Telegram Web Link
Well come /channel ጦቢያ ግጥምን በጃዝ
የውበት ጀርባው

ላንተ የሚታይህ፤ የሚያምር ፈገግታ
ያበባ  ጉትቻ
ላንተ እሚታይህ ውብ ገፅታ ብቻ
ጥርሷን ጉራማይሌ፤ የተነቀሰች ቀን
ያየቺው መከራ፤ ያየቺው ሰቀቀን
የጆሮዋን ጫፉን ፤ በሾህ  ስትበሳ
የበላችው ፍዳ ፤ ያየቺው አበሳ
የዋጠችው ህመም፤  ከሬት የመረረ
የቀመሰው ማነው፤ከሷ በስተቀረ?  
ከያንዳንዱ ታላቅ ፤ ውበት በስተጀርባ
ሲንዠቀዠቅ ኑሯል ፤ ብዙ ደምና እንባ
ይሄም ታላቅ ዜማ
ይሄም ታላቅ ስእል
ይሄም ታላቅ ተረት
ይሄም ታላቅ ድርሰት
ከፊትህ አልቆመም፤ እንደመና ወርዶ 
ስቃይ ያቃልላል፤ ከስቃይ ተወልዶ ፤ 👍


|በዕውቀቱ ስዪም| @Ethio_Art
@Daves_Art
Best art 😍😍
@Ethio_Art
🇪🇹ጦብያው🇪🇹
ጦብያው ለይቅርታ ቅደም
ቀድመህ እንዳትተው ድገም
ደግሞ ቢያስቀይምህ ሰልስ
ያባትክን አደራ መልስ....❤️
@Ethio_Art
ሥዕል በማሳል ለ ወዳጅ ዘመዶ ስጦታ ያበርክቱ
በ+251707601574
ወይም @DaveidArt ላይ  ፎቶ  በመላክ በ ተመጣጣኝ ዋጋ  ማዘዝ ይችላሉ!


ተጨማሪ ስዕሎችን ለመመልከት ከታች ባለው Link ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
@Daves_Art 🤏
don't judge fast😂😂
😋
@Ethio_Art
ሱሰኛው መነኩሴ Part 1

የኔ ልጅ እባክህ ላስቸግርህ እርዳኝ(መለኩሴው ጫት ከምሸጥበት መደብ ፊት ቆመው
አይ አባ እኛም እኮ ቸግሮናል ኑሮ ውድ ነው(ወደ ኪሴ እየገባሁ
አይደለም ልጄ እኔኮ ብር ፈልጌ አይደለም(ሰው እንዳይሰማ በሹክሹክታ እያወሩ
እሺ ምን ፈልገው ነው አባቴ መንገድ ልጠቁሞት?
አረ በፍፁም፤ዘእኔማ ከዝች ከጫቷ ቆንጠር አድርገህ እንድትሰጠኝ ብዬ ነበር በመሸማቀቅ አይናቸወን ስብር አድርገው
የተቀመጥኩበት ወንበር የሰመጠ ያህል ተሰማኝ ጥያቄያቸውን ተከትሎ አፌን ከፍቼ አይኔን አትጉረጥርጩ ቅንድቤን ሰቅዬ አየኋቸው፡፡ምናልባት ይህን ቃል የሠማሁት አጠገቤ ካለ የጫት ደንበኛዬ እንዲሆን በማሰብ አከባቢዬን ቃኘሁት ግን ሁሉም ተርዚናውን አጭቆ አፉን የሚያላውስ የለም የተናገሩት እኚ መለኩሴ ናቸው ጆሮዬ ነው ግራ በመጋባት ደርቄ ስቀር..
የኔ ልጅ አልሰማከኝም እባክህ ሱስ ሆኖብኝ ነው ሰው ሳያይ ቀስ ብለህ ስጠኝ
ተነስቼ መሮጥ ፈለኩኝ፣አልያም በአስማት ከዛ ቦታ የሚሰልበኝን ተአምር ባገኝ ብዬ ተመኘሁ ግን እፒ በነጭ ቆብና በጥቁር ካባ ያሸበረቁ ለሠማይና ለምድር የከበዱ መልዐክ የሚመስሉ መለኩሴ
አሁንም ከፊቴ ፊትለፊቴ ቆመው በልምምጥ እያዩኝ ነው
አባ ይቅርታ እኔ ለእርሶ አልሸጥም እንዴ ለምን እኔ ሰው አይደለሁ
አይ እርሶ የእግዜር ሰው ኖት ሌላ ቦታ ይሂዱ
ብታቅማ አንተም የእግዜር ልጅ ነህ ግን ደሞ ሱስ ነው የምልከው ልጅ የምልከው ልጅ አጥቼ ብቸገር እንጂ ..
እኚ መለኩሴ ለምን አይሄዱም ደግሞስ እውነት ብሰጣቸው እዚ አደባባይ ላይ ይቀበሉኛል?የሚሆነውን ለማየት እጄ እየተንቀጠቀጠ
አንድ እስር ጫት በፔስታል አድርጌ እየፈራሁ ወደ መለኩሴው እጄን ስዘረጋ....ይቀጥላል

jᵒⁱⁿ⇝ @Ethio_Art
የሚወዱትን ያስሉ ዘመን ተሻጋሪ ስጦታ ያበርክቱ 🎁 (Art)
በተመጣጣኝ ዋጋ
📞 0942041374

@DaveidArt
ሱሰኛው መነኩሴ Part 2

እጄን ስዘረጋ ጎሽ የኔ ልጅ በል እንካ ሂሳብክን(በደስታ እየተፍለቀለቁ
እኔ የእርሶን ብር አልፈልግም ሂዱልኝ ከዚ ቦታ ሁለተኛ እኔ ጋር እንዳይመጡ!
እኚ መለኩሴ ዛሬ ምነው ሚስማር ካልዘነበ መብረቅ ካልወረደ አሉሳ
ንዴቴ አናቴ ላይ ወጥቶ አንባረቅኩባቸው የማየው የምሰማው ነገር ድብልቅልቅ አለብኝ እወነት ግን ለምን ተናደድኩ? እኚ ሰው ቆብ ያድርጉ እንጂ እንደኔ ሰው አደሉ ደሞስ እኔ ማን ሆኜ ነው ምወቅሳቸው? ምናልባትም አንዱ የቸገረው ዱርዬ ጫት መቃም ፈልጎ የፈጠረው ድራማ ቢሆንስ? ጭንቅላቴን በጥያቄ ወጥሬ ያልተሸጠ ጫቴን እያስተካከልኩ መልሶ የሚጥል ድንጋጤ ወረረኝ...እኛ ጫት ካልሰጠከኝ እያሉ ሲነታረኩኝ የነበሩት መለኩሴ ለጫት ሲንገበገቡ መስቀላቸውን የጫት መሸጫዬ ላይ ጥለውት
ሄደዋል!!
ድንጋጤ ቅፅበታዊ ሲሆን ፍርሀት ትከሻ ሲወዘወዝ የገጠመኝ በዚህ ቀን ነበር ፍርሀት የማያውቀኝ ሰውዬ እየተርበተበትኩ መስቀሉን አንስቼ እኛ መዘዘኛ መለኩሴ ወደሄዱበት አቅጣጫ ከነፍኩ..ደርሼባቸው በእጄ የያዝኩትን መስቀል እስክሰጣቸው ልቤ ቆሟል ከኋላ አውሬ የሚያባርረኝ ያህል እየተሰባበርኩ ስሮጥ ከሩቁ አባ መቋሚያቸውን እያስቀደሙ ሲራመዱ አየኋቸው ግን እንደ እብድ ብጮኽ አባ ብል አይሰሙም የምርቃና ሰአታቸው ደርሷል... አባ አባቴ ይቁሙ አጠገባቸው ደርሼ ትንፋሼ እየተቆራረጠ ጠራኋቸው አባ የቤ/ክኑ በር ላይ ደርሰው እየተሳለሙ ጥሪዬን ሰምተው በድንጋጤ ዞር አሉ አቤት ምን አጣህ ምን ፈለክ?በቁጣ ግንባራቸውን ቋጥረው እያዩኝ
አረ እኔ መስቀሎትን ጥለው...በፍርሀት እያየኋቸው
በል ና እዚህ ጥሩ አይደለም ውስጥ እቀበልሀለው አሉኝ
እኚ ሰው ዛሬ ለምን አይተወኝም ገብቼ ደሞ እንቃም ሊሉ ነው፣ደሞስ ጫቱን ወደ ቤ/ክ ይዘው ሲገቡ አያፍሩም በዛ ሁሉ ድካም ውስጥ
ይሄ ሀሳብ አእምሮዬ ላይ ሲያቃጭል ዘገነነኝ።ግን አማራጭ ስለሌለኝ
ተከትያቸው ቤ/ክኑን አልፈን እስከ ቤታቸው አደረስኳቸው ና እስቲ አረፍ በል ቆንጆ ምሳ አለ
አረ አባ መስቀሉን ይቀበሉኝ እኔ ለዚ ቦታ አልገባም ልሂድ ስላቸው ....ይቀጥላል

jᵒⁱⁿ⇝ @Ethio_Art
የታዋቂ ሰዓሊያንን ስዕል ለማየት እና ስዕል ለመግዛት ቻናላችንን ይቀላቀሉ ለሚወዱትም ያጋሩ ❇️link (ማስፈንጠሪያውን) ይጫኑ 👉 @Ethio_Art
0707601574
2024/09/28 22:28:07
Back to Top
HTML Embed Code: