Telegram Web Link
ጃዋር መሀመድ የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የአሜሪካ አምባሰደርን የሰላም ጥሪ ማውገዙ አሳዛኝ ነው አሉ

የአሜሪካ በኢትዮጵያ አምባሳደር አርቪን ማሲንጋ “የሰጡትን ሃቀኛ እና ድፍረት የተሞላበት መግለጫ” የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ማውገዙ ግራ የሚያጋባ እና አሳዛኝ ነው ሲሉ አንጋፋው ፖለቲከኛ ጃዋር መሀመድ ገለጹ።

ጃዋር መሀመድ ዛሬ በይፋዊ ፌስቡክ ገጻቸው ላይ አምባሳደሩ የሰጡትን መግለጫ የኢትዮጵያ መንግስት ይቀበለዋል ተብሎ የሚጠበቅ ባይሆንም አምባሳደሩ “በተለመደ ዲፕሎማሲያዊ ንግግር ሳይሸፋፍን ይልቁንም የአገር እውነተኛ ወዳጅ ማድረግ እንዳለበት ሁሉ በግልፅ እና በፍትሃዊነት ሁሉም ተፋላሚ ወገኖች የፖለቲካ ግጭቶችን በትጥቅ ሃይል ለመፍታት የሚያደርጓቸውን አውዳሚ እና የተሳሳተ ሙከራ እንዲተዉ” መጠየቃቸውን አስፍረዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትላንትናው ዕለት አምባሳደር አርቪን ማሲንጋ በሰብዓዊ መብቶች ዙሪያ ያቀረቡት መግለጫ በሕዝብ የተመረጠን መንግስት ለመገልበጥ የተነሱ ቡድኖችን በመዘርዘር መንግስት እንዴት አገሪቷን መምራት እንዳለበት የሚገልጽ ያልተገባ ምክርን ያዘለ ነው” ሲል ተቃውሞታል።

የአምባሳደሩ መግለጫ “ያልተረጋገጡ መረጃዎች ያሉትና የሁለቱን አገራት ግንኙነት የሚጻረር መሆኑን የገለጸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር “ስህተቶች እንዲታረሙ” ከኤምባሲው ጋር በቅርበት  እንደሚሰራ ትናንት ባወጣው መግለጫ ማሳወቁ ይታወሳል።

ጃዋር መሀመድ በጽሁፋቸው የፕሪቶሪያ ስምምነት በመፈራረም መንግስት የእርስ በርስ ጦርነቶችን በድርድር ለመፍታት ፍላጎት እንዳለው ቢያሳይም የገባውን ቃል “አሁን ወደኋላ እየተመለሰ ይመስላል” ብለዋል።

መንግስት ተቃዋሚዎቹን በወታደራዊ መንገድ ለማጥፋት ወደመሞከር የተመለሰ ሲሆን ይህ የተሞከረ እና ያልተሳካለት ስልት ባለፉት ዓመታት አገሪቱን አውድሟል ሲሉ ፖለቲከኛው ገልጸዋል።

በሰላማዊ መንገድ የተገኘውን ውጤት ከማጠናከር ይልቅ ከፍተኛ ወታደራዊ እና የፕሮፓጋንዳ ዘመቻዎችን መንግስት እያደረገ፤ ከዚሁ ጎን ለጎን ገዢው ፓርቲ የፖለቲካ ምህዳሩን ዋስትና በማስጠበቅ የምርጫ ቅስቀሳ ማድረግ ጀምሯል በማለትም አክለዋል።

በቅርቡ በነቀምት እና በባህር ዳር በተደረጉት የድጋፍ ሰልፎች ላይ ከተናገሩት በተቃራኒ በአብዛኛው የአማራ እና የኦሮሚያ ክልሎች በጦርነት የተጎዱ አካባቢዎች እየተስፋፉ እንጂ እየቀነሱ አይደሉም ያሉት ጃዋር መሀመድ፤ መከላከያ ሠራዊት በአንዳንድ አካባቢዎች ጥሩ ውጤት ያስመዘገበ ቢሆንም፣ “ስለ ታጣቂዎች የጅምላ መክዳት በተመለከተ የቅርብ ጊዜ ዘገባዎች በጣም የተጋነኑ እና አንዳንዶቹ ፍጹም የፈጠራ ወሬዎች ናቸው” በማለት ጽፈዋል።

አብዛኛዎቹ ዞኖች እና ወረዳዎች በመንገድ አለመገናኘታቸው ማሳያው የኢትዮጵያ አየር መንገድ የአየር ጉዞው በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር እንደሆነ የጠቀሱት ፖለቲከኛው ጃዋር፤ ገበሬዎች ማዳበሪያ መቀበልም ሆነ ሰብል መትከል አይችሉም፣ በሰላማዊ ዜጎች ላይ እየተፈጸመ ያለው አፈና እና ሕግ-ወጥ ግድያ ህይወትን በገጠሩ ሕዝብ ላይ መቋቋም የማይቻል አድርጎታል ብለዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ቄስ በላይ መኮንንን ጨምሮ በ5 ግለሰቦች ላይ ከባድ የማታለል ሙስና ወንጀል ክስ ተመሰረተ‼️

ቄስ በላይ መኮንንን ጨምሮ በአምስት ግለሰቦች ላይ ከባድ የማታለል ሙስና ወንጀል ክስ በመደበኛ ችሎት ተመሰረተባቸው።

ክሱ የተመሰረተባቸው በፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 3ኛ የሙስና ጉዳዮች ወንጀል ችሎት ሲሆን÷ ተከሳሾቹም 1ኛ ቄስ በላይ መኮንን፣ 2ኛ በግብርና ኢንቨስትመንት የተሰማራው ኢያሱ እንዳለ ወ/መስቀል፣ 3ኛ በኮሚሽን ሥራ የተሰማራው በረከት ሙላቱ ጃፋር፣ 4ኛ ዓለምገና ሳሙኤል ዲንሳ እና 5ኛ የኒሞና ንግድ ሥራ ኃላ/የተ/የግል ማኅበር ሥራ አስኪያጅ አበራ መርጋ ተስፋዬ ናቸው።

4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾች በቁጥጥር ሥር አለመዋላቸው እና ሌሎቹ ግን በችሎቱ መገኘታቸው ተገልጿል፡፡

የፍትሕ ሚኒስቴር የሙስና ወንጀል ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዐቃቤ ሕግም በተከሳሾቹ ላይ ሁለት ከባድ የሙስና ወንጀል ክስ አቅርቦባቸዋል።

በአንደኛው ክስ በሁሉም ተከሳሾች ላይ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የወንጀል ሕግ ቁጥር 32 ንዑስ ቁጥር 1(ሀ) እና የሙስና ወንጀሎች ለመደንገግ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 881/2007 አንቀፅ 32 ንዑስ ቁጥር 2 እና ንዑስ ቁጥር 3 ሥር የተመለከተውን ድንጋጌ ተላልፈዋል የሚል ነው።

በዚሁ የክስ ዝርዝር ላይም ተከሳሾች በጋራ በመሆን ከአፍሪካ ኅብረት ጋር ክፍያ እንዲከፈላቸው የሚያደርግ ምንም ዓይነት የሥራ ግንኙነት ሳይኖራቸው፣ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሚገኘው የኅብረቱ የባንክ ሒሳብ ላይ ገንዘብ በዶላር ተቀንሶ ለተከሳሾች ክፍያ እንዲፈፀም የተሰጠ ምንም ዓይነት የክፍያ ትዕዛዝ በሌለበት ሁኔታ ትዕዛዝ እንዳለ አስመስለው በተጭበረበረ መንገድ ከ6 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር በላይ በመውሰድ ለግል ጥቅማቸው በማዋል የማይገባቸውን ብልፅግና ለራሳቸው ለማግኘትና ለሌሎች ሰዎች ለማስገኘት በማሰብ የሚል ተጠቅሷል።

2ኛ ተከሳሽ ለአፍሪካ ኅብረት ድርጅት የግንባታ ቁሳቁስ እንዳቀረበ በማስመሰል የካቲት/2016 ዓ.ም በማቅረብ ወደ ተከሳሹ ሒሳብ ቁጥር 1 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ከአፍሪካ ኅብረት ሒሳብ ተዘዋውሮ ገቢ እንዲሆንለት ያዘዘ መሆኑን የሚያሳይ ሐሰተኛ የክፍያ ሰነድ በስሙ እንዲዘጋጅ ማድረጉ በክሱ ላይ ተመላክቷል፡፡

3ኛ ተከሳሽ በረከት ሙላቱ ጃፋር ለአፍሪካ ኅብረት ጥልቅ የውኃ ጉድጓድ ቁፋሮ ለመሥራት የተስማማ በመሆኑ ከአፍሪካ ኅብረት ሒሳብ  ወደ ራሱ የሂሳብ ቁጥር 2 ሚሊየን 525 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ገቢ እንዲደረግ ማዘዙን የሚያሳይ ሐሰተኛ የክፍያ ሰነድ በስሙ እንዲዘጋጅ ማድረጉ በክሱ ተገልጿል፡፡

4ኛ ተከሳሽ ዓለምገና ሳሙኤል ዲንሳ ለአፍሪካ ኅብረት የጥልቅ ጉድጓድ የውኃ ቁፋሮ ሥራ የሠሩ በመሆኑ ኅብረቱ ወደ ግለሰቡ የሒሳብ ቁጥር 1 ሚሊየን 315 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ገቢ እንዲደረግ የካቲት 12 ቀን 2016 ዓ.ም ማዘዙን የሚያሳይ ሐሰተኛ የክፍያ ሰነድ በስሙ እንዲዘጋጅ አድርጓል ተብሏል በክሱ ዝርዝር ላይ፡፡

5ኛ ተከሳሽ አበራ መርጋ ተስፋዬ ለአፍሪካ ኅብረት ከማኅበሩ የግንባታ ቁሳቁስ እንዳቀረበ እና ከኅብረቱ ሒሳብ በክፍያ እንዲፈጸምለት ወደ ራሱ በሆነው የድርጀቱ ሒሳብ 1 ሚሊየን 210 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ክፍያ እንዲፈፀም ማዘዙን የሚሳይ ሐሰተኛ የክፍያ ሰነዶች በስሙ እንዲዘጋጅ ማስደረጉና ገንዘቡን ወጪ ለማድረግ ሰነዶቹን በውል ባልታወቀ ጊዜ እና ቦታ ለ1ኛ ተከሳሽ መስጠታቸው በክሱ ተጠቅሷል።

እንዲሁም በሁለተኛው የክስ መዝገብ በሁሉም ተከሳሾች ላይ ዐቃቤ ሕግ በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወንጀል ሕግ ቁጥር 382 ንዑስ ቁጥር 1 ሥር የተመለከተውን በመተላለፍ ተከሳሾቹ ተገቢ ያልሆነ ጥቅምን ወይም መሻሻልን ለማግኘት በማሰብ መጋቢት 7 ቀን 2016 ዓ.ም በግምት ከቀኑ 8 ሠዓት ተኩል ላይ ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ውስጥ ከሚገኘው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አፍሪካ ኅብረት ቅርንጫፍ በመቅረብ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሚገኘው ኅብረቱ ሒሳብ ላይ ገንዘብ በአሜሪካን ዶላር ወጪ ተደርጎ ከ2ኛ እስከ 5ኛ ለተጠቀሱት ተከሳሾች እንዲከፈል የሚያዙ ሐሰተኛ የክፍያ ሰነዶችን ጠቅላላ ድምሩ 6 ሚሊየን 50 ሺህ የአሜሪካ ዶላር ወይም በወቅቱ የምንዛሪ ተመን 346 ሚሊየን 843 ሺህ 475 ብር ለማስተላለፍ ሐሰተኛ ሰነዶቹን ለባንክ እንዲቀርብ በማድረግ እና በማቅረብ በፈጸሙት የክፍያ ሰነዶችን አስመስሎ ማዘጋጀት ወደ ሐሰት መለወጥ ወይም ሐሰተኛ ሰነድ መገልገል ወንጀል ተከሰዋል የሚል ዝርዝር አቅርቦባቸዋል።

ከ1ኛ እስከ 3ኛ ተራ ቁጥር የተጠቀሱ ተከሳሾች ችሎት ቀርበው ማንነታቸውንና አድራሻቸውን ካስመዘገቡ በኋላ የክስ ዝርዝሩ እንዲደርሳቸው ተደርጓል።

3ኛ ተከሳሽ ጠበቃ የለኝም ማለታቸውን ተከትሎ ከጠበቃ ጋር ተማክረው እንዲቀርቡና ክሱንም በንባብ ለማሰማት ለፊታችን ሰኞ ተቀጥሯል።

ፍርድ ቤቱ 4ኛ እና 5ኛ ተከሳሾችን በሚመለከት ፖሊስ አፈላልጎ እንዲያቀርባቸው በቀጣይ ቀጠሮ ትዕዛዝ እንደሚሰጥበት ገልጿል።

ታሪኩ -አዱኛ

@ethio_mereja_news
ቢጂአይ ኢትዮጵያ እና ፐርፐዝ ብላክ ኩባንያ በቢጂአይ ዋና መስሪያ ቤት ሕንጻና የፋብሪካ ሽያጭ ዙሪያ በፈጠሩት ውዝግብ ዙሪያ ፍርድ ቤት-መር በኾነ አስማሚ ወገን አማካኝነት ከስምምነት ላይ መድረሳቸውን ቢጂአይ አስታውቋል።

የፌዴራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ፐርፐዝ ብላክ ኩባንያ በቢጂአይ ላይ መስርቶት የነበረውን ክስ ዘግቶ፣ በቢጂአይ ላይ ጥሎት የነበረውን እግድ አንስቷል።

በአዲሱ ስምምነት መሠረት፣ ቢጂአይ-ኢትዮጵያ ከፐርፐዝ ብላክ የተቀበለውን 1 ቢሊዮን ብር የቀብድ ክፍያ መልሷል ተብሏል።

ቢጂአይ ኢትዮጵያ ኩባንያ ሜክሲኮ የሚገኘውን ዋና መስሪያ ቤቱን በመልቀቅና ፋብሪካውን በመንቀል ወደ ሌላ ቦታ ለማዛወር የወሰነው፣ ፋብሪካው ካረፈበት ቦታ በቁፋሮ የሚወጣው ውሃ መጠኑ በመመናመኑ እንደኾነ ቀደም ሲል መግለጡ አይዘነጋም።

@ethio_mereja_news
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ፖሊስ፣ ዛሬ በወላይታ ዞን ሶዶ ከተማ ያልተከፈላቸው ደመወዝ እንዲከፈላቸው በሰላማዊ ሰልፍ የጠየቁ የመንግሥት ሠራተኞችን በኃይል እንደበተነ ዶይቸቨለ ዘግቧል።

ፖሊስ ሰልፈኞቹን የበተነው፣ አቤቱታቸውን ለማቅረብ ወደ ርዕሰ መስተዳድሩ ጽሕፈት ቤት በመጓዝ ላይ ሳሉ እንደኾነ ዘገባው አመልክቷል።

ከኹለት እስከ ሦስት ወራት ደሞዝ እንዳልተከፈላቸው የጠየቁ ሠራተኞች፣ ባለፈው ማክሰኞም አቤቱታቸውን በሰልፍ ማሰማታቸው አይዘነጋም።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
#Tecno #Camon30Pro5G

የሞባይል ቴክኖሎጂን ጨምሮ የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ብራንድ አምራች የሆነው እና ከ70 በላይ ሀገራት 
ምርቶቹን በስፋት የሚያቀርበው ቴክኖ አዲስ የሞባይል ቴክኖሎጂ ውጤት የሆነውን ካሞን 30 ፕሮ 5G ሞዴል በአዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ሆቴል የተለያዩ ሀገራት አምባሳደሮች፣ ከፍተኛ ባለስልጣናት፣ እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት አስተዋወቀ።

አዲሱ ካሞን 30 ፕሮ 5G የሶኒ(SONY) የካሜራ ሴንሰር ቴክኖሎጂን ጨምሮ የተለያዩ የቴክኖ ምርምር ውጤት የሆኑ የቴክኖሎጂ ግብዓቶችን አካቶ የተመረተ ሞዴል ነው።

የኢትዮ ቴሌኮም ቺፍ ማርኬቲንግ ኦፊሰር የሆኑት አቶ ሰኢድ አራጋው በዝግጅቱ ላይ እንደተናገሩት ‘’ ኢትዮ ቴሌኮም እና ቴክኖ ሞባይል በጋራ በመሆን ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ ይሰራሉ’’ ብለዋል።

#Camon30Et  #Camon30pro5GEt #Camon30 #Camon30Pro5G #TecnoEt
ወልቃይት‼️

የወልቃይት ጠገዴ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሸተ ደምለው የወልቃይት ጠገዴን ቀጠና ከሀገር አፍራሾች በመከላከል የኢትዮጵያን አንድነት እንጠብቃለን ሲሉ ዋና አስተዳዳሪው አመልክተዋል።

👉ከትናንት በስተያ ጀምሮ ለተከታታይ ሁለት ቀናት በወልቃይት አዲረመፅ ከተማ በዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሸተ ደምለው እና በኮለኔል ደመቀ ዘውዱ የተመራ ህዝባዊ ውይይት ተደርጓል።

የወልቃይት ጠገዴ ህዝብ ያለ ማንነቱ ተጭኖበት ከነበረው እዳ ከእስራት ተፈቷል ያሉት ዋና አስተዳዳሪው ቀሪው በህግ አግባብ ማንነቱን የሚያስከብርበት ነፃነቱን የሚዪፀናበት ወሳኝ ምዕራፍ በመሆኑ የወልቃይት ጠገዴ ጉዳይ ከታሪክ፣ ከህግና ከሞራል አኳያ አስተውሎ እውነተኛ መፍትሔ መስጠት የኢትዮጵያን መቃብር ጠባቂዎች አሳፍሮ ዘላቂ ሰላም ከሚያውጁ ጉዳዮች አንዱ ነውና አመታትን ያስቆጠረው ጥያቄያችን ይመለስልን ሲሉ የወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሁመራ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ አሸተ ደምለው መናገራቸውን የአዩዘሀበሻ ምንጮች ገልፀዋል።

የዞኑ የፀጥታ እና ደህንነት ሀላፊ የሆኑት ኮለኔል ደመቀ ዘውዱ በበኩላቸው ህዝቡ በማንነት ትግሉ እንዲፀና እና ወደ ኋላ እንዳያፈገፍግ አሳስበዋል።

ኮለኔሉ የወልቃይት አመራር መስዋዕትነት ለመክፈል መዘጋጀቱን እና መብቱን አሳልፎ እንደማይሰጥ መናገራቸውን በስብሰባው ታዳሚ የነበሩ ሰዎች ለአዩዘሀበሻ ገልፀዋል።

የትግራይ ጊዚያዊ አስተዳደር ምክትል ፕሬዚዳንት ሌ/ጄኔራል ታደሰ ወረደ ደቡብ ትግራይን እስከ ግንቦት 20 እንዲሁም ጠለምትን እስከ ሰኔ 30/2016 ዓ.ም እንደሚረከቡ ከስምምነት ተደርሷል ሲሉ በቅርቡ መግለጫ መስጠታቸው ተሰምቷል።

@ethio_mereja_news
#Update

የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የኦንላይን ተፈታኞች መፈተኛ ይፋ ሆኗል፡፡


የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና በወረቀት እና በበይነ መረብ የሚሰጥ መሆኑ ይታወቃል፡፡

በዚህም በበይነ መረብ ፈተናውን የሚወስዱ ተፈታኞች ከዚህ በታች በተገለፀው አድራሻ ብቻ ፈተናውን እንደሚወስዱ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል፡፡

ስለሆነም ፈተናውን ከመውሰዳቸው በፊት ሁሉም ተፈታኞች በቂ ልምምድ ማድርግ አስፈላጊ

በመሆኑም ከዛሬ ቅዳሜ ግንቦት 10/2016 ዓ.ም ጀምሮ የበይነ መረብ ተፈታኞች ባሉበት ሆነው ልምምድ ማድረግ የሚችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

ተፈታኞች ልምምድ ለማድረግ ከዚህ በፊት ለክልል/ከተማ አስተዳደር የተላከውን የይለፍ ቃል እና ስም (User Name and Password) ከየትምህርት ቤቶቻቸው ማግኘት ይችላሉ፡፡

በዚሁ መሠረት መጀመሪያ ወደ መፈተኛ ሲሰተሙ እንደገቡ የማይረሱትን የግላቸውን የይለፍ ቃል የሚቀይሩ ይሆናል፡፡

ተፈታኞች ከተደለደሉበት ክለስተር ውጪ ሲሰትሙን መጠቀም እንደማይችሉ አገልግሎቱ አሳስቧል።

(ፈተናው የሚሰጥበት አድራሻ እና ተፈታኞቹ የሚገኙበት ክልል/ከተማ አስተዳደር ከላይ ተያይዟል።)

@ethio_mereja_news
#Tecno #Camon30Pro5G

በካሜራ ጥራቱ እና በስልኩ ዲዛይን የተመሰከረለት አዲሱ Tecno camon 30 pro 5G ምርጫዎ ያድረጉ!

#Camon30Et #Camon30pro5GEt #Camon30 #Camon30Pro5G #TecnoEt
አየር መንገዱ ከሰኔ 1 ጀምሮ ወደ አክሱም ዳግም በረራ ይጀምራል ተባለ

ከመጪው ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ትግራይ ክልል አክሱም ከተማ ዳግም በረራ እንደሚጀምር የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ገለጸ።

የአየር መንገዱ የንግድ ዘርፍ ዋና ኃላፊ አቶ ለማ ያዴቻ፤ አየር መንገዱ ወደ አክሱም ዳግም በረራ ለመጀመር የሚያስችሉትን ቅድመ ዝግጅት ሲያደርግ ቆይቷል ብለዋል።

በመሆኑም ከመጪው ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ.ም ጀምሮ ታሪካዊ የቱሪዝም መዳረሻ ወደሆነችው አክሱም ከተማ ዳግም በረራ እንደሚጀመር ገልጸዋል። በረራው መጀመሩ ዓለም አቀፍ ቱሪስቶችና የሀገር ውስጥ ጎብኚዎች ወደ ሥፍራው የሚያደርጉትን ጉዞ ለማሳለጥ እንደሚያስችልም ተናግረዋል።

በረራው በሣምንት ሰባት ጊዜ የሚደረግ መሆኑንም መጠቆማቸውን የዘገበው ኢዜአ ነው። አየር መንገዱ የደንበኞችን ፍላጎት መሰረት በማድረግ በረራውን በቀን ወደ 3 እንደሚያሳድግም ገልጸዋል።የበረራው መጀመር የትራንስፖርት እንቅስቃሴውን ለማሳለጥና ማኅበራዊ መስተጋብርን ለማጠናከር ያስችላል ብለዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የሀዘን መግለጫ‼️

የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ኃይለማርያም መኮንን ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል።

በቅፅል ስማቸው "ሻሾ" በሚል በስፖርት ቤተሰቡ በስፋት የሚታወቁት ኃይለማርያም ከ1940ዎቹ መጨረሻ እስከ 60ዎቹ መጀመርያ በነበረው የተጫዋችነት ህይወታቸው ለጥቅምት 23፣ ሸዋ ፖሊስ፣ ዳኘው እና ሸዋ ምርጥ የተጫወቱ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንንም በተለያዩ የእድሜ እርከኖች እና ዋናው ቡድን አገልግለዋል። በ1954 ኢትዮጵያ የሦስተኛው አፍሪካ ዋንጫ ስታሸንፍም የቡድኑ አባል ነበሩ።

የቀድሞ ተጫዋች ኃይለማርያም መኮንን ሥርዓተ ቀብር በቀጨኔ ደብረ ሰላም መድኃኔዓለም ቤተ-ክርስቲያን ዛሬ 6:00 ላይ የሚፈፀም ይሆናል።

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን በቀድሞ የብሔራዊ ቡድናችን ተጫዋች ህልፈት የተሰማውን ጥልቅ ሀዘን እየገለፀ ለቤተሰብ ፣ ለወዳጅ ዘመድ እና የእግር ኳስ ቤተሰብ መፅናናትን ይመኛል።

ምንጭ -የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በአዲስ አበባ ከተማ በዓመት ከ80 ሺ ቶን በላይ የፕላስቲክ ቆሻሻ ይመነጫል ሲል የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን አሰታወቀ!

በከተማዋ ከሚመነጨው ቆሻሻ 13 በመቶ የሚሆነዉ የፕላስቲክ ሲሆን በዓመት ወደ 80,000 ቶን እንደሚጠጋ ለማወቅ ተችሏል።ባለሥልጣኑ የፕላስቲክ ምርቶችን በመልሶ ማምረት ላይ እየሰሩ ካሉ የፕላስቲክ ፋብሪካዎች፣ ምርቶቹን ከሚጠቀሙ ሱፐር ማርኬቶች፣ ዳቦ አምራችና አከፋፋይ ቤቶች፣ አትክልት ቤቶችና የወረቀት መያዣ  ከሚያመርቱ ባለድርሻ አካላት ጋር የፕላስቲክ ብክለትን ለመከላከል በሚያስችሉ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አካሂዷል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር አካባቢ ጥበቃ ባለሥልጣን ዋና ሥራ አስኪያጅ ዲዳ ድሪባ እንደተናገሩት በመዲናዋ የአካባቢ ብክለትን እያስከተሉ ካሉ የብክለት ዓይነቶች መካከል ፕላስቲክ አንዱ መሆኑን ገልፀው፤ ይህም በሰዎች ጤና፣ የአካባቢ ውበትና የውኃ ኃብታችን ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እያሳደረ ይገኛል ብለዋል።

በዚህ ዉይይት ባለስልጣኑ እንዳስታወቁት አካባቢን የሚበክሉ የፕላስቲክ ምርቶች ውፍረታቸው ከ0.03 ማይክሮ ሜትር በታች ሆነው እንዳይመረቱና አገልግሎት እንዳይሰጡ ማድረግ፣ በፕላስቲክ ምርቶች ላይ ከፍተኛ የሆነ ታክስ መጣል የሚሉትና ሌሎች ላይ ተግባራዊ መደረግ አለበት ባሉት ጉዳይ ዝርዝር ማብራሪያ ሰጥተዋል።

የሀገሪቷ የፕላስቲክ ፍጆታ ከ 2007 ከነበረበት 43000 በ 2022 ወደ 224000 ማደጉ ተገልጿል። በእዛው ልክ ደግሞ የፕላስቲክ ነፍስ ወከፍ ፍጆታ በዓመት ወደ 13 በመቶ አድጓል ። በዓመት 40,000 ቶን ፕላስቲክ ሪሳይክል ይደረጋል ተብሎ የሚገመት ቢሆንም ነገር ግይ ይህ ከሚያመነጨው ግማሹ ብቻ መሆኑ ተመላክቷል።

Via Capita
@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Sport‼️

ማንችስተር ሲቲ የእንግሊዝ ፕሪሜየር ሊግ 2023/2024 ሻምፒዩን ሆነ!!

ቡድኑ በተከታታይ ለ4 ዓመታት የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ በማንሳት አዲስ ታሪክ ጽፏል።

ዘንድሮ እስከ ዛሬው የመጨረሻ መርሀግብር ከ #አርሴናል ጋር አንገት ለአንገት የተናነቀው ሲቲ 91 ነጥብ በመሰብሰብ ነው ዋንጫውን ያሸነፈው።

እጅግ ብርቱ እና ጠንካራ አመትን ያሳለፈው አርሴናል 89 ነጥብ በመያዝ በሁለተኛነት ማጠናቀቅ ችሏል።
Tapswap‼️
ካልጀመራቹት ሊንኩ ከስር አለላቹ ጀምሩ‼️

ሰሞኑን አንድ አለምን ያስገረመ መረጃ እናጋራቹ‼️

የዓለም ህዝብ ለምን ወደ #Tapswap መጉረፍ ጀመረ

የዓለም ህዝብም እንደኛው ዘግይቶ ይገባው ጀምሯል።

በሦስት ቀናት ውስጥ ብቻ ከአራት ሚሊዮን በላይ ህዝብ #Tapswap ን ተቀላቅሏል። (ፈጽሞ ሊገመት የማይችል ጎርፍ ነው።)

በየቀኑ #Tap የሚያደርገው ህዝብ ብዛት ከ7.8 ሚሊዮን አልፏል። በቀጥታ #Tap የሚያደርገው ህዝብ ብዛት ከ430 ሺህ ተሻግሯል።

ለዚህም ከዋነኛ ምክንያቶች መካከል:-
🙏 #Solana በዓለም በጣም ታዋቂ ብሎክቼይን የሚያስተዳድር (በዲጂታል ፋይናንስ ዝርፍ የተሰማራ) ድርጅት (እምነት የሚጣልበት) በመሆኑ

በቴሌግራም ጌም ገንዘብ ማግኘት እንደሚቻል #በNotcoin በተግባር በመረጋገጡ (ለዚህም ማሳያ Notcoin list ከተደረገ በኋላ እጅግ በርካታ ህዝብ Tap ማድረግ መጀመሩ)

ቴሌግራም የዓለም ህዝብን በቀላል መንገድ ወደ ብሎቼይን/ክሪፕቶከረንሲ ለመሳብ የቀየሰው ስትራቴጂ የተሳካ መሆኑ ፕገኙበታል።

ከዚህ በኋላም የተሻለ ጥቅምና እድል የሚያስገኙ በርካታ ተመሳሳይ ጨዋታዎች /የገንዘብ ማግኛ እድሎች/ ወደቴሌግራም መጉረፋቸው የሚቀጥል ሲሆን ለሁላችንም አስቸጋሪ የሚሆነው ከመካከላቸው ጆከሩን መምረጥ ነው።

ሁላችንም በተለያዩ መንገዶች ስለዘርፉ ያለንን ግንዛቤ ማሳደግ ግድ ይለናል። በግሌ ቻናል ከፍቼ የምችለውን ጀምሬያለሁ።

Tapswap ያልጀመራችሁ ካላችሁም ጊዜ አትስጡ - ጀምሩ - Click 👇👇

https://www.tg-me.com/tapswap_mirror_2_bot?start=r_769729488
https://www.tg-me.com/tapswap_mirror_2_bot?start=r_769729488
ጥቆማ‼️

1000 ሺ ሰው ሲሞላ ወደ ስራ እንገባለን‼️
እንዳያመልጣቹ በፍጥነት ተቀላቀሉ👇
https://www.tg-me.com/sheger_crypto

እንዴት ኦንላይን ገንዘብ ማግኘት ይቻላል⁉️
crypto ምንድነው⁉️

የሚሉትን ጥያቄዎች ልንመልስላቹ ነው
አሁን አሁን ቴሌግራም አሪፍ ገንዘብ መስሪያ እየሆነ መቷል።

ታድያ አዲስ በከፈትነው በዚ ቻናል ከ ዜሮ ተነስተን እንዴት ክሪፕቶ እና ኤር ድሮፖችን መስራት እንዳለብን የምንማማርበት የቴሌግራም ቻናል ይሆናል

በዚ ሊንክ ተቀላቀሉ👇👇
https://www.tg-me.com/sheger_crypto
https://www.tg-me.com/sheger_crypto
ሰበር
የኢራን ፕሬዝዳንት እና የውጪ ጉዳይን የያዘች ሄሎከፍተር መከስከሷ ተሰማ።
2024/10/01 15:45:28
Back to Top
HTML Embed Code: