Telegram Web Link
አዳማ‼️

በአዳማ ከተማ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ ቢያንስ 7 ሰዎች ተገደሉ

ብጥብጡ የተነሳው በኮሪደር ልማት በተነሳ ተቃውሞ ነው

(ዋዜማ ሬዲዮ)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
TapSwap‼️

ታፕስዋፕ ትልቅ ፕሮጀክት ነው በቅርብ ቀን List መሆኑ የተረጋገጠ ነው።

ያልጀመራቹ አሁንም ጊዜ አላቹ ባጭር ጊዜ ውስጥ ከ10 M በላይ መስራት ትችላላቹ።

በዚ ሊንክ ጀምሩ👇👇
https://www.tg-me.com/tapswap_mirror_2_bot?start=r_769729488
https://www.tg-me.com/tapswap_mirror_2_bot?start=r_769729488
4 ሕጻናት በደራሽ ውኃ ተወሰዱ!

በምሥራቅ ጉራጌ ዞን ቡኢ ከተማ ከለኪንዶ ወንዝ አራት ሴት ሕጻናት በደራሽ ውኃ መወሰዳቸውን የከተማ አሥተዳደሩ ፖሊስ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ፡፡

በውኃ የተወሰዱት ሕጻናት ዕድሜያቸው ከ13 እስከ 15 እንደሚገመት የቡኢ ከተማ አሥተዳደር ፖሊስ ጽ/ቤት አዛዥ ዋና ኢንስፔክተር መለሰ ተሰማ አስታውቀዋል፡፡

ሕጻናቱ ወደ ከለኪንዶ ወንዝ ለጸበል ብለው በሄዱበት ዛሬ ጠዋት በደራሽ ውኃ መወሰዳቸውንም አረጋግጠዋል፡፡

የሁለቱ ሕጻናት አስክሬን መገኘቱን እና የቀሪዎቹን ለማግኘትም ፍለጋው ተጠናክሮ ቀጥሏል ማለታቸውን የቡኢ ከተማ አሥተዳደር ኮሙኒኬሽን ጽሕፈት ቤት መረጃ አመላክቷል፡፡

ወቅቱ ክረምት ከመሆኑ ጋር ተያይዞ ሕብረተሰቡ ልጆቹን እንዲቆጣጠር እና ጥንቃቄ እንዲያደርግም አሳስበዋል፡፡(Via FBC)

@ethio_mereja_news
አዳማ‼️

በአዳማ ከተማ ከቤት ፈረሳ ጋር በተያያዘ በተፈጠረ ግጭት ነፍሰ ጡርን ጨምሮ 7 ሰዎች መገደላቸው ተሰማ

👉🏼 ቁጥራቸው በዉል ያልታወቁ ሰዎችም ቆስለዋል ተብሏል


በኦሮሚያ ክልል በአዳማ ከተማ አሮሬቲ እና ቶርበን ኦቦ በተባሉ ቀበሌዎች ዛሬ በተቀሰቀሰ ተቃውሞ ላይ የመንግሥት ጸጥታ ኃይሎች በተኮሱት ጥይት አንዲት ነፍሰ ጡርን ጨምሮ 7 ሰዎች እንደተገደሉና ቁጥራቸው ያልታወቁ ሌሎች ሰዎች እንደቆሰሉ ዳጉ ጆርናል ከዋዜማ ዘገባ ተመልክቷል።

ተቃውሞው የተቀሰቀሰው፣ የከተማዋ አስተዳደር 1 ሺሕ 500 ገደማ መኖሪያ ቤቶችን ሕገወጥ ናቸው በማለት ማፍረስ ሲጀምር መኾኑን ነዋሪዎቹ ተናግረዋል። ነዋሪዎቹ፣ መሬቶቹን ከአካባቢው አርሶ አደሮች ገዝተው ከ2005 ዓ፤ም ጀምሮ ለከተማዋ አስተዳደር ግብር ሲከፍሉ መቆየታቸው ገልጸዋል።

ነዋሪዎቹ ቀደም ሲል ለጠቅላይ ሚንስትር ጽሕፈት ቤት ባቀረቡት አቤቱታ መሠረት፣ ጉዳዩ በይደር እንዲታይ ተወስኖላቸው እንደነበርም ዋዜማ ተረድታለች። ዋዜማ በክስተቱ ዙሪያ የከተማዋን አስተዳደር ለማነጋገር ያደረገችው ተደጋጋሚ ጥረት አልተሳካም ስትል ዘግባለች።

@ethio_mereja_news
#HoPR

ዛሬ የህዝብ ተወካዮች ም/ ቤት 36ኛ መደበኛ ስብሰባ እየተካሄደ ይገኛል።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) በምክር ቤቱ ተገኝተዋል።

በስብሰባው የ2016 በጀት ዓመት የስራ አፈጻጸም ሪፖርት እና በወቅታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ማብራሪያ እና ምላሽ ይሰጣሉ፡፡

በአሁን ሰዓት የምክር ቤት አባላት ጥያቄ እያቀረቡ ናቸው።
የተከበሩ ወ/ሮ ራህመት ለጠ/ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ያቀረቡት ጥያቄ

-የፕሪቶሪያዉ የሰላም ስምምነት አፈጻጸም በምን ደረጃ ላይ ይገኛል?

- በአፋር፣ አማራ እና ትግራይ ክልሎች ያሉ የመልሶ ማቋቋም ሂደቶች ምን ላይ ናቸዉ ለቀጣይስ ምን ታስቧል?

የተከበሩ አቶ አቤኔዘር በቀለ ለጠ/ሚኒስትር ዐቢይ ያቀረቡት ጥያቄ

የኑሮ ዉድነቱ ከፍቷል...የመንግስት ሰራተኛዉ መኖር አቅቶታል ፣ መኖር የቅድሚያ ቅድሚያ ሊሰጠዉ የሚገባ ነዉ፥ የኑሮ ዉድነቱን ማረጋጋት አልተቻለም። ስለሆነም እንደመንግስት በቀጣይ አመታት የህዝብን ጥያቄ ለመፍታት ምን ታቅዷል?

@ethio_mereja_news
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ አባል፣ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባል አቶ አበባው ደሳለው👇

"ከአገራዊ ምክክር በፊት "እምነት መገንባት" ይቀድማል፤መንግስት በህዝብ ዘንድ አመኔታ አልፈጠረም ብለን እናስባለን፤ ለዚህም ማሳያው የሰብዓዊ መብት አያያዝ ነው ሲሉ የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) እና የፓርላማ አባሉ ተናግረዋል። በጅምላ የንጹሀን ግድያን ጨምሮ ዘረፋ፣ ውድመት፣ እገታ እና ሌሎችም ወንጀሎችና የመብት ጥሰቶች በአማራ ክልል ተንሰራፍቷል ብለዋል።

በፖለቲካ አመለካከት ልዩነት ሳቢያ ፖለቲከኞች እና ጋዜጠኞች፤ እንዲሁም ዜጎች በማንነት እየተለዩ እየታሰሩ ነው በማለትም የባልደረባቸውን ክርስቲያን ታደለ ጉዳይ በማንሳት የመንግስትን ሀብት ከምዝበራ የመጠበቅ ሀላፊነትን ወስዶ ሲሰራ የቆየን ሰው ለአንድ ዓመት ገደማ በእስር እየማቀቀ ነው ብለዋል።

ከብልጽግና መንግስት ጋር አብረው እየሠሩ የሚገኙ ሰዎችም ስህተት አለ በማለታቸው ታስረዋል፤ ሀብታሙ በላይነህ የተባለው የአብን እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት አባልም ለአራት ወራት የት እንዳለ የማይታወቅ በመሆኑ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ምላሽ እንዲሰጡ እንማጸናለን ብለዋል"።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
"የኑሮ ዉድነቱ ቀንሷል" ሲሉ ጠ/ሚ ዐቢይ አሕመድ ተናገሩ‼️

የዋጋ ግሽበቱ ባለፈው ዓመት ከነበረበት 30 በመቶ ወደ 23 በመቶ ዝቅ ማለቱን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ በሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 36ኛ መደበኛ ስብሰባ ላይ ተናግረዋል።

ጠ/ሚኒስትሩ በተያዘው በጀት ዓመት የኑሮ ዉድነቱ እንደቀነሰ ተናግረዋል። መንግስት የኑሮ ውድነት ጫናን ለመቀነስ በርካታ እቅዶችን ይዞ እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በሰብል ምርትም አምና እንደሀገር 395 ሚሊዮን ኩንታል ተመርቷል ያሉት ጠ/ሚኒስትሩ ዘንድሮ 507 ሚሊዮን ኩንታል መመረቱን ገልጸዋል።ይህንን ዉጤት በርካታ የአለማቀፍ ተቋማት እያደነቁት መሆኑንም ገልጸዋል። የኑሮ ዉድነቱ በኢትዮጵያ ላይ ብቻ የተከሰተ አለመሆኑንና አለምአቀፋዊ የሆኑ ጫናዎች መኖራቸውንም ለማስረዳት ሞክረዋል።

በዚህ ዓመት ከ3 ነጥብ 8 ሚሊዮን ሰው በላይ ስራ አስይዘናል ከእንዚህም ውስጥ 3 ነጥብ 4 ሚሊዮን የሚሆኑትን በሃገር ውስጥ ስራ የተቀጠሩ ናቸው፡፡
በውጭ ሃገር 332 ሺሕ ሰው በህጋዊ መንገድ ሰልጥነው ተቀጥረዋል ብለዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለ ታሳሪዎች ምን አሉ ?

" 4 ኪሎ ተቀምጦ ' ጉዞ ወደ 4 ኪሎ'  ከሚሉ 4 ኪሎ ተቀምጠው ጉዞ ወደ ፓርላማ እያሉ በሰላም ቢታገሉ ችግር የለብኝም " - ጠቅላይ ሚኒስትሩ

ጠ/ሚ ዐቢይ አህመድ (ዶ/ር) ፦

" እስረኛ መፍታት ላይ እኛ እንታማለን ? ' እንዴት እስረኛ ትፈታለህ ? ' ተብለን ስንገመገም እና ስንወቀስ እንዳልነበረ።

ያልፈታነው ጉድ አለ እንዴ ? እስር ቤቱን በሩን ከፍተን ነው የለቀቅነው። በዚህ እንኳን አንታማም።

ከዚህ ፓርላማ የታሰሩት ወንድማችንን በተመለከተ (አቶ ክርስቲያንን ማለታቸው ነው) ሁሉም ተቃዋሚ የሚታሰር ከሆነ ጠያቂዬ (አቶ አበባውን ማለታቸው ነው) ለምን አልታሰሩም ?

ጠያቂዬ ተቀምጠው እየጠየቁ ነው እዚህ።

እርሶን የሚያስቀምጥ እሳቸውን የሚያሳስር ነገር ካለ ልዩነት አለ ማለት ነው። ልዩነቱን ግን እኔ ዳኛ አይደለሁም። ወንጀለኛ ናቸው ፣ ጥፋተኛ ናቸው ልል አልችልም። የፍትሕ ስርዓቱ አይቶ መርምሮ ፈትሾ ፍርድ ይስጥ።

የግል ምኞትህ ያሉኝ እንደሆነ እርሶም እርሳቸውም ከእርሶ ጎን ተቀምጠው ባያቸው ደስታውንም አልችለውም።

በሰላማዊ መንገድ 4 ኪሎ ተቀምጦ ' ጉዞ ወደ 4 ኪሎ'  ከሚሉ 4 ኪሎ ተቀምጠው ጉዞ ወደ ፓርላማ እያሉ በሰላም ቢታገሉ ችግር የለብኝም።

የግል ጥላቻ የለኝም። የግል መግፋትም የለብኝም።

ህግ ከፈታቸውና ከኛ መካከል ቢሆኑ ደስታውን አልችለውም። ነገር ግን ሁላችንም ማወቅ ያለብን ፦
- የፓርላማ አባል መሆን
- ጋዜጠኛ መሆን
- ሚኒስትር መሆን
- ማዕከላዊ ኮሚቴ መሆን ከወንጀል እና ከጥፋት አይታደገንም። አለማጥፋት ነው።

የኔ ዋስትና አለማጥፋት ነው። ካጠፋው እመጣለሁ ያለመከሰስ መብቴ ይነሳል እጠየቃለሁ።

እዚህ አካባቢ ላይ መቀመጥ ለማንኛውም ጥፋት ዋስትና አድርገው ፤ ዝም ብሎ መንገደኛ ይነሳና ዩትዩብ ከፍቶ ጋዜጠኛ ነኝ የሚለው እንደዛ ትክክል አይደለም።

ጋዜጠኛም ህግ አለው ፣ ወታደርም ቢሆን ህግ አለው መጠየቅ አለበት ፣ ሚኒስትርም ህግ አለው።

በዚህ አግባብ ማየት ካልቻልን ስራችንን ቆርጠን ጥለነው በኋላ የማንጠግነው ነገር ይፈጠራል። "#TikvahEthiopia

@sheger_press
" የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት እና ወታደር ዜጎችን በጅምላ አይገድልም " - ጠቅላይ ሚኒስትሩ

ሀገር መከላከያ ሰራዊት በሺዎች የሚቆጠሩ አባላቱን በወታደራዊ ፍርድ ቤት ስርዓት እስር ቤት እንደሚገቡ ማድረጉን ጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።

ዶ/ር ዐቢይ ፤ መከላከያ ከ ' Code of conduct ' ውጭ በማይገባ መንገድ ኦፕሬሽን ሰርታችኋል በሚል በሺዎች የሚቆጠሩ አባላቱን እስር ቤት እንዳስገባ አሳውቀዋል።

የጅምላ ግድያን በተመለከተ ግን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ " የኢትዮጵያ ፌዴራል መንግሥት እና ወታደር ዜጎችን በጅምላ አይገድልም " ሲሉ ተናግረዋል።

" በጅምላ ለማሸነፍ ይነሳና ሲሞት ነው በጅምላ ሞትኩኝ የሚለው እንጂ መንግሥት አይገድልም " ሲሉ ገልጸዋል።

@sheger_press
#FactCheck

"6ቱ ጎረቤቶቻችን ተደምረው ሊኖራቸው የማይችለውን GDP አስመዝግበናል"--- ጠ/ሚር አብይ አህመድ በፓርላማ ከተናገሩት

መንግስት ደጋግሞ የሚጠቀምበትን የ IMF ዳታ ስንመለከት የዘንድሮ የኢትዮጵያ አመታዊ ጥቅል ምርት (Gross Domestic Product- GDP) 205 ቢልዮን ዶላር እንደሚሆን መረጃ አስቀምጧል።

የሌሎቹን ስንመለከት የኬንያ GDP 104 ቢልዮን ዶላር፣ የጅቡቲ 4 ቢልዮን ዶላር፣ የሶማልያ 12 ቢልዮን ዶላር፣ የሱዳን 26 ቢልዮን ዶላር፣ የደቡብ ሱዳን 6 ቢልዮን ዶላር ሲሆን ይህ በድምሩ 152 ቢልዮን ዶላር ይሆናል። ስለ ኤርትራ GDP መረጃ እንደሌለው IMF ያስቀምጣል፣ በርካታ ግምቶች ግን 2 ቢሊዮን ዶላር እንደሆነ ይጠቁማሉ።

ስለዚህ የስድስቱ ጎረቤት ሀገራቶች GDP ድምር 154 ቢልዮን ዶላር ገደማ ሲሆን ይህም ከኢትዮጵያ 205 ቢልዮን ዶላር GDP ያነሰ መሆኑን መመልከት ይቻላል፣ ስለዚህ በፓርላማ የቀረበው መረጃ ትክክለኛ ነው።

ይህንን እንዲሁም የዜጎችን ኑሮን/የመግዛት አቅም በተሻለ ያሳያል የሚባለውን የነፍስ ወከፍ አመታዊ ገቢን (per capita income) ዝርዝር ለመመልከት ሊንኩን ይከተሉ: https://www.imf.org/external/datamapper/NGDPD@WEO/DZA/ZAF/MAR/NGA/EGY/AFQ

ይህ መረጃ እንዲጣራ ታግ በማድረግ እና በኢንቦክስ ለጠየቃችሁ እነሆ...
Elias Meseret

@ethio_mereja_news
የትግራይ ኃይሎች በቅርብ ወራት መልሰው ከተቆጣጠሯቸው ራያ አላማጣ፣ ራያ ባላ፣ ኦፍላ፣ ኮረም፣ ዛታ፣ ዋጃ እና ጥሙጋ እስከ ሰኔ 30 እንዲወጡ ፌደራል መንግሥት ማዘዙን ዋዜማ ከምንጮቿ ሰምታለች፡፡

በግጭት ማቆም ስምምነቱ መሠረት ተፈናቃዮች ወደቀያቸው እንዲመለሱ፣ መከላከያ ሠራዊትና ፌደራል ፖሊስ የትግራይ ታጣቂዎች በቀነ ገደቡ እንዲወጡ እንዲያደርጉ ትዕዛዝ እንደተሰጣቸው ምንጮች ተናግረዋል፡፡

በትዕዛዙ መሠረት፣ ከሰኔ 25 ጀምሮ የትግራይ ኃይሎች ከዋጃ እና ጥሙጋ አንዳንድ አካባቢዎች መውጣት መጀመራቸውንና በአላማጣ ከተማ ግን እስከ ሰኔ 26 ሲንቀሳቀሱ መታየታቸውን ዋዜማ ከነዋሪዎች ሰምታለች፡፡

በከተማዋ ሰላማዊ ሰልፎች የታገዱ ሲኾን፣ የባጃጅ እንቅስቃሴም ከቀኑ 12 ስዓት በኋላ እንዲኹም ከምሽቱ ኹለት ሰዓት ጀምሮ የሰዎች እንቅስቃሴና የምግብ ቤቶችና መዝናኛ ቤቶች አገልግሎት አንዳይኖር ገደብ እንደተጣለ ታውቋል፡፡ (wazema

@sheger_press
በቦታ ርቀት ምክንያት ቤተሰቦቻቸው በደስታ ቀናቸው መገኘት ያልቻሉ ተመራቂ ተማሪዎች።

የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የመጨረሻ ሳምንት ጨዋታዎች መካሄዳቸውን ቀጥለዋል። በዛሬ እለት በተካሄደው የቅዱስ ጊዮርጊስና የፋሲል ከነማ ጨዋታ ይህ ሆነ፣

ቤተሰቦቻቸው በርቀት ምክንያት የልጆቻቸው ምርቃት ላይ መገኘት አልቻሉም፣ ተመራቂዎቹ ደግሞ ከምርቃት በኋላ ከነ ጋወናቸው ስታዲየም ቁጭ ብለው ኳስ እያዩ ነው፣ ተቀይሮ ለመግባት እያሟሟቀ የነበረው አማኑኤል ኤርቦ ተመራቂዎቹን ያያቸዋል የሆነ ነገርም ማድረግ እንዳለበት ያሰበ ይመስላል፣ ተቀይሮ እንደገባ ጎል አስቆጠረ ደስታውን ግን በምርቃታቸው ቀን ወላጆቻቸው ሊገኙ ያልቻሉ ተመራቂዎች ጋር በመሄድ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ደስታውን አብሯቸው ገልጿል። የጎሉንም ማስታወሻ ለተመራቂዎቹ አደረገ።

እኔም ጠጋ ብዬ ስጠይቃቸው ቤተሰቦቻቸው በርቀት ምክንያት ምርቃታቸው ላይ መገኘት ስላልቻሉ ከምርቃት ፕሮግራም በኋላ ጨዋታ በማየት ጊዜያቸውን ለማሳለፍ እንደወሰኑ ነገሩኝ።
ተፃፈ በAku Images
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባ ለቀጣዩ በጀት ዓመት 971 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር በጀት አጽድቋል።

መንግሥት ከበጀቱ 451 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር ያህሉን የመደበው ለመደበኛ ወጪዎች እንዲኹም 283 ነጥብ 2 ቢሊዮኑን ለካፒታል ወጪዎች ሲኾን፣ 236 ነጥብ 7 ቢሊዮኑ ደሞ ለክልሎች ድጎማ የተመደበ ነው። ከበጀቱ 139 ነጥብ 3 ቢሊዮን ብር የአገሪቱን ዕዳ ለመክፈል ተመድቧል።

በጀቱ ከዘንድሮው ዓመት በጀት በ21 ነጥብ 1 በመቶ ብልጫ አለው።

የ2017 ዓ፣ም በጀት የአስር ዓመቱ መሪ የልማት ዕቅድ አካል በኾነው ከ2016 እስከ 2018 በሚቆየው የልማትና ኢንቨስትመንት እቅድ ላይ የተቀመጡ ግቦችን እና ከ2017 እስከ 2021 ዓ፣ም የሚቆየውን የመካከለኛ ዘመን የማክሮ ኢኮኖሚና የፊስካል ማዕቀፍ ለማስፈጸም የተዘጋጀ ነው።

@sheger_press
Samsung  Galaxy  note  3
አዲስ  አንደታሸገ 
32  gb
3 gb ram
ዋጋ 4000  ብር በማከፋፈያ ዋጋ
Call me 👇👇👇👇
☎️ 0909255008
☎️ 0912739699
ተጨማሪ ስልኮችን  ለመመልከት
አና ስልክ ለመሽጥ ከፈለጉ 👇 ቤተሰብ ይውኑ
👉https://www.tg-me.com/used_phone_ethiopian
2024/09/29 13:30:43
Back to Top
HTML Embed Code: