Telegram Web Link
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💥💥 የዋጋ ግሽበት ከመቼውም በላይ እየጨመረ ይገኛል

👉ብልህ ሰዉ ነገዉን ዛሬ ይወስናል !!ይፍጠኑ !!
DMC Real Estate Plc
በለቡ መብራት 65,395ካሬ ላይ ያረፈ ሰፊ እና እጅግ ዉብ መንደር

ቻድ ኢንባሲ እና CDC በቅርብ ርቀት ላይ ይገኛል !
👉በምቹ አከፋፈል 10%  560.ሺ ቅድመ ክፋያ ጀምሮ
👉የንግድ ሱቆች G.floor -2rd floor ከ 24 ካሬ ጀምሮ
👉ከstudio 56ካሬ እስከ 4መኝታ 186ካሬ .በተለያየ የካሬ አማራጭ

👉በሚገርም ወብ Design የቀረበ
👌በዘመነ ፈጣን በተቀላጠፈ ቴክኖሎጂ አልሙንየም ፎርም ወርክ የሚሰራ

😄❗️ሰበር ዜና
❗️ዛሬ አዳዲስ 2ኛ floor ጀምሮ ዝቅተኛቤት floor ጥቂት ቤቶች  አዉተናል ይፋጠኑ,ይምረጡ  !!
🌀 ብርዎትን አሰሩት፤ በኢትዮጵያ ትልቁ አዋጭ የሆነው የሪል እስቴት ቢዝነስ ነው፡፡

ዲኤም ሲ ሪል እስቴት/Dmc Real Estate

ለበለጠ መረጃ /ለሳይት ጉብኝት
ይጀዉሉልን!
☎️ 0961478081
በትግራይ ክልል ከ122 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና እየወሰዱ ነው‼️


በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ዶክተር ታደሰ ካህሳይ እንደገለጹት፤ የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተናው እየተሰጠ ያለው በ1ሺህ 129 ትምህርት ቤቶች ነው።

ፈተናው ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሦስት ቀናት እንደሚሰጥም ተናግረዋል።

እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ፣ ከተፈታኞች መካከል 62 ሺህ 732 የሚሆኑት ሴት ተማሪዎች ናቸው።

ተማሪዎቹ ፈተናውን በተረጋጋ ሁኔታ እንዲወስዱ አስቀድሞ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ መሰራቱን ተናግረዋል።

የፈተና ኩረጃን ለመከላከል ተቆጣጣሪዎች በበቂ ሁኔታ መመደባቸውን ጠቁመው፣ ለፈተናው ሰላማዊነትም የጸጥታ አካላት የበኩላቸውን እየተወጡ መሆኑን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጥቆማ‼️

በቴሌግራም ገንዘብ መስራት ይቻላል ለሱም ምስክር NOTCOIN መመልከት በቂ ነው።

በኦንላይን ገንዘብ መስራት ከፈለጋቹ አሁንኑ ይህንን ቻናል መቀላቀል ግድ ነው👇👇
http://www.tg-me.com/sheger_crypto
http://www.tg-me.com/sheger_crypto
ሂውማን ራይትስ ዎች፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሌሎች ሦስት የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣን በሰብዓዊ መብት ድርጅቶችና ጋዜጠኞች ላይ የሚያደርጉትን አፈና እንዲያቆሙ በጋራ ባወጡት መግለጫ ጠይቀዋል።

ድርጅቶቹ፣ በአገር በቀል የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ላይ የሚፈጸመው ማስፈራሪያና ዛቻ የሰብዓዊ ድርጅቶቹ ሥራቸውን ባግባቡ እንዳይሠሩ አድርጓል ብለዋል።

የመንግሥት የጸጥታና ደኅንነት ኃይሎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ካውንስል (ኢሰመጉ) እና ሌሎች የሲቪክ ድርጅቶችና ጋዜጠኞች ላይ የሚፈጽሙት ማስፈራሪያ እና ዛቻ መጨመሩን ድርጅቶቹ በመግለጫቸው አውስተዋል።

የኢትዮጵያ ዓለማቀፍና አሕጉራዊ አጋሮች፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የፖለቲካ ተቀናቃኞቹን፣ የጋዜጠኞችን፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን መብት እንዲያከብር ግፊት እንዲያደርጉና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤትም ክትትል እንዲያደርጉ ድርጅቶቹ ጠይቀዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Good News‼️

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የመቐለ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተገልጿል።

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ አገልግሎት መስጠት የጀመረው ዛሬ ነው።

በዚህም በጊዜያዊነት የጀመራቸው አገልግሎቶች ፦
☑️ ፓስፖርት ማደስ፣
☑️ የጠፋ ፓስፖርት መተካት፣
የተበላሸ  ወይ እርማት የመስጠት አገልግሎቶች እንደሆነም ተገልጿል።

የመቐለ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ፅህፈት ቤት ተወካይ ክንፈሚካኤል ረዳሀኝ ዛሬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ከጦርነቱ በፊት በፅህፈት ቤቱ በርካታ አገልግሎት ሲሰጥ እንደነበር አመልክተዋል።

በጦርነቱ ሁሉም አገልግሎት ተቋርጦ እንደነበር አስታውሰዋል።

ከፕሪቶሪያ ሰላም ስምምነት በኃላ ቢዘገይም የፓስፓርት እድሳት አገልግሎት አሁም መሰጠት እንደተጀመረ ገልጸው ፤ “ በመላ ትግራይ የሚገኙ የፓስፓርት እድሳት ፈላጊዎች በአካል መምጣት ሳይስፈልጋቸው ባሉበት ሆኖው በኦንላይን መገለግል ይችላሉ “ ብለዋል።

ተገልጋዮች ወደ (መቐለ) ፅ/ቤቱ መምጣት ያለባቸው ሁሉም ነገር ጨርሰው ማህተም ለማስመታት ብቻ እንደሆነ ጠቁመዋል

@sheger_press
@sheger_press
የአዲስ አበባ ሰፈሮች ስያሜ እና ትርጉም

1)ዶሮ ማነቂያ
ይህ ሰፈር በድሮ ጊዜ ወንጀለኞች በስቅላት ይቀጡበት የነበረ ዛፍ ይገኝበት ነበር።በጊዜ ብዛት ቦታው ላይ የስቅላት ቅጣት መፈጸም ቀረ፣ ስዎችም ሰፈሩን ድሮ ማነቂያ እያሉ ይጠሩት ጀመር።በጊዜ ብዛት ድሮ ማነቂያ ወደ ዶሮ ማነቂያ ተለውጦ ቋሚ መጠሪያው ሆነ።

2)በቅሎ ቤት
በአፄ ሀይለስላሴ ዘመነ መንግስት መድፈኛ ጦር መቀመጫው ላንቻ አከባቢ የነበረ ሲሆን በወቅቱ መድፎችን ወደ ሌላ ቦታ መውሰድ ሲፈለግ ተፈታተው በበቅሎ ይጫኑ ነበር።በዚህ ምክንያት በመድፈኛ ጦር ሰፈር ውስጥ ለማጓጓዣነት የሚጠቅሙ ከመቶ ያላነሱ በቅሎዎች ነበሩ።በአከባቢው በርካታ በቅሎዎች ስለነበሩ ሰፈሩ "በቅሎ ሰፈር" እየቆየ ሲሄድ ደሞ "በቅሎ ቤት" እየተባለ መጠራት ጀመረ።

3) ሠራተኛ ሰፈር
በአፄ ምኒልክ ቤተ-መንግስት ውስጥ በዕደ-ጥበባት ሙያ በተሰማሩ ሰራተኞች በመመስረቱ ሰራተኛ ሰፈር ተብሏል።

4)ሰባራ ባቡር
ይህ ሰፈር ስያሜውን ያገኘው ሙሴ ሰርኪስ ተርዚያን በተባሉ አርመናዊ ነጋዴ አማካኝነት ከውጭ ሀገር መጥቶ አሁን ስያሜውን ባገኘበት ቦታ ተበላሽቶ በቀረው የመንገድ መስሪያ ተሽከርካሪ (ሮለር) ምክንያት ነው።

5) አራት ኪሎ
ይህን ስያሜ ሊያገኝ የቻለው አራት መንገዶች የሚገናኙበት ቦታ ስለነበረ ነው።

6)ተረት ሰፈር
ተረት ሰፈር ስያሜውን ያገኘው በአዲስ አበባ ከተከፈቱት የመጀመሪያዎቹ ሆቴሎች አንዱ በነበረው ሆቴል ዳፍራንስ ባለቤት በሆኑት ፈረንሳያዊ ሙሴ ቴረስ ስም ነው።

7) ጎፋ ሰፈር
በቀዳማዊ ሀይለስላሴ ዘመን ለማይጨው ጦርነት ከጋሞ ጎፋ አከባቢ ለመጡና በጦርነቱ ወቅት ከፍተኛ ትግል ላደረጉ አርበኞች የተሰጠ ቦታ በመሆኑ መጠሪያው ጎፋ ሰፈር ተብሏል።

8)ጠመንጃ ያዥ
ሰፈሩ አራተኛ ክፍለ ጦር አከባቢ ይገኛል።ጠመንጃ ያዥ የተባለበት ምክንያት ከጣልያን ወረራ በፊት የቤተ መንግስት ጠባቂዎች በብዛት ይኖሩበት ስለነበረ ነው።

9) ፖፖላሬ
በጣልያን ወረራ ወቅት ተራው ጣልያናዊ ሰራተኛ የሰፈረበት ሰፈር ነበር።ስያሜው ፖፖሎ ከሚለውና ሕዝብ የሚል ትርጉም ካለው የጣልያን ቃል የተወሰደ ነው።

10) ሸጎሌ-
ሼህ ኦጀሌ የቤንሻንጉል ጉሙዝን አከባቢ ሲያስተዳድሩ የነበሩ የበርታ ብሄረሰብ ተወላጅ ነበሩ።እኝህ ሰው ከአፄ ምኒልክ ዘመን ጀምሮ ለማዕከላዊው መንግስት ታማኝ ሆነው አከባቢውን ከጠላት ወረራ ሲከላከሉ ኖረዋል።በዚህም የተነሳ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ በተለምዶ ሸጎሌ የሚባለው አከባቢ ቤተ-መንግስት አላቸው።በዚህም ምክንያት ሰፈሩ በስማቸው ሼህ ኦጀሌ ተባለ፤ በጊዜ ብዛትም ወደ ሸጎሌ ሊለወጥ ችሏል።

ምንጭ፦ አዲስ አበባ መፅሄት እና አዲስ አድማስ ጋዜጣ፣ ኢንጂነር እሸቴ ; ዋሱ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ኢትዮጵያ ውስጥ በቅድመ መደበኛ፣ በመጀመሪያ እና 2ኛ ደረጃ ላይ ያሉ17 ሚሊዮን የሚጠጉ ሕፃናት ከትምህርት ውጪ መሆናቸውን ዩኒሴቭ (UNICEF) አስታወቀ።

ዩኒሴፍ 3.5 ሚሊዮን የሚገመቱ በአንደኛ ደረጃና በሁለተኛ ደረጃ የሚገኙ ሕፃናት ትምህርታቸውን ለማቋረጥ ሥጋት መጋለጣቸውንና ይህም ትምህርት ላይ የተጋረጠውን ቀውስ የበለጠ ማባባሱን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ሥርዓተ ትምህርት "ችግር ፈቺ ያልሆነ፣ የሀገሪቱን ኑሮ እና ተጨባጭ ጉዳዮች የማይመለከት መሆኑ" በውጤትም ሆነ በጥራት ማሽቆልቆል እየታየበት መሆኑን አንድ የትምህርት ባለሙያ ተናግረዋል።

በጦርነትና ግጭት ክፉኛ እየተጎዳ ያለው የኢትዮጵያ የትምህርት ሁኔታ፤ ከዚያም ያለፉት የመንግሥት ሠራተኞች በደሞዝ ማነስ እየተፈተኑ ለትምህርት የሚሰጠውን ዋጋ እየጌዳ ስለመሆኑ ይነገራል።

ትምህርት ሚኒስቴር ኢትዮጵያ ውስጥ ከጠቅላላ ትምህርት ሰጪ 47 ሺህ ገደማ ትምህርት ቤቶች ደረጃቸው የላቁት አራት ናቸው ማለቱ ባለፈው ዓመት የተሰማ አስደንጋጭ እውነታ ሆኖ አልፏል።

በኢትዮጵያ ውስጥ ለሁሉም ሕፃናት ትምህርትን ለማረጋገጥ ጥረቶችን እንደሚመራ ያስታወቀው የመንግሥታቱ ድርጅት የሕፃናት መርጃ ማዕከል ትናንት ባወጣው መረጃ ደግሞ 17 ሚሊዮን የሚጠጉ ኢትዮጵያዊያንሕፃናትና ታዳጊ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ ናቸው።

Via:- Ethio FM
@sheger_press
@sheger_press
- በኦሮምያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ስድስት ወረዳዎች የከፋ ድርቅ ተከስቷል። ነዋሪዎች ለዋዜማ እንደነገሩት ላለፉት ሰላሳ ዓመታት ድርቅ ይከሰታል በሚል በመንግስትና በረድዔት ድርጅቶች በኩል የነፍስ አድን አቅርቦት አስቀድሞ ይዘጋጅና በአካባቢው ይከማች ነበር። አሁን ግን ለአደጋው ተገቢ ትኩረት እንኳን አልተሰጠውም ብለዋል።

- በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በሰሀላ ሰየምት ወረዳ በ2015/16 የምርት ዘመን የተከሠተው ድርቅ ያስከተለው ረኀብ ጉዳቱ በመባባሱ፣ ባለፈው ሳምንት በቢላዛ ቀበሌ የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የቀበሌው አስተዳደር አስታውቋል፡፡

- የዓለም የምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ 15.8 ሚልየን የምግብ እርዳታ የሚያስፈጋቸው ሰዎች መኖራቸውን አስታውቆ በጦርነት፣ በድርቅ እና በጎርፍ አደጋ ሳቢያ የተፈጠረው ቀውስ በአብዛኛው በአማራ፣ ኦሮሚያ እና ትግራይ ክልሎች ውስጥ እንደሆነ ገልጿል። በተጨማሪም አገሪቱ ከደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ኤርትራ እና ሱዳን የተፈናቀሉ 1 ሚልየን ስድተኞችን እያስተናገደች የሚገኝ ሲሆን ከሱዳን አሁንም ስደት የቀጠለ መሆኑ ተመላክቷል።

Photo: UNOCHA

Via VOA/AS/AM

@sheger_press
@sheger_press
የሟቾች ቁጥር ወደ 550 ማደጉ ተሰማ

አመታዊውን የሀጂ ስነስርአት ለመካፈል ወደ ሳኡዲ ካቀኑ ሰዎች መካከል ከ550 በላይ ሰዎች በሙቀት መሞታቸው ተሰምቷል፡፡

ከከፍተኛ የሙቀት መዕበል ጋር በተያየዘ በሚፈጠሩ በሽታዎች ነው ሃጃጆቹ ህይወታቸው ያለፈው፡፡ ከሟቾቹ መካከል 323 የግብጽ ፣ 144 የኢንዶኔዢያ፣ 35 የቱኒዝያ ፣ 11 የኢራን ፣ 6 የሴኔጋል ዜግነት ያላቸው ሃጃጆች ናቸው ተብሏል፡፡

የሟች ቤተሰቦች በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የሳኡዲ ሆስፒታሎች ዘመዶቻቸውን በማፈላለግ ላይ ሲሆኑ ዮርዳኖስ በበኩሏ በሃጂ የሞቱ ዜጎቿን ለመቀበር 41 የመቃብር ስፍራዎችን ማዘጋጀቷን በትላንትናው እለት አስታውቃለች፡፡

የዘንድሮው የሀጂ ስነስርአት ከ1.8 ሚሊዮን በላይ የእስልምና እምነት ተከታዮች የተካፈሉበት ሲሆን ከሰሞኑ በተለያዩ የአለም ክፍላት በተደጋጋሚ የተፈጠረው የሙቀት ማዕበል በሳኡዲም ለሃጃጆች ፈታኝ እንደሚሆን ሲነገር ሰንብቷል፡፡

የሳኡዲ የጤና ሚንስቴር ከሟቾቹ መካከል አብዛኛዎቹ አድሜያቸው የገፋ እና የጤና እክል የነበረባቸው ሃጃጆች መሆናቸውን ገልጾ ከሙቀት ማእበሉ ጋር በተገናኝ የታመሙ 2700 ሃጃጆች የጤና ክትትል እየተደረጋላቸው እንደሚገኙ አስታውቋል፡፡

ሚንስቴሩ ሀጃጆች በሚንቀሳቀሱበት ስፍራ ጃንጥላ እንዳይለያቸው እንዲሁም ከፍተኛ ሙቀት በሚኖርበት ከረፋዱ 5 - እስከ 9 ሰአት ድረስ በቤት ውስጥ እንዲቀመጡ ማስጠንቀቂያዎችን ሲያስነግር መሰንበቱን ነው የተናገረው፡፡

በባለፈው አመት ከሙቀት ጋር በተያያዘ እና በተለያዩ ችግሮች ከ240 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል፡፡

በተጨማሪም በ2015 በተፈጠረ ከፍተኛ መጨናነቅ ከ2000 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ ከ400 በላይ የሚሆኑት ደግሞ የደረሱበት መጥፋቱ ተነግሮ ነበር፡፡

Via:ዐል ዐይን

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
#Amahra

በአማራ ክልል ፤ በምዕራብ ጎንደር ዞን ' ታጣቂዎች ' ባደረሱት ጥቃት አንዲት ሱዳናዊ ስደተኛን ጨምሮ 3 ሰዎች መገደላቸው ተነግሯል።

በጥቃቱ በሌሎች ሁለት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል።

የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት የጥቃቱ ባለፈው እሁድ ሰኔ 9/2016 መፈጸሙን አረጋግጧል።

ጥቃት የተፈጸመው ከገንደ ዉሃ ወደ ነጋዴ ባህር ሲጓዝ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ " ደረቅ አባይ " በተባለ ስፍራ እንደሆነ ተጠቁሟል።

የዞኑ ኮሚኒኬሽን ጥቃቱ ከቀኑ 10 ሰዓት መድረሱን አሳውቋል።

የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት ፥ በህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ ታጣቂዎች ተኩስ ከከፈቱ በኃላ አንድ ውስጥ የነበረ የመንግስት የጸጥታ አባል ወርዶ የታጣቂዎቹ ጥቃት ለመከላከል ባደረገው የተኩስ ልውውጥ ከመኪናው ውስጥ የነበረች አንዲት ሱዳናዊ ስደተኛና ሌሎች ኢትዮጵያውያን መገደላቸውን አስረድቷል።

" የጥቃቱን መድረስ ተከትሎ የመንግስት ጸጥታ ኃይል በአፋጣኝ ባይደርሱ ኖሩ ከአሁኑ የበለጠ የከፋ ጉዳት ሊከሰት ይችል ነበር " ሲልም ገልጿል።

የተፈጸመው ጥቃት በዘፈቀደ እንጂ በስደተኛዋ ላይ ያነጣጠረ እንዳልነበር አክሏል።

ስደተኛዋ በወቅቱ ፤ መድሃኒት ገዝታ ወደ መጠለያዋ እየተመለሰች ነበር ተብሏል።

የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ስደተኞች ከመጠለያ ጣቢያቸው እንዳይወጡ በተደጋጋሚ ቢነገራቸውም አንዳንዶቹ ተግባራዊ ማድረግ ባለመቻላቸው  ለአደጋ እየተጋለጡ ሲል ገልጿል።

የመረጃው የዶቼቨለ ሬድዮ ነው።

@ethio_mereja_news
NewsALert‼️

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የፋኖ ታጣቂዎች በተቆጣጠሯቸውና ወጣ ገባ በሚሉባቸው ወረዳዎች የባንክ አገልግሎት እንዲቋረጥ መደረጉን ዋዜማ ተረድታለች፡፡

በዞኑ የባንክ አገልግሎት ከተቋረጠባቸው ወረዳዎች መካከል መንዝ ላሎ፣ ግሼ ራቤል፣ አንፆኪያ ገምዛና ቀወት እንደሚገኙበት ዋዜማ በየወረዳዎቹ የባንክ ቅርንጫፎች አረጋግጣለች፡፡ የባንክ አገልግሎቱን በተጠቀሱት ወረዳዎች እንዲያቋርጡ የተገደዱት የግል ባንኮች ጭምር መሆናቸውን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

በተጠቀሱት ወረዳዎች የባንክ አገልግሎት የተቋረጠው ካለፈው አርብ ሰኔ 7/2016 ዓ.ም ጀምሮ መሆኑን ዋዜማ ተረድታለች፡፡

ከአርብ ጀምሮ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ስዓት ድረስ በመንዝ ላሎ ወረዳ ወገሬ ከተማ፣ በግሼ ራቤል ወረዳ ራቤል ከተማ፣ በአንፆኪያ ገምዛ ወረዳ መኮይ ከተማና ቀወት ወረዳ ራሳ ከተማ ባንኮች እንደተዘጉ ናቸው፡፡

በአንጻሩ የአንጾኪያ ገምዛ ወረዳ አካል በሆነችው ማጀቴ ከተማ ባንኮች አገለግሎት መስጠት መቀጠላቸውን ዋዜማ ከከተማዋ ነዋሪዎች ሰምታለች፡፡ ምንም እንኳን በከተማዋ አገልግሎት ባይቋረጥም ባንኮች ለደንበኞቻቸው የሚሰጡት ወጪ ገደብ ተጥሎበታል ተብሏል፡፡ 

አገልግሎቱ የተቋረጠው ባንኮቹ ድንገተኛ ትዕዛዝ ከመንግሥት አካል ከደረሳቸው በኋላ መሆኑን፣ የየወረዳዎቹ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የግል ባንኮች ሰራተኞች ለዋዜማ ተናግረዋል፡፡ ድንገተኛ የተባለው ትዕዛዝ ለባንኮቹ የተላለፈው የሸዋ ቀጠናን ከሚመራው ኮማንድ ፖስት መሆኑን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

(Wazema)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
እነ አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ በ50 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ፍርድ ቤት ፈቀደ                                            

ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓትን በትጥቅ ትግል ለመቀየር” በመንቀሳቀስ የተጠረጠሩት አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ፣ የቴአትር አዘጋጅ ዳግማዊ ፈይሳ እና ፍላጎት አብርሃምን ጨምሮ 17 ግለሰቦች እያንዳንዳቸው በ50 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት ፈቀደ።

በዚሁ መዝገብ ተጠርጥረው የቀረቡት ሌሎች ሶስት ግለሰቦች በአንጻሩ 11 ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ተፈቅዶባቸዋል።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ይህንን ብያኔ ያስተላለፈው ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 13/2016 ዓ.ም. ረፋድ ላይ በነበረው የችሎት ውሎ ነው።

ችሎቱ ዛሬ የተሰየመው ከትናንት በስቲያ ማክሰኞ ዕለት በነበረው የፍርድ ቤት ውሎ ግራ ቀኙ ያቀረቧቸው ጥያቄዎችን መርምሮ ብይን ለመስጠት ነበር።

በማክሰኞ ዕለቱ የችሎት ውሎ መርማሪ ፖሊስ ሀያዎቹ ተጠርጣሪዎች ላይ ተጨማሪ የምርመራ ቀናት እንዲፈቀድለት ሲጠይቅ ጠበቆች በአንጻሩ የዋስትና መብት እንዲከበር ጠይቀው እንደነበር ጠበቃ አያሌው ቢታኔ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ከተቀመጠው አሰራር ውጪ የመኖሪያ ቤት ዋጋ ጭማሪ ማድረግ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ።

የአከራይ ተከራይ አዋጅ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በህግ ከተቀመጠው አሰራር ውጪ የመኖሪያ ቤት ዋጋ ጭማሪ ማድረግና የነበረውን የኪራይ ውል ማቋረጥ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ አስታውቋል፡፡

በሀገሪቱ ውስጥ ያለውን ፍትሃዊ ያልሆነ የዋጋ ጭማሪ በማህበረሰቡ ላይ የሚፈጥረው ጫና ከግምት ውስጥ በማስገባት የቤት ኪራይ ስርአቱ በህግ የሚመራ እና ተገቢውን ቁጥጥር በማድረግ ለችግሩ አፋጣኝ ምላሽ መስጠት ተገቢ ሆኖ ሰለታመነበት የመኖሪያ ቤት ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ቁጥር 1320/2016 መጋቢት 24/2016 መውጣቱ ይታወቃል።

የከተማ አስተዳደሩም የአዋጁን ማስፈፀሚያ መመሪያ ቁጥር 7/2016 በማውጣት ተግባራዊ አድርጓል።

በመሆኑም አዋጁ ወጥቶ ተግባራዊ ከሆነበት ቀን ማለትም ከመጋቢት 24/2016 ጀምሮ መንግስት ከሚያስቀምጠው የኪራይ ውሳኔ ውጪ በአከራዮች የሚደረግ የኪራይ ዋጋ ጭማሪ ፈፅሞ የተከለከለ በመሆኑ አዋጁ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ከህግ ከተቀመጠው አሰራር ውጪ የመኖሪያ ቤት ዋጋ ጭማሪ ማድረግና የነበረውን የኪራይ ውል ማቋረጥ በጥብቅ የተከለከለ መሆኑን ቢሮው ገልጿል።

ይህ እንዲፈፀምም ቢሮው ተገቢውን ቁጥጥር እና ክትትል እንደሚያደርግም ማስታወቁን ከአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡

የህግ ክልከላውን ተላልፈው የተገኙ አከራዮች ላይ በመመሪያ ቁጥር 7/2016 አንቀፅ 22 መሰረት አስተዳደራዊ እርምጃ እንደሚወሰድም ቢሮው አሳስቧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
አንድ ቤት ለገዛ አንድ ቤት በነፃ

‼️ከ 300ሺ ብር ጀምሮ

📞0961478081

📍አድራሻ - በደማቋ ለቡ ማብራት-ሀይል

⚡️ሊኖሩበት ቢፈልጉ ሰላሚዊ መንደር፣ ሊያከራዩት ቢያስቡ በጥሩ ዋጋ እና መልሰው እንኳን ቢሸጡት በደንብ የሚያተርፉበት!

💸5% ቅድመ ክፍያ ብቻ
💸 50% የባንክ ብድር አገልግሎት



👉 እንደ ፍላጎቶ ሙሉ በሙሉ ያለቁ(fully-finished) ወይም እርሶ በሚፈልጉት መልኩ የሚጨርሱትን(semi-finished) ሆኖ መረከብ ይችላሉ።

🛌እስቱድዮ - 56 - 58 ካሬ
   ባለ 1 መኝታ - 77.7 - 98 ካሬ
   ባለ 2 መኝታ - 123 - 134 ካሬ
   ባለ 3 መኝታ - 146 -157 ካሬ
   ባለ 4 መኝታ - 177 - 186 ካሬ
የንግድ ሱቆች - 20- 900 ካሬ

👉ለ 50 ቤቶች ብቻ የወጣ ከ 8% - 25%  ቅናሽ አድርገናል

📞0961478081
ስምንት ህጻናትን በህገወጥ መንገድ ከሀገር ሊያስወጡ የነበሩ ሁለት ህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች በእስራት ተቀጡ

በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ስምንት ህጻናትን በህገወጥ መንገድ ከሀገር ሊያስወጡ የነበሩ ሁለት ህገወጥ የሰዎች አዘዋዋሪዎች በድምሩ በ 30 አመት እስራት እንደተቀጡ ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል።

በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ደደር ወረዳ ተከሳሽ መሀመድ አህመድ የተሰኘዉ ግለሰብ ሃምሌ 14 ቀን 2015 ዓ.ም ከቀኑ 8 ሰዓት አካባቢ በደደር ከተማ 08 ቀበሌ ከሚጠራዉ አካባቢ እድሜያቸዉ 15 ዓመት የሆኑ ሶስት ህጻናትን ወደ ሳዑዲ አረቢያ በመሄድ በከፍተኛ ገንዘብ ተቀጥራችሁ ቤተሰቦቻችሁን ትደግፋላችሁ በማለት ቤተሰቦቻቸውን ካሳመነ በኋላ ወደ ሀረር ከተማ ወስዷቸዋል ሲሉ የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ክፍል ሃላፊ አቶ ሱሌማን ቱጁሃን ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

በሀረር ከተማ አንድ ቀን ካሳደራቸዉ በኋላም ወደ ጅግጅጋ ከተማ ታዳጊዎቹን በመዉሰድ የኢትዮ-ሶማሊያ ድንበርን በመጠቀም አደዉ ከተማን ላይ ለሌላ ደላላ አሳልፎ እንደሰጣቸዉ በምርመራ ተረጋግጧል። ህጻናቱን የተረከበዉ ሌላኛዉ ደላላም ወደ ሶማሊላንድ ላሶኖ አሻግሯቸዋል ሲሉ ገልጸዋል።

በሶማሊላንድም ከእያንዳንዳቸው ህጻናት ቤተሰቦች 27 ሺህ ብር እንዲልኩ አስገድዷል ብለዋል። በዚህ መካከል አንደኛዉ ህጻን ከደላሎች እጅ አምልጧል። ፖሊስ ከደላሎች እጅ በወጣዉ ታዳጊ መረጃ መሰረት አደረኩት ባለዉ ክትትል ዋነኛ የወንጀሉ ጠንሳሽ የሆነዉን መሀመድ አህመድን በቁጥጥር ስር አዉሎታል።

ግለሰቡ የቀረበበትን ክስ ሊከላከል ባለመቻሉ የምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሰኔ 4 ቀን 2016 ዓ.ም ባዋለዉ ችሎት በግለሰቡ ላይ የ 15 አመታት እስራት ቅጣት መወሰኑን ተናግረዋል።በተመሳሳይ በዞኑ ጎሮ ጉቱ ወረዳም በህገወጥ የሰዎች ዝዉዉር የተከሰሰዉ ግለሰብ በ 15 አመት እስራት መቀጣቱ ተነግሯል።

ተከሳሽ መገርሳ አብደላ የተባለዉ ግለሰብ ታህሳስ 12 ቀን 2016 ዓ.ም በወረዳዉ ካራ ሚሌ ከተማ እድሜያቸዉ 15 አመት የሆኑ አምስት ህጻናትን በማታለል ወደ ሳዑዲ አረቢያ እልካቸዋል በሚል አታሏቸዋል ተብሏል። ግለሰቡ በተመሳሳይ ህጻናቱን ወደ ሶማሊላንድ ካሻገረ በኋላ ገንዘብ ቤተሰቦቻቸውን ጠይቋል።

ከእያንዳንዳቸው ቤተሰቦችም 1 ሺህ 200 ብር ለመቀበል ሲያስገድድ ነበር ብለዋል። ፖሊስ ግለሰቡን በቁጥጥር ስር አዉሎ በዚህ ግለሰብ ላይም ክስ መስርቶበታል።በምስራቅ ሀረርጌ ዞን ከፍተኛ ፍ/ቤት ሰኔ 7 ቀን 2016 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት ተከሳሽ መገርሳ አብደላን ጥፋተኛ ሲል በ 15 አመታት እስራት እንዲቀጣ ወስኗል ሲሉ የከፍተኛ ፍ/ቤት ቤቱ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ክፍል ሃላፊ አቶ ሱሌማን ቱጁሃን ጨምረዉ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሚንስትሮች ምክር ባቀረበለት የንብረት ታክስ ረቂቅ አዋጅ ላይ ትላንት ተወያይቶ ለፕላን፣ ፋይናንስና በጀት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ መርቷል።

ምክር ቤቱ ረቂቅ አዋጁን ለቋሚ ኮሚቴው ለመምራት በሰጠው ድምጽ፣ ሦስት የተቃውሞ ድምጾች ተመዝግበዋል። ረቂቅ አዋጁን የተቃወሙ ኢዜማን እና የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄን የወከሉ የምክር ቤቱ አባላት፣ መንግሥት የሚጥላቸው ተደራራቢ ታክሶች ድሃውን የኅብረተሰብ ክፍል የሚጎዱ እንደኾኑ ተናግረዋል። የአብን ተወካይ ደሳለኝ ጫኔ፣ ሕዝቡ የንብረት ታክስን ሊቋቋም የሚችልበት አቅም እንደሌለው ገልጠው ምክር ቤቱ ረቂቅ አዋጁን ውድቅ እንዲያደርገው ጠይቀዋል። ረቂቅ አዋጁ፣ በከተሞች በግለሰቦች መሬት፣ በመሬት ላይ በሚደረጉ ማሻሻያዎች እና ሕንጻዎች ላይ መንግሥት ታክስ እንዲሰበስብ የሚፈቅድ ነው። የንብረት ታክስን የመሰብሰብ አዋጅ ለክልሎች እንዲኾን ቀደም ሲል የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና ፌደሬሽን ምክር ቤት በጋራ መወሰናቸው ይታወሳል።
ከእንግዲህ መንግስት እንፈለገ ገንዘብ አይወስድም‼️

ብሄራዊ ባንክ ለመንግስት ቀጥታ ብድር እንዳይሰጥ የሚከለክል ረቂቅ አዋጅ ለፓርላማ ቀረበ

ባለፉት ዓመታት በመቶ ቢሊየን የሚቆጠር ገንዘብ ከብሄራዊ ባንክ የወሰደው መንግስት ከዚህ በኋላ እንደፈለገ የሚበደርበትን አሰራር የሚከለክል አዲስ ረቂቅ አዋጅ ለተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ።

ረቂቅ አዋጁ እንዳሰፈረው መንግስት የከፋ ችግር ካልገጠመው በቀር ከብሄራዊ ባንክ ያለገደብ የሚበደርበት አሰራር ከዚህ በኋላ በህግ የተከለከለ ይሆናል።

ይህ ድንጋጌ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ማቋቋሚያ አዋጅን ለማሻሻል በቀረበው ረቂቅ አዋጅ ላይ ተካቶ የቀረበ ሲሆን በረቂቅ አዋጁ ክፍል አምስት በብሔራዊ ባንክ እና በመንግስት መካከል የሚኖረውን ግንኙነት ባተተበት ምእራፍ ውስጥ ተካቷል።
“በአዋጁ በግልጽ ካልተፈቀደ በስተቀር ብሔራዊ ባንክ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ ለፌዴራል ; ለክልል ; ለማንኛውም የታችኛው የመንግስት የአስተዳደር እርከን ፣ የከተማ አስተዳደር ወይም የመንግስት ተቋም ብድር መስጠት አይችልም ” ይላል።

(ዋዜማ)
@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
YesCoin‼️

እንደሚታወቀው ይህ ኤርድሮፕ List መሆኑ የተረጋገጠና በTon Blockchain List የሚደረግ ነው።

አሪፍ Task ስላሉት ሰብስቡ ።

የጀመራቹ በርትታቹ ስሩ

ያልጀመራቹ ጊዜው ሳይረፈድ ቶሎ ጀምሩ

በዚ Link👇👇
https://www.tg-me.com/theYescoin_bot/Yescoin?startapp=PP9BDi
https://www.tg-me.com/theYescoin_bot/Yescoin?startapp=PP9BDi

ለዝርዝር መረጃው
ይሄን ቻናል ይቀላቀሉ👇👇
http://www.tg-me.com/sheger_crypto
http://www.tg-me.com/sheger_crypto
ሰኔ 16 ስራ ዝግ ይሆናል።የት?👇

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ሰኔ 16 ቀን 2016 ዓ.ም. በቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ በአፋር፣ በሶማሌ እና በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልሎች የሚያስፈጽመውን የ6ኛው ዙር ቀሪና እና የድጋሚ ምርጫን አስመልክቶ መግለጫ ሰጥቷል፡፡

በመግለጫውም ዜጎች ዕለቱን ለድምፅ መስጫ ብቻ መጠቀማቸው ስለሚያስፈልግ የምርጫ አካባቢዎች የሚገኙ የፌዴራልና የክልል መንግሥታዊ ተቋማት ሰኔ 16 ቀን 2016 ዓ. ም. ሥራ ዝግ እንዲያደርጉ ቦርዱ አስታውቋል፡፡

የትራንስፓርት አገልግሎት በተለመደው መንገድ የሚቀጥል ቢሆንም፤ የምርጫ አካባቢዎች ዜጎች ድምፅ ከመስጠት ውጪ ከፍተኛ እንቅስቃሴን የሚፈልጉ ሁነቶችንና ዕቅዶችን እንዳይዙ፤ እንዲሁም እንቅስቃሴያቸውን ድምፅ ለመስጠት ብቻ እንዲያደርጉ ቦርዱ አስታውቋል።(wasu)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ተፈቅዷል‼️

የመንግሥት ሰራተኞች የደረጃ እድገት እና የእርከን ጭማሪ በአዲሱ ረቂቅ አዋጅ ተፈቅዷል፦ የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን

አዲሱ የፌዴራል መንግስት ረቂቅ የሰራተኞች አዋጅ ሰራተኞች ተመዝነው በአፈጻጸማቸው የሚለዩበት እንደሆነ የፌደራል ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) ገለጹ።   

አዋጁን በተዛባ መንገድ መረዳት አይገባም ያሉት ኮሚሽነሩ፤ አንድ ሰራተኛ ሁለት ጊዜ ተመዝኖ ውጤቱ ከመካከለኛ በታች ከሆነ ከስራው እንደሚሰናበትም ጠቁመዋል።
በዚህ ምዘና በቂ ውጤት ያመጡ ሰራተኞች ደግሞ የደረጃ እድገት እንዲሁም በየሁለት ዓመቱ የሚኖር የእርከን ጭማሪ እንዲያገኙ በአዋጁ ተደንግጓል ብለዋል።

የአዋጁ  ዋና ዓላማ ሰራተኛን መቀነስ ሳይሆን ማብቃት ነው ያሉት መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር)፤ በምዘናው  ደረጃ አሟልተው ብቁ የሆኑ፣ የተወሰነ ክፍተት ያለባቸው እና ሰፋ ያለ ክፍተት የታየባቸው ተለይተው ክፍተቶቹ በስልጠና እየተሟሉ ሶስቱም በመንግሥት መዋቅር ውስጥ የሚቀጥሉ ናቸው ብለዋል።

የመንግሥት ሰራተኛው በስራው ተመጣጣኝ ገቢ አለማግኘቱ በኑሮው ላይ ጫና ፈጥሮበታል፤ አዋጁ ይህን ችግር ለመፍታት የሚያስችል ነው ወይ ተብሎ ለቀረበላቸው ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ፥ አዋጁ የብቃት ምዘናውን ያለፉና መስፈርቱን የሚያሟሉ ሰራተኞች የደሞዝ ጭማሪ በእርከንና በደረጃ ዕድገት እያገኙ የሚሄዱበትን አስገዳጅ አሰራር መደንገጉን ተናግረዋል።

አዋጁ የፐብሊክ ሰርቪስ አገልግሎትን ለማሻሻልና ዲጅታል ሲቪል  ሰርቪስን ለመፍጠር ዓላማ ያደረገ ነው ያሉት ኮሚሽነሩ፤ ሁሉም ብሄረሰብ የተማረ የሰው ኃይል አለው ተብሎ ስለሚታሰብ ብዝሃነትን መሰረት ያደረገ ፕብሊክ ሰርቪስ ለመገንባት መታሰቡን ተናግረዋል።

ሥራ ላይ ያለው የፌዴራል መንግሥት የሰራተኞች አዋጅ ፖሊሲን መሰረት አድርጎ የተቀረጸ አይደለም ያሉት ኮሚሽነሩ፤ የመንግሥት አገልግሎትን መሰረታዊ በሆነ መልኩ ለመቀየር የሚያስችልም አልነበረም ብለዋል።

አሁን የተዘጋጀው አዋጅ ነጻና ገለልተኛ ሲቪል  ሰርቪስ ለመገንባት፣ የሰራተኛውን ብቃት ለማረጋገጥ፣ ብዘሃነትና አካታችነትን በተገቢው መንገድ ለመምራት እንደሚረዳ መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) ገልጸዋል።

Via EBC

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/11/18 18:17:01
Back to Top
HTML Embed Code: