Telegram Web Link
ይህ ድርጊት ከባህል፣ከእሴት፣ከስነልቦና አኳያ ሲታይ በርካቶች "ፀያፍ ድርጊት" መሆኑን አውስተዋል‼️

እነዚህ በምስሉ ላይ የሚታዩት አባቶች እና እናቶች እንዲህ በጉልበታቸው እንዲሄዱ ተደርገው በኋላም የተወሰኑት የተገደሉት "የአማራ የሰላም ካውንስል አባል ናችሁ" በሚል ምክንያት ነበር። ድርጊቱ የተፈፀመው የፋኖ ሀይሎች በሚገኙበት ጎጃም ውስጥ ደቡብ ሜጫ ላይ መሆኑ ታውቋል።

ድርጊቱን አዛኝ የሚያደርገው የድርጊቱ ሰለባዎች ከሰላም ካውንስሉ ጋር ምንም ግንኙነት የሌላቸው የአካባቢው ነዋሪዎች እና የአንድ የጤና ተቋም (NGO) ሰራተኞች መሆናቸው ነው።

ከተገደሉት ውስጥ የወረዳ ቤተ ክህነት ስራ አስኪያጁ መርጌታ ግሩም፣ የሀገር ሽማግሌ አቶ አዘነ አድማሱ፣ የሀገር ሽማግሌ አቶ አስማማው አቤ፣ ወ/ሮ የኔአየሁ ዳኛው የተባሉ የከተማው ነዋሪ ይገኙባቸዋል ተብሏል፣ ሌሎች 13 አሁንም በእስር ላይ ይገኛሉ።

ኤልያስ መሰረት

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Update‼️

የኤርትራ አቬሽን ባለስልጣን የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ከመስከረም 20/2017ዓ.ም በኋላ እንዲያቆም መወሰኑን ቀደም ብዬ መዘገቤ ይታወሳል።

በዚህ ዙሪያ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ይህንን ውንጀላውን እንደማይቀበል እና የስም ማጥፋት እንደሆነ ገልጿል።

አየር መንገዱ "በሰማነው ድንገተኛ ውሳኔ አዝነናል፣ በውሳኔው ዙርያ ማብራርያ ለማግኘት ሙከራዎች እያደረግን ነው" ብሏል።

#ኤልያስመሰረት

@ethio_mereja_news
በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ የደረሰውን ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋን በተመለከተ ከኢትዮጵያ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን ባገኘነው ወቅታዊ መረጃ መሰረት

- አስከሬናቸው የተገኙ ወገኖች ቁጥር 194 ደርሷል
- 600 የሚሆኑ ዜጎች ከመኖሪያቸው ተፈናቅለዋል
- የፌደራል መንግስት በኮሚሽኑ በኩል ከ3000 በላይ ለሚሆኑ ዜጎች 520 ኩንታል ምግብና ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች እርዳታ አቅርቧል
- 100 ምግብ ነክ ያልሆኑ ቁሳቁሶች ጥቅል አድርሷል። እያንዳንዱ ጥቅል ለ5 ሰዎች ያገለግላል።
- በአጠቃላይ 5.7 ሚሊዮን ብር የሚገመት የሰብዓዊ ድጋፍ አድርጓል።
ከዚህ በዘለለም ኮሚሽኑ ተጨማሪ የነፍስ አድን ስራው እንዲቀጥልና በአደጋው የስነ-ልቦና ጉዳት የደረሰባቸውም እንዲያገግሙ ከአካባቢው አስተዳደር ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል። ወደ ስፍራው የተላከው አጣሪ የጥናት ቡድን ሁኔታውን እያየ ተጨማሪ ድጋፍ የሚያደርግ ይሆናል።

ተጨማሪ መረጃዎችን ለህዝብ ይፋ ማድረጉንም ይቀጥላል።እስከዛሬዋ እለትም የአካባቢው ማህበረሰብ የሟቾች አስከሬንን በማፈላለግ፣ የተጎዱትን በመንከባከብና ለተፈናቀሉትም መጠለያ በማዘጋጀት በፍፁም ሰብአዊነት ላበረከተው አስተዋፅኦ መንግስት ታላቅ ምስጋና ያቀርባል።

-የመንግስት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት

@ethio_mereja_news
Hamster‼️

hamster ለምትጫወቱ በሙሉ የግድ ይህን ቻናል መቀላቀል ይኖርባችኋል።

ሁሉንም በዝርዝር ይከታተሉ👇👇
https://www.tg-me.com/+fzeZ2gn56UE3NTI0
https://www.tg-me.com/+fzeZ2gn56UE3NTI0
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አጋጥሞኝ ነበር ባለዉ የሲስተም ችግር ገንዘብ ወስደዋል የተባሉ ሁለት ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ

ግለሰቦቹ ባንኩ በሰጠዉ ጥቆማ መያዛቸዉና ክስ እንደተመሰረተባቸውም ሰምተናል


የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም ተፈጠረብኝ ባለዉ ችግር ምክንያት ከ 238 ሺህ በላይ በሆኑ ግብይቶች ከ 800 ሚሊዮን ብር በላይ ተወስዶበት እንደነበር ይታወሳል።

ባንኩ በወቅቱ አለአግባብ ገንዘብ የወሰዱ ሰዎች በፈቃደኝነት ገንዘቡን እንዲመልሱ ፥ ያልመለሱትንም በህግ እንደሚጠይቅ በተደጋጋሚ ግለጾ ነበር።

@ethio_mereja_news
ATTENTION ‼️

በገዜ ጎፋ ወረዳ በደረሰው ድንገተኛ የመሬት ናዳ ምክንያት ብዙ ወገኖቻችን ጉዳት ደርስባቿል ሁላችንም ባለን አቅም ወደ  8091 የተቻለውን የገንዘብ መጠን በመላክ ጉዳት የደረሰባቸውን ወገኖቻችንን እንደግፍ ።

ሁላችንም የቻልነውን መጠን እናግዝ 🙏

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ፀድቋል‼️

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማዋ ያሉ የመንግስት ሰራተኞች በማህበር ተደራጅተው ቤት የሚገነቡበትን አሰራር አፀደቀ‼️

በከተማዋ የሚኖሩና የቤት ችግር ያለባቸውን ነዋሪዎች ችግር በሚቀርፍ አግባብ የከተማ አስተዳደሩ መሬት፣ የሚገነቡ የጋራ መኖሪያ ህንፃዎች ዲዛይን፣ ማህበራቱን የማደራጀትና ግንባታው በሚጀመርበት ጊዜ የመቆጣጠር ሀላፊነት የሚወስድ ሆኖ በማህበር ተደራጅተው የጋራ ህንጻ የሚገነቡ ሰራተኞች፣ መምህራንና የጤና ባለሙያዎች የፀጥታ አካላት ከተደራጁ በኋላ ቁጠባ በአግባቡ መቆጠብ የሚችሉና አስተዳደሩ በሚያዘጋጀው ዲዛይን መሰረት ከፍታቸውን የጠበቁ ህንፃዎች ለመገንባት ዝግጁ የሆኑ ወደ ግንባታ እንዲገቡ ማድረግ የሚያስችል ደንብ ትናንት ምክር ቤቱ ያፀደቀ ሲሆን ዝርዝር የአፈፃፀም ሂደቱ በከተማዋ ካለው የቤት አቅርቦት ማህቀፍ ጋር ተጣጥሞ እንዲፈፀም ውሳኔ አሳልፏል።

@ethio_mereja_news
አየር ጤና መናሀሪያ ፊት ለፊት በደረሰ የእሳት አደጋ 11 የመኖሪያና የንግድ ሱቆች ወደሙ

ሀምሌ 17 ቀን 2016 ዓ.ም ምሽት 2ሰአት ከ30 ላይ በኮልፌ ቀራኒዮ ክፍለ-ከተማ ወረዳ አንድ አየር ጤና መናሃሪያ ፊት ለፊት በደረሰው የእሳት አደጋ በመኖሪያና በንግድ ሱቆች ላይ ጉዳት ማድረሱን የአዲስ አበባ የእሳት አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

በእሳት አደጋዉ አሰራ አንድ አነስተኛ የንግድ የመኖሪያ ቤቶች የተቃጠሉ ሲሆን በአንድ ሰዉ ላይ ቀላልጉዳት መድረሱን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።የአደጋ ጊዜ ሰራተኞችና የአካባቢዉ ማህበረሰብ ባደረጉት ርብርብ የእሳት አደጋዉ በአቅሪቢያ ባሉ የንግድ ህንጻዎችና መኖሪያ ቤቶች ተዛምቶ ተጨማሪ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር  ስለመቻሉም ኮሚሽኑ አስታውቋል።

በአካባቢዉ ከዚህ ቀደም ተመሳሳይ አደጋ ያጋጠመ ሲሆን የንግድና የመኖሪያ ቤቶቹ የተገነበቡት ግብዓት በቆርቆሮና በላሜራ ተጠጋግተዉ የተገነቡ እና ነደጅ በችርቻሮ የሚሸጥበት ስፍራ መሆኑን የገለፁት አቶ ንጋቱ ይኸም በቀላሉ ለእሳት አደጋ መከሰትና መባባስ ምክንያት ሆናል ብለዋል።

የእሳት አደጋዉን ሙሉ በሙሉ ለመቆጣጠር  ሁለት ሰዓት የፈጀ ሲሆን የአደጋዉ መንስዔ በፖሊስ እየተጣራ ነዉም ተብሏል።

@ethio_mereja_news
ጎፋ‼️

በደቡብ ኢትዮጵያ ጎፋ ዞን በደረሰው ተከታታይ የመሬት መንሸራተት አደጋ የሞቱ ሰዎች ቁጥር እስከ 500 ሊደርስ እንደሚችል የተባበሩት መንግሥት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት ገለጸ።

ጽህፈት ቤቱ ከአካባቢው ባለሥልጣናት ያገኘውን መረጃ መሠረት አድርጎ ባወጣው የሁኔታዎች መግለጫ ላይ ነው በአደጋው ሕይወታቸውን ያጡ ሰዎች አሃዝ እስከ 500 ሊደርስ እንደሚችል ያመለከተው።

እሁድ ሐምሌ 14 እና ሰኞ ሐምሌ 15/ 2016 ዓ.ም. በደቡብ ኢትዮጵያ በጎፋ ዞን ገዜ ጎፋ ወረዳ ኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት መንሸራተት አደጋ ተቀብረው የጠፉ ሰዎችን የማፈላለጉ ሥራ ዛሬም ለአራተኛ ቀን እየተካሄደ ነው።

በአደጋው ስፍራ የሚገኙት የቢቢሲ ዘጋቢዎች እንደገለጹት ዛሬን ጨምሮ በአካባቢው እየጣለ ባለው ዝናብ ውስጥ ጭምር ከተንሸራተተው መሬት ስር ለማውጣት የሚደረገው የነፍስ አድን ጥረት ቀጥሏል።

ባለፉት ቀናት በተደረጉት የፍለጋ ጥረቶች በአደጋው ሕይወታቸው አልፎ የተገኙ ሰዎች ቁጥር 257 የደረሰ ሲሆን፣ የሟቾች ቁጥር እስከ 500 ሊደርስ እንደሚችል የአካባቢው አስተዳዳሪዎች ስጋታቸውን መግለጻቸውን የመንግሥታቱ ድርጅት የሰብዓዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ ጽህፈት ቤት (ኦቻ) አመልክቷል።

@ethio_mereja_news
የህወሓት ሊቀመንበር ዶክተር ደብረፂዮን ገ/ሚካኤል ከፌዴራል መንግስትና ምርጫ ቦርድ ጋር በአዲስ አበባ  በነበራቸው ውይይት “ህገወጥ ጉባኤ ካድረጋችሁ በህግ እንደምትጠየቁ እወቁ” የሚል መልስ ተሰጥቷቸው ዛሬ ወደ መቐለ መመለሳቸው ተሰምቷል።

ጠ/ሚ አብይ አሕመድ በተቃዋሚዎች ስብሰባ ላይ ህወሓትን ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በዚሁ ንግግራቸው ላይ ከህወሃት ጋር የገባንበት ቀዉስ ይታወሳል:: ምን ያክል ሰው እንደወደመ፣ ምን ያክል ሃብት እንደወደመ መገመት ትችላላቹህ:: ያ የወደመ ሃብት፣ የወደመ የሰው ህይወት በትክክል ሳይገመገም ፣ እንዴት ጠፋ ሳይባል ፣ ሌላ ጥፋት ማምጣት ጥሩ አይደለም፣ ህዝብ ይጎዳል።

ህወሃት አሁን ማድረግ ያለበት ምርጫ ቦርድ ጋር ሄዶ፣ በ 2-3 ሳምንት ዉስጥ የሚጠበቅበትን ዶክመንት አሟልቶ፣ በሕጋዊ መንገድ ተመዝግቦ ፣ ነው ጉባኤ ማካሄድ ያለበት:: ባያደርግ'ሳ ? እኔ ብፈልግም ባልፈልግም ዋጋ የለዉም፣ ምርጫ ቦርድ ካልተቀበለው፣ TPLF'ን ሕጋዊ ፓርቲ ካላለው ፣ በምርጫ ሊሳተፍ አይችልም ፣ መንግስት ሊሆን አይችልም:: ምን ማለት ነው ተመልሰን ደግሞ ጦርነት እንገባለን ማለት ነው"ማለታቸው ይታወሳል።

ህወሃት በበኩሉ እንደ አዲስ ፓርቲ መመዝገብ አልፈልግም፣የቀድሞ ህጋዊ ሰውነቴ ይመለስልኝ እያለ ይገኛል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
እንኳን ለቅዱስ ገብርኤል ዓመታዊ ክብረ በዓል በሰላም አደረሳቹ።

መልካም በዓል።

@ethio_mereja_news
ዓመታዊው የቅዱስ ገብርኤል የንግሥ በዓል እየተከበረ ነው

ዓመታዊው የቅዱስ ገብርኤል የንግሥ በዓል በቁልቢ እና ሐዋሳ በተለያዩ ሐይማኖታዊ ሥነ-ሥርዓቶች እየተከበረ ነው፡፡

የንግሥ በዓሉ በየዓመቱ ሐምሌ 19 ቀን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋኅዶ ቤተ-ክርስቲያን ምዕመናን ዘንድ በድምቀት ይከበራል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/09/29 21:34:18
Back to Top
HTML Embed Code: