት ኃላፊነት ያለበት መሆኑ ይታወቃል፡፡ በመሆኑም በሁሉም አካባቢዎች የሚገኘው ሕዝባችን ካለፈው የጥፋት ግዜ በመማር ከታሪካዊ ጠላቱ የሚሰነዘርበትን ወረራ ከኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት ጋር በመቀናጀት እንዲመክት፣

2. ህዝባችን ከወያኔ ትጥቅ አስፈች ፕሮፖጋንዳ ራሱን እንዲጠብቅ እና ከዚህ ታሪካዊ ጠላት የሚመጣን ማንኛውንም ውዥንብር ጆሮ እንዳይሰጥ፣ ከዚህ ጋር በተያያዘ አንዳንድ የወገን ኃይሎች ለወያኔ የሚያሳዩትን የተለሳለሰ የባንዳነት መንገድ ህዝባችን ፈፅሞ እንዳያዳምጥ እና እንዲህ ያሉትን ቡድኖች አጥብቆ እንዲታገል፣

3. የአማራ እና የአፋር ህዝብ የጦርነቱ ዋና ገፈት ቀማሽ በመሆኑ የኢትዮጵያ ኃይሎች የሚፈልጉትን ሁሉ በማቅረብ ከሐገሩ ጎን እንዲቆም

4. ህዝባችን ይህን ታሪካዊ ጠላት በመቅጣት የተለመደ ጀግንነቱን እንዲወጣ ስንል ጥሪ እያቀረብን፤ በተለይ መንግስት በህዝባችን ላይ ለአራተኛ ጊዜ እየተፈጸመ የሚገኘውን ወረራ በዝምታ የሚመለከት ከሆነ፤ ህዝባችን ስርአትን አምኖ ችግሮች ሁሉ በህግ አግባብ ይፈታሉ የሚል ቀናኢነቱ ማታለያ ሆኖ ከዋለ፤ ይህ በራያ ብቻ የማይቆም ይልቁንም የሁሉ ነገር መፍረሻና ማፍረሻ እንዲሆን መንግስት የፈቀደ መሆኑን ታሪክ የሚመዘግበው ሀቅ ይሆናል።

5. በህወሐት ችግር የአማራና የትግራይ ህዝቦች እንዲሁም መላ ሀገሪቱና ቀጠናው ችግር ውስጥ እየወደቀ በመሆኑ ይህ በአስቸኳይ እንዲቆም እያሳሰብን በተለይ የፌዴራሉ መንግስትና የአማራ ክልል መንግስት በህዝባችን ላይ እየተፈጸመ የሚገኘውን ወረራ በአስቸኳይ እንዲያስቆሙ አበክረን እንጠይቃለን!

ሚያዝያ 07/2016 ዓ.ም አዲስ አበባ/ኢትዮጵያ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጌታቸው ረዳ‼️

የሕወሃት ኃይሎች በራያ አላማጣ አንዳንድ ቦታዎችን መቆጣጠራቸውን ተከትሎ ፤ የፕሪቶሪያዉ ስምምነት ጠላቶች ያደረጉት እንጂ በሕወሃት አልያም ጊዜያዊ መስተዳድሩ የተፈጸመ አለመሆኑን አቶ ጌታቸዉ ረዳ ተናገሩ

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ርዕሰ መስተዳድር ጌታቸው ረዳ ፣ በደቡብ ትግራይና በሌሎች በኃይል የተያዙ የትግራይ ግዛቶች ባኹኑ ወቅት የተፈጠረው ክስተት በፌደራል መንግሥቱ እና በትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ወይም በሕወሃት ወይንም በትግራይ እና በአማራ ክልሎች መካከል የተፈጠረ ግጭት አይደለም ሲሉ ትናንት እኩለ ሌሊት ላይ በኤክስ ትስስር ገጻቸው ላይ መለጠፋቸውን ዳጉ ጆርናል ተመልክቷል።

ጌታቸው፣ ክስተቱ ኹለቱ ወገኖች የፕሪቶሪያውን ስምምነት ተግባራዊ ለማድረግ እያደረጉት ያለውን አወንታዊ ግንኙነት ለማደናቀፍ የፈለጉ የስምምነቱ ጠላት የኾኑ ኃይሎች የፈጠሩት ነው በማለት ከሰዋል።

ከሩቅም ከቅርብም የግጭት ማቆም ስምምነቱ ጸር የኾኑ ኃይሎች ጦር እየሰበቁ መኾኑን የጠቀሱት ጌታቸው፣ ብቸኛው አዋጭ መንገድ ግን ሰላም ነው ብለዋል።

ኹለቱ ወገኖች ችግሮችን ለመፍታትና የሚስማሙባቸውን ጉዳዮች ለማጎልበት አዲስ አበባ ውስጥ ስብሰባ ላይ እንደኾኑም ጌታቸው ጠቁመዋል።

ሕወሃት ጥቃት ከፍቶ ተቆጣጥሯቸዋል የተባሉት አካባቢዎችን በተመለከተም አብን ማምሻውን ጠንከር ያለ መግለጫ አሰራጭቷል።

አብን የሕወሃት ኃይሎች በድጋሚ በአማራ ሕዝብ ላይ "አራተኛ ዙር" ጥቃት ከፍተዋል ሲል ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ ከሷል። የፌዴራሉ መንግሥትና የአማራ ክልላዊ መንግሥት ሕወሃት በአማራ ሕዝብ ላይ የከፈተውን ሌላ ዙር ጥቃት ባስቸኳይ እንዲያስቆሙ የጠየቀው አብን፣ የአማራ ሕዝብ ከመከላከያ ሠራዊት ጋር በመቀናጀት የሕወሃትን ጥቃት እንዲመክትም ጥሪ አድርጓል።

አብን፣ መንግሥት የሕወሃትን ጥቃት በዝምታ ከተመለከተ፣ ድርጊቱ "የኹሉ ነገር መፍረሻና ማፍረሻ" እንዲኾን ፈቅዷል ማለት ነው ብሏል።

አብን ይህን መግለጫ ያወጣው፣ የሕወሃት ኃይሎች በራያ አላማጣ አካባቢ አንዳንድ ቦታዎችን እየተቆጣጠሩ ስለመኾኑ በተሰማ ማግስት ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሕዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ በመጣስ ለአራተኛ ዙር ሕዝባችን ላይ ወረራ ፈፅሟል-የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት

ከትናንት ታሪካዊ ስህተቱ መማር የተሳነው ሕዝባዊ ወያኔ ሀርነት ትግራይ (ህወሓት) የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ በመጣስ ለአራተኛ ዙር ሕዝባችን ላይ ወረራ ፈፅሟል፡፡

ጀንበር ጠልቃ በወጣች ቁጥር ከጦርነት ውጭ ማሰብ የማይችለው የህወሓት ቡድን ከዉጭ እና ከዉስጥ ጠላቶቻችን ጋር ተናብቦና ተቀናጅቶ በርካሽ ፖለቲካዊ ብያኔና ፍረጃ በጊዜያዊ አሥተዳደሩ ካቢኔ አማካኝነት መጋቢት 16/2016 ዓ.ም የአማራ ክልል ተማሪዎችን መማሪያ መጽሐፍ እንደ ሰበብ ተጠቅሞ በይፋ ጦርነት ማወጁና መቀስቀሱ ይታወቃል፡፡

ይሁን እንጂ ይህን የመላ ኢትዮጵያ ጠላትና የደኅንነት ስጋት የሆነውን የህወሓት ቡድን ባለፉት ሦስት ዙሮች ከተደረገው ደም አፋሳሽ ጦርነት ትምህርት ሊወስድ ይችል ይሆናል በሚል ጭላንጭል ተስፋ  የፌዴራል መንግሥት እጅግ እልህ አስጨራሽ ትዕግስት ተላብሶ ውይይቶች እንዲካሄዱ ተደጋጋሚ ጥረት ሲያደረግ ቆይቷል፡፡

የአማራ ክልል መንግሥትም በተደጋጋሚ ከትግራይ ጊዜያዊ አሥተዳደር ጋር በፌዴራል መንግሥት አማካኝነት ውይይት ለማድረግ በርካታ ሙከራዎች የተደረጉ ቢሆንም ህወሓት ይህን የሰላም አማራጭ ወደ ጎን በመተው የማንነት ጥያቄ ያለባቸውን የራያ አላማጣ፣ ራያ ባላ፣ ኦፍላ፣ ኮረምና ዛታ አካባቢዎች ላይ ወረራ ፈፅሟል፡፡

ህወሓት ወረራ የፈፀመባቸው የራያ አላማጣ፣ ራያ ባላ፣ ኦፍላ፣ ኮረምና ዛታ እንዲሁም የወልቃይት ጠገዴ እና ጠለምት አካባቢዎች የሀገሪቱ ሕገ መንግሥት ከመፅደቁ በፊት በነበሩ አሥተዳደራዊ መዋቅርና አደረጃጀት በኀይል ጠቅልሎ ከመውሰድ ጀምሮ የዘር ማጥፋት ወንጀል እስከመፈጸም ድረስ አሰቃቂ ጥፋት የፈጸመባቸው አካባቢዎች  ናቸው፡፡ እነዚህ አካባቢዎች ስቃይ በተሞላበት ችግር ውስጥም ኾነው በወቅቱ ለነበረው መንግሥት የማንነትና ራስን በራስ የማሥተዳደር ጥያቄዎችን በማንሳት፣ መብቶቻቸው እንዲከበሩላቸው ሲጠይቁ የነበሩ መኾኑ በበርካታ ታሪካዊ ማስረጃዎች የተረጋገጥ ጉዳይ ነው፡፡

ተቸንካሪነት ዋና መለያ የኾነው የህወሓት የጥፋት ቡድን ጥቅምት 24/2013 ዓ.ም በሀገር መከላከያ ሠራዊት ላይ የፈጸመውን አሰቃቂና ታሪክ ምንጊዜም የማይዘነጋው የባንዳነት ተግባር ተከትሎ በተቀሰቀሰው ጦርነት በመላ ኢትዮጵያዊያን እና በጀግኖች የፀጥታ ኀይሎች አማካኝነት የሽንፈት ፅዋን ከመጎንጨቱ ባሻገር የማንነትና የራስ አሥተዳደር ጥያቄ ያለባቸውን አካባቢዎች በጉልበት ተገፎባቸው የነበረውን ራሳቸውን የማሥተዳደር ነጻነት መቀዳጀት ችለዋል፡፡

ይሁን እንጂ ይህ ኹኔታ ያልተመቸው ተቸንካሪው የህወሓት ቡድን በሦስት ዙሮች ከተደረገው ጦርነት ማግሥት የፕሪቶሪያውን ስምምነት በማክበር በሀገራችን ዘላቂ ሰላም እንዲሰፍን የድርሻውን ከመወጣት ይልቅ ስምምነቱን ሙሉ በሙሉ በመጣስ የተለያዩ ጥፋቶችን ሲፈጽም ቆይቷል፡፡አሁንም እየፈጸመ ይገኛል፡፡

ስለሆነም የአማራ ክልል መንግሥት ይህን መሰሉን የህወሓትና የግብረ አበሮቹን ፖለቲካዊ ግልሙትና እና ደም አፋሳሽ ጦርነት ለማድረግ ከመሞከር እንዲታቀብና የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሙሉ በሙሉ በማክበር በአጭር ጊዜ በወረራ የያዛቸውን አካባቢዎች ለቆ እንዲወጣ እየጠየቅን ይህ የማይኾን ከኾነ የአማራ ክልል መንግሥትና ሕዝብ ከሌሎቹ ወንድምና እህት ኢትዮጵያዊያን ጋር በጋራ በመኾን ሀገርን ከማፍረስ መታደግና ሕዝባችንንም ከጥቃት ለመከላከል የምንገደድ መኾኑን ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

የተከበራችሁ በክልላችን በየደረጃው ያላችሁ የፖለቲካና የጸጥታ መዋቅር አባላት፡- ከሰሜን ዕዝ ጥቃት በኋላ ትህነግ በቀሰቀሰው ጦርነት ሕዝባችን ቀጥተኛ ተጠቂ በመኾኑ ምክንያት ለበርካታ ችግሮች ተዳርጎ የነበረ መኾኑ ይታወቃል፡፡ ኾኖም ግን በየደረጃው የሚገኙ የመዋቅር አባላት ከጀግናው የሀገር መከላከያ ሠራዊት፣ ጥምር የጸጥታ ኃይሎችና ከሌሎች ኢትዮጵያዊያን ጋር በመኾን ሀገር አፍራሽ የጥፋት ኀይሉ ላይ የተቀዳጀው ድል ታሪክ አይዘነጋውም፡፡ ዛሬም እንደ ትናንቱ በፅናትና በቁርጠኝነት ሕዝቡን በማደራጀት አካባቢያችሁን በመጠበቅ ታሪካዊ ኀላፊነታችሁን እንድትወጡ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን፡፡

የተከበርከው የክልላችን ሕዝብ፡- በተደጋጋሚ ጥቃት የፈጸመብህ የጥፋት ኀይል ዛሬም እንደ ትናንቱ ወረራ ፈጽሟል፡፡ በመኾኑም መላ የክልላችን ሕዝብ ከሐሰት ፕሮፓጋንዳ እና ሠርጎ ገቦች ራስህን በመጠበቅ ከክልል መንግሥትና በየአካባቢው ከሚገኙ አሥተዳደሮች ጋር የጠበቀ ቁርኝት በመፍጠር ጠላቶቻችን የከፈቱብንን ጥቃት ለመመከት  በሚደረገው ጥረት ውስጥ ከመንግሥት ጎን በመሰለፍ የድርሻህን እንድትወጣ የከበረ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

ለኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መንግሥት፡- የፌደራል መንግሥት ህወሓት የቀሰቀሰው ደም አፋሳሽ ጦርነት በሰላም እንዲቋጭ ማድረጉን ሳናደንቅ አናልፍም፡፡ ከፕሪቶሪያው ስምምነት በኋላም ጥያቄዎች በሰላማዊ መንገድ እንዲፈቱ የተደረገውን ጥረት በሙሉ ልብ በመደገፍ ለውጤታማነቱ የድርሻችንን ስንወጣ ቆይተናል፡፡ ኾኖም ግን ህወሓት በተደጋጋሚ የተሰጠውን ዕድል ባለመጠቀም የፕሪቶሪያውን ስምምነት ሲያፈርስ ቆይቷል፡፡ አሁንም በሙሉ አቅሙ ወደ ጦርነት ገብቷል፡፡ ይህን እኩይ ድርጊቱን የአፍሪካ ኅብረትና የዓለም አቀፍ ታዛቢዎች በቦታው ተገኝተው አረጋግጠዋል፡፡በመኾኑም ይህን እብሪተኛ ቡድን በአጭር ጊዜ ከወረራቸው አካባቢዎች ለቆ እንዲወጣ በማድረግ ሕዝባችንን ከጥፋት መታደግና የሀገራችንን ሉዓላዊነት ማስከበር ይገባል፡፡

ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ
ህወሓት ከምስረታዉ ጀምሮ ለአማራ ሕዝብ ባለው ሥር የሰደደ ጥላቻ  ምክንያት በአማራ ሕዝብና በመላ ሀገሪቱ ሕዝብ ላይ የማያባራ ደም አፋሳሽ ጦርነትን ሲቀሰቅስ ኖሯል፡፡ ለዚህም ነው ህወሓት የኢትዮጵያም ኾነ የአፍሪካ ቀንድ አለመረጋጋት ምንጭ ነው የምንለው፡፡

ኾኖም በአሳሳች የፕሮፖጋንዳ ሥራዎቹ ምክንያት የዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ በተደጋጋሚ በህወሓት ጉዳይ ላይ የተሳሳተ አቋም ሲይዝ ተስተውሏል፡፡ ዛሬ ግን ለዚህ አሳሳች ፕሮፖጋንዳው ያልተመቼ ኹኔታ ተፈጥሯል፡፡ በጠራራ ጸሐይ የአፍሪካ ሕብረትና ዓለም አቀፍ ታዛቢዎች በተገኙበት ወቅት ወረራ መፈጸሙ በገሃድ ታይቷል፡፡

በመሆኑም ከዚህ ቀደም እንዳደረገው በአሁኑ ወቅት የዓለም አቀፉን ማኅበረሰብ ማወናበድ አይችልም፡፡ የአማራ ክልል መንግሥትና ሕዝብ የዓለም አቀፍ ማኅበረሰቡ ህወሓት የፈጸመብንን ወረራ በጥብቅ እንዲያወግዝና ከጎናችን እንዲቆም የከበረ ጥሪያችንን እናቀርባለን፡፡

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት
ሚያዚያ 08 /2016 ዓም
ባሕር ዳር

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሊቅ አዕላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን መጠኑ ከፍተኛ የኾነ ገንዘብ ወደ ግል ሒሳባቸው ሊያስገቡ ሲሞክሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ ተባለ

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተ ክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ የኾኑት ሊቅ አዕላፍ ቀሲስ በላይ መኮንን በጸጥታ አካላት ቁጥጥር ስር መዋላቸውን ዋዜማ ከታማኝ ምንጮች ሰምታለች።

ምክትል ሥራ አስኪያጁ ትላንት ማክሰኞ ሚያዚያ 9 ቀን በጸጥታ ኃይሎች ቁጥጥር ሥር የዋሉት፣ አፍሪካ ኅብረት ዋና መስሪያ ቤት አካባቢ በሚገኝ የንግድ ባንክ ቅርንጫፍ መጠኑ ከፍተኛ የኾነ ገንዘብ ወደ ግል ሒሳባቸው ሊያስገቡ ሲሉ መሆኑን ምንጮች ለዋዜማ መናገራቸውን ሸገር ፕረስ ከዋዜማ ከዘገባ ተመልክቷል።

ሊቀ አዕላፍ በላይ በቁጥጥር ስር ከዋሉ በኋላ ልደታ ወደሚገኘው አምስተኛ ፖሊስ ጣቢያ መወሰዳቸውን ዋዜማ ከምንጮቿ ተረድታለች።

ሊቀ አዕላፍ በላይ ከዓመታት በፊት ከቤተክርስቲያኗ ቅዱስ ሲኖዶስ ጋር ልዩነት ከፈጠሩ በኋላ፣ በእርቅ ወደ ቤተክህነት ተመልሰው የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ምክትል ሥራ አስኪያጅ ኾነው እንደተሾሙ ይታወሳል።

Via ዋዜማ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በጉራጌ ዞን እዣ ወረዳ በደረሰው የመኪና አደጋ የ6 ወጣቶች ህይወት አለፈ ።

አደጋ የደረሰው በእዣ ወረዳ ወርት ቀበሌ እንጨት ጭኖ ወደ ከተማ በመጓዝ ላይ የነበረው ሲኖ የጭነት ተሽከርካሪ በደረሰበት የመገልበጥ አደጋ ከራሱ ጋር በሲኖው ላይ በስራ ላይ የነበሩ የ6ወጣቶች ህይወት ሲያልፍ በ10 ሰዎች ላይ ቀላልና ከባድ ጉዳት መድረሱን ከወረዳው ፖሊስ ፅ/ቤት ያገኘነው መረጃ መረዳት ችለናል ።

ጉዳት የደረሰባቸውም ሰዎች በሆስፒታል ህክምና እየተደረገላቸውም ይገኛል።

የእዣ ወረዳ መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ፅ/ቤ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የፍልስጤም እግር ኳስ ማህበር በጋዛ ወረራ የተነሳ ፊፋ እስራኤልን እንዲያገል ጠየቀ

   👉 የፍልስጤም የተባበሩት መንግስታት ሙሉ አባልነት ጥያቄ ላይ አርብ እለት ድምጽ ይሰጣል


የፍልስጤም እግር ኳስ ማህበር (ፒ ኤፍ ኤ) ለዓለም እግር ኳስ አስተዳዳሪ አካል ፊፋ ባቀረበው ጥያቄ መሰረት በእስራኤል እግር ኳስ ማህበር ውስጥ ያሉ ባለስልጣናት "በጋዛ ውስጥ ለተፈጸመው የዘር ማጥፋት ከፍተኛ ድጋፍ እንደሚሰጡ የሚያመለክቱ" የማህበራዊ ሚዲያ ጽሁፎችን አጋርቷል፡፡

"በጋዛ ውስጥ ያሉት ሁሉም የእግር ኳስ መሠረተ ልማቶች ወድመዋል ወይም በከባድ ሁኔታ ተጎድተዋል፣ በእስራኤል ወረራ ወደ ማጎሪያ ካምፕ የተቀየረውን የአል-ያርሙክን ታሪካዊ ስታዲየም ጨምሮ ከአንድ በላይ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ጉፋትን በሰነድ በማስደገፉ ማቅረቡን" የፍልስጤም እግር ኳስ ማህበር  ተናግሯል።

የእስራኤል እግር ኳስ ማህበር በሊጋው ውስጥ የሚደርሰውን አድልዎ እና ዘረኝነት ላይ እርምጃ መውሰድ አልቻለም፣ይህም የፊፋ ህግጋትን አንቀጽ 3 በቀጥታ የሚጥስ ነው ሲል አክሏል።ከኢየሩሳሌም የመጣ አንድ የእስራኤል ቡድን “እስራኤል ውስጥ እጅግ ዘረኛ ቡድን እንዴት እንደሆነ በኩራት ይዘምራል። ለተቃዋሚ ቡድኖች በሚጫወቱት አረቦች ላይ እንደ ‘አሸባሪ’ ያሉ ፅሁፎችን ያሰማሉ” ሲል የፍልስጤም እግር ኳስ ማህበር ተናግሯል።

በሌላ በኩል የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ቤጂንግ ፍልስጤም የተባበሩት መንግስታት ሙሉ አባል እንድትሆን ትደግፋለች ሲሉ ተደምጠዋል።ዋንግ ከኢንዶኔዥያ አቻቸው ጋር በጃካርታ ያደረጉትን ቆይታ ተከትሎ ለመገናኛ ብዙሃን በሰጡት መግለጫ ለፍልስጤም የተባበሩት መንግስታት ድርጅት አባልነት እንደሚደግፉ አስታውቀዋል ሲል በቻይና መንግስት የሚደገፈው ዲጂታል የዜና ማሰራጫ ዘ ፔፐር ዘግቧል።

ዋንግ በተጨማሪም እስራኤል በጋዛ ላይ ያካሄደችው ጦርነት ሰብአዊ አደጋ ፈጥሯል እና "ምንም ቅድመ ሁኔታ የሌለው የተኩስ አቁም" በአስቸኳይ ተግባራዊ መሆን አለበት ማለታቸዉን የዜና ማሰራጫው ዘግቧል።የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት አርብ  እለት የፍልስጤም የተባበሩት መንግስታት ሙሉ አባልነት ጥያቄ ላይ ድምጽ ይሰጣል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ይህ እርምጃ ዩዩናይትድ ስቴትስ የእስራኤል ጠንካራ አጋርነትን  ሊያግደው ይችላል ተብሎ ይጠበቃል ።
#ኢትዮጵያ

ከሰሞኑን በማህበራዊ ሚዲያዎች አንድ አባት  በጎረምሶች ተከበው ሲመቱ ፣ ሲሰደቡ ፣ ሲዘለፉ ፣ ሲዋከቡ በቪድዮ ታይቷል።

ይህን እጅግ አሳፋሪና በምን አይነት ሁኔታ ላይ እንዳለን ሚያሳይ ቪዲዮ ያጋሩት ደግሞ እራሳቸው የድርጊቱ ፈጻሚዎች ናቸው።

ድርጊቱ ብዙዎችን ክፉኛ አስቆጥቷል። በርካቶች ስለ ነገ በማሳብ ፍርሃት ውስጥ ከቷቸዋል።

በእርግጥ በሀገራችን ያላየነው ግፍ ፣ ያልሰማነው ክፉ ተግባርና ጭካኔ ምን አለ ? እንዘርዝር ብንልስ ቦታው፣ ጊዜው  ይበቃናል ? በፍጹም !

ከዚህ በፊትም እንደምንለው በቪዲዮዎች ተቀርጾ የምናየው ምናልባትእድለኞች ሆነን ከብዙ አንዱ እንጂ ስንት ያላየነው ይኖራል።

ወደ ቪድዮው ስንመለስ ተከበው ሲመቱ፣ ሲዋከቡ ፣ ሲዘለፉ የነበሩት አባት ' እንጀራ ፍለጋ እግር ጥሏቸው እንደመጡ ' ይገልጻሉ የሚጠይቀን የለም ባዮች ጎረምሶች ' እዚህ አካባቢ ምን ትሰራለህ ? ለምን እዚህ መጣህ ? ከመጣህበት ቦታስ እንጀራ የለም ? ' ሲሉ እጅግ በንቀት ያዋክቧቸዋል።

ይህን ተግባራቸውን እንደ በጎ ስራ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ አጋርተውታል።

የትኛውም ዜጋ በገዛ ሀገሩ የመንቀሳቀስ መብት አለው ? ካልሆነ ስለምን #ኢትዮጵያዊ ይባላል ? ጥፋት ካለበት ፣ ከተጠረጠረ የሚጠይቀው ህግ እንጂ የሰፈር ጎረምሳ አይደለም። ግለሰቦቹ ጥርጣሬ አለን ካሉ ህግን ማሳወቅ እንጂ ማነው ፤ የትኛው ህግ ነው ይህንን መብት የሰጣቸው ? 

ይህ ተግባር በተለይ ማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተነዛ ያለው የጥላቻ ስብከት ምን ያህል ስር እንደሰደደ እንደሆነ ፍንትው አድርጎ የሚያሳይ ሲሆን ነገን እጅግ አስፈሪ ያደርገዋል።

ግልጽ የሆነ የብሄርና የግለሰቦች ጥላቻ ፣ ልብም አእምሮም በጥላቻ መሞላት፣ አይንም በጥላቻ መታወር ፦
- ሌላው ይቅር ታላላቆቻችን እንዳናከብር
- ለእምነታችን ፣ ለሃይማኖታችን ቦታ እንዳይኖረን
- ለሰው ልጅ ትንሽ እንኳን ቦታ እንዳንሰጥ
- ለህግ እና ስርዓት ቅንጣት ታክል ደንታ እንዳይኖረን
- ባህል፣ ወግ ፣ አብሮነት ለሚባለው ጉዳይ ቦታ እንደሌለን
- ነገ እኔስ ምን ይገጥመኛል ? ምን እሆን ይሆን ? በህይወት አጋጣሚ የት እሄዳለሁ ፣ ምን አካባቢ እገኛለሁ የሚለውን ለማገናዘብ እንኳን እንዳንችል ያደርገናል።

ሰዎች ወደው ሳይሆን በስርዓት፣ በግለሰቦች፣ በአንቂዎች ፣ በሚዲያዎች... አማካኝነት ነው ጥላቻ እንዲውጣቸው እና ማገናዘብ ፣ ቆም ብሎ ማሰብ የሚባለውን መሰረታዊ ነገር እንዲያጡት የሚሆነው።

ሰዎች ከመሰል ድርጊታቸው እንዲታቀቡ አብሮነት ፣ ፍቅር ፣ መግባባት፣ መከባበር ፣ ህግ ፣ ስርዓት፣ ወንድማማችንነትን ከማስተማር ባለፈ በህግ ማረም ፣ ነገ መዘዙ የከፋ እየሆነ ስለሚሄድ ከወዲሁ እንዲገታ በአንድ ላይ ማውገዝ ፣ ተበዳይን መካስ ፣ እውነት ህግ የበላይ ነው የምንል ከሆነም ለራሳችን ስንል ህግን ሁሌም ማስከበር ነው።

ዛሬ ላይ እንዲህ ያሉና ከዚህ ቀደምም በየሀገሪቱ ክፍሎች የሰማናቸው ፍጹም አደገኛ የሚባሉ ጉዳዮች የሳምንት አጀንዳ እየሆኑ እያለፉ ይመስለን ይሆናል ግን በእርግጠኝነት መዘዛቸው የከፋ ሊሆን ይችላል።

ውጤታቸው ዛሬ ሳይሆን ውሎ አድሮ ምናልባትም አመታትን አልፎ ይታይ ይሆናል ስለሆነም እናስብበት ! ትውልዱን ከስህተቱ እናርመው ፤ ወገኑን እንዲጠላ ሳይሆን እንዲወድ ፣ እንዲያከብር እናስተምረው።

በሁሉም ዘንድ አውቀናል ታውቀናል ፣ ዛሬ ስልጣን አለን፣ ሚዲያውም የኛው ነው የምንል ሰዎችም ' አይ የኔ ወገን ስለሆነ ፍጹም ጻዲቅ ነው ፣ አይሳሳትም ፣ ጀግና ነው ፣ ቢሳሳትም ምንም ችግር የለውም እኔ እከላከልለታለሁ ' ከሚል አደገኛ እና ብዙ መዘዘ ካለው አመለካከት መራቅ ይገባናል።

#Tikvah

@ethio_mereja_news
በጃኔቫ ፤ በመንግስት ላይ የተቃዉሞ ድምጽ ያሰሙ ሰዎችን የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ጽሕፈት ቤት አወገዘ

በጃኔቫ የኢትዮጵያ ቋሚ መልዕክተኛ ጽሕፈት ቤት፣ ማክሰኞ'ለት ለኢትዮጵያዊያን ተረጂዎች ገንዘብ ለማሰባሰብ ጄኔቫ ውስጥ በተካሄደው ዓለማቀፍ መርሃ ግብር ላይ የተወሰኑ ኢትዮጵያዊያን ተቃውሞና ጩኸት ማሰማታቸውን አውግዟል።

አራቱ ትዉልደ ኢትዮጵያዊያን ሰዎች በጉባኤው ተገኝተዉ በኢትዮጵያ እየደረሱ ናቸዉ ያሏቸዉን ጉዳዮች በመጥቀስ በጭኸት ስብሰባውን አዉከዉ እንደነበር ሸገር መዘገቡ አይዘነጋም።

ፖሊስ ጩኸት ያሰሙትን ኢትዮጵያዊያን ይዞ ከአካባቢው እንዳራቃቸው ጽሕፈት ቤቱ ገልጧል። ጽሕፈት ቤቱ፣ ለድርቅ ተጎጂዎች ዓለማቀፉ ኅብረተሰብ እርዳታ በሚያሰባስብበት መድረክ ላይ ጩኸት ማሰማት፣ የአገር ጠላትነት ፖለቲካ እንጂ የተቃውሞ ፖለቲካ አይደለም በማለት ተችቷል።

የኢትዮጵያዊያን ዲያስፖራ ማኅበረሰብ፣ ባልተገባ ቦታ ጩኸት በማሰማት "አገር አዋራጅ" የኾነ ድርጊት የሚፈጽሙ ግለሰቦችን ሊቃወማቸው እንደሚገባም ጽሕፈት ቤቱ አሳስቧል።

ቋሚ መልዕክተኛ ጽሕፈት ቤቱ፣ በአገር ክብር ላይ እጃቸውን የሚዘረጉ ግለሰቦችን በሕግ አግባባብ የምጠይቅበትን አሠራር እከተላለሁ በማለትም አስጠንቅቋል።

Via ዋዜማ
@ethio_mereja_news
ብልፅግና ፓርቲ ‘የሚዲያ ሠራዊት’ አቋቁሞ በሚቃወሙት እና በሚተቹት ላይ ስም ማጥፋት ዘመቻ እንደሚያካሂድ ተገለጸ‼️

በገዢው ብልፅግና ፓርቲ ‘የሚዲያ ሠራዊት’ የሚል መጠሪያ ያላቸው የፓርቲው አባላት፤ መንግሥትን በሚተቹ እና በሚቃወሙ ግለሰቦች ላይ በፌስቡክ በተደረጉ የሐሰተኛ መረጃ እንዲሁም ‘የጥላቻ ንግግር’ ተብለው ሊቆጠሩ የሚችሉ ጽሑፎች እና ምስሎች ሥርጭት ላይ እንደተሳተፉ ቢቢሲ ባደረገው ምርመራ ማረጋገጡን አስታወቀ።

#የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ ዋና ፀሐፊ አቡነ ጴጥሮስ ከአዲስ አበባ ወደ አሜሪካ መጓዛቸውን ተከትሎ በወቅቱ የተሰራጩ መረጃዎችን ቢቢሲ በማሳያነት አቅርቧል።

በቤተክርስቲያኗ እና በገዢው ፓርቲ መካከል የተፈጠረውን ቅራኔ ተከትሎ “ሰበር መረጃ፤ አቡነ ጴጥሮስ ከሀገር ኮበለሉ”፣ “አሜሪካዊው አቡነ ጴጥሮስ ከሀገር ኮብልለዋል!” እና “ከአሜሪካዊ አቡነ ጴጥሮስ ኩብለላ ጀርባ ያሉ እውነታዎች!” የሚል መግቢያ ያላቸው መረጃዎች በወቅቱ ተሰራጭተው እንደነበር አውስቷል።

“ለምንድነው ላይክ፣ ሼር የማታደርጉት?” የሚል ጥያቄ ለተሳታፊዎቹ እንደሚያቀርብ፤ የሚዲያ ሠራዊት አባላት ላክይ፣ ኮሜንት እና ሼር ማድረጋቸውን የሚያሳይ “ስክሪን ሻት” እንዲልኩ እንደሚጠየቁ ቢቢሲ በግሩፑ የተደረጉ የመልዕክት ልውውጦችን ዋቢ በማድረግ አስታውቋል።

መንግስትን የሚቃወሙ ጽሁፎችን ባጋሩ የፌስቡክ ገጾች ላይ ‘የሚዲያ ሠራዊቱ’ አባላት ተዘጋጅቶ የተሰጣቸውን ጽሁፎች ኮሜንት እንደሚያደርጉ አረጋግጫለሁ ብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
🛒ታላቅ ቅናሺ ከሸገር ገበያ📣

✔️m13 Samsung 📱
✔️4ram
✔️64Gb

        ዋጋ 13200

እዚህ ላይ ያናግሩን 👇👇
                  @ethio_sellerr

አዲስአበባ ያሉበት እናደርሳለን 🛵🚵
ክፍለሀገር በፖስታ ይደርሷታል።📩📮
የቻይና ከተሞች እየሰመጡ ነው❗️

ከቻይና ዋና ዋና ከተሞች ግማሽ ያህሉ ላይ የመስመጥ አደጋ መጋረጡ ተሰምቷል።  በበሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በተለይ የባህር ከፍታ ሲጨምር ለጎርፍ አደጋ እየተጋለጡ ነው ሲል በአገር አቀፍ ደረጃ የወጣው የሳተላይት መረጃ  አመልክቷል። በሳይንስ ጆርናል የታተመው ይኸው ጥናት 45 በመቶው የቻይና የከተማ መሬት በአመት ከ3 ሚሊ ሜትር በላይ በፍጥነት እየሰመጠ ነው ያለ ሲሆን 16 በመቶው ደግሞ በዓመት ከ10 ሚሊ ሜትር በላይ መስመጡን ገልጿል።  በከተሞቹ የሚገኙ በርካታ ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች  ምክንያት መሆናቸውን ሮይተርስ በዘገባው አመልክቷል።

@ethio_mereja_news
ተቀጥተዋል😁

በቤጂንግ ግማሽ ማራቶን ከስፖርት ጨዋነት ባፈነገጠ መልኩ ቻይናዊውን አትሌት ሆን ብለው እንዲያሸንፍ አድርገዋል የተባሉ የኬንያ እና የኢትዮጵያ አትሌቶች ያገኙት ሜዳሊያና የገንዘብ ሽልማት ተነጥቀዋል።

ባልተገባ መንገድ ውድድሩን እንዲያሸንፍ የተደረገው ቻይናዊ አትሌትም ሽልማቱን ተነጥቋል።

ኬንያውያኑ አትሌቶች ዊሊ ምናንጋት እና ሮበርት ኬተር እንዲሁም ኢትዮጵያዊው ደጀኔ ሃይሉ ቢቂላ ማሸነፊያው መስመር ላይ ሆን ብለው ቻይናዊው እንዲያሸንፍ ፍጥነታቸውን ሲገቱ እንደነበር መታየታቸው ተገልጿል፡፡

ባለፈው እሁድ በተካሄደው የግማሽ ማራቶን ሩጫ ውድድር ላይ የተፈፀመውን ያልተገባ ድርጊት የተመለከተው የውድድሩ አዘጋጅ ኮሚቴ ጉዳዩን እየመረመረ መቆየቱን ገልጿል፡፡

ኬንያዊው ምናንጋት መጀመሪያ ላይ የእስያ ጨዋታዎች ሻምፒዮናን እንዲያሸንፍ ያደረገው ጓደኛው በመሆኑ ነው ቢልም፤ ነገር ግን በኋላ ላይ ለማሯሯጥ እንደተቀጠረ ተናግሯል።

ይህንንም ተከትሎ የቤጂንግ ግማሽ ማራቶን ውድድር አዘጋጁ የአሸናፊውን ሂ ጄ እና የሦስቱን አትሌቶች ሜዳሊያና የገንዘብ ሽልማት መንጠቁን ሳውዝ ቻይና ሞርኒንግ ፖስት ዘግቧል፡፡

Via:- FBC

@ethio_mereja_news
2024/09/28 23:19:27
Back to Top
HTML Embed Code: