Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ጥንቃቄ : ክረምቱ እየበረታ ነው።

አሽከርካሪዎች ስታሽከረክሩ እየተጠነቀቃችሁ ይሁን።

ከቤት ሳትወጡ የመኪናችሁን ደህንነት በተለይ የዝናብ መጥረጊያ፣ ጎማ ሌሎችንም ነገሮች ሁሌም ማረጋገጥ እንዳትረሱ

የምትሄዱበትን መንገድ እየተጠነቃቃችሁ።

ወላጆችም ልጆቻችሁን ጠብቁ።

በተለይ ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ ክረምት በጣም ቁጥር እጅግ በጣም የሚሰቃዩት ሠራተኞች ናቸው በተለይም በስራ የመግቢያ እና የመውጫ ሰዓት ፥ ይኸው አመታት አልፈዋል ስለ ትራንስፖርት ችግር ሲጮህ ሲጮህ ምንም የተለየ መፍትሄ አልመጣም።

ዛሬም ሠራተኞች / ዜጎች ስራ ለመግባት እና ከስራ ወጥተው ወደ ቤት ለመሄድ፣ ለሌላም ጉዳይ ረጅም ሰዓት በብርድ እና በዝናብ ሰልፍ ላይ ያሳልፋሉ። መቼ ነው መፍትሄ የሚገኘው ?

ለሁሉም ግን ስትንቀሳቀሱ ጥንቃቄ አይለያችሁ።

በክልሎችም በዚህ ክረምት ወቅት ላይ ጉሙ ለመኪና መንገድ አስቸጋሪ ነውና ሹፌሮች ተጠንቅቃችሁ አሽከርክሩ።

ሰላም ወጣችሁ ሰላም ግቡ !

ክፉ አያግኛችሁ !

ቪድዮ ፦ ዛሬ ሐምሌ 26/2016 ዓ/ም አዲስ አበባ (tikvah)


@ethio_mereja_news
በ 5000 ሜትር ማጣሪያ የመጀመሪያው ዙር ኢትዮጵያን የወከሉት ጉዳፍ ፀጋይ እና እጅጋየሁ ታዬ 5ኛ እና 6ኛ በመውጣት ፍፃሜውን ሲቀላቀሉ።

በሁለተኛው ዙር ኢትዮጵያን የወከለችው መዲና አሳም 2ኛ በመውጣት በተመሳሳይ ፍፃሜውን ተቀላቅላለች።

@ethio_mereja_news
በ 800 ሜትር ርቀት ኢትዮጵያን ከወከሉት 3 አትሌቶች

ወርቅነሽ መለሰ በምድብ 2 ሮጣ 1ኛ
አትሌት ፅጌ ድጉማም በ5ኛ ዙር 1ኛ
በመጨረስ ግማሽ ፍፃሜውን ሲቀላቀሉ

ሀብታም አለሙ 7ኛ በመጨረሷ ሌላ ማጣሪያ ትወዳደራለች።

🇪🇹❤️

@ethio_mereja_news
በኦሎምፒክ 10 ሺህ ታሪክ ፈጣኑ ሰአት በተመዘገበበት ውድድር በሪሁ አረጋዊ የብር ሜዳልያ አግኝቷል።

@sheger_press
dollar‼️

ዛሬ ፥ በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ በኢትዮጵያ በህጋዊ መንገድ 1 የአሜሪካ ዶላር ከ 100 ብር በላይ መሸጥ ይጀምራል

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ዛሬ ቅዳሜ የዶላር ዋጋ አውጥቷል መግዧ 95.6931 እንዲሁም መሸጫ 101.437 መሆኑን አሳውቋል።

@ethio_mereja_news
የብሄራዊ ባንክ ገዢ ማሞ ምኅረቱ፣ በአዲሱ የማክሮ ኢኮኖሚ ፖሊሲ የሚመራው ገበያ ችግር ካጋጠው ባንኩ ጣልቃ እንደሚገባ አስታውቀዋል።

ማሞ፣ ኢትዮጵያ ከዓለማቀፉ ገንዘብ ድርጅትና ከዓለም ባንክ ጋር የብድር ስምምነቶችን መፈራረሟን ተከትሎ፣ ከሁለቱ ተቋማት 2 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ወደ ብሄራዊ ባንክ እንደገባ ተናግረዋል።

ኢትዮጵያ ከውጭ ከምታስገባቸው የፍጆታ ዕቃዎች መካከል 18 በመቶዎቹ ብቻ በውጭ ምንዛሬ እንደሚመጡ የገለጡት ማሞ፣ ቀሪዎቹ ግን በትይዩ ገበያ ሲገቡ እንደቆዩ ገልጸዋል።

ባንኩ ጥብቅ የገንዘብ ፖሊሲ ለመተግበር መዘጋጀቱንም ማሞ ተናግረዋል።

@sheger_press
@sheger_press
ባንኮች ከሚገዙበትና ከሚሸጡበት የምንዛሬ ዋጋ ውጭ በተጨማሪነት ኮሚሽን እና ሌሎች ክፍያዎችን ለብቻ ማስከፈል እንዲያቆሙ ተወሰነ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ ባንኮች ይፋ ከሚያደርጉት የውጭ ምንዛሬ መግዣና መሸጫ ዋጋ ውጭ የሚያስከፍሉትን ኮሚሽን እና ሌላ ክፍያ እንዲያቆሙ መወሰኑ ተሰምቷል፡፡እንዲህ ያሉ ክፍያዎችን ካስከፈሉ እንኳን ከመግዣና መሸጫ ዋጋው ጋር አካተው አንድ ላይ ለደንበኞቻቸው ይፋ እንዲያደርጉት መወሰኑን ከብሔራዊ ባንክ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡

ይህም የውጭ ምንዛሬ ግዥና ሽያጭ ላይ ግልፅነትን ለመፍጠር ያለመ ነው ተብሏል፡፡ስለ ጉዳዩ ሸገር የጠየቃቸው የምጣኔ ሐብት ባለሙያ ውሳኔው ለባንክ ደንበኞች የሚበጅ ነው ብለዋል፡፡ይህን ሲያስረዱም የአንዳንድ ምግብ ቤቶችን የዋጋ ዝርዝር እንደ ምሳሌ ያነሳሉ፡፡ሂሳብ ሲያስከፍሉ የምግብ መዘርዘሩ ላይ ከተቀመጠው ዋጋ በላይ የሚጠይቁ አሉ ለዚህም ምክንያቱን ሲጠየቁ የምግብ መዘርዝሩ ዝርዝር ላይ የሰፈረው ዋጋ ቫትን አይጨምርም ይላሉ፡፡

ይህ ለደንበኞች ግልፅነት የጎደለው ወይም መጀመሪያውኑ አጠቃላይ ዋጋውን አይተው እንዳይወስኑ የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡አሁን ባንኮች የውጭ ምንዛሬ ሲሸጡና ሲገዙ የሚያስከፍሉት ኮሚሽን እና ሌላ በፐርሰንት የሚሰላ ክፍያ ካለ ይፍ በሚያደርጉት የመግዣና መሸጫ ላይ እንዲያካትቱ መወሰኑም ደንበኞች ይፋ ከተደረገው ዋጋ ሌላ ክፍያ ስለማይጠይቁ አሰራሩን ግልፅ ያደርገዋል ብለዋል ባለሞያው፡፡በሌላ በኩል ግን ይህ አሰራር ደንበኞች LC ለመክፈት ሲጠይቁ የሚኖረውን ግብይት አይመለከትም ተብሏል፡፡ውሳኔው ከዛሬ ጀምሮ ስራ ላይ መዋል መጀመሩንም ብሔራዊ ባንክ እወቁልኝ ብሏል፡፡(Sheger)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ሩዋንዳ ከ4 ሺህ በላይ ቤተክርስቲያናትና መስጂዶች ዘጋች

የድምጽ ብክለት ማስከተልና የደህንነት ደንቦችን መጣስ ለመዘጋታቸው ምክንያት ሆኖ ቀርቧል።

Alain

@ethio_mereja_news
ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን የነበሩት ሀጂ ኢብሳ ወንድ ልጃቸው በሸኔ እንደተገደለባቸው ገለፁ

ለረጅም ዓመት የገንዘብ ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር ቀጥሎም  የመንግሥት ግዥና ንብረት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር የነበሩት ሀጂ ኢብሳ ብቸኛ ልጃቸውን ሸኔ እንደገደለባቸው ገለጹ።

አቶ ሀጂልጃቸው በሸኔ ስለመገደሉ በፌስቡክ ገፃቸው ባሰፈሩት ፅሁፍ የገለፁ ቢሆንም መችና የት ልጃቸው እንደተገደለ አልገለፁም።

አቶ ሀጂ ኢብሳ በፌስቡክ ገጻቸው "የባለስልጣን ልጅ በመሆኑ ብቻ አንድ ወንድ ልጄን ሸኔ በጥይት ደብድባ ነጠቀችኝ ሲሉ ነው ሀዘናቸውን የገለጹት።

አቶ ሀጂ አክለውም "በመራር ሀዘኔ ከጎኔ የቆማችሁ  እናቶቼ፣አባቶቼ፣እህቶቼና ወንድሞቼ ብድራችሁ በዓለም ይመለስ።" ሲሉ አስፍረዋል።

Via አዲስማለዳ

@ethio_mereja_news
መልካም ዜና‼️

እግዚአብሔር ይመስገን በሰላም ወደ ቤት ተመልሽልያለሁ! ሁላችንም አመሰግናለሁ! "ነፃነት ወርቅነህ"

ከዚህ በፊት ታሞ ሆስፒታል መግባቱን መዘገባችን ይታወሳል።

Humbo Press

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ከ14 ሚሊዮን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት በሚቀጥለው ሳምንት በመላው ሀገሪቱ የሚሰራጭ ይሆናል - ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር)

ገበያን ለማረጋጋት በመንግሥት ግዢው የተፈፀመ ከ14 ሚሊዮን ሊትር በላይ የምግብ ዘይት በሚቀጥለው ሳምንት በመላው ሀገሪቱ እንደሚሰራጭ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስትሩ ካሳሁን ጎፌ (ዶ/ር) አስታውቀዋል።

@ethio_mereja_news
ዶላር በገበያው እንዲወሰን ከተደረገ ወዲህ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰሞኑ ከፍተኛ የዋጋ ጭማሬዎችን አድርጓል‼️
ለአብነት❗️

🎯ከአዲስ አበባ ዱባይ ደርሶመልስ 40,000 ብር የነበረው ወደ 87,000 ብር

🎯ከአዲስ አበባ ወደ ካናዳዋ ዊኒፔግ የነበረው የደርሶ መልስ ቲኬት ዋጋ ከ116,000 ብር ወደ 206,000 ብር

🎯 ከጎንደር አዲስ አበባ 4,600 ብር የነበረው የበረራ ዋጋ አሁን 5,793 ብር

🎯 ወደ ዋሽንግተን ዲሲ 59,000 ብር የነበረው የትኬት ዋጋ አሁን ከ95,000 ብር

🎯ከአዲስ አበባ ወደ ካናዳዋ ዊኒፔግ የነበረው የደርሶ መልስ ቲኬት ዋጋ ከ116,000 ብር ወደ 206,000 ብር ጨምሯል።

🎯ከጎንደር ሃዋሳ 7,609 ብር የነበረው በረራ አሁን 10,237 ብር ሆኗል።

🎯ከአዲስ አበባ አስመራ ለዛሬ በረራ በሰዓታት ውስጥ የትኬት መቁረጫ ዋጋ ከ87,000 ብር ወደ 108,000 ብር ከፍ ብሏል።

የአውሮፕላን ነዳጅ ዋጋ ባለበት ሆኖ ይሄ የተጋነነ የዋጋ ጭማሪ ትክክል እንዳልሆነ ተገልጋዮች እየገለፁ ነው።
(አዩዘሀበሻ)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
BREAKING‼️

ባለፉት 20 ዓመታት ባንግላዴሽን በጠቅላይ ሚኒስትርነት ሲመሩ የነበሩት #ሼክህ_ሐሲና ሰሞኑን በመላ አገሪቱ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች በተቀሰቀሰው ህዝባዊ ተቃዋሞ ሳቢያ በዛሬው ዕለት አገራቸውን ጥለው ኮበለሉ።

የተማሪዎች ተቃውሞ ከተቀሰቀሰበት ከሳምንት በፊት ጀምሮ እስከዛሬ ድረስ 296 ንፁሃን ዜጎች በፖሊስ እንደተገደሉ ሪፓርቶች አመልክተዋል።ባለፉት ጥቂት ወራት በነበረው አገራዊ ምርጫ ድጋሚ እንዳሸነፉ በመገለፁ አገሪቱን ለቀው እስከኮበለሉበት ዛሬ ጥዋት ድረስ በጠቅላይ ሚኒስትርነት ሲያገለግሉ ነበር።

ብዙዎች የአገሪቱ ዜጎችም #አምባገነን ናቸው እያሉ ሲገልጿቸው እንደነበር መረጃዎች ያሳያሉ።በአገሪቱ በተቀሰቀሰው ተቃውሞም የሳቸው ደጋፊና ተቃዋሚ በሁለት ጎራ በመከፈል ርስ በራሳቸው ሲጋጩ ብሎም ሲጠፋፉ ታይቷል።

ባሁኑ ሰዓት አገሪቱን የመከላከያ ሰራዊት ተረክቦ እያስተዳደረ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን፣የቀድሞዋ የባንግላዲሽ ጠቅላይ ሚኒስትር ሼክህ ወደ ህንድ አገር እንደሸሹም ታውቋል።

@ethio_mereja_news
በወላይታ ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ዞን ካዎ ኮይሻ ወረዳ ጤፓ ቀበሌ ከረፋድ 5 ሠዓት አካባቢ በተከሰተ የመሬት ናዳ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ።

በተከሰተው አደጋ እስካሁን በተደረገ ፍለጋ የ11 ሰዎች አስክሬን መገኘቱንና የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ ይችላል ሲሉ የደቡብ ኢትዮጵያ ፖሊስ ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት እና ገጽታ ግንባታ ዳይሬክተር ኢንስፔክተር አሸናፊ ኃይሌ በተለይ ለብስራት ሬዲዮ ቴሌቪዥን ተናግረዋል ።

ህብረተሰቡ በሁሉም አካባቢ ከፍተኛ ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል ተብሏል።

@ethio_mereja_news
አንድ እንጀራ 35 ብር ገብቷል ፤ አምስት ሊትር ዘይት ወደ 2ሺህ ብር እየተንደረደረ ነው ›› - የስድስት ክልል ከተሞች ነዋሪዎች

የኑሮ ውድነትን አሻሽላለው ያለው መንግስት በዚ መልኩ የህዝቡን ችግር እያባባሰው ይገኛል።

@sheger_press
ብር 🇪🇹🇪🇹

የ 800ሜትር ሴቶች ውድድር ፍፃሜውን ሲያገኝ አትሌት ፅጌ ድጉማ ሁለተኛ ደረጃን በመያዝ ለሀገራችን ሁለተኛውን የብር ሜዳሊያ አስገኝታለች ።

1
ኛ ሆድኪንግሰን
2ኛ ፅጌ ድጉማ
3ኛ ሞራ
6ኛ ወርቅነሽ መሰለ
ከእስራኤል ሀገር መጥቶ ጎንደር የተሰዋዉ ጀግና ፋኖ
አስገራሚ ታሪክ👇👇
https://youtu.be/_fk4d_-YgHU?si=hGzq0Z1Yb_vUkFEV
2024/10/01 22:26:43
Back to Top
HTML Embed Code: