Telegram Web Link
የትግራይ ግዚያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ሹመት እንዳይሰጥ በትግራይ የፀጥታ ሀይሎች ምክር ቤት ታገደ

የትግራይ ፀጥታ ሃይሎች፥ ፕሬዝዳንት ጌታቸው ረዳ አዲስ ሹመት መስጠትም ሆነ ማውረድ እንዳይችል መታገዱን ሌ/ጄኔራል ታደሰ ወረደ ተናግረዋል።

ይህ እንዲሆን የተወሰነው በትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር እና በደብረፂዮን ገ/ሚካኤል በሚመራው የህወሓት ቡድን መካከል የተፈጠረው ልዩነት እየሰፋ በመሄዱ እንደሆነ ተመላክቷል::

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ይህ ድርጊት የተፈፀመው ከሳምንት በፊት በኦሮሚያ ክልል ባሌ ዞን ጋሰራ ወረዳ ሲሆን፣አንድ የፖሊስ አባል አንድትን ኒቃብ የለበሰች እህት ላይ ከባድ የሆነ የበትር ድብደባ ሲያደርስባት ያሳያል‼️

ሴትየዋ ወደ ፖሊስ ጣቢያ ከተወሰደች በኋላ በዚህ መልኩ ደብድበዋት ከእስር ለቀዋታል።

በስርቆት ወንጀል ተሳትፋለች የሚሉ መረጃዎችም እየወጡ ነው።

ይህ አሰቃቂ ድርጊት ብዙ ወንድሞችና እህቶችን ያሳዘነ ድርጊት ነው።

የሰራችው ነገር ምንም ይሁን ምንም መጠየቅ ያለባት በህግና በህግ ብቻ ነው።

ጥፋቱ👉አንድ ሰው በህግ ቁጥጥር ስር ከዋለ በኋላ ወደ ህግ ማቅረብ እንጂ ድብደባ መፈፀም ወንጀል ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
እንኳን አደረሳቹ

ለመላያው ኢትዮጲያዊያን በሙሉ እንኳን ለአዲሱ አመት በሠላም አደረሳቹ አዲሱ አመት የሰላም፣ የፍቅር፤ የመተሳሰብ የአብሮነት፥ የደስታ እንዲሆንልሆ ኢትዮ መረጃ ከወዲሁ ምኞቱን ይገልፃል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ የሚመራው ኦሎምፒክ ኮሚቴ በ11 ባንኮች ያለውን ሂሳብ እንዳያንቀሳቅስ በፍ/ቤት ታገደ‼️

የኦሎምፒክ ተሳታፊ ብሄራዊ ፌዴሬሽኖችና በታዋቂ ግለሠቦች የተወከሉ የህግ ባለሙያዎች(ህጋዊ ጠበቆች) 
  ትናንት(ሐሙስ) በኢ.ፊ.ድ.ሪ ባህልና ስፖርት ሚኒስቴር፣በዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ እና በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ሥ/አ ቦርድ አባላት ላይ ክስ መመስረታቸው ተከትሎ፣በትናንትናው ዕለት በተጠቀሱት አካላት ላይ የቀረበውን የክስ አቤቱታ የመረመረውና የተመለከተው ፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ላይ የዕግድ ትዕዛዝ አስተላልፏል።

ፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ገንዘብ ያንቀሳቅስባቸዋል ተብለው የተለዩ በሀገሪቱ የሚገኙ 11 ባንኮች ላይ ያለውን ገንዘብ(አካውንት) ከዛሬ ጳጉሜን 5/13/2016 ዓ.ም ጀምሮ ሌላ ውሳኔ እስኪተላለፍ ድረስ እንዳያንቀሳቅስ የዕግድ ትዕዛዝ ተላልፎበታል።

ፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍ/ቤት በቀን 4/13/16 በቁጥር 320687 ባስተላለፈው የዕግድ ትዕዛዝ መሠረት የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣በወጋገን ባንክ፣በአዋሽ ባንክ፣ በአቢሲኒያ ባንክ፣በዳሽን ባንከ፣በህብረት ባንክ፣በንብ ባንክ፣በአባይ ባንክ፣በግሎባል ባንክ፣በኦሮሚያ ህብረት ስራ ባንክ እና በዘመን ባንክ ያለው የባንክ ሂሳብ ቁጥሮች(አካውንቶች)በከሳሽና በተከሳሾች መካከል ባለው ክርክር ላይ ፍ/ቤቱ ውሳኔ እስኪሠጥ ድረስ ሳይንቀሳቀሱ ታግደው እንዲቆዩ ትዕዛዝ ከመሠጠቱም ሌላ ውሳኔው ለሁሉም ባንኮች ዋና መ/ቤቶች ተልኮ እንዲያስፈፅሙ ያዛል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የካርድ ሽልማት

ምሽት 3 ሰዓት በክሪፕቶ ቻናላችን ለባለ ዕድለኞች የካርድ ሽልማት ተዘጋጅቷል።

ይህን ቻናል በመቀላቀል የውድድሩ ተካፋይ ይሁኑ👇

Join us👇👇👇
https://www.tg-me.com/+fzeZ2gn56UE3NTI0
https://www.tg-me.com/+fzeZ2gn56UE3NTI0
https://www.tg-me.com/+fzeZ2gn56UE3NTI0
ህወሓት እና የኤርትራ ባለሥልጣናት

ህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል ሕወሓት እና ኤርትራ መሪዎች ይፋዊ ያልሆነ ዉይይት አካሂደዉ እንደነበር መናገራቸውን ተሰማ።

ደብረፂዮን መቐለ ላይ ባለፈዉ ማክሰኞ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ የኤርትራ ባለሥልጣናት እና ህወሓት የመጀመርያ ዉይይይት የተካሄደዉ በተባበሩት አረብ ኤሜሪትስ ዱባይ ላይ ከስድስት ወር በፊት ነበር።

በዉይይቱ ላይ የትግራይ ጊዜያዊ ክልላዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጌታቸዉ ረዳ ህወሓትን ወክለዉ በዱባይ በተካሔዱ ዉይይቶች ላይ ተካፍለዉ እንደነበር ተናግረዋል።

ደብረፅዮን ቦታና ቀን ሳይጠቁሙ በዱባይ ከመጀመርያው ስብሰባ በኋላ ከኤርትራ መሪዎች ጋር ቀጣይ ስብሰባዎች መደረጉንም አመልክተዋል።

የህወሓት ዓላማ ሰላም ለመፍጠር "የፋኖ ኃይሎችንና የኤርትራን መንግሥት ጨምሮ ከጎረቤቶቻችን ሁሉ ጋር ሰላም መፍጠር" ነዉ ሲሉ መናገራቸዉም ተዘግቧል።

ዶክተር ደብረፅዮን አክለውም ይህ ከኤርትራ መንግስት ባለስልጣናት ጋር የተካሄደው ውይይት በህወሓት ሥራ አስፈጻሚና በጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዕውቅና መካሄዱን ገልጸዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
እናስታውሶ‼️

ምሽት 3 ሰዓት በክሪፕቶ ቻናላችን ለባለ ዕድለኞች የካርድ ሽልማት ተዘጋጅቷል።

ይህን ቻናል በመቀላቀል የውድድሩ ተካፋይ ይሁኑ👇

Join us👇👇👇
https://www.tg-me.com/+fzeZ2gn56UE3NTI0
https://www.tg-me.com/+fzeZ2gn56UE3NTI0
https://www.tg-me.com/+fzeZ2gn56UE3NTI0
ሶማሊላንድ በሀርጌሳ የሚገኘው የግብጽ ባህላዊ ቤተ መጽሃፍት በቋሚነት እንዲዘጋ አዘዘች‼️

ራስ ገዟ ሶማሊላድ የቤተ መጽሃፍቱ ሰራተኞች በ72 ሰዓታት ውስጥ ሀርጌሳን እንዲለቁ አዛለች

ሶማሊላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የተፈራረሙት የወደብ መግባቢያ ስምምነት የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ ተቀማጭነታቸውን በሀርጌሳ ላደረጉ ዲፕሎማቶች አስታውቃለች።
ሚኒስትሩ ለዲፕሎማቶቹ ከኢትዮጵያ ጋር ያደረጉት የወደብ መግባቢያ ስምምነት የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ መድረሱን እና በቅርቡ የትግበራ ስምምነት እንደደረግ መናገራቸው ተገልጿል፡፡

የሶማሊላንድ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴሩ እያይዘውም “የግብጽ ጦር በጎረቤት ሀገር ሶማሊያ መግባቱ ያሳስበናል፣ የግብጽ ጦር በሶማሊላንድ መስፈሩ በአካባቢው ሀገራት የእጅ አዙር ጦርነት እንዲነሳ ምክንያት ይሆናል“ ማለታቸውም ተገልጿል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በቂ ወታደራዊ ሀይል አለን:-የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር‼️

የሶማሊያ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አሊ ባላድ ከአልጀዚራ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣ ሶማሊያ ሀገሯን ለመጠበቅ የሚያስችል በቂ ወታደራዊ ሃይል አላት ሲሉ ተናገሩ::

የግብፅ ወታደሮች በሶማሊያ መኖራቸውን ቢክዱም፣ግብፅ ሽብርተኝነትን እና የሶማሊያን ሉዓላዊነት የሚያደፈርስ ማንኛውንም ነገር ለመዋጋት ታስቦ ወደ ሞቃዲሾ ወታደራዊ መሳሪያዎችን ማቅረቧን አረጋግጠዋል።

@sheger_press
@sheger_press
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ደብረማርቆስ ከተማ የተፈፀመ ‼️
ሁለት ህፃናትን በስለት በመግደል ሊያመልጥ የነበረው ግለሰብ በአካባቢው ማህበረሰብ ተገደለ‼️

በአማራ ክልል ምስራቅ ጎጃም ዞን በደብረ ማርቆስ ከተማ አስተዳደር በአብማ ክፍለከተማ ቀበሌ 01 ልዩ ቦታው የድሮው ከብት ተራ አካባቢ በቀን 01/2017 ዓ.ም ለአለም አሸብር የተባለ ግለሰብ ለ10 አመት ዶርም ተከራይቶ ከሚኖርበት ቤት ውስጥ ሰው አለመኖሩን በማረጋገጥ 1ኛ ናቲ ሰለሞን የተባለውን የ 7አመት ህፃን በስለት በመግደል እና አቢሴሎም ማማሩን የተባለውን በተመሣሣይ እድሜ ላይ የሚገኘውን ህጻን በስለት ወግቶ ጉዳት አድርሶ እናትየዋንም ለመግደል ሲሞክር ጮሃ ሰው ደርሶ ገዳዩን በዱላ መትውት ህይወቱ አልፏል።(ayu)

@sheger_press
@sheger_press
በኮሬ ዞን በእገታ ላይ የነበሩ አራት አርሶ አደሮች በአሰቃቂ ሁኔታ ተገደሉ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኮሬ ዞን በታጣቂዎች ታግተው የነበሩ አራት አርሶ አደሮች በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን የሟች ቤተሰቦች ለዶቼ ቬለ ገለጹ ፡፡ ታጣቂዎቹ ግድያውን ትናንት ሐሙስ የፈጸሙት አርሶ አደሮቹን ለመልቀቅ በመያዣነት የጠየቁትን አንድ መቶ ሺህ ብር እና አንድ ካርቶን የትምባሆ ሲጋራ ከተቀበሉ በኋላ ነው ተብሏል ፡፡

አርሶ አደሮቹ የታገቱት ትናንት ሐሙስ ማለዳ ከብት እያሠማሩ ባሉበት ወቅት መሆኑን ለዶቼ ቬለ የተናገሩት ሦስት የሟች የቅርብ ዘመዶች «ታጣቂዎቹ ወደ ቀበሌው የገቡት ከአጎራባች የኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ጉጂ ዞን በመነሳት ነው ፡፡ ታጋቾቹን ከያዙ በኋላ ካሊያ ተብሎ ወደ ሚጠራው ጫካ ውስጥ ነው ይዘው የሄዱት ፡፡ አንድ መቶ ሺህ ብር እና አንድ ካርቶን የትምባሆ ሲጋራ ከተሰጣቸው እንደሚለቋቸው መልዕክት ልከውብን ነበር ፡፡ በተጠየቅነው መሠረት የተባልነውን ብንልክም ገንዘቡን እና ትምባሆውን ከተቀበሉ በኋላ ገድለዋቸው ሄደዋል ፡፡ ቀብራቸውም ዛሬ ዓርብ እየተፈፀመ ይገኛል» ብለዋል ፡፡

ዶቼ ቬለ በአርሶ አደሮቹ ግድያ ላይ የኮሬ ዞን አስተዳዳሪንም ሆነ የዞኑ ሰላምና ፀጥታ መምሪያ የሥራ ኃላፊዎችን አስተያየት ለማካተት ያደረገው ጥረት አመራሮቹ ስብሰባ ላይ ናቸው በመባሉ ሊሳካ አልቻለም ፡፡ ያም ሆኖ የአርሶ አደሮቹን መገደል በተረጋገጠ የፌስ ቡክ ገጹ የገለጸው የዞኑ መስተዳድር የድርጊቱ ፈጻሚዎች በአካባቢው የሚንቀሳቀሱ ፀረ ሰላም ቡድኖች ናቸው ሲል ዐሳውቋል ፡፡

@sheger_press
@sheger_press
🛑 "ሀገርን ለማስቀጣት የሚደረገው እንቅስቃሴ በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል!"

"ከሳሾች በውሸት ቃለ መሀላ ፍርድ ቤቱን ያሳሳቱ በመሆናቸው ራሳቸው በሕግ የሚጠየቁበት ጊዜ ሩቅ አይሆንም!" 

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ለከሰሱት ጠበቆችና ለአራቱ ከሳሾች ማስጠንቀቂያ ሰጥቷል

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እንኳን ለ2017 አዲስ አመት በሰላም በጤና አደረሳችሁ በማለት መግለጫ ይጀምራል

#Ethiopia  | የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ በተሰጠው ስልጣን እና ተግባር መሰረት ኃላፊነቱን በአግባቡ እየተወጣ ይገኛል ። ይሁን እንጂ በተቋሙ አሰራር የሚረካ እንዳለ ሁሉ ደስተኛ ያልሆነ ወይም ቅሬታ ያለው አካል ሊኖር ይችላል። ይህ በየትኛውም ድርጅት ያለና የሚኖር ነው።

ተቋሙ በስፖርት መድረክ አለመግባባቶች እና ቅራኔዎች ሲኖሩ የሚስተናገዱበት መንገድ  በመተዳደሪያ ደንቡ በግልፅ አስቀምጧል። አንቀፅ 38 ላይ " በኢትዮጵያ ብሔራዊ የኦሎምፒክ ኮሚቴ ውስጥ ወይም በኢትዮጵያ ብሔራዊ የኦሎምፒክ ኮሚቴ እና በአባላቱ መካከል የሚነሱ ማናቸውም ከስፖርት ጋር የተያያዙ ወይም ተቋማዊ ቅራኔዎች በሚመለከታቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ  የኦሊምፒክ ኮሚቴ የአስተዳደር አባላት ( በሜኔጅመንት በቦርድ ወይም በጠቅላላ ጉባኤ ወይም ለዚሁ ችግር አፈታት በሚቋቋም የፍትህ አካል ይፈታል ።

[ ከስፖርት ጋር የተያያዙ ያለመግባባቶችና ቅሬታዎች ከመደበኛ ፍርድ ቤቶች ውጭ ይፈታሉ ።]

ጉዳዩ ለስራ አስፈፃሚ ቦርድ እና / ወይም የኢትዮጵያ ብሔራዊ የኦሊምፒክ ኮሚቴ ከፍተኛ የስልጣን አካል ለሆነው ለጠቅላላ ጉባኤው ይመራል። ጠቅላላ ጉባኤው በቀረበው ጉዳይ ላይ የመጨረሻ ውሳኔ ለመስጠት ወይም ቅራኔውን ለመፍታት የእርቅ ፣ የግልግል ወይም የሽምግልና አካል እንዲሰየም ውሳኔ ሊሰጥ ይችላል ።

በቀረበው ቅራኔ ላይ የተሰጠ ማንኛውም የመጨረሻ ውሳኔ በአቤቱታ መልክ ብቻ ሉዛን ስዊዘርላንድ ለሚገኘው የስፖርት ዳኝነት ፍርድ ቤት ሊቀርብ ይችላል ።

አቤቱታውን ማቅረብ የሚቻለው የሚመለከተው ውሳኔ ከተሰጠ በኋላ በ21 ቀናት ቀነ ገደብ ውስጥ ነው። " ይላል ።

📌 በዚህ መሰረት :-

1ኛ / የስፖርት ነክ ጉዳዮች በመደበኛ ፍርድ ቤት እንደማይታዩ እና መደበኛ ፍርድ ቤት ስልጣን እንደሌላቸው እየታወቀ ህግና ስርአትን ተከትሎ ጥያቄ ማንሳት ሲገባ  የውሸት ቃለ መሀላ በማቅረብ እና ተረኛ ችሎቱን በማሳሳት እግድ ያወጡበት መንገድ ከሳሽ ነን የሚሉት ግለሰቦች ተከራክረው ማሸነፍ የሚችሉበት የእውነተኛ የሕግ መሰረት የሌላቸው መሆኑን ያሳያል።

በተጨማሪም በውሸት ቃለ መሀላ ያገኙትን እግድ ልክ ተከራክረው እንዳሸነፉ መግለጫ መስጠታቸው የቱን ያህል በኃላፊነት እና በተጠያቂነት ስሜት እንደማይሰሩ በግልፅ የሚያሳይ ነው።

ሀገርን ለማስቀጣት የሚደረገው እንቅስቃሴ በአስቸኳይ ሊቆም ይገባል።

2ኛ/ በአለም አቀፉ ኦሊምፒክ ኮሚቴ (IOC) ሙሉ በሙሉ የታገደው እና  እውቅና በግልፅ የተከለከለው እንዲሁም  የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ አባል ያልሆነው በአቶ እያሱ ወሰን የሚመራው የቀድሞው የቦክስ ፌዴሬሽን ከሳሽ ሆኖ መምጣቱ " እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል! "  እንዳለችው እንስሳ ኦሊምፒክ ኮሚቴን ይዤ ልውደቅ ከሚል ክፉ መንፈስ የመነጨ በመሆኑ ይህንን የኢትዮጵያ ሕዝብ እንዲገነዘበው ለመግለፅ እንወዳለን።

3ኛ/ ሻለቃ ሀይሌ ገብረሥላሴ የባለፉትን አራት አመታት የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ምክትል ፕሬዝደንት ሆኖ መቆየቱ ይታወቃል። ነገር ግን ራሱን 'ከደሙ ንፁህ ነኝ' በሚል እና ከዚህ ቀደምም የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት በነበረበት ወቅት ለማናጀሮች እና ለስፖርት ትጥቅ አምራች ካምፓኒዎች  አሳልፎ በመስጠት ብሄራዊ ቡድን ያፈረሰው ራሱ ሆኖ እያለ የስፖርቱ ተቆርቋሪ ሆኖ መምጣቱ እጅግ አሳዝኖናል።

ለመሆኑ ሻለቃ ሀይሌ ገብረሥላሴ የባለፉትን አመታት የት ነበር ?

4ኛ/ ጀግናው አትሌት ገዛኸኝ አበራ የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ምክትል ፕሬዝዳንት እንደሆነ ይታወቃል። በፌዴሬሽኑ ውስጥ ያለበትን የማኔጅመንት ክፍተት ወደ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ይዞ መምጣቱ " ፍየል ወዲህ ቅዝምዝም ወዲያ! " የሚባለው ብሂል ዓይነት ነው።

5ኛ/ ከዚህ ቀደም በኦሊምፒክ ኮሚቴ ውስጥ የስፖርት ትጥቆችን መርካቶ ድረስ ሄደው  በመቸብቸብ በፈፀሙት ሕገ ወጥ ተግባር በኮሚቴው የታገዱ አካላት ይህንን እንደ መልካም አጋጣሚ በመቁጠር ስልጣን በሌለው መደበኛ ፍርድ ቤት ከሳሽ ሆነው መቅረባቸው እጅግ አሳፋሪ ነው ።

6ኛ/ አንዳንድ የሚዲያ ባለሙያዎች ከግለሰቦች ጋር በግልፅ በገንዘብ በመደለል እና በጥቅም በመተሳሰር (ለዚህም በቂ ማስረጃዎች አሉ ) ለህብረተሰቡ የተዛቡ እና ሚዛናዊ ያልሆኑ የአንድ ወገንን መረጃ ብቻ በማቅረብ የስፖርት ቤተሰቡን እያሳሳቱት ይገኛሉ።

እስካሁን በሆደ ሰፊነት ሁሉንም ችለን አልፈነው የነበረ ቢሆንም ከዚህ በላይ መጓዝ ተቋሙን እና አገርን አደጋ ውስጥ ሊከት ስለሚችል እያንዳንዱን ድርጊታቸውን በማጋለጥ በሕግ የምንጠይቃቸው መሆኑን እንገልፃለን።

[  ከህገ ወጥ ድርጊታቸውም እንዲቆጠቡ ስንል በዚሁ አጋጣሚ እናሳስባለን።]

የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ እየተካሄደ ያለውን ግልፅ ሕገወጥ ተግባር የስፖርት ቤተሰቡ ግራ ቀኙን አገናዝቦ እንዲመለከተው ጥሪውን ያስተላልፋል። የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ምርጫ ታገደ ለሚባለው የደረሰን ነገር ባይኖርም በውሸት ቃለመሀላቸው የተሳሳተ ዳኛ ካለ በሕግ አግባብ እናስቀለብሳለን።

ከሁሉም በላይ እነዚህ ከሳሾች በውሸት ቃለ መሀላ ፍርድ ቤት ያሳሳቱ በመሆናቸው ራሳቸው በሕግ የሚጠየቁበት ጊዜ ሩቅ እንደማይሆን እንረዳለን ።
ዳጉ_ጆርናል

@sheger_press
@sheger_press
በእነ ዳንኤል ዮሐንስ ላይ አቃቤ ህግ ክስ መሰረተ

የፍትህ ሚኒስቴር አቃቤ ህግ ዳንኤል ዮሐንስን ጨምሮ በስድስት ግለሰቦች ላይ ሦሥት ክሶችን መሰረተ፡፡

አቃቤ ህግ ለፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ግለሰቦቹ ላይ የመሰረተው ክስ አውሮፕላንን አላግባብ በመያዝ፣ በማህበራዊ ሚደያ አማካኝነት በቀጥታ በማስተላለፍ መልካም ስም የሚያጎድፍ ተንቀሳቃሽ ምስል በኮምፒዩተር ስርአት አማካኝነት በማሰራጨት እና የመንግስት ሰራተኛ ኦፊሻላዊ የስራ ግዴታውን እንዳይፈፅም መቃወም እና አለመታዘዝ የሚሉ ናቸው፡፡

በሁለቱ ወንጀሎች ሁሉም ሲከሰሱ የመዝገቡ መጠሪያ የሆነው በቲክክቶክ የሚታወቀው ዮሀንስ ዳንኤል በሶስቱም ተከሷል፡፡

ለሁለት ሰአታት ሙሉ ከአውሮፕላን አንወርድም፤ ይከስከስ በማለት ሌሎችም እንዳይወርዱ በማሳደም በቲክቶክ ቀጥታ በማሰራጨት ሳይታገት ታግቻለሁ በማለት በቲክቶክ ስሙ ዮኒ ማኛን ቀጥታ በማስገባት የአየር መንገዱ ስም እንዲጎድፍ አድርጓል የሚለውንም አቃቤ ህግ ዘርዝሮበታል፡፡

@sheger_press
@sheger_press
በአፋሮችና ሶማሌዎች መካከል ሲካሄድ የቆየው የጎሳ ግጭት እንደቆመ ለግጭቱ መፍትሄ ለመስጠት የተቋቋመው ብሄራዊ ኮሚቴ መግለጡን ፋና ብሮድካስት ዘግቧል።

ብሄራዊ ኮሚቴው፣ በግጭት አካባቢዎች በመከላከያና ፌደራል ፖሊስ ቁጥጥር ሥር የኾነ ነጻ ቀጠና እንደተቋቋመና ግጭቶችን ማስቆ እንደተቻለ ኮሚቴው መናገሩን ዘገባው አመልክቷል።

የሰላም ሚንስትር ብናልፍ አንዷለም፣ ከነጻ ቀጣናው ያልወጡ ቀሪ ታጣቂ ኃይሎች ባስቸኳይ እንዲወጡ ማድረግና በአወዛጋቢ አካባቢዎች ሠፈራዎችን ማቆም እንደሚያስፈልግ አሳስበዋል ተብሏል።

@sheger_press
@sheger_press
#በኦሮሚያ ክልል መቂ ከተማ‼️

በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ሸዋ ዞን በመቂ ከተማ ጳጉሜ 2/2016 ዓ.ም በተፈጸመ ጥቃት ቢያንስ የ4 አሽከርካሪዎች ሕይወት ሲያልፍ ከ30 በላይ ተሸከርካሪዎች ደግሞ ጉዳት ማስተናገዳቸውን ከጥቃቱ ያመለጡ እማኞች ተናገሩ፡፡

ጥቃት አድራሾቹ የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ታጣቂዎች እንደሆኑ ቢገለፅም ጥቃት ያደረሱት የኦሮሚያ ክልል ልዩ ሀይል መለዮ የለበሱ ናቸው ሲሉ ከጥቃቱ ያመለጡ አሽከርካሪዎች ተናግረዋል።

@sheger_press
@sheger_press
ሚድሮክ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 400 ሰራተኞቹ ለእያንዳንዳቸው ከ100 እስከ 500 ሺህ ብር ስጦታ አበረከተ

👉 ሼህ መሀመድ ሁሴን አላሙዲን ለሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሰራተኞችና አመራሮች ምስጋና አቅርበዋል



ሼህ መሀመድ ሁሴን አላሙዲን የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ ሰራተኞች እና አመራሮች ላከናወኑት ተግባር ምስጋና አቅርበዋል።

የሜድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በዛሬው ዕለት በሚሊኒየም አዳራሽ የላቀ አፈጻጸም ላሳዩ አመራሮችና ሰራተኞቹ እውቅና ሰጥቷል።

በዚሁ ወቅት ሼህ መሀመድ ሁሴን አላሙዲን በዙም ባስተላለፉት መልዕክት፤ የተቋሙ ሰራተኞች እና አመራሮች ላከናወኑት ተግባር ምስጋና አቅርበዋል።

ሼህ መሀመድ ሁሴን አላሙዲን በቅርቡ ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡም ገልፀዋል።

በመድረኩ ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በ2016 በጀት ዓመት የዕቅዱን 90 በመቶ ማሳካቱ ተጠቅሷል፡፡

ተቋሙ የላቀ ውጤት ላስመዘገቡ 400 ሰራተኞቹ ለእያንዳንዳቸው ከ100 እስከ 500 ሺህ ብር ስጦታም አበርክቷል።

#ዳጉ_ጆርናል

@sheger_press
@sheger_press
በመዲናዋ የ2017 የትምህርት ዘመን በመጪው ሰኞ ይጀመራል

በአዲስ አበባ ከተማ የ2017 የትምህርት ዘመን የፊታችን ሰኞ መስከረም 6 ቀን 2017 ዓ.ም እንደሚጀመር የከተማው ትምህርት ቢሮ አስታውቋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ የ2017 የትምህርት ዘመን በመጪው ሰኞ በሁሉም ት/ቤቶች የሚጀመር መሆኑንም የቢሮው መረጃ ያመላክታል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/09/29 11:29:53
Back to Top
HTML Embed Code: