Telegram Web Link
የግድያ ሙከራ የተደረገባቸው ዶናልድ ትራምፕ ከሆስፒታል ወጡ።

የቀድሞው ፕሬዝዳንት በኒውጀርሲ ወደሚገኘው የጎልፍ ክለባቸው ማቅናታቸውን አሶሼትድ ፕረስ ዘግቧል።

በፔንሲልቫኒያ የምርጫ ቅስቀሳ ላይ እያሉ የግድያ ሙከራ የተደረገባቸው ትራምፕ ቀኝ ጆሯቸው ላይ ጉዳት ደርሶባቸው ፊታቸው በደም ተሸፍኖ ታይቷል።

ትራምፕ ላይ የግድያ ሙከራውን ያደረገው ግለሰብ በአሜሪካ ሚስጢራዊ የደህንነት ባለሙያዎች ወዲያውኑ መገደሉም ተገልጾ ነበር።

የአሜሪካ የፌደራል ምርመራ ቢሮ (ኤፍቢአይ) ከጥቂት ስአት በፊት ባወጣው መግለጫ ትራምፕ ላይ የተኮሰው ግለሰብ ቶማስ ማቲው የተባለ የ20 አመት ወጣት ነው ብሏል።

ማቲው ከፍ ያለ ቦታ ላይ ሆኖ ወደ ትራምፕ እና የምርጫ ቅስቀሳው ታዳሚዎች ደጋግሞ ሲተኩስ ሚስጢራዊ ጠባቂዎቹ በፍጥነት ሊያስቆሙት ያለመቻላቸው ጉዳት አነጋጋሪ ሆኗል።(አልአይን)

@ethio_mereja_news
Internet‼️

ከ330 ቀናት እገዳ በኋላ ዛሬ ከንጋት 12:00 ጀምሮ ኢንተርኔት የተለቀቀላቸው የአማራ ክልል ከተሞች
👉ደሴ
👉ኮምቦልቻ
👉ከሚሴ
👉እንጅባራ
👉ፍኖተ ሰላም
👉ቡሬ
👉ባህር ዳር
👉ደብረ ማርቆስ
👉ደጀን
👉 ጎንደር
👉ደብረ ታቦር
👉ሁመራ
👉ገንደውሃ
👉ደብረ ብርሃን
👉ወልዲያ
👉ባቲ
👉ከሰቆጣ ናቸው።
(wasu)

@ethio_mereja_news
አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ አሜሪካ መግባቱ ተሰማ

እውቁ ተዋናይ አማኑኤል ሚያዝያ 15/2016 ዓ.ም ወደ እስራኤል እየሄደ በፀጥታ አካላት ተይዞ በአዲስ አበባ በእስር መቆየቱ ይታወሳል ።

አርቲስቱ አሁን ከእስር ከተፈታ በኋላ ወደ አሜሪካ ማቅናቱን ከወዳጁ ያሬድ ሹመቴ ፅሁፍ ያመላክታል።

@ethio_mereja_news
አርቲስቱ ታመመ‼️

ተወዳጁና ተጫዋቹ አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ በፀና ታሞ በህንድ Rela ሆስፒታል ይገኛል

ፈጣሪ በምህረት እጁ ይዳብስህ ነፂ🙏🙏

አርቲስት እና የማስታወቂያ ባለሙያ ነፃነት ወርቅነህ ለሕክምና ሕንድ ሃገር በሚገኘው Rela Hospital እንደሚገኝ ከቅርብ ወዳጆቹ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።

በሰላም_ተመለስልን
(ኪንኪንግ ኪያ)

@ethio_mereja_news
መልካም ዜና‼️

አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ በተሻለ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ አስታወቀ!!

ተዋናይ፣ ደራሲ፣ ዳይሬክተር እና የቴሌቪዥን ፕሮግራም አቅራቢው ነፃነት ወርቅነህ ለህክምና ወደ ሀገረ ህንድ መሄዱን የሚገልጽ ማስታወሻ በግል የፌስ ቡክ ገፁ ማጋራቱ ይታወሳል።

ይህን ተከትሎ በርካታ ወዳጆቹ ፣ የሙያ አጋሮቹ እና አድናቂዎች ለአርቲስቱ መልካም ምኞታቸውን ሲገልፁ ነበር።

ገሚሶቹ ደግሞ አርቲስቱ ላይ ያጋጠመው የጤና እክል የከፋ ይሆናል የሚል ስጋታቸውን ጭምር ሲገልፁ እንደነበር ይታወሳል።

ያም ሆኖ ግን አርቲስቱ ጉዳዩን አስመልክቶ በማህበራዊ ትስስር ገፁ ባጋራው መልዕክቱ በመልካም ጤንነት ላይ እንደሚገኝ አስታውቋል።

በተጨማሪም መልካም ምኞታቸውን ለተመኙለት ምስጋናውን በማቅረብ በጥቂት ቀናት ውስጥ የህክምና ክትትሉን አገባዶ ወደ ሀገር ቤት እንደሚመለስ ተናግሯል።

አርቲስቱ በፌስ ቡክ ገፁ ያጋራውን መልዕክት የዝግጅት ክፍላችን ከመረጃው ጋር አያይዞታል፣ ሸገር ፕረስ አርቲስት ነፃነት ወርቅነህ ወደ ቀደመ ጤንነቱ እንዲመለስ ይመኛል።

@sheger_press
@sheger_press
በሲም ካርዳችን ወንጀል ከሚሰሩና ከሚዘርፉ አጭበርባሪዎች ራሳችን እንዴት እንጠብቅ?

የሰዎችን የስልክ ቁጥር የራስ በማስመሰል የሚሰሩ የማጭበርበር ወንጀሎች መበራከታቸው ተነግሯል።

ይህን ስራ የሚሰሩት አጭበርባሪዎች ወደ ቴሌኮም ኩባንያ በመደወል ስልካቸው እንደተሰረቀ ወይም እንደተበላሸ በመንገር የሰዎችን ስልክ ቁጥርን ወደራሳቸው በማዞር ነው ገንዘብ እና ግላዊ ሚስጥሮችን የሚመነትፉት።

የስልክ ቁጥሩ ባለቤት ስልኩ እጁ ላይ እያለ የሚደወሉ ስልኮች እና መልዕክቶች በአጭበርባሪዎቹ እጅ የሚገባ ሲሆን ቀጥሎም የባንክ እና ዲጂታል መገበያያ መተግበርያ የይለፍ ቃሎችን በመቀየር አጭበርባሪዎቹ ያሻቸውን ማድረግ ይችላሉ ተብሏል።

Via:alain
@ethio_mereja_news
የብልፅግና ፓርቲ ስራ አስፈፃሚ ነገ ግምገማ ሊያካሂድ ነው
ብልፅግና ፓርቲ በአመራሩና አባላቱ ላይ ምንም አይነት ግምገማ አካሂዶ የማያውቅ ሲሆን ነገ ጀምሮ ለግምገማ ስብሰባ ሊቀመጥ መሆኑ ተሰምቷል።

ፓርቲው በመላ ሀገሪቱ ያሉ ግጭቶችን ወጥቶ ወደ ሰላምና ልማት ለመመለስ ግምገማው ይጠቅመዋል ተብሎ ይጠበቃል።

ብልፅግና በተለያዩ ጊዚያት የተለያዩ አመራሮቹን ከስልጣን የሚያወርድና የሚያወጣ ቢሆንም ምንም አይነት ግምገማ ግን አድርጎ በህግም ሲጠቅ አይታወቅም እየተባለ ይተቻል ።

ፓርቲው በቀጣይ ለሚያደርገው እንቅስቃሴ ስራ አስፈፃሚውን መገምገም ግዴታ ሆኖበታል።

ፓርቲዎ በከፍተኛ ሙስና የደለቡ ንፁሃንን በማሰርና በማሰቃየት በመግደል ስራ የተሰማሩ የፌዴራል ፓሊስና መሰል ተቋማት አመራሮችን ፈትሾ ተጠያቂ ለማድረግ ሊወስን ይገባል ሲሉ አስተያየት ሰጭዎች ይናገራሉ።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
🔈 #የመምህራንድምጽ

" አይደለም ያለ ደመወዝ በደመወዝም እንኳን ኑሮን አልቻልነውም ፤ ደመወዛችን በአግባቡ ሊከፈለን ይገባል " -  መምህራን
 
ከየካቲት ወር 2016 ጀምሮ #እየተቆራረጠ 50% ፣ 30% እየተከፈለ ቆይቶ እስከ የሰኔ ወር ሳይጨምር ውዝፍ ደመወዝ ከ70 እስከ 120% አልተከፈለንም ያሉ በጎፋ ዞን የአይዳ ፣ ገዜ ጎፋ እና ደምባ ጎፋ ወረዳ መምህራን ቅሬታቸዉን ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሰምተዋል።

" ያለደሞዝ አይደለም በደሞዝም ኑሮን አልቻልነዉም " የሚሉት መምህራኑ " ስቃያችን መች ነዉ የሚያበቃው ? " ሲሉ ቅሬታቸዉን ገልጸዋል።

ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ቃሉን የሰጠው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል መምህራን ማህበር፥ " የመምህራኑን ድምጽ በተደጋጋሚ ለሚመለከተዉ አካል ሳሳዉቅ ቆይቻለሁ " ብሏል።

መምህራኑም አቤቱታቸውን ለሚመለከተው አካል አቅርበው እንደነበርም አስረድቷል።

ነገር ግን የዞኑ አስተዳደር እና የትምህርት መምሪያው ጥያቄያቸውን ተቀብሎ ተገቢውን ምላሽ ባለመስጠቱ መምህራኑ የአመራሩን ምላሽ እየተጠባበቁ እንደሚገኝ ገልጿል።

ከሰምኑ እነዚህ መምህራን ጥያቄያቸውን በሰላማዊ ሠልፍ ለመጠየቅ ሲሞክሩ  የዞኑ መምህራን ማህበር ከአመራሩ ጋር ውይይት እያደረገ በመሆኑ ሠልፍ እንዳይወጡና በትዕግስት እንዲጠብቁ በማድረግ መመለሱን ማህበሩን አሳውቆናል።

ይሁና መምህራኑ ባልተደራጀ ሁኔታም ቢሆን ጥያቄ ለማቅረብ ወደተለያዩ የወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤቶች መሄዳቸውና በዛም " በዚህ ደረጃ መቀጠል አንችልም ደሞዛችን በአግባቡ ሊከፈለን ይገባል !! " በማለት ድምጻቸዉን ማሰማታቸዉ ተገልጿል።

እንዲህ አይነት ጥያቄዎች ካሁን በፊትም በሌሎች የክልሉ ዞኖች ውስጥም መስተዋላቸውን አንስተን ጥያቄ ያቀረብንላቸው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊዉ ዶክተር ታምራት ይገዙ ፤ "  ችግሩን እንደ ክልል ከየካቲት ወር ጀምሮ መቅረፍ ተችሏል " ሲሉ ገልጸዋል።

አሁን ላይ የመምህራንን ደሞዝ በተመለከተ አሰራሩ ዲሴንትራላይዝ ተደርጎ ለየዞኖቹ መሰጠቱን የገለጹት ኃላፊዉ " እኛ ቴክኒካል ድጋፍ እያደረግን ብቻ ነው ያለው " በማለት የደመወዝ ጉዳይ ለነሱ መሰጠቱን ጠቁመዋል።

" ችግሩ በዚህ ደረጃ ከተስተዋለ ግን ገምግመን ድጋፍ የምንሰጥ ይሆናል " ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።(tikvahethiopia)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
"ባካሄድነው ጥናት 90 በመቶ ተማሪ ኮራጅ መሆኑን ደርሰንበታል"-አለማየሁ ተ/ማሪያም(ዶ/ር)‼️

በኢትዮጵያ የኩረጃ ደረጃ ምን ያህል ነው? ሀገርንስ ምን ያህል ይጎዳል? በሚል በ2004 በተደረገ ጥናት 90 በመቶ የሚሆኑ ተማሪዎች ኮራጅ መሆናቸው ተረጋግጧል ሲሉ በአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ የአካቶ ትምህርት ክፍል ተመራማሪ የሆኑት አለማየሁ ተ/ማሪያም (ዶ/ር) ገልፀዋል፡፡

ተመራማሪው በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዳጉ ፕሮግራም በነበራቸው ቆይታ፤ በቀደመው የትምህርት ሥርዓት የመመዘኛ ፈተናዎች የሚሰጡበት ሂደት ለኩረጃ ምቹ እንደነበሩ ተናገረዋል፡፡

ተማሪዎች በፈተና ወቅት የማያውቁትን ጥያቄ መልስ ከሌሎች ለመቅዳት ድሮም ይሞክሩ እንደነበር ገልጸው፤ አሁን ላይ ሥር ሰዶ በዘመቻ መል የሚካሄድ ሆኗል ሲሉ ነው የተናገሩት፡፡

ተማሪዎች ከትምህርቱ በበለጠ የኩረጃ መንገዶችን ያጠናሉ የሚሉት ተመራማሪው፤ በጥናቱ 27 የሚሆኑ የኩረጃ ዘዴዎች እንዳሉ ደርሰንበታል ብለዋል፡፡

በዚህ ሂደት ውስጥ ተማሪዎች ብቻ ሳይሆኑ ወላጆች ልጆቻቸው እንዲያልፉ ከመፈለግ አንፃር እንዲሁም መምህራን፣ ርዕሰ መምህራን፣ የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊዎች ጭምር ለኩረጃው እገዛ እንደሚያደርጉ ይናገራሉ፡፡

ይህም ፈተናውን አልፈው ወደ ዩኒቨርስቲ የሚገቡ ተማሪዎች የሥብዕና ጉድለት እንደሚታይባቸው እዲሁም መሰረታዊ የሆነው መፃፍ እና ማንበብ ሲቸግራቸው እንመለከታለን ይላሉ፡፡

ተመራማሪው፤ ከፈተና አሰጣጥ በተጨማሪ ለግምት አጋላጭ የሆኑ የፈተና ዓይነቶችን ለማስተካከል መስራት እንደሚገባ አዲሱ የፈተና ሥርዓት ያመላከተ መሆኑንም ይናገራሉ፡፡
በተለይም የተጀመረው የበይነ በረብ (ኦን ላይን) ፈተና አሰጣጥ ሲጠናከር የተንሰራፋውን የኩረጃ መጠን በመቀነስ እና ተማሪዎችን በማብቃት ረገድ ላቅ ያለ ሚና ይኖረዋል ነው ያሉት፡፡

@ethio_mereja_news
የአሜሪካዉ ፕሬዝዳንት ጆባይደን በትራምፕ ላይ የተሞከረዉን የግድያ ሙከራ ተከትሎ የፖለቲካዉ ውጥት እንዲቀንስ ጥሪ አቀረቡ ፡፡

ፖለቲካ በፍፁም የዉጊያ  ሜዳ መሆን የለበትም ፈጣሪ የግድያ አዉድማን አጥብቆ ይከላከላል ሲሉ ነዉ  ጆባይደን ጥሪ ያቀረቡት ፡፡

በቅዳሜው የድጋፍ ሰልፍ ላይ ትራምፕ  የግድያ ሙከራ ከተደረገባቸው በኃላ  አሜሪካውያን “በአንድነት እንዲቆሙ” ጠይቀዋል።

ባይደን ሀገሪቱ ወዴት እያመራች እንደሆነ እና ማን ይመራታል በሚለው ላይ አለመግባባት ቢኖርም ፖለቲካ "የሰላማዊ የውይይት መድረክ" መሆን እንዳለበት ደጋግመው አሳስበዋል።

የእኛ እምነት የቱንም ያህል ጠንካራ ቢሆን ወደ ሁከት መግባት የለብንም ሲሉ አክለዋል፡፡

ለጥቃቱ ሪፐብሊካኖች ጣታቸዉን በዲሞክራቲኮች ላይ እየቀሰሩ ይገኛል ዘጋርዲያን ዘግቧል፡፡

አቤል እስጢፋኖስ

ምንጭ ኢትዬ ኤፍ ኤም


@ethio_mereja_news
ለጥንቃቄ‼️

በኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ የዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ ማዕከል ከሚደርሱ የወንጀል ጥቆማዎች መካከል ከፍተኛውን ቁጥር የያዘው አጭበርባሪዎች ከባንክ የተደወለ በማስመሰል ‘'የሞባይል ባንኪንግ አገልግሎትን እናስተካክላለን’' በሚል እና ሌሎች አሳሳች መልዕክቶችን በመጠቀም በባንክ ደንበኞች ሂሳብ ላይ የሚፈፀም ስርቆት መሆኑን ፖሊስ በቅርቡ ሥራ ላይ በዋለው ዘመናዊ ቴክኖሎጂ ማረጋገጡን አስታውቋል፡፡

በባንኮች አሠራር መሰረት ከሞባይል ባንኪንግ አገልግሎት ጋር በተያያዘ ደንበኞች ወደ ባንክ ቅርንጫፍ በአካል ሳይሄዱ በስልክ ተደውሎ የሚሰጥ ምንም ዓይነት አገልግሎትም ሆነ የአሠራር ሂደት እንደለለ ባንኮች ለፖሊስ አሳውቀዋል።

በመሆኑም የባንክ ደንበኞች በስልክ የሚደርሱ ማናቸውንም ዓይነት ጥያቄዎች እንዳያስተናግዱ እና ከአጭበርባሪዎች ገንዘባቸውን እንዲጠብቁ እንዲሁም መሰል የማጭበርበር ድርጊቶች ሲያጋጥሙ የተደወለበትን ስልክ ቁጥር በዜጎች ተሳትፎ መተግበሪያ (EFPApp) የፎቶ፣ የቪዲዮ እና የፅሁፍ መረጃ በመላክ ወይም በ991 ነፃ የስልክ መስመር ላይ በመደወል ጥቆማ እንድትሰጡ የኢትዮጵያ ፌደራል ፖሊስ ጥሪውን አቅርቧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለአዲሱ በጀት ዓመት የ230 ነጥብ 39 ቢሊዮን ብር ረቂቅ በጀት ለከተማዋ ምክር ቤት ማቅረቡን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።

ረቂቅ በጀቱ፣ የከተማዋ አስተዳደር ተጨማሪውን በጀት ጨምሮ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት ከተጠቀመው አጠቃላይ በጀት የ68 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ጭማሪ እንዳለው ከአስተዳደሩ ፋይናንስ ቢሮ መስማቱን ዘገባው ጠቅሷል።

ከአዲሱ ረቂቅ በጀት 62 በመቶውን ድርሻ የሚይዘው የካፒታል ወጪው እንደኾነና 38 በመቶው ደሞ ለመደበኛ ወጪዎች እንደተመደበ ዜና ምንጩ አመልክቷል።

@ethio_mereja_news
በትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ‼️

በድሬዳዋ አሥተዳደር ጀሎ በሊና ቀበሌ ቢርካ አካባቢ ሌሊት 6፡30 ገደማ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ11 ሰዎች ሕይወት አለፈ፡፡

ከሟቾች በተጨማሪም በ10 ሰዎች ላይ የአካል ጉዳት መድረሱን ድሬዳዋ አሥተዳደር ፖሊስ መረጃ አመላክቷል፡፡

አደጋው የደረሰው ከድሬዳዋ ወደ ሐረር ሰው አሳፍሮ ሲጓዝ የነበረ “ዶልፊን” የሚባለው ሕዝብ ማመላለሻ በተቃራኒ መሥመር ይጓዝ ከነበረ ከባድ የጭነት ማመላለሻ “ሲኖትራክ” ተሸከርካሪ ጋር በመጋጨቱው  ነው፡፡

የድሬ መንገድ ጠመዝማዛ ነው ደንገጎ አዳጋች ነው ከርቭ ላይ የሰው መስመር ይዘን ከማሽከርከር እንቆጠብ
ለሟቾች ነፍስ ይማር

@ethio_mereja_news
ለማንኛውም ማስታወቂያው ተነስቷል👏

"ካልጠጡ አይንዱ" በማለት ተለጥፎ የነበረው በቴሌ አርማ ላይ የተሰራው ማስታወቂያ ዛሬ ተነስቷል። ማስታወቂያው የተለጠፈው ለጀበና ቡና ቢሆንም አመላካች ነገር ስላልነበረው ዛሬ ቴሌ አስነስቶታል‼️

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ማንኛውም የመንግስት አመራር ተጨማሪ ገቢ የሚያስገኝ ንግድ እና መስል ስራዎችን መስራት የሚከለክል ረቂቅ ደንብ መዘጋጀቱን የፌደራል የስነ-ምግባር እና ፀረ ሙስና ኮሚሽን አስታውቋል።

የመንግስት አመራሮች ለሙስና ተጋላጭ ናቸው ተብለው ከተለዩ ዘርፎች ውስጥ መሆናቸው የሚናገሩት የኮሚሽኑ የሙስና መረጃ አስተዳደር መሪ ሥራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን በላይነህ በህዝብ ሃብት ላይ ውሳኔን የሚያሳልፉ አካላት የመንግስትና የህዝብን ስራ ብቻ መስራት እንደሚጠበቅባቸው ተናግረዋል፡፡

ኮሚሽኑ ለከፍተኛ ባለስልጣናት የጥቅም ግጭት መከላከል እና የሥነ-ምግባር ደንብ ረቂቅ አዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክርቤት መላኩን የሚናገሩት ሥራ አስፈፃሚው፤ አመራሮች ተጨማሪ ገቢ የሚያስገኙ ስራዎችን ሲሰሩ የጥቅም ግጭቶች እንደሚከሰቱ እና አግባብ ባልሆነ መንገድ የህዝብና የመንግስት ሃብትንም ሊመዘብሩ ስለሚችሉ ያንን ለመከላከል ያለመ ረቂቅ መሆኑን አመላክተዋል፡፡

የረቂቅ ደንቡ ሚናው ከፍተኛ በመሆኑ የሚኒስትሮች ምክርቤት ቶሎ ምልሽ ሊሰጥበት እንደሚገባ የተናገሩት ሥራ አስፈፃሚው ደንቡ ከፀደቀ ኮሚሽኑም ተጨማሪ ገቢ የሚያስገኝ ስራን እየሰሩ ባሉ ከፍተኛ አመራሮች ላይ የምርመራ ስራን እንደሚጀምር አክለው ተናግረዋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
እናት እና ልጅ የ12ኛ ክፍል ፈተና አብረው እየወሰዱ ነው👏

የተፈጥሮ ሳይንስ ትምህርታቸውን አብረው ሲከታተሉ የነበሩት እናት እና ልጅ ሀገር አቀፍ ፈተናውን በጥሩ ውጤት ለማለፍ በጋራ ሲዘጋጁ መቆየታቸውን ይናገራሉ፡፡

እናት ወ/ሮ ፍሬህይወት ኃይሉ የ8ኛ ክፍል ተማሪ እያለች ልጇን በመውለና በማኅበራዊ ጫና ትምህርቷን አቋርጣ ነበር። በሒደት ያቋረጠችውን ትምህርት በመቀጠል፣ ከልጇ ተማሪ ሰብሪና ታጅር ጋር ትምህርቷን በመከታተል የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተናን በጥሩ ውጤት ለማጠናቀቅ ሲዘጋጁ መቆየታቸውን ገልፃለች።

እናት እና ልጅ እየተደጋገፉ ልጅ ቀን እናት በማታ ትምህርታቸውን እየተማሩ በመደጋገፍ ለፈተናው ሲዘጋጁ እንደነበር ወ/ሮ ፍሬህይወት ጠቁመው፤ ባለቤታቸውም ጥሩ ውጤት እንዲያመጡ ድጋፍ ሲያደርግላቸው እንደነበረ ተናግራለች።

እናት እና ልጅ ፈተናቸውን በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ እየወሰዱ ሲሆን፤ ጥሩ ውጤት በማምጣት በቀጣይም አብረው ትምህርታቸውን ለመማር ማቀዳቸውን ለሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ማኅበረሰብ ሬዲዮ ገልፀዋል።

@ethio_mereja_news
2024/09/29 13:33:13
Back to Top
HTML Embed Code: