Telegram Web Link
ኬንያ፣ የኢትዮጵያ እና ሱማሊያን ውዝግብ ለመፍታት ኢጋድ ለውቂያኖስ ሃብቶች አጠቃቀም ቀጠናዊ የስምምነት ማዕቀፍ እንዲነደፍ ሃሳብ ማቅረቧን የአገሪቱ ዜና ምንጮች ዘግበዋል።

ኬንያ፣ ከጅቡቲና ኢጋድ ጋር በመተባበር ያቀረበችው ሃሳብ፣ ወደብ አልባ አገራት ወደቦችን እንዴት መጠቀም እንደሚችሉ የሚገልጽ ነው። ኢትዮጵያ እና ሱማሊያ የመፍትሄ ሃሳቡን እያጤኑት እንደኾነ የኬንያ ባለሥልጣናት መናገራቸውን ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል።

የኬንያ ባለሥልጣናት ይህን የተናገሩት፣ የኬንያው ፕሬዝዳንት ዊሊያም ሩቶ ከሱማሊያው አቻቸው ፕሬዝዳንት ሐሰን ሞሃመድ ጋር ትናንት ናይሮቢ ውስጥ ከተወያዩ በኋላ ነው። [ዋዜማ]

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በኢትዮጵያ የጅምላ ግድያ በአስደንጋጭ ሁኔታ እየተለመደ ነው- አምነስቲ ኢንተርናሽናል‼️

ዓለም አቀፉ የመብቶች ተሟጋች ተቋም አምነስቲ ኢንተርናሽናል በኢትዮጵያ የጅምላ ግድያ መበራከት አሳሳቢ ደረጃ ላይ ደርሷል አለ።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በጥር ወር በአማራ ክልል መራዊ ከተማ የተፈጸመ “የጅምላ ግድያን” አስመልክቶ ባወጣው መግለጫ የመንግስት ቸልተኛነት ለከፋ ጉዳት አጋላጭ ሆኗል በማለት ወቅሷል።

በአማራ ክልል ጥር 21 ዓመታዊ የንግስ ክብረ በዓል በነበረበት ዕለት ከ50 የሚበልጡ ሰዎች መገደላቸውን መረጃ አግኝቻለሁ ያለው የመብት ድርጅቱ፤ ከ20 የሚበልጡ አስክሬኖች በመንገድ ላይ ተጥለው የሚያሳይ የሳተላይት ምስል ዛሬ አጋርቷል።

“የኢትዮጵያ መንግስት ተአማኒነት ያለው ጥረት አለማድረጉ የተገደሉት ቤተሰቦች ፍትህ እንዳያገኙ፣ መሰል ወንጀሎች ለመከላከል እንዳይቻልና ለከፋ ጉዳት የሚያጋልጥ ሆኗል” ሲል አምነስቲ ኢንተርናሽናል መንግስትን ወቅሷል።

ከሦስት ሳምንታት በፊት የመራዊ ጥቃትን በተመለከተ የመጀመሪያ ደረጃ ግኝቶችን ለኢትዮጵያ መንግስት መላኩን ያስታወቀው ድርጅቱ፤ እስካሁን ምላሽ እንዳላገኘ እና እየተጠባበቀ መሆኑን ገልጿል።

አምነስቲ ኢንተርናሽናል በግድያው የኢትዮጵያ መከላከያ ሠራዊት አባላት ለፋኖ የሚዋጉ ሰዎችን ቤት ለቤት በመፈለግ እንደወሰዱ እና አንዳንዶችን ደግሞ ያሉበትን እንዲጠቁሙ በማስገደድ ከቤት እየወሰዱ እንደገደሉ አመልክቷል።

ከአንድ ዓመት በፊት የመንግስታቱ ድርጅት መርማሪዎች ይፋ እንዳደረጉት ከሆነ ለሁለት ዓመታት በጦርነት ውስጥ በቆየው ትግራይ ክልል ብቻ ከፈረንጆቹ 2020 ጀምሮ ከ48 በላይ “ትላልቅ” ግድያዎች ተፈጽመዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በስኳር ህሙማን ማህበር ከ15 ሺ በላይ ህፃናት የመድሀኒት እና ሌሎች ድጋፍ እንደሚደረግላቸው ተገለፀ

በኢትዮጵያ ስኳር ህሙማን ማህበር ፕሮግራም ውስጥ የመድኃኒቶች እና ሌሎች ድጋፍ ከሚደረግላቸው ሰዎች ውስጥ ከ15 ሺ በላይ የሚሆኑት ህፃናት መሆናቸውን የኢትዮጵያየ ስኳር ህሙማን ማህበር አስታውቋል፡፡

በሁሉም ክልሎች በሚገኙ 89 ቅርንጫፎች ለህፃናቶቹ ድጋፍ ይደረጋል። መድኃኒቶቹን ለመውሰድ ከቦታ ቦታ ይዘው የሚጓጓዙ እንዲሁም ደግሞ መድኃኒቶቹ ይዘታቸውን ጠብቀው እንዲጓጓዙ ለማድረግ  የትራንስፖርት ችግር መኖሩን ተገልፆል፡፡

የኢትዮጵያ ስኳር ህሙማን ማህበር የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ኤርሚያስ ገ/ማርያም ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት በማህበሩ ከ25 ዓመት በታች ያሉ ከስኳር ህመም ጋር የሚኖሩ ህፃናት እና ወጣቶች ላይ ልዩ ትኩረት አድርጎ እንደሚሰራ ተናግረዋል፡፡

ማህበሩ ከጤና ተቋማት ጋረ በመሆን ህፃናት እና ወጣቶች የኢንሱሊን፣የላንሴት  ፤ግሉኮሜትር  እና ሌሎችም  መድኃኒቶችን እና መሳሪያዎችን  በነፃ ግብዓቶች ለተለያዩ የህክምና ተቆማት እያደረሰ እንደሆነ ተገልፆል፡፡

ከስኳር ህመም ጋር የሚኖሩ ሰዎች እንዴት መመገብ እና  ኢንሱሊን እራሳቸውን ለመውጋት የሚቸገሩ  ህፃናቶች የመድሀኒቱን የአወሳሰድ  ዝርዝር በየወሩ ለህፃናቱ እና ለቤተሰቦቻቸው የተለያዩ የትምህርት ፕሮግራሞችን በማዘጋጀት የአቅም ግንባታ ላይ እንደሚሰሩ አቶ ኤርሚያስ ገ/ማርያም ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ተናግረዋል፡፡ የኢትዮጵያ ስኳር ህሙማን ማህበር ከተመሰረተ 11 ዓመታት ተቆጥረዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
13 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ውለዋል!!

የምስራቅ ሸዋ ፖሊስ መምሪያ በኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር በቴ ኡርጌሳ ግድያ ጋር በተያያዘ 13 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ።

የምስራቅ ሸዋ ፖሊስ መምሪያ ረዳት ኮሚሽነር ታሪኩ ዲሪባ፤ ግድያውን ለመመርመር የምርመራ ቡድን መቋቋሙን ተናግረዋል።

በአንዳንድ መረጃዎች መሰረት በቁጥጥር ስር ከዋሉት 13 ተጠርጣሪዎች መካከል አንድ የበቴ ወንድም እና እህት ይገኛሉ።

የቤተሰባቸው አባል፤ “የመንግስት የጸጥታ ኃይሎች በሚመስሉ” ሰዎች ማክሰኞ ለሊት ካረፉበት ሆቴል መወሰዳቸውን እና በማግስቱ አስክሬናቸው መንገድ ዳር ተጥሎ መገኘቱን አስታውሶ አዲስ ስታንዳርድ አስነብቧል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ቦሌ የነበረው ተኩስ ‼️

ዛሬ ቦሌ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ ተኩስ ነበር

የተኩሱ መነሻ የጎንደር ፋኖ መሪ የነበረው ናሁሰናይ በመንግሥት የፀጥታ ሀይሎች በመያዙ ምክንያት ነው ተብሏል።

ናሁሰናይን ፖሊስ በቁጥጥር ስር ሊያውለው ሲሞክር ከፀጥታ ኃይሎች ጋር የተኩስ ልውውጥ አድርጓል ያሉ ሲሆን አብረውት ከነበሩት ሁለት ሰዎች ውስጥ አንዱ ወዲያውኑ የሞተ ሲሆን ናሁሰናይ ቆስሎ ቢያዝም ህይወቱ አልፏል ተብሏል። አንደኛው ምንም ሳይሆን ተይዟል ተብሏል።

ከፀጥታ ኃይሎች በኩል አንድ የሞተ ሲሆን የቆሰሉም መኖራቸውን ነው የመረጃ ምንጮቹ የገለፁት።
ከቦሌ SNAP PLAZA እስከ ቦሌ መድሃኒያለም ያለው መንገድ ዝግ ተደርጓል ብለዋል።

@sheger_press
@sheger_press
የሩሲያ ወታደራዊ አስተማሪዎች የጦር ስልጠና ለመስጠት ኒጀር መግባታቸው ተሰማ

ሩሲያ በአስጨናቂው የሳህል ቀጠና የምዕራብ አፍሪካ ተጽኖዋን እያጠናከረች ባለችበት ወቅት የሞስኮ ወታደራዊ አስተማሪዎች ወደ ኒጀር በማቅናት ብሔራዊ ጦሩን ለማሰልጠን ተዘጋጅተዋል።

በኒጀር ዋና ከተማ ኒያሚ የደረሱት ወታደራዊ ስፔሻሊስቶች ከጭነት አውሮፕላን ሲያወርዱ ታይተዋል። “እዚህ የመጣነው የኒጀር ጦርን ለማሰልጠን ነው፤ በሩሲያ እና በኒጀር መካከል ወታደራዊ ትብብርን ለማዳበር እንሰራለን ሲሉ ከአስተማሪዎቹ አንዱ ለኒጀር መንግስታዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ አርቲኤን ተናግረዋል።

ወታደራዊ መምህራኑ የአየር መከላከያ ዘዴን በማምጣት ላይ መሆናቸውን እና ስለ ስርጭቱም ገለጻ አድርገዋል። የአየር መከላከያ ዘዴን ለመጠቀም በቅርቡ የኒጀር ወታደራዊ መንግስት እና ሩሲያ የጸጥታ ትብብርን ለማሳደግ ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ተከትሎ ነው።

በምዕራብ አፍሪካዊቷ ሀገር ኒጀር ባለፈው አመት በመፈንቅለ መንግስት ወታደራዊው ኃይል ስልጣን መቆጣጠሩን ተከትሎ ያለውን ዲፕሎማሲያዊ እና የጦር ትብብርን በተመለከተ ፊቱን ወደ ሩሲያ አዙሯል።

የኒጀር ወታደራዊ መንግስት ከፈረንሳይ ጋር የቆየውን ወታደራዊ እና ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት ያቋረጠ ሲሆን እንደ ጎረቤት ማሊ እና ቡርኪናፋሶ ሁሉ አማፂያንን ለመመከት ድጋፍ ለማግኘት ከሩሲያ ጋር ያለውን ትብብር አጠናክሯል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ኢሚግሬሽን የውልና ማስረጃ ውክልና አልቀበልም በማለቱ እየተጉላላን ነው ሲሉ  ቅሬታ አቅራቢዎች ተናገሩ

የኢትዮጵያ ኢሚግሬሽን የሰነዶች ማረጋገጫ እና ምዝገባ ኤጀንሲ ምዝገባ አገልግሎት  ከሰነዶች ማረጋገጫ እና ውልና ማስረጃን የመጣን የውክልና ወረቀት አልቀበልም ብሎናል ሲሉ ነቻቅሬታ አቅራቢዎች ለብስራት ሬድዮና ቴሌቪዥን ቅሬታቸውን አቅርበዋል።

ነዋሪዎቹ እንደገለፁት የልጆቻችንም ሆነ የእናት አባት ውክልና ይዘን ፓስፓርት ለመቀበል ብንሄድም  ውክልናችሁን አንቀበልም በማለታቸው መጉላላት እንደደረሰባቸው ገልፀዋል።

ብስራት ሬድዮና ቴሌቭዥን ለቅሬታ አቅራቢዎቸ ፓስፓርቱን ለመውሰድ ሌላ አሰራር ተዘርግቷል ወይ የሚል ጥያቄ ያቀረበ ሲሆን አገልግሎቱ አሰራሩን ግልፅ ባለማድረጉ ምክንያት አሁን ላይ ካለው የፓስፓርት ተቀባይ ቁጥር መብዛት እና አሰልቺ ሰልፍ በኃላ ቢሮ ስንገባ ነው ስለ ሁኔታው የሚነገሩን የሚል ምላሽ ሰጥተዋል።

አክለውም የራሳቸውን ውክልና መስጫ ፎርም በማዘጋጀት ቢሮ ቁጥር 11 ወካይም ተወካይም ተገኝቶ ውክልና ፎርም ካልሞላ በሌላ ውክልና ፓስፓርት መውሰድ እንደማንችል ነግረውናል ሲሉ አክለዋል።

በዚህ ጉዳይ ላይ ያነጋገርናቸው የሰነዶች ማረጋገጫና ምዝገባ አገልግሎት የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ሥራ አስፈጻሚ አለምሸት መሸሻ ጉዳዩን እንደማያውቁት እና መስሪያ ቤቶች ለራሳቸው በሚመች ሁኔታ እንደሚሰሩ አንስተዋል።

በጉዳዩ ብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን  የኢትዮጵያ ኢሚግሬሽን እና ዜግነት ምዝገባ አገልግሎት የኮምኒኬሽን ቢሮ በአሰራሩ ዙሪያ ማብራሪያ እንዲሰጠው ያደረገው ጥረት ሊሳካ አልቻለም ።

@sheger_press
@sheger_press
የአይን እማኞች ዛሬ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ በነበረው የተኩስ ልዉዉጥ ሁለት መንገደኞች ጉዳት ደርሶባቸዋል አሉ

ዛሬ ሚሊኒየም አዳራሽ አካባቢ በነበረው የተኩስ ልዉዉጥ በርካቶችን ያስደነገጠ ክስተት ነበር። በዚሁ የተኩስ ልዉዉጥ ወቅት ሁለት ሰዎች የተገደሉ ሲሆን በፖሊስ አባላት ላይም ጉዳት መድረሱን ዳጉ ጆርናል መዘገቡ አይዘነጋም።

በዚሁ ክስተት ህይወታቸዉን ካጡ አንድ መኪናቸዉን በማሽከርከር ላይ ከነበሩ ግለሰብ ዉጪ ሁለት መንገደኞች ላይም ጉዳት መድረሱን እማኞች ተናግረዋል።

ቢቢሲ ያነጋገራቸው የተኩስ ልውውጥ በተፈጸመበት አካባቢ ነዋሪ ከሆኑ አንድ ግለሰብ ሁለት መንገደኞች ላይ ጉዳት መድረሱን ገልጸዋል።

ከዚህ በተጨማሪ የተኩስ ልውውጡ የተፈጸመው ከሚሊኒየም አዳራሽ ጎን በሰንሸይን ቪላ ቤቶች ወደ ቦሌ መድኃኒያለም ወደሚያስወጣ መንገድ ላይ መሆኑን በአካባቢው የነበሩ ሰዎች ለቢቢሲ ተናግረዋል።

የአዲስአበባ ፖሊስ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ ምክትል ኮማንደር ማርቆስ “ናሁሰናይ አንዳርጌ የሚባለው በፖሊስ ቁጥጥር ስር ለማዋል በሚደረገው እንቅስቃሴ እጅ ላለመስጠት ከፍተኛ የሆነ ትግል ነው ያደረገው። ከዚያም አልፎ በዚያ አካባቢ የሚሄድ አንድ ግለሰብ ሕይወት እንዲያልፍ ምክንያት ሆኗል። ሁለት የፖሊስ አባላት ላይ ተኩስ ከፍቶ ከባድ ጉዳት እንዲደርስባቸው ምክንያት ሆኗል” ብለዋል። ሌላ አንድ የግጭቱ ተሳታፊ የነበረ ግለሰብም መገደሉን አረጋግጠዋል።

@sheger_press
@sheger_press
አሜሪካ፣ በሰሜኑ ጦርነት ወቅት ለኢትዮጵያዊያን ስደተኞች የሰጠችውን ጊዜያዊ ከለላ በ18 ወራት አራዝማለች።

በከለላው መራዘም፣ በትንሹ 2 ሺህ 300 ኢትዮጵያዊያን የከለላው ተጠቃሚ መኾን እንደሚቀጥሉና 12 ሺህ 800 ያህል ከሚያዝያ 3 በፊት በአሜሪካ መኖር የጀመሩ ኢትዮጵያዊያን ደሞ ከለላውን ለማግኘት እንዲያመለክቱ ያስችላቸዋል።

አሜሪካ ይህን ርምጃ የወሰደችው፣ በአገሪቱ በሚካሄደው ግጭት ሳቢያ መኾኑን ገልጣለች።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ኢሰመጉ፣ መንግሥት በኦሮሚያና አማራ ክልሎች ከግጭቶች ጋር በተያያዘ በሰላማዊ ሰዎች ላይ የሚፈጸሙ "ግድያዎችን"፣ "ሕገወጥ እስሮችን" እና "ድብደባዎችን" እንዲያስቆምና አጥፊዎችን ለሕግ እንዲያቀርብ ትናንት ምሽት ባወጣው መግለጫ ጠይቋል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ የሰብዓዊ መብት ጥሰት አጣሪ ቦርድም፣ በጥሰቶች ላይ ክትትል በማድረግ አጥፊዎቹ እንዲቀጡ ለሚመለከተው አካል እንዲያቀርብ ኢሰመጉ ጠይቋል።

ኢሰመጉ፣ የጋምቤላ ክልላዊ መንግሥትም በንጹሃን ላይ ጥቃቶችን በሚፈጽሙ ታጣቂዎች ላይ ክትትል አድርጎ ለሕግ እንዲያቀርብ ጥሪ አድርጓል።

ኢሰመጉ፣ የኦነግ አመራር በቴ ኡርጌሳ ግድያን በተመለከተም፣ መንግሥት ድርጊቱ "በገለልተኛ መርማሪዎች" የሚጣራበትን ኹኔታ እንዲያመቻች በመግለጫው ጠይቃል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
ትግራይ‼️

ከተለያዩ የትግራይ አካባቢዎች ተወስደው በኤርትራ ታስረው የነበሩ 46 የትግራይ ተወላጆች ተፈተው በአዲፀፀር በኩል ትናንት ሽራሮ መግባታቸውን ተሰምቷል።

@sheger_press
@sheger_press
18 ሰዓታት በፈጀ  የቀዶ ህክምና 20 ሳ.ሜ ከፍታ ያለው የጭንቅላት እጢ በተሳካ ሁኔታ ተወገደ

18 ሰዓታት በፈጀ የጭንቅላት እጢ በቀዶ ህክምና ማስተካከል መቻሉን የአለርት ኮምፕርሄንሲቭ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል አስታውቋል።በሆስፒታሉ የህዝብ ግንኙነትና ኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ አለምሰገድ ጫኔ ለብስራት ሬዲዮና ቴሌቪዥን እንደተናገሩት በቀዶ ህክምናው ዋና ዋና ተግባራት በጭንቅላቱ ላይ የነበረውን 20 ሳንቲሜትር ከፍታ የለው እብጠት በቀዶ ህክምና እንዲወጣ ተደርጓል ።

አያይዘውም እብጠቱ የወጣበትን ቦታ በሌላ የሰውነት ክፍል የመተካት ተግባር ተከናውኗል።በሶስተኛ ደረጃ ከታካሚው ከተለያዮ የሰውነት ክፍሎች ማለትም ከእጆቹ ላይ ደም ቅዳና ደም መልስ ተመሳሳይ ደም ስሮችን ወደጭንቅላቱ እንዲደርስ ተደርጓል  በማለት ለጣቢያችን ገልፀዋል።

በአራተኛ ደረጃ ደግሞ በቀዶ ህክምና  ወቅት በሰውነት ክፍሉ የደም መፍሰስ ችግር እንዳይኖር አስቀድሞ በቂ ደም የመያዝና  የደም ስሮችን የመቋጠር ተግባር  መከናወኑ ተገልጿል።በመጨረሻም ታካሚው ከ18 ሰአታት በኋላ በፅኑ ህሙማን ክፍል እንደቆየ ተደርጓል ያሉት አቶ አለምሰገድ በአሁኑ ሰአት  በጥሩ የጤንነት ሁኔታ ላይ ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል።

በዚህም የተሳካ ቀዶ ህክምና የተሳተፉ የተለያዩ  ስፔሻሊስቶች ፣  ሰብ ስፔሻሊስት ሀኪሞች፣ አኒስቴትክስ፣ ነርሶች ፣ፖርተሮች እና ፅዳቶች  ሲያከናውኑ የነበሩ የቡድን አባላቶች ስራ እጅግ ከፍተኛ መሆኑ  ተጠቅሷል።ዶ/ር አብዱራዛቅ  የፕላስቲክና ሪኮንስትራክቲቭ ስፔሻሊስት ባለሙያና የማክሮ ሰርጀሪ ሰብ ስፔሻሊስት በዚህ ህክምና ላይ ለተሳተፉ አጠቃላይ ሰራተኞች  ምስጋናቸውን  አቅርበዋል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በጋምቤላ ክልል 14 አመራሮችና አንድ ግለሰብ በህግ ቁጥጥር ስር ዋሉ።

በጋምቤላ ክልል በጆርና በኢታንግ ልዩ ወረዳ ተከስቶ በነበረው የፀጥታ መደፍረስ ምክንያት እጃቸው አለባቸው የተባሉ 14 አመራሮችና አንድ ግለሰብ በህግ ቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ።

የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ኡሞድ ኡሞድ እንዳሉት በቁጥጥር ስር የዋሉት አመራሮችና ግለሰቦች በጆር እና በኢታንግ ልዩ ወረዳ ተፈጥሮ በነበረው የፀጥታ ችግር እጃቸው አለባቸው የተባሉ ናቸው ብለዋል።

በተለይም በመጋቢት 26/2016 ዓመተ ምህረት በጆር ወረዳ ለተከሰተው የሰው ህይወት መጥፋትና ለንብረት መውደም እጃቸው አለባቸው የተባሉ ሁለት የዞን ከፍተኛ አመራሮች እና አምስት የወረዳ አመራሮች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን ገልፀዋል።

ከዚህም በተጨማሪ በኢታንግ ልዩ ወረዳ የሚፈለጉ ተጠርጣሪዎች ለህግ እንዳይቀርቡ እንቅፋት የሆኑ ሰባት የወረዳ አመራሮች በህግ ቁጥጥር ስር ውለው ተገቢው ማጣራት እየተከናወነ መሆኑን አስረድተዋል።

ኮሚሽነሩ አክለውም በተለያዩ መድረኮች በጋምቤላ ከተማ ብሔርን ከብሔር ለማጋጨት የሚሞክር አንድ ግለሰብ ከአመራሮቹ ጋር በቁጥጥር ስር መዋሉንም አስታውቀዋል።

በክልሉ ተከስቶ የነበረው የፀጥታ መደፍረስ ወደ ቀድሞ ሰላሙ እንዲመለስ በየደረጃው የሚገኙ አመራሮች ለሰላም ቅድሚያ ሰጥተው ሊሰሩ እንደሚገባ ኮሚሽነር ኡሞድ ጥሪ አቅርበዋል።

መረጃው የጋምቤላ ክልል የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ነው

@sheger_press
@sheger_press
ፈረንሳይ፣ በኦሮሚያ ክልል መቂ ከተማ ባለፈው ማክሰኞ ተገድለው በተገኙት የኦነግ አመራር በቴ ኡርጌሳ ግድያ ዙሪያ ምርመራ እንዲደረግ ጠይቃለች።

በኢትዮጵያ የፈረንሳይ ኢምባሲ ዛሬ ባወጣው አጭር መግለጫ፣ በበቴ ግድያ ላይ "አስቸኳይ"፣ "ገለልተኛ" እና "ሙሉ" ምርመራ እንዲደረግ፣ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን፣ አውሮፓ ኅብረት እና ሌሎች ዓለማቀፍ አጋሮች ያቀረቡትን ጥያቄ ፈረንሳይ እንደምትጋራው ገልጧል።

ፈረንሳይ፣ በተቃዋሚ ፖለቲከኛው ግድያ ዙሪያ "ፍትህ እና ተጠያቂነት" መስፈኑ አስፈላጊ መኾኑንም ገልጣለች።

የኦሮሚያ ክልላዊ መንግሥት፣ በበቴ ኢርጌሳ ግድያ እጁ እንደሌለበት ገልጦ፣ በግድያው ላይ የወንጀል ምርመራ መጀመሩንና ምርመራው ሲጠናቀቅ ውጤቱን ለሕዝብ ይፋ እንደሚያደርግ ከቀናት በፊት መግለጡ አይዘነጋም።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
በትግራይ ክልል መኾኒ ወረዳ መኾኒ ከተማ የሚገኙ የጦርነት ተፈናቃዮች ዛሬ ጧት የተለያዩ ጥያቄዎችን በማስተጋባት ሰላማዊ ሰልፍ ማድረጋቸውን የክልሉ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

ሰልፈኞቹ፣ የትግራይ እና አማራ ክልሎች ከሚወዛገቡባቸው አላማጣ እና ራያ አካባቢዎች የተፈናቀሉ እንደኾኑ ዘገባው አመልክቷል።

ሰላማዊ ሰልፈኞቹ፣ ከመኾኒ ወደ ኩኩፍቱ ከተማ እና በሪ ተክላይ ባካሄዱት ሰልፍ፣ የትግራይ ግዛታዊ አንድነት እንዲረጋገጥ፣ የአማራ ክልል ታጣቂዎች ከአላማጣና ራያ አካባቢዎች እንዲወጡና ወደ ቀያቸው ባስቸኳይ እንዲመለሱ መጠየቃቸውን ዘገባው ጠቅሷል።

በሪ ተክላይ አካባቢ የሠፈረው የመከላከያ ሠራዊት አዛዦች፣ ለሰልፈኞቹ ንግግር አድርገዋል ተብሏል።

@ethio_mereja_news
ሌላ ጦርነት ፈነዳ‼️

በተፈራው መሰረት ኢራን በእስራኤል ላይ ከፍተኛ የሆነ የሚሳኤልና የአጥፍቶ ጠፊ ድሮኖች ጥቃት ከፍታለች ።

ቀይ ባህርና ሜድትራኒያን ቀጠና ውጥረት ውስጥ ገብቷል ።

በቀጥታ ስርጭቶች እየታየ እንዳለው እስራኤል እንዲሁም አጋሮቿ እንግሊዝና አሜሪካ የኢራንን ጥቃት ሙሉ በሙሉ ኢላማቸውን ከመምታት እንዲከሽፉ መከላከል ይችላሉ ወይ የሚለው ጥያቄ ውስጥ ገብቷል።

ጆ ባይደን ኢራን ላይ ያለንን ጦር መሳሪያ በሙሉ እንጠቀማለን ሲሉ የዛቱ ሲሆን ይህንንም ተከትሎ ዓለም ለኒውክሌር ጦርነት ከምንግዜውም በላይ ቀርባለች ሲሉ ዓለም አቀፍ የዜና አውታሮች እየዘገቡ ይገኛሉ።

@sheger_press
@sheger_press
ኢራን የእስራኤል ቅጣት ተጠናቋል አለች።

ቴህራን ጥቃቱን የመቀጠል ፍላጐት የለኝም ማለቷን ፕሬስ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

የኢራን አብዮታዊ ዘብ ኮማንደር በእስራኤል ላይ የተደረገው ዘመቻ "ከተጠበቀው በላይ ስኬታማ" ነበር ሲል አስታውቋል።

ኢራን በእስራኤል ላይ ቀጥተኛ የሆነ ጥቃት ስታደርስ ይህ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው ተብሏል።

@ethio_mereja_news
@ethio_mereja_news
2024/11/20 08:56:40
Back to Top
HTML Embed Code: