Telegram Web Link
 #Update #TPLF

" ' ስልጣን ልቀቅ አልለቅም ' በሚሉ የሁለት ቡድን ፍላጎት የህዝባችን ስቃይ እንዲራዘም አንሻም " - የህወሓት ማእከላዊ  የቁጥጥር ኮሚሽን አባላት

የህወሓት ማእከላዊ  የቁጥጥር ኮሚሽን አባላት ዛሬ መግለጫ ሰጥተው ነበር።

የኮሚሽኑ አባላት በጋራ በሰጡት መግለጫ " ትናንት ህዝባችን ላይ ያደረስነው ጉዳት በመረዳት ዛሬ መፀፀትና ለደህንነቱ መትጋት ይገባናል " ብሏል። 

" በኛ ጦስ ምክንያት በህዝባችን ላይ ሊከተል የሚችለው መከራ ከወዲሁ በመገንዘብ ሊካሄድ ከታሰበ ጉባኤ ራሳችንን አግልለናል " ሲሉ አሳውቀዋል።

" በህወሓት አቋም የሚባል ጠፍቶ ቦታውን ኔትወርክና መቦዳደን ተክቶታል " ሲሉም ገልጸዋል።

" ግልፅነት ፣ አሳታፊ አሰራር እና ዴሞክራሲ ጠፍቶ ስልጣንን አለአግባብ መጠቀም አይለዋል " ያሉት የኮሚሽን አባላቱ ፥ " 9 አባላት ያሉት የጉባኤ አዘጋጅ ኮሚቴ ለይስሙላ ቢቋቋምም ይህንን ወደ ጎን በመተው ስራውን የሚያከናውነው ሃይል የበላይነት አለኝ የሚል አካል ነው " በማለት ድርጊቱ አውግዘዋል።

" ' ስልጣን ልቀቅ አልለቅም ' በሚሉ የሁለት ቡድን ፍላጎት የህዝባችን ስቃይ እንዲራዘም አንሻም ፤ ከመተማመን መግባባትና ዴሞክራሲያዊ መንገድ ውጪ የሚካሄድ ህዝባዊ ጠቀሜታ ስለሌለው የዚሁ ተግባር አካልና ተባባሪ መሆን አንፈልግም " ብለዋል።

የኮሚሽኑ አባላት ፥ " አካሄዳችሁ አስተካክሉ ላለ አካልና ግለሰብ የሌለ ስም እየሰጡ ማጥላላት የትም አያደርስም " ያሉ ሲሆን " ከኔትወርክ እና መጠላለፍ ያልፀዳ ጉባኤ ማካሄድ ህዝብን ይጎዳል እኛም የዘህ ጉዳት ተባባሪ ላለመሆን ይካሄዳል ከሚባለው ጉባኤ ራሳችን አግልለናል " ሲሉ አሳውቀዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ታወጀ‼️

በኢትዮጵያ ለ3 ቀናት የሚቆይ ብሔራዊ ሐዘን ታወጀ‼️

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን ገዜ ወረዳ የደረሰውን የመሬት መንሸራተት አደጋ ተከትሎ ሕይወታቸው ላለፉ ዜጎች የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከነገ ጀምሮ ለ3 ቀናት የሚቆይ ብሔራዊ ሐዘን አውጇል።

@ethio_mereja_news
አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በጎፋ ዞን በደረሰው አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የ1 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አደረገ!

አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ለተጎዱ ወገኖች የአንድ ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርጓል፡፡

አርቲስት ቴዎድሮስ ካሳሁን በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው ድንገተኛ የመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ድጋፉን በማድረግ በአደጋው ህይወታቸውን ላጡ ወገኖች መጽናናትን ተመኝቷል፡፡

በጎፋ ዞን፣ ገዜ ጎፋ ወረዳ፣ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰው የመሬት መንሸራተት አደጋ ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች ለማገዝ የተለያዩ አካላት ድጋፋቸውን እያደረጉ ሲሆን፤ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎችም አደጋው በደረሰበት ስፍራ በመገኘት ተጎጂዎችን እያፅናኑ ይገኛል።

ከዚህ ጋር ተያይዞ በኢትዮጵያ ከነገ ጀምሮ ለሦስት ቀናት የሚቆይ ብሔራዊ ሐዘን ማወጁን የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያስታወቀ ሲሆን፤ ብሔራዊ ሐዘኑ የታወጀው በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰውን የመሬት መንሸራተት አደጋ የዜጎች ሕይወት በማለፉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

@ethio_mereja_news
አዲስ ገዳይ በሽታ በአለም ላይ ታይቷል‼️

ብራዚል በኦሮፖሼ ቫይረስ የመጀመሪያውን ሞት አስመዘገበች። 

የሀገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስቴር በቫይረሱ ​​በተያዙ ዝንቦች እና ትንኞች የተዛመቱ ሁለት ሴቶች በቫይረሱ ​​መሞታቸውን አስታውቋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የድምጻዊ ያሬድ ነጉ የሀዘን መግለጫ ከጎፋ ሳውላ

በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ ውድ ህይወታቸውን ባጡ ወገኖቻችን ምክኒያት የተሰማን ሀዘን ጥልቅ መሆኑን እየገለጽኩ፦ አቅም በፈቀደ መልኩ ለወገኖቻችን ድጋፍ ይሆን ዘንድ ከጓደኞቼ ጋ በመተባበር ይሄ ቢመጣ የተባልነውን አስጭነን በስፍራው ተገኝተናል።  ይሄ ድጋፋችን በዚህ ብቻ የማይቆም መሆኑን በመግለጽ ወገኖቻችን በፈለጉን ሁሉ ቅጽበት አቤት ብለን የምንገኝ ልጆቻቸው መሆናችንን ስንገልጽ በታላቅ አክብሮት ነው ሲል ድምጻዊው አመልክቷል።

@ethio_mereja_news
Update

" ጉባኤ በማካሄድ የሚፈጠር ግጭት አይኖርም  " - የህወሓት ሊቀመንበር

የህዝባዊ ወያነ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት) ሊቀመንበር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል (ዶ/ር ) ዛሬ ሀምሌ 20/2016 ዓ.ም በክልሉ ለሚገኙ የመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥተው ነበር። 

በዚህም ፥ ከ2 ቀናት በፊት አዲስ አበባ ድረስ በመሄድ ከኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚንስተር አብይ አሕመድ (ዶ/ር) እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት ማካሄዳቸውን ነው ገልጸዋል።

በውይይቱ ላይ ድርጅታቸው ህወሓት በሁለት ሳምንት ውስጥ እውቅና እንዲሰጠው የፌዴራል መንግሥትን መጠየቃቸውን አመልክተዋል።

" ጉባኤ በማካሄድ የሚፈጠር አንዳች ግጭት የለም " ያሉ ሲሆን " በአዲስ አበባ በነበረን ውይይትም ጥሩ መግባባት ላይ ደርሰናል " ሲሉ አክለዋል።
via Tikvahethiopia            

@ethio_mereja_news
የኬንያ ፕሬዚዳንት በመሬት መንሸራተት ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ

የኬንያ ፕሬዚዳንት ዊሊያም ሩቶ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተ የመሬት መንሸራተት አደጋ ሕይወታቸውን ላጡ ሰዎች የተሰማቸውን ሐዘን ገለጹ፡፡

ፕሬዚዳንቱ ባስተላለፉት ሐዘን መግለጫ መልዕክት÷ በአደጋው ሕይወታቸውን ላጡ ወገኖች በኬንያ መንግሥት እና ሕዝብ ስም የተሰማቸውን ሐዘን ገልጸዋል፡፡ ለሟች ቤተሰቦች እና ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች መጽናናትን ተመኝተው÷ ኬንያ ከኢትዮጵያ መንግሥትና ሕዝብ ጎን መሆኗን አረጋግጣለሁ ብለዋል፡፡(FBC)

@ethio_mereja_news
አሳዛኝ ዜና‼️

በተከዜ ወንዝ ወደ ዝቋላ በጀልባ ሲጎዙ የነበሩ 19 የሚደርሱ ሰዎች ሕይወት አለፈ!!

ከስሀላ ሰየምት ወደ ዝቋላ በጀልባ ተሳፍረው ሲጎዙ የነበሩ 19 ሰዎች ሕይወት አለፈ።

ትናንት ከቀኑ 6፡00 ገዳማ ከዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አሥተዳደር ስሃላ ሰየምት ወረዳ ወደ ዝቋላ ወረዳ በተከዜ ወንዝ በጀልባ ሲጎዙ ከነበሩት በግምት 26 ሰዎች ውስጥ 19 የሚደርሱ ሰዎች ሕይወታቸው ማለፉን የስሃላ ሰየምት ወረዳ ዋና አሥተዳዳሪ ሲሳይ ብሩ ገልጸዋል።

ከ26ቱ ሰዎች አንድ ሕጻንን ጨምሮ 7 ሰዎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ሕይወታቸው ተርፏል ያሉት አቶ ሲሳይ የሟቾቹ ቁጥር ከዚያ በላይ ሊኾን ይችላል ብለዋል።

አደጋው ከደረሰ በኋላ የሟቾችን አስከሬን ለመፈለግ በተደረገው ጥረት እስከ ዛሬ ድረስ ሁለት ሰዎች ብቻ አስከሬን መገኘቱን ተናግረዋል።

ዋና አሥተዳዳሪው እንደገለጹት ሕይወቱ የተረፈው አንድ ሕጻን ከፍተኛ ጉዳት ስላስተናገደ ወደ ሰቆጣ ተፈራ ኃይሉ መታሰብያ ጠቅላላ ሆስፒታል ሲላክ የተቀሩት ስድስቱ መሸሀ ጤና ጣብያ ገብተው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ነው።

ከአራት ዓመታት በላይ ከጥቅም ውጭ የኾነው እና እስከ ሰኔ ወር መጨረሻዎች ድረስ ይጠናቀቃል ተብሎ የነበረው ከስሃላ - ዝቋላ የሚያገናኘው የተከዜ የብረት ድልድይ በተያዘለት ጊዜ አለመጠናቀቁ የሰው ሕይወት መቅጠፉን እንዲቀጥል ምክንያት መኾኑን አቶ ሲሳይ ተናግረዋል።(አሚኮ)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ማስተር አብነት ከበደ።

ሰው በጠፋበት ሰው ሆኖ የተገኘ እንቁ ኢትዮጵያዊ።

እሱን አለማመስገን ትልቅ ንፉግነት ነው።

@ethio_mereja_news
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#NewsAlert

ብሄራዊ ባንክ፣ መንግሥት ከዛሬ ጀምሮ ለሚተገብረው በገበያ ላይ የተመሠረተ የውጭ ምንዛሬ ግብይት ተመን እና ለሌሎች የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች ማስፈጸሚያ 13 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላር ማግኘቱን የባንኩ ገዢ ማሞ ምኅረቱ ዛሬ በሰጡት መግለጫ አስታውቀዋል።

ማሞ፣ ገንዘቡ የተገኘው፣ ከዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ)፣ ከዓለም ባንክ እና ከወዳጅ ሀገራት በድጋፍ እና ሌሎች አማራጮች አማካኝነት መኾኑን ገልጸዋል።

10 ነጥብ 7 ቢሊዮን ዶላር ያህሉ ገንዘብ የተገኘው፣ ከዓለማቀፉ የገንዘብ ድርጅት (አይ ኤም ኤፍ)፣ ከዓለም ባንክ እና ከአበዳሪዎች መኾኑን ማሞ ተናግረዋል። ቀሪው 2 ነጥብ 8 ቢሊዮን ዶላር በማዕከላዊ ባንክ ተቀማጭ ሂሳብ እና በአገራት የገንዘብ ልውውጥ መልክ እንደተገኘ ተገልጧል።

ኾኖም 13 ነጥብ 5 ቢሊዮን ዶላሩ የዓለማቀፍ የፋይናንስ ኮርፖሬሽን እና ሌሎች ባለብዙ ወገኖች ወደፊት ለፕሮጀክቶች ከሚሰጧቸው የገንዘብ ድጋፎች ውጭ እንደኾነ ተጠቅሷል።

ገንዘቡ፣ የኢኮኖሚ ማሻሻያዎች የሚያስከትሏቸውን የሽግግር ወቅት ወጪዎች እና ገበያ-መር የኾነው የውጭ ምንዛሬ ግብይት ስርዓት የሚፈጥራቸውን ጫናዎች ለመቀነስ ይረዳል ተብሏል። [ዋዜማ] 📸 File

@ethio_mereja_news
ስድስት የግል ባንኮች በአዲሱ የውጭ ምንዛሬ ግብይት መጠቀም አልጀመሩም

የኢትዮጵያ መንግስት የውጭ ምንዛሬ ተመን ከዛሬ ጠዋት ጀምሮ “በገበያ ላይ የተመሰረተ” እንደሚሆን ቢያስታውቅም፤ ስድስት የግል ባንኮች የውጭ ገንዘቦችን የሚገዙበትን እና የሚሸጡበትን የተሻሻለ ተመን እስከ እኩለ ቀን ድረስ ይፋ አለማድረጋቸውን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገለጹ።

የየባንኮቹ ኃላፊዎች በተመኑ ላይ ለመነጋገር ዛሬ ረፋዱን በየፊናቸው ስብሰባ ተቀምጠው እንደነበር ለማወቅ ተችሏል።

እስከ ዛሬ ድረስ በነበረው አሰራር ባንኮች የውጭ ሀገር ገንዘቦችን የሚገዙበት እና የሚሸጡበትን ተመን የሚያወጣላቸው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ነበር።

ብሔራዊ ባንክ ዛሬ ጠዋት ባወጣው መግለጫ፤ የውጭ ምንዛሬ ተመኑ “በባንኮች እና በደንበኞቻቸው መካከል ወደሚወሰንበት የገበያ ስርአት መሸጋገሩን” አስታውቋል።

ብሔራዊ ባንክ ከዚህ በኋላ “ገበያውን በማረጋጋት ላይ ያተኮረ” እንደሚሆንም ገልጿል። ይህን የብሔራዊ ባንክ የፖሊሲ ለውጥ ተከትሎ የውጭ ምንዛሬ ተመኑን ከሁሉም አስቀድሞ ይፋ ያደረገው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነው።

የግል ባንኮች ያወጣሉ ተብሎ የሚጠበቀው የውጭ ምንዛሬ ተመን፤ ከኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ተመን ጋር “ተመሳሳይ ይሆናል” ብለው እንደሚጠብቁ “ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ያነገረቻቸው የአንድ የግል ባንክ ከፍተኛ ኃላፊ ተናግረዋል። ባንኮች ተመኑን የሚወስኑት ያላቸውን የውጭ መገበያያ ገንዘብ ክምችት መሰረት አድርገው መሆኑንም አክለዋል።

Via:- Ethiopian Insider

@ethio_mereja_news
የመውጫ ፈተና!

87 በመቶ የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ተማሪዎች የመውጫ ፈተና መውደቃቸው ተገለፀ!

ዘንድሮ በተሰጠው የመውጫ ፈተና 22 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት አንድም ተማሪ አላሳለፋም ተባለ

የግል የከፍተኛ ተቋማት በ2016 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ካስፈተኗቸው አጠቃላይ ተማሪዎች መካከል ያሳለፋት 13 በመቶ እንደሆነ ተነግሯል።

የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ደግሞ አጠቃላይ ካስፈተኗቸው ተማሪዎች 58 በመቶ አሳልፈዋል ተብሏል። 202 የግል ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት በዘንድሮ የመውጫ ፈተና ተማሪዎቻቸውን ቢያስፈትኑም 22ቶቹ አንድም ተማሪ ማሳለፍ እንዳልቻሉ የትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ(ኘ/ር) ተናግረዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የዉጭ ሀገር መረጃዎችን ፡ትንታኔዎችን እንደወጡ ለማግኘት የዩትይብ ቻናላችን ይወዳጁ👇👇👇https://youtu.be/erNVjpQTKk0?si=dA2_4ZsdYHKJ3Yw9
ጥቆማ‼️

ክሪፕቶና ኤርድሮፕን በተመለከተ የተለያዩ መረጃዎችን በስፋት የምንዳስስበትን ሁለተኛው ቻናላችንን join ብታደርጉ ትጠቀማላችሁ።


- Crypto trading
- Airdrop list
- Daily combo
- Updates and listing date

አሁንኑ ይቀላቀሉ👇👇
https://www.tg-me.com/sheger_crypto
https://www.tg-me.com/sheger_crypto
የውጭ ምንዛሪ ማግኘት የሚችሉት ተለይተው ታውቀዋል

1👉 የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት የተፈቀደላቸው የመጀመሪያዎቹ ሰዎች ከኢትዮጵያ ውጭ የሚጓዙ ኢትዮጵያዊውያን ወይም በአገሪቱ ውስጥ የሚኖር የውጭ ዜጎች ናቸው።

2👉 ምንዛሪ ለማግኘት የሚፈልጉ ግለሰቦች ለበዓል ፣ ለትምህርት ፣ ለህክምና ጉዞዎች እና ሌሎች የግል ጉዳዮች እንደሚጓዙ የሚያሳይ ፓስፖርት፣ ሕጋዊ የመግቢያ ቪዛ እና የአየር ትኬት የማቅረብ ግዴታ ተጥሎባቸዋል።

3👉 ተጓዦች ከምንዛሪ ቢሮዎች እስከ 5 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ወይም የዚህ አቻ የሆነ የሌላ አገር ገንዘብ በጥሬ ወይም በክፍያ መፈጸሚያ ካርድ (debit card) አማካኝነት ማግኘት ይችላሉ።

4👉 የውጭ ምንዛሪ የባንክ ሂሳብ ያላቸው ተጓዦች እስከ 10 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ድረስ ማግኘት ተፈቅዶላቸዋል።

5👉 በብሔራዊ ባንክ ካልተፈቀደ በስተቀር ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ነዋሪ በአንድ ጉዞ ላይ ከ10,000 የአሜሪካን ዶላር ወይም ተመጣጣኝ ገንዘብ በካሽ መያዝ አይችልም።

6👉 ለንግድ የሚጓዙ ግለሰቦችም የውጭ ምንዛሪ ማግኘት ይችላሉ።

7👉 የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ሕጋዊ የንግድ ፈቃድ፣ ፓስፖርት እና የአየር ትኬት ለሚያቀርቡ ለንግድ ድርጅት ተወካዮች የውጭ ምንዛሪ መሸጥ እንዲችሉ ተፈቅዷል። እነዚሁ ቢሮዎች ፦
- ለንግድ ድርጅቶች፣
- ለበጎ አድራጎት ተቋማት
- ለሃይማኖት ማኅበራት፣
- ለንግድ ትርኢቶች፣
- ለቱሪዝም
- ለባህል እና ለስፖርቶች አዘጋጆች የውጭ ምንዛሪ መሸጥ ይችላሉ።

8👉 የውጭ ምንዛሪ ቢሮዎች ለመንግሥት ተጓዦች ለምግብ፣ ለማረፊያ እና ሌሎች ተያያዥ ወጪዎች ከ10 ሺህ የአሜሪካን ዶላር ወይም ተመጣጣኝ ገንዘብ የማይበልጥ የውጭ ምንዛሬ ሊሸጡ ይችላሉ።

9👉 ነዋሪ ላልሆኑ የውጭ አገር ዜጎች እና ቱሪስቶች ብርን ወደ ውጭ ምንዛሬ ሊለውጡ የሚችሉበት አሠራርም አለ። ፓስፖርት፣ ትክክለኛ ቪዛ እና የአየር ትኬት የሚያቀርቡ ሰዎች ያለማስረጃ እስከ 500 የአሜሪካን ዶላር መለወጥ ይችላሉ። ከ500 ዶላር በላይ መለወጥ የሚፈልጉ ከሆነ ፓስፖርት፣ ሕጋዊ ቪዛ፣ የአየር ትኬት እና ተመጣጣኝ የሆነው የውጭ ምንዛሪ በሕጋዊ መንገድ ወደ አገር ውስጥ ገንዘብ መቀየሩን የሚያሳይ የተረጋገጠ የባንክ ማስረጃ ማቅርብ ይጠበቅባቸዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/09/29 23:20:14
Back to Top
HTML Embed Code: