Telegram Web Link
በትግራይ ክልል የቆላ ተምቤን ወረዳ አስተዳደር፣ ከግጭት ማቆም ስምምነቱ ወዲህ ባሉት ወራት ሳይፈነዱ በቀሩ የጦር መሳሪያዎች ሳቢያ ከ100 በላይ ሰዎች እንደሞቱና አካል ጉዳተኛ እንደኾኑ መናገሩን ቢቢሲ አማርኛ ዘግቧል።

የመንግሥት እና የኤርትራ ጦር ከአካባቢው ከወጡ በኋላ፣ በወረዳው በፈንጂ እና ሌሎች በየቦታው በተጣሉ መሳሪያዎች ሳቢያ 112 ንጹሃን ዜጎች የሞትና የመቁሰል አደጋ እንደደረሰባቸው የወረዳው አስተዳደር መናገሩን ዘገባው አመልክቷል። የሞትና የመቁሰል አደጋ ከደረሰባቸው መካከል፣ በርካታ ሕጻናትና ታዳጊዎች ይገኙበታል ተብሏል።

መሬት ውስጥ የተቀበሩ ፈንጂዎችና ያልፈነዱ ተተኳሾች በትምህርት ቤቶች፣ በእርሻና በሕዝብ መሰብሰቢያ ቦታዎች፣ በመጋዘኖች እና ባጠቃላይ ጦርነት በተካሄደባቸው አካባቢዎች ተበታትነው እንደሚገኙ ተገልጧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ህግ ማስከበሩ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት👏👏👏🏿

ዩቲዩበሮቹ በቁጥጥር ስር ዋሉ...🇪🇹👌

ለማህበረሰቡ ወግና ባህል ፍፁም ተቃራኒ የሆነ ሐሰተኛ እና አፀያፊ የፈጠራ ታሪክ እያሰራጩ ህዝብን የሚያደናግሩ ዩቲዩበሮችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታወቀ፡፡

ሃሰተኛ መረጃ እና ከማህበረሰቡ መልካም ባህልና ወግ የተቃረኑ አፀያፊ የፈጠራ ታሪኮችን በማህበራዊ ሚዲያ እያሰራጩ በህዝብ ላይ ውዥንብር እና መደናገርን የሚፈጥሩ ግለሰቦች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ መጥቷል፡፡

ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ አላማ ከመጠቀም ይልቅ ገንዘብ ለማግኘት ሲሉ ብቻ ከእውነት የራቁ መሰረተ ቢስ የፈጠራ አፀያፊ ወሬዎችን እየፈበረኩ በማሰራጨት የህዝብን ደህንነት ስጋት ላይ የሚጥሉ ዩቲዩበሮችን በቁጥጥር ስር ማዋል መጀመሩን የአዲስ አበባ ፖሊስ አስታውቋል፡፡
በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 8 አማረ እና ቤተሰቦቹ በተባለ ህንፃ ላይ ቢሮ ተከራይተው የተለያዩ የዩቲዩብ ገፆችን በመክፈት የማህበረሰቡን ሥነ ልቦና የሚጎዱ የፈጠራ ታሪክ በማሰራጨት የተጠረጠሩ ስድስት ግለሰቦች በህዝብ ጥቆማ እና ፖሊስ ባደረገው ክትትል ተይዘው በየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ምርመራ እየተጣራ ይገኛል፡፡
በቁጥጥር ስር ከዋሉት መካከል መቅደስ መብራት መኮንን የተባለችው ግለሰብ ሮሄ፣ ልዩነት፣ ጣዕም፣ አዲስ አለም፣ ዘይቤ፣ ህይወት፣ እይታ፣ እና ዩኒት ህይወት የተባሉ የዩቲዩብ ገፆችን በመክፈት በስራ አስኪያጅነት ስትመራ የነበረች ናት ተብሏል፡፡

ብሩክ ወርቅነህ ጌታሰው የተባለ ግለሰብ ደግሞ ገፆቹን በምክትል ስራ አስኪያጅነት እና በአስተባባሪነት ሲመራ የነበረ ሲሆን ናትናኤል አበራ በቀለ፣ እየሩሳሌም አስማረ ምህረት እና ምህረት ያሲን ቲጋ የተባሉት ግለሰቦች ደግሞ በፕሮግራም አቅራቢነት እንዲሁም ናትናኤል ዮሃንስ አሸነፍ በካሜራ ባለሙያነት ሲሰሩ የነበሩ መሆናቸው ተገልጿል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የትዳር አጋሬ ገበያ ሄዳ አልተመለሰችም ያለውን ባል በፖሊስ ቁጥጥር ስር ዋለ!

በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ክልል በካፋ ዞን የገዋታ ወረዳ ፖሊስ አዛዥ ረዳት ኢንስፔክተር ዮሐንስ ለገሰ እንደገለፁት ከወረዳ መዳቦ ቀበሌ ተጥርጣሪው ሚያዚያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም ወረዳው ፖሊስ ዘንድ ቀርቦ የትዳር አጋሬና የልጆቼ እናት ሚያዚያ 20 ቀን 2016 ዓ.ም ወደ ገበያ ለግብይት ሄዳ አልተመለሰችም ጉዳዩን ፖሊስ ይወቅልኝ በሚል ቀርቦ ማስመዝገቡ ነው ፡፡

እንደ ፖሊስ አዛዥ ዮሐንስ  ገለፃ ይኸው ግለሰብ ሚያዚያ 23 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 11 ሰዓት ላይ  በድጋሚ ፖሊስ ዘንድ ቀርቦ የጠፋችውን የባለቤቴን አስክሬን ጫካ ውስጥ አገኘው ብሎ ሊያመለክት በመጣበት ፖሊስ በቁጥጥር ስር አድርጎት አስክሬኑን በጥንቃቄ በማንሳት ለህክምና በመላክ መረጃና ማስረጃ ማፈላለጉን አስረድተዋል፡፡

የገዋታ ወረዳ ፖሊስ የወንጀልና ትራፊክ አደጋ የታክቲክ ምርመራ የስራ ሂደት አስተባባሪ ረዳት ኢንስፔክተር ሙሉጌታ መለሰ በበኩላቸው የወንጀል ድርጊቱን ማን ፈፀመ ለምንስ ተፈፀመ የሚለው ጥያቄ ለመመለስ የወረዳው ፖሊስ የምርመራ ቡድን ተዋቅሮ ስራውን ሲጀምር ባል ሚስቴ ጠፋች ብሎ አስመዝግቦ አስክሬኗን አገኘሁ ማለቱ  ወንጀሉን ሳይፈፅም እንዳልቀረ ከውሳኔ ደርሰው ፖሊስ የተጠርጣሪ ደሳለኝ ወርቁ ከገዋታ ወረዳ ፍርድ ቤት የብርበራ ትዕዛዝ በመያዝ በመኖሪያ ቤቱ ውስጥ በተደረገው ብርበራ ለወንጀል የተፈፀመበት የደረቀ ደም ያለበትን አንድ ጦር እና ገጀራ መገኘቱን ጠቁመዋል፡፡

መርማሪው ፖሊስ ግለሰቡ በሰጠው የእምነት ቃል እንዳረጋገጠው ሚስት ገበያ ውላ ስትመለስ ባል በወረዳው መዳቦ ቀበሌ ልዩ ስሙ ጎጀብ ወንዝ ድልድይ አከባቢ ተደብቆ መንገድ በመጠበቅ ሚያዚያ 20 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 7፡00 ሰዓት ላይ አስቀድሞ ለወንጀሉ መፈፀሚያ ባዘጋጀው ገጀራ ቀኝ እጅዋ ላይ መቶ ከሰበረ በኋላ እንዳትጮህ በለበሰችው ጥምጣም በማነቅ በያዘዉ ገጀራ ጭቅሏትዋ ላይ ሦስት ቦታ በመቁረጥ በቀኝ እና  በግራ ጎንዋ ላይ አንድ ጊዜ በመቁረጥ በቀኝ ጡትዋ ላይ  አንድ ጊዜ በመቁረጥ ከባድ ጉዳት በማድረሰ ከገደላት በኋላ የወንጀል ድርጊቱ እንዳይታወቅበት ፖሊስ ዘንድ ቀርቡ ማስመዝገቡን ፖሊስ በምርመራው ማረጋገጡን አስረድተዋል፡፡

የታክቲክ ምርመራ የስራ ሂደት አስተባባሪ ረዳት ኢንስፔክተር ሙሉጌታ መለሰ የወንጀሉ መንስኤ በተመለከተ ጠይቀናቸው ተጥርጣሪው የግል ተበዳይ እና የሁለት ልጆቹ እናት ጋር ዘወትር በመካከላቸዉ ጭቅጭቅ መኖሩን የጠቆመው ፖሊስ የግል ተበዳይ ሟች ከመጀመሪያው ባለቤቷ ጋር በትዳር ሲኖሩ ሶስት ልጆችን ከወለዱ በኃላ ማግባቱንና ሁለት ልጆችን መወለዳቸውን ገልፆ ከቀድሞ ባለቤቷ ጋር ትማግጣለች በሚል ጥርጣሬ በመነሳት ወንጀሉን መፈፀሙን ለፖሊስ የሰጠው የእምነት ቃሉን በወንጀል ስነስርዓት ቁጥር 35 እንዲያረጋግጥ መደረጉን ገልፀዋል፡፡

ፖሊስ በመጨረሻም በተጠርጣርዉ ላይ ያጣራውን የምርመራ መዝገቡ በግለሰቡ የእምነት ቃል፤በህክምና ማስረጃና ለወንጀሉ የተፈፀመበትን ጦርና ገጀራ እግዝቪት በማደራጀት ክስ እንዲመሰረትበት ለዐቃቤ ህግ እንደሚላክ ጨምረው ተናግረዋል ሲል የደቡብ ምዕራብ ፖሊስ ዘገባ ፋስት መረጃ ተመልክቷል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የወጣቶች ቢሮ፣ ዕድሜያቸው ከ15 እስከ 18 የሚኾኑ የክልሉ ታዳጊዎች ከምሥራቅና ደቡብዊ ዞኖች፣ ከሰሜን ምዕራብና ሰሜናዊ የክልሉ አካባቢዎች እንዲኹም ከመቀሌ ትምህርታቸውን እያቋረጡ በብዛት ወደ ባሕረ ሰላጤው አገራት እየተሰደዱ መኾኑን ለዋዜማ ተናግሯል።

የክልሉ ወጣቶች ማኅበር ከመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ጋር በመተባበር በቅርቡ ባካሄደው ጥናት፣ 81 በመቶ ያህል ወጣቶች ሥራ አጥ መኾናቸው እንደተረጋገጠ ዋዜማ ተረድታለች።

በጥናቱ ከታቀፉት ወጣቶች መካከል፣ 40 በመቶዎቹ ከክልሉ የመውጣት ወይም ከአገር የመሰደድ ፍላጎት እንዳላቸው ታውቋል ተብሏል።

@ethio_mereja_news
ዛሬ ይቺን ምድር ከፈጣሪ በታች የቀላቀለችን ፤ አለም ፊቷን ብታዞርብን እሷ ግን በደስታ ምትቀበለን ፤ ለኛ ሁሉ ነገራችን የሆነች ፤ ከአይኗ ብሌን በላይ ምትሳሳልን እናታችን ቀኗ ነው በእርግጥም ሁሉም ቀን እናታችንን ማክበር አለብን ነገርግን ዛሬ ልዩ ቀኗ ነው።

እንኳን ለእናቶች ቀን በሰላም አደረሳችሁ ፤ የእናቶቻችሁን ደስታ ያሳያችሁ ፤

መልካም ቀን!

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጠቅላይ ሚኒስቴሩ አማራ ክልል ገብተዋል

ገዥው ብልፅግና ፓርቲ ትናንት ቅዳሜ በአማራ ክልል በገበታ ለሀገር በለማው ጎርጎራ የዘጠኝ ወራት የስራ አፈፃፀም ግምገማ ማካሄዱን ጠቅላይ ሚንስትሩ በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው ላይ ገልፀዋል።

በክልሉ የተቀሰቀሰው ግጭት ዛሬም በተለያዩ አካባቢዎች ቀጥሎ ባለበት ነው የፓርቲው ከፍተኛ ሃላፊዎች ጎርጎራ የተገኙት።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2016 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና መርሐግብር ይፋ ሆኗል፡፡

መርሐግብሩ ከትግራይ ክልል ውጪ በሁሉም ክልሎች እና በሁለቱም የከተማ አስተዳደሮች በወረቀት እና በበይነ መረብ ፈተናውን ለሚወስዱ ተፈታኞች እንደሚያገለግል የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት አሳውቋል።

2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና:—

ከሐምሌ 3-5/2016 ዓ.ም ለማኅበራዊ ሳይንስ ተፈታኞች

ከሐምሌ 9-11/2016 ዓ.ም ለተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ይሰጣል።

የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

@sheger_press
@sheger_press
በህንድ የአእምሮ ጤና እክል ያለባት ወጣት መለኮታዊ ኃይል አላት በሚል በመመለክ ላይ ትገኛለች

በታሚል ናዱ ግዛት የሂንዱ ከተማ በሆነችው ቲሩቫናማላይ ውስር ሚስጥራዊ ኃይል አላት የተባለችው ግለሰብ የአእምሮ የጤና ችግር ላይ ብትሆንም የሕንድ ማህበረሰብን ግን እያመለካት ይገኛል።

ህንዳውያን በርከት ያሉ አምላክ እና አማልክቶች ያሏቸው ሲሆን የሂንዱ አማልክቶች ሚስጥሮች እና እውነተኛ ህይወት ላይ በርካታ አወዛጋቢ ጉዳዮች ይነሳሉ። ከነዚህ መካከል ቶፒ አማ የምትባለው ኮፍያ የምታደርገው ሴት ብዙ ጊዜ ‘ሲድዳ’ እየተባለች በቅፅል ስም ትጠራለች። ይህችው ግለሰብ አዳኛችን ናት በማለት መመለክ ላይ ትገኛለች። አማኞች ፍፁም የሆነች ብሩህ ፍጡር ናት ይሏታል። ነገር ግን ዓለማዊ አመለካከት ላላቸው ሰዎች የህክምና እርዳታ የምትፈልግ የአእምሮ እክል ያለባት ሴት ናት።

ለአማኞች የሚታየቸው በቲሩቫናማላይ ጎዳናዎች ውስጥ ስትንቀሳቀስ ማንም በማይረዳው ጥንታዊ የታሚልኛ ቋንቋ ስትናገር ሲያዩ፣ ሌሎች ደግሞ ቤት የሌላት ምስኪን ሴት ያለ አላማ ስትቅበዘበዝ እና ስታጉረመርም ትውላለች ይላሉ። ሁሉም ነገር የአመለካከት ጉዳይ በመሆኑ ልዩነቶች መስተናገዳቸው ግድ ሆኗል።ቶፒ አማ የቲሩቫናማላይ ምልክት ከመሆኗ እና ብዙ ተከታዮችን ከመሳቧ በፊት የነበራት ህይወት እንቆቅልሽ ሆኖ በመቆየቱ ለታዋቂነቷ ትልቅ አስተዋፅኦ አበርክቷል።

ሁለት ወጥ ቃላቶችን እንኳን በአንድ ላይ አሰካክታ መናገር አለመቻሏን መለኮታዊ ኃይል ቢኖራት ነው ብለው ህንዳውያኑ እንዲያስቡ አስገዷቸዋል። በህንዳውያኑ የማህበራዊ ድህረ ገፅ ተጠቃሚዎች ዘንድ ቶፒ አማ ከተማዋን እየዞረች የጠጣችውን የቡና ትራፊ የተባረከ መስዋዕት ነው በማለት ሰዎች አንስተው ሲቀምሱ ይታያል። በሌላ በኩል ይህችኑ ሴት የአዕምሮ ጤና ችግር ያለባት ፣ የቆሸሸ ልብስ የለበሰች ፣ ሰውነቷ ከመታጠብ የራቀ እና በአንዳች እክል ውስጥ እንዳለች ማስተዋል ይችላል።

አንድ የኤክስ ተጠቃሚ ባጋራው ፅሁፍ አንዳንዶች በአእምሮ ህመም እየተሰቃየች ነው ብለው የሚያስቡ እና እርዳታ ትሻለች የሚል ሰዎች ቢኖሩም ስለ እርሷ ውዳሴ የሚያቀርቡና የሚዘምሩ በርካቶች መሆናቸውን ፅፏል።ጥልቅ የሆነ መንፈሳዊ ጥበቧ ካልተገለጠልህ እሷን ማግኘት የሚችሉት የታደሉት ብቻ ናቸው ሲሉም አማኞች ይደመጣሉ።

አስደናቂው ጉዳይ የአእምሮ እክል ላይ የምትገኘው ቶፒ አማ በአብዛኛው አምላኪዎቿን ችላ ብላ የእለት ውሎዋብ ስታሳልፍ አንዳች ምስጢራዊ ኃይል እየተገለጠላት ነው ብለው የሚያስቡ አሉ። በዚህም የተነሳ በሄደችበት ቦታ ሁሉ በርካቶች ይከተሏታል።(dagu)
ጎሮ አካባቢ በተከሰተ የእሳት አደጋ 13 የንግድ ሱቆችና በጋራዥ ዉስጥ የነበሩ አምስት ተሽከርካሪዎች ሙሉ በሙሉ ወደሙ


ግንቦት 3 ቀን 2016 ዓ.ም ሌሊት 6:50 በለሚ ኩራ ክፍለ-ከተማ ወረዳ 9 ጎሮ ገብርዔል ቤተክርስቲያን አጠገብ የተነሳዉ የእሳት አደጋ በንብረት ላይ ከባድ ጉዳት ማድረሱን የእሳትና አደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን አስታውቋል።

በእሳት አደጋዉ በቤተክርስቲን ዙሪያ ያሉ 13 የንግድ ሱቆችና በጋራዥ ዉስጥ የነበሩ አምስት ተሽከርካሪዎች ሙሉ ሙሉ የወደሙ እና በጋራዡ ላይ ከባድ ጉዳት ደርሷል።

የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠር 12 የአደጋ መቆጣጠር ተሽከርካሪዎች 66 የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች የተሰማሩ ሲሆን የእሳት አደጋዉን ለመቆጣጠርም 4 :10 ሰዓት መፍጀቱን የኮሚሽኑ የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል።

የአደጋ ጊዜ ሰራተኞች እሳቱን ለመቆጣጠር ባደረጉት ርብርብ እሳቱ ወደ-ቤተክርስቲያኒቱ እንዳይዛመት ማድረግ የቻሉ ሲሆን በጋራዡ የነበሩ ቁጥራቸዉ 15 የሆኑ ተሽከርካሪዎችንም ማዳን ችለዋል።በአደጋዉ በሰዉ ላይ ምንም ጉዳት አልመድረሱን አቶ ንጋቱ ጨምረው ለብስራት ተናግረዋል።

በጋራዡ ውስጥ የነበሩ ተሽከርካሪዎች የያዙት ነዳጅና ሌሎች ፈሳሽ ተቀጣጣዮች እንዲሁም ንግድ ሱቆቹ እሳትን ሊቋቋሙ ከማይችሉ ቆርቆሮና መሰል ግብዓቶች መገንባታቸዉ  ለእሳቱ መባባስ አስተዋጾኦ ማድረጉን አቶ ንጋቱ ተናግረዋል።

የተሽከርካሪ ጥገና አገልግሎት የሚሰጡ ጋራዦች ደረጃቸዉን በጠበቁ ግብዓቶች የተገነቡና ከንግድ ሱቆች ከመኖሪያ አካባቢዎች  የራቁ መሆን እንዳለበት ኮሚሽኑ አስጠንቅቋል።

የአደጋውን መንስኤ ፖሊስ እያጣራ መሆኑን ብስራት ለማወቅ ችሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ባህር ዳር

በአማራ ክልል ርዕሰመዲና በበባህር ዳር ከተማ በአባይ ወንዝ ላይ የተገነባው ድልድይ ጠቅላይ ሚኒስትሩ በተገኙበት በዚህ ሰዓት የምረቃ ስነስርዓቱ እየተከናወነ ነው።

ድልድዩ 380 ሜ ገደማ ርዝመት እና ወደ ጎን 43 ሜ ርዝመት ያለው ሲሆን ድልድዩ ከሚሰጠው የትራንስፖርት አገልግሎት ባሻገር ለባህርዳር ከተማ ተጨማሪ ውበትን ያጎናፀፈ ሆኗል።

@ethio_mereja_news
በኢትዮጵያ ላይ የአውሮፓ ኅብረት ያሳለፈውን ውሳኔ ካልቀየረ መንግሥት ተመጣጣኝ ዕርምጃ እንደሚወስድ አስታወቀ

የአውሮፓ ኅብረት ምክር ቤት ከሳምንት በፊት ለኢትዮጵያውያን የሚደረገውን የቪዛ አሰጣጥ ሒደት ለማጥበቅ ያሳለፈውን ውሳኔ ካልቀየረ፣ መንግሥት ተመጣጣኝ ውሳኔ እንደሚያስተላልፍ አስታወቀ፡፡

የአውሮፓ ኅብረት በቪዛ ጉዳይ በቅርቡ ያሳለፈውን ውሳኔ እንዲሽር ኢትዮጵያ እንደምትፈልግ ጠቅሰው፣ ይህ ካልሆነ ግን ከውሳኔው ጋር የሚጣጣም የራሷን ተመጣጣኝ ዕርምጃ ትወስዳለች ያሉት የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አቶ ነብዩ ተድላ ናቸው፡፡

ቃል አቀባዩ በሳምንታዊ መግለጫቸው የአውሮፓ ኅብረት በኢትዮጵያ ላይ ያሳለፈው የቪዛ ውሳኔ ትክክል እንዳልሆነ በመግለጽ፣ ኢትዮጵያ ለኅብረቱ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቱን በጠበቀ መንገድ ማሳወቋን አስረድተዋል፡፡

ኅብረቱ ወደ አውሮፓ የገቡ ኢትዮጵያውያን ስደተኞችን ወደ አገራቸው በመመለሱ ረገድ ለኢትዮጵያ መንግሥት ተደጋጋሚ ጥያቄዎች ቢያቀርብም፣ ባለሥልጣናት ተገቢውን ምላሽ ባለመስጠታቸው በኢትዮጵያውያን ላይ የቪዛ አሰጣጥ አሠራሩን ማጥበቁን በማስታወቅ ነበር ውሳኔውን ያስተላለፈው፡፡

በአውሮፓ ኅብረት በተለይም ‹‹ሸንገን ቪዛ›› ውስጥ በሚገኙ አገሮች ጥገኝነት የጠየቁ ኢትዮጵያውያን ጉዳያቸው የመኖሪያ ፈቃድ የማያሰጥ ሆኖ ሲገኝ፣ ጉዳዩ በፍርድ ቤት ታይቶ ወደ አገራቸው መመለስ አለባቸው የሚባሉትን ኢትዮጵያ እንድትወስድ በመጠየቁ ምክንያት ውሳኔው መተላለፉን ቃል አቀባዩ ተናግረዋል፡፡

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
የኢትዮጲያ ፕሬስ ድርጅት የትግራይ ትምህርት ቤቶች ሁኔታ በማስመልከት ያጋራው መረጃ ሚዛናዊ አይደለም ሲሉ የትግራይ ትምህርት ቢሮ  ኃላፊ ዶ/ር ኪሮስ ጉዕሽ ተናገሩ

ኃላፊው በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው ባጋሩት መልዕክትም "የኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት ተማሪዎቻችን በረሃብ ምክንያት ከትምህርት ገበታ እያቋረጡ ፤ ጦርነቱ የፈጠረው ተፅዕኖ መምህራኖቻችን መቋቋም አልቻሉም፤ 552 ትምህርት ቤቶች በወራሪዎች ተይዞብናል እዛው ያሉ ልጆቻችንም ለአምስት ዓመታት ከትምህርት ገበታ ርቀዋል፤ የተፈናቀሉ ወገኖቻችን በትምህርት ቤት ስለተጠለሉ የመማር ማስተማሩ ሥራ  ፈተና ሆኖብናል፤ በጦርነቱ ምክንያት የነበሩን ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ወድመዋል፤ በአጠቃላይ ጦርነቱ የትምህርት ስርዓቱ፣ የሰው ሃይላችን እና ትምህርት ቤቶቻችን ሙሉ በሙሉ ወድምው ትምህርት ማስጀመር ተቸግረናል እና እርዱን ብለን መግለጫ ስንሰጥ ተማፅኖቻችን ወደ ህዝብ እንዲድርስ ኣልተባብረም " ብለዋል።

አያይዘውም "አሁን በቅርቡ ከሚያዝያ 2015 እስከ ሚያዝያ 2016 የተሰሩ በጣም ውስን ስራዎች መረጃ ስናወጣ ስኬት የመሰለው ይህ ድርጅት መረጃውን ወስዶ ኣሰራጭቶ ስላአጋጠሙን ችግሮች ምንም ሳይገልፅ አልፏል" ብለዋል።

ኃላፊው አክለውም የተዘረዙት ነጥቦች ለፕሬስ ድርጁቱ ስኬት መስለው የታዩትም በዋነኝነት  ከዓለም ኣቀፍ ግብረ ሰናይ ድርጅቶች፣ በትግራይ ማህበረሰብ እና ከዓለም ባንክ በተገኘ ድጋፍ የተሰሩ ናቸው ያሉ ሲሆን አሁንም ቢሆን ድርጅቱ የህዝብ ከሆነ እንደአገር በሁሉም አቅጣጫ ያሉን ችግሮች በእኩል እንዲያይና የሚያስተላልፈው ዜናው ሚዛናዊ ሆኖ ሊሰራ ይገባል ሲሉ ተደምጠዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ፣ በአማራ ክልል ነፍጥ ያነሱ ታጣቂ ኃይሎች ወደ ሰላማዊ ሕይወት እንዲመለሱ ትናንት በባሕርዳር ተገኝተው በአዲሱ የአባይ ድልድይ ምረቃ ላይ ባደረጉት ንግግር ጥሪ አቅርበዋል።

ዐቢይ በዚኹ ንግግራቸው፣ "በማይገባ ነገር መገዳደል ይብቃ” የሚል መልዕክት አስተላልፈዋል።

ጠቅላይ ሚንስትሩ፣ ታጣቂ ኃይሎች ወደ ሰላም ተመልሰው ከክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ጋር ከሠሩ፣ ፌደራል መንግሥቱም የራሱን ትብብር ለማድረግ ዝግጁ እንደኾነ ገልጸዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
Update

ከሐዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበረዉ አዉሮፕላን ዉስጥ ታይቷል የተባለዉ ጭስ በዉስጡ ያለዉ ዘይት በመቃጠሉ የተነሳ መሆኑ ተገለፀ!

የኢትዮጵያ አየር መንገድ ከሰሞኑ በአዉሮፕላኑ ላይ የተከሰተው ጉዳይን አስመለክቶ እንዳስታወቀው ከእሳት ወይም ከሌላ ነገር ጋር የተያያዘ ሳይሆን አዉሮፕላን ዉስጥ ያለዉ ዘይት ተቃጥሎ ነዉ በወቅቱ የተከሰተው ጭስ ሊፈጠር የቻለዉ ይህም አልፎ አልፎ የሚያጋጥም ችግር ነዉ ብሏል።

የአየር መንገዱ ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ጣሰዉ በተለይ ለካፒታል እንደተናገሩት " በአዉሮፕላኑ ዉስጥ ያለዉ ዘይት መጋጠሉ እና ከእርሱ ጋር ተያይዞ የተፈጠረ ጭስ ነዉ ይህ ደግሞ የተለመደ ነዉ ብለዋል።

የኢትዮጵያ አየር መንገድ በረራ ቁጥር ET154 ሚያዝያ 29፣ 2016 ከሀዋሳ ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ እያለ በአውሮፕላን ውስጥ ጭስ መታየቱን አስታዉቆ እንደነበር ይታወቃል። via Capital

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/06/29 00:58:02
Back to Top
HTML Embed Code: