Telegram Web Link
በኢትዮጵያ የውስጥ ኦዲት ከሚሰሩ የመንግስት ተቋማት መካከል በአግባቡ ስራቸውን የሚከውኑት ጥቂቶቹ ብቻ ናቸው ተባለ፡፡

ከመንግስት ተቋማት ይልቅ የግል ድርጅቶች ለሰራተኞቻቸው የሚከፍሉት ክፍያ ከፍ ማለቱ ደግሞ ባለሞያዎች ወደ ግል ድርጅቶቹ ማዘንበል ሌላኛው የውስጥ ኦዲት በሚፈለገው ልክ ውጤታማ ስራ እንዳይከወን ምክንያት ከሆኑት መካከል አንዱ ነው ተብሏል፡፡

በዚህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ፣ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና ብሄራዊ ባንክ በውስጥ ኦዲት ሙያ ከበረቱት ተቋማት መካከል መሆናቸውን ሰምተናል፡፡

በኢትዮጵያ የውስጥ ኦዲት ዘርፍ ላይ ብዙ መስራት ይጠበቃል የተባለ ሲሆን ጥቂት ከሚባሉ ተቋማት ውጭ የውስጥ ኦዲት እንደሀገር እየተሰራበት አይደለም ተብሏል፡፡

በተለያየ ጊዜ ተቋማቱ ላይ የሚመጣ ትችት፣ የመልካም አስተዳደር እክል እና ሌሎችም በድርጅቱ ላይ የሚደርሱ ችግሮች በውስጥ ኦዲት ሙያ ላይ ያለቸው አስተዋፆ አናሳ በመሆኑ ነው መባሉን ሰምተናል፡፡

የውስጥ ኦዲት በአግባቡ እንዲሰራ ተቋማት የሚያግዘው የኢትዮጵያ የውስጥ ኦዲት ኢንስቲቲዩት ከአለም አቀፉ የውስጥ ኦዲተሮች ማህበር ጋር በጋራ በመሆን ስራዎችን እንደሚከውን ይናግራል፡፡

ይሄው ኢንስቲቲዩት ተቋማቱ ለሰሩት የውስጥ ኦዲት ማረጋጫ ይሰጣል የተባለ ሲሆን በሚከውነው ስራም ችግሮች እንደሚያጋጥሙት የኢንስቲቲዩቱ ፕሬዚደንት ገነት ሐጎስ ተናግረዋል፡፡

(ሸገር ኤፍ ኤም)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በአማራ ክልል በኮሌራ ወረርሽኝ የአምስት ሰዎች ህይወታቸው ማለፉን፣ ከ500 በላይ ሰዎች መያዛቸውን ተቋሙ አስታወቀ!

በአማራ ክልል ከመጋቢት 27 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ በተከሰተው ሁለተኛ ዙር ኮሌራ ወረርሽኝ ከ500 በላይ ሰዎች መያዛቸውን ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታወቀ።

በዚህም ወረርሽኙ ከተከሰተበት ከመጋቢት 27 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ሰኔ 13 2016 ዓ.ም ባሉት ጊዜያት ከ530 በላይ ሰዎች በኮሌራ መያዛቸው እና አምስት ሰዎች በበሽታው ሕይወታቸውን ማጣታቸውን የተቋሙ ባለሙያ ሲስተር ሰፊ ደርብ እንደገለጹለት ኢፕድ ዘግቧል።

በወረርሽኙ ከተጠቁ ሰዎች መካከል ከ11 በላይ የሚሆኑት በሕክምና ላይ እንደሚገኙ የጠቆመው ዘገባው ቀሪዎቹ በተሰጣቸው የሕክምና አገልግሎት ታክመው መዳናቸውን አመላክቷል።

ወረርሽኙ በደቡብ ወሎ 2 ወረዳዎች፣ በኦሮሞ ብሔረሰብ ዞን 3 ወረዳዎች፣ በሰሜን ጎጃም 2 ወረዳዎች፣ በደሴ ከተማ፣ በኮምቦልቻ ከተማና በባህር ዳር ከተማ እንዲሁም በቅርቡ ጎንደር ከተማ ላይ የተከሰተ መሆኑንም ተገልጿል፡፡

በክልሉ በአጠቃላይ በሽታው በተከሰተባቸው አካባቢዎች የሚገኙ በስድስት የሕክምና ማእከላት ሕክምናው እየተሰጠ መሆኑ ተጠቁሟል፡፡

በክልሉ ከሐምሌ 8/2015 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 7/2016 ዓ.ም ተከስቶ በነበረው የመጀመሪያ ዙር ወረርሽኝ ከ4980 በላይ ሰዎች ተይዘው እንደነበር ያወሳው ዘገባው ይህም ለሁለተኛ ዙር የሚያስፈልጉ የኮሌራ ኪትና ሌሎች ግብአቶችን በቀላሉ ለማግኘት እንዳስቻለ ባለሞያዋ ሲስተር ሰፊ መግለጻቸውን አስታውቋል።

በተጨማሪም የሚያስፈልጉ የሕክምና እና ምርመራ ግብአቶችን ከኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት፣ ከጤና ቢሮና አጋር ድርጅቶች ጋር በጋራ እየቀረበ ነው ሲሉ መናገራቸውንም አካቷል።

@sheger_press
@sheger_press
ፖለቲከኛው ጃዋር መሃመድ የመከላከያ ጄነራሎች ለድርድር ለመቀመጥ ለፋኖ ያደረጉትን ጥሪ፣ የፋኖ አመራርና የአማራ አክቲቪስቶች እንደበጎ እርምጃ እንዲመለከቱትና ለጥሪው ምላሽ ቢሰጡ ለሰላም አማራጭ ይሆናል ሲል በግል የማህበራዊ ሚዲያ የፌስቡክ ገፁ አስፍሯል።

መከላከያ ሰራዊት በሀገሪቱ የተፈጠሩ ግጭቶች በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት በርካታ ጥረቶችን እያደረገ ያለ አንዱ የመንግሥት ተቋም ነው ብሏል።

መከላከያው እየተፈጠረ ያለውን ችግር በቅርበት የሚያውቅ በመሆኑ፣ ከፖለቲከኞች ቀድሞ ጥሪ ማቅረቡ መበረታታት አለበት ብሏል። ከኦነግ ሸኔ ጋርም ሰላም ለመፍጠር ለሁለት ጊዜ የተደራደረው መከላከያው ነው ብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አስጨናቂው የክረምት ወቅት መጥቷል ‼️

ፖስቱ ቫይራል መሆኑ ለእናቶች ይጠቅማቸዋል። ላይክ አርግ። ኮፒ አርጋችሁም በየፔጃችሁ ፖስቱት 🙏

ክረምቱ በዝናብ ታጅቦ መጥቷል ይህም ደግሞ ያለ መከለያ ጎዳና ላይ ጉሊት ለሚሸጡ እናቶች መከራ ሆኗል። የሚሸጧቸውን አትክልትና ፍራፍሬ ከማከፋፈያ ቦታ ከማምጣት ጀምሮ ቸርችሮ እስከመሸጥ ድረስ ያለውን ሂደት ክረምቱ ይበጠብጠዋል። አብዛኞቹ እናቶች በጋ ላይ ያገኙት የነበረውን ገቢ ግማሹንም አሁን ላይ አያገኙትም።

በእንቅርት ላይ ... እንዲሉ ገቢያቸው ሲቀንስ ወጪያቸውን ደግሞ ክረምቱ ያንረዋል። አብዛኞቹ እናቶች ልጆቻቸውን መንግስት ትምህርት ቤት ያስተምራሉ። በጋውን ልጆቻቸውን መንግስት በትምህርት ቤት ምገባ ፕሮግራም ይመግብላቸው ነበረ። ክረምቱ ግን የልጆቻቸውን ፊት ከባዶ ሌማታቸው ጋር ያፋጥጠዋል።

አስቤዛ ስትገዙ እስቲ ጉሊት ግዙ። ዋጋ አትከራከሩ ። ቲፕም ስጡ 🙏

አቅሙ ያላችሁ ሰዎች ደግሞ ጉሊት ጋ መኪና አቁሙና አንዱን መደብ በሺዎች ግዙ። አስደስቷቸው። ተመረቁ🙏

#ጉሊት #ጉሊት_challenge

Tesfa Neda

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች ለተማሪ ቀለብ የሚያዝላቸው በጀት ካለው የምግብ ዋጋ ጋር የሚጣጣም ባለመሆኑ ተጨማሪ በጀት እንዲጠይቁ የሚፈቅድ አሰራር እንዲዘረጋ ተጠየቀ፡፡

ይህ ካልሆነ በመጭው የት/ት ዘመን ተማሪ ተቀብለው ለማስተናገድ እንደሚቸገሩ ሰምተናል፡፡

ለ2017 በተያዘው ረቂቅ በጀት ላይ የህዝብ እንደራሴዎች ምክር ቤት አባላት ውይይት አድርገውበታል፡፡

ሸገር ኤፍ ኤም

@sheger_press
@sheger_press
ጥቆማ‼️

እንዳያመልጣቹ ስልካቹን ብቻ በመጠቀም ምንም ገንዘብ ማውጣት ሳይጠበቅባቹ ::

እንዴት ገንዘብ መስራት እንደምትችሉና ስለ ክሪፕቶ ስለ ኤርድሮፕና ታፕ ታፕ በማረግ ብቻ እንዴት ገንዘብ ማግኘት እንደምትችሉ።

ሁሉንም የONLINE ስራዎች በዝርዝር በዚ ቻናል ያገኛሉ።

በርግጠኝነት ትወዱታላቹ በዚ LINK አሁንኑ ተቀላቀሉ👇👇
http://www.tg-me.com/sheger_crypto
http://www.tg-me.com/sheger_crypto
በአዲስ አበባ የሚስተዋለው የነዳጅ እጥረት በቀናት ውስጥ ይፈታል ተባለ

ካለፉት ሳምንታት ጀምሮ በመዲናዋ ነዳጅ ለመቅዳት የሚጠብቁ ረጃጅም የተሽከርካሪ ሠልፎች መታየታቸውን አሁንም ቀጥለዋል።

የኢትዮጵያ የነዳጅ አቅራቢዎች ድርጅት እጥረት ማጋጠሙን ጠቅሶ፥ በበዓል ምክንያት ለሁለት ቀናት ከጂቡቲ ነዳጅ ባለመጫኑ ምክንያት ችግሩ እንደተፈጠረ መግለጹን ኢቢሲ ዘግቧል።

በዒድ አል አድሃ አረፋ በዓል ምክንያት እሑድ ሰኔ 9 እና በማግሥቱ ሰኔ 10 ቀን 2016 ዓ.ም. ነዳጅ ከጂቡቲ ሳይጫን መቅረቱን ጠቅሷል።

የነዳጅ ማጓጓዝ ሒደቱ አምሥትና ሥድስት ቀናት የሚወስድ መሆኑንና አሁን የሚስተዋለው እጥረት በመጪዎቹ ቀናት እንደሚፈታም ነው የገለጸው። (EBC)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ስብሰባ በዛሬ 37ኛ መደበኛ ስብሰባው ውሳኔዎችን አሳልፏል።ከውሳኔዎቹ መካከል በኢትዮጵያና በኩዌት መካከል በስራ ስምሪት ዘርፍ የተፈረመውን ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ አዋጅ አንዱ ነው፡፡

ስምምነቱ በኩዌት በቤት ሰራተኝነት ተሰማርተው የሚገኙ እና በቀጣይም ከአሰሪዎች ጋር የሥራ ውል ውስጥየሚገቡ ኢትዮጵያውያን ሠራተኞች መብታቸውን ለማስጠበቅ የሚያስችል ሕጋዊ ማዕቀፍ እንዲኖር፣ በአገሪቱ የሚገኙ ዜጎቻችን ክብር፣ መብትና ጥቅም ለማስጠበቅ ትልቅ ጠቀሜታ ያለው እንዲሁም በሁለቱ መንግስታት መካከል የሁለትዮሽ ግንኙነትን ይበልጥ እንዲጠናከር የሚያግዝ ነው፡፡ ምክር ቤቱ በረቂቅ አዋጁ ላይ ከተወያየ በኋላ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤትእንዲተላለፍ በሙሉ ድምጽ ወስኗል፡፡

@ethio_mereja_news
Hamster‼️

ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ሀገራት ላይ እየተዘዋወረ ያለው “ሃምስተር ኮምባት” ምንድነው ?

“ሃምስተር ኮምባት” (Hamster Kombat) ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በበርካቶች ዘንድ እየተዘወተረ የመጣ በቴሌግም ላይ የተመሰረተ ጨዋታ ሲሆን፤ ተጫዋቾቹ በየቀኑ ስክሪናቸውን በጣታቸው መታ መታ (ታፕ ታፕ) ሲያደርጉ ክሪፕቶ ሳንቲሞችን የሚያገኙበት ነው።
“ሃምስተር ኮምባት” (Hamster Kombat) ኢትዮጵያን ጨምሮ በተለያዩ የዓለም ሀገራት ላይ በበርካቶች እየተዘወተረ የመጣ ጨዋታም ሆኗል።

በቴሌግራም ላይ የተመሰረተው ሃምስተር ኮምባት በአለም አቀፍ ደረጃ 200 ሚሊዮን ተጫዋቾችን በማፍራት ከፍተኛ ተወዳጅነትን አግኝቷል።

ሃመስትር ኮምባት በቴልግራም ላይ የተመሰረተ ጨዋታ ሲሆን፤ ኤር ድሮፕ ሊሆኑ የሚችሉ ሳንቲሞችን (ኮይን) ተጫዋቾችን የሚሸልም የቴሌግራም ጨዋታ ነው። እንዲሁም ሰዎች በቴሌግራም ለይ ጓኞቻውን እየጋበዙ በርከት ያለ የክሪፕቶ ሳንቲሞችን ለመሰብሰብ በጋራ የሚጫወቱት ጨዋታ እንደሆነም ይነገራል።

ሃመስትር ኮምባት በቴልግራም ላይ የተመሰረተ ጨዋታ ሲሆን፤ ኤር ድሮፕ ሊሆኑ የሚችሉ ሳንቲሞችን (ኮይን) ተጫዋቾችን የሚሸልም የቴሌግራም ጨዋታ ነው። እንዲሁም ሰዎች በቴሌግራም ለይ ጓኞቻውን እየጋበዙ በርከት ያለ የክሪፕቶ ሳንቲሞችን ለመሰብሰብ በጋራ የሚጫወቱት ጨዋታ እንደሆነም ይነገራል።

ምናልባት ጨዋታ ብቻ ስለሆነ ዋናው ጥቅሙ ምንድነው? የሚል ጥያቄ ሊያስከትል ይችላል፤ ምንም እንኳን በአሁኑ ጊዜ ጨዋታ ቢሆንም፣ በሃመስተር ኮምባት የሰበሰብናቸው ሳንቲች (ኮይኖች) ኤርድሮፕ የመሆን ዝግጅት እንዳለ ነው የሚነገረው።

ይህ ማለትም በዚህ ጨዋታ ሳንቲሞችን (ኮይን) የሰበሰቡ ተጫዋቾች በቲ.ጂ.ኢ (ቶከን ጄኔሬሽን ኢቨንት) ወቅት ለኤር ድሮፕ ብቁ የመሆን እንደል አላቸው። ሳንቲሞቹ አስተዳዳሪዎች ያዋጣል ብለው ያመኑትን ማንኛውንም ተመን በመጠቀም ወደ ቶከን ይቀየራሉ፤ ስለዚህ “ሃምስተር ኮምባት” (Hamster Kombat) መጫወት ከጉዳቱ ጥቅሙ ያመዝናል ነው የተባለው።

ሃምስተር ኮምባት ህጋዊ ወይስ ማጭበርበሪያ ዘዴ ነው?

“ሃምስተር ኮምባት” (Hamster Kombat) በክሪፕቶ ገንዘብ ተፈጥሮ ምክንያት ህጋዊ ወይም ማጭበርበሪያ ዘዴ ነው ብሎ ለመደምደም የሚያስችል ምንም መንገድ የለም። ነገር ግን ሃምስተር ኮምባት ጠቃሚ ነገር ሊሆን እንደሚችል የሚጠቁሙ ምልክቶች አሉ የተባለ ሲሆን፤ ከእነዚህም አንዱ ማሳያዎ እንደ “BingX” ካሉ ልውውጦች ጋር ስትራቴጂካዊ አጋርነት መፍጠሩ ነው።

ይህ ማለት ወደፊት በ”BingX” ልውውጥ ላይ የሃምተርን ተመዝግቦ ልናይ እንችላል፤ ነገርግን አሁን ማድረግ ያለብን ማመን እና ጨዋታውን መጫወት ብቻ ነው። ተለዋዋጭ በሆነው እና ተገማች ባልሆነው በክሪፕቶ ዓለም ውስጥ ማድረግ የምንችለው እንድ ነገር ወይ አምኖ መጫወት አሊያም መተው ብቻ ነው።

መረጃው የ አል አይን ኒውስ ነው

መጀመር የምፈልጉ ደሞ በዚ Link መጀመር ትችላላቹ👇👇
https://www.tg-me.com/hamsTer_kombat_bot/start?startapp=kentId5355126428
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአንዳንድ አገልግሎቶቹ ላይ ከሀምሌ 19 ቀን 2016 ጀምሮ ተግባራዊ የሚደረግ የአገልግሎት ክፍያ ማሻሻያ ማድረጌን እወቁልኝ ብሏል።

ዝርዝሩ ከላይ ተቀምጧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ፍትሕ ሚንስቴር ሕወሃት በልዩ ኹኔታ እንዲመዘገብ ለምርጫ ቦርድ ጥያቄ ማቅረቡን ከምርጫ ቦርድ መስማቱን ጠቅሶ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል።

ምርጫ ቦርድ፣ ሕወሓት በሰሜኑ ጦርነት ወቅት በአመጻ ተግባር ላይ ተሳትፏል በማለት ሕጋዊ ሰውነትቱን የሰረዘው በጥር 2013 ዓ፣ም ነበር።

ፍትሕ ሚንስቴር ሕወሓት “በልዩ ኹኔታ እንደ ፖለቲካ ፓርቲ ለመመዝገብ እንዲችል ቦርዱ አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርግ ከኹለት ቀናት በፊት በደብዳቤ መጠየቁን ዘገባው አመልክቷል።

ቦርድ የሚንስቴሩን ጥያቄ በሥራ ላይ ካሉ ሕጎች አንጻር መርምሮ ውሳኔ እንደሚሰጥ ተናግሯል ተብሏል።

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት በቅርቡ ያሻሻለው የምርጫና ፖለቲካ ፓርቲዎችን አዋጅ፣ በአመጽ ተግባር በመሠማራታቸው ሕጋዊ ሰውነታቸው የተሰረዘባቸው የፖለቲካ ፓርቲዎች ወደ ሰላማዊ እንቅስቃሴ ለመመለሳቸው ማረጋገጫ ከሰጡ በድጋሚ እንዲመዘገቡ የሚፈቅድ አዋጅ ማጽደቁ ይታወሳል።

@sheger_press
@sheger_press
#አስተያየት የፍትህ ሚኒስትሩ ትናንት በንብረት ማስመለስ ህጉ ዙሪያ የሰጡት ማብራሪያ ከመልስ ይልቅ ብዙ ጥያቄዎችን የሚያጭር ሆኖ አግኝቼዋለሁ

(በቢንያም እሸቱ የተፃፈ)/

ከሁሉ በላይ ግርም ያለኝ የወንጀል ህግን መሰረታዊ መርሆ በተለይም ህግ ወደ ሗላ ተመልሶ እንደማይሰራ የሚደነግገውን (The principle of legality, specifically its non-retrospective 'or non-retroactive' aspect, that laws should not apply to actions that occurred before the law was enacted) የሚጣረዝ ህግን ተቀባይነት ያለው አሰራር ለማስመሰል የተጠቀሙት አገላለጽ ነው።

እንደ ፍትህ ሚኒስትሩ ማብራሪያ የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅ ከያዛቸው 57 አንቀጾች ውስጥ 52 የሚሆኑት ከጸደቀበት ቀን ወደፊት ብቻ የሚፈጸሙ ሲሆን4 ወይም 5 የሚሆኑት አንቀጾች ብቻ ወደኋላ ሄደው ተፈፃሚ ይሆናሉ።

በሶስት አህጉራት (በኢትዮጵያ፣ በእንግሊዝና በአሜሪካ) በተማርኳቸው [የህግ] ትምህርቶች የአንቀፆች ይዘት እንጂ ብዛት ቁመነገር እንደሌለው ተገንዝቤያለሁ ።
Elias Meseret

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Forwarded from Sheger Press️️
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አያት አክሲዮን ማሕበር

የአክሲዮን እና ቤት ሽያጭ

አያት ዞን ሁለት ; ሦስት እና ሲኤምሲ አፓርተማዎችን ለሽያጭ አቅርበናል። እንዲሁም "8" እህት ኩባንያዎችን ያካተተዉ እና 51.38% አመታዊ ትርፍ ያከፋፈለዉ አያት "አክሲዮን"በመሸጥ ላይ ነዉ።

አያት የተሰማራባቸው የስራ ዘርፎች

በሪል ስቴት ግንባታና ልማት

በሆቴል እና ቱሪዝም(ራስ& ሮሃ ሆቴል)

በማርብል ማምረቻ ኢንዱስትሪ፣

በጠጠር ማምረቻ ኢንዱስትሪ

በብሎኬት ማምረቻ ኢንዱስትሪ

በእንጨትና ብረታብረት ምርቶች

በትምህርት ኢንቨስትመንት

በፋይናንሻል ኢንቨስትመንት

የትርፍ አከፋፈል ሂደቱ ከ2011 ጀምሮ

በ2011 - 26%

በ2012 - 27%

በ2013 - 31%

በ2014 - 44%

በ2015 - 51.38%

በ2015 የ1,000,000 አክሲዮን የነበራቸዉ 513,000 ብር አትርፈዋል።

የ500,000 የነበራቸዉ ደግሞ....250,000 ብር አትርፈዋል።

ለበለጠ መረጃ... 09-12-62-24-04
ምርጫ ቦርድ፣ ለፖለቲካ ፓርቲዎች ለሚሰጠው የገንዘብ ድጎማ ድልድል ከ10 ሺህ እስከ 900 ሺህ ሴት እና አካል ጉዳተኛ አባል አለን ያሉ 11 ፓርቲዎች እስከ ትናንት ድረስ ማስረጃ ሊያቀርቡለት እንዳልቻሉ አስታውቋል።

ቦርዱ ለፖለቲካ ፓርቲዎች የገንዘብ ድጎማ ድልድል ለማድረግ በመስፈርትነት የሚጠቀመው፣ ፓርቲዎች ያላቸውን የሴት እና አካል ጉዳተኛ አባላት ብዛት ነው።

በተያዘው ዓመት ከ10 ሺህ እስከ 900 ሺህ ሴት እና አካል ጉዳተኛ አባላት አሉን ብለው ለቦርዱ ሪፖርት ካደረጉት ፓርቲዎች መካከል፣ ብልጽግና ፓርቲ፣ አብን፣ ኦብነግ እና ዓረና ትግራይ ይገኙበታል።

ቦርዱ፣ ፓርቲዎቹ በቀጣዮቹ ሰባት ቀናት ማስረጃ ካላቀረቡ ሕጋዊ ርምጃ እወስዳለኹ በማለት አስጠንቅቋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም የክብር ዶክትሬት ተሰጣቸው

የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴዎድሮስ አድሃኖም በቆጵሮስ ኒኮሲያ ከሚገኘው የህክምና ዩኒቨርሲቲ የክብር ዶክትሬት ተሰጣቸው። ዋና ዳይሬክተሩ ለሽልማቱ አድናቆታቸውን ገልጸው "የጤና ባለሙያዎች በቅንነት የሚያገለግሉ ከሆነ በአለም ላይ ትልቅ ለውጥ ከማምጣት የሚያግዳቸው ነገር የለም" ብለዋል።

@ethio_mereja_news
ለልማታዊ መዋጮ በሚል መምህራን ሳይመክሩበት ከደመወዛቸው እየተቆረጠባቸው ነው ተባለ‼️

የኢትዮጵያ መምህራን ማህበር መምህራን ሳይመክሩበት እና ሳይጠየቁ ለልማታዊ መዋጮ እየተባለ ከደመወዛቸው እየተቆረጠባቸው ነው ሲል ቅሬታውን ገልጿል።

ይህ እየተፈጸመ ያለው በተለያዩ ክልሎች ያሉ መምህራን ላይ እንደሆነ የማህበሩ ምክትል ፕሬዚዳንት ሽመልስ አበበ ለአራዳ ተናግረዋል።

ለመንገድ ግንባታ አዋጡ ፣ ለልማት እየተባለ ከመምህራን ደመወዝ የሚቆረጠው መዋጮ እንደማንኛውም የህብረተሰብ ክፍል ተጠይቀው እና አምነውበት ሊሆን እንደሚገባም ነው የተናገሩት።

በክልሎች የሚገኙ መምህራን ከጊዜ ወደ ጊዜ ችግራቸው እየተበራከተ መጥቷል ያሉት አቶ ሽመልስ ማግኘት ያለባቸውን የአቅም ማሳደጊያ፣ የደረጃ እድገት እና መሰል ጥቅማ ጥቅሞቻቸውንም እየተከለከሉ መሆኑን ገልጸዋል።

በተጨማሪም አሁን ባለው የደመወዝ መጠን የኑሮ ውድነትን መቋቋም ያቃታቸው መምህራን ይባስ ብሎ የሶስት እና የአራት ወር ደመወዛቸው ያልተከፈላቸው የደቡብ፣ የአፋር እና የአማራ ክልል መምህራን እንዳሉም አስረድተዋል።

ችግሩን ለመቅረፍ ክልሎችን ብናናግርም ተገቢውን ምላሽ እየሰጡን አይደለም ብለዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አነጋጋሪው የትራምፕ እና የባይደን ክርክር

የአሁኑ እና የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ባይደን እና ዶናልድ የትራምፕ ትናንት ምሽት በመጭው ህዳር ለሚደረገው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ክርክር አድርገዋል።

የዲሞክራቲክ ፓርቲው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን እና የሪፐብሊካን ፓርቲው ፕሬዚዳንታዊ እጩ ዶናልድ ትራምፕ ትናንት ሐሙስ ምሽት በአትላንታ ባደረጉት የ2024 ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ክርክር ስደት እና ኢኮኖሚን ጨምሮ ሌሎች በርካታ ጉዳዮች ተነስተዋል።

አሜሪካውያን በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት በተመለከቱት በዚህ የመጀመሪያ ክርክር ፤የ78 ዓመቱ ዶናልድ ትራምፕ የ81 የዕድሜ ካላቸው ጆ ባይደን የዕድሜ ልዩነታቸው ብዙ ባይሆንም፤ የበለጠ ንቁ ሆነው ታይተዋል።

በክርክሩ ፕሬዝዳንት ባይደን ሃሳባቸውን ለመግለጽ ተቸግረው እና የጀመሩትን አርፈተ ነገር እንኳ መጨረስ አቅቷቸው መታየቱ ብዙዎችን አነጋግሯል።ለ90 ደቂቃ በዘለቀው ክርክር ባይደን ቃላቶች እየጠፏቸው ሃሳባቸውን መግለጽ ሲያቅታቸው ተስተውሏል ከዚህ አንፃር በክርክሩ ትራምፕ ባይደንን በልጠው ታይተዋል።

ጆ ባይደን በተጫናቸው እርጅና ሳቢያ አሜሪካን በፕሬዚዳንትነት ለተጨማሪ አራት ዓመታት መምራት ስለመቻላቸው በርካታ አሜሪካውያን ሲጠራጠሩ የቆዩ ሲሆን፤ የትናንት ምሽቱ የምርጫ ክርክር የአሜሪካውያኑን ስጋት ከፍ አድርጎታል።(ዶቼ ቬሌ)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ያለፍቃዳችን ከደመወዛችን 1000 ብር ተቆረጠብን‼️

#ጋምቤላ ዙሪያ ወረዳ የሚሰሩ የመንግስት ሰራተኞች ህጋዊ ባልሆነ መንገድ 1000 ብር እና ከዚያ በላይ ተቆርጦብናል ሲሉ በርካታ ሰዎች ጥቆማ አድርሰውኛል። 

ለምንድነው ብለን ብንጠይቅ ለትግራይ ክልል መልሶ ማቋቋምና በአማራ ክልል ውጊያ ውስጥ ለሚገኘው የመከላከያ ሰራዊት ድጋፍ የሚውል ነው ሲሉ ምላሽ ሰጥተውናል ብለዋል።

ለምን የእኛ ፍቃደኝነት ሳትጠይቁን ስንላቸው ከፈለጋችሁ እናስወጣችኋለን፣ይሄ እኮ የመንግስት ብር ነው ከኪሳችሁ የሚወጣ አይደለም የሚል መልስ ሰጥተውናል ብለዋል። ከዚህ በተጨማሪ የወር ደመወዝ የሚከፈለን 15-20 ቀን ዘግይቶ ነው ብለዋል።

በህጉ መሰረት የአንድ የመንግሥት ሰራተኛ ደመወዝ ተቀናሽ የሚሆነው ወይም ሊቆረጥ የሚችለው በፍርድ ቤት ትዕዛዝ እና በሰራተኛው ፍቃድ ብቻ እንደሆነ ያስረዳል።

@ethio_mereja_news
መራጮች ላይ ጫና አሳድረዋል

ኢሰመኮ ዕሁድ'ለት ድጋሚ ምርጫ በተካሄደባቸው ክልሎች የቀበሌና የወረዳ አመራሮች እንዲኹም የገዥው ብልጽግና ፓርቲ አባላት በምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ መራጮች ላይ ጫና በሚያሳድር ኹኔታ ድምጽ ሰጪዎችን በመመዝገብና በማነጋገር ድርጊቶች ላይ ተሠማርተው መታዘቡን አስታውቋል።

ኢሰመኮ፣ በአብዛኛዎቹ ምርጫ ጣቢያዎች ውስጥ ወይም ከምርጫ ጣቢያዎች በ500 ሜትር አቅራቢያ የደንብ ልብስ የለበሱ የጸጥታ አካላት ሲንቀሳቀሱ መመልከቱን ገልጧል።

በሶማሌ ክልል በጅግጅጋ እንዲኹም በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል በመስቃን እና ማረቆ ምርጫ ክልሎች በግለሰቦች መኖሪያ ቤቶችና በኃይማኖት ተቋም ትምህርት ቤት ውስጥ አምስት የምርጫ ጣቢያዎች ተቋቁመው እንደነበርም ኢሰመኮ ገልጧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/09/29 01:21:33
Back to Top
HTML Embed Code: