Telegram Web Link
Channel created
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ረመዷን

በአላህ ስም እጅግ በጣም ሩኅሩህ እጅግ በጣም አዛኝ በሆነው፡፡

2፥183 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *”ጾም በእነዚያ ከእናንተ በፊት በነበሩት ላይ እንደ ተጻፈ በእናንተም ላይ ተጻፈ፥ ልትጠነቀቁ ይከጀላልና”*፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ كُتِبَ عَلَيْكُمُ ٱلصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ

“ሰውም” صَوْم ወይም “ሲያም” صِيَام የሚለው ቃል “ተሱም” يَصُمْ ማለትም “ታቀብ” ከሚል ትእዛዛዊ ግስ የመጣ ሲሆን “መታቀብ” ማለት ነው፥ ይህ ቋንቋዊ ፍቺው ሲሆን “ሰውም” صَوْم ወይም “ሲያም” صِيَام በግርድፉና በሌጣው ደግሞ “ጾም” ማለት ነው። አንድ ሰው ምንም ነገር ሳይቀምስ ሲቀር “ጾሙን ዋለ” ይባላል፥ ያ ማለት ከምግብና ከመጠጥ “ተከለከለ” አሊያም “ተቆጠበ” ማለት ነው። ጾም ማለት “መከልከል” ወይም “መቆጠብ” መሆኑን የምናውቀው የአለመናገር ተቃራኒ የሆነውን “ዝምታን” ለማመልከት “ሰውም” صَوْم የሚለው ቃል አገልግሎት ላይ ውሏል፦
19፥26 «ብይም፣ ጠጭም፣ ተደሰችም፡፡ እኔ ለአልረሕማን *”ዝምታን ተስያለሁ”*፤ ዛሬም ሰውን በፍጹም አላነጋግርም» በይ፡፡ فَكُلِي وَاشْرَبِي وَقَرِّي عَيْنًا ۖ فَإِمَّا تَرَيِنَّ مِنَ الْبَشَرِ أَحَدًا فَقُولِي إِنِّي نَذَرْتُ لِلرَّحْمَـٰنِ صَوْمًا فَلَنْ أُكَلِّمَ الْيَوْمَ إِنسِيًّا

መርየም “ሰውማ” صَوْمًا ማለትም “ዝምታ” ስትል ከንግግር መቆጠቧን ካመለከተ ጾም ማለት ከምግብና ከመጠጥ መከልከል እንጂ ከስጋ እና ከስጋ ተዋእፆ ከሆኑት እንቁላል፣ ወተት፣ አይብ እየተቆጠቡ ነገር ግን በእጅ አዙር የስጋ፣ የእንቁላል፣ የወተት ምትክ የሆኑትን ባቄላ፣ አተር፣ በቆሎ፣ ገብስ የመሳሰሉት በሳይክል ተዙሮ የማያልቀውን ቡፌ መብላት አይደለም። ጾም ከምግብና ከመጠጥ ብቻ ሳይሆን ከሚታይ፣ ከሚሰማ፣ ከሚታሰብ ነገር መቆጠብን እንደሚጨም በቋንቋ ሙግት አይተናል።

አምላካችን አላህ ጾምን መጾም ያለባቸው ያመኑትን ምዕምናን ብቻ መሆናቸው ለማመልከት፦ “እናንተ ያመናችሁ ሆይ” በሚል መርሕ ስለ ጾም ይናገራል፦
2፥183 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *”ጾም በእነዚያ ከእናንተ በፊት በነበሩት ላይ እንደ ተጻፈ በእናንተም ላይ ተጻፈ፥ ልትጠነቀቁ ይከጀላልና”*፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ كُتِبَ عَلَيْكُمُ ٱلصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ

“ከእናንተ በፊት በነበሩት” የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት፥ ከእኛ በፊት የነበሩት ነቢያትና ተከታዮቻቸው ናቸው፦
42፥3 እንደዚሁ አሸናፊው ጥበበኛው አላህ *”ወደ አንተ ያወርዳል፡፡ ወደ እነዚያም ከአንተ በፊት ወደ ነበሩት አውርዷል”*፡፡ كَذَٰلِكَ يُوحِي إِلَيْكَ وَإِلَى الَّذِينَ مِن قَبْلِكَ اللَّهُ الْعَزِيزُ الْحَكِيمُ
39፥65 ብታጋራ ሥራህ በእርግጥ ይታበሳል፡፡ በእርግጥም ከከሓዲዎቹ ትኾናለህ ማለት *”ወደ አንተም ወደ እነዚያም ከአንተ በፊት ወደነበሩት በእርግጥ ተወርዷል”*፡፡ وَلَقَدْ أُوحِيَ إِلَيْكَ وَإِلَى الَّذِينَ مِن قَبْلِكَ لَئِنْ أَشْرَكْتَ لَيَحْبَطَنَّ عَمَلُكَ وَلَتَكُونَنَّ مِنَ الْخَاسِرِينَ

ስለዚህ ጾም የተደነገገው ከነቢያችን”ﷺ” በፊት በነበሩትም ነቢያት ጭምር ነው፥ “ኩቲበ” كُتِبَ ማለት “ተደነገገ” “ተደነባ” “ታዘዘ”prescribed” ማለት ነው። ጾም የምንጾምበትን ምክንያት ደግሞ ለማመልከት፦ “ተቅዋ ታገኙ ዘንድ ነው” ይለናል፦
2፥183 እናንተ ያመናችሁ ሆይ! *”ጾም በእነዚያ ከእናንተ በፊት በነበሩት ላይ እንደ ተጻፈ በእናንተም ላይ ተጻፈ፥ “ልትጠነቀቁ ይከጀላልና”*፡፡ يَٰٓأَيُّهَا ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ كُتِبَ عَلَيْكُمُ ٱلصِّيَامُ كَمَا كُتِبَ عَلَى ٱلَّذِينَ مِن قَبْلِكُمْ لَعَلَّكُمْ تَتَّقُونَ

“ተተቁን” تَتَّقُون ማለት “መፍራት” ማለት ነው። ጾም የምንጾምበት ምክንያቱ አንደኛውና ዋናው አምላካችን አላህ ስላዘዘን ሲሆን ሁለተኛውና ተከታዩ ምክንያት “ተቅዋ” ለማግኘት ነው፥ “ይከጀላልና” ተብሎ የተቀመጠው ቃል “ለዐለኩም” لَعَلَّكُمْ ሲሆን “ለዐለኩም” በሚለው ቃል ላይ መነሻ ቅጥያ ሆኖ የመጣው ቃል “ለዐል” لَعَلّ ነው። “ለዐል” ማለት “ዘንድ” so that” ማለት ሲሆን ምክንያታዊ መስተዋድድ ሆኖ የገባ ነው። ስለዚህ የምንጾምበት ምክንያት አካልን ከሚበላና ከሚጠና በመከልከል እራስን ሙሉ ለሙሉ ለዒባዳህ በመስጠት “አላህን ለመፍራት” ነው፥ “ተቅዋ” َتَقْوَى ማለት “አላህ መፍራት” ሲሆን “ሙተቂን” مُتَّقِين ደግሞ አላህ የሚፈራው “ፈሪሃን” ነው። የጾም ድባቡ እራሱ ተቅዋ ያዘለ ዘርፈ ብዙ የአምልኮ መርሃ-ግብር ነው። ሌላው የምንጾምበት ሦስተኛ ምክንያት አላህ በመጠነ-ሰፊ አምልኮ ልናከብረውና ልናመሰግነው ነው፦
2፥185 ቁጥሮችንም ልትሞሉ አላህንም ቅኑን መንገድ ስለመራችሁ *”ታከብሩት እና ታመሰግኑት ዘንድ ይህን ደነገግንላችሁ”*፡፡ وَلِتُكْمِلُوا الْعِدَّةَ وَلِتُكَبِّرُوا اللَّهَ عَلَىٰ مَا هَدَاكُمْ وَلَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ

“ታከብሩት እና “ታመሰግኑት” ዘንድ የሚለው ኃይለ-ቃል ይሰመርበት። “ተክቢር” تَكْبِير በአምልኮ “አሏሁ አክበር” اَللّٰهُ أَكْبَرْ ማለት ሲሆን “ሊቱከብሩ” َلِتُكَبِّرُوا ማለት ይህንኑ ያሳያል። “ተሽኩር” تَشْكُر በአምልኮ አላህ የምናመሰግንበት ነው፥ አላህ “ሻኪር” شَاكِر ማለትም “ተመስጋኝ” ሲሆን ባሮቹ ደግሞ “ሸኩር” شَكُور ማለት እርሱን “አመስጋኝ” ናቸው፥ “ተሽኩሩን” تَشْكُرُون ማለቱ ይህንን ያሳያል። አላህ እንድናከብረውና እንድናመሰግነው ጾምን ደነገገልን።
👉በመቀጠል በሽተኛና መንገደኛ በፆም ወቅት መፆም እንደሌለበትና እንዴት ቀዳ ማውጣት እንዳለበት ይነግረናል፦
2፥184 የተቆጠሩን ቀኖች ጹሙ፡፡ *”ከእናንተም ውሰጥ “በሽተኛ ወይም በጉዞ ላይ የኾነ ሰው” ከሌሎች ቀኖች ቁጥሮችን መጾም አለበት፡፡ “በእነዚያም ጾምን በማይችሉት ላይ ቤዛ ድኻን ማብላት አለባቸው፡፡ ቤዛን በመጨመር መልካምንም ሥራ የፈቀደ ሰው እርሱ ፈቅዶ መጨመሩ ለርሱ በላጭ ነው፡፡ መጾማችሁም ለእናንተ የበለጠ ነው፥ የምታውቁ ብትኾኑ ትመርጡታላችሁ”*፡፡ أَيَّامًا مَّعْدُودَاتٍ ۚ فَمَن كَانَ مِنكُم مَّرِيضًا أَوْ عَلَىٰ سَفَرٍ فَعِدَّةٌ مِّنْ أَيَّامٍ أُخَرَ ۚ وَعَلَى الَّذِينَ يُطِيقُونَهُ فِدْيَةٌ طَعَامُ مِسْكِينٍ ۖ فَمَن تَطَوَّعَ خَيْرًا فَهُوَ خَيْرٌ لَّهُ ۚ وَأَن تَصُومُوا خَيْرٌ لَّكُمْ ۖ إِن كُنتُمْ تَعْلَمُونَ

የምንጾምበት ወር ደግሞ በረመዷን ወር ነው፦
2፥185 *”እንድትጾሙ የተጻፈባችሁ ያ በእርሱ ውስጥ ለሰዎች መሪ ከቅን መንገድ እና እውነትን ከውሸት ከሚለዩም ገላጮች አንቀጾች ሲኾን ቁርኣን የተወረደበት የረመዳን ወር ነው፡፡ ከእናንተም ወሩን ያገኘ ሰው ይጹመው”*፡፡ شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ هُدًى لِّلنَّاسِ وَبَيِّنَاتٍ مِّنَ الْهُدَىٰ وَالْفُرْقَانِ ۚ فَمَن شَهِدَ مِنكُمُ الشَّهْرَ فَلْيَصُمْهُ ۖ وَمَن كَانَ مَرِيضًا أَوْ عَلَىٰ سَفَرٍ فَعِدَّةٌ مِّنْ أَيَّامٍ أُخَرَ ۗ يُرِيدُ اللَّهُ بِكُمُ الْيُسْرَ وَلَا يُرِيدُ بِكُمُ الْعُسْرَ وَلِتُكْمِلُوا الْعِدَّةَ وَلِتُكَبِّرُوا اللَّهَ عَلَىٰ مَا هَدَاكُمْ وَلَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ

የወር ስሞች ቅደም ተከተል፡-
1ኛው ወር- ሙሐረም
2ኛው ወር- ሰፈር
3ኛው ወር- ረቢዑል-አወል
4ኛው ወር- ረቢዑ-ሣኒ
5ኛው ወር- ጀማዱል-አወል
6ኛው ወር- ጀማዱ-ሣኒ
7ኛው ወር- ረጀብ
8ኛው ወር- ሻዕባን
9ኛው ወር- ረመዷን
10ኛው ወር- ሸዋል
11ኛው ወር- ዙል-ቀዒዳህ
12ኛው ወር- ዙል-ሒጃህ ናቸው።
የተቆጠሩ ቀኖች የያዘው ረመዷን 9ኛው ወር ሲሆን ይህ ወር የሚጾምበት ምክንያት ቁርኣን ከጥብቁ ሰሌዳ ወደ ቅርቢቱ ሰማይ የወረደበት ወር ስለሆነ ነው። ረመዷን የወር ስም እንጂ የጾም ስም አይደለም። “ረመዷን” رَمَضَان ማለት “ድርቀት” “ሞቃታማ” ማለት ነው።

ነገር ግን በክርስትና ያሉት ሰባቱ አፅማዋት ማለትም ፅጌ፣ ገና፣ ነነዌ፣ ሁዳዴ፣ ሰኔ፣ፍልሰታ እና እሮብና አርብ የቤተክርስቲያን መሪዎች ቀስ በቀስ በጊዜ ሂደት የደነገጓቸው ሰው ሠራሽ ሕግ እንጂ የመለኮት ትእዛዞች አይደሉም። የነነዌ ጾምም ለነነዌ ሰዎች ለሶስት ቀን የተሰጠ እንጂ አማኞች እንዲጾሙ የታዘዘበት አንቀጽ አይደለም።
በእርግጥም አላህ ለቀደሙት ነቢያት የጾም መርሕ ደንግጎ እንደነበር በተከበረ ቃሉ ነግሮናል። ነገር ግን የአላህ ጥንታዊ ነቢያት የተሰጣቸው ወሕይ የተዋቀረበት አንጓ፣ የተናገሩበት ቋንቋ፣ የመልዕክቱ ምጥቀት ሆነ የቃላቱ ልቀት በዘመናችን እንደሌሉ የታሪክ ምሁራን ያትታሉ፥ ምክንያቱም ከመለኮት የመጣውን እውነት ከሰው ትምህርት ጋር በመጨመር ቀላቅለውታል፤ ከመለኮት የመጣውን እውነት በመቀነስ ደብቀውታል። በዚህም ጾም መቼ እንደሚፃም፣ እንዴት እንደሚፆም፣ ለምን እንደሚፆም፣ ከምን እንደሚጾም ሥረ-መሠረታዊ ጭብጥ በባይብል የለም።

በቁርኣን ግን እነዚህ ምክንያቶች ተገልጸዋል። በጾም ማፍጠሪያ ጊዜ መብላት መጠጣት ብቻ ሳይሆን ከሃላል ጥንድ ጋር ተራክቦ ማድረግም ተፈቅዷል፥ መግሪብ አዛን ካለበት እስከ ፈጅር የኾነው ነጩ ክር የተባለው ብርሃን ጥቁሩ ክር ከተባለው ጨለማ እስከሚለይ ድረስ የፈለግነውን የምግብ አይነት እንድንመገብ አምላካችን አላህ ፈቅዶልናል፦
2፥187 *“በጾም ሌሊት ወደ ሴቶቻችሁ መድረስ ለእናንተ ተፈቀደላችሁ፡፡ እነርሱ ለናንተ ልብሶች ናቸው፤ እናንተም ለእነርሱ ልብሶች ናችሁ፡፡ አላህ እናንተ ነፍሶቻችሁን የምትበድሉ መኾናችሁን ዐወቀ፡፡ በእናንተም ላይ ተመለሰላችሁ፤ ከእናንተም ይቅርታ አደረገ፡፡ አሁን ተገናኙዋቸው፡፡ አላህም ለእናንተ የጻፈላችሁን ነገር ልጅን ፈልጉ፡፡ “ከጎህ የኾነው ነጩ ክርም ከጥቁሩ ክር ለእናንተ እስከሚገልጽላችሁ ድረስ ብሉ፤ ጠጡም”፡፡ ከዚያም ጾምን እስከ ሌሊቱ ድረስ ሙሉ”*፡፡ أُحِلَّ لَكُمْ لَيْلَةَ الصِّيَامِ الرَّفَثُ إِلَىٰ نِسَائِكُمْ ۚ هُنَّ لِبَاسٌ لَّكُمْ وَأَنتُمْ لِبَاسٌ لَّهُنَّ ۗ عَلِمَ اللَّهُ أَنَّكُمْ كُنتُمْ تَخْتَانُونَ أَنفُسَكُمْ فَتَابَ عَلَيْكُمْ وَعَفَا عَنكُمْ ۖ فَالْآنَ بَاشِرُوهُنَّ وَابْتَغُوا مَا كَتَبَ اللَّهُ لَكُمْ ۚ وَكُلُوا وَاشْرَبُوا حَتَّىٰ يَتَبَيَّنَ لَكُمُ الْخَيْطُ الْأَبْيَضُ مِنَ الْخَيْطِ الْأَسْوَدِ مِنَ الْفَجْرِ ۖ ثُمَّ أَتِمُّوا الصِّيَامَ إِلَى اللَّيْلِ ۚ وَلَا تُبَاشِرُوهُنَّ وَأَنتُمْ عَاكِفُونَ فِي الْمَسَاجِدِ ۗ تِلْكَ حُدُودُ اللَّهِ فَلَا تَقْرَبُوهَا ۗ كَذَٰلِكَ يُبَيِّنُ اللَّهُ آيَاتِهِ لِلنَّاسِ لَعَلَّهُمْ يَتَّقُون

አላህ የሚጾመውን ወንድ ባሪያውን “ሷኢሚን” صَّآئِمِين ሲላቸው የምትጾመውን ሴት ባሪያውን ደግሞ “ሷኢማት” صَّآئِمَٰت ብሎ ይጠራቸዋል። አላህ ሷኢሚን እና ሷኢማት ከሚላቸው ባሮቹ ያድርገን! አሚን።

ከወንድም ሳኒ ዑመር


ወሠላሙ ዐለይኩም
አፍጡር ላይ የሚባል

ذَهَبَ الظَّمَأُ وَابْتَلَّتِ الْعُرُوْقُ وَثَبَتَ اْلأَجْرُ إِنْ شَاءَ اللهُ.

‘ዘሐበዝዘመኡ ውበተልለቲል ዑሩቁ፣ ወሠበተል አጅሩ ኢንሻአልላህ  ጥማችን ተቆርጧል፡፡ የደም ሥሮቻችን ረጥበቃል፡፡ የአላህ ፈቃድ ከሆነ ምንዳም ተረጋግጦልናል፡፡ ’

اَللَّهُمَّ إِنِّيْ أَسْأَلُكَ بِرَحْمَتِكَ الَّتِيْ وَسِعَتْ كُلَّ شَيْءٍ أَنْ تَغْفِرَ لِيْ.

‘አልሏሁምመ ኢንኒ አስአሉከ ቢራህመቲከ አልለቲ ወሲዐት ኩልለ ሸይኢን አንተግፊርሊ , አላህ ሆይ! ምህረትን ትለግሰኝ ዘንድ ሁሉንም ነገር ባዳረሰችው እዝነትህ እማፀንሐለሁ፡፡’
🚫 ቁርኣንን በተመለከተ በሙስሊሞች መካከል የተንሰራፉ ስህተቶች 🚫

بسم الله الرحمن الرحيم

1⃣. ቁርኣንን ተቀርቶ ሲጨረስ "ሰደቀላሁል አዚም" ማለት

قال الشيخ الفوزان حفطه الله

«لم يرد أن النبي ﷺ ولا أحدًا من صحابته أو السلف الصالح كانوا يلتزمون بهذه الكلمة بعد الانتهاء من تلاوة القرآن‏.‏ فالتزامها دائمًا واعتبارها كأنها من أحكام التلاوة ومن لوازم تلاوة القرآن يعتبر بدعة ما أنزل به من سلطان‏.»

📙 المنتقى من فتاوى الشيخ الفوزان

ቁርዓን ተቀርቶ ሲጨረስ "ሰደቀላሁል አዚም" አይባልም። የነብዩ ﷺ አልሰሩትም፣ ሰሃባዎች አልሰሩትም፣ ሰለፎች አያውቁትም ሁሌ ተያይዝዞት እንደ ቁርኣን ኣዳብና አሕካም ማድረጉ ቢደዓ ነው።

2⃣. ቁርኣንን ተቀርቶ ሲጨረስ መሳም

قال الشيخ ابن عثيمين رحمه الله

«تقبيل المصحف بدعة لأن هذا المقبل إنما أراد التقرب إلى الله عز وجل بتقبيله ومعلوم أنه لا يتقرب إلى الله إلا بما شرعه الله عز وجل ولم يشرع الله تعالى تقبيل ما كتب فيه كلامه وفي عهد النبي ﷺ كتب المصحف كتب القرآن لكنه لم يجمع إنما كتب فيه آيات مكتوبة ومع ذلك لم يكن يقبلها صلى الله عليه وعلى آله وسلم ولم يكن الصحابة يقبلونه فهي بدعة وينهى عنها بعض الناس أيضا أرى يقبله ويضع جبهته عليه كأنما يسجد عليه وهذا أيضا منكر»

«በዚህ ርእስ (ቁርኣንን በመሳም) ላይ ትክክለኛው አቋም ቢድዓ መሆኑ ነው። ስለዚህ ይህን መተግበር ይከለከላል።
አምልኮን በማሰብ ይህን መሰል ተግባር መፈፀም ውግዝ መሆኑ እርግጥ ነው።»

📙 [سلسلة فتاوى نور على الدرب
الشريط رقم [373]]

💥 በዚህ ዙሪያ [ቁርኣንን ተቀርቶ ሲጨረስ] ነብያዊ ፈለግ ምንድነው ታዲያ ?

"ሱብሃነከላሁመ ወቢሃምዲከ አሽሀዱ አን–ላኢላሃ ኢላ አንተ አስተግፊሩከ ወአቱቡ ኢለይክ" ነው የሚባለው። መረጃው ⤵️

عن عائشة رضي الله عنها قالت :
(ما جلس رسول الله ﷺ مجلسًا قط ، و لا تلا قرآنًا ، و لا صلى صلاة إلا ختم ذلك بكلمات ، قالت: فقلت : يارسول الله! أراك ما تجلس مجلسًا ، و لا تتلوا قرآنًا ، و ولا تصلي صلاة إلا ختمت بهؤلاء الكلمات ؟ قال: نعم، من قال خيًرا خُتِم له طابع على ذلك الخير ، و من قال شرًا كُنّ له كفارة: سبحانك الله و بحمدك لا إله إلا أنت أستغفرك و أتوب إليك).»

وقد ذكره العلامة الألباني-رحمه الله- في السلسلة الصحيحة في بحثه للحديث رقم 3164.

«ዓኢሻ ማንኛውም ቦታ ተቀምጠህ ፣ ቁርአንም አንብበህ ፣ ሶላትም ሰግደህ ስትጨርስ ይህን ዚክር ሰትል አይሃለሁ ለምንድን ነው ብላ ስትጠይቅ ነብዩም ﷺ ጥሩ ለሰራ መልካም መቋጫ ፣ ሸር ለፈጸም ደግሞ ማካካሻ ስለሆነ ነው ብለው መለሱላት»


📮 ኢማሙ ነሳኢ

باب ما تُختم به تلاوة القرآن

በሚል ርዕስ (ሱነኑ ነሳኢ አል-ኩብራ) በዚህ ሐዲስ ባብ አስቀምጧል።

📮 ይህ ዚክር በጣም አስፈላጊ ከመሆኑ ጋር የተረሳ ሱና ሁኗል ።

3⃣. ቁርኣን እየቀሩ ጭንቅላትን ማወዛወዝ ወደ ፊት ወደ ሃላ ወደ ግራ ወደ ቀኝ ይህ ፈጠራ ከመሆኑ ተጨማሪ ከየሁዳጋ መመሳሰል አለበት።

قاﻝ ﺑﻜﺮ ﺃﺑﻮ ﺯﻳﺪ رحمه الله:

«ﺍﺷﺘﺪﺕ ﻛﻠﻤﺔ ﻋﻠﻤﺎﺀ ﺍﻷﻧﺪﻟﺲ ﻓﻲ ﺍﻟﻨﻜﻴﺮ ﻋﻠﻰ:ﺍﻟﺘﻤﺎﻳﻞ , ﻭﺍﻻﻫﺘﺰﺍﺯ , ﻭﺍﻟﺘﺤﺮﻙ , ﻋﻨﺪ ﻗﺮﺍﺀﺓ ﺍﻟﻘﺮﺁﻥ , ﻭﺃﻧﻬﺎ ﺑﺪﻋﺔ ﻳﻬﻮﺩ , ﺗﺴﺮﺑﺖ ﺇﻟﻰ ﺍﻟﻤﺸﺎﺭﻗﺔ ﺍﻟﻤﺼﺮﻳﻴﻦ , ﻭﻟﻢ ﻳﻜﻦ ﺷﻲﺀ ﻣﻦ ﺫﻟﻚ ﻣﺄﺛﻮﺭﺍً ﻋﻦ ﺻﺎﻟﺢ ﺳﻠﻒ ﻫﺬﻩ ﺍﻷﻣﺔ» 📙 "ﺑﺪﻉ ﺍﻟﻘﺮﺍﺀ" ﺹ43 : 44

4⃣ . ወደቁርኣን አቅጣጫ እግሮችን መዘርጋት ይህ የተጠላ ይልቁንም ከፊል ኡለማዎች ዘንድ ሐራም ነው። ለምን ቁርኣንን ልናከረው የግድ ነው። እግሮችን ወደሱ መዘርጋት ማክበር አይባልም።

قال الإمام النووي رحمه الله :-
« أجمع العلماء على وجوب صيانة المصحف واحترامه »
المجموع" للنووي (٢/٨٤)

وقال في "الإقناع" (١/٦٢) " ويكره مد الرجلين إلى جهته (أي: المصحف) وفي معناه: استدباره وتخطيه " انتهى

5⃣. ሌላ በዚህ ዙሪያ የምታውቁት ስህተት ካለ በ @realSanie 1441 ላኩልን ባይሆን በመረጃ የተደገፈ መሆን አለበት ከዚያም ይለቀቃል ጥቅሙ ለሁሉ እንዲሆን ኢንሻአላህ።

#“ሼር” በማድረግ ከአጅሩ ይቋደሱ፡፡

📡 @AAAAAEsu9NIRL6lo5NNODg
🌸 ለእህቴ፦
የሃይድን ደም ከአፍጡር ቦሃላ ያየች ሴት ብይን፡

[ደሙ የመጣው ከመግሪብ በፊት ይሁን ከመግሪብ ቦሃላ አታውቅም ግን ያስታወቃት ከመግሪብ ቦሃላ ነው?]

📩 ጥያቄ፦
አንድ ሴት በረመዷን እየፆመች ሳለ ከእለታት አንድ ቀን መግሪብ ደርሶ ሙኣዚኑ አዝኖ እሷም አፈጠረችና ተነስታ ውዱዕ ልታደርግ ሄደች። በዚህ ሰኣት የለመደችውን የሃይድ ምልክት አየች ፆሟ ትክክል ነው ወይስ አይደለም?

📄 #ምላሽ
ፀሃይ ከገባች ቦሃላ ደሙ ቢገኝ ፆሟ ትክክል ነው። ደሙ መገኘቱን ከመግሪብ ቦሃላ እንጂ ያላወቀች ከሆነ የዚህ ቀኑ ፆሟ ትክክል ነው።
👉ነገር ግን ደሙ ፀሃይ ከመግባቷ በፊት ከሆነ የመጣው ይህንንም እርግጠኛ ሆና ካወቀች የዚህ ቀኑ ፆሟ ትክክል አይሆንም። እንደው ቀዷዕ ከምታወጣቸው ቀኖቿ ጨምራ ልትቆጥረው ይገባታል። ደሟ የመጣው ፀሃይ ከገባች ቦሃላ ከሆነ ፆሟ ትክክል ነው። ደሙ መገኘቱን ከመግሪብ ቦሃላ እንጂ ያላወቀች ከሆነ ።
ነገር ግን ደሙ ፀሃይ ከመግባቷ በፊት እንደመጣ ካወቀችና ፀሃይ ከመግባቷ በፊት ላሷ ደም ከታያት የዚህ በቀኑ ክፍል ደም የታየበት ፆሟ ትክክል አይሆንም። ስለዚህ ከረመዷን ቦሃላ መክፈል አለባት።

👉እንደዚህ አይነቱ ጉዳይ ብዙ ሴቶች ካፍጥር ቦሃላ ለውዱዕ ከሄዱ እንጂ አያውቁም #ኢንሸ_አሏሁ_ተዓላ_ፆማቸው_ትክክል_ነው
📗 الموقع الرسمي للشيخ ابـن بـاز 📗


ቅድሚያ ለሚሰጠው ቅድሚያ እንስጥ።
🌻 • • • ● ❀ 🎀 ❀ ●

👇👇Join ብላችሁ በመግባት ሊንኩን ለወዳጅ ዘመደዎ ሸር ያድረጉ።
👇👇👇
https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAEsu9NIRL6lo5NNODg
በወርሃ ረመዳን በብዛት የሚያጋጥሙ ስህተቶች
1. ከመጠን በላይ መመገብ፡-
ይሄ ችግር በተለይም ረመዳን ላይ በሰፊው ይስተዋላል፡፡
ያለመጠን መመገብ ለብዙ ሸር መንሰኤ ነው፡፡ ሱፍያን
አሥሠውሪ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “አካልህ ጤናማ
እንዲሆን፣ እንቅልፍህ እንዲቀል ከፈለግክ ምግብህን አቅልል፡፡”
ጌታችን እንዲህ ይላል፡-
ﻭَﻛُﻠُﻮﺍ ﻭَﺍﺷْﺮَﺑُﻮﺍ ﻭَﻟَﺎ ﺗُﺴْﺮِﻓُﻮﺍ ۚ ﺇِﻧَّﻪُ ﻟَﺎ ﻳُﺤِﺐُّ ﺍﻟْﻤُﺴْﺮِﻓِﻴﻦَ
“ብሉ ጠጡ፡፡ አታባክኑ፡፡” [አልአዕራፍ፡ 31]
ታላቁ ዓሊም ኢብኑ ቀይም አልጀውዚያ ረሒመሁላህ ከዚች
አንቀፅ ቀጥለው እንዲህ ይላሉ፡- “ባራገፉት ፋንታ ሰውነታቸውን
የሚያቆሙበት ምግብና መጠጥ እንዲያስገቡ ባሮቹን
ጠቆማቸው፡፡ መጠኑም አይነቱም አካላቸው በሚጠቀምበት
መጠን እንዲሆንም አሳሰባቸው፡፡ ይህንን ባለፈ ጊዜ ብክነት
ይሆንበታል፡፡ ሁለቱም ጤናን ጎጅ፣ በሽታን ጎታች ነው፡፡ ማለትም
አለመብላትና አለመጠጣት እንዲሁም በምግብና በመጠጥ
ድንበር ማለፍ፡፡” [አጥጢቡ አንነበዊ፡ 181]

2. በስህተት የበላ ወይም የጠጣ ሰው ፆሙ ተበላሽቷል በሚል
መቀጠል፡፡ በስህተት መመገብም ሆነ መጠጣት በምንም
መልኩ ፆምን አያበላሽም፡፡ ነብዩ ﷺ “አንድ ሰው ረስቶ ከበላና
ከጠጣ ፆሙን ይቀጥል፡፡ ያበላውና ያጠጣው አላህ ነው”
ብለዋል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]

3. የወር አበባ ከመጣ በኋላ ፆምን መቀጠል፡፡ አንዳንድ ሴቶች
ፆም ይዘው ቀኑን ካጋመሱ በኋላ የወር አበባ ሲመጣባቸው
ደክሜበታለሁ ብለው ይቀጥላሉ፡፡ ይሄ አጉል ልፋት ነው፡፡ የወር
አበባ ላይ ያለች ሴት በኢጅማዕ ፆም አይፈቀድላትም፡፡
ይልቁንም በዚያው ልክ ቀዷ ታወጣለች፡፡

4. የተምር ፍሬዎችን በየመስጂዱና ካልሆነ ቦታ መጣል፣

5. ከእኩለ ቀን በኋላ መፋቂያ መጠቀም እንደማይፈቀድ
ማሰብ፡- በርግጥ ይሄ እሳቤ ቀጥተኛ ማስረጃ ባይኖረውም
ከአንዳንድ ዑለማዎች የተወሰደ ነው፡፡ ሆኖም ግን ከዚህ
በተቃራኒ ከብዙ ዑለማዎች ተዘግቧል፡፡ በዚያ ላይ ነብዩ ﷺ
“ከፆመኛ በላጭ ነገሮች ውስጥ አንዱ ሲዋክ ነው” ብለዋል፡፡
ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል፡፡ ሶሐብዩ ዓሚር ኢብኑ ረቢዐ
ረዲየላሁ ዐንሁ “ነብዩን ﷺ ፆመኛ ሆነው እጅግ ብዙ ጊዜ ሲዋክ
ሲጠቀሙ አይቻለሁ” ብለዋል፡፡ ቲርሚዚ ዘግበውታል፡፡

6. የወር አበባ እና የወሊድ ደም ላይ ያሉ ሴቶች “ፆም አልያዝንም” ብለው ከመልካም ስራ መዘናጋታቸው፡- የተከለከሉት
ፆምና ሶላት ነው፡፡ ስለዚህ ዚያራ፣ ሶደቃ፣ ባበወርሃ ረመዳን በብዛት የሚያጋጥሙ ስህተቶች
1. ከመጠን በላይ መመገብ፡-
ይሄ ችግር በተለይም ረመዳን ላይ በሰፊው ይስተዋላል፡፡
ያለመጠን መመገብ ለብዙ ሸር መንሰኤ ነው፡፡ ሱፍያን
አሥሠውሪ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “አካልህ ጤናማ
እንዲሆን፣ እንቅልፍህ እንዲቀል ከፈለግክ ምግብህን አቅልል፡፡”
ጌታችን እንዲህ ይላል፡-
ﻭَﻛُﻠُﻮﺍ ﻭَﺍﺷْﺮَﺑُﻮﺍ ﻭَﻟَﺎ ﺗُﺴْﺮِﻓُﻮﺍ ۚ ﺇِﻧَّﻪُ ﻟَﺎ ﻳُﺤِﺐُّ ﺍﻟْﻤُﺴْﺮِﻓِﻴﻦَ
“ብሉ ጠጡ፡፡ አታባክኑ፡፡” [አልአዕራፍ፡ 31]
ታላቁ ዓሊም ኢብኑ ቀይም አልጀውዚያ ረሒመሁላህ ከዚች
አንቀፅ ቀጥለው እንዲህ ይላሉ፡- “ባራገፉት ፋንታ ሰውነታቸውን
የሚያቆሙበት ምግብና መጠጥ እንዲያስገቡ ባሮቹን
ጠቆማቸው፡፡ መጠኑም አይነቱም አካላቸው በሚጠቀምበት
መጠን እንዲሆንም አሳሰባቸው፡፡ ይህንን ባለፈ ጊዜ ብክነት
ይሆንበታል፡፡ ሁለቱም ጤናን ጎጅ፣ በሽታን ጎታች ነው፡፡ ማለትም
አለመብላትና አለመጠጣት እንዲሁም በምግብና በመጠጥ
ድንበር ማለፍ፡፡” [አጥጢቡ አንነበዊ፡ 181]
2. በስህተት የበላ ወይም የጠጣ ሰው ፆሙ ተበላሽቷል በሚል
መቀጠል፡፡ በስህተት መመገብም ሆነ መጠጣት በምንም
መልኩ ፆምን አያበላሽም፡፡ ነብዩ ﷺ “አንድ ሰው ረስቶ ከበላና
ከጠጣ ፆሙን ይቀጥል፡፡ ያበላውና ያጠጣው አላህ ነው”
ብለዋል፡፡ [ቡኻሪና ሙስሊም]
3. የወር አበባ ከመጣ በኋላ ፆምን መቀጠል፡፡ አንዳንድ ሴቶች
ፆም ይዘው ቀኑን ካጋመሱ በኋላ የወር አበባ ሲመጣባቸው
ደክሜበታለሁ ብለው ይቀጥላሉ፡፡ ይሄ አጉል ልፋት ነው፡፡ የወር
አበባ ላይ ያለች ሴት በኢጅማዕ ፆም አይፈቀድላትም፡፡
ይልቁንም በዚያው ልክ ቀዷ ታወጣለች፡፡
4. የተምር ፍሬዎችን በየመስጂዱና ካልሆነ ቦታ መጣል፣
5. ከእኩለ ቀን በኋላ መፋቂያ መጠቀም እንደማይፈቀድ
ማሰብ፡- በርግጥ ይሄ እሳቤ ቀጥተኛ ማስረጃ ባይኖረውም
ከአንዳንድ ዑለማዎች የተወሰደ ነው፡፡ ሆኖም ግን ከዚህ
በተቃራኒ ከብዙ ዑለማዎች ተዘግቧል፡፡ በዚያ ላይ ነብዩ ﷺ
“ከፆመኛ በላጭ ነገሮች ውስጥ አንዱ ሲዋክ ነው” ብለዋል፡፡
ኢብኑ ማጀህ ዘግበውታል፡፡ ሶሐብዩ ዓሚር ኢብኑ ረቢዐ
ረዲየላሁ ዐንሁ “ነብዩን ﷺ ፆመኛ ሆነው እጅግ ብዙ ጊዜ ሲዋክ
ሲጠቀሙ አይቻለሁ” ብለዋል፡፡ ቲርሚዚ ዘግበውታል፡፡
6. የወር አበባ እና የወሊድ ደም ላይ ያሉ ሴቶች “ፆም
አልያዝንም” ብለው ከመልካም ስራ መዘናጋታቸው፡- የተከለከሉት
ፆምና ሶላት ነው፡፡ ስለዚህ ዚያራ፣ ሶደቃ፣ ባጠቃላይ ሌሎች
ኸይር ስራዎችን በመስራት በረመዳን በተለየ የሚገኘውን ምንዳ
ለማግኘት ሊጥሩ ይገባል፡፡
7. አንዳንድ ሴቶች የወር አበባ ስሜት ስለተሰማቸው ብቻ ደም
ሳያዩ ፆማቸውን ማፍረሳቸው፡- የወር አበባ በታወቀ ጊዜ
የሚመጣ የታወቀ የደም አይነት ነው፡፡ ኢብኑ ጁረይጅ
ረሒመሁላህ ዐጣእን “በወር አበባዋ ቀናት ከደሙ ቀደም ብሎ
የምታየው ዳለቻ ወይም ውሃ ፈሳሽ የወር አበባ ነውን?” ብየ
ጠየቅኳቸው ይላሉ፡፡ እሳቸውም “በጭራሽ! ደሙን እስከምታይ
ድረስ ሶላት እንዳትተው፡፡ ከሶላት ሊያግዳት የሚያስብ ሸይጣን
እንዳይሆን እፈራለሁ፡፡” [ሙሶነፍ ዐብዲርዛቅ፡ 1160]
8. መስጂድ ውስጥ ረጅም የውስጥ ሱሪ ሳይለብሱ መተኛት፡-
ሃፍረተ ገላ ሲጋለጥ ያጋጥማል፡፡ ይሄ በኢዕቲካፍም ጊዜ ሆነ
በሌላ ሰዓት መስጂድ ውስጥ ከሚተኙ ሰዎች ዘንድ በብዛት
የሚያጋጥም ስህተት ነው፡፡ ስለዚህ ይሄ ችግር እንዳያጋጥምና
ሌሎችም እንዳይቸጋገሩ ጥንቃቄ ሊኖረን ይገባል፡፡
9. አንዳንድ የወለዱ ሴቶች ደም ከቆመም በኋላ አርባ ቀን
አልሞላንም ብለው አይፆሙም፡፡ ይሄ ስህተት ነው፡፡ ኢማም
አትቲርሚዚ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “የነብዩ ﷺ ሶሐቦች፣
ታቢዕዮችና ከነሱም በኋላ ያሉ ምሁራን የወሊድ ደም ላይ ያሉ
ሴቶች ለአርባ ቀናት እንደማይሰግዱ ተስማምተዋል፡፡ ከዚህ
በፊት የጠራች ካልሆነች በስተቀር፤ በዚህን ጊዜ (ከአርባ በፊት
ከጠራች) ታጥባ ትሰግዳለች፡፡” [ጃሚዑ አትቲርሚዚ፡ 1/258]
ከተለያዩ ኪታቦች የተሰበሰበ ባጠቃላይ ሌሎች
ኸይር ስራዎችን በመስራት በረመዳን በተለየ የሚገኘውን ምንዳ
ለማግኘት ሊጥሩ ይገባል፡፡

7. አንዳንድ ሴቶች የወር አበባ ስሜት ስለተሰማቸው ብቻ ደም
ሳያዩ ፆማቸውን ማፍረሳቸው፡- የወር አበባ በታወቀ ጊዜ
የሚመጣ የታወቀ የደም አይነት ነው፡፡ ኢብኑ ጁረይጅ
ረሒመሁላህ ዐጣእን “በወር አበባዋ ቀናት ከደሙ ቀደም ብሎ
የምታየው ዳለቻ ወይም ውሃ ፈሳሽ የወር አበባ ነውን?” ብየ
ጠየቅኳቸው ይላሉ፡፡ እሳቸውም “በጭራሽ! ደሙን እስከምታይ
ድረስ ሶላት እንዳትተው፡፡ ከሶላት ሊያግዳት የሚያስብ ሸይጣን
እንዳይሆን እፈራለሁ፡፡” [ሙሶነፍ ዐብዲርዛቅ፡ 1160]

8. መስጂድ ውስጥ ረጅም የውስጥ ሱሪ ሳይለብሱ መተኛት፡-
ሃፍረተ ገላ ሲጋለጥ ያጋጥማል፡፡ ይሄ በኢዕቲካፍም ጊዜ ሆነ
በሌላ ሰዓት መስጂድ ውስጥ ከሚተኙ ሰዎች ዘንድ በብዛት
የሚያጋጥም ስህተት ነው፡፡ ስለዚህ ይሄ ችግር እንዳያጋጥምና
ሌሎችም እንዳይቸጋገሩ ጥንቃቄ ሊኖረን ይገባል፡፡

9. አንዳንድ የወለዱ ሴቶች ደም ከቆመም በኋላ
Channel photo updated
👉🚤ማራኪ የሆነ ገጠመኝ🚤👈


👉🕋 ከጣውላ አምላኪነት ወደ አላህ አምላኪነት

📝 ኢብኑ ቁዳማ አል~መቅደሲ رحمه الله ኪታቡ ተዋቢን በተሰኘው ኪታባቸው ላይ አብዱል ዋሂድ ቢን ዘይድ አስተላልፎታል በተባለው ክስተቱን እንደ ሚከተለው ጠቅሰውታል።

👉🚤 ከዕለታት አንድ ቀን በጀልባ እየተጓዝን ሳለን ጀልባችን ንፋስ አናወጣትና ከሆነች ደሴት ላይ አረፍን። እዛ ቦታ ላይ ግን አንድ ታቦት (ተጠርቦ የተሰራ ነገር) የሚያመልክ ሰው ነበር። ወደሱም ተቀጣጨንና አናገርነው።

👉🌟እኛ => አንተዬ ሆይ ምንድን ነው ምታመልከው
👉እሱ=> ወደ ታቦቱ አሳየን

👉🌟እኛ => የዚህ ዐይነት ነገር ከኛ መሃል ጠርቦ ሚሰራ አለ ይህ እኮ ሚመለክ አምላክ አይደለም አልነው

👉እሱ=> እናንተስ ምንድን ነው ምታመልኩት? አለን
👉🌟እኛ=> አላህ አልነው

👉እሱ=> አላህ ምንድን ነው?አለን
👉🌟እኛ=> ያ አርሹ ከሰማይ በላይ የሆነው፣ በምድር ላይ ተቆጣጣሪ የሆነው፣ በህያውና በሙታን ላይ የሱ ውሳኔ ሚፈፀመው። አልነው

👉እሱ=> ስለሱ እንዴት አወቃችሁ? አለን
👉🌟እኛ=> ይህ ትልቅ አሸናፊና የተከበረ የሆነው ጌታ ወደኛ መልዕክተኛ ላከልንና በሱ አማካኝነት ነገረን። አልነው

👉እሱ=> እሺ መልዕክተኛው ምን አደረገ? አለን
👉🌟እኛ=> መልዕክቱን አደረሰ ከዝያም አላህ ወሰደው(ሞተ) ። አልነው

👉እሱ=> እናንተ ዘንድ ምልክት ትቷልን? አለን
👉🌟እኛ=> አዎን። አልነው

👉እሱ=> ምንድን? አለን
👉🌟እኛ=> ከዛ ከሀያሉ ንጉስ የሆነ መፅሀፍ(ቁርዐን)። አልነው

👉እሱ=> እስኪ የንጉሱ መፅሀፍ አሳዩኝ። ከዚህ ንጉስ የሆነው መፅሀፍ እጅግ ያማረ መሆን አለበት። አለን
👉🌟እኛ=> የያዝነው ቁርዐን ነበር ሰጠነው
👉እሱ=> ይህማ ማንበብ አልችልበትም። አለን

👉🌟 ከዝያም ከቁርዐን የሆነች ሱራ መርጠን ማንበብ ጀመርን እኛ እናነብለታለን እሱ ያለቅሳል በዚህ መልኩ ሱራውን ጨርሰን ቀራንለት።

👉እሱ=> ቁርዐኑ ካዳመጠን በኋላ እንዲህ ዐይነቱ ጌታማ ሊታመፅ አይገባውም። አለና እስልምናን ተቀበለ።
👉🌟ከዝያም የተወሰኑ የቁርዐን አንቀፆችና የእስልምና ድንጋጌዎች አስተምረነው ከኛው ጋ ይዘነው ሄድን።

👉 🌟 የተወሰነ ከተጓዝን በኋላ ሲጨላልምብን ማደሪያችን አመቻችተን አረፍን። የተወሰነ እንዳረፍን ተነሳና

👉እሱ=> እናንተዬ ሆይ ይህ አምላካቹ ለሊቱ ሲጨልምበት ይተኛልን? አለን
👉🌟እኛ=> አይ እሱማ ብርቱና ህያው ነው አይተኛም። አልነው

👉እሱ=> እናንተማ
👉አለንና ትቶን አምልኮውን መፈፀም ጀመረ።
👉🌟 ከጉዞ ጨርሰን ወደ ሀገራችን ስንደርስ ወደ ባልደረቦቼ ሄጄ ይህ ሰውዬ ወደ እስልምና ከገባ ገና ቅርብ ጊዜ ነው። ለሀገሩም እንግዳ ነው ስለዚህ የሆነ ነገር ያስፈልገዋል ብያቸው የተወሰነ ነገር ሰበሰብንለትና ልንሰጠው ስንሄድ

👉እሱ=> ይህ ምንድን ነው? አለን
👉🌟እኛ=> ለጉዳይህ ማስፈፀሚያ መጠቃቀሚያ ይሆንሃል። አልነው

👉እሱ=> በመገረም لا إله إلا الله (ከአላህ በስተቀር በእውነት የሚመለክ አምላክ የለም) አለና
እኔ በዛ የባህር ጠረፍ ላይ ሆኜ ከሱ ውጭ የሆነ ነገር እየተገዛሁኝ ሳለሁ ያልተወኝ አላህ አሁን እሱን ሳውቀው ይተወኛል እንዴ?ብሎ አልቀበል አለ

👉🌟ከተወሰኑ ቀናቶች በኋላ "ያ ሰውዬ እኮ እየሞተ ነው" ተብሎ ተነገረኝ። ከዝያም ተነስቼ ሄድኩኝና ሚፈፀምልህ ጉዳይ አለን? ስለው
"እናንተን ወደ ደሴቴ ያመጣልኝ የሆነው ጉዳዬን ፈፅሞልኛል" አለኝ [አላህን ፈልጎበት ማለት ነው]

👉🌟 አብዱል ዋሂድ የተባለው እዚህ ቦታ ላይ እንቅልፍ አሸንፎኝ ተኛሁኝ አለ ከዝያም በህልሜ ቀብር አየሁኝ ቀብሩ ውስጥ ድንኳን ነገር አለ ድንኳኑ ውስጥ አልጋ አለ እሱም ላይ ኮረዳ (ወጣት ሴት) አለች እንደሷ ዐይነት ቆንጆ አይቼ ማላቅ የሆነች።

👉🌟 እንዲህም አለችኝ "በአላህ እጠይቅሃለው እሱን አፍጥንልኝ በጣም ነው የናፈቀኝ" አለችኝ።
ወድያው ከእንቅልፌ ባነንኩኝ, ሳየው በእርግጥም ዱንያን ተለይቷል (ሙቷል)።

👉🌟 ተነስቼ አጠብኩት፣ ከፈንኩትኝና ቀበርኩት። ለሊቱ በጨለመ ጊዜ (ከተኛሁ በኋላ) በህልሜ በዛች ድንኳን ውስጥ ከልጅቷ ጋ ሆኖ ይህንን የአላህ ንግግር ሲያነብብ አየሁት።

📖 {۝ وَالْمَلٰٓئِكَةُ يَدْخُلُونَ عَلَيْهِم مِّن كُلِّ بَابٍ * سَلٰمٌ عَلَيْكُم بِمَا صَبَرْتُمْ ۚ فَنِعْمَ عُقْبَى الدَّارِ }[ سورة الرعد :٢٣ الى ٢٤ ]

📖 [ወደ ጀነት ሰዎች መላዒካዎች ወደ እነርሱ ከሁሉም በር ይገባሉ* ሰላም በእናንተ ላይ ይሁን። (ይህም) ትዕግስት በማድረጋችሁ ነው። የመጨረሻይቱ ሀገርም ምንኛ ያማረች ናት (ይሏቸዋል)} [አል_ራዕድ:23_24]

[التوابين لابن قدامة: ٣٠٠_٣٠٢]

🤝 አላህ መልካም ለተባለው ሁሉ ይምራን።


🌼͜͡ ͜͜͜͜͡͡͡ ͜͡ ͜͡ ͜͜͜͜͜͜͜͡͡͡͡͡͡͡ ͜͜͜͜͜͡͡͡͡ ͜͡ ͜͡ ͜͜͜͜͡͡͡ ͜͡ ͜͜͜͜͜͡͡͡͡ ͜͡ ͜͡ ͜͜͜͜͜͜͜͡͡͡͡͡͡͡ ͜͜͜͜͜͡͡͡͡ ͜͡ ͜͜͜͜͡͡͡ ͜͡ ͜͜͜͜͜͡͡͡͡ ͜͡ ͜͜͜͜͜͡͡͡͡ ͜͡ ͜͡ ͜͜͜͜͜͜͜͜͜͜͜͡͡͡͡͡͡͡͡͡͡ ͜͡ ͜͡ ͜͜͜͜͜͜͜͡͡͡͡͡͡͡ ͜͡ ͜͡ ͜͜͜͜͜͜͜͡͡͡͡͡͡͡ ͜͡ ͜͜͜͜͜͜͜͡͡͡͡͡͡͡ ͜͜͡͡ ͜͜͜͜͜͜͜͡͡͡͡͡͡͡ ͜͜͜͜͡͡͡ ͜͡ ͜͡ ͜͜͜͜͜͜͜͡͡͡͡͡͡͡ ͜͜͡͡ ͜͜͜͜͜͜͜͡͡͡͡͡͡͡ ͜͜͜͜͜͜͜͜͡͡͡͡͡͡͡͡ ͜͡ ͜͜͜͡͡͡ ͜͜͜͡͡🌼
🖥የ Telegram ግሩፕ ለማግኘት
https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAEsu9NIRL6lo5NNODg
ፆም የሚያበላሹ (የሚያስፈጥሩ) ነገሮች፦
1⃣ኛ - እያወቁ ሳይረሱ መብላትና መጠጣት
2⃣ኛ - ግብረ-ሥጋ ግንኙነት መፈፀም
3⃣ኛ - አውቆ ማስታወክ
4⃣ኛ - ሴቶች የወር አበባና የወሊድ ደም በቀን ከመጣባቸው
5⃣ኛ - የዘር ፈሳሽ አውቆ ማስወጣት
6⃣ኛ - አፈጥራለሁ ብሎ በልብ መወሰን (መነየት)
7⃣ኛ - ከኢስላም መውጣት (መክፈር)
8⃣ኛ - ዋግምት ማድረግ ፡ ናቸው።
“ጥቂት ተጨማሪ ነጥቦች በተራዊህ እና ዊትር ዙሪያ”
================
ከዚህ ቀደም በዚህ ርእስ የለቀቅነው ት/ት ከመኖሩ ጋር ከቀረቡልን ሃሳቦችና ጥያቄዎች አኳያ በመነሳት የሚከተሉትን ነጥቦች ለማከለን ፈለግን።

(1) የለሊት ሰላት በቁጥር የተገደበ አይደለም። ይሁንና መልዕክተኛው እንደተገበሩት 11 ወይም 13 መስገዱ ሸጋ ነው። 23 ረከዓዎች ቢሰገድም ክፋት የለውም። ነገር ግን 11 ረከዓዎችን የሚሰግድ ሰው ቁጥሩ ላይ ብቻ አተኩሮ በአስርና አስራ አምስት ደቂቃዎች ሚጨረስ ከሆነ ተገቢ አይደለም። የረከዓዎቹን ቁጥር ሲያሳንስ በተቻለ አቅም ቂያሙን በማርዘም የሳቸውን ሱና ለመግጠም መሞከሩ የተሻለ ነው።

(2) የለሊትና ዊትር ሰላት ግዜ ከዒሻ ሰላት በኋላ አንስቶ ጎህ እስኪቀድ ነው።

(3) የዊትር ቁኑት ግዴታ ካለመሆኑ ጋር ዱዓውን ያልሸመደደ ከሆነ እስኪሃፍዝ ለግዜው ከወረቀት ወይም የተዘጋጀ ሪሳላ ይዞ ቢጠቀም አይከለከልም። ይሁንና ከዝርዝርና ረጃጅም ዱዓዎች ተቆጥቦ ጥቅላዊና ሁሉን አካታች የተመጠኑት ላይ ማተኮር አለበት። በዚህ ዘመን በየመስጂዶች እንደሚስተዋለው ዱዓን በቁርኣን ቅላፄ ( እየሳቡና እያጠበቁ ) በዜማ መልክ ማለቱ ስህተት ነው።

(3) በህብረት ሚሰግድ ሰው ከኢማሙ ጋር ጀምሮ መጨረሱ ለሊቱን ሙሉ እንደቆመ ስለሚቆጠርለት ትኩረት ሊሰጠው ይገባል።

(5) በአንድ ለሊት ሁለቴ ዊትር ስለሌለ ከለሊቱ መጀመሪያ ወይም መሃከል ላይ ዊትር የሰገደ ሰው አጋጣሚ ከለሊቱ መጨረሻ ተነስቶ ለመስገድ ቢፈልግ ሰላተል ለይል መስገድ ይችላል ነገር ግን ዊትርን አይደግምም።
والله أعلم
ከምፅዋት (ሶደቃ ) ጥቅሞች
-- ከመጥፎ ነገር ይጠብቃል
-- በላእ ይከላከላል
-- ወንጀልን ያብሳል
-- ገንዘብን ( ከጥፋት ) ይጠብቃል
-- ሪዝቅ ያመጣል
-- የልብ ደስታ ይሰጣል
-- በአላህ ላይ መተማመን ያመጣል
-- ሸይጣን ባፍንጫው እንዲደፋ ያደርጋል
-- ነፍስን ያጠራል
-- አላህ ዘንድና ባሮቹ ዘንድ ተወዳጆ ያደርጋል
-- ነውር ይሰትራል
-- እድሜ ይጨምራል
-- የሙእሚኖች ዱዓእ ያስገኛል
-- የቀብር ቅጣት ይከላከላል
-- የቂያማ ቀን ጥላ ይሆናል
-- አማላጅ ይሆናል
-- የዱኛና የአኼራ ጭንቀት ይቀንሳል
ከዒደቱ ሳቢሪን ( 304 ) የተወሰደ
ይህን የተከበረው ወር በዚህ ከአላህ ካዝና ከሚዘርፉ ሰዎች በመሆን የዘላለማዊው ሀገር አካውንታችንን እናደልብ
ከሚጠቀሙት አላህ ያድርገን ::
🕋 እስልምና ማለት ምን ማለት ነው

👉📝 ክፍል አንድ📝👈


📝 እጅግ ሩህሩህ እና አዛኝ በሆነው በአላህ ስም እጀምራለሁ

👉 አላህ በስራችን ላይ እንዲያግዘንና መልካም ለሆነው እንዲመራን እንለምነዋለን!!!

📝 እስልምና ማለት በትርጉም ደረጃ ምን ማለት ነው ካልን ምሁራኖች በዚህ መልኩ ያስቀምጡታል።

📝 " الإسلام هو الاستسلام لله بالتوحيد والانقياد له بالطاعة والبراءة من الشرك وأهله "

📝 {እስልምና ማለት ለአላህ በብቸኝነቱ እጅ እግር መስጠት፣ ለትዕዛዙ መጎተት እና በሱ ላይ ከማጋራትና ከሚያጋሩ ሰዎች መጥራት ማለት ነው"}

👉 አላህ ብቻውን ፈጥሮን ብቻውን እየመገበን ብቻውን እየተንከባከበን፣ ብቻውን እንደ ሚገለንና ብቻውን እንደ ሚቀሰቅሰን ሁሉ እሱን ብቻ እንድናመልክና እንድንገዛው ያዘናል።

👉 እንዲሁም በአጠቃላይ የሰው ልጅም ይሁን አጋንንት የፈጠረበት አላማ ለዚሁ እንደ ሆነ ይገልፃል።

👉💫 አላህ በተከበረው ንግግሩ እንዲህ ይላል:-

📖 {۝ { وَمَا خَلَقْتُ الْجِنَّ وَالْإِنسَ إِلَّا لِيَعْبُدُونِ ۝} [سورة الذاريات : ٥٦ ]

📖 {አጋንንቶችም ይሁን የሰው ልጆች አልፈጠርኳቸውም እኔን (በብቸኝነት) እንዲገዙኝ ቢሆን እንጂ} [አል_ዛሪያት:56]

👉 ይህ ትዕዛዙ ያኖረውና ሚቀበለው ደግሞ እስልምና ሀይማኖት ይዞ ለኖረና ለሞተ ብቻ ነው። ከእስልምና ውጪ ሌላ ሀይማኖት የያዘ ሰውም ለክስረት የተገባ ሰው ይሆናል።
ስለዚህ ሲነግረን በተከበረው ንግግሩ

👉💫 እንዲህ ይላል

📖 {۝ إِنَّ الدِّينَ عِندَ اللَّهِ الْإِسْلٰمُ ۗ} " [سورة آل عمران : ١٩]
📖 {አላህ ዘንድ (ተቀባይነት ያለው) ሀይማኖት እስልምና ነው} [አል_ኢምራን:19]

👉💫 በሌላም አንቀፅ እንዲህ ይላል:-

📖 {۝ وَمَن يَبْتَغِ غَيْرَ الْإِسْلٰمِ دِينًا فَلَن يُقْبَلَ مِنْهُ وَهُوَ فِى الْءَاخِرَةِ مِنَ الْخٰسِرِينَ } [ سورة آل عمران : ٨٥ ]

📖 {ከእስልምና ሌላ ሀይማኖት የሚፈልግ ሰው ከሱ ምንም ተቀባይነት የለውም። እሱም በመጨረሻይቱ ህይወት ከከሳሪዎች ይሆናል} [አል_ኢምራን:85]

👉 ይህ እስልምና ነው አላህ ዘንድ በብቸኝነት ተቀባይነት ያለው። ለዚህም ስለ ሆነ ነው አላህ ወደ ሁሉም ህዝቦች የላካቸው መልዕክተኞቹ በአጠቃላይ ጥሪያቸው ወደ እስልምና (አላህን በብቸኝነት) ወደ ማምለክ ነበር።

👉💫 አላህ በተከበረው ንግግሩ እንዲህ ይላል:-

📖 {۝ { وَلَقَدْ بَعَثْنَا فِى كُلِّ أُمَّةٍ رَّسُولًا أَنِ اعْبُدُوا اللَّهَ وَاجْتَنِبُوا الطّٰغُوت۝ َ ۖ فَمِنْهُم مَّنْ هَدَى اللَّهُ وَمِنْهُم مَّنْ حَقَّتْ عَلَيْهِ الضَّلٰلَةُ ۚ ۝ فَسِيرُوا فِى الْأَرْضِ فَانظُرُوا كَيْفَ كَانَ عٰقِبَةُ الْمُكَذِّبِينَ } [سورة النحل : ٣٦]

📖 {በእርግጥም በሁሉም ህዝቦች ላይ አላህን ተገዙ ጣዖትን ራቁ (የሚሉ) መልዕክተኞች ልከናል። ከእነርሱ አላህ የመራው አለ ከእነርሱም ጥመት የተረጋገጠበት አለ። በምድር ላይ ሂዱ የአስተባባዮች መጨረሻ እንዴት እንደ ነበር ተመልከቱ} [አል_ነኽል:36]

👉 አላህ መልዕክተኞቹ በአጠቃላይ የላካቸው ወደ እስልምና እንዲጣሩ ነበር። ከጣዖት (ከአላህ ውጪ ከሚመለክ ነገርም) ያስጠነቅቁ ነበር።

👉 እነዚህ መልዕክተኞች ያስተባበሉት ግን አላህ በተለያየ ጊዜና ቦታ የተለያየ በሆነ አሳማሚ ቅጣት ቀጥቷቸዋል። የተለያዩ የሆኑ አደጋዎች እያደረሰም አጥፍቷቸዋል። እኛም እነርሱ እንደ ጠፉት እንዳንጠፋ "ሂዱና እንዴት እንደ ጠፉ ተመልከቱ" ይለናል።

👉🇸🇦 እኛም ይህንን እስልምና ያልተረዱና ያልተቀበሉ ወገኖቻችን ከጥፋትና ከክስረት ይድኑ ዘንድ ወደ ስኬታማው እስልምና እንጠራቸዋለን።

. ክፍል ሁለት ይቀጥላል።
┈┈┈┈•••✿❒🌹❒✿•••┈┈┈┈


👌ግሩፑን join በማድረግ ለሁሉም ወዳጅ ዘመድ ያስተላልፉ

🖥የ Telegram ግሩፕ ለማግኘት
👇🏾👇🏾👇🏾
https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAEsu9NIRL6lo5NNODg
⚠️የካፊሮች ጥላቻ በሙስሊሞች ላይ❗️


وَلَن تَرْضَىٰ عَنكَ ٱلْيَهُودُ وَلَا ٱلنَّصَٰرَىٰ حَتَّىٰ تَتَّبِعَ مِلَّتَهُمْ ۗ قُلْ إِنَّ هُدَى ٱللَّهِ هُوَ ٱلْهُدَىٰ ۗ وَلَئِنِ ٱتَّبَعْتَ أَهْوَآءَهُم بَعْدَ ٱلَّذِى جَآءَكَ مِنَ ٱلْعِلْمِ ۙ مَا لَكَ مِنَ ٱللَّهِ مِن وَلِىٍّۢ وَلَا نَصِيرٍ

"አይሁዶችና ክርስቲያኖችም ሃይማኖታቸውን እስከምትከተል ድረስ ካንተ ፈጽሞ አይወዱም፡፡ «የአላህ መምራት (ትክክለኛው) መምራት እርሱ ብቻ ነው» በላቸው፡፡ ከዚያም እውቀቱ ከመጣልህ በኋላ ዝንባሌያቸውን ብትከተል ለአንተ ከአላህ (የሚከለክልልህ) ዘመድና ረዳት ምንም የለህም፡፡"


👉ታሪኩ ላይ መስቀላውያንና ታታራውያን ሙስሊሞችን ለመውጋት እንዳበሩ አይተናል።
ይልቁንም በኖርማል አእምሯችን ምናስበው የነበረው መስቀላውያን ከሙስሊሞች ጋር ሆነው የጋራ ጠላታቸው የነበሩትን ታታራውያን ሊወጉ
የሚችሉ ነበር የሚመስለው ግን ኢስላምን ለማጥቃት ጠላትና ጠላት እራሱ ሲወዳጅ አይተናል‼️


🕋💒ሁሌም ቢሆን ድል የኢስላም ነው!!!


3፥151 በእነዚያ “በካዱት ሰዎች” ልቦች ዉስጥ አላህ በእርሱ አስረጅ ያላወረደበትን ነገር በአላህ “በማጋራታቸዉ” ምክንያት “ፍርሃትን” الرُّعْبَ እንጥላለን መኖሪያቸዉም እሳት ናት፤ “የበዳዮችም” መኖርያ ምን ትከፋ!

سَنُلْقِي فِي قُلُوبِ الَّذِينَ كَفَرُوا الرُّعْبَ بِمَا أَشْرَكُوا بِاللَّهِ مَا لَمْ يُنَزِّلْ بِهِ سُلْطَانًا وَمَأْوَاهُمُ النَّارُ وَبِئْسَ مَثْوَى الظَّالِمِينَ ” ፤

አላህ ለመላእክቱ በእነዚያ በካዱት ልቦች ውስጥ ፍርሃትን በእርግጥ እጥላለሁ ብሏል፦

8፥12 ጌታህ ወደ መላእክቱ፦ እኔ ከናንተ ጋር ነኝና፣ እነዚያን ያመኑትን አጽናኑ፤ በነዚያ በካዱት ልቦች ውስጥ ፍርሃትን በእርግጥ እጥላለሁ፤ ከአንገቶችም በላይ ምቱ፤ ከነሱም የቅርንጫፎችን መለያልይ ሁሉ ምቱ፤ ሲል ያወረደውን አስታውስ

إِذْ يُوحِى رَبُّكَ إِلَى ٱلْمَلَٰٓئِكَةِ أَنِّى مَعَكُمْ فَثَبِّتُوا۟ ٱلَّذِينَ ءَامَنُوا۟ ۚ سَأُلْقِى فِى قُلُوبِ ٱلَّذِينَ كَفَرُوا۟ ٱلرُّعْبَ فَٱضْرِبُوا۟ فَوْقَ ٱلْأَعْنَاقِ وَٱضْرِبُوا۟ مِنْهُمْ كُلَّ بَنَانٍۢ ።


=<({አል-ቁርአን 3:139})>=

{139} ደካሞች አትሁኑ፤ አትዘኑም። በእርግጥ እውነተኛ አማኞች ከሆናችሁ የበላዮች(አሸናፊዎች) ትሆናላችሁ።

ሱረህ አስሷፋት

37:173 - ሰራዊቶቻችንም በእርግጥ አሸናፊዎቹ እነርሱ ናቸው፡፡


ነብያችን”ﷺ” ሐዲስ ደግሞ ጎራ ብለን ይህንን
እናብራራው

ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 56 , ሐዲስ 186:
አቢ ሁረይራህ”ረ.ዐ.” እንደነገረን የአላህ መልክተኛ”ﷺ” እንዲህ አሉ፡- “ጠቅላይ ንግግርን በመስጠት ተላክሁኝ፤ በጠላት ልብ ውስጥም “ፍርሀት” بِالرُّعْبِ እንዲጣል በመደረግ ተረዳኹኝ፤ ተኝቼ ሳለ የምድር ካዝናዎችም በእጄ ላይ ተደረጉልኝ”

عَنِ ابْنِ شِهَابٍ، عَنْ سَعِيدِ بْنِ الْمُسَيَّبِ، عَنْ أَبِي هُرَيْرَةَ ـ رضى الله عنه ـ أَنَّ رَسُولَ اللَّهِ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ بُعِثْتُ بِجَوَامِعِ الْكَلِمِ، وَنُصِرْتُ بِالرُّعْبِ، فَبَيْنَا أَنَا نَائِمٌ أُتِيتُ بِمَفَاتِيحِ خَزَائِنِ الأَرْضِ، فَوُضِعَتْ فِي يَدِي ‏”‌‏


ኢማም ቡኻሪይ መጽሐፍ 7 , ሐዲስ 2:
ጃቢር ኢብኑ ዐብዲላህ”ረ.ዐ.” እንዳስተላለፈው ነብዩም”ﷺ” እንዲህ አሉ፡- “ከኔ በፊት ለነበሩት ነቢያት ያልተሰጠ አምስት ነገር ተሰጠኝ፦ የወር መንገድ ያህል ሲቀረው በጠላት ልብ ውስጥ “ፍርሀት” بِالرُّعْبِ እንዲገባ በማድረግ ተረዳሁ፣ ምድር በጠቅላላ ጡሀራና የመስገጃ ክልል ተደረገልኝ፣ ከኡመቶቼ ማንኛውም ሙስሊም ሶላት ወቅቱ በገባበት ማንኛውም ቦታ ላይ ሁኖ ይስገድ፣
የምርኮ ገንዘብ ከዚህ በፊት ለነበሩት ነቢያት ያልተፈቀደ ሲሆን ለኔ ሐላል ተደረገልኝ፣ የአማላጅነት ፈቃድ ተሰጠኝ፣
ከኔ በፊት የነበሩት ነቢያት ለህዝቦቻቸው ሲላኩ፡ እኔ ግን ለሰዎች በመላ ተላክሁኝ”

قَالَ أَخْبَرَنَا جَابِرُ بْنُ عَبْدِ اللَّهِ، أَنَّ النَّبِيَّ صلى الله عليه وسلم قَالَ ‏ “‏ أُعْطِيتُ خَمْسًا لَمْ يُعْطَهُنَّ أَحَدٌ قَبْلِي نُصِرْتُ بِالرُّعْبِ مَسِيرَةَ شَهْرٍ، وَجُعِلَتْ لِيَ الأَرْضُ مَسْجِدًا وَطَهُورًا، فَأَيُّمَا رَجُلٍ مِنْ أُمَّتِي أَدْرَكَتْهُ الصَّلاَةُ فَلْيُصَلِّ، وَأُحِلَّتْ لِيَ الْمَغَانِمُ وَلَمْ تَحِلَّ لأَحَدٍ قَبْلِي، وَأُعْطِيتُ الشَّفَاعَةَ، وَكَانَ النَّبِيُّ يُبْعَثُ إِلَى قَوْمِهِ خَاصَّةً، وَبُعِثْتُ إِلَى النَّاسِ عَامَّةً


ይህንንም በታሪኩ የመጨረሻ ድል አድራጊ የነበሩት ሙስሊሞች እንደነበሩ አይተናል።ለዱንያ ተራ ብልጭልጭ መኖር ትተን የአላህን ውዴታ በመፈለግ እዚህ ምድር ላይ እስከኖርን ድረስ አሸናፊነቱ የኛ እንደሆነ እንረዳለን።



👉የኛ ችግራችን ይህን የአላህ ንግግር አለመተግበራችን ነው

8:46 - አላህንና መልክተኛውንም ታዘዙ፡፡ አትጨቃጨቁም፡፡ ትፈራላችሁና ኃይላችሁም ትኼዳለችና፡፡ ታገሱም፤ አላህ ከትዕግስተኞች ጋር ነውና፡፡

🔵መፍትሄውን
አላህﷻ ሲነግረን:-

فَإِن تَنَٰزَعْتُمْ فِى شَىْءٍۢ فَرُدُّوهُ إِلَى ٱللَّهِ وَٱلرَّسُولِ إِن كُنتُمْ تُؤْمِنُونَ بِٱللَّهِ وَٱلْيَوْمِ ٱلْـَٔاخِرِ ۚ ذَٰلِكَ خَيْرٌۭ وَأَحْسَنُ تَأْوِيلًا

"በማንኛውም ነገር ብትከራከሩ በአላህና በመጨረሻው ቀን የምታምኑ ብትኾኑ (የተከራከራችሁበትን ነገር) ወደ አላህና ወደ መልክተኛው መልሱት፡፡ ይህ የተሻለ መጨረሻውም ያማረ ነው፡፡" ኒሳእ 59


👉ኢብኑ ከሲር ወደ አላህና መልዕክተኛው መልሱት የሚለውን ወደ ቁርዓንና ሃዲስ መልሱት ማለት ነው ሲሉ ፈስረውታል።ስለዚህ ማንኛውም አይነት ሚያከራክር ነገር ሲገጥመን ወደ ቁርዓንና ሃዲስ መመለስ ይጠበቅብናል!
Best:
አንተ መልካም ፈላጊ ሆይ ና ፊትህን ወደ አሏህ አዙር በርታ።

አንተ ክፉ ፈላጊ ሆይ ከተግባርህ ተቆጠብ አቁም።

የጀነት በሮች ተከፍቷል ፣የጀሀነም በሮች ተዘግተዋል፣ሸይጧኖች ታስረዋል፣በዚህ ወር ውስጥ አንዲት ሌሊት አለች ከሌላ ጊዜ አንድ ሺህ ወራቶች የምትበልጥ፣አሏህ በየ ሌሊቱ ሰዎች ከእሳት ነፃ የሚያወጣበት ወር ነው።

ወንጀልህ የሚማርበት፣ምንዳህ አሏህ ራሱ የሚይዝልህ፣የአፍ ጠረንህ ሚስክ ሚስክ የሚሸትበት፣ዑምራህ እንደ ሀጅ የሚቆጠርልህ ።

ያሏህ ምንኛ መልካምዋ የበዛ ወር ናት!

እንግዲያውስ ሜዳውም ይኸው ፈረሱም ይኸው።

አሏህ ከሚጠቀሙበት ያድርገን።



///////////////
============================
Https/www.tg-me.com/AAAAAEu9NIRL6lo5NNODg
2024/10/01 10:16:18
Back to Top
HTML Embed Code: