Telegram Web Link
የአገራዊ የምክክር ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ትናንት ያቀረበችበትን ቅሬታ ተከትሎ ከቤተክርስቲያኗ ቅዱስ ሲኖዱስ ጋር ለመወያየት ዝግጁ መኾኑን አስታውቋል።

ኮሚሽኑ፣ የአካታችነት መርሁ ከኹሉም የኃይማኖት ተቋማት ጋር "በእኩልነት የሚተገበር" መኾኑን  ገልጧል።

ቅዱስ ሲኖዶሱ፣ አገራዊ የምክክር ኮሚሽኑ ቤተክርስቲያኗ በምክክር ተሳታፊዎች እና አጀንዳ ልየታ ሂደቱ እንድትሳተፍ ጥሪ ሳያደርግ መቅረቱ ቅሬታ እንደፈጠረበት ትናንት ባወጣው መግለጫ ገልጦ ነበር።

ኮሚሽኑ ግን፣ ከጅምሩ በምክክር ሂደቱ አብሮ ለመስራት የመግባቢያ ሠነድ የተፈራረመው ከኢትዮጵያ የሃይማኖት ተቋማት ጉባዔ ጋር እንደኾነ ጠቅሷል፡፡

ጉባዔው፣ በተሳታፊዎች ልየታ እና በአዲስ አበባ አጀንዳ የማሰባሰብ ሂደት "ከፍተኛ አስተዋጽኦ" ማድረጉንም ኮሚሽኑ ጠቅሷል።

@ethio_mereja_news
የአክሱም አየር ማረፊያ ዛሬ አገልግሎት መስጠት ጀመረ‼️ 

በጦርነቱ ወቅት የህወሓት ሃይሎች ከጥቅም ውጪ አድርገውት የቆየው የአክሱም አየር ማረፊያ ፤ ከሶስት አመት ቦኃላ በፌደራል መንግስት ተጠግኖ በዛሬው ዕለት ሰኔ 1 /2016 ዓ.ም አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

@ethio_mereja_news
#Notcoin

❤️Telegram wallet verify ማድረግ ያልቻላችሁ ወይም tonkeeper ላይ notcoin ያላችሁ መሸጥ የምትፈልጉ

😄 በዚህ አናግሩን 👉 @Birukepromo

❤️ልብ ይበሉ

በእነዚህ user name መጥታችሁ ስትገበያዩ ገንዘባችሁ 100% ይሰጣችኋል (ሀላፊነቱን @sheger_press ይወስዳል)

ክፍያው እንደ ስምምነታችሁ ይፈፀማል

በእነዚህ ሰዎች ለመገበያየት ስትሄዱ ያላችሁ ስክሪንሽት አድርጋችሁ ማሳየት ግድ ነው

ton space ቤታ ከሆነ ኮይናችሁ ደግሞ 0.2 ክፍያ ስለሚጠይቅ ቶን ኮይን ከሌላችሁ ቅድሚያ ከፍላችሁ መውሰድ

notcoinu ልካችሁ ስትጨርሱ አድሚኑ በተስማማቹበት ዋጋ ብራችሁ መልሶ ያስገባል!!


🚫ለማጭበርበር የምትመጡ ካላችሁ ወዲያው Block ሰለምናረጋችሁ አትልፉ እንዳመጡ!!

ሲቀጥል የማትሸጡ አትምጡ ጊዜያችን አታቃጥሉ

ለተለያዩ ONLINE ስራዎች ለመስራት ይህን ቻናል ይቀላቀሉ👇👇
https://www.tg-me.com/sheger_crypto
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ዛሬ የመኖሪያ ቤት የአከራይና ተከራይ የውል ስምምነት ምዝገባ ማካሄድ ጀምሯል።

የከተማዋ የቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ አከራዮችንና ተከራዮችን የውል ምዝገባ በኹሉም ክፍለ ከተሞች የጀመረው፣ የከተማዋ አስተዳደር ያወጣውን የመኖሪያ ቤቶች ኪራይ ቁጥጥርና አስተዳደር አዋጅ ተግባራዊ ለማድረግ ነው።

አዋጁ፣ የመኖሪያ ቤት አከራዮች አስተዳደሩ በዓመት አንድ ጊዜ ከሚወስነው የኪራይ ጣሪያ በላይ ኪራይ ከመጨመርና ተከራዮችን በግዳጅ ከማስወጣት የሚከለክል ነው።

አስተዳደሩ አዋጁን ያወጣው፣ ተከራዮች በአገሪቱ የተከሰተውን የኑሮ ውድነት መቋቋም እንዲችሉ አስተዋጽኦ ያደርጋል በሚል እምነት እንደኾነ መግለጡ ይታወሳል።

@ethio_mereja_news
ባለፈው ረቡዕ ታጣቂዎች በኦሮሚያው ሆሮ ጉደሩ ወለጋ ዞን አሙሩ ወረዳ በፈጸሙት ጥቃት ሦስት ሰዎች እንደተገደሉ ዴይቸቨለ ዘግቧል።

በሞተር ሳይክል በመጓዝ ላይ በነበሩ ሰዎች ላይ በተፈጸመው ጥቃት ከተገደሉት ሰዎች መካከል፣ አንድ መምህር እንደሚገኝበት ዘገባው አመልክቷል።

ጥቃቱን ያደረሱት፣ በዞኑ ኡሙሩ ወረዳ እና በአጎራባቹ የምሥራቅ ወለጋ ዞኑ ኪረሙ ወረዳ አዋሳኝ አካባቢዎች የሚንቀሳቀሱ ታጣቂዎች እንደኾኑ የወረዳው አስተዳደር ሃላፊዎች መናገራቸውን ዜና ምንጩ ጠቅሷል።

በኡሙሩ ወረዳ የኦነግ ሸኔ ታጣቂዎች በተለይ ባለፉት ሦስት ዓመታት በፈጽሟቸው ማንነትን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች ሳቢያ ከ40 ሺህ በላይ ሰላማዊ ሰዎች ተፈናቅለውበት የነበረ አካባቢ ነው።

@ethio_mereja_news
ከሃምሳ አመታት ጥረት በኋላ የወንዶች እርግዝና መከላከያ መድሃኒት በቅርቡ መመረት ይጀምራል ተባለ፡፡

የወንዶች እርግዝና መከላከያ መድሃኒትን ለማምረት ላለፉት 50 ዓመታ የተለያዩ ጥረቶች ሲደረጉ ቆይተዋል፡፡

ይሁንና እስካሁን ድረስ አንድም የወንዶች እርግዝና መድሃኒት ማምረት ያልተቻለ ሲሆን የተደረጉ ጥረቶች አሁን ላይ ወደ መጨረሻው ምዕራፍ መድረሳቸው ተገልጿል፡፡

እንደ ሲቢኤስ ዘገባ ከሆነ የወንዶች እርግዝና መከላከያ መድሃኒትን ለማምረት የተለያዩ ኩባንያዎች በሙከራ ለይ ሲሆኑ በክትባት መልኩ እና በሌሎች መልኩ የሚሰጡ መድሃኒቶችን ለማምረት ሙከራዎች እየተካሄዱ ናቸው፡፡

እየተደረጉ ካሉ የወንዶች እርግዝና መከላከያ መድሃኒቶች መካከል በጄል መልክ ክንድ ላይ የሚቀባው መድሃኒት አንዱ ነው፡፡
በአሜሪካ ብሔራዊ የወሊድ መከላከያ ኢንስቲትዩት በኩል እየተደረገ ያለው ይህ ጄል መሳይ የወንዶች እርግዝና መከላከያ መድሃኒት የመጀመሪያውን እና ሁለተኛውን ደረጃ ሙከራ ማጠናቀቁ ተገልጿል፡፡

የወንዶች የወሊድ መከላከያ እንክብል 99 በመቶ ውጤታማ ሆኗል ተብሏል።

ይህ ጄል የወንዶችን የዘር ፈሳሽ መጠን በመቀነስ እርግዝና እንዳይፈጠር የሚያደርግ ነው የተባለ ሲሆን በ222 በጎ ፈቃደኛ ወንዶች ላይ ተሞክሮ እስካሁን ውጤታማ ሆኗል ተብሏል፡፡

ሌሎች ተቋማትም የወንዶች እርግዝና መከላከያ መድሃኒቶችን ለማምረት ጥረቶች ላይ ናቸው የተባለ ሲሆን ከሆርሞን ጋር የማይገናኙ የህክምና ቁሳቁሶችን ለማምረትም ተመሳሳይ ተቋማት የመጨረሻ ደረጃዎች ላይ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

እስካሁን በዓለማችን የወንዶች እርግዝና መከላከያ መድሃኒት ለማምረት የተመዘገበ ህጋዊ ተቋም የሌለ ሲሆን በሙከራ ለይ ያሉ ተቋማት ከሚቀጥለው ዓመት ጀምሮ መድሃኒቶችን ለማምረት ፈቃድ ለማግኘት እንደሚያመለክቱ አስታውቀዋል፡፡
Via Al ain

@ethio_mereja_news
#ኢትዮጵያ አየር መንገድ ከአራት አመታት በኋላ ወደ አክሱም ከተማ ዳግም በረራ ጀምሯል። 

#ትግራይ ጦርነት ጉዳት የደረሰበት አጼ ዮሐንስ 4ኛ አውሮፕላን ማረፊያ የተደረገለት ጥገና ተጠናቆ ዛሬ ሰኔ 2 ቀን 2016 መደበኛ ስራ ጀምራል።

ዛሬ በተደረገ የመጀመሪያ በረራም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑትን አቶ መስፍን ጣሰውን፣ የፌደራል እና የክልል የስራ ሃላፊዎችን ጨምሮ 140 ተጓዦች የያዘው  አውሮፕላን አክሱም ሃፀይ ዮሐንስ አራተኛ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርስ አቀባበል ተደርጓል።

በአቀባበል ስነ ስርዓቱ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳን ጨምሮ ሌሎች የክልሉ ባለስልጣናት ተገኝተዋል።

በረራውም በየቀኑ 1 ጊዜ የሚደረግ ሲሆን በቀጣይ የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት በማድረግ በቀን ወደ 3 ጊዜ ለማሳደግ እንደሚሰራም ተጠቁሟል፡፡

@ethio_mereja_news
የበርካታዎችን ሕይወት በቀጠፈው የሰሜኑ ጦርነት ወቅት በየቦታው የተቀበሩ እና የተጣሉ ተተኳሾች ፣ ፈንጂዎች አሁንም በሰው ህይወት ላይ አደጋ ማድረሳቸው ቀጥሏል።

በአፋር፣ በትግራይ እና በአማራ ክልሎች የተቀበሩ ፈንጂዎች ለሰው ህይወት መጥፋትና ለአካል መጉደል ምክንያት እንደሆኑ በተደጋጋሚ ሲገለጽ ነበር።

በትግራይ ክልል በምሰራቃዊ ዞን ሐውዜን ወረዳ ማይጎቦ ቀበሌ ገበሬ ማህበር ትናንት ሰኔ 1 2016 በፈነዳ ተተኳሽ አራት ሰዎች ሕይወት መቀጠፉ ተሰምቷል።

@sheger_press
በራያ አላማጣ ከተማ ዛሬ ለሊቱን በርካታ የህወሓት ታጣቂዎች ወደ ከተማዋ መግባታቸውን የአይን እማኞች ገልፀውልኛል።

በከተማ በሚገኙ ምስራቅ ፀሀይ፣ታዳጊዋና ሹሜ በርሄ ትምህርት ቤት ከሰፈረው ታጣቂ በተጨማሪ ምድረገነት ትምህርት ቤት ዛሬ ለሊቱን በርካታ ታጣቂዎች ገብተው ሰፍረዋል ብለዋል።

ትናንት የራያ ህዝብ በከተማዋ የሚገኙ የህወሓት ታጣቂዎች ከቀናት በፊት አንድ የመብራት ሀይል ሰራተኛ የነበረ ወጣትን በመግደላቸው ምክንያት ትናንት ህዝቡ በአደባባይ ወጥቶ ቅሬታውን ማሰማቱ አይዘነጋም። ዛሬ ለሊቱን ታጣቂዎች በተኮሱት ተኩስ አራት ሰዎች ላይ ከባድ እና ቀላል ጉዳት አድርሰዋል ብለዋል።

በከተማዋ የሚገኙ ሁሉም ትምህርት ቤቶች ታጣቂዎቹ ስለሰፈሩባቸው ትምህርት ከተዘጋ ወራቶች ሊቆጠሩ ነው ብለዋል(አዩዘሀበሻ)።
#ጋምቤላ‼️

በጋምቤላ ከተማ የታጣቂዎች ጥቃት ዘጠኝ ሰዎች መቁሰላቸውን ነዋሪዎች ገለጹ!!

በጋምቤላ ከተማ፣ ባለፈው ሳምንት ዐርብ፣ ታጣቂዎች በአንድ የመዝናኛ ክበብ ውስጥ በከፈቱት ተኩስ፣ ዘጠኝ ሰዎች መቁሰላቸውን፣ የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል፡፡

የጋምቤላ ከተማ የመጀመሪያ ደረጃ ሆስፒታልም፣ የጥቃቱ ሰለባ የኾኑ ሰዎችን ተቀብሎ እያከመ መኾኑንና፣ ከመካከላቸው ከባድ ጉዳት የደረሰበት አንድ ሰው፣ ለተሻለ ሕክምና ወደ አዲስ አበባ ተልኳል፡፡

የክልላዊ መንግሥቱ፣ የሰላም እና ጸጥታ ቢሮ ደግሞ፣ በጥቃቱ ዘጠኝ ሰዎች መቁሰላቸውን አረጋግጦ፣ ጥቃት ፈጻሚዎቹ ግን “እስከ አሁን አልተያዙም፤” ብሏል፡፡

@ethio_mereja_news
ኤርትራ በሌሊት ብቻ የሚሰራ የኢንተርኔት አገልግሎት መስጠት መጀመሯ ተሰማ

👉🏼 የሙሉ ሌሊት ኢንተርኔት ተጠቃሚዎች እስከ 105 ዶላር ድረስ መክፈል ይጠበቅባቸዋል ተብሏል


ኤርትረ በትናንትናው እለት የሌሊት ኢንተርኔት አገልግሎት መስጠት መጀመሯን ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ሰምቷል።

ኤርትራ በሌሊት ብቻ ይሰጣል ባለችዉ የኢንተርኔት አገልግሎት እጅግ ዉድ ሊሰኝ እንደሚችል የኢንተርኔት እና የኮምፒውተር ባለሙያ ለብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ተናግረዋል። በሰከንድ 512 ኪሎ ባይት ድረስ አገልግሎት ይሰጣል የተባለዉ ኢንተርኔት በቤት ስልክ መስመር የሚመጣ ሲሆን ተጠቃሚዎች ወደ ሞባይል እና ኮምፒውተሮቻቸዉ ማገናኘት እና መጠቀም ይችላሉ ተብሏል።

ኤርትራ በትናንትናው እለት ሌሊቱን ያስጀመረችዉ የኢንተርኔት አገልግሎት ባለሙያዎች ገለጻ ዘንድ ቀርፋፋ ነዉ የተሰኘዉን ነዉ።

ሁለት አይነት የኢንተርኔት ማስተላለፊያ መስመሮች ያሉ ሲሆን ኤዲኤስኤል (ADSL) በሲርናል ኢንተርኔት የሚደርስበት ሲሆን ቀርፋፋ የኢንተርኔት አገልግሎት የሚሰጥበትም ነዉ። በአንጻሩ በፋይበር የሚተላለፈዉ ኢንተርኔት በብርሃን አጋዥነት አገልግሎት የሚሰጥበት ሲሆን እጅግ ፈጣኑም እንደሆነ ባለሙያዉ ገልጸዋል።

ታድያ ኤርትራ አስጀመረችዉ የተባለዉ የኢንተርኔት አገልግሎት ኤዲኤስኤል (ADSL) የተሰኘዉን ነዉ። ይህ አሁንም በኢትዮጵያ አገልግሎት እየሰጠ ቢሆንም ቀርፋፋዉ አገልግሎት መሆኑን ባለሙያዉ ገልጸዋል።

ከሌሊቱ 4 ሰዓት እስከ ንጋት 12 ሰዓት ድረስ ከ 512 እስከ 1 ሜጋባይት ድረስ በሰከንድ ኢንተርኔት የሚያስጠቅነዉን አገልግሎት ለማግኘት ኤርትራውያን 1575 ናቅፋህ ወይንም 105 የአሜሪካ ዶላር መክፈል አለባቸው ተብሏል።

የተለያዩ አገልግሎቶች ይሰጣሉ የተባለ ሲሆን ተጠቃሚዎች እስከ 10 ጊጋ ባይት ድረስ የሆነና ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎትን ማግኘት ካሻቸዉ ደግሞ 4200 ናቅፋህ ወይንም 280 የአሜሪካ ዶላር ከፍያ መፈጸም እንዳለባቸው ብስራት ራዲዮና ቴሌቪዥን ከተሰራጨው ማስታወቂያ ላይ መታዘብ ችሏል።

@ethio_mereja_news
2024/10/02 06:25:05
Back to Top
HTML Embed Code: