Telegram Web Link
ክቡርነትዎ፣

ሀገራችን ለም እና ቆንጆ ናት። ይሁንና:

- ህዝቡ ልጆቹን ሞፈር አሸክሞ 'ሰላም አውርዱልን' እያለ ከፈጣሪው አልፎ የሰው ልጅን እየለመነ ነው፣

- በትናትናው እለት ብቻ ሰሜን ሸዋ ላይ በርካታ ሰዎች ታግተው ተወስደዋል፣ በየቀኑ ለቁጥር የሚታክቱ ዜጎች በታጣቂዎች እንደ እንስሳ እየተነዱ ወደ ጫካ ይወሰዳሉ፣

- እርስዎ የወጡበት የአማራ ክልል ውስጥ እንኳን በየቀኑ ለቁጥር የሚታክት ህዝብ በጥይት እያለቀ ነው፣

- በጦርነት የተዳከመ በሚሊዮን የሚቆጠር ህዝብ በኑሮ ጫና እያለቀሰ ነው፣

- ዛሬ እንኳን ወደ ኦሞ ዞር ብንል ወንዝ ሞልቶ ህዝብ ከዛሬ ነገ ተዋጥኮ ብሎ የድረሱልኝ ጩኸት እያሰማ ነው።

እውነት አሁን ያለንበት ግዜ የምድር ገነት መሆናችንን እንድናስብ እና ውበቷን እንድናጣጥም የሚያረገን ነው አንገት የሚያስደፋ ሁኔታ ውስጥ ነን?

We need some soul searching!

EliasMeseret

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
🚨ATTENTION!!! 🚨

🌀 የዋጋ ግሽበት ከመቼውም በላይ እየጨመረ ይገኛል :: #Ethiopia ከዓለም በዋጋ ግሽበት 10 ኛ ደረጀ ላይ ተቀምጣለች :: በዚህ አስቸጋሪ ወቅት ፤ ብሮትን ባንክ ውስጥ በማስቀመጥ በየሰከንዱ ዋጋ ሲያጣ አትዩት!!

🌀 ብሮትን አሰሩት፤ በኢትዮጵያ ትልቁ የኢኮኖሚ ሴክተር ላይ ኢንቨስት በማረግ በያመቱ ትርፍ የውሰዱ!!!

"ታሞ ከመማቀቅ አስቀድሞ...."
💰💰 አክሲዮን ድርሻዎችን በመግዛት የግዙፍና አትራፊ ድርጅቶች ባለቤት ይሁኑ፣ለልጅ ልጅ የሚተላለፍ ሐብት ያፍሩ፣ገንዘብዎትን ከግሽበት ይጠብቁ፤እጥፍ ድርብ ትርፍ ያግኙ!

💰💰 በኢትዮጵያ የባንክ ዘርፍ ኢንቨስት በማድረግ በአማካይ ከ30 እስከ 45 ፐርሰንት(Dividend + Capital gain) ትርፍ ማግኘት ይቻላል!

🛑የባንክ ባለቤት በመሆን 30%-45% ማትረፍ ይፈልጋሉ?
🛑መሉ መረጃውን ከላይ በፎቶ ተያይዞዋል ፈጥነው አክሲዮን በመግዛት አትራፊ ይሁኑ ለበለጠ መረጃ ከታች ባለው ስልክ መደወል ይችላሉ።
  📲0913013439📲
  📲0913013439📲

ለበለጠ መረጃ በTelegram ይቀላቀሉን:
👉 www.tg-me.com/stockBKGH or
👉 www.tg-me.com/stockEthio
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር፤ የመንግስት መ/ቤቶች ንብረት ያላግባብ በሀላፊዎች እጅ እንደሚገኝ በኦዲት መረጋገጡ ተገለጸ!

የኦዲት ምርመራው 13 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት በሀላፊዎች እጅ እንደሚገኝ አሳይቷል፡፡በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 269 ተቋማት ላይ በተደረገ የንብረት ቆጠራ ወደ 24 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት በጉድለት መገኘቱም ተጠቁሟል።ጉድለት የተገኘባቸው የተቋማት ሃላፊዎች ላይም እርምጃ እንደተወሰደባቸውም ተነግሯል።

የአዲስ አበባ ከተማ የመንግስት ንብረት አስተዳደር_ባለስልጣን የህንፃና ንብረት ኦዲት ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ምሩጽ ታዬ፤ በተቋማቶች ላይ ከተገኘው ጉድለት ውስጥ ወደ 10.9 ሚሊዮን ብር የሚገመት ንብረት እንዲመለስ ተደርጓል ብለዋል።አቶ ምሩፅ አያይዘውም በተቋማቱ ከተመዘገበው ንብረት ላይ ጉድለት የተገኘባቸው ሃላፊዎች ከስራ ገበታ እንዲባረሩ እና በህግ እንዲጠየቁ ተደርጓል ማለታቸውን የሸገር ሬድዮ ዘገባ ያሳያል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ፑቲን እንዲታሰሩ ተጠየቀ❗️

ዩክሬን የሩሲያው ፕሬዝደንት ብላድሚር ፑቲን በሚቀጥለው ሳምንት ሞንጎሊያን በሚጎበኙበት ወቅት ሀገሪቱ በቁጥጥር ስር እንድታውላቸው ጠይቃለች።

ፑቲን አለምአቀፉ የወንጀለኞች ፍርድ ቤት(አይሲሲ) የእስር ማዘዣ ካወጣባቸው ወዲህ የፍርድ ቤቱ አባል ወደ ሆነች ሀገር የሚያደርጉት ይህ ጉብኝት የመጀመሪያቸው ይሆናል።
ፍርድ ቤቱ በፑቲን ላይ የእስር ማዘዣ ያወጣባቸው የዩክሬን-ሩሲያ ጦርነት ከተጀመረ ወዲህ የዩክሬን ህጻናትን ያለፍቃዳቸው ወደ ሩሲያ በመውሰድ የጦር ወንጀል ፈጽመዋል በሚል ምክንያት ነው።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጥቆማ‼️

ቴሌግራምን በመጠቀም ብቻ በርካቶች በርካታ ብር በማግኘት ላይ ናቸው።

እናንተም ይህን ቻናል በመቀላቀል ሙሉ ትምህርት ማግኘት ትችላላቹ።

Join us👇👇👇👍
https://www.tg-me.com/+fzeZ2gn56UE3NTI0
https://www.tg-me.com/+fzeZ2gn56UE3NTI0
ባጃጅ ተሽከርካሪዎች የሰሌዳ ለውጥ ማድረግ እንደሚጠብቅባቸው የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አሳሰበ

AMN - ነሐሴ 25/2016 ዓ.ም

በአዲስ አበባ ከተማ የሚገኙ የባለሶስት እና አራት እግር ወይም ባጃጅ ተሽከርካሪዎች የሰሌዳ ለውጥ ማድረግ እንደሚጠብቅባቸው የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ አሳስቧል።

ቢሮው በአዋጅ በተሰጠው ስልጣንና ኃላፊነት መሰረት የከተማዋን የትራንስፖርት አገልግሎት አሰጣጥ በበላይነት ይመራል፣ ይቆጣጠራል እንዲሁም የአሰራር ስርዓት ይዘረጋል።

ቢሮው አሁን ያለውን የባለሶስት እግር ወይም ባጃጅ ተሽከርካሪዎችን የሕግ ጥሰቶችን እና የደንብ መተላለፎችን ለመከላከል እና አገልግሎት አሰጣጡን ለመቆጣጠር እንዲያስችል ከዚህ ቀደም በህጋዊ ማህበር በመደራጀት አገልግሎት እየሰጡ የሚገኙ ባለንብረቶች ተሽከርካሪው ከነበረበት ክልል ክሊራንስና የአዲስ አበባ ነዋሪነት ማረጋገጫ መታወቂያ በማቅረብ ምትክ የአዲስ አበባ ሰሌዳ ማውጣት እንደሚገባ አሳውቋል።

ይህንን አሟልተው እስኪገኙ ማንኛውም የባጃጅ ተሽከርካሪዎች በከተማዋ ከነገ ጀምሮ ሙሉ በሙሉ አገልግሎት መስጠት እንደማይችሉ ቢሮው በጥብቅ አሳስቧል።

ወደ አገልግሎት ለመመለስ ቀደም ሲል አገልግሎቱን ሲሰጡበት ከነበረው የትራንስፖርት ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አስፈላጊውን ህጋዊ መረጃ በማሟላት ቢሮው በሚያስቀምጠው የአሰራር ስርዓት መሰረት አገልግሎቱን መስጠት እንሚቻል ቢሮው በማኅበራዊ ትሥሥር ገጹ ባወጣው መልዕክት አሳውቋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በኦሮሚያ ክልል የጅማ ዞን አስተዳደር ከሁለት ወረዳዎች ለመሬት መንሸራተት አደጋ ተጋላጭ የኾኑ ነዋሪዎችን በሌላ አካባቢ ማስፈር መጀመሩን አስታውቋል።

ሰሞኑን ባከባቢው የጣለውን ከባድ ዝናብ ተከትሎ፣ ጎማ እና ጌራ በተባሉ ወረዳዎች የተለያዩ ቀበሌዎች የመሬት መንሸራተት አደጋዎች ተከስተዋል።

የዞኑ አስተዳደር፣ ከጌራ ወረዳ 591 ነዋሪዎችን እና ከጎማ ወረዳ ደሞ 330 ነዋሪዎችን በማንሳት በሌሎች አካባቢዎች እያሠፈረ እንደሚገኝ ገልጧል።

በዞኑ፣ ሰቃ ጨቆርሳ፣ ሸቤ ሶምቦ፣ ሰጠማ እና ነዲ ጊቤ የተባሉ ወረዳዎሽም የመሬት መንሸራተት ስጋት እንዳለባቸውና በአደጋዎች ጉዳት እንዳይደርስ የቅድመ መከላከል ሥራ እየተሠራ ነው ተብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
News ‼️

ብሔራዊ ባንክ የዉጪ ምንዛሪ ቢሮ ፍቃድ መስጠት የሚያስችለውን ሂደት መጨረሱን ገለፀ‼️

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከዚህ ቀደም መደበኛ ባልሆነ መንገድ የዉጪ ምንዛሪ ላይ የሚሳተፉ አካላትን ህጋዊ ሆነዉ ፍቃድ አዉጥተዉ መስራት እንዲችሉ መፍቀዱን ተከትሎ ከወዲሁ ብዙ ሰዎችና ኩባንያዎችን እየተቀበለ እንደሚገኝ አስታዉቋል።

የዉጪ ምንዛሪ ገበያ ዉስጥ የሚሳተፉ በፊት ባንኮች ብቻ የነበሩ ቢሆንም አሁን ግን ከባንኮች በተጨማሪ ሌሎች በግላቸው በዘርፉ ላይ ለመሰማራት የሚፈልጉ አካላት እንዲሰሩ ተደርጓል።

ባንኩ የውጭ ምንዛሪ ክትትልና መጠባበቂያ አስተዳደር ምክትል ዳይሬክተር አቶ አበባየሁ ዱፈራ እንደተናገሩት  " የዉጪ ምንዛሪ ዚሮዉን ለመክፈት ፍላጎት አሳይተዋል ያላቸዉን ሰዎች መቀበሉን " የገለፁ ሲሆን ከንግድ ሚኒስትር ጋር ያለዉ ጉዳይ ከተፈታ ወዲያው ፍቃድ መስጠት እንጀምራለን በእኛ በኩል ሁሉም ነገር አልቋል ሲሉ ተደምጠዋል ።

እንደ ምክትል ዳይሬክተሩ ገለፃ "ኢትዮጵያ ዉስጥ የሚኖሩ የዉጪ ሀገር ዜጎችም አካዉንት ከፍተዉ ሲፈልጉ ብቻ ወደ ብር ቀይረዉ እንዲጠቀሙ ተፈቅዷል " ይህም በድፍረት የተደረገ ነዉ ማለት ይቻላል ሲሉም እርጃዉን አድንቀውታል።

ሀገር ዉስጥ ያሉ ማንኛውም የዉጪ ምንዛሪ የሚያገኙ ግለሰቦች በትንሹ  በ 100 ዶላር የዉጪ ምንዛሪ አካዉንት መክፈት እንደሚችሉ የጠቆሙት አበባየሁ ዱፈራ ይህ ጥቅሙ ለግለሰቦች ሳይሆን ሀገርም ጭምር ተጠቃሚ ይሆናል ብለዋል።
#Capital

@sheger_press
@sheger_press
የግብፅ ነገር‼️

የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አምስተኛ ምዕራፍ ሙሌትን በመቃወም ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ፕሬዝዳንት በዛሬው ዕለት ደብዳቤ አስገብተዋል።

በደብዳቤው ላይ ኢትዮጵያ የአንድ ወገን ፖሊሲዎችን እየተገበረች ነው፣ይህ ደግሞ የዓለም አቀፍ ህግ መርሆዎችን የሚጥስ ነው በማለት ለፀጥታው ምክር ቤት ደብዳቤ መላካቸውን ከግብፅ ሚዲያዎች ያገኘሁት መረጃ ያመላክታል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መንግሥት መፍትሔ ያልሰጠው ግን በተደጋጋሚ የቀረበ ጥያቄ👇

👉"ሰራተኛው ኑሮውን እንዴት እንደሚመራ ግራ ተጋብቷል" ኢሰማኮ

የዝቅተኛ ደመወዝ ወለል አለመወሰን ለሰራተኞች የመኖር እና የአለመኖር ጉዳይ ሆኗል ሲሉ የኢትዮጵያ ሰራተኛ ማህበራት ኮንፌዴሬሽን (ኢሰማኮ) ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፎሎ አስታወቁ።

በአሁኑ ወቅት በዝቅተኛ ደረጃ የሚገኙ ሰራተኞች ደመወዝ 5 ሊትር ዘይት እንኳን አይገዛም ያሉት የኢሰማኮ ፕሬዝዳንት አቶ ካሳሁን ፤ በተለይ የፋብሪካ ሰራተኞች ለከፋ ችግር መዳረጋቸውን አብራርተዋል።

አቶ ካሳሁን ዝቅተኛ የደመወዝ ወለል እንዲስተካከል የቀረቡ ተደጋጋሚ ጥያቄዎች ምላሽ አለማግኘታቸውንና በቅርቡም ጥያቄው በድጋሚ ለመንግስት መቅረቡን ተናግረዋል።

ኮንፌደሬሽኑ ከዝቅተኛ ደመወዝ ወለል ባሻገር የገቢ ግብር ቅነሳን የሚመለከት ጥያቄ ቢኖረውም በአፋጣኝ ይመለሳሉ ወይ በሚለው ዙሪያ ስጋት አለው ያሉት ፕሬዝዳንቱ ለሰራተኛው በቶሎ መልስ ይሰጠው ዘንድ ጠይቀዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የሱማሊያዉ ፕሬዝዳንት ክተት አወጁ‼️

የሱማሊያዉ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼህ መሀመድ ሁሉም የሶማሊያ ዜጋ እና አመራር ለወታደራዊ ግዳጁ ይዘጋጂ ሲሉ ቀጭን ትእዛዝ አስተላልፈዋል ፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መረጃ‼️

እስካሁን ከ1,000 በላይ የግብፅ ኮማንዶዎች ሶማሊያ ማረፋቸውን የተባበሩት አረብ ኢምሬትስ የዜና አገልግሎት መረጃ ያመላክታል።

ትናንት የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ባድር አብደላቲ የታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ አምስተኛ ምዕራፍ ሙሌትን በመቃወም ለተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ደብዳቤ ያስገቡ ሲሆን በደብዳቤው ላይ "ግብጽ ኢትዮጵያ በአባይ ወንዝ ላይ እየገነባች ባለችው ግድብ ምክንያት የውሃ ደኅንነቷን ለማረጋገጥ አስፈላጊው የሆነ እርምጃ የመውሰድ መብት አላት"ብለዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ አስመራ የሚያደርገውን በረራ አቋረጠ

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ኤርትራ ዋና ከተማ አስመራ የሚያደርገውን በረራ ከነገ ጀምሮ እንደሚያቋርጥ አስታውቋል፡፡

አየር መንገዱ በረራውን ያቋረጠው በኤርትራ ውስጥ አገልግሎቱን ለመስጠት ባጋጠመው ከአቅም በላይ በሆነ የአሰራር ችግር ነው፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ዜና ሹመት

የአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ለተለያዩ የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ሹመት ሰጥተዋል።

በዚህ መሠረት፦

1. አቶ አወቀ አስፈሬ ሁነኛው - የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ

2. አቶ ተስፋሁን ሲሳይ መንግስቴ - የምዕራብ ጎንደር ዞን ዋና አስተዳዳሪ

3. አቶ ማስተዋል አሰሙ ወንድማገኘሁ - በዞን ምክትል አስተዳዳሪ ማዕረግ የሰሜን ጎጃም ዞን ዋና አስተዳዳሪ የሕዝብ ግንኙነትና አደረጃጀት አማካሪ

4. አቶ ጌታዬ ሙጬ ደርሰህ - የሰሜን ጎጃም ዞን ገቢዎች መምሪያ ኃላፊ በመሆን ተሹመዋል፡፡

ተሿሚዎች በተለያዩ የመንግሥት የሥራ ኃላፊነቶች የሠሩ ሲሆን የላቀ ዕውቀት፣ ብቃት፣ ቁርጠኝነት እና ታታሪነት ያላቸው ስለመሆኑም ተገልጿል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በኢትዮጵያ ሲሰለጠኑ የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ የሶማሊላንድ ብሔራዊ ጦር አባላት ስልጠናቸውን አጠናቀው መመረቃቸው ተገለጸ

ስልጠና ሲሰጣቸው የነበሩ በሺዎች የሚቆጠሩ #የሶማሊላንድ ብሔራዊ ጦር አዳዲስ ምልምል አባላት ከኢትዮጵያ መከላከያ ማሰልጠኛ ማዕከል ስልጠናቸውን ጨርሰው መመረቃቸው ተገለጸ።

ነሃሴ 24 ቀን 2016 ዓ.ም የተመረቁት የሶማሊንድ ወታደሮች በኢትዮጵያ ከአንድ አመት በፊት ጀምሮ በተከታታይ ዙር የተጠናከረ ስልጠና ሲሰጣቸው ከነበሩ የሀገሪቱ ጦር አባላት መካከል መሆናቸውን እና 8ኛ ዙር ሰልጣኞች መሆናቸውን ሆርን ዲፕሎማት በድረገጹ አስነብቧል።

በታላቅ ድምቀት በተካሄደው የምረቃ ስነ ስርዓት ላይ የሁለቱም ሀገራት ከፍተኛ ባለስልጣናት መታደማቸውን የጠቆመው ዘገባው በሶማሌላንድ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ወታደራዊ ትብብር አጉልቶ ያሳየ ነው መባሉን አስታውቋል።

በምረቃ ስነስርአቱ ላይ በክብር ከታደሙት እንግዶች መካከል የሶማሌላንድ ብሄራዊ ጦር አዛዥ ሜጀር ጄኔራል ኑህ እስማኤል ታኒ ይገኙበታል ያለው የድረገጹ ዘገባ የጦር አዛዡ በምረቃ ስነ-ስርዓት ላይ መገኘት ሶማሌላንድ ብሔራዊ የመከላከያ አቅሟን ለማጠናከር ቁርጠኛ መሆኗን ያሳየ ነው ነው ሲል ገልጿል።ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በርካታ የሶማሊላንድ ወታደሮች በተከታታይ በኢትዮጵያ ስልጠና መውሰዳቸውንም አውስቷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/09/29 19:23:24
Back to Top
HTML Embed Code: