Telegram Web Link
የኦሮሚያ ክልል የምክክር ተሳታፊዎች፣ አዲስ አበባ፣ ሐረርና ሞያሌ ከተሞች በኦሮሚያ ክልል ሥር እንዲተዳደሩ ለአገራዊ ምክክር ኮሚሽን አጀንዳ ማቅረባቸውን ከተሳታፊዎቹ መስማቱን ጠቅሶ ሪፖርተር ዘግቧል።

አዲስ አበባ በሕገመንግሥቱ መሠረት በፌደራል መንግሥቱ ሥር የምትተዳደር ሲኾን፣ ሐረር ደሞ የሐረሬ ክልል ዋና ከተማ ናት።

ባንጻሩ በሱማሌና ኦሮሚያ ክልሎች መካከል ለዓመታት የግጭት ማዕከል የነበረችው ሞያሌ፣ ባኹኑ ወቅት ከኹለት ተከፍላ የኹለቱም ክልሎች ባንዲራዎች እንደሚውለበለቡባት ይታወቃል።

የክልሉ የምክክር ተሳታፊዎቹ፣ በክልሎች የወሰን አከላለል፣ ኦሮምኛን የፌደራል የሥራ ቋንቋ በማድረግና ኹሉንም ብሄረሰቦች የሚያግባባ ብሔራዊ ሰንደቅ ዓላማ እንዲኖር በማድረግ ዙሪያ አጀንዳዎችን ማቅረባቸውንም መናገራቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

ባንጻሩ፣ በሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 39 የተቀመጠው የመገንጠል መብት ባለበት እንዲቀጥል ተሳታፊዎቹ አጀንዳ አቅርበዋል ተብሏል።(wazema)

@Sheger_press
@Sheger_press
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ሃድያ ዞን ጊቤ ወረዳ በሚገኙ 12 ቀበሌዎች ካለፈው ዓመት ጀምሮ በመንግሥት ሥር እየተዳደሩ እንዳልኾነ ዋዜማ ከነዋሪዎች ሰምታለች።

መንግሥት በ12ቱ ቀበሌዎች የ2016 በጀት ዓመት ግብር አለመሰብሰቡንና የፖሊስ መዋቅሩ መደበኛ የጸጥታ ማስከበር ሥራውን እንደማያከናውን ዋዜማ ተረድታለች። በቀበሌዎቹ የመንግሥት መዋቅር የፈረሰው፣ ማኅበረሰቡ መንግሥት የወረዳ ጥያቄችን አልተቀበለም በማለት ተቃውሞ ማሰማቱን ተከትሎ እንደኾነ ታውቋል።

በቀበሌዎቹ ውስጥ የሚገኙ መምህራንና የጤና ባለሙያዎች ከደሞዝ ጋር በተያያዘ ያነሱት ጥያቄ ምላሽ ባለማግኘቱ፣ ትምህርት ቤቶች ተዘግተው ነበር፤ የጤና ጣቢያዎች አገልግሎትም ተስተጓጉሎ ነበር ተብሏል።

ከአንድ ወር በፊት ከፌደራል ተቋማት ወደ አካባቢው ለሥራ ተጉዘው የነበሩ ሠራተኞችን የአካባቢው ማኅበረሰብ አስሯቸው እንደነበርም ዋዜማ ተምታለች።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
Online ተጨማሪ ገቢ ለማግኘት ምን ልስራ ብላቹ ብትጠይቁ በጣም ብዙ ምርጫዎች አሉ።

ትርፋማ ሊያደርገኝ የሚችለው የትኛው Skill ነው?
የት ሄጄ ልማረው እችላለው?
በአጭር ጊዜስ ወደ ስራ ለመግባት እና ገንዘብ ለመስራት ምንድን ነው ማድረግ ያለብኝ?

እነዚህን ጥያቄዎቻቹን ለመመለስ የፊታችን ታህሳስ 16, 18 እና 20 ነጻ Online Webinar አዘጋጅቼላቹሃለው!

በዚህ Webinar የራሴን ልምድ እንዲሁም በዙሪያየ ያሉ ስኬታማ ሰዎችን ልምድ አምጥቼ እያንዳንዱን ነገር ብትንትን እያደረግን እንመለከታለን

ለመሳተፍ ከእናንተ የሚጠበቀው ኢንቴርኔት እና ስልክ ወይም ላፕቶብ በቂ ነው።
ታህሳስ 16, 18 እና 20, ከምሽቱ 2፡00ሰዓት
በሰሜን ሸዋ ዞን በሴቶችና ህፃናት ላይ ጥቃት ፈፃሚዎችን ከእድር የማባረርና የቀብር ስነ ስርዓት እንዳይከናውንላቸው ተፅዕኖ የመፍጠር ስራ ተጀመረ

በሰሜን ሸዋ ዞን 31 ወረዳዎች ዉስጥ 9 የከተማ  አስተዳደሮች ይገኛሉ።በዞኑ በሴቶችና ህፃናት ላይ የሚደርሰዉ ጥቃት ካለዉ የሰላም እጦት ጋር ተያይዞ ካለፉት አመታት ጋር ሲነፃፀር ቁጥሩ እንደጨመረ ተገልጿል።

በ2016 ዓ.ም 64 ሴቶችና ህፃናት ለፆታዊ ጥቃት ተጋላጭ የሆኑ ሲሆን ከዚህ ዉስጥም 23ቱ ህፃናት ናቸው ።በጥቃቱ ላይ ተሳታፊ የነበሩ ከ31 በላይ ግለሰቦች በህግ ቁጥጥር ስር ይገኛሉ። ጥቃቱን ለመከላከል ከበጎ አድራጎትና መንግስታዊ ድርጅቶች ጋር ጎጂ ልማዳዊ ድርጊቶችን አስወጋጅ ኮሚቴ በማቋቋም በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን የዞኑ ሴቶችና ህፃናት ማህበራዊ ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወ/ሮ የሮምነሽ ጋሻዉጠና ከብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ጋር በነበራቸዉ ቆይታ ገልፀዋል ።

በቅንጅት ከሚሰራባቸዉ ስራዎች መካከል ዋነኛዉ ግንዛቤ የማስጨበጥ ስራ ሲሆን በሚፈጠረው ግንዛቤ ልክ ግን ጥቃቱን ማስቆም አለመቻሉ ተገልጿል ። ዞኑ ከፖሊስና ፍርድ ቤቶች ጋር በመቀናጀት የምክር ፣የስነ ልቦናና የህክምና አገልግሎት እየሰጠ ሲሆን እንደ ዞን ደብረብርሀን ከተማ ላይ ለሁለቱ ዞኖች የሚያገለግል የሴቶች ማገገሚያ ወይም ማረፊያ ተገንብቷል።

በማገገሚያዉ ዉስጥ ከህክምና እና ስነልቦናዊ ድጋፍ በተጨማሪ ተጠቂዎቹ ለሶስት ወራት የተለያዩ ስልጠናዎችን በመዉሰድ ወደ መደበኛ ህይወታቸዉ እንዲመለሱ ይሰራል።በእምነት ተቋማትና በዕድር ቦታዎችም ላይ ስለጥቃቱ በተሻለ መልኩ ትምህርቶች የሚሰጡ ሲሆን ጥቃቱን የፈፀመ ከእድር እንደሚባረርና የቀብር ስርዓት እንደማይከናወንለት ተፅዕኖ የመፍጠር ስራ ከህግ ጎን ለጎን በስፋት እየተሰራበት ይገኛል።

አሁን ላይ ከፖሊስ ፣ፍርድቤትና ከሚመለከታቸዉ አካላት ጋር የምክክር ሰነድን በመፈራረም ወደ ስራ መግባታቸዉን በቀጣይም በደንብ ወደታች ወርዶ ለመስራት የተቀናጀ ዕቅድ መኖሩን ገልፀዋል ። ስለ ፆታዊ ጥቃት የተለያዩ ስልጠናዎችን የሚሰጡ ድርጅቶች ዞኑ ላይ አስፈላጊ በመሆናቸዉ ፍላጎት ያላቸዉን ድርጅቶች አጋርነት እንደሚሹ ወ/ሮ የሮምነሽ ጨምረዉ ለጣቢያችን ገልጸዋል ።

@Sheger_press
@Sheger_press
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የበርካታ ገዳማት ባለቤት ነች፡፡

በፈቃደ እግዚአብሔር ከ5ተኛው መቶ ክፍለ ዘመን ጀምሮ በመላው ሀገሪቱ እየተስፋፉና እያደጉ የመጡት እነዚሁ ገዳማት የምናኔና የጸሎት እንዲሁም ድኀነተ ሥጋ ወነፍስ የሚገኝባቸው ቦታዎች ናቸው፡፡

ለቤተ ክርስቲያናችን ዘርፈ ብዙ አገልግሎት ከመስጠት ጎን ለጎን የሊቃውንት መፍለቂያና የበርካታ ቅዱሳን ምንጭ በመሆንም ሲያገለግሉ እንደኖሩ ይታወቃል፡፡


በሀገሪቱ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማኀበራዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ አዎንታዊ ተፅዕኖ ከመፍጠራቸውም በላይ የሀገሪቱ የትምህርትና የሥልጣኔ ማእከላት በመሆን አገልግለዋል ፡፡ ገዳማት የቤተክርስቲያን ስውር ጓዳዎችና የሚስጥር መዝገቦች ናቸው ፤ ገዳማት የመማፀኛ ከተማ ናቸው ፤ ገዳማውያን ለእግዚአብሄር የሚቀርቡ አስራት በኩራት ናቸው ።

ይህ በዚህ እንዳለ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ገዳማት በተለያዩ አዝማናት በሀገሪቱና በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ በደረሱ ውጪያዊና ውስጣዊ የጥፋት ዘመቻዎች ቀጥተኛ ተጠቂዎችም ነበሩ፡፡

ተፈጥሮአዊ በሆኑ ችግሮችም እንደየአካባቢው መልክአ ምድራዊ አቀማመጥ ተጋላጭ ሆነው ኖረዋል፡፡ አጽራረ ቤተ ክርስቲያንም በየጊዜው በተለያየ ስልት የገዳማውያኑን አኗኗር፣ ሥርዓትና ትውፊት ለመበረዝ ሲንቀሳቀሱና ገዳማቱን ሲዋጉ እንደኖሩ ግልጽ ነው፡፡

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ በለሳ ወረዳ የሚገኘው ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም ከዘጠና በላይ ገዳማውያን መነኮሳት ያሉበት ልዩ ስፍራ ነው፡፡ ከዓለት መሀል በመነኮሳት ፀሎት ብቻ በሚቆረጥ የማር እምነትና ድውያንን የሚፈውስ ድንቅ ጸበል ያለበት፤ ስለ ዓለምና ስለ ሀገራችን ሌት ተቀን የሚጸልዩበት ቅዱስ ስፍራ ነው፡፡


በተደጋጋሚ ባደረግነው ጥሪ መሠረትም የዘረጋችሁት እጃችሁ ድንቅ ነገር ሰርቷል፡፡ የእናት ገዳማውያን መኖሪያ ባማረና በዘመነ ሁኔታ ተሰርቶ፣ የሶላር ኃይል ተገጥሞለት ጭምር ተጠናቋል፡፡ ለዚህም ባወጣችሁት አብዝቶ ይተካ፣ በዘረጋችሁት እጅ ማለቂያ የሌለው በረከት ያሳፍሳችሁ ለማለት እንወዳለን ፤ አመስጋኝ ልብ የአንድ አማኝ ቀዳሚ መለያ ባህሪ ነውና በመልዓኩ በቅዱስ ሚካኤል ስም ከልብ እናመሰግናለን ፡፡


አሁን እየተሰሩ ካሉ ስራዎች አኳያ ገዳሙ የሚያስፈልገውን ያህል ባይሆንም " ጋን በጠጠር ይደገፋል " እንዲሉ የተቻለውን አገልግሎት ለመስጠት ጥረት ሲደረግ ቆይቷል  አሁንም ይህ ልግስናችሁ ተጠናክሮ ይቀጥል፡፡ አንድ ትልቅ ምዕራፍ ብንጓዝም ለመስራት ከታሰበው ግማሽ ያህል እንኳ አልተጠናቀቀምና ገዳማውያኑ ልገሳችሁን ይሻሉ፡፡ ከላይ እንዳልነው ገዳማውያን ለእግዚአብሄር የሚቀርቡ አስራት በኩራት ናቸውና አሁንም ከጎናቸው በመቆም አለን እንበላቸው ፡፡  


ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
በቱርክ በደረሰ ፍንዳታ የ12 ሰዎች ሕይወት አለፈ

በሰሜን-ምዕራብ ቱርክ ባሊኬሲር ከተማ በአንድ የጦር መሣሪያ እና ፈንጂ ፋብሪካ ውስጥ በደረሰ ፍንዳታ የ12 ሰዎች ሕይወት ሲያልፍ በአራት ሰዎች ላይ ጉዳት ደረሰ፡፡

የአዳጋው መንስዔ አለመታወቁን እና ተጨማሪ አደጋ እንዳይከሰት ሁኔታውን መቆጣጠር መቻሉን የቱርክ የሀገር ውስጥ ጉዳይ ሚኒስትር አሊ ዬርሊካያ ተናግረዋል፡፡

አደጋውን ተከትሎ የእሳት አደጋ ቡድንን ጨምሮ የደኅንነት እና የጤና ባለሙያዎች ወደ ስፍራው ማምራታቸውን የገለጹት ደግሞ የባሊኬሲር ከተማ ከንቲባ ኢስማኤል ኡስታኦግሉ ናቸው፡፡

የአደጋውን መንስዔ ለማወቅ ተጨማሪ ምርመራዎች እየተደረጉ ነው ማታቸውን ጠቅሶ ቢቢሲ ዘግቧል፡፡

ፍንዳታው ባስከተለው የእሳት ቃጠሎም የፋብሪካው ግማሽ ክፍል መውደሙን ከተንቀሳቃሽ ምስሎች ለማየት ተችሏል፡፡
ይህንን ያውቁ ኖሯል?

በፈስ መፍሳት መሀል ጥቅሙ በጥቂቱ

የደም ግፊትን መቀነስ ፣ የኩላሊት ጥንካሬን ማሻሻል እና የእርጅና ምልክቶችን መቀነስ ከጥቅሞቹ መሀል ይካተታሉ።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የስራ አመራር ቦርድ ለአምስት የዩኒቨርሲቲው ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ መስጠቱን አስታውቋል፡፡

በዚህም መሰረት፡-
1. ዶ/ር አለማየሁ ተ/ማሪያም……. በስፔሻል ኒድስ ኤጁኬሽን
2. ዶ/ር አስራት ወርቁ ……………. በጂኦቴክኒክስ ኢንጂነሪንግ
3. ዶ/ር መኮንን እሸቴ ……………. በፕላስቲክ ሰርጀሪ
4. ዶ/ር ሚርጊሳ ካባ ……………… በፐብሊክ ሄልዝ
5. ዶ/ር ተባረክ ልካ ………………. በዴቨሎፕመንት ጂኦግራፊ የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ አግኝተዋል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
አንድ የዓለም ባንክ ባለሙያና አንድ የባንኩ አማካሪ፣ ባንኩና ዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት ባለፈው ሐምሌ ያዘጋጁት የዕዳ ዘላቂነት የትንተና ሰነድ ችግሮች እንዳሉበት በጽሁፍ መግለጣቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

የዕዳ ትንተና ሰነዱ አገሪቱ የአጭር ጊዜ እና የረጅም ጊዜ ዕዳዎችን የመክፈል ችግሮች እንደገጠሟት የሚያብራራ ሲኾን፣ ኹለቱ ባለሙያዎች ግን የአገሪቱ ችግር በዋነኛነት የአጭር ጊዜ ብድር የመክፈል አቅም ውስንነት ብቻ ነው ማለታቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

ባለሙያዎቹ፣ ኢትዮጵያ 1 ቢሊዮን ዶላር የዩሮ ቦንድ ዕዳ የያዙባትን ዓለማቀፍ ኢንቨስተሮች መጠየቅ ያለባት የዕዳ መክፈያ ጊዜው እንዲራዘምላት እንጅ የቦንዱ ዋጋ እንዲቀነስላት መኾን የለበትም ማለታቸውንም ዘገባው አመልክቷል።

የገንዘብ ሚንስትር ደኤታ እዮብ ተካልኝ በበኩላቸው፣ የዓለም ባንክና የዓለማቀፉ ገንዘብ ድርጅት ባለሙያዎች የዕዳ ትንተና ሰነዱን በቅርቡ በድጋሚ ከልሰውት እንደነበርና፣ ኾኖም ግዙፍ ለውጥ እንደሌለ ተናግረዋል ተብሏል።

ዓለማቀፍ ቦንድ ያዦቹ ከመንግሥት ጋር ያላቸው ልዩነት፣ አገሪቱ በትክክል የገጠማት የአጭር ጊዜ ወይስ የረጅም ጊዜ ዕዳ የመክፈል አቅም ውስንነት ነው? የሚለው ጥያቄ እንደኾነ ይታወቃል።

መንግሥት፣ የዕዳ ትንተና ሰነዱን በመንተራስ በቦንዱ ዋጋ ላይ ቅናሽ እንዲያደረግለት መጠየቁና ቦንድ ያዦቹም ጥያቄውን ውድቅ ማድረጋቸው ይታወሳል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
በሳዑዲ አረቢያ ከሚኖሩ 7መቶሺህ ኢትዮጵያዊያን መካከል 4መቶ50ሺዎቹ መደበኛ ያልሆኑ ናቸዉ ተባለ፡፡

ከ2017 እስከ 2023 ባለዉ ጊዜ ዉስጥ ከ5መቶ61ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ወደ አገራቸዉ መመለሳቸዉም ተገልጿል፡፡

93ሺህ 5መቶ የሚሆኑ ዜጎች በ2022 በግዴታ ወደ አገራቸዉ ተመልሰዋል ነዉ የተባለዉ፡፡

በ2023 ደግሞ 43ሺህ የሚሆኑ ዜጎች በግዴታ ወደ አገራቸዉ መመለሳቸዉን ዘ ፍሪደም ፈንድ የተባለ ግብረሰናይ ድርጅት አስታዉቋል፡፡

የሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር በበኩሉ፤1መቶ33 ሺህ የሚሆኑ ዜጎች ከሳዑዲ መመለሳቸዉን የገለጸ ሲሆን፤ 46 የሚሆኑት ከባድ ጉዳት የደረሰባቸዉ ነበሩ ብሏል፡፡

ህጻናትን እና የአዕምሮ ህሙማንን ጨምሮ 6ሺህ ኢትዮጵያዊያንም ወደ አገራቸዉ ተመልሰዋል ሲል ሚኒስቴሩ አስታዉቋል፡፡

ከሱዳን ከጦርነቱ መቀስቀስ በኋላ ወደ 47ሺህ 8መቶ ዜጎች ወደ ኢትዮጵያ ተመልሰዋል ያለዉ ሴቶች እና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ ከየመን ከ4ሺህ በላይ ዜጎቻችን ተመልሰዋል ብሏል፡፡

በሁለት ዙር በተደረገ ስራ 2መቶ80ሺህ ዜጎች ወደ አገር መመለሳቸዉንም ሰምተናል፡፡

@Sheger_press
@Sheger_press
ኢትዮ መረጃ - NEWS
Photo
#ሠላሳ፣ ስልሳ፣ መቶም ያማረ ፍሬ ይስጣችሁ


ብርሃነ ዓለም ቅዱስ ጳውሎስ መስጠትን ከዘር ጋር አነጻጽሮ በምሳሌ ያስተምራል፡፡

ዘር በእጅ የያዙትን ይበዛልኛል፣ ስለ አንዷ ሰላሳ፣ ስልሳ፣ መቶም ያማረ ፍሬ አፈራለሁ ብሎ በእምንት በእርሻ ቦታ መበተንን ይጠይቃል፡፡

መስጠትም ይህን ይመስላል፡፡ በእጅ ያለውን በልግስና አሳልፎ ሰጥቶ ከእግዚአብሔር ሰፊ በረከት አገኛለሁ ብሎ በእምነት መስጠት፡፡

ይህን ቅዱስ ቃል አምናችሁ በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ በለሳ ወረዳ ለሚገኘውና ከዘጠና በላይ ገዳማውያን መነኮሳት ላሉበት ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አድነት ገዳም ያደረጋችሁት በአይነት የእህል ልገሳ በዚህ መልኩ ተጭኖ ለገዳሙ ተልኳል፡፡


“በጥቂት የሚዘራ በጥቂት ያጭዳል፤ በበረከትም የሚዘራ ደግሞ በበረከት ያጭዳል፤ እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ፥ በኀዘን ወይም በግድ አይደለም።” (2ኛ ቆሮ 9፥7) እንዲል፤ ስለ መስጠትና መቀበል በሰፊው አስተምሮበታል፡፡

የዘራ እንደሚሰበስብ፣ የሰጠም ዋጋውን አያጣምና የተዘራባት ምድር የዘሩባት አብዝታ እንደምትሰጥ፣ በልግስና የሰጣችኋቸው ገዳማውያን በጸሎታቸው ትልቅ ዋጋ፣ በሚያልፍ ስጦታ የማያልፍ በረከት፤ በሚያልቅ ልግስና የማያልቅ ዋጋ ያስገኛሉና፡፡ ቅዱስ ጳውሎስ ምጽዋትን በዘር መስሎታል፡፡


እኛም እንላለን፣ ስለሰጣችሁት እያንዷንዷ ቅንጣት የእህል ዘር ስለአንዱ ፋንታ ሰላሳ፣ ስልሳ፣ መቶም ያማረ ፍሬ ይስጥልን፡፡ በወጣ አብዝቶ ይተካ፡፡ በዚህ አጋጣሚ የተሰራው ከታቀደው አንጻር ገና ብዙ ይቀረዋልና ገዳማውያኑን በዚህ መልኩ በአይነት ማለትም ቀለብ በመስፈር፣ የግንባታ እቃዎች ጠጠር፣ አሸዋ፣ ሲሚንቶ፣ ብረት በልባችሁ እንዳሰባችሁ በመስጠት መደገፍ የምትፈልጉ ካላችሁ በደስታ እንቀበላለን፡፡ በገንዘብ ድጋፍ ለምታደርጉም የገዳሙ አካውንት ከታች ተቀምጧልና የቻላችሁትን እንድታደርጉ ገዳማዊያኑ እየተጣሩ ነው።



ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ  ማር  ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት  ገዳም


ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444


የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ለይፋዊ የስራ ጉብኝት ኤርትራ ገቡ፡፡

የሶማሊያ ዝሬዝዳንት ሀሰን ሼክ ሞሃመድ ዛሬ ታህሳስ 16/ 2017 ከሰዓት በኋላ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት አስመራ መግባታቸውን የኤርትራ ማስታወቂያ ሚኒስትር አስታወቀዋል።

ፕሬዝዳንቱና ልዑካን ቡድናቸው አስመራ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ ሲደርሱ የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂ ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል ሲሉ የማስታወቂያ ሚንስትሩ የማነ ገ/መስቀል በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል።

ሁለቱ መሪዎች የሁለትዮሽ ግንኙነቶችን እንዲሁም የጋራ ጠቀሜታ ያላቸውን ቀጠናዊ እና ዓለም አቀፍ ጉዳዮች የበለጠ ማጠናከርን በተመለከተ ይወያያሉ ተብሏል።

በመስከረም ወር መገባደጃ የሶማሊያ ፕሬዝዳንት ሃሰን ሼክ ሞሃመድ፣ የግብጹ ፕሬዝዳንት አብደል ፈታ አልሲሲ እና የኤርትራው ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈውርቂ ጋር በኤርትራ ባደረጉት የሶስትዮች ጉባኤ ሶማሊያ የየብስ እና የባህር ድንበሮቿን ለመጠበቅ የሚስያችል አቅሟን ለማጠናከር ስምምነት አድርገዋል።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
በምሥራቅ ጎጃም ሀገረ ስብከት እየተካሄደ ባለው ጦርነት ሳቢያ አንድ የአብነት መምህርን ጨምሮ ከ 599 በላይ ኦርቶዶክሳውያን እንደተገደሉ እና ከ 780 በላይ የአብነት ደቀ መዛሙርት መበተናቸው ሀገረ ስብከቱ የ 43ኛው መደበኛ ሰበካ ጉባኤ ባካሄደበት ዕለት በገለጸው ሪፖርት አሳውቋል።

በዕለቱ በእነማይ ወረዳ ከ 103 በላይ ምእመናን ሞት እና በጉባኤ ቤት ደቀ መዛሙርት ከፍተኛ የሆነ መቀዛቀዝ መፈጠሩና በደባይ ጥላት ወረዳ በ 7 አጥቢያ የሚማሩ ከ 300 በላይ ደቀ መዛሙርት መበተናቸውንና በተጨማሪም በባሶ ሊበን ወረዳ አንድ የአብነት መምህርና 395 ምእመናን ሲገደሉ በአነደድ ወረዳ ከ 250 በላይ ደቀ መዛሙርት ከጉባኤ ቤት ውጭ መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡
በደብረ ኤልያስ የቅኔና የመጻሕፍት ትምህርት ቤት ከ 230 በላይ ደቀ መዛሙርት ሲበተኑ በሸበል ወረዳ ከ 100 በላይ ምእመናን መሞታቸው በሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤው የተገለጸ ሲሆን በሀገረ ስብከቱ ጠቅላላ የሰበካ መንፈሳዊ ጉባኤ በሀገረ ስብከቱ ፈተና ስለሆነው የዶግማና የቀኖና ጥሰት ጉዳይ ፣ ስለ ወቅታዊ የቤተ ክርስቲያን ፈተናዎችና መፍትሔዎቻቸው ፣ሰበካ ጉባኤ ስለማጠናከርና አብነት ት/ቤቶች ስለማጠናከር ውይይት በማድረግ በትናትናው ዕለት ማጠናቀቁ ተገልጿል።

ዘገባው የማኅበረ ቅዱሳን ብሮድካስት አገልግሎት ነው።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ኢንጅነር ጌቱ ገረመው ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዝዳንት፣ አትሌት መሰረት ደፋርን ምክትል ፕሬዚዳንት አድርጎ መረጠ።

28ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን መደበኛ ጠቅላላ ጉባኤ ኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን ፕሬዚዳንት እንዲሁም ፌዴሬሽኑን ለቀጣይ አራት ዓመታት የሚመሩትን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት መምረጡ የሚታወስ ነው።

በጉባኤው የተመረጠው አዲሱ የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ  ዛሬ የመጀመሪያውን ሰብሰባውን በፌዴሬሽኑ ጽ/ቤት አድርጓል ።

በኮማንደር አትሌት ስለሺ ስህን የሚመራው ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ የስራ ክፍፍል ያደረገ ሲሆን ኢንጅነር ጌቱ ገረመው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ተቀዳሚ ምክትል ፕሬዚደንት እንዲሁም አትሌት መሰረት ደፋር የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዚዳንት በማድረግ መርጧል ።

ስራ አስፈጻሚ ኮሚቴው  ጨምሮም የተለያየ የስራ ክፍፍል ያደረገ ሲሆን :-

👉ወይዘሮ አበባ ዮሴፍ አቃቤ ንዋይና የአስተዳደር ፋይናንስ ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ

👉አቶ ቢኒያም ምሩፅ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የኮሚኒኬሽን ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ

👉ወይዘሮ ሳራ ሀሰን የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የሃብት አሰባሰብ ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ

👉አቶ አድማሱ ሳጂ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የጥናትና ምርምር ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ

👉ዶክተር ትዕዛዙ ሞሴ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባልና የስነምግባርና ቅሬታ ሰሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ

👉ዶክተር ኢፍራህ መሀመድ  የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባልና የህክምናና ፀረ አበረታች ቅመሞች ንኡስ ኮሚቴ ሰብሳቢ

👉አትሌት በላይነሽ ኦልጂራ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል

👉አትሌት የማነ ፀጋይ የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባል በማድረግ  ስብሰባውን አጠናቀዋል ።

https://www.tg-me.com/ethio_mereja_news
2024/12/25 18:06:31
Back to Top
HTML Embed Code: