Telegram Web Link
በአዲስ አበባ ከነገ ጀምሮ የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ!

ከኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል ጋር በተያያዘ ለተሽከርካሪ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን የአዲስ አበባ ፖሊስ ይፋ አድርጓል።
 
የኢሬቻ ሆራ ፊንፊኔ በዓል መስከረም 25/ 2017 ዓ/ም በአዲስ አበባ ይከበራል ፤ ይህን ተከትሎ የሚከተሉት መንገዶች ይዘጋሉ።

- ከቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ ቅዱስ ኡራኤል አደባባይ ላይ፤

- ከቦሌ አቅጣጫ ወደ መስቀል አደባባይ ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ኦሎምፒያ አደባባይ ላይና ታች እንዲሁም ግራና ቀኝ፤

- ከመስቀል ፍላወር ወደ ኦሎምፒያ የሚወስደው መንገድ ጋዜቦ አደባባይ ላይ፤

- ከአጎና  ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ለከባድ ተሽከርካሪ  አጎና ሲኒማ አጠገብ እንዲሁም ለቀላል ተሽከርካሪ ጥላሁን አደባባይ (አራተኛ ክፍለ ጦር ላይ)፤

- ከለገሀር መብራት ወደ መስቀል አደባባይ ለገሀር መብራት ላይ፤

- ከቴሌ ማቋረጫ ወደ ስታድዮም  ለሚጓዙ ቴሌ ማቋረጫ፤

- ከራስ ሆቴል ወደ ስታድዮም ለሚመጡ ተሽከርካሪዎች ራስ ሆቴል ላይ፤

- ከሃራምቤ  መብራት ወይም ከአምባሳደር ሲኒማ ወደ መስቀል አደባባይ ሃራምቤ  መብራት ላይ፤

- ከብሔራዊ ቤተ መንግስት  ወደ መስቀል አደባባይ የሚወስደው መንገድ  ብሔራዊ  ቤተ መንግስት አጠገብ፤

- ከካዛንቺስ ሼል ወደ ባምቢስ ሚወስደው መንገድ ካዛንቺስ ሼል አጠገብ፤

- ከጁፒተር ሆቴል ወደ ECA የሚወስደው መንገድ ባምቢስ ሳልኮት ህንፃ አጠገብ፤


ከመስከረም 24/ 2017 ዓ/ም ከቀኑ 6፡00 ሰዓት ጀምሮ ፕሮግራሙ እስከሚጠናቀቅ ድረስ መንገዶቹ ለተሽከርካሪ ዝግ እንደሚሆኑ ተገልጿል።

በዓሉ በሚከበርበት ዙሪያና በአካባቢ በግራና በቀኝ ለረጅምም ሆነ ለአጭር ጊዜ ተሽከርካሪ አቁሞ መሄድ ፍፁም የተከለከለ ነው ተብሏል።

ህብረተሰቡ ለፀጥታ ስጋት የሆኑ አጠራጣሪ ነገሮች ሲያጋጥሙት በ011-1-11-01-11 እንዲሁም በ991 ነፃ የስልክ መስመር ጥቆማ መስጠት ይችላል።

    #AddisAbabaPolice

@sheger_press
@sheger_press
2024/10/04 01:28:17
Back to Top
HTML Embed Code: