Telegram Web Link
በእስራኤል ዋና ከተማ ቴላቪቭ በተከፈተ የጅምላ ተኩስ ስድስት ሰዎች ተገደሉ

ኢራን በእስራኤል ላይ ከፈፀመችው የሚሳኤል ጥቃት በተለየ ሁኔታ፣ በቴል አቪቭ የጅምላ ተኩስ ተከስቷል።

ዛሬ ማምሻውን ታጣቂዎች በከተማው ጎዳና ላይ በሰዎች ላይ ተኩስ ከፍተዋል ሲል ፖሊስ የገለፀ ሲሆን የእስራኤል መገናኛ ብዙሃን ቢይንስ ስድስት ሰዎች መሞታቸውን ዘግበዋል። ቢያንስ ሰባት ሰዎች ደግሞ መቁሰላቸው የተዘገበ ሲሆን አንዳዳዶቹ በአስጊ ሁኔታ ላይ ይገኛሉ መባሉን ዳጉ ጆርናል ዘግቧል።

በማህበራዊ ድረ-ገጾች ላይ የተለጠፉት ምስሎች እንዳሳዩት ታጣቂው በጃፋ አካባቢ በሚገኝ የባቡር ጣቢያ ላይ መሬት ላይ ተኝተው በተሰበሰቡ ሰዎች ላይ ሲተኩስ ታይቷል። ፖሊስ የጥቃቱን ምክንያት “ሽብር” ሲል ገልጾታል።
መስማት የተሳናትን የ ስምንት አመት ልጅ እና የአእምሮ ውስንነት ያለባትን የ አስራ ስድስት አመት ልጅ ላይ የአገድዶ መድፈር ጥቃት የፈፀሙ ሁለት ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ

በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ዳዋ ወረዳ ውስጥ መስማት የተሳናትን የስምንት አመት ልጅ እና በጎሮ ወረዳ የአስራ ስድስት አመቷን የአእምሮ ውስንነት ያለባትን ልጅ አስገድዶ የደፈረው ግለሰብ ላይ የእስራት ቅጣት መተላለፉን የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ አስታወቀ።

እንደ ደቡቡ ምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ ገለፃ ተከሳሽ ፈይሳ ከበደ የተባለው ግለሰብ ሰኔ 1ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 5 ሰአት ላይ በደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ዳዋ ወረዳ ቡሳ 01 ቀበሌ የስምንት አመቷን መስማት የተሳናትን ልጅ አባብሎ በመውሰድ የመድፈር ጥቃት እንደፈፀመባት ተገልጿል። ተከሳሹ መስማት የተሳናት የስምንት አመት ልጅ ላይ የመድፈር ጥቃት ከፈፀመ በኋላ የስምንት አመቷ መስማት የተሳናት ልጅ የተፈፀመባት ድርጊት መቋቋም አቅቷት ስትጮህ የአካባቢው ሰዎች ደርሰው ድርጊቱን ለማስጣል ሲሞክሩ የመድፈር ጥቃት ፈፃሚው ሮጦ ለማምለጥ ቢሞክርም በህብረተሰቡ ትብብር በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል።

ፖሊስም በህብረተሰቡ ትብብር በቁጥጥር ስር የዋለውን ተከሳሽ ላይ የምርመራ መዝገቡን በማጣራት ተጎጂዋን የስምንት አመት ልጅ ወደ ጤና ጣቢያ በመላክ በማስመርመር የህክምና እርዳታ እንድታገኝ አድርጓል። በህክምና ማስረጃ መሰረት በታዳጊዋ ላይ የመደፈር ጥቃት ሙከራ መከናወኑን የሚገልፅ በመሆኑ እና በአይን እማኝ ምስክርነት የምርመራ መዝገቡን በማጣራት ለአቃቤ ህግ መላኩን ገልፀዋል።አቃቤ ህግም ከፖሊስ የተላከለትን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በወንጀል ህግ 627 ንዑስ አንቀፅ 1 መሰረት ለአቅመ ሄዋን ባልደረሱ እንስቶች ላይ የሚፈፀም የመድፈር ጥቃትን በመጥቀስ ክስ መስርቷል። በአቃቤ ህግ የተመሰረተውን ክስ ሲመለከት የነበረው የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት ተከሳሽን በ6 ዓመት እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል።

በተመሳሳይ በደቡብ ምዕራብ  ሸዋ ዞን ጋልዮ ሞጆ ቀበሌ ውስጥ በአስራ ስድስት አመቷ የአይምሮ ውስንነት ባለባት ልጅ ላይ የመድፈር ጥቃት በመፈፀም ክብረ ንፅህናዋን የወሰደው ግለሰብ በእስራት መቀጣቱን የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ መምሪያ ገልፆል።ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 5 ሰአት ላይ ተከሳሽ ጌታቸው ታደሰ የተባለው ግለሰብ የ አስራ ስድስት ዓመቷን የአይምሮ ውስንነት ያለባትን ልጅ በጉልበት እጇን በመጠምዘዝ ወደ ሰዋራ ስፍራ ወስዶ የመድፈር ጥቃት እንንዳደረሰባት በማስረጃ መረጋገጡን ገልፆል። ተጎጂዋ የደረሰባትን ጥቃት መቋቋም አቅቷት ስትጮህ የሰሙ የአካባቢው ሰዎች ደርሰው ተከሳሹን ወዲያውኑ እጅ ከፍንጅ በመያዝ ለፖሊስ ማስረከባቸውን ተገልጿል። ፖሊስም የድርጊቱ ፈፃሚ በመያዝ ጥቃት የደረሰባት ታዳጊ የአይምሮ ውስንነት ያለባት ልጅ የክብረ ንፅህናዋ እንደተወሰደ በማረጋገጥ ማስረጃውን ለአቃቤ ህግ መላኩን የፖሊስ መምሪያው ገልፆል። 

አቃቤ ህግ ከፖሊስ የተላከለትን የምርመራ መዝገብ ተመልክቶ በወንጀል ህግ 620 ንሁስ አንቀፅ 2 ቸአይምሮ ውስንነት ባለባቸው ሰዎች ላይ በሚፈፀም የመድፈር ጥቃት መሠረት በማድረግ ክስ ይመሰርታል። በአቃቤ ህግ የተመሠረተውን ክስ ሲከታተል የነበረው የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድቤት ተከሳሽ ጌታቸው ታደሰ በአቃቤ ህግ የቀረበበት ክስ ሙሉ በሙሉ ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ በ ዘጠኝ አመት እስራት እንዲቀጣ ወስኖበታል ሲል የደቡብ ምዕራብ ሸዋ ዞን ፖሊስ ገልፆል።
2024/10/02 06:22:26
Back to Top
HTML Embed Code: