Telegram Web Link
በሳዑዲ አረቢያ ከሚኖሩ 7መቶሺህ ኢትዮጵያዊያን መካከል 4መቶ50ሺዎቹ መደበኛ ያልሆኑ ናቸዉ ተባለ፡፡

ከ2017 እስከ 2023 ባለዉ ጊዜ ዉስጥ ከ5መቶ61ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸዉ መመለሳቸዉም ተገልጿል፡፡

93ሺህ 5መቶ የሚሆኑ ዜጎች በ2022 በግዴታ ወደ አገራቸዉ ተመልሰዋል ነዉ የተባለዉ፡፡

በ2023 ደግሞ 43ሺህ የሚሆኑ ዜጎች በግዴታ ወደ አገራቸዉ መመለሳቸዉን ዘ ፍሪደም ፈንድ የተባለ ግብረሰናይ ድርጅት አስታዉቋል፡፡

የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ፤1መቶ33 ሺህ የሚሆኑ ዜጎች ከሳዑዲ መመለሳቸዉን የገለጸ ሲሆን፤ 46 የሚሆኑት ከባድ ጉዳት የደረሰባቸዉ ነበሩ ብሏል፡፡

ህጻናትን እና የአዕምሮ ህሙማንን ጨምሮ 6ሺህ ኢትዮጵያዊያንም ወደ አገራቸዉ ተመልሰዋል ሲል ሚኒስቴሩ አስታዉቋል፡፡

ከሱዳን ከጦርነቱ መቀስቀስ በኋላ ወደ 47ሺህ 8መቶ ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል ያለዉ ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ ከየመን ከ4ሺህ በላይ ዜጎቻችን ተመልሰዋል ብሏል፡፡

በሁለት ዙር በተደረገ ስራ 2መቶ80ሺህ ዜጎች ወደ አገር መመለሳቸዉንም ሰምተናል፡፡

@Sheger_press
@Sheger_press
ኢትዮ መረጃ - NEWS
Photo
#ሠላሳ፣ ስልሳ፣ መቶም ያማረ ፍሬ ይስጣችሁ


ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ መስጠትን ከዘር ጋር አነጻጽሮ በምሳሌ ያስተምራል፡፡

ዘር በእጅ የያዙትን ይበዛልኛል፣ ስለ አንዷ ሰላሳ፣ ስልሳ፣ መቶም ያማረ ፍሬ አፈራለሁ ብሎ በእምንት በእርሻ ቦታ መበተንን ይጠይቃል፡፡

መስጠትም ይህን ይመስላል፡፡ በእጅ ያለውን በልግስና አሳልፎ ሰጥቶ ከእግዚአብሔር ሰፊ በረከት አገኛለሁ ብሎ በእምነት መስጠት፡፡

ይህን ቅዱስ ቃል አምናችሁ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ በለሳ ወረዳ ለሚገኘውና ከዘጠና በላይ ገዳማውያን መነኮሳት ላሉበት ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አድነት ገዳም ያደረጋችሁት በአይነት የእህል ልገሳ በዚህ መልኩ ተጭኖ ለገዳሙ ተልኳል፡፡


“በጥቂት የሚዘራ በጥቂት ያጭዳል፤ በበረከትም የሚዘራ ደግሞ በበረከት ያጭዳል፤ እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ፥ በኀዘን ወይም በግድ አይደለም።” (2ኛ ቆሮ 9፥7) እንዲል፤ ስለ መስጠትና መቀበል በሰፊው አስተምሮበታል፡፡

የዘራ እንደሚሰበስብ፣ የሰጠም ዋጋውን አያጣምና የተዘራባት ምድር የዘሩባት አብዝታ እንደምትሰጥ፣ በልግስና የሰጣችኋቸው ገዳማውያን በጸሎታቸው ትልቅ ዋጋ፣ በሚያልፍ ስጦታ የማያልፍ በረከት፤ በሚያልቅ ልግስና የማያልቅ ዋጋ ያስገኛሉና፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ምጽዋትን በዘር መስሎታል፡፡


እኛም እንላለን፣ ስለሰጣችሁት እያንዷንዷ ቅንጣት የእህል ዘር ስለአንዱ ፋንታ ሰላሳ፣ ስልሳ፣ መቶም ያማረ ፍሬ ይስጥልን፡፡ በወጣ አብዝቶ ይተካ፡፡ በዚህ አጋጣሚ የተሰራው ከታቀደው አንጻር ገና ብዙ ይቀረዋልና ገዳማውያኑን በዚህ መልኩ በአይነት ማለትም ቀለብ በመስፈር፣ የግንባታ እቃዎች ጠጠር፣ አሸዋ፣ ሲሚንቶ፣ ብረት በልባችሁ እንዳሰባችሁ በመስጠት መደገፍ የምትፈልጉ ካላችሁ በደስታ እንቀበላለን፡፡ በገንዘብ ድጋፍ ለምታደርጉም የገዳሙ አካውንት ከታች ተቀምጧልና የቻላችሁትን እንድታደርጉ ገዳማዊያኑ እየተጣሩ ነው።



ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ኤርትራ ገቡ፡፡

የሶማሊያ ዝሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃመድ ዛሬ ታህሳስ 16/ 2017 ከሰዓት በኋላ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አስመራ መግባታቸውን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አስታወቀዋል።

ፕሬዝዳንቱና ልዑካን ቡድናቸው አስመራ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል ሲሉ የማስታወቂያ ሚንስትሩ የማነ ገ/መስቀል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል።

ሁለቱ መሪዎች የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን እንዲሁም የጋራ ጠቀሜታ ያላቸውን ቀጠናዊ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች የበለጠ ማጠናከርን በተመለከተ ይወያያሉ ተብሏል።

በመስከረም ወር መገባደጃ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሃሰን ሼክ ሞሃመድ፣ የግብጹ ፕሬዝዳንት አብደል ፈታ አልሲሲ እና የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈውርቂ ጋር በኤርትራ ባደረጉት የሶስትዮች ጉባኤ ሶማሊያ የየብስ እና የባህር ድንበሮቿን ለመጠበቅ የሚስያችል አቅሟን ለማጠናከር ስምምነት አድርገዋል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት እየተካሄደ ባለው ጦርነት ሳቢያ አንድ የአብነት መምህርን ጨምሮ ከ 599 በላይ ኦርቶዶክሳውያን እንደተገደሉ እና ከ 780 በላይ የአብነት ደቀ መዛሙርት መበተናቸው ሀገረ ስብከቱ የ 43ኛው መደበኛ ሰበካ ጉባኤ ባካሄደበት ዕለት በገለጸው ሪፖርት አሳውቋል።

በዕለቱ በእነማይ ወረዳ ከ 103 በላይ ምእመናን ሞት እና በጉባኤ ቤት ደቀ መዛሙርት ከፍተኛ የሆነ መቀዛቀዝ መፈጠሩና በደባይ ጥላት ወረዳ በ 7 አጥቢያ የሚማሩ ከ 300 በላይ ደቀ መዛሙርት መበተናቸውንና በተጨማሪም በባሶ ሊበን ወረዳ አንድ የአብነት መምህርና 395 ምእመናን ሲገደሉ በአነደድ ወረዳ ከ 250 በላይ ደቀ መዛሙርት ከጉባኤ ቤት ውጭ መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡
በደብረ ኤልያስ የቅኔና የመጻሕፍት ትምህርት ቤት ከ 230 በላይ ደቀ መዛሙርት ሲበተኑ በሸበል ወረዳ ከ 100 በላይ ምእመናን መሞታቸው በሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው የተገለጸ ሲሆን በሀገረ ስብከቱ ጠቅላላ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በሀገረ ስብከቱ ፈተና ስለሆነው የዶግማና የቀኖና ጥሰት ጉዳይ ፣ ስለ ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ፈተናዎችና መፍትሔዎቻቸው ፣ሰበካ ጉባኤ ስለማጠናከርና አብነት ት/ቤቶች ስለማጠናከር ውይይት በማድረግ በትናትናው ዕለት ማጠናቀቁ ተገልጿል።

ዘገባው የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ነው።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ኢንጅነር ጌቱ ገረመው ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት፣ አትሌት መሰረት ደፋርን ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ።

28ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን ፕሬዚዳንት እንዲሁም ፌዴሬሽኑን ለቀጣይ አራት ዓመታት የሚመሩትን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት መምረጡ የሚታወስ ነው።

በጉባኤው የተመረጠው አዲሱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ  ዛሬ የመጀመሪያውን ሰብሰባውን በፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት አድርጓል ።

በኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን የሚመራው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የስራ ክፍፍል ያደረገ ሲሆን ኢንጅነር ጌቱ ገረመው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት እንዲሁም አትሌት መሰረት ደፋር የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት በማድረግ መርጧል ።

ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው  ጨምሮም የተለያየ የስራ ክፍፍል ያደረገ ሲሆን :-

👉ወይዘሮ አበባ ዮሴፍ አቃቤ ንዋይና የአስተዳደር ፋይናንስ ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ

👉አቶ ቢኒያም ምሩፅ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የኮሚኒኬሽን ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ

👉ወይዘሮ ሳራ ሀሰን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የሃብት አሰባሰብ ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ

👉አቶ አድማሱ ሳጂ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የጥናትና ምርምር ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ

👉ዶክተር ትዕዛዙ ሞሴ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የስነምግባርና ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

👉ዶክተር ኢፍራህ መሀመድ  የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የህክምናና ፀረ አበረታች ቅመሞች ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ

👉አትሌት በላይነሽ ኦልጂራ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል

👉አትሌት የማነ ፀጋይ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል በማድረግ  ስብሰባውን አጠናቀዋል ።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
ጥቆማ‼️

በሀገራችን እዉቅ ጋዜጠኞች የተመሰረተና የመረጃ አነፍናፊና አዲሱ tikvah የተባለለት የቴሌግራም ቻናል እናስተዋዉቃችሁ

እውነተኛ መረጃ ከፈለጋቹ በፍጥነት ይህን ቻናል መቀላቀል ይኖርባችኋል።

በዚ LINK ግቡ👇
👇👇👇
https://www.tg-me.com/+gPveFwjiiXdiMDE0
https://www.tg-me.com/+gPveFwjiiXdiMDE0
የምዕመናን ጫማዎችን ሰርቆ ከቤተክርስቲያን ቅጥር ግቢ ሲወጣ የተያዘዉ ተከሳሽ በ18 ዓመት ፅኑ እስራት ተቀጣ

በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ጉራጌ ዞን ሙህር አክሊል ወረዳ ቤተ-ክርስቲያን ውስጥ ዘልቆ በመግባት የምእመናን ጫማዎች የሰረቀው ግለሰብ በ18 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ መወሰኑ ተገለጸ።

ተከሳሽ ደምሴ ደሳለኝ በእስራት ሊቀጣ የቻለዉ በጉራጌ ዞን በሞህር አክሊል ወረዳ ህዳር 20 ቀን 2017 ዓ.ም በግምቱ ከሌሊቱ 7፡00 ሰዓት ግድም በሀዋርያት ከተማ ወንጀል ለመፈፀም እንድያመቸው የተወሰኑ የማብራት ቆጣሪዎችን ካጠፋ በኋላ ሀዋርያት ፅርሀ ፅዮን የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ውስጥ ዘልቆ በመግባት ለህዳር 21 ቀን 2017 ዓ.ም ለክብረ በዓል መጥተው ቤተ-መቅደስ ገረንገር ላይ ጫማቸው አውልቀው ቤተመቅደስ የገቡ የ9(ዘጠኝ ) ሰዎች ጫማ በለበሰው ጃኬት ሸክፎ ሲወጣ በክትትል በመፈፀሙ ከባድ የስርቆት ወንጀል በተመሰረተበት ክስ ነዉ።

ተከሳሹ የወንጀል ሪከርድ ያለበት መሆኑንና ፍርድ ቤት ቀርቦም የእምነት ክህደት ቃሉ እንዲሰጥ ተጠይቆ ክሱን እንደማይቃወም ወንጀሉን መፈፀሙ አምኖ በዝርዝር ያስረዳ በመሆኑና በሰጠዉ የእምነት ቃል መሰረት ፍርድ ቤቱ በተከሳሹ ላይ የጥፋተኝነት ብይን ሰጥቷል።

የሞህር አክሊል ወረዳ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት ታህሳስ 15 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለዉ የወንጀል ችሎት ተከሳሽ ደምሴ ደሳለኝን በ18 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ የተወሰነበት መሆኑ ከምሁር አክሊል ወረዳ ፍትህ ጽ/ቤት የተገኘዉ መረጃ ያመላክታል።

Via: መናኸሪያ ሬዲዮ
#NewAlert

አንጋፋው የሰብዓዊ መብት ተሟጋች የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ጉባኤ (ኢሰመጉ) በመንግስት መታገዱን ዋዜማ ሰምታለች።

የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅቶች ባለሥልጣን ኢሰመጉን ያገደው፣ ከተቋቋመለት ዓላማ ውጭ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ ያደርጋል በማለት ነው።

የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች በአመራሮቹና ሠራተኞቹ ላይ ማስፈራሪያና ዛቻ እንደሚፈጽሙ ለበርካታ ወራት ሲገልጽ የቆየው ኢሰመጉ፣ ዋና ዳይሬክተሩ ዳን ይርጋ በዚኹ ዛቻና ማስፈራሪያ ሳቢያ ከአገር ለመሰደድ እንደተገደዱ በቅርቡ መግለጡ ይታወሳል።

ባለሥልጣኑ በዲሞክራሲና መብቶች ዕድገት ማዕከል እና ጠበቆች ለሰብዓዊ መብቶች በተሰኙት ሲቪል ማኅበራት ላይ ባለፈው ኅዳር ወር በተመሳሳይ ምክንያት ጥሎት የነበረውን እገዳ ካነሳ በኋላ፣ ድርጅቶች የተሰጧቸውን የማስተካከያ ርምጃዎቾ ተግባራዊ አላደረጉም፤ ይልቁንም የቀድሞ ጥፋታቸውን ቀጥለውበታል በማለት በቅርቡ በድጋሚ እንዳገዳቸው አይዘነጋም። [ዋዜማ]

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
መፍትሄ ያላገኘው የሂጃብ ጉዳይ‼️

በትግራይ ክልል የአክሱም ከተማ ሙስሊም ተማሪዎች በሂጃባቸው ምክንያት ትምህርት አቋርጠው ያለመፍትሔ መቀመጣቸውን ገልጸዋል።

"እኛ ከትምህርት ቤቶቹ ዩኒፎርም ጋር የሚመሳሰል ሀይማኖታችን በሚያዘው መሰረት ሂጃብ ለብሰን ትምህርታችንን እንማር ብለን ነው የጠየቅነው የሚሉት ተማሪዎቹ ነገር ግን ፀጉራቹሁ ካልታየ መማር አትችሉም ተብለን ከትምህርት ገበታ ተፈናቅለናል" ብለዋል።

የ12ኛ ክፍለ ዩኒቨርስቲ መግቢያ ፈተና ለመውሰድ ፎርም የሚሞላበት የመጨረሻ ቀን ነገ ረቡዕ እንደሆነ የገለፁት ተማሪዎች "ሂጃብ ካላወለቃችሁ" በመባሉ ምክንያት አንድም ሙስሊም ተማሪ ፎርሙን አለመሙላቱን ተናግረዋል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊ ጉዞ ወደ ቅዱስ ላሊበላ!

በነፍሳችን ዲያብሎስ ፣ በስጋችን ቄሳር እንዳይነግስ፣ ያለወንድ ዘር በረቂቅ ሚስጥር ከብጽዕት ማርያም የተወለደውን ወልድ እግዚአብሔርን ኑ በምስጋና እናንግሰው።

ንጉሧን ያላወቀች እስራኤል ከምድር ያሳደደችው ፣ በመስቀል ሆኖ "ንጉሥ" የተባለ ፣ በመላእክት የተበሰረ ዜና ልደቱን፣ በያሬዳዊ ዝማሬ በታሪካዊው ቅዱስ ላሊበላ በማክበር በረከተ ነፍስ በረከተ ስጋን እናትርፍ።

ለአረጋውያን ፣  ለነፍሰጡር ፣ ለህፃናት እና ለአካል ጉዳተኞች በጤና ባለሙያዎች ልዩ እንክባቤ እንሰጣለን። ስለማረፊያዎ አያስቡ፤ያሉን ቦታዎች ውስን ናቸውና ፈጥነው በመመዝገብ ቦታ ይያዙ።

የጉዞ መነሻ ቀን:- 24/04/17

የጉዞ መመለሻ ቀን:- 02/05/17

የጉዞ ዋጋ:- ምግብን ፣ ማረፊያን ፣ መስተንግዶን እና አስጎብኚን ጨምሮ :-6,500

ለበለጠ መረጃ:-0938944444

አዘጋጅ:- ማኀበረ ቁስቋም
አሐዱ ራዲዮና ቴሌቭዥን የፖለቲከኛው ጀዋር መሐመድ ቃለመጠይቅ ላለማስተላለፍ መወሰኑን የጣቢያው የቅርብ ምንጮች ገልፀዋል።

አሐዱ ቃለመጠይቁን በኬንያ ናይሮቢ ተገኝቶ ከሰራ በኋላ እንደሚያስተላልፍም ማስታወቂያ ማስነገሩን አስታውሶ ሆኖም
አቶ ጀዋር ለቢቢሲ አማርኛ ተመሳሳይ ቃለመጠይቅ በመስጠቱ ምክንያት ለዚህ ውሳኔ እንዳበቃው ተጠቁሟል።

ከጣቢያው በጉዳዩ ላይ ይፋዊ ማብራሪያ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው አልተሳካም።

አቶ ጀዋር መሐመድ ከሰዓታት በፊት ምንጮችና ራዊ ድረገፁ ባሰፈረው ሐተታ ቃለመጠይቁ ሳይከለከል እንዳልቀረ በመጥቀስ ቃለመጠይቁን በአማራጭ ሚድያ ለመልቀቅ እንደሚገደድ ፅፏል።
ባለፉት አምስት ወራት 380 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰቡን የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የገቢዎች ሚኒስትር ዓይናለም ንጉሴ ገለፁ።

ሚኒስትሯ ባለፉት የለውጥ አመታት የገቢ አሰባሰብ አፈጻጸምን በተመለከተ በሰጡት ማብራሪያ፤ በሀገር ደረጃ የተያዙ የልማት ዕቅዶችን ተግባራዊ ለማድረግ ዋነኛ አቅም ተደርጎ የሚወሰደው የሀገር ውስጥ ገቢን ማሻሻልና ማሳደግ ነው ብለዋል።

ይህም የህዝብ የልማት ፍላጎትን ደረጃ በደረጃ የሚመልሱ መሰረተ ልማቶችን መገንባት እንደሚያስችልም ገልጸው።

እንደ ሀገር የኢኮኖሚ ማሻሻያውን ሊደግፍ የሚችል እና አስተማማኝ የፋይናንስ ምንጭ እንዲኖር የገቢ አሰባሰብ ሂደት ላይ በትኩረት እየተሰራ ነው ብለዋል።

ባለፉት የለውጥ ዓመታት የኢትዮጵያን የብልፅግና ጉዞ ሊደግፍ የሚችል የሀገር ውስጥ የፋይናንስ አቅም መገንባቱንም አረጋግጠዋል።

@Sheger_press
@Sheger_press
ጥንቃቄ‼️

ዛሬ ማለትም ታህሳስ 17 /2017 ዓ.ም ጀምሮ ብዙ የቴሌግራም አካውንቶች ከላይ በተጠቀሰው የማስገሪያ (phishing link) እና ሌሎች ተጨማሪ ማስገሪያዎች አማካኝነት መረጃዎች እየተመዘበሩ ስለሆነ ከማንኛውም የቴሌግራም ተጠቃሚ (ከምታውቁት እና ከማታውቁት ) ግለሰብ ሊንክ ቢላክላችሁ መክፈት እንደሌለባችሁ እና ወዲያውኑ እንድታጠፉት ይመከራል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
በፕሮፌሺናል ጋዜጠኞች ተከፍቶ መረጃዎችን ተከታትሎ በሚዛናዊነት የሚያቀርብ ቻናል ልጠቁማችሁ ፡፡

ተማመኑበት ታተርፉበታላችሁ ተቀላቀሉት
👇👇👇
https://www.tg-me.com/+gPveFwjiiXdiMDE0
https://www.tg-me.com/+gPveFwjiiXdiMDE0
2024/12/26 18:40:10
Back to Top
HTML Embed Code: