Telegram Web Link
በወላይታ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ጤፓ ቀበሌ ከረፋድ 5 ሠዓት አካባቢ በተከሰተ የመሬት ናዳ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ።

በተከሰተው አደጋ እስካሁን በተደረገ ፍለጋ የ11 ሰዎች አስክሬን መገኘቱንና የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ ይችላል ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ኢንስፔክተር አሸናፊ ኃይሌ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

ህብረተሰቡ በሁሉም አካባቢ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል ተብሏል።

@ethio_mereja_news
አንድ እንጀራ 35 ብር ገብቷል ፤ አምስት ሊትር ዘይት ወደ 2ሺህ ብር እየተንደረደረ ነው ›› - የስድስት ክልል ከተሞች ነዋሪዎች

የኑሮ ውድነትን አሻሽላለው ያለው መንግስት በዚ መልኩ የህዝቡን ችግር እያባባሰው ይገኛል።

@sheger_press
ብር 🇪🇹🇪🇹

የ 800ሜትር ሴቶች ውድድር ፍፃሜውን ሲያገኝ አትሌት ፅጌ ድጉማ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ለሀገራችን ሁለተኛውን የብር ሜዳሊያ አስገኝታለች ።

1
ኛ ሆድኪንግሰን
2ኛ ፅጌ ድጉማ
3ኛ ሞራ
6ኛ ወርቅነሽ መሰለ
ከእስራኤል ሀገር መጥቶ ጎንደር የተሰዋዉ ጀግና ፋኖ
አስገራሚ ታሪክ👇👇
https://youtu.be/_fk4d_-YgHU?si=hGzq0Z1Yb_vUkFEV
በኦሮሚያ ክልል 5ሺህ ብር ይከፍሉ የነበረው "የኮቴ" ክፍያ 90ሺህ ብር መግባቱ ፈተና እንደሆነባቸው የለስላሳ እና የቢራ ፋብሪካዎች ለዋዜማ ገልፀዋል ።
የጉድ ሀገር‼️

የኢትዮጵያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ወደ ፓሪስ ከላከዉ ልዑክ ዉስጥ የክልል ሹማምንትን ሲያሳትፍ አትሌቶች እና አሰልጣኞችን ተገፍተዉ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ አድርጓል‼️

  ፓሪስ ከተጓዙ በርካታ አመራሮች መካከል በምስሉ ላይ የሚታዩት አምስት የመንግስት ሹማምንት ይገኙበታል፤ ክልሎቻቸውን ወክለው ኦሊምፒኩ ላይ ታድመዋል፥ እነሆ፦

1️⃣ አቶ አርሻሎ አርካሌ፦ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ

2️⃣ አቶ ያሲን የሱፍ፦ የሀረሪ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር

3️⃣ አቶ ማቲዎስ ሰቦቃ፦ የኦሮሚያ ወጣቶችና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ

4️⃣ አቶ ፋንታሁን ብላቴ፦ የደቡብ ምዕራብ ክልል ባህል ቱሪዝምና ስፖርት ቢሮ ሀላፊ

5️⃣ አቶ የሱፍ አልበሽር፦ የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር

🟣 እነዚህ የመንግስት ሹመኞች ከመክፈቻው እለት ጀምሮ እስካሁን ፓሪስ ይገኛሉ

የአውሮፕላን ትኬትና የሆቴል ወጪ እንዲሁም የቀን አበል በኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ኮሚቴ ተችለዋል

🟣የተሰጣቸው ባጅ የነፃ ትራንስፖርት፣ የነፃ ስታዲየም መግቢያ፣ የነፃ ምግብና መጠጥ አቅርቦትን ያካትታል

🟣 ለእያንዳንዳቸው ኪሳቸው ባዶ እንዳይሆን ተብሎ ከ3ሺህ ዶላር በላይ ተሰጥቷቸዋል

🟣 ልምድ ለመቅሰምና ለተሾሙበት ክልል ወጣቶች ተሞክሯቸውን ለማካፈል ነው የሄዱት የሚል ምክንያት ይቀርብላቸዋል።

🟣 138 የክልል ኮሚሽነሮችና የመንግስት ዋናና ምክትል ኃላፊዎች ፓሪስ ተንጋግተው የገቡት ማራቶን ለመሮጥ ነው? 
 
👉ለእያንዳንዳቸው 3ሺ ዶላር አበል ተቆርጦላቸዋል።
 
👉ለፓሪስ ኦሎምፒክ ዶላር ብርቋ ከሆነባት የምስኪና ሀገር ካዝና ተራቁቶ ከ400ሺ ዶላር በላይ ተጭኖ ፈረንሳይ ገብቷል። ትናንት በ800ሜ የብር ሜዳሊያ ያመጣችሁ የፅጌ ድጉማ አሰልጣኝን ጨምሮ ሌሎች ወደ ሀገራቸው እንዲመለሱ ተደርገዋል።
Via ታምሩ ዓለሙ
የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ለፓስፖርት አገልግሎቶች የዋጋ ጭማሪ አደረገ

የኢፌዴሪ ኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት ለተለያዩ ፓስፖርት አገልግሎቶች የዋጋ ማሻሻያ ማድረጉን አስታውቋል፡፡

ተቋሙ ከነሐሴ 1 ቀን 2016 ጀምሮ ለመደበኛ፣ ለአስቸኳይ፣ ለእድሳት፤ ለጠፋ እና ለእርማት ፓስፖርት አገልግሎቶች ነው የዋጋ ማሻሻያ ያደረገው፡፡

በዚህ መሰረት አዲስ ፓስፖርት ለማውጣት፣ ለእድሳት እና የፓስፖርት ገጽ ላለቀባቸው ተገልጋዮች በመደበኛ 5ሺህ ብር ፣ በአስቸኳይ በሁለት ቀን የሚደርስ ፓስፖርት 25 ሺህ ብር እንዲሁም አስቸኳይ በአምስት ቀን የሚደርስ 20 ሺህ ብር እንደሚያስከፍል አስታውቋል፡፡

ለሌሎች በርካታ አገልግሎቶች በመደበኛ ከ12 ሺህ 500 በአስቸኳይ እስከ 40 ሺህ 500 ብር ዋጋ ማውጣቱን አስታውቋል። ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን በቅርቡ የኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት የዋጋ ጭማሪ እንደሚያደርግ መዘገቡ ይታወሳል።

@sheger_press
@sheger_press
ገርበ ጉራቻ አካባቢ ከታገቱት ተማሪዎች ውስጥ 16ቱ ተለቀቁ፤ በታጋቾች ላይ ጾታዊ ጥቃትና ድብደባ ተፈጽሟል ተብሏል‼️
#ኦሮሚያ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን #ገርበ_ጉራቻ አካባቢ በታጣቂዎች ከታገቱ ከ167 በላይ የደባርቅ ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች መካከል ባለፉት ቀናት 16ቱ በመቶ ሺዎች የሚቆጠር የማስለቀቂያ ገንዘብ ከፍለው መለቀቃቸው ተገለጸ።

በታጋቾቹ ላይ ግርፋት፣ ድብደባ እንዲሁም ጾታዊ ጥቃት መፈጸሙን የተማሪዎቹን እገታ ከቤተሰብ ጋር ሆነው በቅርበት እየተከታተሉ ያሉ ምንጮች ለቢቢሲ ገልጸዋል። 

አንድ የታጋች ተማሪ ቤተሰብ “ታጣቂዎቹ በተማሪዎቹ ፊት ሁለት ሰዎችን መግደላቸውን እያለቀሱ ነግረውናል” ብለዋል።

ከ30 በላይ ይሆናሉ የተባሉት ታጣቂዎቹ ‘ፀጉራቸውን የተሰሩ፣ የሲቪል ልብስ የለበሱ እና የተማሩ’ መሆናቸውን ተማሪዎቹ አመልክተዋል።

@sheger_press
@sheger_press
ኢትዮጵያውያን አትሌቶች ሜዳሊያ ሊያሸንፉ እንደሚችሉ ቅድመ ግምት ያገኙበት የወንዶች የሦስት ሺህ ሜትር መሰናክል የፍጻሜ ውድድር ዛሬ ምሽት ይደረጋል።

በውድድሩ የክብረ ወሰን ባለቤቱ ለሜቻ ግርማ ከሀገሩ ልጆች ሳሙኤል ፍሬው እና ጌትነት በተጨማሪ ከኬንያ እና ሞሮኮ አትሌቶች ብርቱ ፍልሚያ ይጠብቀዋል። አትሌቶቹ በማጣሪያው ከየምድባቸው አንደኛ፣ ሁለተኛ እና ሦስተኛ በመውጣት ነው ለፍጻሜ የደረሱት ።

አትሌት ሳሙኤል ፍሬው የማጣሪያ ውድድሩን ካጠናቀቀ በኋላ ተጎድቶ በቃሬዛ ነበር ከሜዳ የወጣው ። አሁን በወጣው መረጃ ግን ለምሽቱ የፍጻሜ ውድድር ዝግጁ ነው። ውድድሩ ምሽት በኢትዮጵያ ሰዓት አቆጣጠር 4:40 ላይ ይደረጋል።ትናንት ምሽት በተደረገው የሴቶች የሦስት ሺህ ሜትር መሰናክል የተካፈሉት ኢትዮጵያዉያን በሜዳሊያ ሰንጠረዥ ውስጥ መካተት አልቻሉም። አትሌት ሲምቦ አለማየሁ አምስተኛ ደረጃ እንዲሁም ሎሚ ሙለታ ስምንተኛ ደረጃ በመያዝ አጠናቀዋል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ዛሬ ረፋድ ላይ በተደረገ የአምስት ሺህ ሜትር የማጣሪያ ውድድር ኢትዮጵያን የወከሉት ሦስቱም አትሌቶች ለፍጻሜ ማለፋቸውን አረጋግጠዋል። አትሌት ሐጎስ ገብረሕይወት ከምድብ አንድ በ 14:08:18 ሰአት ሁለተኛ ደረጃ ፤ አትሌት ቢኒያም መሐሪ ከምድብ ሁለት 13:51:82 ሰአት በሁለተኛ ደረጃ እንዲሁም አትሌት አዲሱ ይሁኔ ከምድቡ ስምንተኛ በመውጣታቸው በፍጻሜው ለመወዳደር እንደሚችሉ ታውቋል

@sheger_press
ከጥቂት ደቂቃዎች በፊት በተጠናቀቀው የወንዶች 3000 ሜትር መሰናክል ኢትዮጵያዊያኖቹ ሳሙኤል ግርማ 6ኛ ጌትነት ዋለ ደግሞ 9ኛ ሆነው አጠናቀዋል፤ የርቀቱ የአለም ክብረወሰን ባለቤት የሆነው ለሜቻ ግርማ በመጨረሻው ዙር መሰናክሉን ሲዘል ባጋጠመው ጉዳት ውድድሩን አልጨረሰም፤ ከስታዲየም በቀጥታ ወደ ሆስፒታል ተወስዷል፤ የጉዳቱ መጠን ምን ያህል እንደሆነ በዚህች ቅፅበት አልታወቀም፤ በፍጥነት እንድታገግም አምላክ ይርዳህ!

ውድድሩን የሞሮኮው ሱፋኒ ኤል ባካሊ ርቀቱን 8:06:05 በመግባት የአመቱን ምርጥ ሰዓት አስመዝግቦ አሸንፏል፤ አሜሪካዊው ኬኒት ሩክስ ሁለተኛ ኬኒያዊው አብርሀም ኪብዌት ሶስተኛ ሆነው ጨርሰዋል

(ታምሩ ዓለሙ)

@sheger_press
አትሌት ለሜቻ ግርማ!

የ3,000 ሜትር መሰናክል ሪከርድ ባለቤቱ ለሜቻ ግርማ ትናንት ምሽት በውድድሩ ወቅት ሲዘል ባጋጠመው ጉዳት ምክንያት በፍጥነት ወደ ሆስፒታል እንደተወሰደ እና አሁን በመልካም ጤና ላይ እንደሚገኝ ተገልጿል።

አትሌት ለሜቻ ግርማ ትናንት ምሽት ባጋጠመው ከባድ ጉዳት ምክንያት ራሱን ስቶ ወደ ሆስፒታል የተወሰደ ሲሆን በአሁኑ ወቅት ሙሉ በሙሉ የነቃ ሲሆን በተደረገለት የሲቲ ስካንና የኤም አር አይ ምርመራ ምንም አይነት ጉዳት እንዳልተገኘበት ኦሊምፒክ ኮሚቴው አስታውቋል።

የፓሪስ 2024 ኦሎምፒክ ቃል አቀባይ በበኩላቸው ፤ " አትሌት ለሜቻ ግርማ አስፈላጊ የሆነ አፋጣኝ ህክምና ተደርጎለታል " ብለዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በደቡብ ጎንደር ዞን የሦስት ወረዳዎች ነዋሪዎች በጎርፍ መከበባቸው ተገለፀ‼️

በደቡብ ጎንደር ዞን ሦስት ወረዳዎች፣ ከባድ ዝናም መጣሉን ተከትሎ በሺሕዎች የሚቆጠሩ ሰዎች በጎርፍ መከበባቸውን የገለጹ ነዋሪዎች እና የአካባቢው ባለሥልጣናት፣ ከ15ሺሕ በላይ ነዋሪዎች አስቸኳይ የነፍስ አድን ሥራ እንደሚያስፈልጋቸው አመልክተዋል፡፡

የፎገራ እና የሊቦ ከምከም ወረዳ አደጋ መከላከል እና ምግብ ዋስትና ማስተባበሪያ ጽሕፈት ቤት ባለሞያዎች፣ ትናንት ረቡዕ ለአሜሪካ ድምፅ ሲናገሩ፣ በሁለቱ ወረዳዎች በተለይ ከ12 በላይ የሚኾኑ ቀበሌዎች በጎርፍ መከበባቸውን አስታውቀዋል፡፡

በቀበሌዎች ያሉ ስድስት ትምህርት ቤቶች እና ሁለት የእምነት ተቋማት፣ በጎርፉ ጉዳት እንደደረሰባቸው የተናገሩት ባለሞያዎቹ፣ “በ3ነጥብ7 ሄክታር መሬት ላይ የነበረ ማሳ ወድሟል፤ በርካታ የቤት እንስሳትም በጎርፍ ተወስደዋል፤” ብለዋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Become an AI Engineer for the Ethiopian FinTech Sector!

The Kifiya AI Mastery Training Program offers an intensive, project-based learning approach to make you job-ready for the Ethiopian FinTech sector and beyond!

In 3 months we will prepare you for top-notch job offers with hands-on projects, and you’ll gain practical skills for real-world applications. This program is fully funded and FREE!

This training is offered by Kifiya Financial Technology and powered by 10 Academy.

Application Open Until 16 AUG, 2024

Our curriculum covers key technology areas:
- Generative AI Engineering
- Machine Learning Engineering
- Data Engineering

Women, people with disabilities ( long-term physical, mental, intellectual, or sensory impairments), refugees, returnees, and IDPs are highly encouraged to apply.

Apply Today: apply.10academy.org

Learn more about the program at https://10academy.org/kifiya/learn-more
Forwarded from Sheger Press️️
Become an AI Engineer for the Ethiopian FinTech Sector!

The Kifiya AI Mastery Training Program offers an intensive, project-based learning approach to make you job-ready for the Ethiopian FinTech sector and beyond!

In 3 months we will prepare you for top-notch job offers with hands-on projects, and you’ll gain practical skills for real-world applications. This program is fully funded and FREE!

This training is offered by Kifiya Financial Technology and powered by 10 Academy.

Application Open Until 16 AUG, 2024

Our curriculum covers key technology areas:
- Generative AI Engineering
- Machine Learning Engineering
- Data Engineering

Women, people with disabilities ( long-term physical, mental, intellectual, or sensory impairments), refugees, returnees, and IDPs are highly encouraged to apply.

Apply Today: apply.10academy.org

Learn more about the program at https://10academy.org/kifiya/learn-more
ሰሞኑን የዶላር ዋጋ መጨመሩን ተከትሎ ገበያው ለያዥ ለገናዥ እያስቸገረ ነው‼️

አዲስ አበባ ውስጥ ባሉ የገበያ ስፍራዎች ከዶላር ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌላቸው ምርቶች ድንገት ዋጋቸው ሲንር ተስተውሏል፡፡

መንግስትም #የዶላር_ጭማሪውን ተገን በማድረግ ዋጋ መጨመር አይቻልም፤ የሚጨምሩት ላይ እርምጃ እየወሰድሁኝ ነው ቢልም በነጋዴዎች ዘንድ ይህ እርምጃ ዋና አከፋፋዮቹን ሳይሆን ቸርቻሪው ነጋዴ ላይ ነው የበረታው ሲሉ እየተቹት ነው፡፡

በችርቻሮ ንግድ ላይ የተሰማሩ #ነጋዴዎች እንዳሉን ከሆነ ምርት አከፋፋይ ነጋዴዎች የዋጋ ጭማሪ አድርገዋል፤ መንግስት እነሱ ላይ እያደረገው ያለው ቁጥጥር የላላ ነው ሲሉ ተናግረዋል፡፡

ቸርቻሪ ነጋዴው ላይ ግን ቁጥጥሩ እጅግ የበረታ ነው ብለዋል፡፡

ታዲያ መንግስት አሁን እየሰራ ያለው አከፋፋዮችን ከመቆጣጠር ይልቅ ቸርቻሪ ነጋዴው ላይ ነው እየበረታ ያለው ገበያው እንዲረጋጋ ከተፈለገ ቅድሚያ #አከፋፋዮች እና አምራቾችን መከታተልና መቆጣጠር የዋጋ ንረት ችግሩን ይፈታል ብለዋል፡፡
# ሸገር ኤፍ ኤም

@ethio_mereja_news
2024/09/30 05:27:17
Back to Top
HTML Embed Code: