Telegram Web Link
ፒያሳ የሚገኘው የመብራት ሀይል ህንፃ የንግድ ቤት ኪራይ ጨረታ በካሬ 19ሺ ብር መቅረቡ ተሰማ

በአዲስ አበባ ፒያሳ የሚገኘው የመብራት ሀይል ህንፃ ለንግድ ቤቶች ኪራይ ጨረታ መቅረቡን ተከትሎ በካሬ 19ሺ ብር እየተጫረተ መሆኑን የወጡ መረጃዎች ያመላክታሉ፡፡

ይህ የብር ተመን የቀረበው 40 ካሬ ላለዉ ምድር ላይ ለሚገኘው የንግድ ቤት ሲሆን አሸናፊው ቫት እና የጋራ ወለል ኪራይን ሳይጨምር በወር 760 ሺህ ብር ይከፍላልም ተብሏል ።
<< ምላሽ ባለማግኘታችን ለጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዳግም ደብዳቤ ጽፈናል >> - የኢሰማኮ ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ‼️

ዝቅተኛ የደሞዝ ወለል፣ የገቢ ግብር ቅነሳ፣ መንግስት አደርገዋለሁ ያለው የደመወዝ ማሻሻያና ተዛማጅ ጉዳዮችን በተመለከተ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ደብዳቤ ማስገባታቸውን የኢትዮጵያ ሠራተኞች ማህበራት ኮንፌደሬሽን ገለፀ ።
<< ረሃብ ጊዜ አይሰጥም >> የሚሉት ፕሬዝዳንቱ << መንግስት የደመወዝተኛ ሰራተኛውን የህልውና ጥያቄ እንዲመለስ >> አበክረው ጠይቀዋል።

ባለፈው 2015 ዓመት ነሐሴ መገባደጃ ከጠቅላይ ሚኒስትር ዐብይ አህመድ(ዶ/ር) ጋር በጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት ቢወያዩም፣ አቅጣጫ ቢቀመጥም እስካሁን ተግባራዊ ሊሆን አልቻለም።

ይህን ተከትሎ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይፋዊ ደብዳቤ ዳግም ለመፃፍ መገደዳቸውን የኢሰመኮ ፕሬዝዳንት ካሳሁን ፎሎ ለአሻም ቲቪ ተናግረዋል።

@ethio_mereja_news
በኢትዮጵያ አየር መንገድ አደጋ የተከሰከሰው የቦይንግ 737 ማክስ 85 አውሮፕላን ከአደጋው በፊት የኤሌክትሪክ ችግሮች እንዳሉበት የሚያሳየውን መረጃ መደበቁን የቀድሞ የቦይንግ ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ።

ፋውንዴሽን ፎር አቪየሽን ሴፍቲ የተባለ ቡድን የሚመሩት የቦይንግ የቀድሞ ሥራ አስኪያጅ ለ157 ሰዎች እልቂት የሆነው እና ከስድስት ዓመት በፊት በኢትዮጵያ የተከሰከሰው 737 ማክስ 9 አውሮፕላን የኤሌክትሪክ ችግሮች እንዳሉበት በኩባንያው ይታወቅ ነበር ብለዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በዝቅተኛ ከፍታ ላይ ከቁጥጥር ውጭ ሊሆን እንደሚችል እና በርካታ እክሎች እንደነበሩበት ይፋ አድርገዋል።

ፋውንዴሽኑ በአሁኑ ወቅት እየበረሩ ያሉ ከ1000 በላይ የቦይንግ አውሮፕላኖች በሚመረቱበት ወቅት በነበሩ ችግሮች ምክንያት የኤሌክትሪክ ብልሽት ስጋት እንደተጋረጠባቸው ገልጿል።

ከቦሌ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ተነስቶ ጉዞውን በጀመረ በስድስት ደቂቃዎች ውስጥ የተከሰከሰው አውሮፕላን የኤሌክትሪክ ብልሽቶች ነበሩበት ብለዋል።

አውሮፕላኑ በተከሰከሰበት ወቅት አዲስ ሞዴል 737 ማክስ 9 ነበር።

ከዚያ ቀደም ብሎ ተመሳሳይ 737 ማክስ 9 አውሮፕላን በኢንዶኔዥያው አየር መንገድ አደጋ ተከስክሶ የ189 ሰዎች ሕይወት ተቀጥፏል።(መረጃው የቢቢሲ ነው።)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሰሜን ጎንደር : በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ
የ10 ሰዎች ሕይዎት አልፏል!

ነሐሴ 18/2016 ዓ.ም በሰሜን ጎንደር ዞን ጠለምት ወረዳ አብና ቀበሌ ልዩ ስሙ ኖላ በተባለ ቦታ ነሐሴ 18/2016 ዓ.ም በደረሰ የመሬት መንሸራተት አደጋ በሰው ሕይዎት ላይ ጉዳት ደርሷል።

በአደጋው የ10 ሰዎች ሕይዎት አልፏል ያሉት የጠለምት ወረዳ የመንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ተስፋየ ወርቅነህ ናቸው።

ኀላፊው ከአሚኮ ጋር በስልክ በነበራቸው ቆይታ የአራት ሰዎች አስከሬን በፍለጋ ተገኝቷል ብለዋል። የቀሪ ስድስት ሰዎች አስከሬን ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ጊዜ ድረስ ሊገኝ አልቻለም ነው ያሉት።

በጉዳቱ በስምንት ሰዎች ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል ያሉት ኀላፊው በደጃች ሜዳ ጤና ጣቢያ የሕክምና እርዳታ እየተደረገላቸው ነው ብለዋል።

በመሬት መንሸራተት አደጋው ከ35 በላይ የቤት እንሰሳት ሞተዋል። ከ30 ሄክታር በላይ በሰብል የተሸፈነ መሬት ጉዳት ደርሷል ተብሏል።

እንደ አቶ ተስፋየ መረጃ በደረሰው አደጋ 480 አባውራዎች እና 2 ሺህ 400 የቤተሰብ አባላት ከመኖሪያ ቤታቸው ተፈናቅለዋል። በቀበሌው ማዕከል ወደሚገኙ ማኅበራዊ ተቋማት በጊዜያዊ እንዲጠለሉ መደረጉንም ኀላፊው ጠቁመዋል።

ኀላፊው አያይዘውም በቀጣይም የመሬት መንሸራተት አደጋ ሊከሰትባቸው ይችላሉ በተባሉ የኖላ፣ ላጌ፣ ውፋ፣ ኩዳድ እና ጅብ ዋሻ አካባቢዎች የሚኖሩ ወገኖች ጥንቃቄ እንዲያደርጉም አሳስበዋል።

አሁን ካለው ከባድ የዝናብ ስርጭት አንጻር ማኅበረሰቡ ከጎርፍ እና መሰል አደጋዎች ጥንቃቄ ማድረግ እንዳለበት ያሳሰቡት ኀላፊው ለተፈናቃዮች አፋጣኝ የሰብዓዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ነው ያሉት።
@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የTelegram መስራች የሆነው Pavel Durov ታስሯል ‼️

በሰላም እንዲፈታ ፀሎታችን ነው።(ሸገር ክሪፕቶ)

@ethio_mereja_news
ከሸዋ አካባቢ የሚወጡ ፈጣን እና ታማኝ መረጃዎችን እንዲሁም የጦር ግንባር ዜናዎች የምታገኙበት ምርጥ ቻናል

ልጠቁማችሁ👇👇👇
   https://www.tg-me.com/SNN_merja
   https://www.tg-me.com/SNN_merja
ሰበር ዜና

በሊባኖስ የሚገኘዉ ይስራኤል ዋነኛ ባላንጣዉ ሄዝቦላ እስራልን በእሳት አጠባት፡፡

የኢራኑ ሄዝቦላህ እስራኤል ላይ የበቀል ጥቃቱን ዛሬ ለሊቱን መጀመሩን ሁሉም ይወቅልኝ ብሏል። የሄዝቦላህ አለቃ ሃሰን ነስረላህ አሁን የበቀል ሰይፋችን መውረድ ይጀምራል ብለው በቴሌቭዥን መስኮት ብቅ ባሉ በግማሽ ሰዓት ልዩነት ከሊባኖስ ወደ እስራኤል የሮኬት፣ ሚሳኤል እና ድሮን በረዶ ዘንቧል።

ባለፈዉ ወር መጀመሪያ ላይ በቤይሩት አቅራቢያ እስራኤል የሄዝቦላህ የጦር ኮማንደርን ለገደለችበት አፀፋ ነዉ በሚል በዛሬዉ ንጋት ላይ 320 የሚጠጉ ሮኬቶችንና ድሮኖችን አዝንቦ 11 የእስራኤል ወታደራዊ ጣቢያዎችን መምታቱን ዘ ጋርዲያን ዘግቧል፡፡

የሂዝቦላህ ዶፍ መዝነቡን ያየው የእስራኤል አየር ሃይልም በአንድ ግዜ 6 የሚጠጉ አሜሪካ ሰራሾቹን ኤፍ-15 ተዋጊ ጀቶችን ክተት ብሎ ወደ ሊባኖስ ጥሰው በመግባት ሊባኖስን እንደ ደረሰ ሰብል በሚሳኤልና ቦምብ ሲያጭዳት ታይቷል። በዚህ የእስራኤል ጥቃትም 40 የሚጠጉ የሄዝላህ ወታደራዊ ስፍራዎችን ማዉደሙን አስታዉቋል፡፡

የእስራኤል ከፍተኛ ወታደራዊ ቃል አቀባይ ሪር አድሚራል ዳንኤል ሃጋሪ በደቡባዊ ሊባኖስ ውስጥ “በደርዘን የሚቆጠሩ” የጦር አውሮፕላኖች የሄዝቦላህ መሸሸጊያ የሆኑ ኢላማዎችን እየመቱ ነዉ ሲሉ ገልፀዋል።
@ethio_mereja_news
በደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት ማንኛውም አይነት የስልጣን ሹምሽር አልቀበልም ብሏል!!

በእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) የሚመራው ህወሓት " በማንኛው የሃላፊነት እርከን በራስ ፍላጎት የሚደረግ የስራ ምደባና ሹምሽር ተቀባይነት የለውም " ብሏል።

የእነ ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር) ህወሓት ለሁሉም የዞንና የወረዳ የድርጅቱ ፅህፈት ጠቅሶ ባሰራጨው ደብዳቤ ፥ " ከሰርዓታዊና ተቋማዊ አሰራር ውጪ የሚካሄዱ የስራ ምደባዎች ኢህጋዊ ብቻ ሳይሆኑ ተጠያቂነትን ያስከትላሉ " ሲል አስጠንቅቋል።

የጊዚያዊ አስተዳደሩ ፕሬዜዳንት ጌታቸው ረዳ ነሃሴ 17/2016 ዓ.ም በህወሓት የፓሊት ቢሮ አባልዋ ወ/ሮ ሊያ ካሳ ምትክ ፀጋይ ገብረተኽለ ገ/ክርስቶስ የደቡባዊ ምስራቅ ዞን አስተዳዳሪ በማድረግ ተሾመዋል።

ነሃሴ 18/2016 ዓ.ም የወጡ መረጃዎች እንደሚያመለክቱት ደግሞ በሰሜናዊ ምዕራብ ዋና አስተዳዳሪና በቅርቡ ህወሓት ባካሄደው ጉባኤ የፓሊት ቢሮ አባል ሆነው በተመረጡት ተክላይ ገ/መድህን ምትክ የክልሉ የስፓርት ኮሚሽን ኮምሽነር የነበሩት ተኽላይ ፍቓዱ ተሹመዋል።

@ethio_mereja_news
አሳዛኝ መረጃ‼️

በኢትዮጵያ ፊልም ኢንዱስትሪ በርካታ ፊልሞችን በመስራት የሚታወቀው ተዋናይ ጌታቸው እጅጉ ( ባቡጅ )ትናንት ምሽት ከዚህ አለም በሞት ተልይቷል።

ባቡጂ የሞተው በችግር ምክንያት
እንደሆነ እየተነገረ ነው ።

ለመላው ቤተሠቦቹና ⁠ለአድናቂዎቹ መፅናናቱት ይሰጥልን።

ተዋናይ ጌታቸው እጅጉ ( ባቡጅ )
ነፍስህ በሰላም ትረፍ!!!

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አትሌት ታምራት ቶላ በትውልድ አካባቢው አቀበባል ተደረገለት

በፓሪስ ኦሊምፒክ የወንዶች ማራቶን አሸናፊው አትሌት ታምራት ቶላ በዛሬው ዕለት በትውልድ አካባቢው አሌልቱ ከተማ ደማቅ አቀባበል ተደረገለት።

አትሌቱ በከተማው ሲደርስ የአካባቢው ማህበረሰብ፣ የወረዳው አመራሮችና የአትሌቱ ቤተሰቦች የጀግና አቀባበል አድርገውለታል።

አትሌት ታምራት ቶላ በፓሪስ ኦሊምፒክ በማራቶን ክብረወሰን በማሻሻል ጭምር አሸንፎ ለኢትዮጵያ የወርቅ ሜዳሊያ ማስገኘቱ ይታወቃል።

በዚህም አትሌቱ የእነ አበበ ቢቂላን፣ ማሞ ወልዴን እና ገዛኽኝ አበራን ታሪክ በመድገም ስሙን ከታላላቆቹ የኦሎምፒክ አሸናፊ አትሌቶች ጎን እንዲመዘገብ ማድረጉ ይታወሳል ሲል ፋና ዘግቧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ቲክቶከሩ ጆን ጨምሮ በሽብር ተከሰሱ‼️

የፌደራል ፖሊስ የአቪዬሸን አሰራርን ጥሰዋል ባላቸው 6 ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብር ወንጀል ምርመራ ጀመረ

የፌደራል ፖሊስ ሰሞኑን ከአዲስ አበባ መቀሌ ለጉዞ በተዘጋጀ አውሮፕላን ውስጥ የአቪዬሸን አሰራርን በጣሰ መንገድ ግርግርና ወከባ በፈጠሩ 6 ተጠርጣሪዎች ላይ የሽብር ወንጀል ምርመራ መጀመሩን አስታወቀ።
ተጠርጣሪዎቹ ዮሀንስ ዳንኤል በርሄ፣ አማኑኤል መውጫ አብርሃ፣ ናትናኤል ወንድወሰን ሹሜ፣ ኤልያስ ድሪባ፣ ይዲድያ ነጻነት አበበ እና እሌኒ ክንፈ ናቸው።
የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ የምርመራ መዝገብ እንደሚያሳየው፥ እነዚህ ተጠርጣሪዎች ተፈጥሮ በፈጠረው የአየር መዛባት ምክንያት አውሮፕላኑ መብረር አይችልም እየተባለ፣ አስገድዶ ለማስኬድ የፈጠሩት አምባጓሮ በወንጀል ሕጉ ተጠያቂ ያደርጋቸዋል ብሏል።

የፖሊስ የምርመራ ቡድን ተጠርጣሪዎች ላይ በወንጀል ተጠያቂ ለማድረግ ከተጀመረው ምርመራ ባሻገር፣ ከጸረሰላም ሃይሎች ተልእኮ ተቀብለው የተንቀሳቀሱ በመሆናቸው በሽብር ወንጀልም መጠርጠራቸውን ነው የሚያመላክተው።

በወቅቱ የአየር መንገዱ ከደህንነት ኃይሎች ጋር በመሆን በትዕግስት ቢማጸናቸውም፣ ድብቅ አጀንዳቸውን እያራመዱ በመሆናቸው አሻፈረን ማለታቸውንም በምርመራ መዝገቡ አካቷል።

ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ተግባር መጠቀም ሲገባቸው፣ የሀገር ኩራት እና የራሳቸውን ንብረት የሆነውን አየር መንገድ አንቋሽሸው አሳዛኝ ተግባር ስለመሆኑም የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ ገልጿል።

በመሆኑም እነዚህ በቁጥጥር ስር የሚገኙ 6 ተጠርጣሪዎችን ቢሮው በተላለፉት የሀገር ውስጥ እና ዓለም አቀፍ የበረራ አሰራር ጥሰት ብሎም በሽብር ወንጀሎች የምርመራ መዝገብ ነገ ነሀሴ 20/2016 ፍርድ ቤት እንደሚያቀርባቸው ለማወቅ ተችሏል።

@ethio_mereja_news
ለጥንቃቄዎ
ጥሩ እንቅልፍ የማይተኙባቸው ምክንያቶችን
ያስወግዱ!!

1. በውስጥዎ ጭንቀት ካለ።
2. የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎችን መጠቀም።
3. ከመኝታ በፊት ሲጋራ ማጨስ።
4. በቂ እንቅስቃሴ(ስፖርት) አለማድረግ።
5. በመኝታ ሰዓት አካባቢ ከመጠን በላይ የአልኮል መጠጦች መጠጣት።
6. የመኝታ ሠዓት ሲቃረብ ቡና መጠጣት።
7. ከፍተኛ የስብ መጠን ያለው እራት መመገብ።
8. የመኝታ ክፍልዎ የብርሃን እና የአየር ሁኔታ።
9. የሆርሞኖች መቀያየር (መለዋወጥ)።
10. በመኝታ ክፍል ውስጥ የቤት እንሰሳቶች ካሉ።

በሰላም እደሩ

@Merkato_media
16 ጅብ‼️

ዓለም ገና (ዳለቲ )ኣከባቢ ዛሬ ረፋድ ላይ ጅብ ኣንዲት የ4 አመት ህፃን በመውሰድ ይበላታል በዚህው የተበሳጨ የአከባቢው ሰው ርብርብ በማድረግ 16 ጅቦች ገድለዋል፡።

@sheger_press
@sheger_press
2024/11/05 23:10:00
Back to Top
HTML Embed Code: