Telegram Web Link
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቢሾፍቱ አቅራቢያ ለማስገንባት ላቀደው ለግዙፉ ዓለማቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለዲዛይን ሥራ እና የማማከር አገልግሎት "ዳር" ከተሰኘ ዓለማቀፍ ኩባንያ ጋር ዛሬ ውል ተፈራርሟል።

ኩባንያው ባንድ ዓመት ውስጥ የአውሮፕላን ማረፊያውን የዲዛይን ሥራ እንደሚያጠናቅቅ በስምምነቱ ላይ ተገልጧል።

በአምስት ዓመት ውስጥ እንዲጠናቀቅ ከስምምነት የተደረሰበት አውሮፕላን ማረፊያ፣ በ35 ስኩየር ኪሎ ሜትር ላይ የሚያርፍ ሲኾን፣ ግንባታው ሲጠናቀቅ ባንድ ጊዜ አራት አውሮፕላኖችን ማስተናገድ እንደሚችል ተነግሮለታል።

አውሮፕላን ማረፊያው በመጀመሪያው የግንባታ ምዕራፍ 60 ሚሊዮን እንዲኹም በሁለተኛው ምዕራፍ 100 ሚሊዮን ደንበኞችን ማስተናገድ ይችላል ተብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ኢትዮጵያና ሱማሊያ በባሕር በር ውዝግባቸው ዙሪያ በመጭው ሳምንት አንካራ ውስጥ ተገናኝተው ሁለተኛውን ዙር ንግግር እንደሚያደርጉ የቱርክዬ ውጭ ጉዳይ ሚንስትር ሃካን ፊዳን ተናግረዋል።

ፊዳን፣ ከሳምንት በፊት ወደ አዲስ አበባ በተጓዙ ጊዜ ኢትዮጵያ ከሶማሌላንድ ጋር በተፈራረመችው የባሕር በር የመግባቢያ ስምምነት ሳቢያ ከሱማሊያ ጋር በተፈጠረው ውጥረት ዙሪያ ከጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ጋር "በጥልቀት" እንደተወያዩበት አንካራ ውስጥ ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል።

ፊዳን፣ "ኢትዮጵያ ለሶማሊያ የግዛት አንድነትና የፖለቲካ ሉዓላዊነት" ዕውቅና እስከሰጠች ድረስ በሱማሊያ በኩል የባሕር በር ታገኝና በመካከላቸው ያለው ውጥረትም ያበቃል" ብለዋል።

የሁለቱ አገራት ውጭ ጉዳይ ሚንስትሮች ከጥቂት ሳምንታት በፊት አንካራ ውስጥ በፊዳን አስተባባሪነት ቀጥተኛ ያልኾነ ንግግር አድርገው የነበረ ሲኾን፣ ሁለተኛው ዙር ንግግር ነሃሴ 27 እንደሚካሄድ በወቅቱ ተገልጦ ነበር።

@ethio_mereja_news
የ10,000ሜ ሴቶች ፍፃሜ ውድድር ከጀመረ 10 ደቂቃዎች አልፈዋል።

ሀገራችን
🇪🇹 በአትሌት ጉዳፍ ፀጋይ
🇪🇹 በአትሌት ጽጌ ገብረሰላማ እና
🇪🇹 በአትሌት ፎቴን ተስፋይ ተወክላለች።

መልካም ዕድል ! ይቅናን !
5 ዙር ይቀራል

@ethio_mereja_news
ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ደረጃ ውስጥ አልገቡም
ኢትዮጵያ በ 10000ሜትር ምንም አይነት ሜዳሊያ ማግኘት ሳትችል ቀርታለች።

ኬንያ ወርቅ ፣ ጣልያን ብር እንዲሁም ኔዘርላንድ ነሐስ ማግኘት ችለዋል።

THE WORST OLYMPIC IN ETHIOPIAN ATHLETICS HISTORY

@ethio_mereja_news
ሀይሌ ያሰጀመረው የፓሪሱ ማራቶን 30ኪሜ አልፏል።

ይቅናን
አትሌት ታምራት ቶላ እየመራ ይገኛል

@ethio_mereja_news
አትሌት ታምራት ቶላ አሁንም እየመራ ይገኛል። 4KM አካባቢ ይቀራል

መጨረሻው ያሳምርልን

@ethio_mereja_news
1KM ቀርቷል
እንኳን ደስ ያላቹ ።
እንኳን ደስ ያለን ።

እልልልልልል እናት ሀገር አሸነፈች🇪🇹🇪🇹

Congraaaaaaaa🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹🇪🇹

በመጨረሻም ስናፍቀው የነበረው ወርቅ ወደ ቤቱ ተመልሷል።

ታምራት ቶላ ለኢትዮጵያ የመጀመሪያውን ወርቅ አስገኝቷል።

ጀግና

ዛሬ የድል ቀን ነው🇪🇹🇪🇹🇪🇹

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
እልህ ፣ወኔ ፣ አልበገር ባይነት ያሸናፊነት መንፈስ ሁሉንም የያዘ የሀገራችን ምርጥ እንቁ አትሌት ታምራት ቶላ!!

በነገራችን ላይ ሪከርድ በመስበር ጭምር ነው ያሸነፈው።

የኦሎምፒክ ሪከርድን በስድስት ሴኮንዶች ያሻሻለ ጀግና!

ታምራት ቶላ ከ 24 አመታት በኋላ በኦሎምፒክ ማራቶንን ያሸነፈ ኢትዮጵያዊ ሆነ።

ተጠባባቂ ተብሎ በደል የደረሰበት አትሌት በተጎዳ ሰው ተተክቶ ለሀገሬ በማራቶን የመጀመሪያ ወርቅ አስገኘ 💪💪💪

ታምራት ቶላ ይገባሀል 🇪🇹🇪🇹🇪🇹

@ethio_mereja_news
ለሕዝባችን የሚገባውን ደስታና ኩራት አመጣህለት!! የዛሬው ድል ልዩ ትርጉም አለው።

ፈጣሪ ይባርክህ!!"

ፕሬዚዳንት ሣህለ ወርቅ ዘውዴ

@sheger_press
@sheger_press
ክቡር ጠ/ር ዶ/ር ዐብይ አህመድ ያስተላለፉት የእንኳን ደስ ያላቹ መልክት

በፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ጀግናው አትሌት ታምራት ቶላ በማራቶን ውድድር ላይ ወርቅ በማግኘት ሰንደቅ አላማችንን በድጋሚ ከፍ አድርጓል።

እንኳን ደስ አላችሁ!

@ethio_mereja_news
ጀግናው አትሌት ታምራት ቶላ ከድሉ በኋላ ለሲዲ ስፖርት በሰጠው አጭር ቃል በእንባ ታጅቦ በደስታ ሲያለቅስ ታይቷል ።

ከድሉ በኋላ የመጀመሪያ በሆነው ቃሉ ''ደስታ ነው ያስለቀሰኝ እግዚአብሔር ይመስገን '' ብሏል

በድጋሚ እንኳን ደስ አለን‼️

@ethio_mereja_news
የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በጎፋ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ለተፈናቀሉ ዜጎች የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን በጎፋ ዞን በድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተፈናቀሉ ዜጎች ድጋፍ የሚውል የ5 ሚሊዮን ብር ድጋፍ በዛሬው እለት አሰረክቧል፡፡

የገንዘብ ድጋፉን የኮርፖሬሽኑ ምክትል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ ኃይለብርሀን ዜና በቦታው በመገኘት አስረክበዋል፡፡ አቶ ኃይለብሀን ዜና በወገኖቻችን ላይ በደረሰው ድንገተኛ አደጋ የኮርፖሬሽኑ አመራሮችና ሠራተኞችን ማዘናቸውን ገልጸዋል፡፡

ኮርፖሬሽኑ በመላ አገሪቱ የሚከሰቱ ሰው ሠራሽ እና ተፍጥሯዊ አደጋዎች ምክንያት ጉዳት ለደረሰባው ወገኖች የገንዘብ ድጋፍ ሲያደርግ መቆቱን አስተውሰው በ6 ዓመታት ብቻ ኮርፖሬሽኑ ማህበራዊ ኃላፊነቱን ለመወጣት ታሳቢ በማድረግ ያደረገው ድጋፍ ግማሽ ቢሊየን ብር መሻገሩን ተናግረዋል፡፡

በጎፋ ዞን በድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተፈናቀሉ ዜጎች መልሶ ለማቋቋም እየተደረገ ያለውን አንቅስቃሴ መደገፉን አጠናክሮ ይቀጥላልም ነው ያሉት አቶ ኃለብርኃን ዜና ፡፡

የጎፋ ዞን ዋና አስተዳዳሪ ኢንጂነር ዳግማዊ አየለ በበኩላቸው ከፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ለተደረገው የገንዘብ ድጋፍ ምስጋናቸውን አቅርበው ፣ ድጋፉ በአደጋው ለተጎዱ እና የተፈናቀሉ ወገኖችን መልሶ ለማቋቋም የሚደረገውን ጥረት የሚያግዝ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በአደጋው ለተጎዱና ለተፈናቀሉ ወገኖች ተገቢው የሆነ ሰብዓዊ ድጋፍ እየተደረገ እንደሆነ ጠቁመው ተፈናቃዮችን ከአደጋ ስጋት ነጻ ወደ ሆነ ቦታ የማስፈር ሥራ እየተሰራ እንደሆም ገልጸዋል፡፡
ኮርፖሬሽኑ ያደረገው የገንዘብ ድጋፍም ለመልሶ ማቋቋም ሥራው ትልቅ አጋዥ እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Dogs‼️

Dogs ያልጀመራቹ ብዙዎች መቆጨታቹ አይቀርም እያሉ ነው

ስለዚ ጀምሩ ያልጀመራቹ 👇👇

https://www.tg-me.com/dogshouse_bot/join?startapp=qA4t5KguQWKX0tWVVEhxSQ

https://www.tg-me.com/dogshouse_bot/join?startapp=qA4t5KguQWKX0tWVVEhxSQ
በአማራ ክልል በደቡብ ወሎ ዞን በኮምቦልቻ ከተማ ዛሬ ጠዋት ልዩ ስሙ ዶሮ እርባታ አካባቢ አንድ ግለሰብ ውሻ አርዶ በመግፈፍ ላይ እያለ በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን ጥቆማዎች ደርሰውኛል።

ከዚህ በፊት የውሻ ስጋን ወደ ሽያጭ ሲያወጣ እንደነበር ከግለሰቡ ቃል ለመገንዘብ ተችሏል ሲሉ ምንጮች ገልጸዋል።(ayu)

@ethio_mereja_news
2024/09/30 09:28:20
Back to Top
HTML Embed Code: