Telegram Web Link
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ6ተኛ ክፍል ውጤት ይፋ አደረገ‼️

ቢሮው የ2016 የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና የማለፊያ ነጥብ 50 ከመቶ እንዲሆን ተወስኗል ብሏል፡፡

ለአካል ጉዳተኛ ተማሪዎች ደግሞ 45 ከመቶ እንዲሆን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የአጠቃላይ ካውንስል አባላት ወስኗል፡፡

በ2016 የ6ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ከወሰዱ 85ሺ 46 በመንግስትና በግል ትምህርት ቤቶች በቀን እና በማታ ትምህርታቸውን ከተከታተሉ ተማሪዎች መካከል 94 ነጥብ 3 የሚሆኑ ተማሪዎች 50 ከመቶ እና ከዚያ በላይ አምጥተዋል፡፡

ቀሪ 5 ነጥብ 7 ከመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ማለፊያ ነጥብ አላመጡም ሲል ትምህርት ቢሮው ካወጣው መረጃ ለመረዳት ተችሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አያት  ሪልስቴት  የቤትና  አክሲዮን ሽያጭ(51.38%) ትርፍ

ታልቅ የዋጋ ቅናሽ  ከአያት ሪል እስቴት 79,971 ብር በካሬ
       በኮዶሚኔም ዋጋ
72ካሬ ባለ 2 መኝታ ተጨማሪ የሰራተኛ ክፍል ያለዉ
      ጠቅላላ ዋጋዉ
                    5,757,912 ብር
          ቅድመ ክፍያ 8% =460,633ብር
105ካሬ ...ባለ 3 መኝታ ተጨማሪ የሰራተኛ ክፍል ያለዉ
       ጠቅላላ ዋጋዉ
                           8,396,955
                ቅድመ ክፍያ 8% = 671,756
125 ካሬ  ባለ 3 መኝታ ተጨማሪ የሰራተኛ ክላስ
      ጠቅላላ ዋጋዉ
                        9,996,375 ብር
    ቅድመ ክፍያ 8% =799,710 ብር
138 ካሬ ባለ 4 መኝታ ተጨማሪ የሰራተኛ ክፍል
ጠቅላላ ዋጋዉ .=11,035,998 ብር
ቅድመ ክፍያ  8%  =882,880ብር

እንዲሁም "ስምንት(8)" እህት ኩባንያዎችን ያካተተዉ   እና  51.38% አመታዊ ትርፍ ያከፋፈለዉ አያት "አክሲዮን"በመሸጥ ላይ ነዉ::
በ2015... የ1,000,000 አክሲዮን የነበራቸዉ 513,000 ብር አትርፈዋል።
ለበለጠ መረጃ... 0912622404
አትሌት ቀነኒሳ በቀለ የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ አፍሪካዊ ስፖርተኛ ተብሏል።

ኢትዮጵያ እና ኬኒያ ሁለት አትሌቶችን በማስመረጥ ቀዳሚውን ደረጃ ይዘዋል።

ኢትዮጵያዊው የረጅም ርቀት ሯጭ አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ቀዳሚውን ደርጃ ሲይዝ ኬንያዊው የረጅም ርቀት ሯጭ ኤሉድ ኪፕቾጌ ሁለተኛ እንዲሁም ካሜሮናዊው የእግር ኳስ ጥበበኛ ሳሞኤል ኤቶ ሶስተኛ ደረጃን ይዘዋል።

በሴቶች የዚምቧብዌዋ የዋና ስፖርት ተወዳዳሪ ክርስቲ ኮቨንትሪ ቀዳሚውን ደርጃ ስትይዝ ኢትዮጵያዊቷ የረጅም ርቀት ሯጭ አትሌት ጥሩነሽ ዲባባ በሴቶች ሁለተኛ በሁለቱም ጾታ ደግሞ አምስተኛ ደረጃ ላይ መቀመጥ ችላለች።

አይቮሪኮስታዊው ዲድየር ድሮግባ ፣ ኬኒያዊቷ ፌዝ ኪፕዬጎን ፣ ደቡብ አፍሪካዊው ጃኩዌስ ካሊስ ፣ ናይጀሪያዊቷ አሲሳት ኦሽዋላ እንዲሁም ግብጻዊው ሞሃመድ ሳላህ ከስድስተኛ እስከ አስረኛ ያለውን ደረጃ ይዘዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
''በአትሌቲክስ ጉዞዬ ለረዱኝ ሁሉ ልባዊ ምስጋናዬን መግለጽ እፈልጋለሁ''።

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ

ዛሬ ESPN የ21ኛው ክፍለ ዘመን ምርጥ አትሌት በሚል መረጃ መጋራቱን ተከትሎ አትሌት ቀነኒሳ የምስጋና ምላሽ ሰጥቷል !

እንደዚህ አይነት ክብር ያለው ማዕረግ መቀበል በእውነት ትልቅ ክብር ነው፣ በአትሌቲክስ የህይወት ጉዞዬ ሁሉ ለረዱኝ ልባዊ ምስጋናዬን መግለጽ እፈልጋለሁ ሲል አትሌት ቀነኒሳ በይፋዊ ማህራዊ ትስስር ገፁ ፅፏል ።

በእኔ እምነት ስላላቸው ሁሌም አዲስ ከፍትና ውጤት እንድደርስ ለሚያነሳሱኝ አድናቂዎቼ ጓደኞቼ ቤተሰቦቼ ምስጋና አቀርባለው ሲል መልእክት አስተላልፏል ።

(ባላገሩ ስፖርት)

@ethio_mereja_news
#Update ‼️

" ባነር አሰርተን ልመና ወጥተናል ገንዘብ ግን እየተገኘ አይደለም " - የታጋች ተማሪ ቤተሰብ

ትምህርት አጠናቀው ወደ ቤተሰቦቻቸው እየተመለሱ የነበሩ ከ2ኛ እስከ 4ኛ ዓመት የደባርቅ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች “ ገብረ ጉራቻ ” የሚባል ቦታ ሲደርሱ መታገታቸው አይዘነጋም።

ተማሪዎቹ የታገቱት ሰኔ 26/2016 ዓ/ም ከጠዋቱ 4:00 ሰዓት ገደማ ሲሆን፣ ብዛታቸው በትክክል ባይታወቅም ደባርቅ ዩኒቨርሲቲ እንዲሁም ከእገታው ያመለጡ ተማሪዎች በሁለት ታታ አውቶብስ የነበሩ መሆናቸውን በወቅቱ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸው ነበር።

ከታጋቾቹ መካከል አንዳንዶቹ ከፍተኛ ብር ከፍለው መለቀቃቸውን መግለጻቸውም ይታወሳል።

@ethio_mereja_news
የፖሊስ አዛዡ በቁጥጥር ስር ዋሉ።

በወላይታ ዞን በሙስናና በህገ ወጥ ተግባር የተጠረጠረ የዳሞት ወይዴ ወረዳ የፖሊስ አዛዥ ቁጥጥር ስር መዋሉን የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ም/ኮ/ር ንጋቱ ጌታቸዉ አስታወቁ።

በወላይታ ዞን ዳሞት ወይዴ ወረዳ ከኮንትሮባንድ ኔጋዴዎች ጋር በመተባበር ወንጀል ሲፈጽም በመገኘት የተጠረጠረ የወረዳዉ ፖሊስ አዛዥ በቁጥጥር ስር ሆኖ ምርመራ መቀጠሉን የዞኑ ፖሊስ አዛዥ ም/ኮ/ር ንጋቱ ጌታቸዉ አስታውቀዋል።

ከመንግስትና ከህዝብ የተሰጠዉን ኃላፊነት ወደ ጎን በመተዉ ከህገ ወጥ ኔጋዴዎችና ኮንትሮባንድስቶች ጋር በመተባበር ከወላይታ ሶዶ እስከ ሞያሌ ድረስ የሌብነት መስመር በመዘርጋት የዞኑንና የወረዳዉን ህጋዊ ኔጋዴዎች እንዲዳከሙ ከማድረጉም በላይ መንግስት የጀመረዉን የብልፅግና ጉዞ የሚያደናቅፍ ተግባር መፈጸሙን የወረዳዉ አጠቃላይ የፖሊስ አመራርና አባላት በተገኙበት በተደረገ የግምገማ መድረክ በመረጋገጡና በሙስናና ብልሹ አሰራር የተዘፈቀ መሆኑ ገልጸዋል።

በከተማ ዉስጥ በተለያየ የወንጀል ተግባር የሚጠረጠሩና ህገ ወጥ ኔጋዴዎች ጋር ባለዉ ትስስር የህግ የበላይነት እንዳይረጋገጥ እያደረገ እንደሆነም ጠቅሰዋል።

በፖሊስ ጣቢያ ዉስጥ ከወንጀል ጋር በተያያዘ የሚገኙ የተለያዩ ኤግዚቢት ንብረት በመሸጥና ጉቦ ተቀብሎ በመልቀቅ ወንጀል በመጠርጠሩና ሌሎች በርካታ ብልሹ አሠራሮችን መፈጸሙ የተረጋገጠበት ሁኔታ በመኖሩ ትጥቃቸዉን ፈተዉ ታስረዉ ምርመራ እየተጣራ መሆኑንም አስታውቀዋል።

በአዛዡ ላይ የተጀመረዉ ምርመራ እንደተጠናቀቀ ክስ እንደሚመሰረት ጠቅሰዉ የመጨረሻ ዉጤት ለህዝብ ይፋ እንደሚደረግም ገልጸዋል።
(ምንጭ፦ የወላይታ ዞን ፖሊስ መምሪያ)

@ethio_mereja_news
ሰበር ዜና ‼️

ባይደን ከቀጣዩ ምርጫ ራሳቸውን አገለሉ

የዩናይትድ ስቴትስ ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን "ለፓርቲዬ እና ለሀገሬ ይበጃል" በማለት በድጋሚ ለመመረጥ የሚያደርጉትን እጩነታቸውን እንደሚያቋርጡ አስታውቀዋል። ዋይት ሀውስ ለመግባት የሚደረገው ፉክክር በተቃረበበት እና አሜሪካውያን ወደ ምርጫው ከማቅናታቸው ከአራት ወራት በፊት ነው።

በሰኔ ወር መጨረሻ በተደረገው የምርጫ ክርክር ከሪፐብሊካኑ ዶናልድ ትራምፕ ደካማ የክርክር አፈፃፀም ማሳየታቸውን ተከትሎ ከዲሞክራቶች ባልደረቦቻቸው ሳይቀር ለሳምንታት የዘለቀ ከፍተኛ ጫና ሲደረግባቸው ነበር። በማህበራዊ ሚዲያ ላይ በለጠፉት መረጃ በፕሬዝዳንትነት ማገልገሌ በሕይወቴ ውስጥ ትልቅ ክብር ነው ብለዋል።

እናም በድጋሚ ለመመረጥ አላማዬ ቢሆንም፣ በቀሪው የስራ ዘመኔ በፕሬዚዳንትነቴ ሀላፊነቴን መወጣት ላይ ብቻ በማተኮር ከምርጫው መገለሌ ለፓርቲዬ እና ለሀገሬ ይጠቅማል ብዬ አስባለሁ ብለዋል።በሚቀጥለው ሳምንት በጉዳዩ ላይ ለህዝቡ መልዕክት እንደሚያስተላልፉ ተናግረዋል። ፕሬዝዳንት ባይደን ምክትል ፕሬዚዳንቱን ካማላ ሃሪስን አመስግነዋል፣ ልዩ አጋር ነበረች ብለዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የመንግስት ሚዲያዉ በሞት ለተለዩት ሲሞንፒየትሮ ሳሊኒ (አባት)፥ የልጃቸውን ምስዕል ተጠቀመ

በትናንትናው እለት ህይወታቸው ባለፈው የ 'ዊ ቢዩልድ' ወይም በቀድሞው ስሙ 'ሳሊኒ ኮንስትራክሽን' መስራች እና ባለቤት በሲሞንፒየትሮ ሳሊኒ ህልፈት ዙርያ ዋልታ በሰራው ዘገባ ላይ የተጠቀመው ምስል አሳሳች መሆኑን ተመልክተናል።

በዜና ዘገባው ላይ ምስላቸው የተቀመጠው የአሁኑ የድርጅቱ ዋና ስራ አስኪያጅ የሆኑት ፒየትሮ ሳሊኒ ናቸው። ፒየትሮ ሳሊኒ የሲሞንፒየትሮ ሳሊኒ ልጅ ናቸው።

ሚድያዎች የሚጠቀሟቸውን ምስሎች፣ ቪድዮዎች እንዲሁም ሌሎች መረጃዎች ለህዝብ ከማድረሳቸው በፊት ማጣራት (fact check) በማድረግ ለህዝቡ የጠራ መረጃ ማድረስ ይጠበቅባቸዋል።

ሳሊኒ እንደ ህዳሴ ግድብ፣ የጊቤ ሀይል ማመንጫ ግድቦች እንዲሁም ሌሎች ትላልቅ ሀገራዊ ፕሮጀክቶች ላይ ለበርካታ አስርት አመታት የተሳተፈ ግዙፍ የጣልያን የግንባታ ተቋም ነው።

Via EthiopiaCheck

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
"ከዚህ በኃላ በወረቀት የሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና እየቀነሰ በበይነ መረብ የሚሰጠው ፈተና ቁጥር እየጨመረ የሚሔድ ይሆናል፡፡" - ትምህርት ሚኒስቴር

የዘንድሮው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና በወረቀት እና በኦንላይን መሰጠቱ ይታወቃል፡፡ ለመጀመሪያ ጊዜ በኦንላይን በተሰጠው ፈተና 29,718 ተማሪዎች በበይነ መረብ መፈተናቸውም ተገልጿል፡፡

"የመሠረተ ልማት ሥራና የኮምፕዩተሮች አቅርቦትን አጠናክሮ በመቀጠል ወደፊት ሙሉ በሙሉ በበይነ መረብ ለመስጠት እየተሠራ እንደሚገኝ" ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል፡፡

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን ከሦስት ዓመት በኋላ ሙሉ በሙሉ በበይነ መረብ ለመስጠት መንግሥት አቅዶ እየሰራ እንደሚገኝ ከዚህ ቀደም መግለፁ ይታወሳል፡፡

@ethio_mereja_news
የሶማሊያ መንግሥት ከግብጽ ጋር የተደረሰውን ወታደራዊ ስምምነት አጸደቀ

የሶማሊያ መንግሥት ከወራት በፊት ከግብፅ ጋር ተደርሷል የተባለውን ወታደራዊ ስምምነት ተግባራዊ እንዲሆን ማፅደቁ ተገለጸ::

የሶማሊያ ካቢኔ ዝርዝሩ ይፋ ያልሆነ ወታደራዊ ስምምነት አርብ ሐምሌ 12/2016 ዓ.ም. ባደረገው ስብሰባ ላይ ማጽደቁን የአገሪቱን ብሔራዊ ቴሌቪዥን ጣቢያን ዋቢ አድርጎ ቢቢሲ ዘግቧል።

ኢትዮጵያ #ሶማሊላንድ ጋር የፈረመችውን የባህር በር ስምምነት ተከትሎ የሶማሊያው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሼክ ሞሐሙድ ከግብፁ አቻቸው አብዱል ፋታህ አል-ሲሲ ጋር በስልክ ተነጋግረው የነበረ ሲሆን በወቅቱ አል-ሲሲ “ግብፅ ከሶማሊያ ጎን ለመቆም ያላትን ጠንካራ አቋም” መግለፃቸው ተነግሮ ነበር::

የሶማሊያ እና የግብጽ መሪዎች ባለፈው ጥር ወር በአካል ግብጽ ካይሮ ተገናኝተው ወታደራዊ ስምምነትን የሚጨምር በተለያዩ ጉዳዮች ላይ ትብብር ለማድረግ ስምምነት እንደሚፈራረሙ የተነገረ ሲሆን አሁን ላይ የሶማሊያ መንግሥት ካቢኔ ያፀደቀው ወታደራዊ ስምምነት የሁለቱ መሪዎች የካይሮ ቆይታ ውጤት ሊሆን እንደሚችል ተገልጿል::

ኢትዮጵያ እና ሶማሊላንድ የተፈራረሙትን የባሕር በር ስምምነትን ተከትሎ ሶማሊያ ከግብጽ በተጨማሪ ከቱርክ መንግሥት ጋር ባለፈው የካቲት 1/2016 ዓ.ም. “የሶማሊያን የባሕር ኃይል ለማሠልጣን እና ለማስታጠቅ እንዲሁም በአካባቢው ያለውን የባሕር ላይ ደኅንነት ለማስጠበቅ ያለመ” ነው የተባለን ወታደራዊ ስምምነት መፈራረሟ ይታወሳል::

@ethio_mereja_news
ጥቆማ‼️

እንዳያመልጣቹ ስልካቹን ብቻ በመጠቀም ምንም ገንዘብ ማውጣት ሳይጠበቅባቹ ::

እንዴት ገንዘብ መስራት እንደምትችሉና ስለ ክሪፕቶ በዝርዝር።

ሁሉንም የONLINE ስራዎች በዝርዝር በዚ ቻናል ያገኛሉ።

በርግጠኝነት ትወዱታላቹ በዚ LINK አሁንኑ ተቀላቀሉ👇👇
http://www.tg-me.com/sheger_crypto
http://www.tg-me.com/sheger_crypto
⚡️የዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የሥራ ሃላፊዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ።

ሃላፊዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በሙስናና በሃብት ምዝበራ ተጠርጥረው ነው።

በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚዳንት ሀብታሙ አበበ (ዶ/ር) እና ምክትል ፕሬዚዳንቱ ታምራት ታገሰ (ዶ/ር) ይገኙበታል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አሳዛኝ ዜና‼️

በጎፋ ዞን በደረሰ የመሬት ናዳ የ20 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ የሟቾች ቁጥር ሊጨምር እንደሚችል ተነገረ

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በጎፋ ዞን በገዜ ጎፋ ወረዳ በኬንቾ ሻቻ ጎዝዲ ቀበል ሰኞ ከረፋዱ 4:00 ሰዓት አካባቢ በደረሰ ድንገተኛ የመሬት ናዳ አደጋ የበርካታ ሰዎች ሕይወት አልፏል።

የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ምስክር ምትኩ አደጋውን አስመልክተው በሰጡት መግለጫ፥  እሰካሁን በተደረገው ፍለጋ ከ 20 በላይ አስከሬን መገኘቱንና የሟቾች ቁጥር ሊያሻቅብ እንደሚችል ገልጸዋል።
በስፍራው ለነፍስ አድን ተግባር የተሰበሰቡ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ  የአካባቢው ነዋሪዎች የአደጋው ሰለባ መሆናቸውን አቶ ምስክር ተናግረዋል።

በአደጋው ሰለባ ከሆኑት ሰዎች መካከል የወረዳው ፖሊስ አባላትን ጨምሮ ሴቶችና ሕፃናት እንደሚገኙ ተገልጿል።በአሁኑ ሰዓት የአስክሬን ፍለጋና የነፍስ አድን ሥራው ተጠናክሮ መቀጠሉን ዋና አስተዳዳሪው ተናግረዋል።

የዞኑ አደጋ ስጋት ሥራ አመራር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ማርቆስ መለሰ በበኩላቸው በአደጋው ጉዳት የደረሰባቸውን የህብረተሰብ ክፍሎችን በመለየት የነፍስ አድን ሥራ እየተከናወነ መሆኑን የጎፋ ዞን መንግስት ኮምንኬሽን መረጃ ያመላክታል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/09/29 17:35:12
Back to Top
HTML Embed Code: