Telegram Web Link
የሸዋ አማራ የጦር ግንባር ዉሎዎችን በሚዛናዊነት እየተከታተለ የሚያቀርብ ቻናል ልጠቁማችሁ👇👇
https://www.tg-me.com/SNN_merja
እስራኤል በዛሬው እለት በደቡባዊ ቤይሩት ከተማ የሂዝቡላህ ዋና መስሪያቤትን ጨምሮ ሶስት ህንፃዎችን ሙሉ በሙሉ በማውደም በርካታ ሰዎች ህይወት አልፏል።

የጥቃቱ ኢላማ የሂዝቡላሁ መሪ ሰይድ ሀሰን ነስረላህ የነበረ ሲሆን ኢላማዋ አለመሳካቱን ቡድኑ አስታውቋል።

ሂዝቡላህ ከጥቃቱ በሗላ በሰጠው አጭር መግለጫ ሰይድ ሀሰን ነስረላህ ደህንነቱ በተጠበቀ ቦታ ነው ብሏል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ የእስራኤሉ ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት(ተመድ) 79ኛ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ተገኝተው ስሜት የተሞላበት ንግግር አድርገዋል፡፡ 

“ዘንድሮ በጉባኤው የመሳተፍ እቅድ አልነበረኝም፤ ሀገሬ በከፍተኛ ውጥረት ውስጥ በምትገኝበት ጊዜ እዚህ የተገኘሁት በመድረኩ ከተለያዩ አካላት ለቀረበብን ወቀሳ ምላሽ ለመስጠት ነው” በሚል ንግራቸውን የጀመሩት ጠቅላይ ሚንስትሩ እየተዋጋን ያለነው ከምድረ ገጽ ሊያጠፉን ከሚሹ “አረመኔ ጠላቶች” ጋር ነው ብለዋል።

“እስራኤል ኢራን በከፈተችው 7 አውደ ውግያዎች እየተዋጋች ትገኛለች፤ ተሄራን ከምታሰማራቸው ርህራሄ የለሽ ገዳዮች እራሳችንን መከላከላችንን እንቀጥላለን፡፡ ይህ ሲሆን በኢራን ውስጥ የእስራኤል ረጅም ክንድ የማይደርስበት ቦታ አለመኖሩ ሊታሰብበት ይገባል” ነው ያሉት

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/09/29 09:33:03
Back to Top
HTML Embed Code: