Telegram Web Link
መቀሌ

በዶ/ር ደብረፅዮን የሚመራው ህውሃት በመቀሌ ከተማ ህዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው።

መድረኩን የህወሓት ሊቀ መንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፣ አማኑኤል አሰፋ እና የመቀሌ ከተማ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና ከንቲባ ይትባረክ አምሃ እየመሩት ይገኛሉ።

ውይይቱ ከመስከረም 11 እስከ 16 በሁሉም ከተሞችና ወረዳዎች ይካሄዳል።

በውይይት መድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሕወሃት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብፅዮን ገብረሚካኤል መድረኩ በዚህ ፈታኝ ጊዜ ውስጥም ቢሆን ከህዝቡ ጋር በመመካከር መካሄድ አለበት ብለዋል።

እነዶ/ር ደብረፅዮን ከሠሞኑ በጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር ውጥረት ውስጥ መግባታቸው ይታወሳል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የ15 ዓመት ታዳጊን ለአራት በመሆን የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀሙ ተከሳሾች በእስራት ተቀጡ

በኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ ኦፓላሼ ቀበሌ ለአራት በመሆን የ15 ዓመት ታዳጊን አስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀሙ ተከሳሾች በእስራት ተቀጡ።

ተከሳሾች በቁጥር አራት ሲሆን አስፋቸው አለሙ፣ አሻግሬ አበራ፤  ማቲዎስ ደዋና እና አስማማው አሉላ የተባሉ ግለሰቦች ናቸው።

ግለሰቦቹ በአመያ ዙሪያ ወረዳ በግምት 8:00 አካባቢ  ጫሬ ዶቄ ቀበሌ ቤተሰብ ለመጠየቅ ወደ ኦፓላሼ ቀበሌ እየሄደች የምትገኝ የ15 አመት ታዳጊ አስገድደው መድፈራቸውን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች  ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ  እና  ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው ክስ የቀረበባቸው ወንጀለኞች ጳግሜ 5 ቀን 2016 ዓ.ም  በዋለው ችሎት ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተከሳሾች እያንዳንዳቸው 7 ዓመት ፅኑ እስራት  ተቀጥተዋል።

አራተኛ ተከሳሽ ዕድሜው ከ10 እስከ 13 ዓመት በመሆኑ ተከሳሹ  መታሰር የማይችልና እንደዚህ ዓይነት ታዳጊ እስረኞችን ተቀብሎ   በማረምያ ተቋም በዞኑ ባለመኖሩ ምክንያት ቤተሰቡ ፈርሞ ወስዶት ክትትልና በቁጥጥር እንዲያደርግ በማለት ውሳኔ መሰጠቱን ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ  እና  ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

#ዳጉ_ጆርናል

@sheger_press
@sheger_press
በእሳት አቃጠሉት ‼️

በብራዚል የአንድ አመት እና የሰባት ወር ህፃናትን በደፈረ ግለሰብ የተቆጡ ሰዎች ፖሊስ ጣብያውን ሰብረው በመግባት ደፋሪውን ከነ ህይወቱ አቃጥለውታል።

@sheger_press
@sheger_press
ከእኛ ጋር የሰሩ ምስክሮቻችን ናቸዉ!
ደንበኞችን ካሉበት ወደ እርሶ ማድረሱን ተክነንበታል።
ከርሶ እሚጠበቀዉ ወደ እኛ መምጣት ብቻ ነው!

አድራሻችን:22 ማዞሪያ ኮሜት ህንጻ፣ ቢሮ ቁጥር 206

ስልክ፡ 0988800031
ኢ-ሜል፡ [email protected]
ቴሌግራም: @AiQEMContact


Telegram
Facebook
LinkedIn
Twitter
ቤንዚን እና ጥቁር ገበያው
በአዲስ አበባ ቤንዚን ረጅም ሰዓት ሰልፍ ሳይሰለፉ ማግኘት ዘበት ከሆነ ሰነባብቷል።

ባለፉት ሳምንታት በትንሽ በትንሹ የጀመረው የቤንዚን ሰልፍ ከሰሞኑን እጅግ ብሶበታል።

በአንዳንድ ማደያዎች " ቤንዚን የለም " እየተባለ ሲለጠፍ ቤንዚን ያለባቸው ማደያዎች እጅግ በጣም ረጅም ሰልፍ ነው ያለው።

በዚህም ምክንያት የመኪና አሽከርካሪዎች ቀናቸውን በቤንዚን ሰልፍ ለማሳለፍ እየተገደዱ ይገኛሉ።

በሜትር ታክሲ አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ዜጎችም ስራቸውን በአግባቡ ለመስራት ተቸግረዋል። ቀናቸውን ሁሉ በቤንዚን ሰልፍ ለማሳለፍ እየተገደዱ ናቸው።

በክልል ከተሞችም የቤንዚን ነገር ብሶበታል።

ቀድሞውንም ቤንዚን በማደያ እንደልብ በማንኛውም ሰዓት ማግኘት የማይቻልባቸው የክልል ከተሞች አሁንም ችግሩ እንዳለ ነው።

በክልል ከተሞች አሽከርካሪዎች ቤንዚን በማደያ " የለም " የሚባሉ ሲሆን በጀርባ ግን በየቦታው በህገወጥ መንገድ በጥቁር ገበያ ቤንዚን ሲቸበቸብ ይታያል።

ይህ ህዝብን እያማረረ ያለው የጥቁር ገበያ የነዳጅ ሰንሰለት መቼ እንደሚበጠስ አይታወቅም። ከዚህ ጀርባ እጃቸው የረዘመ አካላት መኖራቸውን ግን አሽከርካሪዎች ይናገራሉ።

ቤንዚን በክልል ከተሞች ከማደያ ውጭ በእጥፍ ዋጋ ነው የሚቸበቸበው።
ስራ ቀይረው በጥቁር ገበያው ቤንዚን ነጋዴ የሆኑም በርካቶች ናቸው።

@sheger_press
@sheger_press
ሁሌ እንደማደርገው አይቼ ላልፈው ነበር...!

"በነፃነት ያሻን ቦታ መሄድ" የሚለውን ሳይ ግን...

አሁን ላይ ስንቱ ወገን ነው ጠግቦ በልቶ እያደረ ያለው? ስንቱ ነው በነፃነት እያሰበ እና እየተናገረ ያለው? ማነው ከአዲስ አበባ ውጪ ንቅንቅ ብሎ ያሻው ቦታ የሚሄድ? ስንቱ ነው ለፍቶ ጥሮ ያገኘውን ጥሪት በልማት ስም እየተቀማ እና እየፈረሰበት ያለ?

ይሄ አላማ ከስንት አመት በኋላ ይሳካ ይሆን?

መሬት ላይ ካለው ችግር ይልቅ እንዲህ አይነት የተስፈኛ አካሄድ እጅጉን ያስፈራል፣ የባሰው ችግር ገና ወደፊት እንደሆነም ያመላክታል።

#Ethiopia eliasmeseret

@sheger_press
@sheger_press
በመስቀል ደመራ በዓል የተከለከሉ ነገሮችን ለብሶም ሆነ ይዞ መምጣት ክልክል ነው

የዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ተደርጎ ወደ ሥራ መገባቱን ጥምር የፀጥታ ኃይሉ አስታውቋል፡፡

በዓሉ ወደሚከበርበት ስፍራ ከበዓሉ አከባበር ጋር ግንኙነት የሌላቸውን ነገሮች ይዞ መምጣት አመፅን የሚቀሰቅሱ እና ተከባብሮ የመኖር እሴትን የሚሸረሽሩ ፅሁፎች ያሉባቸውን አልባሳት ለብሶ መምጣት በአጠቃላይ የተከለከሉ ነገሮችን
ይዞ መምጣትና እንዲሁም ደመራ የማብራት ስነ ስርዓት በሚከናወንባቸው የተለያዩ ቦታዎች ላይ ርችት ማፈንዳት ክልክል መሆኑን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ ለፀጥታ ሃይሎች ሥራ ተባባሪ እንዲሆን ጥምር የፀጥታ ኃይሉ አሳስቧል፡፡

@sheger_press
@sheger_press
News ‼️

ግዙፉ መንግስታዊ የቴሌኮም አቅራቢ ድርጅት የሆነዉ ኢትዮቴሌኮም በተወሰኑ ምርትና አገልግሎቶቹ ላይ የታሪፍ ማሻሻያ ሊያደርግ እንደሚችል አስታዉቋል

ተግባራዊ ከተደረገ አንድ ወር ያለፈዉ የማክሮኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ ተከትሎ የደበንኞችን የመክፈል አቅም ያገናዘበ የታሪፍ ማሻሻያ ለማድረግ መታሰብ ተቋሙ ገልጿል።

የኢትዮቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ እንደተናገሩት ሁሉም ደንበኞች እና አገልግሎቶች ላይ ዋጋ አንጨምርም ነገር ግን የደንበኞችን የመክፈል አቅም ያገናዘበ በአንድአንድ ምርትና አገልግሎቶች ላይ የታሪፍ ማሻሻያ ይደረጋል ብለዋል።

የኢኮኖሚ ሪፎርሙን ተከትሎ ወዲያዉ ያልተስተካከለበት ምክንያት የደንበኞቹን አጠቃላይ ደግሞ የማክሮኢኮኖሚ ለዉጥ እንዲረጋጋ በማሰብ መሆኑ ተነግሯል ።

ባለፉት ሁለት አስርት አመታት የብር ዋጋ ከ750% በላይ ሲቀንስ ኢትዮቴሌኮም ባለፉት ስድስት አመታት በከፍተኛ ደረጃ የዋጋ ቅናሽ በማሳየቱ ዋጋው ከአለም ዝቅተኛው እና ለተጠቃሚዎች በጣም ተመጣጣኝ እንዲሆን አድርጎታል። 

እንደ ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ገለፃ እ.ኤ.አ በ 2018 ላይ ከ 40 እስከ 50 በመቶ የታሪፍ ቅናሽ ያደረገ ሲሆን በሂደትም የተለያዩ የታሪፍ ማሻሻዎችን ማድረጉን እንዲሁም ፤ የቅርብ ጊዜ ሪፖርቶችንም ደግሞ ከተመለከትን ኢትዮ ቴሌኮም ዝቅተኛ ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑን ነው የሚያሳየው ብለዋል።

"ዘለን ታሪፉን ያላስተካከለው የደንበኞቻችንን እንዲሁም በአጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ለውጡ እንዲረጋጋ እና ጤናማ እንዲሆን ስለምንፈልግ ነው” በማለትም ተናግረዋል።

አሁን ላይ ተቋሙ በተለይ በድምፅና በዳታ አገልግሎት ላይ የሚያስከፍለዉ ታሪፍ ርካሽ እንደሆነ ያነሱት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አዲስ የታሪፍ ለማድረግ እንደታሰበ ከመናገር ዉጪ መቼ እንደሚተገበር ግን ከመናገር ተቆጥበዋል።

@sheger_press
@sheger_press
#ሶማሊላንድ #ግብፅ ወደ ሞቃዲሹ  ከባድ የጦር መሳሪያ ማስገባቷን ተከትሎ ማስጠንቀቂያ ሰጠች‼️

የሶማሌ ላንድ መንግስት ግብፅ ለሶማሊያ የምታቀርበውን ከባድ የጦር መሳሪያ አሳሳቢነት በመግለጽ እርምጃው ቀድሞውንም ደካማ የነበረውን የቀጠናውን ደህንነት ይበልጥ አደጋ ላይ ይጥላል ስትል አስጠንቅቃለች።

የሶማሊላንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፣ “በተለይ የሞቃዲሾ አስተዳደር በብቃት ለማስተዳደር ወይም ለመጠበቅ የሚያስችል አቅም ስለሌለው የእነዚህ መሳሪያዎች ዝውውር በእጅጉ አስደንግጦናል ብለዋል።

ሶማሊላንድ በተጨማሪም ይህ የጦር መሳሪያ ዝውውር የአፍሪካ ቀንድን ወደ አልተረጋጋ ቀውስ እና የጦር መሳሪያ እሽቅድምድም እድልን ከፍ እንደሚያደርግ አፅንዖት ሰጥታለች።

@sheger_press
@sheger_press
"ጄኔራል ፃድቃን ከማን ጋር ነው የምንደራደረው ? ብሎናል " ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር)‼️
ደብረፅዮን ገ/
ሚካኤል (ዶ/ር) ፤ ጄነራል ጻድቃን ገ/ትንሳኤን ስልጣን ለመጠቅለል በማቀድና የቆየ ቂም ለመወጣት በሚል ከሰሱ።

ቅዳሜ በመቐለ በተካሄደና የህወሓት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ህወሓትን ለማጥፋት፣ ስልጣን ለመጠቅለል የሚንቀሳቀሱ ተብለው የተገለፁ አመራሮች በስም እየተጠቀሱ ወቀሳ ሲሰነዘርባቸው ተሰምቷል።

በዚሁ መድረክ ደብረፅዮን (ዶ/ር) ፥ የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዝደንት የሆኑት ጀነራል ፃድቃን ገብረትንሳኤን፥ ስልጣን ለመጠቅለል በማቀድ፣ የቆየ ቂም በመወጣት እና ሌሎች በርካታ ጉዳዮች በማንሳት እንዲሁም ከዚህ በፊት በይፋ ያልተሰሙ መረጃዎች በመግለፅ ሲተቹ ተደምጠዋል።

በንግግራቸው እርሳቸው የሚመሩትን ህወሓት ሰላም የማይፈልግ አድርጎ የማቅረብ የተሳሳተ ፍረጃ ከትግራይ ባለስልጣናት በኩል እየቀረበበት መሆኑ ገልጸው " ይህ ውሸት ነው " በማለት አጣጥለዋል።

ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ፤ " ለምሳሌ በደቡባዊ ዞን በተደረገ መድረክ ጀነራል ጻድቃን እኛ ሰላም እንፈልጋለን፣ እነሱ የሚሹት ጦርነት ነው ሲል ሰምታችሁታል። በጦርነቱ ወቅት ደሴ ተሻግረን ሰሜን ሸዋ ስንጠጋ፥ ድርድር ያስፈልጋል ወይ ሲባል እኔ አዎን ያስፈልጋል ነው ያልኩት። በሰላም ሊፈታ ስለሚገባው። እሱ ግን ከማን ጋር ነው የምንደራደረው፣ ውጊያው አልቋል ሲል የነበረ ነው። አሁን ግን እኔ ሰላም ነኝ እነሱ ጦርነት ናቸው የሚፈልጉ ማለት ጀመረ " ብለዋል። #ዶቼቨለ

@sheger_press
@sheger_press
#ግብፅ

በርካታ ከባድ የጦር መሳሪያዎችን የጫነች የግብጽ መርከብ ሞቃዲሾ ወደብ መድረሷ ተገለጸ።

ካይሮ የላከቻቸው የአየር እና የታንክ መቃወሚያዎችን ጨምሮ ሌሎች ከባድ የጦር መሳርያዎች ወደ ሀገሪቱ መከላከያ ሚኒስቴር መስርያ ቤትና የተለያዩ የጦር ካምፖች መጓጓዛቸውም ተዘግቧል።

ግብጽ በነሀሴ ወር በሁለት ወታደራዊ አውሮፕላኖች ለሶማሊያ የጦር መሳርያና ወታደሮችን ልካለች መባሉ የሚታወስ ሲሆን፥ ሞቃዲሾ ግን የወጡትን ዘገባዎች ማስተባበሏ አይዘነጋም።

በሶማሊላንድ እና በኢትዮጵያ መካከል የወደብ የመግባብያ ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ የአዲስ አበባ እና ሞቃዲሾ ግንኙነት መሻከሩን ተከትሎ የግብጽና ሶማሊያ ወታደራዊ ትብብር እያደገ ይገኛል።
 
ከግብጽ የተላኩትን የጦር መሳርያዎች ከትላንትናው እለት ጀምሮ ከሞቃዲሾ ወደብ የማራገፍ ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ ሲነገር፤ ወደ ሀገሪቱ መከላከያ ሚንስትር መስርያ ቤት እና በአካባቢው ወደሚገኙ የጦር ካምፖች ጦር መሳርያዎቹን እየተጓጓዙ ነው ተብሏል፡፡

ይህን ተከትሎም ወደቡ እና ዋና ዋና መንገዶች ለንግድ እና ለሲቪሊያን እንቅስቃሴዎች ዝግ መደረጋቸውን ዘገባው ጨምሮ አስነብቧል።በሶማሊላንድና በኢትዮጵያ መካከል የወደብ የመግባብያ ስምምነት መፈረሙን ተከትሎ የአዲስአበባና ሞቃዲሾ ግንኙነት መሻከሩ ይታወሳል፡፡ 

በዚህም የአባይ ውሀን ከመቆጣጠር ጋር በተያያዘ ከኢትዮጵያ ጋር ቆየት ያለ ባላንጣነት ያላት ካይሮ ወደ አፍሪካ ቀንድ እየቀረበች እንደምትገኝ ተንታኞች ይናገራሉ፡፡በሶማሊያ የአፍሪካ ህብረት የሽግግር ተልዕኮ (አትሚስ) በቀጣይ የሚኖረው አዲስ የሰላም ተልዕኮ አወቃቀር ላይ የኢትዮጵያን ወታደሮች መካተት አልቀበልም ያለችው ሶማሊያ ግብጽ በሰላም አስከባሪ ሀይሉ ውስጥ እንድትሳተፍ ፍላጎቷ መሆኑን ተናግራለች፡፡(አልአይን)

@sheger_press
@sheger_press
ቴሌግራም የተጠቃሚዎቹን መረጃ ለመንግስታት አሳልፎ ሊሰጥ ነው

ቴሌግራም የተጠቃሚዎቹን መረጃ ህግን በተከተለ መልኩ ሲጠየቅ ለመንግስት ተቋማት አሳልፎ ሊሰጥ እንደሚችል አስታወቀ።

ውሳኔው ድርጅቱ ለረጅም ዓመታት ይዞት የነበረውን የደንበኞቹን መረጃ አሳልፎ ያለመስጠት ፖሊሲ የሻረ መሆኑ ተገልጿል።

በዚህም ድርጅቱ ህግን የተከተለ ጥያቄ ሲቀርብለት የተጠቃሚዎቹን አይ ፒ አድራሻ፣ ስልክ ቁጥር እና ሌሎች መረጃዎችን አግባብ ላላቸው የመንግስት አካላት እንደሚሰጥ አስታውቋል።

ቴሌግራም እዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰው መስራቹና ዋና ስራ አስፈጻሚው ፓቬል ዱሮቭ ባለፈው ነሐሴ ወር በፈረንሳይ መንግስት መታሰሩን ተከትሎ መሆኑ ተጠቅሷል።

በመተግበሪያው ላይ የሚሰራጩ ፅንፈኛ አቋም ያላቸው ይዘቶችን አልተቆጣጠረም በሚል ክሱ የተመሰረተበት ዋና ስራ አስፈጻሚው በዋስ ተፈቶ ከአገር እንዳይወጣ መታገዱ ይታወሳል።

ውሳኔውን አስመልክቶ ፓቬል ዱሮቭ ይፋዊ የቴሌግራም ቻናሉ ላይ ባሰፈረው መረጃ “የቴሌግራምን ህግ የሚጥሱ ተጠቃሚዎች የስልክ ቁጥርና አይፒ አድራሻ ህግን ተከትለው ጥያቄ ላቀረቡ አካላት አሳልፈን እንደምንሰጥ ግልፅ አድርገናል” ብለዋል።

@sheger_press
@sheger_press
2024/09/29 05:26:59
Back to Top
HTML Embed Code: