Telegram Web Link
ኑሮ የከበዳቸው የመንግሥት ሠራተኞች የምሳ ሰዓትን በቤተ እምነቶች እያሳለፉ መሆኑ ተነገረ‼️
👉የቤት ኪራይ መክፈል ያልቻሉ ተደብቀው ቢሮ ውስጥ ያድራሉ ተብሏል።

መንግሥት የሚከፍላቸው ወርኃዊ ደመወዝ አልበቃ ያላቸው የመንግሥት ሠራተኞች የምሳ ሰዓታቸውን ወደ ቤት እምነቶች በመሄድ፣ እንዲሁም ቤት ተከራይተው መኖር የማይችሉት ደግሞ ቢሮ ውስጥ ተደብቀው እንደሚያድሩ ተገለጸ፡፡

በ2010 ዓም ተሻሽሎ ወደ ሥራ ገበቶ የነበረው ባለ 106 አንቀጽ የፌዴራል መንግሥት ሠራተኞች አዋጅ፣ ከስድስት ዓመታት አገልግሎት በኋላ፣ በ160 አንቀጾች ተዋቅሮ በረቂቅ አዋጁ ላይ ውይይት እየተደረገበት ነው፡፡

ለመንግሥት መሥሪያ ቤት ኃላፊዎች የበዛ ሥልጣን የሚሰጥ፣ ለሠራተኞች ችግር ደግሞ መፍትሔ የማያመጣና ተቋማዊ አሠራርና አደረጃጀት ላይ ብቻ ያተኮረ ነው የሚል ትችት በረቂቅ አዋጁ ላይ ቀርቧል፡፡ የመንግሥት ሠራተኛውን ሕይወት የሚቀይር ሥራ እንጂ አዋጅ ማውጣት ብቻ አገርን አይቀይርም የሚሉ ድምፆችም ተሰምተዋል፡፡

ለመንግሥት ሠራተኞች የሚከፈለው ደመወዝ አነስተኛና ሊያኖር የማይችል ከመሆኑም በላይ፣ በበርካታ የኢትዮጵያ ክልሎች የሚገኙ የመንግሥት ተቋማት ደመወዝ መክፈል ተስኗቸው ሠራተኞች ለወራት ደመወዝ ሳይከፈላቸው መቆየታቸውን፣ እንዲሁም በአንዳንድ ክልሎች ደግሞ ከሚቀጥሉት ዓመታት በጀት ተበድረው ደመወዝ እየከፈሉ መሆናቸው በተደጋጋሚ ሲነገር ይደመጣል፡፡

በረቂቅ አዋጁ ላይ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የፐብሊክ ሰርቪና ሰው ሀብት ልማት ቢሮ የሰው ሀብት ሥራ አመራር ድጋፍና ክትትል ቡድን መሪ አቶ አብርሃም ደግፌ በሰጡት አስተያየት፣ በከተማ አስተዳደሩ 70 ያህል የመንግሥት ተቋማት ላይ ክትትል እንደሚያደርጉና ሥልጠና እንደሚሰጡ ጠቅሰው የሠራተኛው ሕይወት እጅግ በሚያሳዝን ሁኔታ ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡

በከተማ አስተዳድሩ አንድ ከፍተኛ የሚባል ባለሙያ ያልተጣራ ደመወዙ 9,056 ብር መሆኑን ጠቅሰው፣ ‹‹ከዚህ ግብር ተከፍሎበት በእጁ የሚደርሰውን ገንዘብ አስልታችሁ ድረሱበት፤›› ሲሉ ተሳታፊዎችን ጠይቀዋል፡፡ በዚህ ደመወዝ የቤት ኪራይ የከተማዋ ጫፍ እንኳ ቢኬድ 10,000 ብር መድረሱን፣ ነገር ግን ይህ ከፍተኛ ባለሙያ ሙሉ ደመወዙን ለቤት ኪራይ ላድርግ ቢል ገንዘቡ እንደማይበቃው አስረድተዋል፡፡

በዚህ ሁኔታ ላይ ያለ አንድ ሠራተኛ የተሻለ አገልግሎት መስጠት ይቻላል ወይ?  ተፈጥሯዊ ሁኔታውስ በራሱ ይፈቅድለታል ወይ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡ ይህ ችግር ደመወዝ በመጨመርም ይፈታል ብለው እንደማያስቡ ገልጸው፣ በሌሎች አማራጮች እንዲጠቀም ቢደረግ ችግሩ ሊቀል ይችላል እንጂ 2,000 ብር ቢጨመር እንኳን ሕይወቱ ላይ ለውጥ እንደማያመጣ ተናግረዋል፡፡ ‹‹በዚህም የተነሳ ሠራተኞች አንዳንዴ ቢሮ መጥተው ያለቅሱብናል፣ ምሳ  የምንበላበት የለም በማለት በግልጽ ይናገራሉ፤›› ብለዋል፡፡

ገንዘብ አልበቃቸው ያሉ የመንግሥት ሠራተኞች በምሳ ሰዓት ወደ ቤተ እምነቶች ሄደው እንደሚያሳልፉ አስረድተዋል፡፡ የመንግሥት ሠራተኛው ታማኝ ግብር ከፋይ ቢሆንም፣ ነገር ግን የሠራተኛውን ሕይወት የሚቀይር ነገር እስካልመጣ ድረስ በሚፈለገው ደረጃ አገልግሎት ሊሰጥ እንደማይችል ኃላፊው ተናግረዋል፡፡

በተመሳሳይ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክተር አቶ ሰሎሞን ይልማ፣ ‹‹የረቂቅ አዋጁን መዘጋጀት የሰማ የመንግሥት ሠራተኛ የደመወዝ ጭማሪ አለ የሚል አዝማሚያ እየሰማን ነው፤›› ብለዋል፡፡ የመንግሥት ሠራተኛው የረቂቅ አዋጁን ዝርዝር የማየትና የመስማት ፍላጎት እንደሌለው ጠቅሰው፣ ‹‹አዋጁ ቶሎ ተዘጋጅቶ ሠራተኛው የሚጠቀምበት አሠራር ካልተዘረጋ በቀጣይ ከሠራተኛው ጋር የምንጋፈጠው እኛው ነን፤›› ብለዋል፡፡ የመንግሥት ሠራተኛው ተስፋ መቁረጡንና ችግር ውስጥ መሆኑን የጠቀሱት አቶ ሰሎሞን፣ ‹‹አሁን ስለአዋጁ ወይም ዝርዝር እንድናወራለት ፍላጎት የለውም?›› ሲሉ አስረድተዋል፡፡

በአዲስ አበባ ደንብ ማስከበር ባለሥልጣን ውስጥ የሚሠሩና ደንብ የሚቆጣጠሩ ከ6,500 በላይ ኦፊሰሮች በወር 3,934 ብር እየተከፈላቸው ለአሥር ዓመታት በተመሳሳይ ደመወዝ እያገለገሉ መሆኑን ኃላፊው ተናግረዋል፡፡ በዚህ የተነሳ መሄጃ እያጡ ቢሮ ምቹ ሁኔታ አለ በሚል እየተደበቁ የሚያድሩ አሉ ብለዋል፡፡ በመሆኑም የመንግሥት ሠራተኞች መነሻና መድረሻ ደመወዝ ሊስተካከል ይገባል ሲሉ አሳስበዋል፡፡

በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሰው ሀብት ዳይሬክተር አቶ ካሳየ አረጋ፣ ሠራተኞች በተደጋጋሚ እየለቀቁ ዓመቱን በሙሉ ቅጥር ሲፈጸሙ እንደሚውሉ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ነገር ግን በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አገልግሎት ለመስጠት የተሻለ አደረጃጀትና ባለሙያ፣ ቢቻልም የሥራ አስፈጻሚው የመንግሥት አካል ውስጥ ያለውን ባለሙያ ሊገዳደሩና ሊጠይቁ የሚችሉ፣ ለቋሚ ኮሚቴዎች የተሻለ ድጋፍና ሙያ ያላቸው ሠራተኞች ቀጥረን ልንሠራ ይገባል፤›› ብለዋል፡፡

‹‹አልቻልንም ባለሙያም የለም፣ ጉዳዩ በደንብ መታየት አለበት፤›› ያሉት ዳይሬክተሩ፣ አዋጅ በወጣ ቁጥር ሠራተኛው ተስፋ የሚያደርግበት ድንጋጌ እየገባ ነገር ግን ለዓመታት ሳይተገበር ቆይቶ እንደገና እንዲሻሻል መምጣቱ በቅጡ ሊጤን ይገባል ብለዋል፡፡ 

የቤት ሠራተኛ ወርኃዊ ደመወዝ ከ2,500 ብር ላይ ባለፈበት በዚህ ጊዜ አንድ መንግሥት የፅዳት ሠራተኛ በ1,300 ብር መቅጠር የሰብዓዊ መብት ጥሰት አይሆንም ወይ ሲሉ ጥያቄ አቅርበዋል፡፡ በመሆኑም አሁንም ወደፊት ታይቶ የሚባለው ነገር ቀርቶና ያለው ነባራዊ ሁኔታ ግምት ውስጥ ገብቶ፣ ታች ያለው ሠራተኛ ዜጋ በመሆኑ ችግሩ ሊታይለት ይገባል ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

በፌዴሬሽን ምክር ቤት የሕገ መንግሥት ትርጉምና የሕጎች ሕገ መንግሥታዊነት ዳይሬክተር አቶ ሙለዬ ወለላው፣ የመንግሥት ሠራተኛው ሀቀኛና ታማኝ ግብር ከፋይ ሆኖ እያለ ለተለያዩ ዓይነቶች የታክስ ግዴታዎች ተገዥ መደረጉን፣ ለአብነትም ሠራተኛውን እንዲጠቅም ተብሎ ለትራንስፖርትና ለቤት ኪራይ የሚከፈል ገንዘብ ጭምር ግብር እየተከፈለበት እየተበዘበዘ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፐብሊክ ሰርቪስ ቢሮ የሰው ሀብት ክትትል ድጋፍና ኦዲት ዳይሬክተር አቶ መላኩ ተመስገን በሰጡት አስተያየት፣ አዋጆች እየወጡ ቁልፍ ጉዳዮች በመመርያ ይታያሉ እየተባሉ ነገር ግን መመርያ ሳይወጣና በውስጡ ያለው ድንጋጌ ሳይፈጸም ጊዜው ደርሶ እንደገና እንደሚሻሻል አስረድተዋል፡፡

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ተወዳዳሪ ባለመሆኑ ሠራተኞችን መሳብና ማቆየት እንደማይቻልና አንዳንዶችም ‹‹መሄጃ አጣን ብለው የተቀመጡ መሆናቸውን›› የተናገሩት አቶ መላኩ፣ እነዚህ ሠራተኞች እንዴት አገልግሎት ማሻሻል ይችላሉ? ሲሉ ጠይቀዋል፡፡

የሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን ኮሚሽነር መኩሪያ ኃይሌ (ዶ/ር) በሰጡት ምላሽ፣ በአዲስ አበባ ያለው ክፍያ የፌዴራል ተቋማት ከሚከፍሉት ይሻላል ብለዋል፡፡ ነገር ግን በሁለቱም የሚከፈለው ግን የኑሮ ሁኔታን ለመቋቋም የሚያስችል አለመሆኑን ገልጸዋል፡፡ 

‹‹ብዙውን ጊዜ ትኩረት የሚሰጠው የመጨረሻ ውጤት ላይ እንጂ ደመወዝ እዚህ ደረጃ ድረስ እንዲወርድ ያደረገው ምንድነው የሚለው በሚገባ አይታይም፡፡ አሁን ኃላፊነት ላይ ያለን ሰዎች ነን ወይ በዚህ ጉዳይ ላይ መጠየቅ ያለብን?›› ሲሉ ተሳታፊዎችን ጠይቀዋል፡፡
#ሪፖርተር

@ethio_mereja_news
የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ ወለጋ ዞን ወደ ምትገኘው ነቀምቴ ከተማ በሣምንት ሦስት ቀናት በረራ መጀመሩን አስታወቀ።

ከነቀምቴ ከተማ በ35 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ በ1.3 ቢሊዮን ብር የተገነባው የጉዲና ቱምሳ አየር ማረፊያ ዛሬ እሁድ ሲመረቅ ከአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ መስፍን ጣሰው በተጨማሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ ታገሰ ጫፎ፣ የገንዘብ ሚኒስትር ዴኤታ ኢዮብ ተካልኝ እና የትራንስፖርት እና ሎጂስቲክስ ሚኒስትሩ ዓለሙ ስሜ ተገኝተዋል።

@ethio_mereja_news
ደረሰኝ ካልያዙ ንብረቶ ሊወረስ ነው🤔

መንግሥት ባለፈው ሳምንት ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ያቀረበው "የንብረት ማስመለስ" አዋጅ፣ ከውጭ በተላከላቸው ገንዘብ ሃብት ያፈሩ ዜጎች ገንዘቡን የተረከቡበትን ደረሰኝ ለፍርድ ቤት አቅርበው ካላረጋገጡ መንግሥት ንብረታቸው እንዲወረስ ሥልጣን የሚሰጥ እንደኾነ ሪፖርተር ዘግቧል።

ማንኛውም ሰው ሊታወቅ ከሚችል ገቢው በላይ ሃብት አፍርቶ የምንጩን ሕጋዊነት ማረጋገጥ ካልቻለ፣ መንግሥት ንብረቱን የመውረስ ሥልጣን እንዳለው ረቂቅ አዋጁ እንደሚደነግግ ዘገባው አመልክቷል። ዓቃቤ ሕግ ምንጩ አይታወቅም ብሎ ለሚጠረጥረው 5 ሚሊዮን ብር ለሚገመት ንብረት 10 ዓመት ወደኋላ ሂዶ ክስ ማቅረብ እንደሚችልም ረቂቅ አዋጁ ይፈቅዳል ተብሏል።

@ethio_mereja_news
ተፈቱ‼️

ጋዜጠኛ በቃሉ አላምረው፣ በላይ ማናዬ እና ቴዎድሮስ ዘርፉ ከእስር ተፈቱ

ለፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት “አካልን ነጻ የማውጣት” አቤቱታ ያቀረቡት ሶስት ጋዜጠኞች ከእስር ተፈቱ። ዛሬ እና ከትላንት በስቲያ ቅዳሜ ከእስር የተለቀቁት ጋዜጠኞች በቃሉ አላምረው፣ በላይ ማናዬ፣ ቴዎድሮስ ዘርፉ ናቸው።

ሶስቱ ጋዜጠኞች የፌደራል ፖሊስ “ሕገ መንግስታዊ መብታቸውን በመጣስ በእስር እንዲቆዩ” ማድረጉን በመጥቀስ ለፍርድ ቤት አቤቱታ ያቀረቡት ባለፈው ሳምንት ነበር። ከአቤቱታ አቅራቢዎች አንዱ የሆነው ጋዜጠኛ በላይ ከእስር የተፈታው፤ ዛሬ ሰኞ ሰኔ 10፤ 2016 ከሰዓት መሆኑን ባለቤቱ በላይነሽ ንጋቱ ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ተናግራለች።

“ኢትዮ ኒውስ” የተሰኘው የበይነ መረብ መገናኛ ብዙኃን መስራች እና አዘጋጅ የሆነው ጋዜጠኛ በላይ፤ በህዳር 2016 በፖሊስ ቁጥጥር ስር ከዋለው በኋላ ለሰባት ወራት በአዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ በእስር ላይ ቆይቷል። ጋዜጠኛው ባለፈው ግንቦት ወር አዲስ አበባ ወደሚገኘው የፌደራል ፖሊስ የወንጀል ምርመራ ቢሮ መዘዋወሩ ይታወሳል።

አስር ወራትን በአዋሽ አርባ ወታደራዊ ካምፕ በእስር ያሳለፈው ሌላኛው ጋዜጠኛ ቴዎድሮስ፤ ባለፈው አርብ ሰኔ 7፤ 2016 ወደ አዲስ አበባ እንዲመጣ ከተደረገ በኋላ በማግስቱ ከእስር መለቀቁን ለ“ኢትዮጵያ ኢንሳይደር” ገልጿል። “ምኒልክ” እና “ዓባይ”በተሰኙ የበይነ መረብ እና የሳተላይት ቴሌቪዥን ቻናሎች ላይ በፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ያተኮረ ፕሮግራም ያዘጋጅ የነበረው ቴዎድሮስ፤ በፖሊስ ቁጥር ስር የዋለው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ በፓርላማ ከጸደቀ ከአንድ ሳምንት በኋላ ነበር።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በኖኖ ወረዳ በሰርገኞች ላይ በተወረወረ ቦምብ ሙሽሮችን ጨምሮ  ሁሉም ሰርገኛ ህይወት አለፈ‼️

በኦሮሚያ ክልል ፤ በምዕራብ ሸዋ ዞን ፤ ኖኖ ወረዳ ሰርገኞችን ዒላማ ባደረገ ጥቃት ከ20 በላይ ሰዎች መገደላቸውን የአካባቢው ኮማንድ ፖስት እና ነዋሪዎች ገለጹ።

የኖኖ ወረዳ ኮማንድ ፖስት ኃላፊ አቶ ተሾመ ሰቦቃ ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ በሰጡት ቃል ፥ ጥቃቱ ቅዳሜ ሰኔ 8 ንጋት ላይ ነው የተፈጸመው።

ጥቃት አድራሾቹ " ጽንፈኛ የአማራ ታጣቂዎች  ናቸው " ብለዋል።

ኃላፊው " ሰርገኞቹ ቤት ውስጥ እያሉ በር ዘግተውባቸው ቦምብ ወረወሩባቸው። ቤት ውስጥ ከነበሩት አንድም በሕይወት የወጣ የለም። እዚያው ተቃጥለው አልቀዋል "  ሲሉ ሁኔታውን አስረድተዋል።

አንድ የአካባቢው ነዋሪ ታጣቂዎቹ ሰርግ ቤቱ ላይ ከአንድ በላይ ቦምብ ወርውረው ሙሽሮቹን እና አብረዋቸው የነበሩ ሰዎችን መግደላቸውን ተናግረዋል።

የኮማንድ ፖስት ኃላፊን ጨምሮ የአካባቢው ነዋሪዎች በሰጡት ቃል ፥ በሰርግ ቤት ላይ የተነሳውን እሳት ለማጥፋት የመጡ የአካባቢው ነዋሪዎች በታጣቂዎቹ የተኩስ እሩምታ ተከፍቶባቸው በርካታ ሰዎች ተገድለዋል።

የአካባቢው ነዋሪ የሟቾች ቁጥር ከ30 እስከ 50 ሊደርስ እንደሚችል ተናግረዋል።

በጥቃቱ ሙሽሪት እና ሙሽራውን ጨምሮ የሰርጉ ታዳሚዎች የሆኑ ሰዎች በሙሉ ሕይወታቸው ማለፉን ነዋሪው ተናግረዋል።

የወረዳው የኮማንድ ፖስት ኃላፊ አቶ ተሾመ ሰቦቃ ፥ " በእሳት ተቃጥለው የሞቱ ሰዎችን ቁጥር መለየት አስቸጋሪ በመሆኑ ትክክለኛውን የሟቾች ቁጥር መለየት አልተቻለም " ሲሉ ለቢቢሲ ቃላቸውን ሰጥተዋል።

ባለፈው ሚያዚያ ወር ላይ በዚህ ወረዳ በ5 ቀበሌዎች በተፈጸመ ጥቃት 12 ሰዎች መገደላቸውን ፤ ቤቶች መቃጠላቸውን ፣ ከብቶችም እየተነዱ መወሰዳቸውን ነዋሪዎች መግለጻቸው ይታወሳል።

ኢሰመኮም መረጃውን የማጣራት ስራ እየሰራ እንደነበር መግለጹ አይዘነጋም።

ከሟቾች አብዛኛዎቹ የአማራ ብሔር ተወላጆች እንደነበሩ ፤ ጥቃት ፈጻሚዎችም የ " ሸኔ (የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት) ታጣቂዎች " እንደሆኑ ነዋሪዎች መናገራቸው ይታወሳል።

ዘገባው tikvahethiopia ነው።


@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
መንግሥት ያቋቋመው ብሄራዊ ኮሚቴ በሳዑዲ ዓረቢያ ባስቸጋሪ ኹኔታ ላይ የነበሩ 1 ሺህ 172 ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን ወደ አገራቸው እንደመለሰ የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚንስቴር አስታውቋል።

ከተመላሾቹ ስደተኞች መካከል፣ ኹለት ጨቅላ ሕጻናት እና ዕድሜያቸው ከአስራ ስምንት ዓመት በታች የኾኑ 29 ታዳጊዎች እንደሚገኙበት ሚንስቴሩ ገልጧል።

ብሄራዊ ኮሚቴው ከሚያዚያ 4 ጀምሮ እስከ ትናንት ድረስ ከ45 ሺህ በላይ ኢትዮጵያዊያን ፍልሰተኞችን መመለስ ችሏል።

@ethio_mereja_news
16 የፌደራሉ መንግስት መስሪያ ቤቶች በስራ ገበታቸው ለሌሉና ለተሰናበቱ ሰራተኞች ግማሽ ሚሊዮን ብር ገደማ ክፍያ ከህግ ውጪ መፈፃማቸውን ዋና ኦዲተር አጋለጠ‼️

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከደንብና መመሪያ ውጪ 3 ሚሊዮን ብር ክፍያ በመፈጸም በቀዳሚነት ሲቀመጥ የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር በሁለተኛነት ይከተላል፡፡
ይህ የተነገረው የፌደራል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት የ2015 በጀት ዓመት የፌደራል መንግስት መስሪያ ቤቶች የፋይናንስ ህጋዊነት ኦዲት እና የክዋኔ ኦዲት ሪፖርትን በዛሬው ዕለት ለህዝብ አንደራሴዎች ምክር ቤት ባቀረበበት ወቅት ነው፡

ዋና አዲተር መሠረት ዳምጤ በንባብ ባቀረቡት በዚህ ሪፖርት 30 የፌደራል መንግስት መስሪያ ቤቶች 16 ሚሊዮን 470ሺህ ብር ከደንብና መመሪያ ውጪ አላግባብ መክፈላቸውን አረጋግጠዋል፡፡

ከእነዚህ ከህግ ውጪ ክፍያ ከፈጸሙ የመንግስት መስሪያ ቤቶች መካከል በአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ሊቀመንበር በለጠ ሞላ(ዶ/ር) የሚመራው የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር 3 ሚሊዮን ብር ከደንብና መመሪያ ውጪ በመፈጸም በቀዳሚነት ተቀምጧል፡፡

በለገሠ ቱሉ (ዶ/ር) የሚመራው የመንግስት ኮሚኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስቴር ደግሞ  ብር 2 ሚሊዮን 889ሺህ ክፍያዎችን አላግባብ ከደንብና መመሪያ ውጪ መፈጸማቸውን በኦዲት መረጋገጡን ዋና ኦዲተሯ ለአንደራሴዎቹ አስረድተዋል፡፡ ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርስቲ፣ የመደ ወላቡ ዩኒቨርሰቲዎች ከህግ ውጪ ክፍያዎችን ከፈጸሙ ተቋማት መካከል ዋናኞቹ መሆናቸው ተመላክቷል፡፡

ዋና ኦዲተሯ ይህን ከደንብና መመሪያ ውጪ የተፈጸሙ ክፍያዎችን ከዘረዘሩ በኋላ ተቋማቱ ደንብና መመሪያ ተከትለው ክፍያ እንዲፈጽሙ፣ አላግባብ የከፈሉትንም ተመላሽ እንዲያደርጉ አሳስበዋል፡፡

በዋና ኦዲተሯ በኩል የቀረበው ሌላው የኦዲት ክዋኔ ሪፖርት በመስሪያ ቤቱ ውስጥ ለሌሉ እና ለተሰናበቱ ሰዎች የተከፈሉ ክፍያዎችን ይመለከታል፡፡ በዚህም በ16 መስሪያ ቤቶች በስራ ላይ ለሌሉና ለተሰናበቱ ሰራተኞች ከ485ሺህ ብር በላይ አላግባብ ክፍያ መፈጸሙ ተረጋግጧል፡፡

እንደ ሪፖርቱ ከሆነ በ2014 እና ከዚያ በፊት 92 መስሪያ ቤቶች ተመላሽ እንዲደርጉ በሚል አስተያየት ከተሰጠበት 443 ሚሊዮን ብር፣ ከ23 ሺህ ዶላር በላይ ገንዘብ ተመላሽ የሆነው 11 በመቶ ብቻ ወይም 48.2 ሚሊዮን ያህል መሆኑን መሠረት ዳምጤ በሪፖርታቸው አቅርበዋል፡፡
ይህም ማለት 89 በመቶ ወይም 394.8 ሚሊዮን ብሩ ተመላሽ አልተደረገም፡፡(አሻም)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በሰሜን ሸዋ ዞን ደራ ወረዳ ታጣቂዎች በፈጸሙት ጥቃት አራት ሰዎች ተገደሉ፣ የአከባቢው ባለስልጣናት እና ነዋሪዎች “የፋኖ ታጣቂዎችን” ተጠያቂ አድርገዋል!

ስለጥቃቱ አዲስ ስታንዳርድ የጠየቃቸው #የጨካ ከተማ ከንቲባ ሁኔታውን ሲያስረዱ ግጭቱ የተፈጠረው “በጽንፈኛው የፋኖ ሀይሎች” እና በኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ሸኔ) መካከል መሆኑን ጠቁመው የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ሸኔ) ሀይሎች የፋኖ ሀይሎችን ከከተማዋ በማስወጣት ተቆጣጥረዋት ነበር ብለዋል።

እንደ ከንቲባው ገለጻ ከሆነ የፋኖ ሀይሎች በተደጋጋሚ ይህንን ለመበቀል ወደ ከተማዋ በመዝለቅ በንጹሃን ላይ ጥቃት ይፈጽማሉ ብለዋል።

“የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊት (ሸኔ) ታጣቂዎች በከተማዋ የገበያ ቦታ ላይ በቅርቡ በፈጸሙት ጥቃት የሶስት ሰዎች ህይወት ማለፉን እና በርካቶች መቁሰላቸውንም” ገልጸዋል።

በአከባቢው ያለው የጸጥታ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ ነው ሲሉ ጠቁመዋል። በዚህም ሳቢያ የመንግስት የጸጥታ ሀይሎች አከባቢውን ለማረጋጋት መግባታቸውን አስታውቀዋል፤ አከባቢው በጣም ሰፊ በመሆኑ እና በረሃማ አየር ጸባይ ስላለው የጸጥታ ቁጥጥሩን አስቸጋሪ አድርጎታል ሲሉም ገልጸዋል።

የኦሮሞ ነጻነት ሰራዊትን (ሸኔን) እንቅስቃሴ ለመቆጣጠር ጥረት ሲደረግ የፋና ሀይሎች በሌላ አቅጣጫ ጥቃት እንደሚከፍት ጠቁመዋል፤ ይህም በወረዳዋ የጸጥታ እና መረጋጋት ስራውን እንዳወሳሰበት አስታውቀዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
💥💥 የዋጋ ግሽበት ከመቼውም በላይ እየጨመረ ይገኛል

👉ብልህ ሰዉ ነገዉን ዛሬ ይወስናል !!ይፍጠኑ !!
DMC Real Estate Plc
በለቡ መብራት 65,395ካሬ ላይ ያረፈ ሰፊ እና እጅግ ዉብ መንደር

ቻድ ኢንባሲ እና CDC በቅርብ ርቀት ላይ ይገኛል !
👉በምቹ አከፋፈል 10%  560.ሺ ቅድመ ክፋያ ጀምሮ
👉የንግድ ሱቆች G.floor -2rd floor ከ 24 ካሬ ጀምሮ
👉ከstudio 56ካሬ እስከ 4መኝታ 186ካሬ .በተለያየ የካሬ አማራጭ

👉በሚገርም ወብ Design የቀረበ
👌በዘመነ ፈጣን በተቀላጠፈ ቴክኖሎጂ አልሙንየም ፎርም ወርክ የሚሰራ

😄❗️ሰበር ዜና
❗️ዛሬ አዳዲስ 2ኛ floor ጀምሮ ዝቅተኛቤት floor ጥቂት ቤቶች  አዉተናል ይፋጠኑ,ይምረጡ  !!
🌀 ብርዎትን አሰሩት፤ በኢትዮጵያ ትልቁ አዋጭ የሆነው የሪል እስቴት ቢዝነስ ነው፡፡

ዲኤም ሲ ሪል እስቴት/Dmc Real Estate

ለበለጠ መረጃ /ለሳይት ጉብኝት
ይጀዉሉልን!
☎️ 0961478081
በትግራይ ክልል ከ122 ሺህ በላይ ተማሪዎች የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና እየወሰዱ ነው‼️


በትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር የትምህርት ጥራት ማረጋገጫ ኤጀንሲ ዳይሬክተር ዶክተር ታደሰ ካህሳይ እንደገለጹት፤ የስምንተኛ ክፍል ክልላዊ ፈተናው እየተሰጠ ያለው በ1ሺህ 129 ትምህርት ቤቶች ነው።

ፈተናው ዛሬን ጨምሮ ለተከታታይ ሦስት ቀናት እንደሚሰጥም ተናግረዋል።

እንደ ዳይሬክተሩ ገለጻ፣ ከተፈታኞች መካከል 62 ሺህ 732 የሚሆኑት ሴት ተማሪዎች ናቸው።

ተማሪዎቹ ፈተናውን በተረጋጋ ሁኔታ እንዲወስዱ አስቀድሞ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራ መሰራቱን ተናግረዋል።

የፈተና ኩረጃን ለመከላከል ተቆጣጣሪዎች በበቂ ሁኔታ መመደባቸውን ጠቁመው፣ ለፈተናው ሰላማዊነትም የጸጥታ አካላት የበኩላቸውን እየተወጡ መሆኑን መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጥቆማ‼️

በቴሌግራም ገንዘብ መስራት ይቻላል ለሱም ምስክር NOTCOIN መመልከት በቂ ነው።

በኦንላይን ገንዘብ መስራት ከፈለጋቹ አሁንኑ ይህንን ቻናል መቀላቀል ግድ ነው👇👇
http://www.tg-me.com/sheger_crypto
http://www.tg-me.com/sheger_crypto
ሂውማን ራይትስ ዎች፣ አምነስቲ ኢንተርናሽናል እና ሌሎች ሦስት የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች፣ የኢትዮጵያ መንግሥት ባለሥልጣን በሰብዓዊ መብት ድርጅቶችና ጋዜጠኞች ላይ የሚያደርጉትን አፈና እንዲያቆሙ በጋራ ባወጡት መግለጫ ጠይቀዋል።

ድርጅቶቹ፣ በአገር በቀል የሰብዓዊ መብት ድርጅቶች ላይ የሚፈጸመው ማስፈራሪያና ዛቻ የሰብዓዊ ድርጅቶቹ ሥራቸውን ባግባቡ እንዳይሠሩ አድርጓል ብለዋል።

የመንግሥት የጸጥታና ደኅንነት ኃይሎች ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ካውንስል (ኢሰመጉ) እና ሌሎች የሲቪክ ድርጅቶችና ጋዜጠኞች ላይ የሚፈጽሙት ማስፈራሪያ እና ዛቻ መጨመሩን ድርጅቶቹ በመግለጫቸው አውስተዋል።

የኢትዮጵያ ዓለማቀፍና አሕጉራዊ አጋሮች፣ የኢትዮጵያ መንግሥት የፖለቲካ ተቀናቃኞቹን፣ የጋዜጠኞችን፣ የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾችን መብት እንዲያከብር ግፊት እንዲያደርጉና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የሰብዓዊ መብቶች ምክር ቤትም ክትትል እንዲያደርጉ ድርጅቶቹ ጠይቀዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Good News‼️

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት የመቐለ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት አገልግሎት መስጠት መጀመሩ ተገልጿል።

ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ አገልግሎት መስጠት የጀመረው ዛሬ ነው።

በዚህም በጊዜያዊነት የጀመራቸው አገልግሎቶች ፦
☑️ ፓስፖርት ማደስ፣
☑️ የጠፋ ፓስፖርት መተካት፣
የተበላሸ  ወይ እርማት የመስጠት አገልግሎቶች እንደሆነም ተገልጿል።

የመቐለ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ፅህፈት ቤት ተወካይ ክንፈሚካኤል ረዳሀኝ ዛሬ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ በሰጡት ቃል ከጦርነቱ በፊት በፅህፈት ቤቱ በርካታ አገልግሎት ሲሰጥ እንደነበር አመልክተዋል።

በጦርነቱ ሁሉም አገልግሎት ተቋርጦ እንደነበር አስታውሰዋል።

ከፕሪቶሪያ ሰላም ስምምነት በኃላ ቢዘገይም የፓስፓርት እድሳት አገልግሎት አሁም መሰጠት እንደተጀመረ ገልጸው ፤ “ በመላ ትግራይ የሚገኙ የፓስፓርት እድሳት ፈላጊዎች በአካል መምጣት ሳይስፈልጋቸው ባሉበት ሆኖው በኦንላይን መገለግል ይችላሉ “ ብለዋል።

ተገልጋዮች ወደ (መቐለ) ፅ/ቤቱ መምጣት ያለባቸው ሁሉም ነገር ጨርሰው ማህተም ለማስመታት ብቻ እንደሆነ ጠቁመዋል

@sheger_press
@sheger_press
የአዲስ አበባ ሰፈሮች ስያሜ እና ትርጉም

1)ዶሮ ማነቂያ
ይህ ሰፈር በድሮ ጊዜ ወንጀለኞች በስቅላት ይቀጡበት የነበረ ዛፍ ይገኝበት ነበር።በጊዜ ብዛት ቦታው ላይ የስቅላት ቅጣት መፈጸም ቀረ፣ ስዎችም ሰፈሩን ድሮ ማነቂያ እያሉ ይጠሩት ጀመር።በጊዜ ብዛት ድሮ ማነቂያ ወደ ዶሮ ማነቂያ ተለውጦ ቋሚ መጠሪያው ሆነ።

2)በቅሎ ቤት
በአፄ ሀይለስላሴ ዘመነ መንግስት መድፈኛ ጦር መቀመጫው ላንቻ አከባቢ የነበረ ሲሆን በወቅቱ መድፎችን ወደ ሌላ ቦታ መውሰድ ሲፈለግ ተፈታተው በበቅሎ ይጫኑ ነበር።በዚህ ምክንያት በመድፈኛ ጦር ሰፈር ውስጥ ለማጓጓዣነት የሚጠቅሙ ከመቶ ያላነሱ በቅሎዎች ነበሩ።በአከባቢው በርካታ በቅሎዎች ስለነበሩ ሰፈሩ "በቅሎ ሰፈር" እየቆየ ሲሄድ ደሞ "በቅሎ ቤት" እየተባለ መጠራት ጀመረ።

3) ሠራተኛ ሰፈር
በአፄ ምኒልክ ቤተ-መንግስት ውስጥ በዕደ-ጥበባት ሙያ በተሰማሩ ሰራተኞች በመመስረቱ ሰራተኛ ሰፈር ተብሏል።

4)ሰባራ ባቡር
ይህ ሰፈር ስያሜውን ያገኘው ሙሴ ሰርኪስ ተርዚያን በተባሉ አርመናዊ ነጋዴ አማካኝነት ከውጭ ሀገር መጥቶ አሁን ስያሜውን ባገኘበት ቦታ ተበላሽቶ በቀረው የመንገድ መስሪያ ተሽከርካሪ (ሮለር) ምክንያት ነው።

5) አራት ኪሎ
ይህን ስያሜ ሊያገኝ የቻለው አራት መንገዶች የሚገናኙበት ቦታ ስለነበረ ነው።

6)ተረት ሰፈር
ተረት ሰፈር ስያሜውን ያገኘው በአዲስ አበባ ከተከፈቱት የመጀመሪያዎቹ ሆቴሎች አንዱ በነበረው ሆቴል ዳፍራንስ ባለቤት በሆኑት ፈረንሳያዊ ሙሴ ቴረስ ስም ነው።

7) ጎፋ ሰፈር
በቀዳማዊ ሀይለስላሴ ዘመን ለማይጨው ጦርነት ከጋሞ ጎፋ አከባቢ ለመጡና በጦርነቱ ወቅት ከፍተኛ ትግል ላደረጉ አርበኞች የተሰጠ ቦታ በመሆኑ መጠሪያው ጎፋ ሰፈር ተብሏል።

8)ጠመንጃ ያዥ
ሰፈሩ አራተኛ ክፍለ ጦር አከባቢ ይገኛል።ጠመንጃ ያዥ የተባለበት ምክንያት ከጣልያን ወረራ በፊት የቤተ መንግስት ጠባቂዎች በብዛት ይኖሩበት ስለነበረ ነው።

9) ፖፖላሬ
በጣልያን ወረራ ወቅት ተራው ጣልያናዊ ሰራተኛ የሰፈረበት ሰፈር ነበር።ስያሜው ፖፖሎ ከሚለውና ሕዝብ የሚል ትርጉም ካለው የጣልያን ቃል የተወሰደ ነው።

10) ሸጎሌ-
ሼህ ኦጀሌ የቤንሻንጉል ጉሙዝን አከባቢ ሲያስተዳድሩ የነበሩ የበርታ ብሄረሰብ ተወላጅ ነበሩ።እኝህ ሰው ከአፄ ምኒልክ ዘመን ጀምሮ ለማዕከላዊው መንግስት ታማኝ ሆነው አከባቢውን ከጠላት ወረራ ሲከላከሉ ኖረዋል።በዚህም የተነሳ ጉለሌ ክፍለ ከተማ ውስጥ በተለምዶ ሸጎሌ የሚባለው አከባቢ ቤተ-መንግስት አላቸው።በዚህም ምክንያት ሰፈሩ በስማቸው ሼህ ኦጀሌ ተባለ፤ በጊዜ ብዛትም ወደ ሸጎሌ ሊለወጥ ችሏል።

ምንጭ፦ አዲስ አበባ መፅሄት እና አዲስ አድማስ ጋዜጣ፣ ኢንጂነር እሸቴ ; ዋሱ

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ኢትዮጵያ ውስጥ በቅድመ መደበኛ፣ በመጀመሪያ እና 2ኛ ደረጃ ላይ ያሉ17 ሚሊዮን የሚጠጉ ሕፃናት ከትምህርት ውጪ መሆናቸውን ዩኒሴቭ (UNICEF) አስታወቀ።

ዩኒሴፍ 3.5 ሚሊዮን የሚገመቱ በአንደኛ ደረጃና በሁለተኛ ደረጃ የሚገኙ ሕፃናት ትምህርታቸውን ለማቋረጥ ሥጋት መጋለጣቸውንና ይህም ትምህርት ላይ የተጋረጠውን ቀውስ የበለጠ ማባባሱን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ሥርዓተ ትምህርት "ችግር ፈቺ ያልሆነ፣ የሀገሪቱን ኑሮ እና ተጨባጭ ጉዳዮች የማይመለከት መሆኑ" በውጤትም ሆነ በጥራት ማሽቆልቆል እየታየበት መሆኑን አንድ የትምህርት ባለሙያ ተናግረዋል።

በጦርነትና ግጭት ክፉኛ እየተጎዳ ያለው የኢትዮጵያ የትምህርት ሁኔታ፤ ከዚያም ያለፉት የመንግሥት ሠራተኞች በደሞዝ ማነስ እየተፈተኑ ለትምህርት የሚሰጠውን ዋጋ እየጌዳ ስለመሆኑ ይነገራል።

ትምህርት ሚኒስቴር ኢትዮጵያ ውስጥ ከጠቅላላ ትምህርት ሰጪ 47 ሺህ ገደማ ትምህርት ቤቶች ደረጃቸው የላቁት አራት ናቸው ማለቱ ባለፈው ዓመት የተሰማ አስደንጋጭ እውነታ ሆኖ አልፏል።

በኢትዮጵያ ውስጥ ለሁሉም ሕፃናት ትምህርትን ለማረጋገጥ ጥረቶችን እንደሚመራ ያስታወቀው የመንግሥታቱ ድርጅት የሕፃናት መርጃ ማዕከል ትናንት ባወጣው መረጃ ደግሞ 17 ሚሊዮን የሚጠጉ ኢትዮጵያዊያንሕፃናትና ታዳጊ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታ ውጪ ናቸው።

Via:- Ethio FM
@sheger_press
@sheger_press
- በኦሮምያ ክልል ምስራቅ ሐረርጌ ስድስት ወረዳዎች የከፋ ድርቅ ተከስቷል። ነዋሪዎች ለዋዜማ እንደነገሩት ላለፉት ሰላሳ ዓመታት ድርቅ ይከሰታል በሚል በመንግስትና በረድዔት ድርጅቶች በኩል የነፍስ አድን አቅርቦት አስቀድሞ ይዘጋጅና በአካባቢው ይከማች ነበር። አሁን ግን ለአደጋው ተገቢ ትኩረት እንኳን አልተሰጠውም ብለዋል።

- በዋግ ኽምራ ብሔረሰብ አስተዳደር ዞን በሰሀላ ሰየምት ወረዳ በ2015/16 የምርት ዘመን የተከሠተው ድርቅ ያስከተለው ረኀብ ጉዳቱ በመባባሱ፣ ባለፈው ሳምንት በቢላዛ ቀበሌ የሁለት ሰዎች ሕይወት ማለፉን የቀበሌው አስተዳደር አስታውቋል፡፡

- የዓለም የምግብ ፕሮግራም በኢትዮጵያ 15.8 ሚልየን የምግብ እርዳታ የሚያስፈጋቸው ሰዎች መኖራቸውን አስታውቆ በጦርነት፣ በድርቅ እና በጎርፍ አደጋ ሳቢያ የተፈጠረው ቀውስ በአብዛኛው በአማራ፣ ኦሮሚያ እና ትግራይ ክልሎች ውስጥ እንደሆነ ገልጿል። በተጨማሪም አገሪቱ ከደቡብ ሱዳን፣ ሶማሊያ፣ ኤርትራ እና ሱዳን የተፈናቀሉ 1 ሚልየን ስድተኞችን እያስተናገደች የሚገኝ ሲሆን ከሱዳን አሁንም ስደት የቀጠለ መሆኑ ተመላክቷል።

Photo: UNOCHA

Via VOA/AS/AM

@sheger_press
@sheger_press
የሟቾች ቁጥር ወደ 550 ማደጉ ተሰማ

አመታዊውን የሀጂ ስነስርአት ለመካፈል ወደ ሳኡዲ ካቀኑ ሰዎች መካከል ከ550 በላይ ሰዎች በሙቀት መሞታቸው ተሰምቷል፡፡

ከከፍተኛ የሙቀት መዕበል ጋር በተያየዘ በሚፈጠሩ በሽታዎች ነው ሃጃጆቹ ህይወታቸው ያለፈው፡፡ ከሟቾቹ መካከል 323 የግብጽ ፣ 144 የኢንዶኔዢያ፣ 35 የቱኒዝያ ፣ 11 የኢራን ፣ 6 የሴኔጋል ዜግነት ያላቸው ሃጃጆች ናቸው ተብሏል፡፡

የሟች ቤተሰቦች በአሁኑ ወቅት በተለያዩ የሳኡዲ ሆስፒታሎች ዘመዶቻቸውን በማፈላለግ ላይ ሲሆኑ ዮርዳኖስ በበኩሏ በሃጂ የሞቱ ዜጎቿን ለመቀበር 41 የመቃብር ስፍራዎችን ማዘጋጀቷን በትላንትናው እለት አስታውቃለች፡፡

የዘንድሮው የሀጂ ስነስርአት ከ1.8 ሚሊዮን በላይ የእስልምና እምነት ተከታዮች የተካፈሉበት ሲሆን ከሰሞኑ በተለያዩ የአለም ክፍላት በተደጋጋሚ የተፈጠረው የሙቀት ማዕበል በሳኡዲም ለሃጃጆች ፈታኝ እንደሚሆን ሲነገር ሰንብቷል፡፡

የሳኡዲ የጤና ሚንስቴር ከሟቾቹ መካከል አብዛኛዎቹ አድሜያቸው የገፋ እና የጤና እክል የነበረባቸው ሃጃጆች መሆናቸውን ገልጾ ከሙቀት ማእበሉ ጋር በተገናኝ የታመሙ 2700 ሃጃጆች የጤና ክትትል እየተደረጋላቸው እንደሚገኙ አስታውቋል፡፡

ሚንስቴሩ ሀጃጆች በሚንቀሳቀሱበት ስፍራ ጃንጥላ እንዳይለያቸው እንዲሁም ከፍተኛ ሙቀት በሚኖርበት ከረፋዱ 5 - እስከ 9 ሰአት ድረስ በቤት ውስጥ እንዲቀመጡ ማስጠንቀቂያዎችን ሲያስነግር መሰንበቱን ነው የተናገረው፡፡

በባለፈው አመት ከሙቀት ጋር በተያያዘ እና በተለያዩ ችግሮች ከ240 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ማለፉ ይታወሳል፡፡

በተጨማሪም በ2015 በተፈጠረ ከፍተኛ መጨናነቅ ከ2000 በላይ ሰዎች ህይወታቸው ሲያልፍ ከ400 በላይ የሚሆኑት ደግሞ የደረሱበት መጥፋቱ ተነግሮ ነበር፡፡

Via:ዐል ዐይን

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
#Amahra

በአማራ ክልል ፤ በምዕራብ ጎንደር ዞን ' ታጣቂዎች ' ባደረሱት ጥቃት አንዲት ሱዳናዊ ስደተኛን ጨምሮ 3 ሰዎች መገደላቸው ተነግሯል።

በጥቃቱ በሌሎች ሁለት ሰዎች ላይ ጉዳት መድረሱ ተሰምቷል።

የስደተኞች እና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት የጥቃቱ ባለፈው እሁድ ሰኔ 9/2016 መፈጸሙን አረጋግጧል።

ጥቃት የተፈጸመው ከገንደ ዉሃ ወደ ነጋዴ ባህር ሲጓዝ በነበረ የህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ " ደረቅ አባይ " በተባለ ስፍራ እንደሆነ ተጠቁሟል።

የዞኑ ኮሚኒኬሽን ጥቃቱ ከቀኑ 10 ሰዓት መድረሱን አሳውቋል።

የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች አገልግሎት ፥ በህዝብ ማመላለሻ ተሽከርካሪ ላይ ታጣቂዎች ተኩስ ከከፈቱ በኃላ አንድ ውስጥ የነበረ የመንግስት የጸጥታ አባል ወርዶ የታጣቂዎቹ ጥቃት ለመከላከል ባደረገው የተኩስ ልውውጥ ከመኪናው ውስጥ የነበረች አንዲት ሱዳናዊ ስደተኛና ሌሎች ኢትዮጵያውያን መገደላቸውን አስረድቷል።

" የጥቃቱን መድረስ ተከትሎ የመንግስት ጸጥታ ኃይል በአፋጣኝ ባይደርሱ ኖሩ ከአሁኑ የበለጠ የከፋ ጉዳት ሊከሰት ይችል ነበር " ሲልም ገልጿል።

የተፈጸመው ጥቃት በዘፈቀደ እንጂ በስደተኛዋ ላይ ያነጣጠረ እንዳልነበር አክሏል።

ስደተኛዋ በወቅቱ ፤ መድሃኒት ገዝታ ወደ መጠለያዋ እየተመለሰች ነበር ተብሏል።

የምዕራብ ጎንደር ዞን አስተዳደር ስደተኞች ከመጠለያ ጣቢያቸው እንዳይወጡ በተደጋጋሚ ቢነገራቸውም አንዳንዶቹ ተግባራዊ ማድረግ ባለመቻላቸው  ለአደጋ እየተጋለጡ ሲል ገልጿል።

የመረጃው የዶቼቨለ ሬድዮ ነው።

@ethio_mereja_news
NewsALert‼️

በአማራ ክልል ሰሜን ሸዋ ዞን የፋኖ ታጣቂዎች በተቆጣጠሯቸውና ወጣ ገባ በሚሉባቸው ወረዳዎች የባንክ አገልግሎት እንዲቋረጥ መደረጉን ዋዜማ ተረድታለች፡፡

በዞኑ የባንክ አገልግሎት ከተቋረጠባቸው ወረዳዎች መካከል መንዝ ላሎ፣ ግሼ ራቤል፣ አንፆኪያ ገምዛና ቀወት እንደሚገኙበት ዋዜማ በየወረዳዎቹ የባንክ ቅርንጫፎች አረጋግጣለች፡፡ የባንክ አገልግሎቱን በተጠቀሱት ወረዳዎች እንዲያቋርጡ የተገደዱት የግል ባንኮች ጭምር መሆናቸውን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

በተጠቀሱት ወረዳዎች የባንክ አገልግሎት የተቋረጠው ካለፈው አርብ ሰኔ 7/2016 ዓ.ም ጀምሮ መሆኑን ዋዜማ ተረድታለች፡፡

ከአርብ ጀምሮ ይህ ዘገባ እስከተጠናቀረበት ስዓት ድረስ በመንዝ ላሎ ወረዳ ወገሬ ከተማ፣ በግሼ ራቤል ወረዳ ራቤል ከተማ፣ በአንፆኪያ ገምዛ ወረዳ መኮይ ከተማና ቀወት ወረዳ ራሳ ከተማ ባንኮች እንደተዘጉ ናቸው፡፡

በአንጻሩ የአንጾኪያ ገምዛ ወረዳ አካል በሆነችው ማጀቴ ከተማ ባንኮች አገለግሎት መስጠት መቀጠላቸውን ዋዜማ ከከተማዋ ነዋሪዎች ሰምታለች፡፡ ምንም እንኳን በከተማዋ አገልግሎት ባይቋረጥም ባንኮች ለደንበኞቻቸው የሚሰጡት ወጪ ገደብ ተጥሎበታል ተብሏል፡፡ 

አገልግሎቱ የተቋረጠው ባንኮቹ ድንገተኛ ትዕዛዝ ከመንግሥት አካል ከደረሳቸው በኋላ መሆኑን፣ የየወረዳዎቹ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክና የግል ባንኮች ሰራተኞች ለዋዜማ ተናግረዋል፡፡ ድንገተኛ የተባለው ትዕዛዝ ለባንኮቹ የተላለፈው የሸዋ ቀጠናን ከሚመራው ኮማንድ ፖስት መሆኑን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡

(Wazema)

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
እነ አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ በ50 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲፈቱ ፍርድ ቤት ፈቀደ                                            

ሕገ መንግሥታዊ ሥርዓትን በትጥቅ ትግል ለመቀየር” በመንቀሳቀስ የተጠረጠሩት አርቲስት አማኑኤል ሀብታሙ፣ የቴአትር አዘጋጅ ዳግማዊ ፈይሳ እና ፍላጎት አብርሃምን ጨምሮ 17 ግለሰቦች እያንዳንዳቸው በ50 ሺህ ብር ዋስትና ከእስር እንዲለቀቁ ፍርድ ቤት ፈቀደ።

በዚሁ መዝገብ ተጠርጥረው የቀረቡት ሌሎች ሶስት ግለሰቦች በአንጻሩ 11 ተጨማሪ የምርመራ ቀናት ተፈቅዶባቸዋል።

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ የጊዜ ቀጠሮ ችሎት ይህንን ብያኔ ያስተላለፈው ዛሬ ሐሙስ ሰኔ 13/2016 ዓ.ም. ረፋድ ላይ በነበረው የችሎት ውሎ ነው።

ችሎቱ ዛሬ የተሰየመው ከትናንት በስቲያ ማክሰኞ ዕለት በነበረው የፍርድ ቤት ውሎ ግራ ቀኙ ያቀረቧቸው ጥያቄዎችን መርምሮ ብይን ለመስጠት ነበር።

በማክሰኞ ዕለቱ የችሎት ውሎ መርማሪ ፖሊስ ሀያዎቹ ተጠርጣሪዎች ላይ ተጨማሪ የምርመራ ቀናት እንዲፈቀድለት ሲጠይቅ ጠበቆች በአንጻሩ የዋስትና መብት እንዲከበር ጠይቀው እንደነበር ጠበቃ አያሌው ቢታኔ ለቢቢሲ ተናግረዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/07/01 04:52:01
Back to Top
HTML Embed Code: