Telegram Web Link
ስድስት የግል ባንኮች በአዲሱ የውጭ ምንዛሬ ግብይት መጠቀም አልጀመሩም

የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ ምንዛሬ ተመን ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ “በገበያ ላይ የተመሰረተ” እንደሚሆን ቢያስታውቅም፤ ስድስት የግል ባንኮች የውጭ ገንዘቦችን የሚገዙበትን እና የሚሸጡበትን የተሻሻለ ተመን እስከ እኩለ ቀን ድረስ ይፋ አለማድረጋቸውን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገለጹ።

የየባንኮቹ ኃላፊዎች በተመኑ ላይ ለመነጋገር ዛሬ ረፋዱን በየፊናቸው ስብሰባ ተቀምጠው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

እስከ ዛሬ ድረስ በነበረው አሰራር ባንኮች የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዙበት እና የሚሸጡበትን ተመን የሚያወጣላቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ነበር።

ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ጠዋት ባወጣው መግለጫ፤ የውጭ ምንዛሬ ተመኑ “በባንኮች እና በደንበኞቻቸው መካከል ወደሚወሰንበት የገበያ ስርአት መሸጋገሩን” አስታውቋል።

ብሔራዊ ባንክ ከዚህ በኋላ “ገበያውን በማረጋጋት ላይ ያተኮረ” እንደሚሆንም ገልጿል። ይህን የብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ ለውጥ ተከትሎ የውጭ ምንዛሬ ተመኑን ከሁሉም አስቀድሞ ይፋ ያደረገው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነው።

የግል ባንኮች ያወጣሉ ተብሎ የሚጠበቀው የውጭ ምንዛሬ ተመን፤ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተመን ጋር “ተመሳሳይ ይሆናል” ብለው እንደሚጠብቁ “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያነገረቻቸው የአንድ የግል ባንክ ከፍተኛ ኃላፊ ተናግረዋል። ባንኮች ተመኑን የሚወስኑት ያላቸውን የውጭ መገበያያ ገንዘብ ክምችት መሰረት አድርገው መሆኑንም አክለዋል።

Via:- Ethiopian Insider

@ethio_mereja_news
የመውጫ ፈተና!

87 በመቶ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መውደቃቸው ተገለፀ!

ዘንድሮ በተሰጠው የመውጫ ፈተና 22 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አንድም ተማሪ አላሳለፋም ተባለ

የግል የከፍተኛ ተቋማት በ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ካስፈተኗቸው አጠቃላይ ተማሪዎች መካከል ያሳለፋት 13 በመቶ እንደሆነ ተነግሯል።

የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ አጠቃላይ ካስፈተኗቸው ተማሪዎች 58 በመቶ አሳልፈዋል ተብሏል። 202 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በዘንድሮ የመውጫ ፈተና ተማሪዎቻቸውን ቢያስፈትኑም 22ቶቹ አንድም ተማሪ ማሳለፍ እንዳልቻሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ(ኘ/ር) ተናግረዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የዉጭ ሀገር መረጃዎችን ፡ትንታኔዎችን እንደወጡ ለማግኘት የዩትይብ ቻናላችን ይወዳጁ👇👇👇https://youtu.be/erNVjpQTKk0?si=dA2_4ZsdYHKJ3Yw9
ጥቆማ‼️

ክሪፕቶና ኤርድሮፕን በተመለከተ የተለያዩ መረጃዎችን በስፋት የምንዳስስበትን ሁለተኛው ቻናላችንን join ብታደርጉ ትጠቀማላችሁ።


- Crypto trading
- Airdrop list
- Daily combo
- Updates and listing date

አሁንኑ ይቀላቀሉ👇👇
https://www.tg-me.com/sheger_crypto
https://www.tg-me.com/sheger_crypto
የውጭ ምንዛሪ ማግኘት የሚችሉት ተለይተው ታውቀዋል

1👉 የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት የተፈቀደላቸው የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ከኢትዮጵያ ውጭ የሚጓዙ ኢትዮጵያዊውያን ወይም በአገሪቱ ውስጥ የሚኖር የውጭ ዜጎች ናቸው።

2👉 ምንዛሪ ለማግኘት የሚፈልጉ ግለሰቦች ለበዓል ፣ ለትምህርት ፣ ለህክምና ጉዞዎች እና ሌሎች የግል ጉዳዮች እንደሚጓዙ የሚያሳይ ፓስፖርት፣ ሕጋዊ የመግቢያ ቪዛ እና የአየር ትኬት የማቅረብ ግዴታ ተጥሎባቸዋል።

3👉 ተጓዦች ከምንዛሪ ቢሮዎች እስከ 5 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ወይም የዚህ አቻ የሆነ የሌላ አገር ገንዘብ በጥሬ ወይም በክፍያ መፈጸሚያ ካርድ (debit card) አማካኝነት ማግኘት ይችላሉ።

4👉 የውጭ ምንዛሪ የባንክ ሂሳብ ያላቸው ተጓዦች እስከ 10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ድረስ ማግኘት ተፈቅዶላቸዋል።

5👉 በብሔራዊ ባንክ ካልተፈቀደ በስተቀር ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ነዋሪ በአንድ ጉዞ ላይ ከ10,000 የአሜሪካን ዶላር ወይም ተመጣጣኝ ገንዘብ በካሽ መያዝ አይችልም።

6👉 ለንግድ የሚጓዙ ግለሰቦችም የውጭ ምንዛሪ ማግኘት ይችላሉ።

7👉 የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ ፓስፖርት እና የአየር ትኬት ለሚያቀርቡ ለንግድ ድርጅት ተወካዮች የውጭ ምንዛሪ መሸጥ እንዲችሉ ተፈቅዷል። እነዚሁ ቢሮዎች ፦
- ለንግድ ድርጅቶች፣
- ለበጎ አድራጎት ተቋማት
- ለሃይማኖት ማኅበራት፣
- ለንግድ ትርኢቶች፣
- ለቱሪዝም
- ለባህል እና ለስፖርቶች አዘጋጆች የውጭ ምንዛሪ መሸጥ ይችላሉ።

8👉 የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ለመንግሥት ተጓዦች ለምግብ፣ ለማረፊያ እና ሌሎች ተያያዥ ወጪዎች ከ10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ወይም ተመጣጣኝ ገንዘብ የማይበልጥ የውጭ ምንዛሬ ሊሸጡ ይችላሉ።

9👉 ነዋሪ ላልሆኑ የውጭ አገር ዜጎች እና ቱሪስቶች ብርን ወደ ውጭ ምንዛሬ ሊለውጡ የሚችሉበት አሠራርም አለ። ፓስፖርት፣ ትክክለኛ ቪዛ እና የአየር ትኬት የሚያቀርቡ ሰዎች ያለማስረጃ እስከ 500 የአሜሪካን ዶላር መለወጥ ይችላሉ። ከ500 ዶላር በላይ መለወጥ የሚፈልጉ ከሆነ ፓስፖርት፣ ሕጋዊ ቪዛ፣ የአየር ትኬት እና ተመጣጣኝ የሆነው የውጭ ምንዛሪ በሕጋዊ መንገድ ወደ አገር ውስጥ ገንዘብ መቀየሩን የሚያሳይ የተረጋገጠ የባንክ ማስረጃ ማቅርብ ይጠበቅባቸዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ዶላር ጨምሯል በሚል ያለአግባብ የዋጋ ጭማሪ በሚያደርጉ ነጋዴዎች ላይ እርምጃ ይወሰዳል ተባለ

ኢትዮጵያ ያደረገችውን የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ የውጭ ምንዛሬ ይጨምራል በሚል አንዳንድ ነጋዴዎች አለአግባብ ዋጋ እየጨመሩ ይገኛሉ ተብሏል።

ምንም እንኳን የኢኮኖሚ ሪፎርሙ የዋጋ ንረት ማስከተሉ የሚገመት ቢሆንም የተጋነነ እና አግባብ ያልሆነ ጭማሪ በሚያደርጉት ላይ ግን ቁጥጥር እንደሚያደርግ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ለአራዳ ኤፍ ኤም ገልጿል።

ከዋጋ ጭማሪ ባሻገር ምርት የሚያከማቹና የሚደብቁ ነጋዴዎች ላይ የበር ለበር ክትትል ለማድረግም በምክትል ከንቲባ አቶ ጃንጥራር አባይ የሚመራና የተለያዩ አካላትን ያቀፈ ግብረኃይል መኖሩን ጣቢያችን ሰምቷል።

በተለይም ሆን ተብሎ የኑሮ ውድነትን በሚፈጥሩ አካላት ላይ እርምጃ እንደሚወስድ የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ተናግረዋል።(Arada_Fm)

@ethio_mereja_news
ዛሬ ሀምሌ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ንጋት 11:14 ሰዓት ላይ በንፋስ-ስልክ ላፍቶ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 14 ሰፈራ አካባቢ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የሶስት ሰዎች ህይወት ሲያልፍ አራት ሰዎች ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

አደጋዉ የደረሰዉ ሰባት ሰዎችን ጭኖ ሲጓዝ የነበረ አንድ ደብል ፒካአፕ ተሽከርካሪ በቆመ ከባድ ተሽከርካሪ ጋር በመጋጨቱ ሲሆን በዉስጡ ከነበሩ ሰባት ሰዎች ዉስጥ ሶስቱ ወዲያዉ ህይወታቸዉ ሲያልፍ ቀሪ አራት ሰዎች ከበድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

የኮሚሽኑ የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች በተለይ ጉዳት የደረሰባቸዉን ሰዎች ከተሽከርካሪዉ ወስጥ በማዉጣት ወደህክምና ተቋም የላኩ ሲሆን ህይወታቸዉ ያጡትን ሶስት ሰዎች አስከሬን አዉጥተዉ ለፖሊስ የአስረከቡ ሲሆን ዝርዝር የአደጋ ምክንያት በፖሊስ እየተጣራ ነዉ።

በሌላ በኩል ትላንት ምሽት 4:43 ሰዓት ላይ በንፋስ-ስልክ ላፍቶ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 10 አደይ አበባ አካባቢ በሚገኝ DN የጨረቃ ጨርቅ ፋብሪካ ላይ በአጋጠመ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ጉዳት ደርሷል።

በእሳት አደጋዉ በመጋዘን ዉስጥ የነበረ የጥጥ ክምችት ላይ ከባድ ጉዳት የደረሰ ሲሆን የእሳት አደጋዉ ወደፋብሪካዉ ማሽነሪዎችና ሌሎች ጨርቃ-ጨርቆች ላይ ተዛምቶ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ እሳቱን መቆጣጠር ተችሏል።

የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር 3:10 ሰዓት የፈጀ ሲሆን በአደጋዉ በሰዉ ላይ ምንም ጉዳት አልደረሰም።

መረጃውን ለፋስት መረጃ ያደረሰን አቶ ንጋቱ ማሞ የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ህዝብ ግንኙነት ባለሞያ ነው።

@sheger_press
የዉጭ ሀገር መረጃዎችን ፡ትንታኔዎችን እንደወጡ ለማግኘት የዩትይብ ቻናላችን ይወዳጁ👇👇👇https://youtu.be/erNVjpQTKk0?si=dA2_4ZsdYHKJ3Yw9
https://www.youtube.com/watch?v=XYbB67hq9UI
"የኤርትራ ክስ የኢትዮጵያን አየር መንገድ ስም የማጥፋት ሥራ በመሆኑ ክሱ ተቀባይነት የለውም" - አቶ መስፍን ጣሰው

የኢትዮጵያ አየር መንገድ፤ ከኤርትራ ሲቪል አቬሽን ባለሥልጣን የቀረበበትን ክስ “የአየር መንገዱን ስም የማጥፋት ሥራ በመሆኑ ተቀባይነት የለውም” ሲል ውድቅ አደረገ።የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ መስፍን ጣሰው ፤ የኤርትራ ሲቪል አቬሽን ባለሥልጣን በላከው ደብዳቤ ይህንን አጥፍታችኋል የሚል ምንም ዓይነት ማብራሪያ አልነበረውም ብለዋል።

ኢትዮጵያ አየር መንገድ በህይወት ያሉ “ለላብራቶሪ አገልግሎት የሚውሉ እንደ ጦጣ ያሉ እንሰሳትን ወደ አሜሪካ ያጓጉዛል” በሚል ከእንስሳት ተቆርቋሪ ተቋም ለሚነሳበት ቅሬታ፤ “ይህ ዓለም አቀፍ አሰራር ስለሆነ፤ ህጋዊ ፈቃድ የተሰጠው ከአሜሪካም ከሌላም ሀገር ህጋዊ ፈቃድ የተሰጠው ድርጅት እስከመጣ ድረስ ያንን የዓለም አቀፍ ህጉን ተከትለን እናጓጉዛለን” በማለት ምላሽ ሰጥተዋል።

አየር መንገዱ “ወታደሮችን ያጓጉዛል” በሚል ለሚነሳትበት ሌላኛው ቅሬታ፤ አቶ መስፍን ጣሰው” ወታደሮች በአውሮፕላኖች የሚሄዱበት አሰራር አለ፤ አየር መንገዱ ዓለሞ አቀፍ አሰራሮችን ጠብቆ ነው የሚሰራው” ብለዋል።አየር መንገዱ ሁለት አውሮፕላኖችን መድቦ ለየተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሰላም አስከባሪ ወታደሮች ብቻ ያጓጉዛል። በተለይ አንደኛው አውሮፕላን ለዚሁ ግልጋሎት ብቻ የተመደበ ነው ሲሆን ሁለተኛው ተጨማሪ ሲያስፈልግ አገልግሎት ይሰጣል ሲሉ ተናግረዋል።

Via Addis Standard

@sheger_press
የኢቢኤስ መዝናኛ ፕሮግራም አዘጋጁ ትንሳኤ ብርሃን በ1 ሚሊየን ብር የባሊ ፉድ ፕሮሰሲንግ አምባሳደር ሆነ

ባሊ ፉድ ፕሮሰሲንግ ሀላፊነቱ የተወሰነ ድርጅት (Balli Food Processing) ለሚያመርታቸው በማር ወለላ የተቀመመ QQ yammy snack እና በኦቾሎኒ ጣዕም ለሚያመርተው QQ coated peanut የኢቢኤስ የመዝናኛ እና የቁምነገር አዘጋጅ የሆነውን ትንሳኤ ብርሃንን የብራንድ አምባሳደር አድርጎ በዛርው እለት ሾሟል፡፡

@ethio_mereja_news
#MoE

የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ለሚያስመርቋቸው ተማሪዎች የሚሰጡት ዲግሪ የህትመት ሥራ በመንግሥት ሊከናወን ነው፡፡

የዲግሪ ህትመት ሥራው በሀገር ውስጥ እነደሚከናወንና አሰራሩም ከቀጣይ ዓመት ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚሆን የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትሩ ይህን ያሉት የትምህርትና ስልጠና ባለሥልጣን ትናንት ባዘጋጀው የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዳግም ምዝገባ የውይይት መድረክ ላይ ነው፡፡

"ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ዲግሪ በማሳተም ለተማሪዎቻቸው መስጠት አይችሉም" ያሉት ሚኒስትሩ፤ ዲግሪ የሚታተመው በትምህርት ሚኒስቴር በኩል እንደሚሆንና ለዚህም ተቋማቱ ክፍያ ለሚኒስቴሩ እንደሚፈፅሙ ገልፀዋል፡፡

ትምህርት ሚኒስቴር የተማሪዎቹን ዲግሪ የሚያትመው ተቋማቱ በሚልኩት መረጃ እና የተማሪዎቹ የሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ውጤትን መሰረት በማድረግ እንደሚሆንም ጠቁመዋል፡፡

አሰራሩ ተግባራዊ ሲደረግ በሀገሪቱ የሚታየውን የሐሰተኛ ዲግሪ ህትመት ለማስቆም እንደሚያስችል ሚኒስትሩ አስረድተዋል፡፡

መንግሥት የ Security Printing ሥራ በሀገር ውስጥ በ2017 ዓ.ም መጨረሻ አካባቢ እንደሚጀምር ሚኒስትሩ ተናግረዋል፡፡

@ethio_mereja_news
Breaking‼️

የተደረገው ድርድር ያስገኘው ውጤት ይፋ ሆኗል።
የዓለም ባንክ በዛሬው እለት the Ethiopia First Sustainable and Inclusive Growth Development Policy Operation በሚል ባወጣው መግላጫ ኢትዮጵያ እያከናወነች ላለችው የሀገር በቀል የኢኮኖሚ ሪፎርም ለመደገፍ በርካታ የድጋፍ ማዕቀፎችን ይፋ አድርጓል።
በዚህ መሰረት ዓለም ባንክ አሁን በቀጥታ ከሚሰጠው 7 ቢሊዮን ዶላር በተጨማሪ በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት 8.5 ቢሊዮን ዶላር በመጨመር ኢትዮጵያ በጠቅላላው 15.5 ቢሊዮን ዶላር ከዓለም ባንክ ብቻ ታገኛለች። ከዚህ በተጨማሪ
♦️ 1 ቢሊዮን ዶላር ቀጥተኛ ስጦታ (grant)
♦️ 500 ሚሊዮን ዶላር የእዳ ክፍያ እንዲራዘም፤
♦️ 320 ሚሊዮን ዶላር ዓለም አቀፍ የኢንቨስትመንት ትብብር (IFC)
♦️ 1.15 ቢሊዮን ዶላር የባለብዙ ወገን ኢንቨስትመንት ኤጀንሲ
♦️ 6 ቢሊዮን ዶላር በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት ለበጀት ድጎማ
♦️ 2.1 ቢሊዮን የአሜሪካ ዶላር ዓለም አቀፍ የፋይናንስ ትብብር ለኢንቨስትመንት የምታገኘውን ሲጨምር ኢትዮጵያ አሁን ከምታገኘው 7 ቢሊዮን ዶላር በተጨማሪ በሚቀጥሉት ሶስት ዓመታት በጠቅላላው 16̂.6 ቢሊዮን ዶላር ታገኛለች።

@ethio_mereja_news
አራት የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ሰራተኞች፤ በታጣቂዎች ታግተው ተወሰዱ‼️

በኦሮሚያ ክልል፣ ምስራቅ ሸዋ ዞን፣ ፈንታሌ ወረዳ በሚገኘው የመተሐራ ስኳር ፋብሪካ ተቀጥረው የሚሰሩ አራት ሰራተኞች፤ በ“ኦነግ ሸኔ” ታጣቂ ቡድን ታግተው መወሰዳቸውን የፋብሪካው ሰራተኞች ገለፁ።

የፋብሪካው ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አብዱልቃድር የሱፍ፤ በሰራተኞች ላይ እገታ ሲፈጸም በአስራ አምስት ቀናት ውስጥ የአሁኑ ለሁለተኛ ጊዜ መሆኑን ተናግረዋል።

የስኳር ፋብሪካው ሰራተኞች የታገቱት ባለፈው ቅዳሜ ሐምሌ 20፤ 2016 ጠዋት ሁለት ሰዓት ገደማ መሆኑን በዕለቱ በስራ ገበታቸው ላይ የነበሩ አንድ ሰራተኛ ተናግረዋል። ከታገቱት ሰራተኞች ሁለቱ የቀን ሰራተኞች ሲሆን ሌሎቹ በፋብሪካው የሱፐርቫይዝ እና የፎርማን የስራ ኃላፊነት ያላቸውን መሆኑንም አስረድተዋል።

“ሱፐርቫይዘሩ እና ፎርማኑ ‘ኤፍ አንድ’ ከሚባለው የሸንኮራ ማሳ አካባቢ ነው የተወሰዱት። ሁለቱ የቀን ሰራተኞች ‘ኤፍ ሃያ ስድስት’ ከሚባለው የሸንኮራ ማሳ አካባቢ ነው የወሰዷቸው። የሱፐር ቫይዘሩን መኪና አቃጥለዋል።

መኪናው ሲቃጠል የፌደራል ፖሊሶች በአካባቢው ደርሰው ነበር። ግን ምንም ማድረግ ሳይችሉ፤ ሰዎቹን ታጣቂዎቹ ይዘዋቸው ሄዱ” ሲሉ በፋብሪካው ለ26 ዓመታት ያገለገሉት ሰራተኛ አብራርተዋል።

ኢትዮጵያ ኢንሳይደር

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
እስራኤል እንዴት ኢራን ዉስጥ ገብታ የሃማሱን መሪ ገደለች
ቤይሩትም በቦምብ ተደብድባለች
👇👇
https://youtu.be/1f0IflxV8TM?si=itrGyrhBKtSJGcWF
ዶላር ጨምሯል በሚል የዋጋ ጭማሪ ባደረጉ የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃ መዉሰዱን  የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታወቀ

የአዲስ አበባ ንግድ  ቢሮ  በ13 የንግድ ድርጅቶች ላይ አስተዳደራዊ እርምጃ  መዉሰዱን ለኢትዮ ኤፍ ኤም አስታወቋል፡፡

ቢሮዉ ባደረገዉ የክትትል ስራ  በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ 11 እንዲሁም በየካ ክ/ከ 2 በድምሩ 13  የንግድ ድርጅቶች ላይ እርምጃመዉሰዱን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ ህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ሰውነት አየለ ለጣቢያችን ተናግረዋል።

የማክሮ ኢኮኖሚ ማሻሻያ ተከትሎ በምርቶች ላይ ጭማሪ ባሳዩ ነጋዴዎች ላይ  አስተዳደራዊ  እርምጃ መዉሰዱን ነግረዉናል፡፡

ንግድ ቢሮዉ  በከተማዉ በሚገኙ የንግድ ድርጅቶች ላይ ቁጥጥር እያደረገ መሆኑን ና ህብረተሰቡ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ድርጅቶችን ሲመለከት 8588 የነፃ መስመር ጥቆማ እንዲያደርስ አሳስበዋል ፡፡

አቤል እስጢፋኖስ (ethio_fm)

ሐምሌ 24 ቀን 2016 ዓ.ም

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Hamster‼️

ሀምስተርና ታፕ ስዋፕ የምትጫወቱ ሁሉ የግድ ይህን ቻናል መቀላቀል አለባቹ።

እጅግ ወሳኝ መረጃዎችን ያደርሳል።

በዚ Link ተቀላቀሉ👇👇👇

https://www.tg-me.com/+fzeZ2gn56UE3NTI0
https://www.tg-me.com/+fzeZ2gn56UE3NTI0
https://www.tg-me.com/+fzeZ2gn56UE3NTI0
😭😭😭

ያማል

ነብስ ይማር

እሁድ እለት ሰርጉን አለሙን ለማየት ሚስቱን ሊያገባ የነበረው ወጣት ሞቶ ተገኘ

ዮናስ ይባላል የአዲስ አበባ ልጅ ሲሆን እሁድ እለት በ21.11.2016 ሰርጉን ለመደገስ ዓለሙን ለማየት

ቤተሰቡ ና ራሱ ዮናስ ዝግጅት እያደረገ እያለ እንዲሁም የሰርጉ ታዳሚዎች የሰርግ ጥሪ ወረቀት ተቀብለው በነበሩበት ስአት ነው

ዮናስ የጠፋው ነገር ግን

ራሱን አጥፎቶ ነው የሚለው ምክንያት
ጉርሻዎች ያላሳመነ ሆኖ አግኝተነዋል

ጉርሻዎች ከአንዳንድ የቤተስብ አባል ጋር ከሰኞ እለት ጀምሮ ውይይት ያደረገን ሲሆን

ዮናስ ምንም አይነት ራሱን ሊያጠፋ የሚችልበት ሁኔታ ላይ እንዳልነበረ እንዲሁም በጣም ለሰርጉ ዝግጅ ና excited ሆኖ እንደነበረ አውቀናል::

በጣም ውስብስ ያለ ና የቤተሰብ ጣልቃ ገብነት እንዲሁም በሀብታም ቤተሰብ አሳዳጊነት ያደገ ልጅ ሲሆን እጅግ ዘመናዊ ምርመራ የሚያስፈልገው ሁኖ አግኝተነዋል

ስለዚህ የአዲስ አበባ ፖሊስ ምርመራውን ከክፍል ከተማው ፖሊስ ወስዶ እንደ አዲስ ምርመራውን አድርጎ የዚህ ልጅ ነብስ ፍትህ እንድታገኝ እንዲያደርግ በትህትና እንጠይቃለን::

እሁድ እለት ሰርጉ የነበረው
ዮናስም እለተ ሰኞ ቀብሩ ተፈፅሟል::

ነብስህ ይማረው ወንድማችን

@ethio_mereja_news
ኢቢኤስ እና አርቲስት ፍቃዱ ከበደ ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል።

ኢቢኤስ ሲኒማ ለተመልካቾቹ በየዕለቱ በሚያቀርበው ጥያቄው የአርቲስት ፍቃዱ ከበደ ፎቶን በመጠቀም "የዚህችን ተዋናይት ሙሉ ስም እና ከሰራቸው ፊልሞች  መካከል አንድ ጥቀስ ?" በማለት የጠየቀው ጥያቄ መነጋገሪያ ሆኗል።በዚህም ከአርቲስቱ ጋር ውዝግብ ውስጥ ገብተዋል።

አርቲስቱም በማህበራዊ ትስስር ገፁ " አንዳንድ ቴሌቪዥን ጣቢያዎች ነገር ፈልገዋችሁ ታዋቂ ለመሆን ሲሞክሩ አይገርምም?። በርግጥ ጉዳዩን ጠበቃዬ ይዞታል እኔ የ3 ልጆች አባት ፆታዬ ወንድ ኢትዮጵያዊ ነኝ። ከቴሌቪዥን ጣቢያው ጋር በቅርብ በጠረጴዛ ዙሪያ ውይይት የምናደርግ ይሆናል"

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/09/30 23:44:07
Back to Top
HTML Embed Code: