Telegram Web Link
ኤክስፐርት ለመሆን እና ከፍተኛ ተፈላጊነት ባላቸው ሙያዎች የምስክር ወረቀት ማግኘት ይፈልጋሉ? የ Safaricom Talent Cloud ትክክለኛው ቦታ ነው፡ https://bit.ly/3Re7G22

በመረጡት የትምህርት ዘርፍ እውቀትን ለመገንባት በጥሩ ሁኔታ ከተዘጋጁ ኮርሶች በተጨማሪ የሚከተሉትን ያገኛሉ፡-

- በመረጡት የሙያ መስክ የላቀ ለመሆን እንዲረዳዎ በባለሙያዎች የተመረጡ የትምህርት ካሪኩለሞች
- እጅግ ታዋቂ ከሆነው Pluralsight የonline መማሪያ ድህረገጽ ሰርተፍኬት
ልምድ ባላቸው ባለሙያዎች የሚመሩ የስልጠና ቡድኖችን
- በየወሩ ነጻ የ6 GB የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚም ይሆናሉ

እነዚህን ተጨማሪ ጥቅማጥቅሞችና ግልጋሎቶች በማግኘት በፍጥነት ያሎትን እዉቀትና ክህሎት በማሳደግ በስራ ዘርፎ ዉጤታማ መሆን ይችላሉ። https://bit.ly/3Re7G22 ይጎብኙ!

ለበለጠ መረጃ ቴሌግራሞ ቻናላችንን ይቀላቀሉ https://www.tg-me.com/+3nNaOCMHiXgyMTA0
ዛሬ መስከረም 11 2017 ባንኮች 1 ዶላርን በስንት ብር እየመነዘሩ ነው?

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ 1 ዶላር በ112 ብር እየገዛ፤ በ123 እየሸጠ ይገኛል

ኢትዮጵያ ገበያ መር የውጭ ምንዛሬ ተመን ስርአት ተግባራዊ እንዲደረግ መወሰኗን ተከትሎ ባንኮች አዲሱን የምንዛሬ ተመን ተግባራዊ በማድረግ ላይ ይገኛሉ።

የ2017 አዲስ ዓመት አስመልክቶም ባንኮች በውጭ ሀገራት የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውያውን በባንኮች አማካኝነት ገንዘብ እንዲልኩ የሚያበረርታታ ተመን እያወጡ ነው።

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አዲስ ዓመትን ምክንያት በማድረግ በዓለም አቀፍ የገንዘብ አስተላላፊ ድርጅቶች በኩል የሚላክን ገንዘብ ከባንኩ ለሚቀበሉ ደንበኞቹ ተጨማሪ የ6.82 በመቶ የበዓል ስጦታ እንደሚሰጥ አስታውቋል።

ባንኩ ዛሬ መስከረም 11 2017 ዓ.ም መደበኛ የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዛበትን እና የሚሸጥበትን ዋጋ ይፋ ሲያደርግ የመግዣ ዋጋውን የትናንቱን አስቀጥሏል። በዚህም አንድ የአሜሪካ ዶላርን በ112.3957 ብር እየገዛ በ123.6353 ብር እየሸጠ ይገኛል።

እስከ መስከረም 30 ቀን 2017 ዓ.ም ባለው ጊዜ የሚላክን አንድ የአሜሪካ ዶላር በ125 ብር እንደሚመነዝር ያስታወቀው ንብ ባንክም መደበኛውን (እለታዊ የምንዛሬ ተመን) ይፋ አድርጓል።

ባንኩ በእለታዊ መደበኛ የመንዛሬ ዋጋ አንድ የአሜሪካ ዶላር በ109.7209 ብር እየገዛ በ122.8874 ብር እየተሸጠ መሆኑን ገልጿል።

ኦሮሚያ ባንክም በዓልን ምክንያት በማድረግ ከውጪ በሃዋላ የተላከ አንድ የአሜሪካ ዶላርን ከእለታዊ ተመን በተጨማሪ 17 በመቶ ጉርሻ እንደሚሰጥ እና በዚህም 1 ዶላርን በ126+ ብር እንደሚመነዝር ማስታወቁ ይታወሳል።
ባንኩ የዛሬ የመስከረም 11 2017 መደበኛ የምንዛሬ ተመኑን ይፋ ሲያደርግ 1 የአሜሪካ ዶላር በ109.2120 ብር እየገዛ በ125.4096 ብር እየሸጠ መሆኑን ነው የጠቆመው።[አል አይን]
Forwarded from Sheger Press️️
Want to become an expert and get certified in skills that are in high demand? The Safaricom Talent Cloud is the right place: https://bit.ly/3Re7G22

Besides well-designed courses to build expertise in the area you pick, you also get:

• Personalized learning paths to help you master your chosen field
• Certificates from the popular online learning site Pluralsight
• Coaching groups led by experienced professionals to guide you
• Free 6GB internet data every month for learning

With these benefits and resources, you can quickly develop valuable expertise and advance your career. Visit: https://bit.ly/3Re7G22
Join our Telegram channel https://www.tg-me.com/+3nNaOCMHiXgyMTA0
መቀሌ

በዶ/ር ደብረፅዮን የሚመራው ህውሃት በመቀሌ ከተማ ህዝባዊ ውይይት እየተካሄደ ነው።

መድረኩን የህወሓት ሊቀ መንበር ዶ/ር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል፣ አማኑኤል አሰፋ እና የመቀሌ ከተማ የማዕከላዊ ኮሚቴ አባልና ከንቲባ ይትባረክ አምሃ እየመሩት ይገኛሉ።

ውይይቱ ከመስከረም 11 እስከ 16 በሁሉም ከተሞችና ወረዳዎች ይካሄዳል።

በውይይት መድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የሕወሃት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብፅዮን ገብረሚካኤል መድረኩ በዚህ ፈታኝ ጊዜ ውስጥም ቢሆን ከህዝቡ ጋር በመመካከር መካሄድ አለበት ብለዋል።

እነዶ/ር ደብረፅዮን ከሠሞኑ በጊዜያዊ አስተዳደሩ ጋር ውጥረት ውስጥ መግባታቸው ይታወሳል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የ15 ዓመት ታዳጊን ለአራት በመሆን የአስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀሙ ተከሳሾች በእስራት ተቀጡ

በኮንታ ዞን አመያ ዙሪያ ወረዳ ኦፓላሼ ቀበሌ ለአራት በመሆን የ15 ዓመት ታዳጊን አስገድዶ መድፈር ወንጀል የፈፀሙ ተከሳሾች በእስራት ተቀጡ።

ተከሳሾች በቁጥር አራት ሲሆን አስፋቸው አለሙ፣ አሻግሬ አበራ፤  ማቲዎስ ደዋና እና አስማማው አሉላ የተባሉ ግለሰቦች ናቸው።

ግለሰቦቹ በአመያ ዙሪያ ወረዳ በግምት 8:00 አካባቢ  ጫሬ ዶቄ ቀበሌ ቤተሰብ ለመጠየቅ ወደ ኦፓላሼ ቀበሌ እየሄደች የምትገኝ የ15 አመት ታዳጊ አስገድደው መድፈራቸውን የደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች  ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነትና ኮሙኒኬሽን ዳይሬክተር ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ  እና  ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

በአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጥፋተኛ ሆነው ክስ የቀረበባቸው ወንጀለኞች ጳግሜ 5 ቀን 2016 ዓ.ም  በዋለው ችሎት ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተከሳሾች እያንዳንዳቸው 7 ዓመት ፅኑ እስራት  ተቀጥተዋል።

አራተኛ ተከሳሽ ዕድሜው ከ10 እስከ 13 ዓመት በመሆኑ ተከሳሹ  መታሰር የማይችልና እንደዚህ ዓይነት ታዳጊ እስረኞችን ተቀብሎ   በማረምያ ተቋም በዞኑ ባለመኖሩ ምክንያት ቤተሰቡ ፈርሞ ወስዶት ክትትልና በቁጥጥር እንዲያደርግ በማለት ውሳኔ መሰጠቱን ኢንስፔክተር ደጀኔ አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ  እና  ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

#ዳጉ_ጆርናል

@sheger_press
@sheger_press
በእሳት አቃጠሉት ‼️

በብራዚል የአንድ አመት እና የሰባት ወር ህፃናትን በደፈረ ግለሰብ የተቆጡ ሰዎች ፖሊስ ጣብያውን ሰብረው በመግባት ደፋሪውን ከነ ህይወቱ አቃጥለውታል።

@sheger_press
@sheger_press
ከእኛ ጋር የሰሩ ምስክሮቻችን ናቸዉ!
ደንበኞችን ካሉበት ወደ እርሶ ማድረሱን ተክነንበታል።
ከርሶ እሚጠበቀዉ ወደ እኛ መምጣት ብቻ ነው!

አድራሻችን:22 ማዞሪያ ኮሜት ህንጻ፣ ቢሮ ቁጥር 206

ስልክ፡ 0988800031
ኢ-ሜል፡ [email protected]
ቴሌግራም: @AiQEMContact


Telegram
Facebook
LinkedIn
Twitter
ቤንዚን እና ጥቁር ገበያው
በአዲስ አበባ ቤንዚን ረጅም ሰዓት ሰልፍ ሳይሰለፉ ማግኘት ዘበት ከሆነ ሰነባብቷል።

ባለፉት ሳምንታት በትንሽ በትንሹ የጀመረው የቤንዚን ሰልፍ ከሰሞኑን እጅግ ብሶበታል።

በአንዳንድ ማደያዎች " ቤንዚን የለም " እየተባለ ሲለጠፍ ቤንዚን ያለባቸው ማደያዎች እጅግ በጣም ረጅም ሰልፍ ነው ያለው።

በዚህም ምክንያት የመኪና አሽከርካሪዎች ቀናቸውን በቤንዚን ሰልፍ ለማሳለፍ እየተገደዱ ይገኛሉ።

በሜትር ታክሲ አገልግሎት ላይ የተሰማሩ ዜጎችም ስራቸውን በአግባቡ ለመስራት ተቸግረዋል። ቀናቸውን ሁሉ በቤንዚን ሰልፍ ለማሳለፍ እየተገደዱ ናቸው።

በክልል ከተሞችም የቤንዚን ነገር ብሶበታል።

ቀድሞውንም ቤንዚን በማደያ እንደልብ በማንኛውም ሰዓት ማግኘት የማይቻልባቸው የክልል ከተሞች አሁንም ችግሩ እንዳለ ነው።

በክልል ከተሞች አሽከርካሪዎች ቤንዚን በማደያ " የለም " የሚባሉ ሲሆን በጀርባ ግን በየቦታው በህገወጥ መንገድ በጥቁር ገበያ ቤንዚን ሲቸበቸብ ይታያል።

ይህ ህዝብን እያማረረ ያለው የጥቁር ገበያ የነዳጅ ሰንሰለት መቼ እንደሚበጠስ አይታወቅም። ከዚህ ጀርባ እጃቸው የረዘመ አካላት መኖራቸውን ግን አሽከርካሪዎች ይናገራሉ።

ቤንዚን በክልል ከተሞች ከማደያ ውጭ በእጥፍ ዋጋ ነው የሚቸበቸበው።
ስራ ቀይረው በጥቁር ገበያው ቤንዚን ነጋዴ የሆኑም በርካቶች ናቸው።

@sheger_press
@sheger_press
ሁሌ እንደማደርገው አይቼ ላልፈው ነበር...!

"በነፃነት ያሻን ቦታ መሄድ" የሚለውን ሳይ ግን...

አሁን ላይ ስንቱ ወገን ነው ጠግቦ በልቶ እያደረ ያለው? ስንቱ ነው በነፃነት እያሰበ እና እየተናገረ ያለው? ማነው ከአዲስ አበባ ውጪ ንቅንቅ ብሎ ያሻው ቦታ የሚሄድ? ስንቱ ነው ለፍቶ ጥሮ ያገኘውን ጥሪት በልማት ስም እየተቀማ እና እየፈረሰበት ያለ?

ይሄ አላማ ከስንት አመት በኋላ ይሳካ ይሆን?

መሬት ላይ ካለው ችግር ይልቅ እንዲህ አይነት የተስፈኛ አካሄድ እጅጉን ያስፈራል፣ የባሰው ችግር ገና ወደፊት እንደሆነም ያመላክታል።

#Ethiopia eliasmeseret

@sheger_press
@sheger_press
በመስቀል ደመራ በዓል የተከለከሉ ነገሮችን ለብሶም ሆነ ይዞ መምጣት ክልክል ነው

የዘንድሮው የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም ተከብሮ እንዲያልፍ አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ተደርጎ ወደ ሥራ መገባቱን ጥምር የፀጥታ ኃይሉ አስታውቋል፡፡

በዓሉ ወደሚከበርበት ስፍራ ከበዓሉ አከባበር ጋር ግንኙነት የሌላቸውን ነገሮች ይዞ መምጣት አመፅን የሚቀሰቅሱ እና ተከባብሮ የመኖር እሴትን የሚሸረሽሩ ፅሁፎች ያሉባቸውን አልባሳት ለብሶ መምጣት በአጠቃላይ የተከለከሉ ነገሮችን
ይዞ መምጣትና እንዲሁም ደመራ የማብራት ስነ ስርዓት በሚከናወንባቸው የተለያዩ ቦታዎች ላይ ርችት ማፈንዳት ክልክል መሆኑን ህብረተሰቡ ተገንዝቦ ለፀጥታ ሃይሎች ሥራ ተባባሪ እንዲሆን ጥምር የፀጥታ ኃይሉ አሳስቧል፡፡

@sheger_press
@sheger_press
News ‼️

ግዙፉ መንግስታዊ የቴሌኮም አቅራቢ ድርጅት የሆነዉ ኢትዮቴሌኮም በተወሰኑ ምርትና አገልግሎቶቹ ላይ የታሪፍ ማሻሻያ ሊያደርግ እንደሚችል አስታዉቋል

ተግባራዊ ከተደረገ አንድ ወር ያለፈዉ የማክሮኢኮኖሚ ፖሊሲ ማሻሻያ ተከትሎ የደበንኞችን የመክፈል አቅም ያገናዘበ የታሪፍ ማሻሻያ ለማድረግ መታሰብ ተቋሙ ገልጿል።

የኢትዮቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ፍሬህይወት ታምሩ እንደተናገሩት ሁሉም ደንበኞች እና አገልግሎቶች ላይ ዋጋ አንጨምርም ነገር ግን የደንበኞችን የመክፈል አቅም ያገናዘበ በአንድአንድ ምርትና አገልግሎቶች ላይ የታሪፍ ማሻሻያ ይደረጋል ብለዋል።

የኢኮኖሚ ሪፎርሙን ተከትሎ ወዲያዉ ያልተስተካከለበት ምክንያት የደንበኞቹን አጠቃላይ ደግሞ የማክሮኢኮኖሚ ለዉጥ እንዲረጋጋ በማሰብ መሆኑ ተነግሯል ።

ባለፉት ሁለት አስርት አመታት የብር ዋጋ ከ750% በላይ ሲቀንስ ኢትዮቴሌኮም ባለፉት ስድስት አመታት በከፍተኛ ደረጃ የዋጋ ቅናሽ በማሳየቱ ዋጋው ከአለም ዝቅተኛው እና ለተጠቃሚዎች በጣም ተመጣጣኝ እንዲሆን አድርጎታል። 

እንደ ዋና ስራ አስፈፃሚዋ ገለፃ እ.ኤ.አ በ 2018 ላይ ከ 40 እስከ 50 በመቶ የታሪፍ ቅናሽ ያደረገ ሲሆን በሂደትም የተለያዩ የታሪፍ ማሻሻዎችን ማድረጉን እንዲሁም ፤ የቅርብ ጊዜ ሪፖርቶችንም ደግሞ ከተመለከትን ኢትዮ ቴሌኮም ዝቅተኛ ዋጋ የሚያስከፍል መሆኑን ነው የሚያሳየው ብለዋል።

"ዘለን ታሪፉን ያላስተካከለው የደንበኞቻችንን እንዲሁም በአጠቃላይ የማክሮ ኢኮኖሚ ለውጡ እንዲረጋጋ እና ጤናማ እንዲሆን ስለምንፈልግ ነው” በማለትም ተናግረዋል።

አሁን ላይ ተቋሙ በተለይ በድምፅና በዳታ አገልግሎት ላይ የሚያስከፍለዉ ታሪፍ ርካሽ እንደሆነ ያነሱት ዋና ስራ አስፈፃሚዋ አዲስ የታሪፍ ለማድረግ እንደታሰበ ከመናገር ዉጪ መቼ እንደሚተገበር ግን ከመናገር ተቆጥበዋል።

@sheger_press
@sheger_press
#ሶማሊላንድ #ግብፅ ወደ ሞቃዲሹ  ከባድ የጦር መሳሪያ ማስገባቷን ተከትሎ ማስጠንቀቂያ ሰጠች‼️

የሶማሌ ላንድ መንግስት ግብፅ ለሶማሊያ የምታቀርበውን ከባድ የጦር መሳሪያ አሳሳቢነት በመግለጽ እርምጃው ቀድሞውንም ደካማ የነበረውን የቀጠናውን ደህንነት ይበልጥ አደጋ ላይ ይጥላል ስትል አስጠንቅቃለች።

የሶማሊላንድ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው ይፋዊ መግለጫ፣ “በተለይ የሞቃዲሾ አስተዳደር በብቃት ለማስተዳደር ወይም ለመጠበቅ የሚያስችል አቅም ስለሌለው የእነዚህ መሳሪያዎች ዝውውር በእጅጉ አስደንግጦናል ብለዋል።

ሶማሊላንድ በተጨማሪም ይህ የጦር መሳሪያ ዝውውር የአፍሪካ ቀንድን ወደ አልተረጋጋ ቀውስ እና የጦር መሳሪያ እሽቅድምድም እድልን ከፍ እንደሚያደርግ አፅንዖት ሰጥታለች።

@sheger_press
@sheger_press
2024/09/30 13:31:41
Back to Top
HTML Embed Code: